" ደሞዝተኞች ላይ የሚጣለው ግብር ሊሻሻል ይገባል " - ፕራግማ ካፒታል
ደሞዝተኛው ማህበረሰብ ከከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የሚደርስበትን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ፣ መንግስት በደሞዝ ላይ የሚጥለውን የግብር መጠን ሊያሻሽል እንደሚገባ ፕራግማ ካፒታል የተሰኘው ድርጅት ገለጸ።
ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በደሞዝተኞች ላይ ከፍተኛ ግብር የምትጥል ሀገር መሆኗን አመልክቷል።
ከፍተኛ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ከግብር ጫናው ጋር ተዳምሮ በደሞዝተኞች ላይ ከባድ የኢኮኖሚ ጫና እየፈጠረ መሆኑን የገለጰው ድርጅቱ፣ መንግሥት የደሞዝ ግብር ስርዓቱን ሊያሻሽለው እንደሚገባ ጠቁሟል።
መረጃው ከኢትዮኤፍኤም የተወሰደ ነው።
@Addis_Reporter

👍16❤5
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የገነባችው ግዙፍ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ!!
የወርቅ ግዥን ወደ ንግድ ባንኮች ለማዘዋወር ጥናት እየተደረገ ነው ተብሏል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የአገሪቱ የመጀመሪያው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ በመጪው አንድ ወር ውስጥ ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር አስታወቁ።
ገዥው ይህንን የገለጹት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሰባተኛ ስብሰባው የገመገማቸውን የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሁኔታዎች፣ ያቀረባቸውን ምክረ ሐሳቦችና የብሔራዊ ባንክ ቦርድ ያፀደቃቸውን የፖሊሲ ውሳኔዎች አስመልክቶ ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሲሰጡ ነው።
ከአፍሪካ አልፎ ከዚያ በላይ በግዙፍነቱ የሚጠቀስ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ (ሪፋይነሪ) ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት እዮብ (ዶ/ር)፣ ፋብሪካው በመጪው አንድ ወር ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ፣ ለአገሪቱ የወርቅ ገበያ እጅግ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
የአገር ውስጥ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ወጪን በከፍተኛ ደረጃ ከመቀነሱም በላይ፣ ቀደም ሲል ወርቅ ወደ ውጭ በመላክ እንዲነጠር ተደርጎ ከዚያ በኋላ ለሌሎች ክምችት በዶላር የመሸጠን አሠራር ሙሉ ለሙሉ የሚያስቀር ነው ብለዋል። በመሆኑም ፋብሪካው ለኢትዮጵያ የወርቅ ገበያ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ቀጣናው ትልቅ አቅም ሊሆን ይችላል ሲሉ ገልጸዋል።
ገዥው ይህንን ቢሉም ፋብሪካው የት አካባቢ እየተገነባ እንዳለና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ዘገባው የኢትዮጵያ ሪፖርተር ነው

❤17🤪9👍5🤔1
ፀሎት እና ዱአ ተጀመረ‼️
የዘንድሮው ክረምት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል መዘግየቱን ተከትሎ ትናንት ሀምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ፈጣሪ ዱኣ እና ፀሎት መጀመሩን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱን ጥቆማዎች ያሳያሉ።
የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ አገልግሎት በመጪዎቹ አስር ቀናት ውስጥ በቂ ዝናብ እንደሚኖር ገልጿል።

🙏20❤13🤣6👍3
በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ‼️
ለሐምሌ 11 የተጠራው ሰልፍ ፈቃድ አገኘ‼️
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ አፈሳ ለማውገዝ በአዲስ አበባ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ የተፈናቀሉትን እንደሚያሳትፍ ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ ለመጪው ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም የተጠራውና በሕገ-ወጥ ወታደራዊ ምልመላ እንዲሁም በሰላማዊ ዜጎች እስር ላይ ያተኮረው የተቃውሞ ሰልፍ የመንግስትን ፈቃድ ማግኘቱንና በከተማዋ የሚገኙ በርካታ የትግራይ ተፈናቃዮችም በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል።።
የስምረት ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተው የትግራይ ሰላምና የለውጥ ምክር ቤት የጠራው ይህ ሰልፍ፤ በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ነው ያሉትን ወታደራዊ አፈሳ ለማውገዝ፣ የታሰሩ እናቶችንና ገበሬዎችን ድምጽ ለማሰማት እንዲሁም ለአዲስ አበባ ተፈናቃዮች ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግ ለመጠየቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የስምረት ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሃለፎም ምርአ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፤ የሰልፉ ዋና ዓላማ በትግራይ ክልል ሕጋዊ ያልሆነ አዋጅን መነሻ በማድረግ በወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላና ያለአግባብ የታሰሩ እናቶችንና ገበሬዎችን በደል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ ማድረግ ነው።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የነፈገውን የህወሃት ቡድን “የፕሪቶሪያው ስምምነት ፈርሷል” በሚል እያከናወነ ያለውን ተግባር ለማውገዝ፣ የፌደራል መንግሥት የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ለመጠየቅና በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው አዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች አስፈላጊውን ሰብአዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻል እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

🤣26❤18👍5
የአጭር ጊዜ ቪዲዮዎች (TikTok እና Reels) ራስን የመቆጣጠር እና የዲሲፕሊን ክህሎትን የሚገነባውን የአንጎል ክፍል ስራ እንደሚያደናቅፉ አዲስ ጥናት አመለከተ
ተጠቃሚዎች በምስሎቹ ቢደሰቱም ባይደሰቱም፥ ቪዲዮዎቹ በአንጎል ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተፅዕኖ አይቀሬ መሆኑ ተረጋግጧል።
ጥናቱ እንደሚያሳየው፣ እነዚህ ምስል-ወለድ ይዘቶች የተመልካቹን ቀልብ አንዴ ከሳቡ በኋላ ፈጣን የዶፓሚን ሆርሞን መለቀቅን ያስከትላሉ።
ይህም የአንጎልን የተፈጥሮ ውሳኔ ሰጪነት በማደንዘዝ፣ ከዕፅ ሱስ የጠነከረ ከፍተኛ የሱስ የመለከፍ አደጋ ይፈጥራል።
ይህ የፈጣን መዝናኛ አባዜ የሰውን ልጅ ወደ ማገናዘብ የማይችል “ዞምቢ” እየቀየረው መሆኑን ተመራማሪዎች አስጠንቅቀዋል።
ራስን የመግዛት አቅምን ለመጠበቅ ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መገደብ ወሳኝ እንደሆነም ተመክሯል።

❤27👍8
ኢራን የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤን በቋሚነት እንደምትቆጣጠር አስታወቀች
የኢራን ባለስልጣናት በአሜሪካ እና በእስራኤል የተጀመረው ጦርነት ከመነሻው አንስቶ የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤን "ቀይ መስመር" ወይም ሊጣስ የማይገባ ወሳኝ ጉዳይ አድርገው ሲገልጹት ቆይተዋል። ብሪጋዲየር ጄኔራል ኢብራሂም ዞልፋጋሪ በሰጡት መግለጫም ይህንኑ አቋም የሚያጠናክር ነው።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የኢራንን የኃይል ማመንጫና ማከፋፈያ መሰረተ-ልማቶች ስለማጥቃት በተደጋጋሚ መናገራቸው፣ ይህ መግለጫ የተሰጠዉ በወሳኝ ጊዜ እንዲሆን አድርጎታል።የወታደራዊው ዋና መስሪያ ቤት እንደገለጸው፣ አሜሪካ በኢራን መሰረተ-ልማቶች ላይ ተጨማሪ ጥቃቶችን ብትፈጽም፣ ኢራንም በአካባቢው የሚገኙ መሰረተ-ልማቶች ላይ የአጸፋ ጥቃት ትሰነዝራለች። ኢራን እስካሁን ይህን ያላደረገችው አቅም ስለሌላት ሳይሆን፣ የመታቀብ ፖሊሲ ስላላት ነው ፤ ነገር ግን አሜሪካ እንደዚህ አይነት ጥቃቶችን ከፈጸመች ያ የመታቀብ ፖሊሲ ያበቃል ሲል መስሪያ ቤቱ አክሏል።
የኢራን ዋና ተደራዳሪ እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ባጌር ጋሊባፍ እንደተናገሩት፣ የኢራን ብሔራዊ ደህንነት በሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤ ውስጥ "የኢራን አሰራሮችን" በመጠበቅ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ "ጠላት" ይህንን በኃይል ለማዳከም እየሞከረ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።ኢራናውያን የሚያወሩት ስለ ሆርሙዝ ጊዜያዊ ቁጥጥር አይደለም፤ ይልቁንም ለዓለም የሚያስተላልፉት መልእክት ኢራን በዚህ ስትራቴጂካዊ የውሃ መስመር ላይ ዘላቂ ቁጥጥር እና ሉዓላዊነት እንዲኖራት ነው። ይህ ደግሞ በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ላለው ውጥረት ዋና ምክንያት ነው።

❤12👍3🤔1
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤8👍4
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በውጪ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሐምሌ 15 ቀን፣ 2018 ዓ፣ም ጀምሮ አዲሱን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ለማግኘት በተቋሙ የበይነ መረብ ቅጽ ላይ መመዝገብ እንደሚችሉ አስታወቀ።
አዲሱን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አገልግሎት በውጭ አገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች በኩል ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የጠቀሠው ተቋሙ፣ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ከሐምሌ 15 በኋላ የፓስፖርት ማመልከቻ ምዝገባዎችን በአዲሱ የተቋሙ የበይነ መረብ ቅጽ ላይ ብቻ እንዲሞሉ አሳስቧል።
ተቋሙ፣ "የተጭበረበሩ" እና "ሐሰተኛ" ሠነዶችን በማቅረብ በሕገወጥ መንገድ ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠይቁ አመልካቾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መሄዱን ገልጧል።
በ2018 ዓ፣ም ብቻ 4 ሺሕ 883 ኢትዮጵያዊያን እና የውጪ ዜጎች በሐሰተኛ ሰነድ አገልግሎት ለማግኘት ሲሞክሩ ተይዘው ሕጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል፡፡

❤7👍4🤪2👌1
ጋዜጠኞች በቡና ፍጆታ ቀዳሚ ናቸው
በግምት 20,000 በሚሆኑ ሰራተኞች ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው በጋዜጠኝነት እና በመገናኛ ብዙሃን (በሚዲያ) ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከማንኛውም ሌላ የስራ መስክ በላይ ከፍተኛ የቡና ተጠቃሚዎች መሆናቸውን አረጋግጧል።

❤8🤣4👍2
በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ የተገላገለችው እናት ልጇን "ምክክር" ስትል ሰየመችው::
የሀገር ፍቅር እና የቁርጠኝነት ትልቅ ማሳያ የሆነችው ወጣት ክርኑዶ ኡጁሉ፣ የመውለጃዋ ቀን ተቃርቦ ሳለ “ሀገሬ ጠርታኝ አልቀርም” በሚል ትልቅ አላማ ከጋምቤላ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ ስትሳተፍ ቆይታለች።
በጉባኤው ሂደት ላይ እያለችም በዘውዲቱ ሆስፒታል ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።
ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ እናቲቱ ባረፈችበት ቤት በአካል በመገኘት እንኳን ደስ አለሽ ብለዋታል።
ወጣቷ እናት የተለመደውን የቤተሰብ ስም የማውጣት ባህል በመተው፣ የልጇን ስም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እንዲያወጣላት በጠየቀችው መሠረት የሕፃኑ ስም "ምክክር" ተብሎ ተሰይሟል።
ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ የመጣችበትን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ወደ ምክክር ጉባኤው በልበ ሙሉነት እንደምትመለስ ያረጋገጠች ሲሆን፣ ጉባኤውን አጠናቃ ወደ መጣችበት እስክትመለስ ድረስ ለእሷና ለልጇ የሚያስፈልገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግላት ተገልጿል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ይህ ታሪክ ለሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፣ እናቲቱ በሰላም ተገላግላ በደስታ እንደተሞላች ሁሉ ሀገሪቱም ከገጠሟት ፈተናዎች በምክክር እና በውይይት ተገላግላ ወደ ተሻለ የሽግግር ምዕራፍ እንደምትሻገር ፅኑ እምነታቸውን ገልጸው ለሕፃኑ እና ለኢትዮጵያ ሕፃናት በሙሉ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

🤣56❤22👍7😡2🤪1
ኢትዮጵያ ከ6 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ600 በላይ የህክምና ተማሪዎችን በ‘ስፔሻሊቲ’ ደረጃ እያሰለጠነች ነው
ኢትዮጵያ ከ6 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ600 በላይ ተማሪዎችን በህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም እያሰለጠነች እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ "ፕሮግራሙ የአህጉሪቱን የህክምና አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው" ብለዋል።
ስልጠናው በ6 ዓመት ጊዜ ውስጥ የተከናወነ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቅሰዋል።
መረጃው ይፋ የሆነው በተጠናቀቀው የአፍሪካ የህክምና ትምህርት ተቋማት ሕብረት ሁለተኛ ጉባኤ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ለአህጉሪቱ ምሳሌ መሆኑን ወይዘሮ ሳህረላ አብራርተዋል።
በአውሮፓውያኑ 2017 በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበሩት ስፔሻሊስት ሐኪሞች 1 ሺህ 500 ብቻ እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ 1 ሺህ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ይመረቃሉ ተብሏል።
ይህ አቅም የውጭ ሀገራት ተማሪዎችን ለመቀበል እድል መፍጠሩ ተገልጿል። ተማሪዎቹ ከሩዋንዳ፣ ሶማሌላንድ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ ናቸው ተብሏል።
የጉባኤው ዋነኛ ዓላማ በአህጉር ደረጃ ያለውን የትምህርት ጥራት እና የካሪኩለም ክፍተት መፍታት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሌሎች ሀገራት የመስራት እድል እንዲያገኙ የማመቻቸት ዓላማ እንዳለውም ተገልጿል።

🤣12👍7❤4🤪1
የአሜሪካ ግሪን ካርድ ለማግኘት የ100,000 ዶላር ቅድመ ክፍያ ሊጠየቅ ነው
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ስደተኞች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ለመግታት አዲስ ጥብቅ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ።
በታቀደው አዲስ ረቂቅ መመሪያ መሠረት፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ሆነው የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ (ግሪን ካርድ) የሚያመለክቱ ግለሰቦች የ100,000 ዶላር የገንዘብ ዋስትና በቅድሚያ እንዲያስይዙ ሊገደዱ ይችላሉ።
ይህ የተያዘው ገንዘብ አመልካቾቹ የአሜሪካ ዜግነት ሲያገኙ የሚመለስላቸው ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም አዲሶቹ ስደተኞች በራሳቸው መተዳደር የሚችሉ መሆናቸውንና የመንግስትን ድጋፍ እንደማይጠብቁ ለማረጋገጫነት እንዲያገለግል ነው።
ይህ አሰራር በተለይ ከድሃ ሀገራት ለሚመጡና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የቅርብ ዘመዶቻቸውን (ትዳር አጋር፣ ወላጅና እህትማማቾች) ለማስገባት ለሚፈልጉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ትልቅ እንቅፋት እንደሚሆን ተገልጿል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መመሪያውን መጀመሪያ በጥቂት ሀገራት ላይ ለመፈተሽ አቅዷል።

👍5❤4😱3🤪1