አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
416 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ትልቁ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 110 ሚሊዮን ዶላር አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ በሶማሌ ክልል ለሚገነባውና 300 ሜጋ ዋት አቅም ለሚኖረው የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 110 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ።

ሲጠናቀቅ በኢትዮጵያ ትልቁ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ፕሮጀክት፣ ከባንኩ በሚገኘው የፋይናንስ ድጋፍ ከሚከናወኑት ውስጥ 80 ሚሊዮን ዶላር ከባንኩ፣ 20 ሚሊዮን ዶላር ከንጹህ ቴክኖሎጂ ፈንድ፣ እንዲሁም 10 ሚሊዮን ዶላር ከዘላቂ ኢነርጂ ለአፍሪካ ፈንድ የተገኘ ነው።

ባንኩ ከሌሎች የልማት ፋይናንስ ተቋማት ተጨማሪ 381 ሚሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ለማሰባሰብም አቅዷል። የፋይናንስ ፓኬጁ የአምስት ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታን እና ነባሩን የአይሻ ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያን የማሻሻል ስራን ይደግፋል።

በጠቅላላው 508 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ የተገመተው ይህ ፕሮጀክት፣ በዓመት ወደ 1,189 ጊጋ ዋት ሰዓት ንጹህ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። እንደ ባንኩ ገለጻ፣ ፕሮጀክቱ በ25 ዓመቱ የአገልግሎት ዘመኑ ወደ 1.39 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የካርቦን ልቀትን ለመከላከል እና በግንባታው ወቅት እስከ 1,525 ቀጥተኛ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያስችላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍6🤣2
"ኦሮሚያ ክልል 'ጠፍቶ' ለማየት የሚመኙ አሉ፤ ምኞታቸው ግን በፍጹም አይሳካም" አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኦሮሚያ ክልል "ጠፍቶ" ለማየት የሚመኙና "ኦሮሚያ" የሚለውን ቃል መስማት የማይፈልጉ አካላት እንዳሉ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በአዳማ ከተማ በተካሄደ የመንግሥት አመራሮች መድረክ ላይ ርዕሰ መሥተዳድሩ በኦሮምኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር፣ ይህ ምኞት "በፍጹም" ሊሳካ እንደማይችልና ክልሉ ይበልጥ እየጠነከረና ውጤታማ እየሆነ እንደሚሄድ አረጋግጠዋል።

አቶ ሽመልስ የእነዚህን አካላት ማንነት በስም ባይጠቅሱም፣ ንግግሩን ያደረጉት የክልሎች አወቃቀር ጉዳይ ለአገራዊ ምክክር ጉባኤ በአጀንዳነት በቀረበ ማግስት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣4512👍8🤪5🥰3🙉2🤷‍♂1🙊1
አራት ኪሎ መሄድ አይጠበቅብንም‼️
"ጠላቶቻችንን ለመጣል የግድ አራት ኪሎ መሄድ አይጠበቅብንም" ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ‼️

"እኛ ካሁን በኋላ አዲስአበባ የመሄድ ፍላጎት (ወይም አባዜ) የለንም ፤ አዋሳ የመሄድ አባዜም የለንም።የኛ አላማ ሉዓላዊነታችንን ማስከበር ነው።

የኛ አላማ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብታችንን መልሰን ወደ እጃችን  ማስገባት(ማስመለስ) ነው።ይሄንን እንዳናደርግ ያነቀንን (እንቅፋት የሆነብንን) ጠላት የግድ መጣል አለብን።

ይሄንን ጠላት ለመጣል የግድ አራት ኪሎ መሄድ አይጠበቅብንም።ታዲያ እንዴት እንጣለው ? ለሚለው ....ይሄንን ጠላት አፈር ድሜ ለማብላት ከወዲሁ ስራዎችን እንደምንሰራ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል ፤ ለዚህ ተልዕኮም ራሳችንን አብቅተን መዘጋጀት አለብን።እነዚህን ጠላቶች ካላስወገድን ሰላም አናገኝም" ሲሉ ከህወሓት ጄኔራሎች ውስጥ አንዱ የሆኑት ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23🤪20👍4🤣2🤯1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካ የኢራንን ድልድዮች ማጥቃት ጀመረች‼️
አሜሪካ የኢራንን ዋና ድልድዮች እንዲሁም የውሃ ማጣሪያ ተቋሟት ላይ ጥቃት በመፈፀም ጉዳት አድርሳለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11😢10👍7😡4🤩1
#ስለህግ #የህግመረጃ

በዕርቅ_ማለቅ_የሚችሉ_የወንጀል_አይነቶች!

በወንጀል ጉዳዮች እርቅ የሚከናወነው በልዩ ሁኔታ ነው፡፡ምክንያቱም በመርህ ደረጃ ወንጀል የህዝብን እና የመንግስትን ጥቅም የሚጉዳ ተግባር ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡

👉ክስም የሚቀርበው መንግስት በወከለው ዐቃቤ ህግ ሲሆን ሙሉ ወጪውም የሚሸፈናው በመንግስት ይሆናል፡፡ስለሆነም በወንጀል ህጎች ስር በእርቅ ማለቅ የሚችሉ ገዳዮች በግልፅ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡

ለአብነት ለመጥቀስ ያክል ፡-
1. ታስቦ የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ 556(1)፣
2. በቸልተኝነት የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ-559(3))፣
3. የእጅ እልፊት (አንቀጽ-560(1)) ፣
4. የዛቻ ወንጀል (አንቀጽ-580) ፣
5. አመንዝራነት (አንቀጽ-652) ፣
6. የሥድብ እና ማዋረድ (አንቀጽ-615) ፣
7. የስም ማጥፋት ወንጀል (አንቀጽ-618) ፣
8. በቤተዘመድ ንብረት ላይ የተፈጸመ ንብረት ነክ ወንጀል (አንቀጽ-664)
9. ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም(አንቀጽ-646)፣
10. ቀለብ የመስጠት ግዴታን ያለመወጣት(አንቀጽ-558)፣
11. በሌላ ሰው ሀብት ያለአግባብ መጠቀም(አንቀጽ-678)፣
12. አግኝቶ መደበቅ(አንቀጽ-679)፣
13. በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ(አንቀጽ-686)፣
14. በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ(አንቀጽ-689)…ወዘተ ይገኙበታል፡፡

ወንጀሉ የፈጸመው ሰው ቀደም ሲል ተመሳሳይ ወንጀል የፈጸመ ከሆነ ፣ በሕጻናት ወይም በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የተፈጸመ ከሆነ​ተጎጂው በሕግ ፊት የመወሰን አቅም የሌለው ከሆነ እርቅ ላይሰራ ይችላል።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍7🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢራን ሚሴኤሎች ኢላማቸውን መቱ‼️
ኢራን በጆርዳን በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ በቀጥታ ጥቃት ስትፈፅም የሚያሳይ ምስል ይፋ አድርጋለች።
በዚህ ጥቃት በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ቅንጡ የሆነውን Hawk helicopter (21million dollar) ማውደሟን፣በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ገልፃለች።
ለዚህ ኢላማውን ለጠበቀ ጥቃት አሜሪካ ራሺያን እና ቻይናን እየወቀሰች ትገኛለች።
አሜሪካም በሆርሙዝ ዳርቻ በሚገኘው የኢራን ነዳጅ ማከማቻ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ማድረሱን ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍6
የዝንጀሮ መንጋ ግድያ‼️
በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ያለው የዝንጀሮ መንጋ አርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪውን ዕለታዊ እንቅስቃሴ እያወከ በመሆኑ ቁጥሩን ለመቀነስ 10/11/2018 ዓ/ም ጀምሮ እርምጃ ስለሚወሰድ ነዋሪው በጥይት ተኩስ ድምፅ እንዳይደናገር የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ጽ/ቤት አሳስቧል።
የመግለጫው ርዕስ፦ጉዳዩ፡- የሰዉና የዝንጀሮ ግጭትን ይመለከታል።

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የሚኖሩ የዝንጀሮ መንጋዎች በአርባ ምንጭ ከተማ ማለትም በቴሌቪዥን ሰፈር፤ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፤ በአርባ ምንጭ አየር ማረፊያ እና በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደጋጋሚ ግጭቶች የፈጠሩ መሆናቸው ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ የቴሌቪዥን ሰፈር ነዋሪዎች በዝንጀሮ መንጋው የደረሰባቸውን ጉዳት በመጥቀስ ተቋማችን ከሰዉ የፍርድ ቤት አፈፃፀም ውሳኔ ደርሶን ቆይቷል።

ስለሆነም ከቀን 10/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተጠና መንገድ የዝንጀሮ ቅነሳ ስራውን ስለምንጀምር የአካባቢው ማህበረሰብ የጥይት ድምፅ ሰምቶ ድንጋጤ ውስጥ እንዳይገባ ጉዳዩ የሚመለከተው ተቋም ለአካባቢው ማህበረሰብ የማሳወቅና ለተግባራዊነቱም ትብብር እንድታደርጉልን በትህትና እንጠይቃለን።"ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1810👍5😡2
ወታደራዊ አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️
በትግራይ ክልል በዛሬው ዕለት ከአዲጉዶም (ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ መውጫ ላይ) ወደ ሂንታሎ ሲሄዱ የነበሩ ወጣቶች ከመኪና ላይ በግዳጅ ተወስደዋል።
(የዓይን እማኝ መረጃ)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8😢7👍6
አሳዛኝ አደጋ:-  የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼️

በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ ዛሬ ንጋት ላይ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በ3 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።

አደጋው የተከሰተው በአንድ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና በአይሱዙ ጭነት መኪና መካከል በተፈጠረ ግጭት መሆኑን የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል። የአደጋው መንስኤ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ እየተጣራ ይገኛል።

የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሐመድ በአደጋው ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለጹ ሲሆን፣ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናት ተመኝተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5😢4👍2
ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የአመራር ሹመት መምሪያ ይፈ አደረገ‼️

ትምህርት ሚኒስቴር በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሾሙ ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች አሰያየምን የሚገዛ አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል።

መመሪያው በብቃትና በውድድር ላይ የተመሰረተ አሰራርን ለማስፈን ያለመ ሲሆን፣የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የአንድ ጊዜ የስራ ዘመን 6 ዓመት እና የምክትል ፕሬዝዳንቶች 4 ዓመት መሆኑ ተነግሯል።

በማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ ሁለት ጊዜ በፕሬዝዳንትነት ያገለገለ አመራር በድጋሚ መወዳደር እንደማይችልም ተገልጿል።

ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ወንድ እጩዎች ቢያንስ የረዳት ፕሮፌሰርነትና ከዚያ በላይ ማዕረግ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን፣ቢያንስ 2 ዓመት በፕሬዝዳንትነት ወይም 3 ዓመት በምክትል ፕሬዝዳንትነት/ዲንነት ያገለገሉ መሆን እንደለባቸው ገልጿል።

አመራሩ በየ 3 ወሩ በቦርዱ የሚገመገም መሆኑ እና ። ውጤቱ በሁለት ተከታታይ የስድስት ወር ግምገማዎች ከ60% በታች ከሆነ፣ በጤና እክል ወይም በዲሲፕሊን ጉድለት ከሃላፊነቱ እንዲነሳ ለሚኒስቴሩ ሀሳብ ይቀርባል ተብሏል።

በምልመላና ምርጫ ሂደቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተወዳዳሪ፣ ውጤቱ በይፋ በተገለጠ በ10 ቀናት ውስጥ ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ቅሬታውን ማቅረብ እንደሚችል አረጋግጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪65👍2
በአሜሪካ የኢትዮጵያ የፀሐይ ኃይል ምርቶች ላይ ምርመራ ተጀመረ

የአሜሪካ ንግድ መምሪያ በኢትዮጵያ የሚመረቱ የፀሐይ ኃይል ምርቶች፣ በቻይና ላይ የተጣለውን የንግድ ታሪፍ ለመሸሽ የሚረዱ መሆናቸውን ለማጣራት ምርመራ ሊጀምር ነው። ይህ እርምጃ የተወሰደው የቻይና አምራቾች ኢትዮጵያን ተጠቅመው የአሜሪካን የንግድ ቀረጥ  ለመሻገር እየሞከሩ ነው በሚል ስምንት የአሜሪካ ኩባንያዎች ባቀረቡት አቤቱታ ነው።

ከ2025 አጋማሽ ወዲህ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኢትዮጵያ የፀሐይ ኃይል ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ማደጋቸው ለዚህ ምርመራ መነሻ ሆኗል። የአሜሪካ ንግድ መምሪያ የመጀመሪያ ደረጃ ውሳኔውን በታኅሣሥ 2026፣ የመጨረሻውን ደግሞ በግንቦት 2027 እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4😢2😡1
"ኔታንያሁ ኒዮርክ ከተማ ከገቡ ይታሰራሉ" - ከንቲባ ማምዳኒ

የኒዮርክ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የወጣውን የእስር ትዕዛዝ ተግባራዊ አደርጋለሁ አሉ።

ዓለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) እስራኤል በጋዛ ጦርነት የጦር ወንጀል ፈፅማለች በሚል በኔታንያሁና ሌሎች ሁለት ባለስልጣናት ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱ ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ ሳምንት ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመወያየት ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ።

ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያም ኔታንያሁ በሚመሯት የኒዮርክ ከተማ ከገቡ እንደሚታሰሩ ተናግረዋል።

"በጉዳዩ ዙሪያ እየተወያየን ነው፤ ግን ህግ እንደ አዲስ አይፃፍም" ሲሉ አይሲሲ ያወጣውን መመሪያ እንደሚተገብሩ ጠቁመዋል።

"በኒውዮርክ እስካለው ድረስ የከተማ ህግ አድርገው ብሎ የሚፈቅድልኝን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ" ብለዋል። ማምዳኒ "ኔታንያሁ የጦር ወንጀል ፈፅመዋል ብየ አምናለሁ"ሲሉ ገልጸዋል።

"እሱ ባለፉት አመታት በሰራቸው ወንጀሎች መቅረብ ያለበት ሄግ በሚገኘው ፍርድቤት ነው" ብለዋል። ከንቲባ ማምዳኒ ወደ ኃላፊነት እንደመጡ ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ኔታንያሁ ከማምዳኒ ሹመት በኋላ ወደ አሜሪካ ቢያቀኑም ኒዮርክ ከተማ ግን አልገቡም።

ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከንቲባው ወደ ሚያስተዳድሯት ኒዮርክ የሚገቡት በመጪው መስከረም ወር በሚካሄደው የተመድ አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ነው።  

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤪14🤣4👍3🤷‍♂2😢1🙊1
የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል-ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል‼️
ዛሬ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም በመቀሌ ህዝቡን እና አመራሩን ሰብስበው አወያይተዋል።
የትግራይ ህዝብ ጭቆናን የመሸከም ታሪክ የለውም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፤ ይልቁንም መብቶቹ ለማረጋገጥ በመደራጀት ታግሏል፣ መብቶቹን አስከብሯል እንዲሁም የሌሎች ብሔረሰቦችን መብቶች አክብሮ የመጣ ህዝብ ነው ብለዋል።

ለ17 ዓመታት በተደረገው የትጥቅ ትግል ውስጥ የትግራይ ህዝብ ከባድ መስዋእትነት በመክፈል አንባገነኑ የደርግ ስርዓት መደምሰሱን ያወሱት ዶክተር ደብረፅዮን፤ በአንባገነኑ መቃብር በሃገር ደረጃ ሰላም፣ ልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ማረጋገጡን ጠቅሷል፡፡

ሆኖም፣ ይህንን መቀበል ያልቻሉ ሐይሎች ጊዜና አጋጣሚውን በመጠበቅ፣ የትግራይን ህዝብ ከምድረገፅ ለማጥፋት በህዝባችን ላይ ጀኖሳይድ ፈፅሟል ያሉት ፕረዝዳንቱ፤  የትግራይ ህዝብ አንድነቱ በመጠበቅ ልህልውናው በከፈለው መስዋዕትነት ጭቆናን እና ህልውናውን ለማጥፋት ለመጣው ሐይል የማይቀበል መሆኑ በዓለም አደባባይ ያስመሰከረ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡ 

የፕሪቶሪያው ስምምነት ሲፈረም፤ የትግራይ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ፣ ተፈናቃዮችን ለመመለስ እና ልማትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ተስፋ አድርገን ነበረ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፤የፌደራል መንግሥቱ በታቀደ ሁኔታ ትግራይን ዳግም ወደ ከበባና ክልከላ በማስገባት ለዳግም ጀኖሳይድ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡

እንደ ትግራይ፣ ለሰላም ስንል ከፍተኛ ትዕግስትና መስዋዕትነት እየከፈልን ነው፤ ይሁን እኛ ብቻ ሰላም ስለ ፈለግን ሊሳካልን አልቻለም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ አንድነታችን አጠናክረን የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄዎች ማረጋገጥ ብቸኛ መፍትሔ ሆኖ መገኘቱ ተናግሯል፡፡

አሁን ባለንበት ሁኔታ መቀጠል አንችልም ያሉ ሲሆን እንደህዝብ የመከተ ዓቅሞቻችን በማደራጀት ህልውናችን ለማረጋገጥ በምንወስንበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡
የፌደራል መንግስቱ ለሰላም በፍጹም ዝግጁ አይደለም፤ ስለዚህ ብሔራዊ ክብራችንና ሉዓላዊነታችንን ለመመለስ እንዲሁም የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም ትግላችንን ወደ ተጨባጭና ውጤታማ ደረጃ ማሸጋገር ይገባናል ብሏል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤣8👍3🫡2🕊1🤪1😎1
መንግስት አዲስ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ታክስ ሊጥል ነው

​መንግስት በ2020 በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ታክስ ለመጣል እየተዘጋጀ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የህግ ረቂቁን በታህሳስ ወር መጨረሻ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርብ ካፒታል ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል ።ታክሱ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እስከ 0.2 በመቶ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🤔13👍3👀3😢2🤪2🙊2🤷‍♂1🤣1
65 የመንግስት ኤጀንሲዎች የቦርድ አባላት በሙሉ ከስልጣን ተነሱ

የኬንያ መንግስት በሀገሪቱ የህዝብ ተቋማት ውስጥ የነበረውን የፖለቲካ ተፅዕኖ ለመቀነስ በሚል በ65 የመንግስት ኤጀንሲዎች ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ የቦርድ አባላትን በሙሉ በይፋ ማሰናበቱን አስታውቋል። ይህ እርምጃ የተወሰደው በቅርቡ ተግባራዊ በሆነው የ2025 የመንግስት ድርጅቶች ህግ (GOE Act) መሰረት መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ ለውጥ የመንግስት ድርጅቶችን አሰራር ሙያዊ እና ግልጽ ለማድረግ ያለመ ነዉ የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል የቦርድ አባልነት ለፖለቲካዊ ሹመት ሲውል እንደነበርና ይህም ለሙስና እና ለቅልጥፍና ማጣት መንስኤ ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል።

አዲሱ ህግ ለቦርድ አባልነት የሚወዳደሩ ሰዎች ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በንቃት በፖለቲካ ስራ ውስጥ መሳተፍ እንደሌለባቸው ይደነግጋል። ቦርዶቹም በግልፅ እና በውድድር ሂደት በሚመረጡ ባለሙያዎች እንዲዋቀሩ ይደረጋል።

የቦርድ አባላቱ በሶስት ዓመት የስራ ዘመን የሚያገለግሉ ሲሆን፣ በድጋሚ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሊመረጡ ይችላሉ ተብሏል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ይህ ለውጥ የመንግስት ተቋማትን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ በማውጣት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2🤣1
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራ እና ሶማሊያ አቻዎቻቸው ጋር በቀጣናዊ  ትብብር ዙሪያ ውይይት አደረጉ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

🇪🇬 ዛሬ ዕሑድ በካይሮ በተለያዩ መድረኮች በተደረጉ ስብሰባዎች፣ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ከኤርትራ አቻቸው ኡስማን ሳሌህ እና ከሶማሊያ አቻቸው አብዱሰላም አብዲ አሊ ጋር መወያየታቸውን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ስብሰባዎቹ የሁለትዮሽ ግንኙነትን፣ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ማጠናከር እና በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቅንጅት መሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንደተደረገባቸው ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18😡4👍2🤣2
ስፔን አርጀንቲናን በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች
***

የ2026 ዓለም ዋንጫ ዛሬ ፍጻሜውን ሲያገኘ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። 120 ደቂቃ በወሰደው ፍጻሜ ተቀይሮ የገባው ፌራን ቶሬስ የስፔንን ግብ አስቆጥሯል።

በአርጀንቲና በኩል መደበኛ 90 ደቂቃው መጠናቀቂያ ላይ የቼልሲው አማካይ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ፓው ኩባርሲ ላይ በሰራው ጥፋ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

የ2010 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ ስፔን በታሪኳ ለ2ኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያነሳችበት ሆኗል።

አርጀንቲና የዓለም ዋንጫን ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ ለመውሰድ ለፍጻሜ ብትደርስም ሳይሳካላት ቀርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28👍9🤪3🤷‍♂1🥰1😢1🎉1👌1😎1
ታክስ ሊጣል ነው‼️
መንግስት በአዲስ የተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ ታክስ ሊጥል ነው‼️
​መንግስት በ2020 በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ታክስ ለመጣል እየተዘጋጀ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የህግ ረቂቁን በታህሳስ ወር መጨረሻ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርብ
ታውቋል።
ታክሱ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እስከ 0.2 በመቶ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢125👍2🤔2🤯1