አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
416 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአንድ መስኮት አገልግሎት በኩል እንዲያገኙ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡

ባንኩ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዲስ ፍቃድ ላወጡ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር አሰጣጥን የሚያቀል አዲስ የዲጂታል አገልግሎት አስተዋውቋል፡፡

አገልግሎቱ የባንኩ የሂሳብ ቁጥሮች በጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል ያለምንም ውጣ ውረድ እንዲሰጥ በማስቻል አስተዳደራዊ ሂደቶችን የሚቀንስና ፈጣን የንግድ አሰራርን የሚደግፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

አዲሱ አገልግሎት የሚመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ለሚያወጡና አዲስ ፍቃድ ላገኙ አስመጪዎችና ላኪዎች ብቻ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማት ለሁሉም የገቢና የወጪንግድ ግብይቶቻቸው ይጠቀሙበት በነበረው ነባር ቁጥር መጠቀም እንደሚችሉ ባንኩ ገልጿል፡፡

ይህ አሰራር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከገቢና ወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የንግድ አሰራርን ምቹ ለማድረግ እንዲሁም የዲጂታል የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር እያከናወነ ያለው ጥረት አካል መሆኑንም አመልክቷል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3
በቀን 3 ቴምር መብላት  ለአእምሮ ጥንካሬና ከአልዛይመር ለመከላከል ፍቱን መፍትሔ _ጥናት‼️

​በሎማ ሊንዳ ዩኒቨርሲቲ (ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ) ተመራማሪዎች የተጠናና በቅርቡ ‘ጆርናል ኦፍ ኒውትሪሽን’  ላይ የታተመ ጥናት እንደሚያመለክተው  በቀን ሦስት ቴምር መመገብ ለአእምሮ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ከመሆኑም በላይ የትርሳን (የአልዛይመር) በሽታ የመያዝ ተጋላጭነትን በእጅጉ ይቀንሳል።

ቴምር የአእምሮ ሴሎችን ከጉዳት የሚጠብቁና እብጠትን የሚከላከሉ እንደ ፍላቮኖይድስ እና ፌኖሊክ አሲድ ያሉ አንቲኦክሲዳንቶች እንዲሁም በርካታ ጠቃሚ ቪታሚኖች በውስጡ ይዟል።

​በሳይንሳዊ ምርምሮች መሠረት፣ ቴምር በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩትንና ለአልዛይመር በሽታ መከሰት ዋነኛ መንስኤ የሆኑትን የ"አሚሎይድ ፕላኮች" (amyloid plaques) ክምችት የመከላከል ከፍተኛ አቅም አለው።

​ሆኖም ግን ቴምር ከፍተኛ የካሎሪና የስኳር መጠን ስላለው (በ100 ግራም ውስጥ ወደ 66 ግራም ስኳር ይገኛል)፣ በተለይ የስኳር ህመምተኞች እና የጨጓራ ወይም የአንጀት ችግር ያለባቸው ሰዎች በሚመገቡበት ጊዜ መጠን ማወቅና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ምሁራን ያሳስባሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍11💊1
ነገ በአዲስ አበባ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ‼️

ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ”አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል።

ሰልፉ ተጀምሮ  እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዚህም መሰረት:-
👉 ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
👉 በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
👉 ከጎተራ  ወደ መስቀል አደባባይ  ለከባድ ተሽከርካሪ  አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት
👉 ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ
👉 ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት
👉ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ
👉ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ  ዝግ ይሆናሉ።

ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5😡4🤔2🤪1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
👍5
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
''አዳዲስ ቀረጦች ሊጣሉ ነው‼️
በነዳጅ፣ በሪል እስቴት፣ በአልኮልና በትምባሆ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ታክስ ነፃ መብቶች ላይ አዳዲስ ቀረጦች ሊጣሉ መሆኑ ተሰምቷል።

IMF እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት 5 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ብድር ለማግኘት ሲል እነዚህን ሰፊ የታክስ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል። ይህ የሆነው የብድሩ ቅድመ ሁኔታ የሀገሪቱን የውስጥ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ስለሚጠይቅ እንደሆነም ተብራርቷል።

በዚህም መሠረት የነዳጅ ድጎማው ሙሉ በሙሉ ተነስቶ ዋጋው በገበያ እንዲወሰን የሚደረግ ሲሆን፣ በሪል እስቴት፣ በመኪና ባለቤትነት እና በተለያዩ ምርቶች ላይ አዳዲስ ቀረጦች የሚጣሉ ይሆናል ተብሏል።

• ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአንድ ወቅት የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (IMF) ብድር ቀላልነት ሲገልጹ «ከአይ.ኤም.ኤፍ መበደር ከእናት መቀነት እንደ መፍታት ነው...» ማለታቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ የዚያ "ቀላል" ብድር ዋጋና ቅድመ-ሁኔታዎች በዜጎች ኪስ ላይ እየፈጠሩት ያለው ጫና ቀላል አለመሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።

በየጊዜው የሚጨመሩ ታክሶች፣ አዳዲስ ቀረጦች እና የዋጋ ንረቱ «ለመሆኑ ለብድር ተብሎ በሕዝብ ላይ ታክስ መጫን ተለመደ እንዴ?» የሚል ጥያቄ አስነስቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ እየተተገበሩ ያሉ የፖሊሲ ለውጦች (የኤክሳይዝ ታክስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማሻሻያዎች እና የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪዎች) ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ ክፉኛ እየፈተኑት ይገኛሉ።

ከውጭ ምንዛሬ ተመን መለቀቅ ጋር ተዳምሮ የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። መንግስት ገቢውን ለማሳደግ ታክስ ያልነካቸውን ዘርፎች ሁሉ ወደ ታክስ መረቡ ለማስገባት የሚያደርገው ጥረት በንግዱ ማህበረሰብና በሸማቹ ላይ ድርብ ጫና ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1812👍6😱2🤯1🤪1
#ሰበር ዜና

በዶናልድ ትራምፕ እና በቤንያሚን ኔታንያሁ መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጠረ!

የግጭቱ መነሻ ምንድን ነው?ኔታንያሁ አሜሪካ ዘመናዊ የኤፍ-35 (F-35) ተዋጊ ጄቶችን ለቱርክ ለመሸጥ ወይም ሀገሪቱን በድጋሚ በፕሮግራሙ ውስጥ ለማካተት ያቀደችውን ስምምነት በይፋ መቃወማቸውን ተከትሎ ነው።

ኔታንያሁ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ቱርክ በፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ስር "አስተማማኝ አጋር" አይደለችም በማለት፣ ይህ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የሃይል ሚዛን ያናጋል ሲሉ ዋሽንግተንን አሳስበዋል።

ይህ የኔታንያሁ ይፋዊ ጣልቃ ገብነት በዋይት ሀውስ ውስጥ ከፍተኛ ብስጭት ቀስቅሷል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኔታንያሁ በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውሳኔ ላይ ጣልቃ የመግባት "ምንም መብት የላቸውም" በሚል ክፉኛ መቆጣታቸው ተገልጿል።

የታቀደው ስብሰባ ተሰረዘ?ውጥረቱን ለማርገብ በዋይት ሀውስ ኦቫል ኦፊስ (Oval Office) ይደረጋል ተብሎ ታስቦ የነበረው ፈጣን ስብሰባ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።

የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ስብሰባው ሊካሄድ እንደነበር ቢዘግቡም፣ የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት ግን ለኔታንያሁ የተያዘ ምንም ዓይነት ይፋዊ ቀጠሮ እንዳልነበረና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ስብሰባውን በራሳቸው ፍላጎት ብቻ ለመፍጠር እየሞከሩ እንደነበር ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍6🤔1
መረጃ‼️

ኢትዮጵያ የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውሎት ትብብር ድርጅት መስራች አባል ኾነች። የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውሎት ትብብር ድርጅትን የመመስረቻ  ስምምነት ትናንት ቻይና ሻንጋይ ከተማ ውስጥ በተፈረመበት ወቅት ኢትዮጵያ ከፈራሚዎቹ 29 አገራት አንዷ ኾናለች።

የድርጅቱን የመመስረቻ ስምምነት ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ደቡብ አፍሪካን እና አልጀሪያን ጨምሮ 10 የአፍሪካ አገራት ፈርመውታል።

ዋና መስሪያ ቤቱን ሻንጋይ የሚያደርገው ዓለማቀፉ ድርጅት ዓላማው፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዙሪያ አገራት እንዲተባበሩና ዓለማቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አስተዳደር እንዲኖር ማስቻል ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20🤪9👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች ተጎዱ‼️
ኢራን ጆርዳን በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ ወታደሮች መጎዳታቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳረጋገጡለት ነገር ግን ቁጥሮቹን ለመግለፅ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ CBS ዘግቧል።
አሜሪካ እና ኢራን ከባድ የተኩስ ልውውጥ ውስጥ ሲሆኑ አሜሪካ የኢራንን መሰረተ ልማት እና ድልድዮችን እያጠቃች ትገኛለች።
የኢራን ዋና የኤሌክትሪክ መስመር ጉዳት ያስተናገደ ሲሆን የቴህራን ዜጎች ኤሌክትሪክ ቆጥበው እንዲጠቀሙ ኢራን ለዜጎቿ መልዕክት አስተላልፋለች።
ኢራን በባህሬን እና ኩዬት የሚሳኤል ጥቃቷን የቀጠለች ሲሆን ኩዬት ለኢራን ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ማቀዷን በመግለፅ ለዜጎቿ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፋለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍7
#ጤናመረጃ

የሀበሻ ጎመን ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች!

​የሀበሻ ጎመን በቪታሚኖች (C, A, K) በማዕድናት (ካልሲየም፣ ብረት) እና በፀረ-ኦክሲዳንት ንጥረ ነገሮች እጅግ የበለፀገ ነው።

1. ለአጥንት ጥንካሬና ጤንነት፦ የሀበሻ ጎመን እጅግ ከፍተኛ የካልሲየም (Calcium) እና የቪታሚን ኬ (Vitamin K) ይዘት ስላለው፣ ለአጥንት መገንባት፣ ለጥንካሬ እና የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል አስተዋጽኦ አለው።

2. በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር፦ በውስጡ ባለው ከፍተኛ የቪታሚን ሲ መጠን ምክንያት፣ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓት በማገዝ ከኢንፌክሽኖች እና ከተለያዩ በሽታዎች ይጠብቃል።

3. የደም ማነስን ለመከላከል፦ ጎመን በውስጡ ከፍተኛ የiron ማዕድን ይዟል። ይህም የሰውነታችንን ቀይ የደም ሴል ምርት በማገዝ የደም ማነስ ችግር እንዳይከሰት ትልቅ እገዛ ያደርጋል።

4. ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፦ ልክ እንደ ጥቅል ጎመን ሁሉ፣ የሀበሻ ጎመንም ከፍተኛ የፋይበር (የቃጫ) ይዘት ስላለው የሆድ ድርቀትን ለመከላከል እና የአንጀትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል።

5. ለአይን ጤንነትና እይታ፦ በአይን ላይ የሚመጡ የዕድሜ መግፋት ጉዳቶችን እና ሌሎች የዓይን በሽታዎችን የመከላከል አቅም ያላቸውን ሉቲን እና ቪታሚን ኤ በበቂ መጠን ይዟል።

6.ለቆዳና ለፀጉር ውበት፦ በውስጡ የሚገኙት ቪታሚኖች (A,C,E) እና ፀረ-ኦክሲዳንቶች ለቆዳ ጤንነት፣ ለወጣትነት ገጽታ እና ለፀጉር ጥንካሬ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

ጠቃሚ ምክር :- የሀበሻ ጎመንን ከመጠን በላይ ሳያበስሉ (ሳይሞት) በመጠኑ አብስሎ መመገብ በውስጡ ያሉትን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ለማግኘት ይረዳል።(ኢትዮ-መረጃ)

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍6
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
" ጄኔራሉ በቁም እስር ላይ እንዳሉ ተሰማ‼️
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት የተቋቋመውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን በፕሬዝዳንትነት የመሩት ሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከሥልጣን ከተነሱ በኋላ ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ ትግርኛ መረጃ የሰጡ የቅርብ ሰዎቻቸው እንደሚሉት፤ ጄኔራሉ በተግባር " በቁም እስር " ላይ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከትላንት በስቲያ ወደ መቐለ ባቀኑበት ወቅት ከሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው ነበር።

ይህ ቀጠሮ ከዚህ ቀደም ተሰርዞ የነበረ ቢሆንም፣ በዚህ ሳምንት ረቡዕ ሁለተኛ ሙከራ ተደርጎ ነው።

" የትናንቱ ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ 'ይገናኛሉ' የሚል ተስፋ ነበረን። ቀጠሮው ከቀኑ 5 ሰዓት ነበር፤ እሳቸውም ቀጠሮ እንዳላቸው ያውቁ ነበር " ይላሉ የጄኔራሉ የቅርብ ሰው።

ነገር ግን ቀጠሮው ሊደርስ አንድ ሰዓት ብቻ ሲቀረው (ከቀኑ 4 ሰዓት ገደማ) ከቪአይፒ (VIP) ጥበቃ ኃላፊ በተደወለ ስልክ ሁኔታዎች ሁሉ ተቀየሩ።

ለጄኔራሉ ጥበቃ፣ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች የተላለፈው አስቸኳይ መመሪያ ፦

" ምንም ዓይነት አጀባ አታድርጉ፤ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አታካሂዱ፤ ተሽከርካሪዎች አይንቀሳቀሱ፤ ይህንም ለራሱ [ለጄኔራል ታደሰ] አሳውቁት። ይህ ትዕዛዝ ከተላለፈ በኋላ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ብታደርጉ ሊያስቆማችሁ የሚችል ሌላ ኃይል አለ። ስለዚህ ምንም ችግር እንዳይፈጠር ማንኛውንም ዓይነት እንቅስቃሴ አታድርጉ " የሚል ነበር።

የጥበቃ ኃላፊው ይህን ትዕዛዝ ሲያስታውቋቸው ጄኔራል ታደሰ ወረደ ድርጊቱን እንዳልተቀበሉት እና " እኔ ራሴ መኪና ነድቼ እሄዳለሁ! " ማለታቸውን የቅርብ ሰዎቻቸው ገልጸዋል።

ይህ አቋማቸው በቤተሰቦቻቸው እና ጥበቃዎቻቸው ላይ ትልቅ ስጋት በመፍጠሩ፣ የቅርብ ሰዎቻቸው " እባክህ ተወው፤ ባለው ሁኔታ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም " በማለት እንደለመኗቸውና ከቤት እንዳይወጡ እንዳደረጓቸው ተናግረዋል።

በኋላም ጄኔራሉ በስልክ ከአሜሪካው አምባሳደር ጋር እንደተነጋገሩና የስጋቱን ሁኔታ እንዳስረዱ ፤ ለ20 ደቂቃ ያህል ውይይት እንዳደረጉ አመልክተዋል። የስልክ ውይይቱ ዝርዝር ይዘት ግን አልታወቀም።

አምባሳደር ማሲንጋ ከሌሎች የክልሉ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተው ቢመለሱም፣ የጄኔራሉ ሁኔታ ግን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው አንድ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጭ ገልጸዋል።

" ይህ ክስተት አንድ ክልል ሲመሩ የነበሩ ጄነራል የመናገር፣ ሰዎችን የማግኘት እና የመንቀሳቀስ መብታቸው በተግባር እንደታገደ ያሳያል። ቢወጡ ኖሮስ ምን ያጋጥማቸው ነበር? " ሲሉ ጥያቄ ሰንዝረዋል።

ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከሥልጣን ከተነሱ ከሚያዚያ 30 በኋላ ፦
- ወደ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ሄደው እንደማያውቁ፣
- ከስልጣን ካነሷቸው ከነ ደብረጽዮን  ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) አስተዳደር ጋር ምንም ግኑኝነት እንደሌላቸው ... የቅርብ ሰዎቻቸው ገልጸዋል።

አብዛኛውን ጊዜያቸውን ቤት ውስጥ መጻሕፍት በማንበብ እያሳለፉ ቢሆንም አልፎ አልፎ ቤታቸው አጠገብ ወዳለ ቢሯቸው ይሄዳሉ።

ቢሯቸው አንዳንዴ ጊዜም ፕላኔት ሆቴል ሰዎችን ያገኙ የነበረ ሲሆን ይህ የሚሆነው በባለስልጣናት ፍቃትና በደህንነት ቁጥጥር ስር ሆነው ነው።

አሁን ላይ ጥበቃቸው እየተቀነሰ እና የመንቀሳቀስ ነፃነታቸው ሙሉ በሙሉ እየተገደበ መሆኑን የገለጹት የቅርብ ሰዎቻቸው " ከረቡዕ በኋላ በቁም እስር ላይ እንዳሉ ነው የተሰማን " ሲሉ ደምድመዋል።
ቢቢሲ ትግርኛ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5😢1
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ትልቁ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 110 ሚሊዮን ዶላር አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ በሶማሌ ክልል ለሚገነባውና 300 ሜጋ ዋት አቅም ለሚኖረው የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 110 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ።

ሲጠናቀቅ በኢትዮጵያ ትልቁ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ፕሮጀክት፣ ከባንኩ በሚገኘው የፋይናንስ ድጋፍ ከሚከናወኑት ውስጥ 80 ሚሊዮን ዶላር ከባንኩ፣ 20 ሚሊዮን ዶላር ከንጹህ ቴክኖሎጂ ፈንድ፣ እንዲሁም 10 ሚሊዮን ዶላር ከዘላቂ ኢነርጂ ለአፍሪካ ፈንድ የተገኘ ነው።

ባንኩ ከሌሎች የልማት ፋይናንስ ተቋማት ተጨማሪ 381 ሚሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ለማሰባሰብም አቅዷል። የፋይናንስ ፓኬጁ የአምስት ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታን እና ነባሩን የአይሻ ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያን የማሻሻል ስራን ይደግፋል።

በጠቅላላው 508 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ የተገመተው ይህ ፕሮጀክት፣ በዓመት ወደ 1,189 ጊጋ ዋት ሰዓት ንጹህ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። እንደ ባንኩ ገለጻ፣ ፕሮጀክቱ በ25 ዓመቱ የአገልግሎት ዘመኑ ወደ 1.39 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የካርቦን ልቀትን ለመከላከል እና በግንባታው ወቅት እስከ 1,525 ቀጥተኛ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያስችላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍6🤣2
"ኦሮሚያ ክልል 'ጠፍቶ' ለማየት የሚመኙ አሉ፤ ምኞታቸው ግን በፍጹም አይሳካም" አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኦሮሚያ ክልል "ጠፍቶ" ለማየት የሚመኙና "ኦሮሚያ" የሚለውን ቃል መስማት የማይፈልጉ አካላት እንዳሉ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በአዳማ ከተማ በተካሄደ የመንግሥት አመራሮች መድረክ ላይ ርዕሰ መሥተዳድሩ በኦሮምኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር፣ ይህ ምኞት "በፍጹም" ሊሳካ እንደማይችልና ክልሉ ይበልጥ እየጠነከረና ውጤታማ እየሆነ እንደሚሄድ አረጋግጠዋል።

አቶ ሽመልስ የእነዚህን አካላት ማንነት በስም ባይጠቅሱም፣ ንግግሩን ያደረጉት የክልሎች አወቃቀር ጉዳይ ለአገራዊ ምክክር ጉባኤ በአጀንዳነት በቀረበ ማግስት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣4512👍8🤪5🥰3🙉2🤷‍♂1🙊1
አራት ኪሎ መሄድ አይጠበቅብንም‼️
"ጠላቶቻችንን ለመጣል የግድ አራት ኪሎ መሄድ አይጠበቅብንም" ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ‼️

"እኛ ካሁን በኋላ አዲስአበባ የመሄድ ፍላጎት (ወይም አባዜ) የለንም ፤ አዋሳ የመሄድ አባዜም የለንም።የኛ አላማ ሉዓላዊነታችንን ማስከበር ነው።

የኛ አላማ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብታችንን መልሰን ወደ እጃችን  ማስገባት(ማስመለስ) ነው።ይሄንን እንዳናደርግ ያነቀንን (እንቅፋት የሆነብንን) ጠላት የግድ መጣል አለብን።

ይሄንን ጠላት ለመጣል የግድ አራት ኪሎ መሄድ አይጠበቅብንም።ታዲያ እንዴት እንጣለው ? ለሚለው ....ይሄንን ጠላት አፈር ድሜ ለማብላት ከወዲሁ ስራዎችን እንደምንሰራ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል ፤ ለዚህ ተልዕኮም ራሳችንን አብቅተን መዘጋጀት አለብን።እነዚህን ጠላቶች ካላስወገድን ሰላም አናገኝም" ሲሉ ከህወሓት ጄኔራሎች ውስጥ አንዱ የሆኑት ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23🤪20👍4🤣2🤯1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካ የኢራንን ድልድዮች ማጥቃት ጀመረች‼️
አሜሪካ የኢራንን ዋና ድልድዮች እንዲሁም የውሃ ማጣሪያ ተቋሟት ላይ ጥቃት በመፈፀም ጉዳት አድርሳለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11😢10👍7😡4🤩1
#ስለህግ #የህግመረጃ

በዕርቅ_ማለቅ_የሚችሉ_የወንጀል_አይነቶች!

በወንጀል ጉዳዮች እርቅ የሚከናወነው በልዩ ሁኔታ ነው፡፡ምክንያቱም በመርህ ደረጃ ወንጀል የህዝብን እና የመንግስትን ጥቅም የሚጉዳ ተግባር ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡

👉ክስም የሚቀርበው መንግስት በወከለው ዐቃቤ ህግ ሲሆን ሙሉ ወጪውም የሚሸፈናው በመንግስት ይሆናል፡፡ስለሆነም በወንጀል ህጎች ስር በእርቅ ማለቅ የሚችሉ ገዳዮች በግልፅ ተደንግገው ይገኛሉ፡፡

ለአብነት ለመጥቀስ ያክል ፡-
1. ታስቦ የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ 556(1)፣
2. በቸልተኝነት የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ-559(3))፣
3. የእጅ እልፊት (አንቀጽ-560(1)) ፣
4. የዛቻ ወንጀል (አንቀጽ-580) ፣
5. አመንዝራነት (አንቀጽ-652) ፣
6. የሥድብ እና ማዋረድ (አንቀጽ-615) ፣
7. የስም ማጥፋት ወንጀል (አንቀጽ-618) ፣
8. በቤተዘመድ ንብረት ላይ የተፈጸመ ንብረት ነክ ወንጀል (አንቀጽ-664)
9. ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም(አንቀጽ-646)፣
10. ቀለብ የመስጠት ግዴታን ያለመወጣት(አንቀጽ-558)፣
11. በሌላ ሰው ሀብት ያለአግባብ መጠቀም(አንቀጽ-678)፣
12. አግኝቶ መደበቅ(አንቀጽ-679)፣
13. በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ(አንቀጽ-686)፣
14. በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ(አንቀጽ-689)…ወዘተ ይገኙበታል፡፡

ወንጀሉ የፈጸመው ሰው ቀደም ሲል ተመሳሳይ ወንጀል የፈጸመ ከሆነ ፣ በሕጻናት ወይም በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የተፈጸመ ከሆነ​ተጎጂው በሕግ ፊት የመወሰን አቅም የሌለው ከሆነ እርቅ ላይሰራ ይችላል።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍7🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢራን ሚሴኤሎች ኢላማቸውን መቱ‼️
ኢራን በጆርዳን በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ በቀጥታ ጥቃት ስትፈፅም የሚያሳይ ምስል ይፋ አድርጋለች።
በዚህ ጥቃት በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ቅንጡ የሆነውን Hawk helicopter (21million dollar) ማውደሟን፣በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ገልፃለች።
ለዚህ ኢላማውን ለጠበቀ ጥቃት አሜሪካ ራሺያን እና ቻይናን እየወቀሰች ትገኛለች።
አሜሪካም በሆርሙዝ ዳርቻ በሚገኘው የኢራን ነዳጅ ማከማቻ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ማድረሱን ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍6
የዝንጀሮ መንጋ ግድያ‼️
በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ያለው የዝንጀሮ መንጋ አርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪውን ዕለታዊ እንቅስቃሴ እያወከ በመሆኑ ቁጥሩን ለመቀነስ 10/11/2018 ዓ/ም ጀምሮ እርምጃ ስለሚወሰድ ነዋሪው በጥይት ተኩስ ድምፅ እንዳይደናገር የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ጽ/ቤት አሳስቧል።
የመግለጫው ርዕስ፦ጉዳዩ፡- የሰዉና የዝንጀሮ ግጭትን ይመለከታል።

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የሚኖሩ የዝንጀሮ መንጋዎች በአርባ ምንጭ ከተማ ማለትም በቴሌቪዥን ሰፈር፤ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፤ በአርባ ምንጭ አየር ማረፊያ እና በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደጋጋሚ ግጭቶች የፈጠሩ መሆናቸው ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ የቴሌቪዥን ሰፈር ነዋሪዎች በዝንጀሮ መንጋው የደረሰባቸውን ጉዳት በመጥቀስ ተቋማችን ከሰዉ የፍርድ ቤት አፈፃፀም ውሳኔ ደርሶን ቆይቷል።

ስለሆነም ከቀን 10/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተጠና መንገድ የዝንጀሮ ቅነሳ ስራውን ስለምንጀምር የአካባቢው ማህበረሰብ የጥይት ድምፅ ሰምቶ ድንጋጤ ውስጥ እንዳይገባ ጉዳዩ የሚመለከተው ተቋም ለአካባቢው ማህበረሰብ የማሳወቅና ለተግባራዊነቱም ትብብር እንድታደርጉልን በትህትና እንጠይቃለን።"ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1810👍5😡2