አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የድሮን ጥቃት‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ “በመካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም በድሮን ጥቃት የመነኮሳት ህይወት አለፈ”‼️

በዛሬው ዕለት ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም በምዕራብ ወሎ በመካነ ሰላም በዓባይ ወንዝ ዳርቻ በሚገኘው ዓባይ ገዳመ አስቀጤስ የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ምክንያት በገዳሙ ውስጥ የሚኖሩ 2 ሴቶች ወዲያው ህይወታቸው ማለፉን እና ሌሎች መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው የፋኖ ሀይሎች ከትመዋል በሚል ነው ተብሏል።
ሰላም ለሀገራችን🕊🕊

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢57💔2815😱3
የዝናብ ሁኔታ‼️
በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።
በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ።

ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ መሰረት፣ ከሐምሌ 14 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት አስር ቀናት ውስጥ የዝናብ ሁኔታን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች የበለጠ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አሰታወቋል።

በዚህም መሰረት በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቷ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ ሥርጭት መጠን  ይኖራቸዋል።

በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል።

በተጨማሪም በመካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቷ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ ብሏል።

በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች  ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ነው ኢንስቲትዩቱ የጠቆመው።

በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቷ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል።

በተጨማሪም በኤሊ ዳር፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ ቡሬ፣ አሳይታ፣ ሁንዱፎ፣ ገዋኔ፣ ሚሌ፣ ዳሊፋጊ፣ አይሻ፣ ጉሊና፣ አዋሽ አርባ፣ ባቲ፣ ዶሎ አዶ፣ ዳዋ፣ አሶሶ፣ ጎዴ፣ ቋራ፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ ጭፍራ፣ ላሬ፣ መተሀራ እና፣ ላሬ፣ ፉኙዶ አካባቢዎች  ከሚኖረው የቀን ከፍተኛ የፀሀይ ሀይል ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሙቀት ይኖራቸዋል።

ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ቀናት የሚኖረውን መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም እና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክር ሀሳብን ከወዲሁ መተግበር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍7
ብሄራዊ ባንክ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 500 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያካሂድ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ2019 ዓ.ም የፋይናንስ ዓመት የመጀመሪያው ሩብ በንግድ ባንኮች በኩል 500 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ወደ ገበያው ለማስገባት አቅዷል።

ማዕከላዊ ባንኩ በነሐሴ እና መስከረም ወራት አራት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎችን እንደሚያካሂድ ገልጿል።

በእያንዳንዱ ጨረታም 125 ሚሊዮን ዶላር ለንግድ ባንኮች እንደሚቀርብ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍3
በትግራይ በረዶ አዘል ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ቀጠፈ

በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ተቃራኒ የአየር ሁኔታዎች በሕዝብና በግብርና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆናቸው ተገልጿል።

በአንድ በኩል በረዶ አዘል ከባድ ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ በአዝርእትና በመስኖ ላይም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ 176 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት እስካሁን የክረምት ዝናብ እንዳላገኙ ተገልጿል።

በማዕከላዊ ዞን ወረዳ ቀይሕ ተኽሊ ዶክተር አታኽልቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፣ ለሁለት ሰዓታት ያለማቋረጥ የዘነበው በረዶ አዘል ከባድ ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ከመቅጠፉ በተጨማሪ በአዝርእትና በመስኖ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

በተመሳሳይ በዞኑ ወረዳ አሕፈሮም ሴሮ ቀበሌ የዘነበው ብርቱ ዝናብም በአዝርእትና በአትክልት ላይ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

በሌላ በኩል የትግራይ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ጥበቃ ቢሮ ሐምሌ 13፣ 2018 ዓ.ም. ባወጣው መረጃ፣ በክልሉ ከሚገኙ 600 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት መካከል 176 በሚሆኑት እስካሁን የክረምት ዝናብ እንዳልዘነበ አስታውቋል።

ይህ ሁኔታ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ከመጠን ያለፈ ዝናብ ጉዳት እያደረሰ ሲሆን፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ የዝናብ እጥረት በእርሻ ሥራና በምርት ላይ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ያሳያል።#ቲክቫህ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😢9👍2
መረጃ‼️

59 በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ክፍል ቤት ውስጥ እንደሚኖር የፌደራል ስታትስቲክስ አገልግሎት ከአውሮፓዊያኑ 2024 እስከ 2025 ያካሄደው ጥናት አመለከተ።

የመኖሪያ ቤቶች መጨናነቅ በተለይ በከተሞች አካባቢ እንዲባባስ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ፣ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ያልተቋረጠ ፍልሠት መኾኑን ዋዜማ ከጥናቱ ላይ ተመልክታለች።

በተጠቀሠው ጊዜ ውስጥ በጥናቱ 31 በመቶ የሴቶች እና 24 በመቶ የወንዶች ፍልሠት ተመዝግቧል።

የተሻለ የሥራ ዕድል፣ ትምህርትና የመሠረተ ልማት አቅርቦትን ፍለጋ የሚደረገው ፍልሠት፣ በከተሞች ላይ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠሩ በባለ ሁለት ክፍል ቤቶች የሚኖሩ ዜጎች ድርሻ 31 በመቶ መድረሱን ሪፖርቱ ያትቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢207👍3🤣2
አብይ አህመድ ስለ ህወሃት‼️👇
ህወሓት አዲስ ነገር ለመስማት እና ለማየት ፍላጎት የለውም'-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)‼️

ህወሃት ወደ መሬት መውረድ በማይችል ያረጀ አስተሳሰብና ሀሳብ የታጠረ ድርጅት ነው።

ይህ ብቻ ሳይሆን ራሱን ወደ አደጋ የሚከቱ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፣አሁንም እየወሰደ ይገኛል።

ይህ ደግሞ ጤና ያለው ድርጅት ባህሪ አይደለም።

አዲስ ነገር ለመስማት ጆሮ የለውም፣አዲስ ነገር ለማየት አይን የለውም፣ፍላጎትም የለውም።

አዲስ ነገር ለመስማት ዝግጁ ያልሆነ ድርጅት ለህዝቡ ጥሩ ስራ ይሰራል ተብሎ አይጠበቅም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ሐምሌ 15 ስለህወሓት በትግርኛ ከተናገሩት ተተርጉሞ የተወሰደ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25🤣21🤪4👍3
#የውቅያኖስ ወለል ምስጢር፦ የዓለምን ኢንተርኔት የሚያንቀሳቅሱት የባህር ስር መስመሮች
ብዙዎቻችን በየቀኑ በስልካችን የምንጠቀመው ኢንተርኔት፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ዓለም አቀፍ የመረጃ ፍሰት በሳተላይት በኩል በአየር ላይ የሚጓዝ ቢመስለንም፣ እውነታው ግን ከዚህ እጅግ የራቀ ነው።

የዓለማችን 99 በመቶ የሚያህለው የኢንተርኔት ዳታ የሚጓዘው በጨለማውና በጥቁሩ የውቅያኖሶች ወለል ላይ በተዘረጉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች በኩል ነው። በዓለም ዙሪያ በውቅያኖሶች ስር የተዘረጉት እነዚህ ከ550 በላይ ንቁ ካብሎች ከ1.4 ሚሊዮን ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን፣ በሴኮንድ በመቶ ቴራባይት የሚቆጥር ዳታ የሚያስተላልፉት እነዚህ መስመሮች እንደተጠበቀው ትልቅ ሳይሆኑ የመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያ ወይም የጓሮ ቧንቧ ያህል ውፍረት ብቻ ያላቸው ናቸው።

በኬብሉ መሃል የሚገኙት የመረጃ ማስተላለፊያ የብርጭቆ ጫፎች ወይም ቀጫጭን የብርጭቆ ገመዶች የሰው ፀጉር ያህል ቀጫጭን ሲሆኑ፣ መረጃን በብርሃን ፍጥነት ያጓጉዛሉ።እነዚህ መስመሮች ለአደጋ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ በመሆኑ በየዓመቱ በአማካይ ከ100 በላይ የመቆረጥ አደጋዎች ያጋጥሟቸዋል ተብሏል።

የመርከብ መልሕቆች መሬት ሲቧጥጡ፣ የባህር ስር የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ወይም አልፎ አልፎ የሻርክ አሳዎች ሲነክሷቸው መስመሮቹ የሚበጠሱ ሲሆን፣ አንድ የባህር ስር ኬብል ከተቋረጠ የሙሉ ሀገር ወይም ቀጠና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ ወይም ሊዘገይ ይችላል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት እንደ Google፣ Meta፣ Microsoft እና Amazon ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የራሳቸውን የባህር ስር ኬብሎች በመዘርጋት የዓለምን የመረጃ መረብ በባለቤትነት እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22👍5
በወላይታ ሶዶ ከተማ ፌስታል ሲጠቀሙ በተገኙ 130 አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ
 
በወላይታ ሶዶ ከተማ በህግ የተከለከለውን ፌስታል ሲጠቀሙ በተገኙ 130 ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን የከተማው የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ጽ/ቤት አስታውቋል።እርምጃው በአብዛኛው በሱቆችና በንግድ ተቋማት ላይ የተወሰደ ሲሆን ከየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው ክትትል የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።
 
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ ለማ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን በመተላለፍ ፌስታል በመያዝ እና ለንግድ አገልግሎት ጥቅም ላይ ሲያውሉ በተገኙ 130 አካላት ላይ በህጉ መሠረት እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።በቅርቡ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል አንድ ነጋዴ 17 ኩንታል ማዳበሪያ ይዞ በመገኘቱ የተወረሰበት ሲሆን በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ጨምር እንዲቀጣ ተደርጓል።
 
በመሆኑም ግለሰቦችና ተቋማት ፌስታል መጠቀም በህግ የተከለከለ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ህጉን ሊያከብሩ ይገባል ሲሉ አቶ ጴጥሮስ ለማ  ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በአዋጁ መሰረት ፌስታል ይዞ የተገኘ ግለሰብ  በ2 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል።እንዲሁም በተቋም ደረጃ ፌስታል ያከማቸ፣ የሸጠ ወይም ለንግድ ዓላማ እንደ እቃ መያዣ ያቀረበ ተቋም እስከ 200 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ባለንብረቶችም  እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ ተጠቅሷል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤪12👍2🤯1
ሰበር መረጃ‼️
የኢትዮጵያን መንግስት ለመጣል ያለመ ስብሰባ በኤርትራ ድንበር ተደረገ፣ስብሰባውን የመሩት አቶ አማኑኤል አሰፋ ናቸው።
ሕወሓት የብልጽግናን መንግስት አስወግዳለሁ እያለ ነው፡፡ ቡድኑ ካለፈው እሁድ አንስቶ 'ህልውናችን የሚረጋገጠው በብልጽግና መቃብር ላይ ነው' በሚል መሪቃል ስብሰባዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ የሕወሓት አመራሮች ‹‹ብልጽግናን ከስልጣን ማስወገድ አለብን›› በማለት በግላጭ እየተናገሩ ነው፡፡
በሚዲያዎቻቸውም የፌደራል መንግስቱን 'ጄንኖሳይዳዊ አገዛዝ' የሚል ስያሜ ሰጥተው በትግራይ ቴሌቪዥን ጭምር ዜና መስራት ጀምረዋል። የፌደራል መንግሥቱ ለህወሓት የጦርነት ጉሰማ በቀጥታ የሰጠው ምላሽ የለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍48🤪179👌4🥰2🕊2👀1
ጄነራል ታደሰ ወረደ ወዴት ተሰወሩ
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በመቀሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መሰወራቸው ተሰማ። እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ መኖሪያ ቤታቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቅና በጥበቃ ተሽከርካሪዎች የተከበበ የነበረ ቢሆንም፣ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ ግን አብረዋቸው የነበሩ ጥበቃዎችና ሰራተኞች ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል።

ጄነራሉ ከጥቂት ቀናት በፊት ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር እንዳይገናኙ በትግራይ ጸጥታ ቢሮ ተከልክለው እንደነበርና ቤተሰቦቻቸውም ስለ ደህንነታቸው ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ይታወቃል።

ጄነራል ታደሰ ወረደ በፌደራል መንግሥት ዳግም በተሾሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሕወሓት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የሚታወስ ነው። ከኃላፊነታቸው ከመነሳታቸው በፊትም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ለመገልበጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ክልሉን ወደ አዲስ ጦርነት እንደሚያስገባ አስጠንቅቀው ነበር።

በአሁኑ ወቅት በሕወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው የፖለቲካ ውጥረት በጨመረበት ሁኔታ፣ የጄነራሉ ከአካባቢው መሰወር በትግራይ ክልል አዲስ የጸጥታ ስጋት ደቅኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3😢1🎉1🤪1
ለምክክር ጉባዔ መጥታ ወንድ ልጅ የተገላገለችው እናት የልጇን ሥም "ኮሚሽን" አለችዉ

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወክላ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።

ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የነበረች የጋምቤላ ክልል ተወካይዋ ወ/ሮ ክርኑዶ ኡጁሉ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላ ስሙም "ምክክር" መባሉ የሚታወስ ነው።

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ የመጣችው ሌላኛዋ የምክክሩ ተሳታፊ ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ በተመሳሳይ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን፥ ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።

የመውለጃ ጊዜዬ እየደረሰ መሆኑን ባውቅም ለኢትዮጵያዊያን አብሮነትና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ በሚመከርበት በዚህ ጉባኤ መሳተፍ አለብኝ በሚል አቋም ተገኝቻለሁ ብላለች፡፡

በጉባኤው አጀንዳዎች ላይ ለሀገራችን ይበጃል የምትለውን ሀሳብ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ የቆየች ሲሆን፥ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ልጇን በመገላገሏ መደሰቷን ገልጻለች።

ዘገባዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዲያ ነዉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣7011😡6👍3
በሩሲያ አንድ የቧንቧ ሥራ ኩባንያ የመጸዳጃ ቤት ዉሃ የመጠጣት ውድድር ማዘጋጀቱ ዉዝግብ አስነሳ
 
በሩሲያ ስታቭሮፖል የሚገኝ አንድ የቧንቧ ሥራ ኩባንያ፣ በቅርቡ "Game of Thrones" በሚል ያልተለመደ ውድድር ምክንያት በኢንተርኔት ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊዎች አዲስ ከሆኑ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫዎች ውስጥ፣ ትላልቅ የመምጠጫ ቱቦዎችን በመጠቀም "አልኮል ያልያዘ ጋዝ ያለው መጠጥ" እንዲጠጡ ይጠበቅባቸው ነበር፤ መጠጡን በፍጥነት የጨረሰውም አሸናፊ ተብሎ ተለይቷል።
 
በስታቭሮፖል ከተማ በሚገኝ የ"ዶሚክስ" መደብር ውስጥ የተካሄደው ይህ ያልተለመደ ውድድር፣ በርካታ ተሳታፊዎች የ100,000 ሩብል (1,276 የአሜሪካ ዶላር) ሽልማት ለማግኘት ሲሉ ከመጸዳጃ ቤት ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ በፍጥነት እንዲጠጡ የሚያስገድድ ነበር። ተወዳዳሪዎቹ በሰባት ሰዎች ቡድን የተከፋፈሉ ሲሆን፣ ፈጣኑ ጠጪ ወደ ሁለተኛው ዙር ያልፍ ነበር።
 
በውድድሩ ሁለተኛ ምዕራፍ፣ ከቀዳሚው ዙር ያለፉት ሰባቱ አሸናፊዎች በተዘጋ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ላይ በተቻለ መጠን ረጅም ጊዜ መቀመጥ ነበረባቸው፤ በመጨረሻም መቀመጥ የቻለው ሰው የዚህ ያልተለመደ ዉድድር አሸናፊ ተብሎ ታዉጇል።

በቤዛዊት አራጌ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😡4👍2🥱2
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ33.2 በመቶ ዕድገት ያሳየ ነው።መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ለተመዘገበው ዕድገት እንደ አንድ ምክንያት የጠቀሰው የገቢ ምንጮቹ መስፋፋትን ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 16፤ 2018 በሰጡት መግለጫ፤ ከዚህ ቀደም የኩባንያው የገቢ ምንጮች በሞባይል ድምጽ፣ በዳታ እና በኔትወርክ ትስስር (interconnect) ላይ ብቻ የተገደቡ እንደነበሩ አስታውሰዋል።

ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ላገኘው ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ ካበረከቱ የአገልግሎት ዓይነቶች መካከል የዳታ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ይጠቀሳሉ።ሁለቱ አገልግሎቶች ከተቋሙ ገቢ ያላቸው ድርሻ 31.1 በመቶ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ እንዳገኘው የገለጸው ያልተጣራ ትርፍም፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ51.9 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት ተመዝግቦበታል።

ኩባንያው በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበው ያልተጣራ ትርፍ 38.7 ቢሊዮን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢176👍3🥱2🤪2
በኢትዮጵያ ብቁ የሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር ከ500 አይበልጥም ተባለ !

በኢትዮጵያ የሰለጠኑ እና  ብቁ የሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር   እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም የተመሰከረላቸውን የሂሳብ ባሙያዎች  እጥረት ለመቅረፍ  የሚያስችል ስልጠና ኤችኤስቲ ስኪል አካዳሚ  መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

በተቋሙ በትምህርት እና ስልጠና ላይ ስትራቴጂክ ቢዝነስ ዩኒት ስኪል አካዳሚ ዳይሬክተር የቦርድ አባል እና የሪስክ እና ኦዲቲ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጎበዜ ደሳለኝ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በኢትዮጵያ  በሂሳብ አያያዝ ቴክኒካል ብቃት ብቁ የሆኑ የሒሳብ ባለሙያዎች  ቁጥር ከ500 አይበልጥም።ከዚህ ቀደም ስልጠናውን ለማግኘት ወደ ውጪ ሀገራት  መሄድ አስገዳጅ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጎበዜ ይህንን የሚያስቀር እና ከከፍተኛ ወጪ የሚያድን ስልጠና በሀገር  ውስጥ  በድረገጽ አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል

ከ12ኛ ክፍል ጀምሮ በተለያዩ የስራ ሁኔታዎችም ሆነ የትምህርት ዘርፍ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ቦታ ላይ ሆኖ ስልጠናውን መውሰድ ይችላል። በማኔጅመንት፣ በኦዲት ፋይናንስ ታክስ፣ እንዲሁም በሌሎች የሙያ ዘርፎች በ12 የትምህርት አይነቶች ስልጠናው የሚሰጥ ሲሆን ትምህርቱን ለመማር ከ12 እስከ 18  ወራት ይወስዳል

ለአንድ የትምህርት ዘርፍ የ3ሺህ ብር  የገንዘብ ክፍያ ብቻ  የሚጠየቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ጎበዜ አስራ አንድ ድርጅቶች ስልጠናውን ይሰጣሉ ሲሉ አክለዋልከእነዚህም መካከል ሶስቱ የግል ድርጅቶች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን  ጨምሮ ስምንቱ  ደግሞ የመንግስት ድርጅቶች ናቸው።የዩኒቨርሲቲ ተቋማት በቋሚነት ከሚሰጡት ትምህርት በተለየ መልኩ  ስልጠናውን በተግባር እንደሚሰጡ ተነግሯል

@Addis_Reporter
9👍3🎉1💊1
የአፍሪካ የሰዎችና ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተላለፉ ፍርዶችና የሞት ቅጣቶች እንደገና እንዲታዩ "ሁሉንም መንገዶች" እንዲጠቀምና የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን ኢትዮጵያዊያን ደኅንነት ለማስከበር አስፈላጊ "የዲፕሎማቲክ" እና "የቆንስላ" ርምጃዎችን እንዲወስድ ጠየቀ።

ኮሚሽኑ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ላይ የተጣለው የሞት ቅጣት በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያዊያኑ "የሕግ ውክልና" እና የፍርድ ቤት "የትርጉም አገልግሎት" እንዲያገኙና ከቤተሰባቸው ጋር እንዲገናኙ ጥረት እንዲያደርግ፤ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሠተኞችን መብት "በሁለትዮሽ ግንኙነቶች" እና በጠንካራ "የቆንስላ ድጋፎች" እንዲያስከብርም ኮሚሽኑ ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍7