የነዳጅ ቦቴ ባለንብረቶች ከገበያ ልንወጣ እንችላለን ሲሉ ስጋታቸውን ገለጹ
በሀገሪቱ እየታየ ያለው የመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ መናር እና የታሪፍ ማሻሻያ አለመደረግ አክሳሪ እንደሆነባቸው የገለጹት የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች፣ ችግሩ ባልተፈታበት ሁኔታ ስራቸውን ማስቀጠል አስቸጋሪ እንደሆነባቸው በመግለጽ ከገበያው የመወጣት ስጋት እንደደቀነባቸው አስታወቁ።
የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር የነዳጅ ፍላጎት እድገትን እና የወጡ ወጪዎችን ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ተደጋጋሚ ጥናቶችን ማቅረቡን ያስታወሰ ቢሆንም፣ በመንግስት በኩል ግን እስካሁን አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን ገልጿል።
የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ ፀጋ አስማረ እንደገለጹት፤ ጥናቱ ዝም ብሎ የቀረበ ሳይሆን ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እንዲሁም ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተወጣጡ ባለሙያዎች ጋር በጥጋቢ ሁኔታ ተጠናቆ የቀረበ ነው። ሆኖም ምላሽ በመዘግየቱ አባላቱ ለአላስፈላጊ ክሳራ መዳረጋቸውን አብራርተዋል።
ከታሪፍ መዘገየት በተጨማሪ ባለንብረቶች ሌላ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው አሽከርካሪዎች ከባለንብረቱ እውቅና ውጪ በሚፈጽሙት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ምክንያት ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ የመወረስ እርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል ብለዋል።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማህበር አባላቱን በመጥራት በዘርፉ በተደቀኑ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች እና በቀጣይ የጋራ አቋሞች ዙሪያ የምክክር ስብሰባ አካሂዷል።
@Addis_Reporter

❤5👍4
አስቸኳይ መረጃ ‼️
በመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ላይ የተከለከሉ ዋና ዋና ተግባራት ይፋ ሆኑ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል አፈጻጸም ላይ በአከራዮችና በተከራዮች ዘንድ የተከለከሉ ተግባራትን አስመልካች መረጃ ይፋ አድርጓል።
እንደ ቢሮው ማስታወቂያ፤ በሁለቱ ወገኖች መካከል በሚደረግ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ውስጥ የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም በሕግ የተከለከለ ነው፡
❌ በሕግ የተከለከሉ ተግባራት፡
1 ያለ ውል ማከራየት፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሳያስመዘግቡ መከራየት እና ማከራየት፤
2 የጊዜ ገደብ ማሳለፍ፡ በአከራይ ወይም ተከራይ ቸልተኝነት የኪራይ ውሉን በአዋጁ የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ አሳልፎ ማስመዘገብ፤
3 ውል አለማደስ፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እድሳትን በወቅቱ አለማስመዘገብ፤
4 ሕገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪ፡ በአዋጁ ከተፈቀደው አግባብ ውጪ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ፤
5 ያለጊዜው ከቤት ማስወጣት፡ በአዋጁ ከሚፈቀደው ውጪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት፤
6 ያለ ማስጠንቀቂያ ውል ማቋረጥ፡ በአዋጁ የተቀመጠውን የማስታወቂያ ወይም የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሳይሰጡ ውል ማቋረጥ፤
7 ከመጠን በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ፡ በአዋጁ ከተቀመጠው መጠን በላይ የቅድመ ክፍያ (አድቫንስ) እንዲፈጸም ማስገደድ፤
8 በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም፡ የቤት ኪራይ ክፍያን በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ (ዲጂታል) መንገድ አለመፈጸም፤
9 ቤትን ያለ አገልግሎት ባዶውን ማስቀመጥ፡ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየን የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤትን ያለአገልግሎት እንዲቀመጥ ማድረግ፤
10 ሐሰተኛ መረጃ ማቅረብ፡ በአዋጁ ለአከራይ የተሰጠውን ማበረታቻ ያለአግባብ ለመጠቀም ሐሰተኛ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ።
መረጃው ለአከራዮችና ለተከራዮች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ይተባበሩ!
Via የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

❤13👍8✍1🥰1👌1
ገላሽን በሙቅ ውሃ አጥብሻለሁ በማለት የ2 ዓመት ህፃን እንዳትጮህ አፉን በማፈን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ኤዳ ዳቡስ ቀበሌ ጎጥ አንድ በሚባል አካባቢ ነው የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ ኮማንደር ሀሩን ሄረላ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ተከሳሽ አወድ አልሀሪብ የተባለ ሲሆን ግንቦት 16 ቀን 2018 ከረፍዱ 4፡00 ሰዓት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሟል።
የ2 አመት ህፃን የሆነችውን ገላሽን በሙቅ ውሃ አጥብሻለሁ በማለት እናቷ ውሃ ልትቀዳ መሄዷን በማረጋገጥ ወደ ራሱ መኖሪያ ቤት ከወሰዳት በኋላ አፏን በማፈን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡
የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በማስደገፍ ለዐቃቤ ህግ ያቀርባል ዐቃቤ ህጉም ተከሳሹ በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1) ስር በተደነገገው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ለባምባሲ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል፡፡
ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሳሹን ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ የወንጀሉን ክብደትና የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ ኮማንደር ሀሩን ሄረላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

😡17💔13❤12🤯3👍2😱2😢1
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የስንዴ እና ማሽላ እርዳታ ላከች
የአሜሪካ መንግሥት ወደ 47,000 ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የምግብ እህል የጫነ የጭነት መርከብ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓዘ መሆኑን አስታወቀ።
በ”ሰላም ለምግብ” መርሃ ግብር የተላከው ይህ እርዳታ 37,700 ቶን ማሽላ እና 9,200 ቶን ስንዴን ያካተተ ነው።
ይህ እርዳታ የተላከው የኢትዮጵያ መንግሥት በስንዴ ምርት ራሱን መቻሉን እና ወደ ውጭ መላክ መጀመሩን በተደጋጋሚ ከገለጸበት ማግስት ነው።
ይሁን እንጂ፣ የአሜሪካ የግብርና መምሪያ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመሆኑ፣ ሀገሪቱ አሁንም ወደ 1.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የስንዴ ምርት ከውጭ ማስመጣት እንደምትፈልግ ያሳያል።
ከዚህ በተጨማሪ፣ በግጭት፣ በመፈናቀል እና በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህ የአሜሪካ እርዳታ የሀገሪቱን የስንዴ ራስን የመቻል ጥያቄዎች እና የሰብአዊ ድጋፍ አስፈላጊነትን ዳግም አነጋጋሪ አድርጎታል።

🤣74❤12🌚5🤩3👍2🙏1
የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ተመዛኞች በሙሉ
የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቃችሁ ጤና ባለሙያዎች በነሀሴ ወር 2018 ዓ.ም የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለመስጠት ተመዛኞች ከሰኔ 30/2018ዓ.ም ጀምሮ መረጃችሁን በማስተሳሰር ላይ እንደምትገኙ ይታወቃል፡፡
ስለዚህም መረጃችሁን ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ማስተሳሰር የምትችሉት እስከ ሃምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን ተገንዝባችሁ ይህንን https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ/Link/ በመጫን የብሄራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (National ID FAN 16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
▪ ይህ መረጃን የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥል እናሳውቃለን፡፡
▪ በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን የሚጠበቅባችሁ መሆኑን አሳስቧል።

❤5👍2
ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ታጥረው የተተዉ መሬቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ታጥረው ያለምንም አገልግሎት የተቀመጡ መሬቶችን በማጣራት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
ከንቲባዋ ይህን ያስታወቁት፣ በከተማ አስተዳደሩ የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድና የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው።
እንደ ከንቲባዋ ገለጻ፣ አዲስ አበባ መሬት ታጥሮ የሚቀመጥባት ከተማ መሆን እንደሌለባት ቀደም ሲል የተደረሰውን ስምምነት የሚጥሱ አካላት ተጨማሪ ዕድል እንደማይሰጣቸው አስጠንቅቀዋል።
በሌላ በኩል፣ በከተማዋ የሰላምና ደህንነት ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን በመግለጽ፣ በርካታ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶች ያለ የደህንነት ችግር በሰላም መጠናቀቃቸውን አስታውሰዋል።
በተጨማሪም፣ የከተማዋ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት መዘመኑ ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጥናት መሠረት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአፍሪካ ከተመረጡ ስድስት ምርጥ ከተሞች መካከል በአሠራር ደረጃ አንደኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ በጤናው ዘርፍ የሕክምና ባለሙያዎች የሙያ ሥነ-ምግባርና የአገልግሎት ጥራት መሻሻሉን፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የጤና አገልግሎትና የመሠረተ ልማት ሥራዎችም ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸሩ በእጥፍ መጨመራቸውን ገልጸዋል።

❤20🤪4🤣3👍2🤔1
" ከሰሞኑን ለ15 ቀናት በቆየ ኦፕሬሽን በአዲስ አበባ፣ በሐረሪና በሌሎች አካባቢዎች ነው የተያዙት " - አቶ ጃይላን አብዲ
"እጅግ አደገኛ ናቸው" የተባሉ ሰው አዘዋዋሪዎች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " ከ60 በላይ ስደተኞች ለሞት እና በርካታ ሴቶች ለመደፈር ተጠያቂ ናቸው " ያላቸውን አደገኛ 17 ተጠርጣሪ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መያዙን አስታውቋል።
ፖሊስ እንደገለጸው፣ በ"መሐመድ ጣሂር አደም (ወርዲ)" የሚመራው ቡድን ሰዎችን ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በደላሎች አማካኝነት በመልመል በጂቡቲና በየመን በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያዘዋውር ነበር።
እነዚህ አደገኛ የሰው አዘዋዋሪዎች ከ40,000 በላይ ሰዎች እንዳዘዋወሩ እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ እንደሰበሰቡ ተገልጿል።
ተጎጂዎች በየመን ውስጥ በመጋዘኖች ታግተው ድብደባ፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ሲገለጽ፣ ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲልኩ ለማስገደድ የስቃይ ቪዲዮዎች ይላኩ እንደነበር ተጠቁሟል።
በምርመራውም ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውና በርካታ ሴቶች መደፈራቸው መረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።
የፌደራል ፖሊስ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ጄይላን አብዲ፣ ተጠርጣሪዎቹ ሰሞኑን ለ15 ቀናት በቆየ ኦፕሬሽን በአዲስ አበባ፣ በሐረሪና በሌሎች አካባቢዎች መያዛቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል።
ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹ የምርመራ ፋይል ለፍትሕ ሚኒስቴር መተላለፉን ገልጿል።
በስማቸው የነበሩ ቤቶች ፣ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶችም መታገዳቸው ታውቋል።

❤11👍8🥰1👌1🤣1
ኮስትሸሪንግ❌‼️
የኬንያ መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ በበጀት ሊሸፈን መሆኑን አስታወቀ‼️
የኬንያ መንግስት ከሚቀጥለው መስከረም 2026 ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚገቡ ሁሉንም ተማሪዎች ትምህርት ሙሉ በሙሉ በመንግስት በጀት እንደሚሸፈን ይፋ አደረገ። ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ አዲሱ የትምህርት ፋይናንስ ማዕቀፍ ከቤተሰብ ኢኮኖሚያዊ አቅም ውጪ በውጤት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንደሆነ ገልጸዋል።
ቀደም ሲል ተግባራዊ ተደርገው የነበሩት የዩኒቨርሲቲ በጀት አሰጣጥ ሥርዓቶችና የብድር ድብልቅ ሞዴሎች ተቋማቱንና ተማሪዎችን በቂ ድጋፍ ማድረግ ባለመቻላቸው መቋረጣቸውን ተናግረዋል።
አዲሱ ሥርዓት ወላጆች በፈቃደኝነት ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት የክፍያ ጫና እንዳይኖርባቸው የሚያደርግና ድህነት ትምህርት እንዳያስተጓጉል የሚያስችል ነው ተብሏል። ለዚህም እንዲመች ፓርላማው የከፍተኛ ትምህርት ብድር ቦርድን ጨምሮ አስፈላጊውን የህግ ማሻሻያ በፍጥነት እንዲያጸድቅ ተጠይቋል።

👍31❤18👌3🙏2🥰1
37 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለኢራን ጦርነት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሜሪካ በኢራን እያካሄደች ባለው ጦርነት እስካሁን 37.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓ ተገለጸ።
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ከተቀሰቀሰ ወዲህ ዋሽንግተን እስከ አሁን 37 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት አስታውቀዋል። ይህ ወጪ ባለፈው ግንቦት ወር ከተደረገው ግምት ጋር ሲነጻጸር የ8 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ ሚኒስትሩ አሁንም ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ በሴኔት የገንዘብ ድልድል ኮሚቴ ፊት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ፣ ኮንግረሱ አስቸኳይ ተጨማሪ በጀት ካላፀደቀ የሀገሪቱ ወታደራዊ ስልጠናዎች ሊስተጓጎሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
ሄግሴት ለመከላከያ መስሪያ ቤታቸው (ፔንታጎን) 87 ቢሊዮን ዶላር እንዲፈቀድ የጠየቁ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 67 ቢሊዮን ዶላሩ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚካሄዱ ወታደራዊ ዘመቻዎች የሚውል መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የበጀት ጥያቄ የቀረበው በመካከለኛው ምስራቅ ሶስት የአሜሪካ ወታደሮች በተገደሉበት እና ጦርነቱ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በደረሰበት ወቅት ነው። ዋይት ሃውስ ለቀጣዩ የበጀት ዓመት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር ለፔንታገን እንዲመደብ መጠየቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህም የአሜሪካን ወታደራዊ ወጪ በታሪክ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደርሰዋል።
አሜሪካ በኢራን ላይ ለ11 ተከታታይ ቀናት ጥቃት መሰንዘሯን የቀጠለች ሲሆን ኢራንም በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ የአጸፋ ጥቃት በመሰንዘር ላይ ትገኛለች።
ዘገባው የቢቢሲ ነው

❤15
ኤሌክትሮኒክስ ላይ ረጅም ሰዓት የሚያሳልፉ የልዩ ፍላጎት ልጆች የንግግር እና የመግባባት ክህሎታቸውን ሊጎዳ እንደሚችል ተነገረ
ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ታዳጊዎች በቤት ውስጥ ረጅም ጊዜን በሚያሳልፋበት የክረምት ወቅት ላይ ቴሌቭዥንን ጨምሮ ከሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ነገሮች መራቅ ይኖርባቸዋል። ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች ለአእምሮ እድገታቸው እንቅስቃሴ ያሏቸው ጨዋታዎችን እንዲጫወቱ ፣ በአእምሮ የሚሰሩና የሚገጣጠሙ መጫዎቻዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማገዝ ያስፈልጋል ሲሉ የፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሸዋጌጥ ክብረት ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
ልዩ ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ትምህርት ቤት ስለሄዱ ብቻ ውጤታማ መሆን ስለማይችሉ ብቻቸውን ከማዋል ይልቅ ልጆች ያሉባቸው እንዲሁም ሊደሰቱባቸው የሚችሉባቸው ቦታዎች ላይ እንዲሆኑ ማድረግ የመግባባት ክህሎታቸውን ለማዳበር ያግዛል። ከቴሌቪዥን እና ከሞባይል ጋር ረጅም ሰዓትን የሚያጠፉ የልዩ ፍላጎት ልጆች ከንግግር እና ከመግባባት ችሎታ ወደ ኋላ እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል።
ይህ አይነቱ ችግር ያለባቸው ልጆች ንዴታቸውን የሚገልጹት ራሳቸውን በመጉዳት ሊሆን ስለሚችል ከልጅነት ጀምሮ በሚኖራቸው አስተዳደግ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረግ እና ሊያናድዳቸዉ የሚችሉ ነገሮችን መቅረፍ ያስፈልጋል።ዋና ስራ አስኪያጇ አክለውም ወላጆች ይህን ህመም የማመን ችግር እንደሚገጥማቸው ገልፀው፤ ስልጠና በመውሰድ ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ማግኘት እንደሚችሉ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤8👍2
በኮንታ ልዩ ወረዳ እናትን ገድሎ ልጃቸውን የደፈረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
በኮንታ ልዩ ወረዳ የግንባ አጋሬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አብርሃም አመለ ቦንጆሬ፣ በፈጸማቸው ሶስት ከባድ ወንጀሎች በሞት እንዲቀጣ የኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።
ተከሳሹ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከገበያ ስትመለስ የነበረችውን የ15 ዓመት ታዳጊ ጠልፎ ወደ ጫካ በመውሰድ ሊደፍራት ሲታገል፣ የልጇን ጩኸት ሰምታ የደረሰችውን እናት ወይዘሮ አይናቴ ኬቶን በጩቤ ወግቶ በመግደል ገደል ውስጥ ወርውሯታል።
ተከሳሹ እናትን በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ካደባየ በኋላ የጠለፋትን ታዳጊ ልጅ አስገድዶ መድፈሩን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እና የዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች አረጋግጠዋል።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት፣ ተከሳሹ በፈጸማቸው በጭካኔ የመግደል፣ በታዳጊ ልጅ ጠለፋ እና በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ጥፋተኛ በማለቱ የሞት ቅጣት እንዲወሰንበት አድርጓል።

❤22🙉13🤯10💯8🫡3👍2🤔2😢1
ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ ጄኤፍኤም 106.7 የብሮድካስት አዋጅ ቁጥር 1238/2013 እና የፈቃድ ውል ስምምነቱን አልጠበቀም ሲል አስታውቋል።
ጣቢያው 60% የሚሆነውን ስርጭት ለፈቃድ አካባቢው የማዋል፣ ህዝብን የሚያስተምሩና የሚያዝናኑ ፕሮግራሞችን የማቅረብ፣ እንዲሁም ሀገራዊ እና ህገ-መንግስታዊ እሴቶችን የማጠናከር ግዴታዎቹን አልተወጣም ተብሏል።
ባለሥልጣኑ በተደጋጋሚ የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም መሻሻል ባለመታየቱ እርምጃው ሊወሰድበት ችሏል።
በዚህም መሠረት የሬዲዮ ጣቢያው ከተሰጡት ማስጠንቀቂያዎች በኋላ አስፈላጊዎቹን ግዴታዎች ሙሉ ለሙሉ አሟልቶ እስኪገኝ ድረስ ለቀጣዮቹ 6 ወራት ከስርጭት ሙሉ በሙሉ ታግዷል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣንም ለጄኤፍኤም የተመደበው 106.7 የሬድዮ ሞገድ እግድ ፀንቶ እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ ፍሪኩዌንሲውን ጥቅም ላይ ማዋል እንደማይቻል ለጣቢያው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

😡20❤11👍4🤷♂3🤡2🤔1
ኢትዮጵያ መብራት አቋረጠችብች-ሱዳን‼️
የሱዳን የኢነርጂ እና ነዳጅ ሚኒስቴር በትናትናው ዕለት ሀምሌ 14/2018 ዓ.ም እንዳስታወቀው 'በመላ ሀገሪቱ የሚታየው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በበርካታ ምክንያቶች የተከሰተ መሆኑን ጠቅሶ ከእነዚህም መካከል ከኢትዮጵያ ጋር በተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በኩል የሚደረገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት መቋረጥ በዋናው መስመር ላይ ጉዳት መድረሱን ሌላኛው ፈተና መሆኑን ገልጿል። ሚኒስትሩ በካርቱም ከፍተኛ የተባለ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር መፈጠሩን ጠቅሷል።

🤣25❤14👍4🤔1🤪1
የድሮን ጥቃት‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ “በመካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም በድሮን ጥቃት የመነኮሳት ህይወት አለፈ”‼️
በዛሬው ዕለት ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም በምዕራብ ወሎ በመካነ ሰላም በዓባይ ወንዝ ዳርቻ በሚገኘው ዓባይ ገዳመ አስቀጤስ የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ምክንያት በገዳሙ ውስጥ የሚኖሩ 2 ሴቶች ወዲያው ህይወታቸው ማለፉን እና ሌሎች መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው የፋኖ ሀይሎች ከትመዋል በሚል ነው ተብሏል።
ሰላም ለሀገራችን🕊🕊

😢57💔28❤15😱3
የዝናብ ሁኔታ‼️
በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።
በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ።
ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ መሰረት፣ ከሐምሌ 14 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት አስር ቀናት ውስጥ የዝናብ ሁኔታን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች የበለጠ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አሰታወቋል።
በዚህም መሰረት በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቷ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ ሥርጭት መጠን ይኖራቸዋል።
በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል።
በተጨማሪም በመካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቷ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ ብሏል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ነው ኢንስቲትዩቱ የጠቆመው።
በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቷ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል።
በተጨማሪም በኤሊ ዳር፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ ቡሬ፣ አሳይታ፣ ሁንዱፎ፣ ገዋኔ፣ ሚሌ፣ ዳሊፋጊ፣ አይሻ፣ ጉሊና፣ አዋሽ አርባ፣ ባቲ፣ ዶሎ አዶ፣ ዳዋ፣ አሶሶ፣ ጎዴ፣ ቋራ፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ ጭፍራ፣ ላሬ፣ መተሀራ እና፣ ላሬ፣ ፉኙዶ አካባቢዎች ከሚኖረው የቀን ከፍተኛ የፀሀይ ሀይል ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሙቀት ይኖራቸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ቀናት የሚኖረውን መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም እና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክር ሀሳብን ከወዲሁ መተግበር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

❤13👍7
ብሄራዊ ባንክ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 500 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያካሂድ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ2019 ዓ.ም የፋይናንስ ዓመት የመጀመሪያው ሩብ በንግድ ባንኮች በኩል 500 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ወደ ገበያው ለማስገባት አቅዷል።
ማዕከላዊ ባንኩ በነሐሴ እና መስከረም ወራት አራት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎችን እንደሚያካሂድ ገልጿል።
በእያንዳንዱ ጨረታም 125 ሚሊዮን ዶላር ለንግድ ባንኮች እንደሚቀርብ አስታውቋል።

❤4👍3
በትግራይ በረዶ አዘል ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ቀጠፈ
በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ተቃራኒ የአየር ሁኔታዎች በሕዝብና በግብርና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆናቸው ተገልጿል።
በአንድ በኩል በረዶ አዘል ከባድ ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ በአዝርእትና በመስኖ ላይም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ 176 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት እስካሁን የክረምት ዝናብ እንዳላገኙ ተገልጿል።
በማዕከላዊ ዞን ወረዳ ቀይሕ ተኽሊ ዶክተር አታኽልቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፣ ለሁለት ሰዓታት ያለማቋረጥ የዘነበው በረዶ አዘል ከባድ ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ከመቅጠፉ በተጨማሪ በአዝርእትና በመስኖ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
በተመሳሳይ በዞኑ ወረዳ አሕፈሮም ሴሮ ቀበሌ የዘነበው ብርቱ ዝናብም በአዝርእትና በአትክልት ላይ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
በሌላ በኩል የትግራይ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ጥበቃ ቢሮ ሐምሌ 13፣ 2018 ዓ.ም. ባወጣው መረጃ፣ በክልሉ ከሚገኙ 600 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት መካከል 176 በሚሆኑት እስካሁን የክረምት ዝናብ እንዳልዘነበ አስታውቋል።
ይህ ሁኔታ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ከመጠን ያለፈ ዝናብ ጉዳት እያደረሰ ሲሆን፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ የዝናብ እጥረት በእርሻ ሥራና በምርት ላይ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ያሳያል።#ቲክቫህ

❤10😢9👍2