በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ የተገላገለችው እናት ልጇን "ምክክር" ስትል ሰየመችው::
የሀገር ፍቅር እና የቁርጠኝነት ትልቅ ማሳያ የሆነችው ወጣት ክርኑዶ ኡጁሉ፣ የመውለጃዋ ቀን ተቃርቦ ሳለ “ሀገሬ ጠርታኝ አልቀርም” በሚል ትልቅ አላማ ከጋምቤላ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ ስትሳተፍ ቆይታለች።
በጉባኤው ሂደት ላይ እያለችም በዘውዲቱ ሆስፒታል ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።
ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ እናቲቱ ባረፈችበት ቤት በአካል በመገኘት እንኳን ደስ አለሽ ብለዋታል።
ወጣቷ እናት የተለመደውን የቤተሰብ ስም የማውጣት ባህል በመተው፣ የልጇን ስም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እንዲያወጣላት በጠየቀችው መሠረት የሕፃኑ ስም "ምክክር" ተብሎ ተሰይሟል።
ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ የመጣችበትን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ወደ ምክክር ጉባኤው በልበ ሙሉነት እንደምትመለስ ያረጋገጠች ሲሆን፣ ጉባኤውን አጠናቃ ወደ መጣችበት እስክትመለስ ድረስ ለእሷና ለልጇ የሚያስፈልገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግላት ተገልጿል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ይህ ታሪክ ለሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፣ እናቲቱ በሰላም ተገላግላ በደስታ እንደተሞላች ሁሉ ሀገሪቱም ከገጠሟት ፈተናዎች በምክክር እና በውይይት ተገላግላ ወደ ተሻለ የሽግግር ምዕራፍ እንደምትሻገር ፅኑ እምነታቸውን ገልጸው ለሕፃኑ እና ለኢትዮጵያ ሕፃናት በሙሉ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
@Addis_Reporter

🤣56❤22👍7😡2🤪1
ኢትዮጵያ ከ6 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ600 በላይ የህክምና ተማሪዎችን በ‘ስፔሻሊቲ’ ደረጃ እያሰለጠነች ነው
ኢትዮጵያ ከ6 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ600 በላይ ተማሪዎችን በህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም እያሰለጠነች እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ "ፕሮግራሙ የአህጉሪቱን የህክምና አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው" ብለዋል።
ስልጠናው በ6 ዓመት ጊዜ ውስጥ የተከናወነ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቅሰዋል።
መረጃው ይፋ የሆነው በተጠናቀቀው የአፍሪካ የህክምና ትምህርት ተቋማት ሕብረት ሁለተኛ ጉባኤ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ለአህጉሪቱ ምሳሌ መሆኑን ወይዘሮ ሳህረላ አብራርተዋል።
በአውሮፓውያኑ 2017 በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበሩት ስፔሻሊስት ሐኪሞች 1 ሺህ 500 ብቻ እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ 1 ሺህ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ይመረቃሉ ተብሏል።
ይህ አቅም የውጭ ሀገራት ተማሪዎችን ለመቀበል እድል መፍጠሩ ተገልጿል። ተማሪዎቹ ከሩዋንዳ፣ ሶማሌላንድ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ ናቸው ተብሏል።
የጉባኤው ዋነኛ ዓላማ በአህጉር ደረጃ ያለውን የትምህርት ጥራት እና የካሪኩለም ክፍተት መፍታት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሌሎች ሀገራት የመስራት እድል እንዲያገኙ የማመቻቸት ዓላማ እንዳለውም ተገልጿል።

🤣12👍7❤4🤪1
የአሜሪካ ግሪን ካርድ ለማግኘት የ100,000 ዶላር ቅድመ ክፍያ ሊጠየቅ ነው
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ስደተኞች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ለመግታት አዲስ ጥብቅ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ።
በታቀደው አዲስ ረቂቅ መመሪያ መሠረት፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ሆነው የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ (ግሪን ካርድ) የሚያመለክቱ ግለሰቦች የ100,000 ዶላር የገንዘብ ዋስትና በቅድሚያ እንዲያስይዙ ሊገደዱ ይችላሉ።
ይህ የተያዘው ገንዘብ አመልካቾቹ የአሜሪካ ዜግነት ሲያገኙ የሚመለስላቸው ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም አዲሶቹ ስደተኞች በራሳቸው መተዳደር የሚችሉ መሆናቸውንና የመንግስትን ድጋፍ እንደማይጠብቁ ለማረጋገጫነት እንዲያገለግል ነው።
ይህ አሰራር በተለይ ከድሃ ሀገራት ለሚመጡና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የቅርብ ዘመዶቻቸውን (ትዳር አጋር፣ ወላጅና እህትማማቾች) ለማስገባት ለሚፈልጉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ትልቅ እንቅፋት እንደሚሆን ተገልጿል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መመሪያውን መጀመሪያ በጥቂት ሀገራት ላይ ለመፈተሽ አቅዷል።

👍5❤4😱3🤪1
አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ ተፈቀደ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአንድ መስኮት አገልግሎት በኩል እንዲያገኙ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡
ባንኩ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዲስ ፍቃድ ላወጡ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር አሰጣጥን የሚያቀል አዲስ የዲጂታል አገልግሎት አስተዋውቋል፡፡
አገልግሎቱ የባንኩ የሂሳብ ቁጥሮች በጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል ያለምንም ውጣ ውረድ እንዲሰጥ በማስቻል አስተዳደራዊ ሂደቶችን የሚቀንስና ፈጣን የንግድ አሰራርን የሚደግፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አዲሱ አገልግሎት የሚመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ለሚያወጡና አዲስ ፍቃድ ላገኙ አስመጪዎችና ላኪዎች ብቻ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማት ለሁሉም የገቢና የወጪንግድ ግብይቶቻቸው ይጠቀሙበት በነበረው ነባር ቁጥር መጠቀም እንደሚችሉ ባንኩ ገልጿል፡፡
ይህ አሰራር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከገቢና ወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የንግድ አሰራርን ምቹ ለማድረግ እንዲሁም የዲጂታል የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር እያከናወነ ያለው ጥረት አካል መሆኑንም አመልክቷል፡፡

❤11👍3
በቀን 3 ቴምር መብላት ለአእምሮ ጥንካሬና ከአልዛይመር ለመከላከል ፍቱን መፍትሔ _ጥናት‼️
በሎማ ሊንዳ ዩኒቨርሲቲ (ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ) ተመራማሪዎች የተጠናና በቅርቡ ‘ጆርናል ኦፍ ኒውትሪሽን’ ላይ የታተመ ጥናት እንደሚያመለክተው በቀን ሦስት ቴምር መመገብ ለአእምሮ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ከመሆኑም በላይ የትርሳን (የአልዛይመር) በሽታ የመያዝ ተጋላጭነትን በእጅጉ ይቀንሳል።
ቴምር የአእምሮ ሴሎችን ከጉዳት የሚጠብቁና እብጠትን የሚከላከሉ እንደ ፍላቮኖይድስ እና ፌኖሊክ አሲድ ያሉ አንቲኦክሲዳንቶች እንዲሁም በርካታ ጠቃሚ ቪታሚኖች በውስጡ ይዟል።
በሳይንሳዊ ምርምሮች መሠረት፣ ቴምር በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩትንና ለአልዛይመር በሽታ መከሰት ዋነኛ መንስኤ የሆኑትን የ"አሚሎይድ ፕላኮች" (amyloid plaques) ክምችት የመከላከል ከፍተኛ አቅም አለው።
ሆኖም ግን ቴምር ከፍተኛ የካሎሪና የስኳር መጠን ስላለው (በ100 ግራም ውስጥ ወደ 66 ግራም ስኳር ይገኛል)፣ በተለይ የስኳር ህመምተኞች እና የጨጓራ ወይም የአንጀት ችግር ያለባቸው ሰዎች በሚመገቡበት ጊዜ መጠን ማወቅና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ምሁራን ያሳስባሉ።

❤20👍11💊1
ነገ በአዲስ አበባ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ‼️
ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ”አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል።
ሰልፉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
በዚህም መሰረት:-
👉 ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
👉 በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
👉 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት
👉 ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ
👉 ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት
👉ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ
👉ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

❤10👍5😡4🤔2🤪1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።
🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።
🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።
አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy
@sputnik_ethiopia

👍5
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
''አዳዲስ ቀረጦች ሊጣሉ ነው‼️
በነዳጅ፣ በሪል እስቴት፣ በአልኮልና በትምባሆ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ታክስ ነፃ መብቶች ላይ አዳዲስ ቀረጦች ሊጣሉ መሆኑ ተሰምቷል።
IMF እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት 5 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ብድር ለማግኘት ሲል እነዚህን ሰፊ የታክስ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል። ይህ የሆነው የብድሩ ቅድመ ሁኔታ የሀገሪቱን የውስጥ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ስለሚጠይቅ እንደሆነም ተብራርቷል።
በዚህም መሠረት የነዳጅ ድጎማው ሙሉ በሙሉ ተነስቶ ዋጋው በገበያ እንዲወሰን የሚደረግ ሲሆን፣ በሪል እስቴት፣ በመኪና ባለቤትነት እና በተለያዩ ምርቶች ላይ አዳዲስ ቀረጦች የሚጣሉ ይሆናል ተብሏል።
• ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአንድ ወቅት የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (IMF) ብድር ቀላልነት ሲገልጹ «ከአይ.ኤም.ኤፍ መበደር ከእናት መቀነት እንደ መፍታት ነው...» ማለታቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ የዚያ "ቀላል" ብድር ዋጋና ቅድመ-ሁኔታዎች በዜጎች ኪስ ላይ እየፈጠሩት ያለው ጫና ቀላል አለመሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።
በየጊዜው የሚጨመሩ ታክሶች፣ አዳዲስ ቀረጦች እና የዋጋ ንረቱ «ለመሆኑ ለብድር ተብሎ በሕዝብ ላይ ታክስ መጫን ተለመደ እንዴ?» የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ እየተተገበሩ ያሉ የፖሊሲ ለውጦች (የኤክሳይዝ ታክስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማሻሻያዎች እና የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪዎች) ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ ክፉኛ እየፈተኑት ይገኛሉ።
ከውጭ ምንዛሬ ተመን መለቀቅ ጋር ተዳምሮ የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። መንግስት ገቢውን ለማሳደግ ታክስ ያልነካቸውን ዘርፎች ሁሉ ወደ ታክስ መረቡ ለማስገባት የሚያደርገው ጥረት በንግዱ ማህበረሰብና በሸማቹ ላይ ድርብ ጫና ፈጥሯል።

😢18❤12👍6😱2🤯1🤪1
#ሰበር ዜና
በዶናልድ ትራምፕ እና በቤንያሚን ኔታንያሁ መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጠረ!
የግጭቱ መነሻ ምንድን ነው?ኔታንያሁ አሜሪካ ዘመናዊ የኤፍ-35 (F-35) ተዋጊ ጄቶችን ለቱርክ ለመሸጥ ወይም ሀገሪቱን በድጋሚ በፕሮግራሙ ውስጥ ለማካተት ያቀደችውን ስምምነት በይፋ መቃወማቸውን ተከትሎ ነው።
ኔታንያሁ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ቱርክ በፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ስር "አስተማማኝ አጋር" አይደለችም በማለት፣ ይህ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የሃይል ሚዛን ያናጋል ሲሉ ዋሽንግተንን አሳስበዋል።
ይህ የኔታንያሁ ይፋዊ ጣልቃ ገብነት በዋይት ሀውስ ውስጥ ከፍተኛ ብስጭት ቀስቅሷል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኔታንያሁ በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ውሳኔ ላይ ጣልቃ የመግባት "ምንም መብት የላቸውም" በሚል ክፉኛ መቆጣታቸው ተገልጿል።
የታቀደው ስብሰባ ተሰረዘ?ውጥረቱን ለማርገብ በዋይት ሀውስ ኦቫል ኦፊስ (Oval Office) ይደረጋል ተብሎ ታስቦ የነበረው ፈጣን ስብሰባ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።
የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ስብሰባው ሊካሄድ እንደነበር ቢዘግቡም፣ የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት ግን ለኔታንያሁ የተያዘ ምንም ዓይነት ይፋዊ ቀጠሮ እንዳልነበረና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ስብሰባውን በራሳቸው ፍላጎት ብቻ ለመፍጠር እየሞከሩ እንደነበር ገልጸዋል።

❤23👍6🤔1
መረጃ‼️
ኢትዮጵያ የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውሎት ትብብር ድርጅት መስራች አባል ኾነች። የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውሎት ትብብር ድርጅትን የመመስረቻ ስምምነት ትናንት ቻይና ሻንጋይ ከተማ ውስጥ በተፈረመበት ወቅት ኢትዮጵያ ከፈራሚዎቹ 29 አገራት አንዷ ኾናለች።
የድርጅቱን የመመስረቻ ስምምነት ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ደቡብ አፍሪካን እና አልጀሪያን ጨምሮ 10 የአፍሪካ አገራት ፈርመውታል።
ዋና መስሪያ ቤቱን ሻንጋይ የሚያደርገው ዓለማቀፉ ድርጅት ዓላማው፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዙሪያ አገራት እንዲተባበሩና ዓለማቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አስተዳደር እንዲኖር ማስቻል ነው።

❤20🤪9👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች ተጎዱ‼️
ኢራን ጆርዳን በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ ወታደሮች መጎዳታቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳረጋገጡለት ነገር ግን ቁጥሮቹን ለመግለፅ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ CBS ዘግቧል።
አሜሪካ እና ኢራን ከባድ የተኩስ ልውውጥ ውስጥ ሲሆኑ አሜሪካ የኢራንን መሰረተ ልማት እና ድልድዮችን እያጠቃች ትገኛለች።
የኢራን ዋና የኤሌክትሪክ መስመር ጉዳት ያስተናገደ ሲሆን የቴህራን ዜጎች ኤሌክትሪክ ቆጥበው እንዲጠቀሙ ኢራን ለዜጎቿ መልዕክት አስተላልፋለች።
ኢራን በባህሬን እና ኩዬት የሚሳኤል ጥቃቷን የቀጠለች ሲሆን ኩዬት ለኢራን ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ማቀዷን በመግለፅ ለዜጎቿ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፋለች።

❤14👍7
#ጤናመረጃ
የሀበሻ ጎመን ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች!
የሀበሻ ጎመን በቪታሚኖች (C, A, K) በማዕድናት (ካልሲየም፣ ብረት) እና በፀረ-ኦክሲዳንት ንጥረ ነገሮች እጅግ የበለፀገ ነው።
1. ለአጥንት ጥንካሬና ጤንነት፦ የሀበሻ ጎመን እጅግ ከፍተኛ የካልሲየም (Calcium) እና የቪታሚን ኬ (Vitamin K) ይዘት ስላለው፣ ለአጥንት መገንባት፣ ለጥንካሬ እና የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል አስተዋጽኦ አለው።
2. በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር፦ በውስጡ ባለው ከፍተኛ የቪታሚን ሲ መጠን ምክንያት፣ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓት በማገዝ ከኢንፌክሽኖች እና ከተለያዩ በሽታዎች ይጠብቃል።
3. የደም ማነስን ለመከላከል፦ ጎመን በውስጡ ከፍተኛ የiron ማዕድን ይዟል። ይህም የሰውነታችንን ቀይ የደም ሴል ምርት በማገዝ የደም ማነስ ችግር እንዳይከሰት ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
4. ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፦ ልክ እንደ ጥቅል ጎመን ሁሉ፣ የሀበሻ ጎመንም ከፍተኛ የፋይበር (የቃጫ) ይዘት ስላለው የሆድ ድርቀትን ለመከላከል እና የአንጀትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል።
5. ለአይን ጤንነትና እይታ፦ በአይን ላይ የሚመጡ የዕድሜ መግፋት ጉዳቶችን እና ሌሎች የዓይን በሽታዎችን የመከላከል አቅም ያላቸውን ሉቲን እና ቪታሚን ኤ በበቂ መጠን ይዟል።
6.ለቆዳና ለፀጉር ውበት፦ በውስጡ የሚገኙት ቪታሚኖች (A,C,E) እና ፀረ-ኦክሲዳንቶች ለቆዳ ጤንነት፣ ለወጣትነት ገጽታ እና ለፀጉር ጥንካሬ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
ጠቃሚ ምክር :- የሀበሻ ጎመንን ከመጠን በላይ ሳያበስሉ (ሳይሞት) በመጠኑ አብስሎ መመገብ በውስጡ ያሉትን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ለማግኘት ይረዳል።(ኢትዮ-መረጃ)
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

❤23👍6