አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
65 የመንግስት ኤጀንሲዎች የቦርድ አባላት በሙሉ ከስልጣን ተነሱ

የኬንያ መንግስት በሀገሪቱ የህዝብ ተቋማት ውስጥ የነበረውን የፖለቲካ ተፅዕኖ ለመቀነስ በሚል በ65 የመንግስት ኤጀንሲዎች ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ የቦርድ አባላትን በሙሉ በይፋ ማሰናበቱን አስታውቋል። ይህ እርምጃ የተወሰደው በቅርቡ ተግባራዊ በሆነው የ2025 የመንግስት ድርጅቶች ህግ (GOE Act) መሰረት መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ ለውጥ የመንግስት ድርጅቶችን አሰራር ሙያዊ እና ግልጽ ለማድረግ ያለመ ነዉ የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል የቦርድ አባልነት ለፖለቲካዊ ሹመት ሲውል እንደነበርና ይህም ለሙስና እና ለቅልጥፍና ማጣት መንስኤ ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል።

አዲሱ ህግ ለቦርድ አባልነት የሚወዳደሩ ሰዎች ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በንቃት በፖለቲካ ስራ ውስጥ መሳተፍ እንደሌለባቸው ይደነግጋል። ቦርዶቹም በግልፅ እና በውድድር ሂደት በሚመረጡ ባለሙያዎች እንዲዋቀሩ ይደረጋል።

የቦርድ አባላቱ በሶስት ዓመት የስራ ዘመን የሚያገለግሉ ሲሆን፣ በድጋሚ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሊመረጡ ይችላሉ ተብሏል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ይህ ለውጥ የመንግስት ተቋማትን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ በማውጣት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2🤣1
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራ እና ሶማሊያ አቻዎቻቸው ጋር በቀጣናዊ  ትብብር ዙሪያ ውይይት አደረጉ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

🇪🇬 ዛሬ ዕሑድ በካይሮ በተለያዩ መድረኮች በተደረጉ ስብሰባዎች፣ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ከኤርትራ አቻቸው ኡስማን ሳሌህ እና ከሶማሊያ አቻቸው አብዱሰላም አብዲ አሊ ጋር መወያየታቸውን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ስብሰባዎቹ የሁለትዮሽ ግንኙነትን፣ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ማጠናከር እና በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቅንጅት መሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንደተደረገባቸው ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18😡4👍2🤣2
ስፔን አርጀንቲናን በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች
***

የ2026 ዓለም ዋንጫ ዛሬ ፍጻሜውን ሲያገኘ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። 120 ደቂቃ በወሰደው ፍጻሜ ተቀይሮ የገባው ፌራን ቶሬስ የስፔንን ግብ አስቆጥሯል።

በአርጀንቲና በኩል መደበኛ 90 ደቂቃው መጠናቀቂያ ላይ የቼልሲው አማካይ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ፓው ኩባርሲ ላይ በሰራው ጥፋ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

የ2010 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ ስፔን በታሪኳ ለ2ኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያነሳችበት ሆኗል።

አርጀንቲና የዓለም ዋንጫን ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ ለመውሰድ ለፍጻሜ ብትደርስም ሳይሳካላት ቀርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28👍9🤪3🤷‍♂1🥰1😢1🎉1👌1😎1
ታክስ ሊጣል ነው‼️
መንግስት በአዲስ የተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ ታክስ ሊጥል ነው‼️
​መንግስት በ2020 በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ታክስ ለመጣል እየተዘጋጀ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የህግ ረቂቁን በታህሳስ ወር መጨረሻ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርብ
ታውቋል።
ታክሱ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እስከ 0.2 በመቶ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢125👍2🤔2🤯1
የሀገር ውስጥ የቡና ዋጋ‼️
ለሀገር ውስጥ የቡና ዋጋ መናር ዋነኛው ምክንያት የቡና ነጋዴዎች ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ቀዳሚ የቡና አምራች ሀገር ብትሆንም፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለሚታየው የሀገር ውስጥ የቡና ዋጋ መጨመር ዋነኛው ምክንያት የቡና ላኪዎች ምርቱን በተጋነነ ዋጋ ማቅረባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ሰፊሳ አባቡ ለመናኸሪያ ሬድዮ እንደገለጹት፣ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበው የቡና ምርት የተገኘው ገቢ ከፍተኛ ቢሆንም፣ በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ ግን የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።

ባለስልጣኑ በዘርፉ የቁጥጥር ሥራ እያከናወነ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ የቡና ዋጋ ከአለም አቀፍ የገበያ ተመን ጋር ሲነጻጸር ሰፊ ልዩነት እንዳለው አስረድተዋል።

ላኪዎች እርስ በርሳቸው በመነጋገር ተቀራራቢና የተረጋጋ ዋጋ እንዲያቀርቡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም፤ ወዳልተገባ የዋጋ ሽሚያ በመግባታቸው ምክንያት በገበያው ላይ አለመረጋጋት መፈጠሩን ኃላፊው ገልጸዋል።

ይህ የዋጋ መጋነን የሀገሪቱን የቡና ዘርፍ ወደ ኋላ የሚጎትት በመሆኑ ባለስልጣኑ ላኪዎችን በውይይት ለማስማማት ጥረት ማድረጉን ጠቅሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍5🥰1💯1
በኢትዮጵያ መካንነት ከፍተኛ የጤና ችግር እየሆነ መምጣቱ ተነገረ
 
የመካንነት ችግር በሴቶች ፣በወንዶች እንዲሁም በሁለቱም አጋሮች በጋራ ሊከሰት እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።በኢትዮጵያ የመካንነት ችግር ከሚጠበቀው በላይ ከፍተኛ መሆኑን በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት እንዲሁም የመካንነት ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶክተር በላይ ቤተማሪያም ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
 
ከጥንዶች መካከል ከ20 እስከ 25 በመቶ የሚሆኑት በዚህ ችግር እንደሚጠቁ ተናግረዋል።በኢንፌክሽን ምክኒያት የሚከሰት የማህፀን ቱቦ መዘጋት በሴቶች ላይ ለሚከሰት የመካንነት ችግር 35 በመቶ ድርሻ እንዳለዉ ሰብ ስፔሻሊስቱ አስገንዝበዋል ።በባክቴሪያ ፣በፈንገስ እና በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት የሴቶች የመራቢያ አካል ወይም የማህፀን ኢንፌክሽን ህክምና ካላገኘ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ መካንነትን ሊያስከትል ይችላል።
 
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ 20 በመቶ የሚሆነው በወንድ በኩል የሚኖር መካንነት ነው።በጭንቅላት ውስጥ የሚመረት ሆርሞን ማነስ ፣በዘር ፍሬ ላይ የሚያጋጥም ስፐርም የማምረት ችግር ፣የወንድ የዘር ቱቦ መዘጋት እንዲሁም ምክንያቱ የማይታወቅ የወንድ መካንነት ዋና ዋናዎቹ መንስኤዎች ናቸው ።
 
የእንቁላል መፈጠር ወይም መለቀቅ ችግር ፤ በሆርሞን መዛባት  ወይም በእድሜ ምክኒያት እንቁላል በወር አበባ ዑደት ውስጥ አዘውትሮ አለመፈጠር በሴቶች ላይ ለሚከሰት የመካንነት ችግር ዋነኛቹ ምክኒያቶች መሆናቸውን ዶክተር በላይ አስረድተዋል ።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍3😱1
የመብራት ታሪፍ‼️
👉ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት አዲስ የክፍያ ታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።
‹‹በኤሌክትሪክ ክፍያ ላይ የታየው ለውጥ አዲስ ጭማሪ ሳይሆን ቀድሞ የተወሰነ ማስተካከያ ሂደት ነው››-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ በደንበኞች ላይ የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ ክፍያ ቀደም ሲል በስትራቴጂው መሠረት የተወሰነ መሆኑን አስታዉቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሽያጭና ደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ይኸይስ ስዩም ለኢትዮ ኤፍኤም 107.8 እንደገለጹት፤ በ2017 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ የተጀመረው የታሪፍ ማሻሻያ የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ በ24 የሩብ ዓመታት ተከፋፍሎ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ይህ የታሪፍ ማስተካከያ ተቋሙ ከአራት ዓመት በኋላ የሚሰበሰበውን አጠቃላይ ክፍያ በመስከረም 2017 ዓ.ም ላይ በአንድ ጊዜ ማስከፈል የነበረበት ቢሆንም፣ የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅም ታሳቢ በማድረግ በጥቂት በጥቂቱ ከፋፍሎ እንዲከፍል የተዘረጋ ስትራቴጂ ነው በማለት ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያለው ታሪፍ ዝቅተኛውን የኅብረተሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ ለመደገፍ  የመንግሥት ድጎማ የሚደረግበት ነው ያሉ ሲሆን፣ እስከ 50 ኪሎ ዋት ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት 96 ሳንቲም ብቻ እንዲከፍሉ እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዶ/ር ይኸይስ አክለውም፤ እስከ 2መቶ ኪሎ ዋት የሚጠቀም ማንኛውም ደንበኛ በትክክለኛው የታሪፍ ዋጋ ሳይሆን በድጎማ እንዲከፍል እየተደረገ ነው ብለዋል።

ደንበኞች በአንድ ወር ውስጥ በተደጋጋሚ ኃይል ሲገዙ ስለሚገጥማቸው የዋጋ ልዩነት ሲያብራሩም፤ የዋጋ አተማመን ሥርዓቱ በ30 ቀናት ውስጥ የተጠቀሙትን አጠቃላይ የኃይል መጠን በአንድ ላይ ደምሮ ስለሚያሰላው የኪሎ ዋት መጠኑ ሲጨምር ታሪፉም አብሮ እንደሚጨምር አስገንዝበዋል።

ይህንን ሁኔታ ተከትሎ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ተቋሙ በየክፍለ ከተማው ከነዋሪዎች ጋር ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን እያደረገ ሲሆን፣ ባለፉት 15 ቀናት ውስጥም ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለሚዲያ አካላት ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡2115👍3💊2👌1🥱1👀1🙉1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
👍31
የምግብ ዋጋ ግሽበት 15.1 በመቶ ደረሰ

የሰኔ ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።

የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 15.1 በመቶ የጨመረ ሲሆን በዋናነት አትክልት፣ ስጋ ፣ የወተት ተዋፅኦዎች፣ እንቁላል፣ ፍራፍሬ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 12.2 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 14.3 በመቶ፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ 14.5 በመቶ፣ በኮሙዩኒኬሸን 8.9 በመቶ ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 12.0 በመቶ እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች 17.9 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢11👍63🤪1
አሜሪካ ወደ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የ«አትሂዱ» ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ሀገራትን የፀጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በሚያወጣው መመሪያ፣ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን በከፍተኛው የደረጃ 4 የጉዞ ማስጠንቀቂያ ዝርዝር ውስጥ አስፍሯል።

ዋሽንግተን የራሷ ዜጎች ወደነዚህ ሀገራት ፍጹም ጉዞ እንዳያደርጉ ያሳሰበችው በእነዚህ ቀጠናዎች ባለው እጅግ አሳሳቢ የፀጥታ ችግር፣ የሽብርተኝነት ስጋት፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ የታጠቁ አማፂያን ጥቃት እና ለአሜሪካ ዜጎች የሚሰጠው የቆንስላ ወይም የድንገተኛ ጊዜ ድጋፍ እጅግ ውስን በመሆኑ ነው።

በዚህ የዩናይትድ ስቴትስ የ«አትሂዱ» ጥብቅ መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቡርኪና ፋሶ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ እንደ ቻድ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ሀገራት ደግሞ በተለይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚያገናኟቸው ድንበሮችና የተወሰኑ ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ግዛቶቻቸው ላይ ተመሳሳይ የደረጃ 4 እገዳ ተጥሎባቸዋል።

በሌላ በኩል ዩጋንዳ በደረጃ 3 (Reconsider Travel ወይም ጉዞን መልሶ ማሰብ) ስር የምትገኝ ሲሆን፣ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ከመጓዛቸው በፊት በወንጀል እና በሽብርተኝነት ስጋቶች ዙሪያ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተመክሯል።

ይህ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየጊዜው የሚሻሻለው የደረጃ 4 የጉዞ ማስጠንቀቂያ ከአፍሪካ ውጭ እንደ ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ አፍጋኒስታን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢራን እና ጋዛን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦርነትና የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ያሉ የዓለማችን አካባቢዎችንም ያጠቃልላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ዘንድሮ ክልል አቀፉን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 85,531 ተማሪዎች 83,342 ተማሪዎች ወይም 97.4 በመቶ ማለፋቸውን አሳውቋል።

ከ1,538 ት/ቤቶች ውስጥ 1,017 ትምህርት ቤቶች ሁሉንም ተማሪዎቻቸውን እንዳሳለፉም ያሳወቀው ክልሉ አንድም ትምህርት ቤት ተማሪ ያላሳለፈ የለም ብሏል።

ሌላው የዘንድሮው ውጤት ከ2017 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር በ61.5 በመቶ መሻሻሉንም ጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🤣10👍4
በአከራይ ተከራይ ውል መፈጸም የሌለባቸው እና የተከለከሉ ተግባራት...

በአዲስ አበባ ከተማ በአከራይ ተከራይ ውል የሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም የተከለከለ ነው።

👉የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሳያስመዘግቡ መከራየትና ማከራየት፤

👉በአከራይ ወይም ተከራይ ቸልተኝነት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል በአዋጁ የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ አሳልፎ ማስመዝገብ፤

👉የመኖሪ ቤት ኪራይ ውል እድሳት አለማስመዝገብ፤

👉በአዋጁ ከተፈቀደው አግባብ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ፤

👉አዋጁ ከሚፈቅደው ውጪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ከቤት ማስወጣት፤

👉በአዋጁ የተቀመጠውን የማስታወቂያ ወይም የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሳይሰጥ ውል ማቋረጥ፤

👉አዋጁ ላይ ከተቀመጠው መጠን በላይ የቅድመ ክፍያ እንዲፈፀም ማስገደድ፤

👉 በባንክ ወይሞ በሌላ ሕጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ስርዓት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ክፍያ አለመፈፀም

👉 ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ መኖሪያ ቤት ያለአገልግሎት እንዲቀመጥ ማድረግ እና ፤

👉በአዋጁ ለአከራይ የተሰጠውን ማበረታቻ ያለአግባብ ለመጠቀሞ ሀሰተኛ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18😡7👍2
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት፣ አስፈላጊ ማስረጃዎችን ያላሟሉ የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ እንደሚያቋርጥ አስጠነቀቀ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ የፈረሙበት ደብዳቤ፤ ከሚያዝያ ጀምሮ በመንግሥት ሠራተኞች የትምህርትና ሌሎች ማስረጃዎች ላይ ማጣራት ሲደረግ መቆየቱንና የሠራተኞች የትምህርት ማስረጃዎችና ተያያዥ መረጃዎች ተደራጅተው አለመገኘታቸውን ጠቅሷል፡፡ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በአካል ቀርቦ አስፈላጊ መረጃዎችን እስከ ሐምሌ 30 ቀን ድረስ ሞልቶ ማጠናቀቅ እንዳለበትም የክልሉ መንግሥት አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍2
የ20 ዓመት ሴት ልጅ የገዛ ልጁን አስገድዶ ግብረ ስጋ ግንኘነት ያደረገው አባት በእስራት ተቀጣ

ሐምሌ 14, 2018 ዓ.ም ምዕራብ ዓባያ ወረዳ።

በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ መንደር ሰባት ነዋሪ የሆኑት ኢንስፐክተር ግርማ ጌታቸው እና ከወ/ሮ መስከረም ሙሉጌታ የተወለደችው ልጅ ሐና ግርማ ዕድሜዋ 20 ዓመት የደረሰና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን መንግሥት ባስታጠቀው ሽጉጥ በማስፈራራት በቀን 6/9/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ቡና እያፈለች ባለችበት ኳላ በመምጣት በጉልበት ወደ መኝታ ክፍል በማምራት የለበሰችሁን ቀምስ በማወለቅ ክብረ ንጽህና በመገርሰስ በጉልበት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈፅም ልጅቷ ባሰማችው የድረሱልኝ ጥሪ ጎረቤት በመሰማት መደፈራዋን ከአንደበቷ ሰምተው ሲያረጋግጡ ለፖሊስ ጥቆማ በማድረግ የማጣራት ስራ በመስራት በህግ ሲታይ ቆይቶ የምዕራብ አባያ ወረዳ ፍ/ቤት በተከሳሹ ላይ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት 9 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል ሲል ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔30😡23🙉98👍2😱2🤯1😢1👀1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጦርነት ድባብ እየተሰማ ነው‼️
በትግራይ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ከባለፈው እሁድ ጀምሮ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ህዝቡ እና ወጣቱ ለጦርነት እንዲዘጋጅ ከሁሉም አመራሮች በግልጽ እየተነገራቸው ይገኛል።
የህወሓት ዋና ፀሃፊ የሆኑት ፈትለወርቅ (ሞንጀሪኖ) ባካሄዱበት ስብሰባ ላይ "አዲስ አበባ እስክንገባ ብቻችን እንሸከመዋለን ማለት አይደለም፥ ብዙ አጋሮች አሉን ። አዲስ አበባ በር ላይ ፋኖ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አለ ስለዚህ ብዙ ወዳጆች አሉን” ሲሉ ተደምጠዋል።
ሰላም ለሀገራችን🕊🕊

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
46👍12🫡6🤣5🙉5🤯4🕊4👀1🙊1
እየተባባሰ የመጣው የኦንላይን ማጭበርበር

በማኅበራዊ ሚዲያዎች " ውጭ ሀገር እኖራለሁ " ፣ " የፍቅር ጓደኛ እፈልጋለሁ " ወይም " ለሞት የሚዳርግ በሽታ ይዞኛል፤ ሀብቴን የሚያስተዳድርልኝ ታማኝ ሰው እፈልጋለሁ " በሚሉ መልዕክቶች ተጠቃሚዎችን በማታለል እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ እያሳጡ መሆናቸውን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ እጣወርቅ ተስፋዬ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ እንዳሉት፣ አጭበርባሪዎቹ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ቴሌግራምን በመጠቀም የውሸት ማንነት በመፍጠር ተጎጂዎችን ያጠምዳሉ።

" ሀብታም ነኝ "፣ " ከሁሉም አንተን/አንቺን መርጫለሁ " የሚሉ መልዕክቶችም ከሚጠቀሙባቸው የማጭበርበሪያ ስልቶች መካከል ናቸው።

ከተጎጂዎች ጋር ግንኙነታቸውን ካጠናከሩ በኋላ፣ ሌላ ሰው በተለየ ስልክ ቁጥር በመደወል " የላክነው ዕቃ ጉምሩክ ደርሷል፤ ነገር ግን ዶላር ወይም ወርቅ ስላለበት ክፍያ ያስፈልጋል " በማለት የታሸገ ዕቃ ፎቶ በመላክ ገንዘብ እንዲልኩ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

በዚህ ሂደት ከ500 ሺህ እና ከዛ በላይ ገንዘብ ሰዎች እንደሚጭበረበሩ አመልክተዋል።

ወ/ሮ እጣወርቅ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች " ከሁሉም ሰው እኔ ለምን ተመረጥኩ ? " እና " ለስጦታ እንዴት ክፍያ ይጠየቃል ? " የሚሉ ጥያቄዎችን ራሳቸውን በመጠየቅ ከመሰል ማጭበርበሮች እንዲጠነቀቁ አሳስበዋል።

የኦንላይን ማጭበርበር ወንጀል እየተስፋፋ ሲሆን፣ ባለፈው የበጀት ዓመት ብቻ ከ100 ሺህ ብር በላይ ጉዳት ያስከተሉ ከ80 በላይ ዋና ዋና የክስ መዝገቦች በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ መመስረታቸው ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3👍3👀2
የነዳጅ ቦቴ ባለንብረቶች ከገበያ ልንወጣ እንችላለን ሲሉ ስጋታቸውን ገለጹ

በሀገሪቱ እየታየ ያለው የመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ መናር እና የታሪፍ ማሻሻያ አለመደረግ አክሳሪ እንደሆነባቸው የገለጹት የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች፣ ችግሩ ባልተፈታበት ሁኔታ ስራቸውን ማስቀጠል አስቸጋሪ እንደሆነባቸው በመግለጽ ከገበያው የመወጣት ስጋት እንደደቀነባቸው አስታወቁ።

የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር የነዳጅ ፍላጎት እድገትን እና የወጡ ወጪዎችን ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ተደጋጋሚ ጥናቶችን ማቅረቡን ያስታወሰ ቢሆንም፣ በመንግስት በኩል ግን እስካሁን አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን ገልጿል።

የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ ፀጋ አስማረ እንደገለጹት፤ ጥናቱ ዝም ብሎ የቀረበ ሳይሆን ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እንዲሁም ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተወጣጡ ባለሙያዎች ጋር በጥጋቢ ሁኔታ ተጠናቆ የቀረበ ነው። ሆኖም ምላሽ በመዘግየቱ አባላቱ ለአላስፈላጊ ክሳራ መዳረጋቸውን አብራርተዋል።

ከታሪፍ መዘገየት በተጨማሪ ባለንብረቶች ሌላ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው አሽከርካሪዎች ከባለንብረቱ እውቅና ውጪ በሚፈጽሙት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ምክንያት ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ የመወረስ እርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል ብለዋል።

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማህበር አባላቱን በመጥራት በዘርፉ በተደቀኑ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች እና በቀጣይ የጋራ አቋሞች ዙሪያ የምክክር ስብሰባ አካሂዷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍4
አስቸኳይ መረጃ ‼️
በመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ላይ የተከለከሉ ዋና ዋና ተግባራት ይፋ ሆኑ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል አፈጻጸም ላይ በአከራዮችና በተከራዮች ዘንድ የተከለከሉ ተግባራትን አስመልካች መረጃ ይፋ አድርጓል።

እንደ ቢሮው ማስታወቂያ፤ በሁለቱ ወገኖች መካከል በሚደረግ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ውስጥ የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም በሕግ የተከለከለ ነው፡

በሕግ የተከለከሉ ተግባራት፡

1 ያለ ውል ማከራየት፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሳያስመዘግቡ መከራየት እና ማከራየት፤

2 የጊዜ ገደብ ማሳለፍ፡ በአከራይ ወይም ተከራይ ቸልተኝነት የኪራይ ውሉን በአዋጁ የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ አሳልፎ ማስመዘገብ፤

3 ውል አለማደስ፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እድሳትን በወቅቱ አለማስመዘገብ፤

4 ሕገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪ፡ በአዋጁ ከተፈቀደው አግባብ ውጪ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ፤

5 ያለጊዜው ከቤት ማስወጣት፡ በአዋጁ ከሚፈቀደው ውጪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት፤

6 ያለ ማስጠንቀቂያ ውል ማቋረጥ፡ በአዋጁ የተቀመጠውን የማስታወቂያ ወይም የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሳይሰጡ ውል ማቋረጥ፤

7 ከመጠን በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ፡ በአዋጁ ከተቀመጠው መጠን በላይ የቅድመ ክፍያ (አድቫንስ) እንዲፈጸም ማስገደድ፤

8 በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም፡ የቤት ኪራይ ክፍያን በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ (ዲጂታል) መንገድ አለመፈጸም፤

9 ቤትን ያለ አገልግሎት ባዶውን ማስቀመጥ፡ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየን የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤትን ያለአገልግሎት እንዲቀመጥ ማድረግ፤

10 ሐሰተኛ መረጃ ማቅረብ፡ በአዋጁ ለአከራይ የተሰጠውን ማበረታቻ ያለአግባብ ለመጠቀም ሐሰተኛ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ።

መረጃው ለአከራዮችና ለተከራዮች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ይተባበሩ!
Via የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍81🥰1👌1