ህወሓት ዳግም ያቋቋመው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ሀገራዊ የምክክር መድረኩን ውድቅ በማድረግ በሂደቱ ላይ እንደማይሳተፍ አስታወቀ
በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሃት) ዳግም የተቋቋመው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት ውድቅ ማድረጉን ያስታወቀ ሲሆን፥ «ተቀባይነት የሌለው» ሲል በገለጸው የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ መንግሥትም ሆነ የትግራይ ሕዝብ አልተወከሉም ብሏል።
የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ትናንት ባወጣው መግለጫ፥ መድረኩ የትግራይ ሕዝብ የሚጋፈጣቸውን መሠረታዊ ጥያቄዎች መመለስ አልቻለም በሚል አስተዳደሩ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቋል። ቢሮው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የፌዴራል መንግሥት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ቁልፍ ድንጋጌዎችን ተግባራዊ አላደረገም ሲል የከሰሰ ሲሆን፥ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቢፈረምም ትግራይ አሁንም ከባድ ሰብአዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደኅንነት ተግዳሮቶች እየገጠሟት ይገኛል ብሏል።
@Addis_Reporter

❤15🤪7👍5🤣3🤯2
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አጋሮች የቀነሰባቸውን 2.8 በመቶ ድርሻ መልሰው የመግዛት መብት እንዳላቸው ተገለጸ
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚንቀሳቀሰው ቅርንጫፍ ኩባንያው ያደረገውን ተጨማሪ የካፒታል ኢንቨስትመንት ተከትሎ፣ ሌሎች አብረውት ኢንቨስት ያደረጉ አጋሮቹ ያጡትን የ2.78 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ መልሰው የመግዛት መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን አስታወቀ።
የቴሌኮም ኩባንያው እና ደቡብ አፍሪካዊው የእናት ኩባንያው ቮዳኮም ግሩፕ ‘ቮዳፋሚሊ ኢትዮጵያ ሆልዲንግ’ በተሰኘው የኢንቨስትመንት ተቋማቸው አማካኝነት፣ እስከ እኤአ መጋቢት 2026 በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 21.3 ቢሊዮን የኬንያ ሺሊንግ የሚያወጣ የካፒታል ማሰባሰቢያ ጥሪ ላይ ብቻቸውን ተሳትፈዋል።
ይህንን የካፒታል ማሳደግ ጥሪ ሳፋሪኮም እና ቮዳኮም ብቻቸውን በመሸፈናቸው በኢትዮጵያው ኩባንያ ውስጥ የነበራቸውን ጥምር ድርሻ ከ57.41 በመቶ ወደ 60.19 በመቶ ከፍ ማድረግ ችለዋል። ይህ እርምጃ እንደ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን ፣ ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ያሉትን ሌሎች አጋር ኩባንያዎች የነበራቸውን የባለቤትነት ድርሻ እንዲቀንስ አድርጎት ነበር።
ይሁን እንጂ ሳፋሪኮም አጋሮቹ የተዳከመውን ድርሻቸውን ወደነበረበት ለመመለስና ያጡትን የ2.78 በመቶ ድርሻ መልሰው መግዛት የሚችሉበት ሕጋዊ መብት እንዳላቸው በይፋ አረጋግጧል።
ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን የኔትወርክ ተደራሽነት ለማስፋፋት እና የንግድ እንቅስቃሴውን ለማጠናከር ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ የሚገኝ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እስከ መጋቢት 2027 ዓ.ም ድረስ ወጪና ገቢውን አጣጥሞ ሙሉ በሙሉ ትርፋማ መሆን እንደሚጀምር ግምቱን አስቀምጧል።

❤12👍7
የአዲስ አበባ ታክሲዎች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ክፍያ እንዲሰበስቡ ተወሰነ
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከተወሰነው ታሪፍ በላይ እንዲሚያስከፍሉ ከማኅበረሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት ክፍያው ከመነሻው እንዲሰበሰብ የሚያስገድድ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል።
አሽከርካሪዎች በታሪፍ መመሪያው መሠረት ብቻ ከመነሻው የትራንስፖርት ክፍያ እንዲሰበስቡ ለማስቻል ተቆጣጣሪዎች በመነሻ መጫኛ ቦታዎች ላይ ተመድበው ሥራ መጀመራቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ተናግረዋል።
ይህ አሠራር በጉዞ ወቅት "ሒሳብ ጨምሩ" በሚል ከአሽከርካሪዎች የሚነሳውን አግባብነት የሌለው ጥያቄ ለመግታት የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
ይሁን እንጂ አዲሱ አሠራር ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ አንዳንድ ተግዳሮቶች መፈጠራቸውን የቢሮው ኃላፊዎች ጠቁመዋል።
በከተማዋ በሚገኙ መነሻዎች ላይ ክፍያውን አስቀድሞ በመሰብሰብ ሂደት የተወሰነ ጊዜ እየወሰደ መሆኑ በማኅበረሰቡ በኩል ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል።
በተመሳሳይ አንዳንድ አሽከርካሪዎች መንገድ ከጀመሩ በኋላ ታሪፍ የመጨመር አዝማሚያዎችን እያሳዩ መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል።
ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ማኅበረሰቡ የጉዳዩን ፋይዳ በመገንዘብ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግና ህገ-ወጥ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ጥቆማዎችን በመስጠት የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አቶ ዳኛቸው አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ያለ ረዳት በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ቢሆንም፤ ቢሮው በአሁኑ ወቅት ትኩረቱን አዲሱ የአሠራር ሥርዓት ላይ ማድረጉን አመልክቷል።
ይሁን እንጂ የረዳት አጠቃቀምን በተመለከተ ግልጽና ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት እንደሚያስፈልግ አቶ ዳኛቸው ገልጸዋል።

❤35👍9🤔1
ኢትዮጵያ ዛሬ 180 ሚሊየን ዶላር (29 ቢሊየን ብር) እዳዋን ዘጭ አድርጋ እንደምትከፍል የሚጠበቅበት ቀን ነው!
👉ሌላ 100 ሚሊየን ዶላር ሊኖር ይችላል
ኢትዮጵያ እና የዩሮቦንድ ባለይዞታዎች ከሰሞኑ በደረሱበት የቴክኒክ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ካለባት እዳ ውስጥ 180 ሚሊየን ዶላሩን ዛሬ መክፈል ይጠበቅባታል፡፡
የእዳ መልሶ ማዋቀር ስምምነቱ ሲደረስ ከታህሳስ 2016 እስከ ታህሳስ 2017 ዓም መከፈል የሚገባቸው ሶስት የወለድ ክፍያዎች በጥቅሉ 100 ሚሊየን ዶላር በአንዴ መከፈል የሚገባው መሆኑ ይታወሳል፡፡
በመርህ ደረጃ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ቀሪ
👉100 ሚሊዮን ዶላር – 15 ጁላይ 2027
👉300 ሚሊዮን ዶላር – 15 ጁላይ 2028
👉300 ሚሊዮን ዶላር – 15 ጁላይ 2029 የሚከፈል ይሆናል።
አሁን ጥያቄው የዛሬውን እሺ ያንን የሚያክል ገንዘብ በአንዴ የመክፈል አቅም ይኖረናል ወይ? ነው ጥያቄው።

❤7😢7👍4👀1🤪1
ያልተመረጠ መንግሥት ከቀይ ባሕር አባሮናል‼️
‹‹በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ለሚያንዣብቡ አሞራዎች መልዕክት አለኝ›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
‹‹በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ለሚያንዣብቡ አሞራዎች መልዕክት አለኝ፤ ከብቱን መርጠን የምንገዛ እኛ ነን፤ የቅርጫውን ባለቤት የምንወስን እኛ ነን፤ የተረፈንን የማንፈልገውን ካልሆነ በቀር የትኛውን አሞራ በጉልበት ከየትኛውም የቅርጫ መደብ ላይ አንዲት ኪሎ ስጋ መውሰድ እንደማይችል ላረጋግጥላቸው እፈልጋለሁ፤ ስንፈልግ ለማጋት ዝግጁ ነን፤ ከፍቃዳችን ውጪ ግን ለሺህ አመታት የኖረች ኢትዮጵያን አሁን ባለው ፕሮፓጋንዳ ትዘናጋለች ጥቅሟን አሳልፋ ትሰጣለች ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው›› ያሉ ሲሆን ‹ያልተመረጠ መንግሥት በሸፍጥ ከቀይ ባህር አባረረን ብለዋል።
‹‹ኢትዮጵያ ለዘመናት ያስከበረችውን ቀይ ባህር ያልተመረጠ መንግሥት በሸፍጥ የጂኦግራፊ እስረኛ ያደረገበት ምክንያት በውስጣችን ያለ ስንፍና እንጂ የኢትዮጵያን መሻት እና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል ስለነበረ አይደለም›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአገራዊ ምክክር ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከተናገሩት ተቀንጭቦ የተወሰደ።

❤20🤪19👍6🤔2😎2
የአውሮፓ ህብረት በሱዳን ወርቅ ላይ ማዕቀብ ጣለ
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የሀገሪቱን የጦርነት ኢኮኖሚ ለማዳከም እና የቀጠለውን ግጭት የገንዘብ ምንጭ ለመቀነስ ከሱዳን የሚመጣን ወርቅ መግዛት፣ ማስገባት (ማስመጣት) ወይም ማጓጓዝ ላይ ነው ማዕቀብ የጣለው።
ማዕቀቡ ከሱዳን የሚመጣን ወርቅ መግዛት፣ ወደ ሀገር ማስገባት ወይም ማጓጓዝ ላይ የተጣለ ሙሉ እገዳ ሲሆን ለወርቅ ማዕድን ማውጣት እና ማጣራት ሂደት ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉትን ሜርኩሪ እና ሲያናይድ ኬሚካሎችን ለሱዳን መሸጥ፣ ማቅረብ፣ ማስተላለፍ ወይም መላክ ይከለክላል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከወርቅ እና ከእነዚህ ኬሚካሎች አቅርቦት ጋር የተያያዙ ቴክኒካዊ እገዛ፣ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ ህብረቱ አግዷል፡፡

❤9👍3
ያገለገሉ ንብረቶችን በመሸጥ ከ411.5 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተነገረ
የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ካከናወናቸው ተግባራት መካከል በሽያጭ ከተወገዱ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ንብረቶች ከ411.5 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታወቀ። ይህ የተገኘው ገቢ የዕቅዱን 103 ፐርሰንት ያሳካ ሲሆን በአገልግሎቱ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገብ ተመላክቷል።
የአገልግሎቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ረድኤት ተክሉ በበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እንደገለጹት፥ ተቋሙ በስትራቴጂ እና በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ 15.6 ቢሊየን ብር የሚያወጡ 74 ውሎችን ተፈራርሟል።
በተጨማሪም ለማዕቀፍ ስምምነት ዕቃዎች ግዥ ከ9.2 ቢሊየን ብር በላይ ለአሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊነት ደብዳቤ ተሰጥቶ ውል እንደተገባ አስረድተዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስማረ ይገዙ በበኩላቸው፥ በ2018 በጀት ዓመት ያልተከናወኑ ተግባራትን በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት፣ አሰራርን በማዘመን እና ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ በማድረግ ከአሁኑ በበለጠ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

❤11🤣6👍3
“ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሽ ሲል፤ ያደፈጡ፣ የሚነቁ፣ የዘመናት ያልተቋረጠ የጠላትነት ስሜት ያላቸው ሀገራት አሉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ “በቀጣይ” አዲስ ህገ መንግስት ሊኖራት እንደሚችልም ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8፤ በይፋ በተከፈተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቆማ ሰጥተዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ በዚሁ ንግግራቸው ከሀገራዊ ጉባኤው የሚጠበቁ ጉዳዮችን እና በምክክሩ ይሳካሉ ብለው የሚጠብቋቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።
“አሁን የምንመካከረው ስለ ትላንትናው አይደለም። የትላንትን ችግር ፈተን ለነገ መልካም መሰረት ለማኖር ነው” ሲሉ አብይ ከሀገራዊ ጉባኤው የሚጠበቀውን አመልክተዋል።
“የአሜሪካ ህገ መንግስት በ55 ሰዎች ቢሰራም ልባም ነበሩና ለምዕተ ዓመታት የሚቆይ ስራ ሰርተዋል። የእኛ አራት ሺህ ሰዎች ከእነሱ በላይ፣ ከእነሱ በተሻለ ጊዜ ይበልጥ ልባም ሆነው፣ ሁሉን ወገን፣ መላው ኢትዮጵያን የሚሰበስብ ምክክር ቢያደርጉ፤ በቀጣይ የሚኖረን ህገመንግስት ከዚህ ቀደም እንደለመድነው የመጣ ሁሉ የሚቀደው ሳይሆን፤ እኛ በአራት ሺህ ጀምረናል፣ በ10 ሺህ ምክክር ሳይደርግ፤ አንድም ሰው መቀየር አይችልም ማለት ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ቀይ ባህር ጉዳይ በተለይ ሲናገሩ፣ "ኢትዮጵያ ለሺ ዘመናት ያስተዳደረችውን፣ በባለቤትነት የያዘችውን፣ ለራሷም ለከባቢውም መጠቀሚያ ያኖረችውን ቀይ ባህር ያልተመረጠ መንግስት፣ ያልተወያየ መንግስት በሸፍጥ ኢትዮጵያን የጂኦግራፊ እስረኛ እንዲያደርግ ያደረገበት ዋናው ምክንያት በውስጥ ያለን ስንፍና እንጂ የኢትዮጵያን መሻትና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል ስለነበረ፣ ስላለ፣ ስለሚኖር አይደለም " ብለዋል።

❤20🤣8👍4🤔1🤪1
#እጅግ በጣም አስቸኳይ መልዕክት‼️
ከዲፕሎማ ወደ ድግሪ ትምህርታቸውን በክረምት መርሃግብር ለመማር ዕድል የሚያገኙ መምህራን በሐምሌ 11/2018 የ12 ክፍል ተማሪዎች በተፈተኑበት ማዕከላት ፈተና ስለሚሰጥ በቶሎ ተዘጋጅተው ወደ ማዕከላቱ እንዲደርሱ ደብዳቤ ተጽፏል።

❤7👍5🥰1
በሰሜን ኢትዮጵያ የዝናብ መጠን አነስተኛ ነው‼️
የሰሜንና የሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በክረምቱ የሚኖረው ዝናብ አነስተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡
በዚህም ምክንያት የሚኖረው የዝናብ መጠን አነስተኛ ነው ህብረተሰቡም በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል፡፡
የክረምት ዝናብ አሁን ላይ ባላገኙ አንዳንድ አካባቢዎች በሚቀጥሉት ቀናት የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ ጠቅሷል፡፡
የዝናብ እጥረት በሚታይባቸው አካባቢዎችም በመጪዎቹ ቀናት የተሻለ የዝናብ መጠን ሊያገኙ እንደሚችልም ኢንስቲትዩቱ ትንበያውን ነግሮናል፡፡
በመጪዎቹ 10 ቀናት በአብዛኛው የዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የሚኖረው የዝናብ መጠን ከቀላል እስከ መካከለኛ ነው ተብሏል፡፡
በመካከለኛው የአማራ አካባቢዎች ፣ የምዕራብ ሻዋ ፣ ምዕራብ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል አስረድቷል፡፡
ህብረተሰቡን ከባድ ዝናብ በሚጥልባቸው አካባቢዎች አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ጠይቋል፡፡
የዝናብ እጥረት ሊከሰትባቸው ይችላል በተባሉ አካባቢዎች ላይ ደግሞ የግብርና ስራዎች ሲሰራ አስፈላጊው ዝግጅትና አማራጮች እንዲወሰድም መክሯል፡፡

❤15👍3🙏1🤪1
ከአሜሪካው አምባሳደር እንዳይገናኙ ሆነ!
የቀድሞ የ #ትግራይ ጊዜያዊ ክልል አስተዳደር ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ ከ #አሜሪካው አምባሳደር ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸው ተገለፀ
የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በ #መቀለ ሊያደርጉት የነበረው ውይይት፤ የጸጥታ ኃይሎች ሌተናል ጄነራሉ ወደ ስብሰባው እንዳይጓዙ በመከልከላቸው ምክንያት መሰረዙን ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ገለጹ።
ይህ የሆነው አምባሳደር ማሲንጋ ለስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት መቐለ መግባታቸውን ተከትሎ ነው።
ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የነበሩት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ከአምባሳደር ማሲንጋ ጋር ለመገናኘት የተያዘ ቀጠሮ የነበራቸው ቢሆንም፥ የጸጥታ ኃይሎች ለጄነራሉ የተመደቡ ጠባቂዎች የጀነራሉን እንቅስቃሴ እንዲገድቡ መመሪያ ሰጥተዋል።
በአካል ሊደረግ የታቀደው ስብሰባ ከተሰረዘ በኋላ፥ አምባሳደር ማሲንጋ እና ሌተናል ጄነራል ታደሰ በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ምንጮቹ አክለዋል።
Via:- Addis Standard Amharic

❤17👍5😢1
በአዲስ አበባ ከተማ አልኮል ጠጥተው ሲያሽከረክሩ የነበሩ 3ሺ አሽከርሪዎች በደንብ መተላለፍ ተቀጡ
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት አልኮል ወይም አደንዛዥ እጽን ተጠቅሞ ማሽከርከርን ለመከላከል የቁጥጥር ስራ አከናውኗል።
የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ዲባባ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በተካሄደው የቁጥጥር ሥራ 3,356 አሽከርካሪዎች አልኮል ጠጥተው ሲያሽከረክሩ በመገኘታቸው በደንብ መተላለፍ ተቀጥተዋል።
ባለስልጣኑ ጠጥቶ ማሽከርከር ለአሽከርካሪውም ሆነ ለሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ከፍተኛ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ ቁጥጥሩን በከተማዋ በሚገኙ 11ኡም ክፍለ ከተሞች አካሂዷል፡፡
በቀጣይም አልኮል ጠጥቶ ማሽከርከርንና ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን ለመከላከል ቁጥጥሩ እንደሚጠናከር ባለስልጣኑ ገልፆ አሽከርካሪዎችና እግረኞች የትራፊክ ሕግና ደንብን አክብረው እንዲጠቀሙ አሳስቧል።

❤12👍5⚡1🍾1
የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ በክልሉ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቀቂያ ፈተና የወረቀት ተፈታኞች ከሌሎች በተለየ ከሐምሌ 22 እስከ 24 ፈተናውን እንዲወስዱ የተወሠነው ውሳኔ "ብሔራዊ አድልዎ" እና "በደል" ነው በማለት ከሠሠ።
ቢሮው፣ የክልሉ የወረቀት ተፈታኞች በዕለቱ ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች እንዳይሄዱ ትምህርት ሚንስቴር ሰኔ 27 ቀን በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጧል።
ቢሮው፣ የክልሉን የወረቀት ተፈታኞች የፈተና ቀን የሚያስቀይር "የቴክኒክ"፣ "የጸጥታ" ወይም "የሎጅስቲክ" ችግር በሌለበት ሁኔታ የተወሠነው ውሳኔ "ፖለቲካዊ" እንድምታ ያለው ነው በማለት ተችቷል።
የትምህርትና የፈተናዎች ምዘና አገልግሎት ለወረቀት ተፈታኞች ፈተናውን ከሐምሌ 1 እስከ 8 እየሠጠ ሲኾን፣ የ15 ሺሕ 349 የትግራይ የወረቀት ተፈታኞችን መርሃ ግብር ግን ወደ ሐምሌ 22 ማራዘሙ ይታወሳል።
ቢሮው፣ ለተማሪዎቹ በክልል ደረጃ የራሱን ፈተና እንደሚያዘጋጅ ካሁን ቀደም አስጠንቅቆ ነበር።

❤9👍4
ቤት ሰርቶ ያለማከራየት አይቻልም ተብሏል።
📌አከራዮች ተጠንቀቁ፤ በአዲስ አበባ አዲስ መመሪያ ወጥቷል።
ቤት ሰርተው ወይም አድሰው ሳይጠቀሙበት ወይም ሳያከራዩ ለስድስት ወራት ካስቀመጡ፣ መንግስት ቢከራይ ሊያገኝ የሚችለውን ገቢ አስልቶ ግብር እንዲከፍሉ ያደርጋል ተብሏል።
ይባስ ብሎ ደግሞ ቤቱ ሳይከራይ ከአምስት አመት በላይ ከቆየ፣ አመታዊ የንብረት ግብሩ ላይ ሃያ አምስት በመቶ ተጨማሪ ቅጣትም ይጣልበታል። አከራዮች 'ቤቴ ነው፣ የፈለኩትን አደርጋለሁ' ማለት አይችሉም ተብሏል።
የህግ ባለሙያዎችም ቤት ለማግኘት ህዝቡ እየተቸገረ፣ ቤት ዘግቶ ማስቀመጥ መብት አይደለም እያሉ ይገኛሉ። ቤታችሁን ዘግታችሁ ያስቀመጣችሁ አከራዮች ሰው ይኑርበት ተብላችኋል።

👍32❤15🤔13🤣5🥰4🤪2🌭1👀1🙊1
የሚስተካከሉ የስራ መደቦች ይኖራሉ‼️
👉ከሰራተኛ ቅነሳ ጋር አይገናኝም።
“የምንገነባው ጥራቱንና ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን የጠበቀ ሲቪል ሰርቪስ ነው” - ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
የኢትዮጵያ መንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲን መሠረት ያደረገ፣ የተናበበ ተቋምና ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት አካሄደ።
ኮሚሽኑ በሁለተኛው ምዕራፍ (Wave Two) ወደ ሪፎርም ከገቡ የፌዴራል ተቋማት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተገኙበት መድረክ የመሩት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ፤ እንደ ሀገር ተቋማት ከአፈጣጠራቸው ጀምሮ አደረጃጀታቸው በደንብ ተፈትሾ የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያሳኩና ጠንካራ ተቋማት ሆነው እንዲዘልቁ አድርጎ መመስረት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ተቋማት ነፃ፣ ገለልተኛ፣ አካታች፣ ቀልጣፋና ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስን በመገንባት ረገድ ግንባር ቀደም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አቅጣጫ ሲያስቀምጡ ሲሆን ፤ በዚሁ መድረክ የተሳተፉ ሚኒስቴር ድኤታዎችና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴክተር ሀላፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በተጨማሪም በአገሪቱ 5.5 ሚሊዮን የሥራ መደቦች ቢፈጠሩም በአሁኑ ሰአት ያለው የመንግስት ሠራተኛ 2.5 ሚሊዮን እንደደረሰ ጠቁመው አንዳንድ የስራ መደቦች በቀን ስምንት ሰዓት ሊያሰሩ የሚችሉበት ሁኔታ እንደሌለ የታወቀ በመሆኑ ይህም በኢኮኖሚው ላይ ጫና እየፈጠረ ስለሚመጣ እያንዳንዱ የሥራ መደብ በዝርዝር ታይቶ በሪፎርሙ ሊስተካከል እንደሚገባ ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።
ይህን አደረጃጀት ማስተካከልም ከሰራተኛ ቅነሳ ጋር ግንኙነት እንደሌለው አሳስበዋል፡፡

❤12👍4
ነጋዴው አገልግሎት ሰጪ ተቋም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከ42 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በበጀት አመቱ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መሰጠት መቻሉንና የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች 23 ማድረሳቸውን ገልጸዋል።
አክለውም 1,046,286 ቪዛ፣ 32,952 ትውልደ ኢትዮጵያውያን መታወቂያ እንዲሁም 21,163 ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ከ42 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ስኬታማ ስራ መሰራቱም የተገለፀ ሲሆን፥ በአየር እና በየብስ ድንበር አለማቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ በጉዞ ሰነድ ለ7,225,691 ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው፤ 433 የውጭ ዜጎችና 4ሺህ 450 ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ 4ሺህ 883 ዜጎች በሐሰተኛ ሰነድ የማጭበርበር ድርጊት ሲፈጽሙ ተይዘው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል።
በተጨማሪም 25ሺህ 407 ኢትዮጵያውያን እና 29ሺህ 606 የውጭ ሀገር ዜጎች በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገቡና ሊወጡ ሲሉ ተይዘው ተጠያቂ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ ስድስት ሚሊዮን የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን ይህን ሂደት ለመምራት የተለዩ የዲጂታል አማራጭ መተግበሪያ እና ስረአት መዘርጋቱን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

❤7😡7👍2
" ደሞዝተኞች ላይ የሚጣለው ግብር ሊሻሻል ይገባል " - ፕራግማ ካፒታል
ደሞዝተኛው ማህበረሰብ ከከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የሚደርስበትን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ፣ መንግስት በደሞዝ ላይ የሚጥለውን የግብር መጠን ሊያሻሽል እንደሚገባ ፕራግማ ካፒታል የተሰኘው ድርጅት ገለጸ።
ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በደሞዝተኞች ላይ ከፍተኛ ግብር የምትጥል ሀገር መሆኗን አመልክቷል።
ከፍተኛ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ከግብር ጫናው ጋር ተዳምሮ በደሞዝተኞች ላይ ከባድ የኢኮኖሚ ጫና እየፈጠረ መሆኑን የገለጰው ድርጅቱ፣ መንግሥት የደሞዝ ግብር ስርዓቱን ሊያሻሽለው እንደሚገባ ጠቁሟል።
መረጃው ከኢትዮኤፍኤም የተወሰደ ነው።

👍16❤5
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የገነባችው ግዙፍ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ!!
የወርቅ ግዥን ወደ ንግድ ባንኮች ለማዘዋወር ጥናት እየተደረገ ነው ተብሏል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የአገሪቱ የመጀመሪያው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ በመጪው አንድ ወር ውስጥ ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር አስታወቁ።
ገዥው ይህንን የገለጹት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሰባተኛ ስብሰባው የገመገማቸውን የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሁኔታዎች፣ ያቀረባቸውን ምክረ ሐሳቦችና የብሔራዊ ባንክ ቦርድ ያፀደቃቸውን የፖሊሲ ውሳኔዎች አስመልክቶ ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሲሰጡ ነው።
ከአፍሪካ አልፎ ከዚያ በላይ በግዙፍነቱ የሚጠቀስ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ (ሪፋይነሪ) ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት እዮብ (ዶ/ር)፣ ፋብሪካው በመጪው አንድ ወር ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ፣ ለአገሪቱ የወርቅ ገበያ እጅግ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
የአገር ውስጥ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ወጪን በከፍተኛ ደረጃ ከመቀነሱም በላይ፣ ቀደም ሲል ወርቅ ወደ ውጭ በመላክ እንዲነጠር ተደርጎ ከዚያ በኋላ ለሌሎች ክምችት በዶላር የመሸጠን አሠራር ሙሉ ለሙሉ የሚያስቀር ነው ብለዋል። በመሆኑም ፋብሪካው ለኢትዮጵያ የወርቅ ገበያ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ቀጣናው ትልቅ አቅም ሊሆን ይችላል ሲሉ ገልጸዋል።
ገዥው ይህንን ቢሉም ፋብሪካው የት አካባቢ እየተገነባ እንዳለና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ዘገባው የኢትዮጵያ ሪፖርተር ነው

❤17🤪9👍5🤔1