አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የዓለም ባንክ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ድጋፎች የፖሊሲ ለውጦች አደረገ

የዓለም ባንክ ከ2027 እስከ 2036 ያለውን የ10 ዓመታት የአጋርነት ማዕቀፍ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት 10ዓመታት ቅድሚያ ይሰጣቸው የነበሩ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ሙሉ በሙሉ ከዕቅዱ ውጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ሪፖርተር የተመለከተው የዓለም ባንክ አዲስ የስትራቴጂ ሰነድ ትኩረቱን በዋናነት በየዓመቱ ወደ ሥራው ዓለም ለሚቀላቀሉ ወደ ሁለት ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ላይ አድርጓል፡፡

ግዙፍ በመንግሥት የሚመሩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን፣ ዋና ዋና የአስፋልት መንገዶችንና የቱሪዝም ዘርፍን በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ሙሉ በሙሉ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች ዝርዝር ውጪ አድርጓቸዋል፡፡

👉የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ከዕቅዱ ውጪ እንዲሆኑ የተደረጉት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባደረገችው ኢንቨስትመንት በቂ የማመንጨት አቅም ስላላት ሲሆን፣ የቱሪዝም ዘርፍ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታና የመሠረተ ልማት ሁኔታ መሻሻል እስከሚታይበት ድረስ ከዝርዝሩ ውጪ እንዲሆን መደረጉን ጠቁሟል፡፡

የከተማ አውራ ጎዳናዎችን የመገንባት ዕቅድም ቀርቶ፣ በተመሳሳይ መልኩ የገጠር መንገዶችን ወደ ማስፋፋት እንዲዞር የተደረገ ሲሆን፣ ይህም አርሶአደሩ ምርቱን በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲያቀርብ ለማገዝ፣ የጉምሩክ አሠራርን ለማዘመንና የወጪ ንግድ ወጪን ለመቀነስ ያለመ አዲስ መዋቅራዊ አቅጣጫ መሆኑ ተመልክቷል።

👉ባንኩ በቀጣይ እቅዶቹ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ማስተካከል፣ የኃይል መቆራረጥን መቀነስና በሚሊዮኖች ለሚቆጠር ሕዝብ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን አስተማማኝ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍8🤣6🤷2🤪1
🔴የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ ኩርስክ ግዛት የሚገኘውን ግዙፍ የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎች ዴፖ አወደሙ‼️
የዩክሬን ልዩ ኃይል በሩሲያ የድንበር ቀጠና በሆነው የኩርስክ (Kursk) ግዛት ውስጥ እስከዛሬ ከተሰነዘሩት እጅግ ስልታዊ የተባለውን ጥቃት መፈጸሙን የኪየቭ የጦር እዝ ይፋ አድርጓል።

በጥቃቱ የዩክሬን የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ድሮኖች የሩሲያ ጦር ለሰሜን ኮሪያ ሰራሽ ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና ለከባድ መሣሪያ ጥይቶች ማከማቻነት ይጠቀምበት የነበረን አንድ ግዙፍ ወታደራዊ መጋዘን ሙሉ በሙሉ አውድመዋል።

የወታደራዊ ደህንነት ተንታኞች እንደገለጹት፣ ድሮኖቹ መጋዘኑን በትክክል መምታታቸውን ተከትሎ በስፍራው የነበሩት ሚሳኤሎችና ፈንጂዎች እርስ በርሳቸው መፈንዳት በመጀመራቸው በአካባቢው ሰፊ የመሬት መንቀጥቀጥ መሰል ንዝረትና እስከ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ የሚታይ ግዙፍ የእሳት ነበልባል ተመዝግቧል።

ይህ ጥቃት ሩሲያ በዩክሬን ግንባር ላይ ለምታደርገው የክረምት ወራት ጥቃት ያዘጋጀችውን የትጥቅ አቅርቦት በእጅጉ የሚያስተጓጉልባት መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16💔12👍4🤯1
#ኢራን#አሜሪካ ጥቃቶች በሰጠችው የአፀፋ ምላሽ በባሕረ ሰላጤው ሀገራት በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ላይ በርካታ ጥቃቶችን ሰነዘረች

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በ #ኩዌት፣ በ #ባሕሬን፣ በ #ጆርዳን እና በ #ኦማን በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የተቀናጀ የሚሳይል እና የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃቶች ማድረሱን ገለጸ። ጥቃቶቹ በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ሥፍራዎች ላይ በቅርቡ ለተሰነዘሩት የአሜሪካ ጥቃቶች የተሰጡ የአጸፋ ምላሾች መሆናቸውን አልጄዚራ እና ኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በኩዌት የሚገኙትን ዓሊ አል ሳሌም እና አሕመድ አል-ጃበር የአየር ኃይል ካምፖችን ማጥቃቱን የገለጸ ሲሆን፥ ጥቃቱ የሚሳይል ሥርዓቶችን፣ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎችን፣ የፓትሪዮት የአየር መከላከያ ባትሪዎችን፣ ራዳሮችን፣ ምሽጎችን እና መጋዘኖችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን አስታውቋል። በተጨማሪም ጥቃቶቹ በባሕሬን የሚገኘውን ሼክ ኢሳ የአየር ኃይል ካምፕ እና በጁፌር የሚገኘውን የአሜሪካ አምስተኛ የጦር መርከብ ሰፈር እንዲሁም በጆርዳን የሚገኘውን ልዑል ሐሰን የአየር ኃይል ካምፕ እና በኦማን የሚገኙ ራዳሮችን መምታታቸውን ገልጿል።

ኩዌት የአየር መከላከያዋ «የአየር ላይ ኢላማዎችን» ማክሸፉን የገለጸች ሲሆን፥ ጆርዳን በበኩሏ በርካታ ሚሳይሎችን ማክሸፏንና ምንም ዓይነት ከባድ ጉዳት ወይም ከፍተኛ ውድመት አለመድረሱን አስታውቃለች።

ኢራን ጥቃቶቹ በባንደር አባስ፣ በቄሽም ደሴት፣ በሲሪክ፣ በጃስክ እና በሌሎች የባሕር ጠረፍ አካባቢዎች አቅራቢያ በሚገኙ ወታደራዊ እና የክትትል መሠረተ ልማቶች ላይ በቅርቡ አሜሪካ ለሰነዘረችው ጥቃት ምላሽ መሆናቸውን የገለጸች ሲሆን፥ ቴህራን ጥቃቶቹ በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይም ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግራለች።

ሮይተርስ እንደዘገበው የቅርብ ጊዜዎቹ ጥቃቶች በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ያለውን ፍጥጫ በከፍተኛ ደረጃ የሚያባብሱ ሲሆን፥ ኢራን በባሕረ ሰላጤው በሚገኙ የአሜሪካ ተቋማት ላይ የሚሳይል እና የድሮን ጥቃቶችን በመሰንዘር የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመዝጋት በድጋሜ ዝታለች። ሆኖም የአሜሪካ ባለሥልጣናት ምንም እንኳን ውጥረቱ ቢጠናከርም ስልታዊው የውኃ መስመር ለንግድ መርከቦች ክፍት እንደሆነ ቀጥሏል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍119🕊2🤔1
አሜሪካ በኢራን ሦስተኛ ዙር ጥቃት ስትፈጽም፤ ኢራን የአጸፋ ርምጃ መውሰዷን አስታወቀች

አሜሪካ ዛሬ ሌሊት በኢራን ላይ ሦስተኛ ዙር ጥቃት ስትፈጽም፤ ቴህራን በምላሹ በቀጣናው የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ኢላማ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ እዝ (ሴንትኮም) ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ በማለፍ ላይ በነበረው የቆጵሮስ የእቃ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽማለች ሲል ወንጅሏል፡፡

ማዕከላዊ እዙ ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የመርከቧ አካል መቃጠሉንና የመርከቧ ሲቪል ሰራተኛ መሰወሩን ጠቅሶ፥ በዚህም ጉዞዋን መቀጠል እንዳልቻለች አመልክቷል፡፡

የአሜሪካ ጦር ጥቃቱን ተከትሎ በወሰደው ሦስተኛ ዙር ወታደራዊ ርምጃ የኢራን የሚሳኤል፣ የባህር ኃይል እና የድሮን ጣቢያዎችን ጨምሮ 140 ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል፡፡

ኢራን በምላሹ የኳታር የአል ኡዴይድ የአየር ኃይል ጣቢያን ጨምሮ በባህሬን፣ ኩዌት እና ጆርዳን በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች፡፡

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዛሬ ንጋት ላይ በጆርዳን በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ እና የድሮን ማከማቻን ጨምሮ ቁልፍ ኢላማዎችን መምታቱን ገልጿል፡፡

ስምምነቱን በመጣስ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ የሚገኙት አሜሪካ እና ኢራን ለሚቃጣባቸው ጥቃት የአጸፋ ርምጃዎችን እንደሚወስዱ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ በቀጣናው ያለው ውጥረት ተባብሶ መቀጠሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍6
በሳዑዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ፣ በተለይም የሕግ ሂደቶችና የፍርድ እርምጃዎችን እየጠበቁ ካሉ ዜጎች ጋር በተያያዘ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተሳተፈ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ አገር ለሚኖሩ ዜጎቹ ደህንነት፣ ጥበቃ እና ቆንስላዊ ድጋፍ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል ያለው ሚኒስቴሩ፣ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር በከፍተኛ የመንግሥት የሥልጣን እርከን ግንኙነቱን ቀጥሏል ብሏል፡፡

በተጨማሪም ሚኒስቴሩ በሪያድ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በጅዳ በሚገኘው ጠቅላላ ቆንስላ በኩል፣ ዜጎች ሰብዓዊ አያያዝ እንዲደረግላቸው፣ የቆንስላ ድጋፍ እንዲያገኙ እና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ተገቢው መፍትሔ እንዲፈለግ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር መደበኛ እና ገንቢ ግንኙነት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቦሌ አትላስ አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብና ንፋስ በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት ደረሰ

በትናንትናው ዕለት ከላይ በቪዲዮ እንደምትመለከቱት በአስደንጋጭ ሁኔታበዋና ከተማዋ ቦሌ አትላስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጣለው ኃይለኛ ዝናብ እና በነፈሰው ብርቱ ንፋስ ምክንያት...

ከአንድ የግንባታ ቦታ ላይ የብረት ቁሳቁሶች ተፈንቅለው በመውደቃቸው በአቅራቢያው በነበረ ዘመናዊ መኪና ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።

ምንም እንኳን በንብረት ላይ አደጋው ጉዳት ቢያስከትልም፣ በአምላክ ምስጋና ይግባና በአደጋው ወቅት በሰው ሕይወትም ሆነ አካል ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለ ተረጋግጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍5👀2🤔1🙏1
የቤት ኪራይ አልቀመስ ብሏል‼️
በአዲስ አበባ ከተማ እያጋጠመ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ መናር ከነዋሪዎች የመክፈል አቅም በላይ እየሆነና ጣሪያ እየነካ መምጣቱ ተሰምቷል።

በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እያሻቀበ የሚገኝ ሲሆን፣ ለአንድ መደበኛ ክፍል ቤት ከ25 ሺህ እስከ 30 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እየተጠየቀ ይገኛል።

ባለ ሁለት እና ባለ ሦስት መኝታ ክፍሎች ደግሞ ዋጋቸው በአስገራሚ ሁኔታ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ለነዋሪዎች ለመጥራት እንኳ የሚያስፈራ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነግሯል።

ይህ የቤት ኪራይ ዋጋ በዚህ ፍጥነት ሊያሽቀበቅብ የቻለባቸው ዋነኛ ምክንያቶች በሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች በጸጥታና አለመረጋጋት ምክንያት ደኅንነት ፍለጋ ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የሚደረገው ፍልሰት በከተማዋ ያለውን የቤት ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉ ነው።

በተጨማሪም በከተማዋ ለኮሪደርና ለተለያዩ ልማቶች ተብለው በርካታ መኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸውን ተከትሎ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በአንድ ጊዜ ወደ ኪራይ ገበያው እንዲገቡ መገደዳቸው በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ከፍተኛ አለመጣጣም ፈጥሯል።

ይህ ተደራራቢ ጫና ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየዳረጋቸው ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢4117👍2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
👍32
የባንኮች የማበደር ገደብ ተነሳ
የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ (ቁጥር 7) ስብሰባ ዋና ዋና ውሳኔዎችና የኢኮኖሚ አፈጻጸም አጭር መግለጫ:-

፩. ዋና ዋና የፖሊሲ ውሳኔዎች

📌የብድር ገደብ መነሳት፦ በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የዓመታዊ የብድር ዕድገት ገደብ (Credit Cap) ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ተወስኗል።

📌 የፖሊሲ ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ፦ የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔ (Policy Rate) በ1.0 በመቶ ነጥብ ከፍ በማለት ከ15 በመቶ ወደ 16 በመቶ እንዲያድግ ተደርጓል።

📌 የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ግዴታ (FX Surrender)፦ ላኪዎችና የውጭ ምንዛሬ አስገኚዎች ለባንኮች ገቢ የሚያደርጉት የውጭ ምንዛሬ ግዴታ ከ50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተወስኗል።

📌 የኮሚሽን ምጣኔ ቅነሳ፦ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ግዢ ጋር ተያይዞ የሚያስከፍሉት የኮሚሽን ምጣኔ ከ2.5 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

   ፪. የኢኮኖሚ አፈጻጸም ማጠቃለያ
📌 የኢኮኖሚ ዕድገት፦ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ዕድገት 9.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

📌የዋጋ ግሽበት፦ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም. ወደ 13.4 በመቶ ዝቅ ብሏል።

📌 የበጀት ጉድለት፦ የአገሪቱ የበጀት ጉድለት ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) አንጻር ወደ 0.9 በመቶ ወርዷል።

📌 የውጭ ኢኮኖሚ ክምችት፦ አጠቃላይ የውጭ ክፍያ ሚዛን ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ማሻሻያው ከመደረጉ በፊት ከነበረው አንጻር በ20 እጥፍ አድጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2
አሜሪካ ለሆርሙዝ ክፍያ ልጠይቅ‼️
ትራምፕ "አሜሪካ የሆርሙዝ ሰርጥ ጠባቂ' አድርገው ማወጃቸውን አስታወቁ።
በዚህም ለሆርሙዝ ሰርጥ ደህንነት ሲባል ዓለም አቀፍ የባህር ላይ ትራንስፖርት 20% ክፍያ እንዲፈጽም አዘዋል። ኢራን በበኩሏ ከራሷ ውጪ ማንም የሆርሙዝ ሰርጥ ደህንነት ጠባቂ እንደማይሆን ገልፃለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍5👀3🤡2🥱1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሟቹ የቀድሞ የኳታር አሚር ለቅሶ ለመድረስ ዶሃ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ፣ የቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሃማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን ተከትሎ የተሰማቸውን ሐዘን ለመግለጽ ዛሬ ሰኞ ዶሃ መድረሳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካን ቡድናቸው ሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ በኳታር ትራንስፖርት ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱላህ እና በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል ኢብራሂም አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ​“የእሳቸው ማለፍ ለአፍሪካም ሆነ ለመላው ቀጣና ትልቅ ኪሳራ ነው” ነው ሲሉ የኢሚሩ ሕልፈተ ሕይወት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት የሐዘን መልዕክት ገልጸዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2717👍4🤣4🥱1
የምርጫ ቀን ስለሆነ መንግስትም የለም በማለት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ
 
አቶ አክሊሉ አለማየሁ የተባለው ግለሰብ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ ሲዶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ደብተር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕድሜዋ 15 ዓመት የሚሆናትን ታዳጊ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፍዱ 4 ሰዓት ገደማ  የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅሟል።
 
ተከሳሹ 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድበት ዕለት ተበዳይን መንገድ ላይ ጠብቋት ዛሬ የምርጫ ቀን ስለሆነ መንግስትም የለም በማለት አንድ ጊዜ ወገቧ ላይ እና አንድ ጊዜ ትከሻዋ ላይ በመምታት እራሷን ከሳተች በኋላ ያለፍላጎቷ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞባታል።
 
የወረዳው ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት  ብርቱ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ልኳል።
 
የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ መዝገቡን ተመልክቶ ክስ መመስረቱን የአሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ  በየነ ጉዶ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ክሱ የቀረበለት የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ12 ዓመት  ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወስኗል፡፡
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤔125👍3
የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን፣ ሁሉም የበይነ መረብ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ሊያስገድድ መኾኑን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ፣ የበይነ መረብ ጣቢያዎች ተመዝግበው ብቻ እንዲሠሩ ለማስቻል የመገናኛ ብዙኀን ዋጁን ለማሻሻል ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ገልጧል።

አዋጁ፣ የበይነ መረብ ጣቢያዎች ምዝገባ በፈቃደኝነት ላይ ብቻ እንዲኾን የሚፈቅድ ነው።

በዚህ ምክንያት፣ ፌስቡክን፣ ቲክቶክን እና ዩትዩብን በመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይዘቶችን የሚያስተላልፉ አብዛኞቹ ድርጅቶችና ግለሰቦች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ሳይወስዱና እውቅናና ፈቃድ ሳያገኙ እየሠሩ እንደሚገኙ ባለሥልጣኑ ጠቅሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😱4👍3
ትምህርት ሚኒስቴር በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና አዲስ ማዕቀፍ አዘጋጅቷል።

ማዕቀፉ መምህራን በክረምት ስልጠና ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የሚሸጋገሩበት መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ በቀን 06/11/2018 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፣ ከአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ማስገባት መቋረጡን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ በቀጣይ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተዘጋጀ የስልጠና ማዕቀፍ፣ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

በ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠናውን ለመስጠት ስምንት አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መመረጣቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ለክረምት ስልጠናው የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች፦

1. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
2. ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
3. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
4. መቐለ ዩኒቨርሲቲ
5. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
7. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
8. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ተቋማት እና የስልጠናው አሰጣጥ አግባብነት ከትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ ከላይ ከተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በክረምት መምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና መስጠት የማይቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ከ2011 ዓ.ም በፊት ስልጠና ጀምረው ያላጠናቀቁ መምህራን ከዚህ በፊት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዲያጠናቅቁ እንዲደረግ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ይገልጻል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍106😢1
ለአንድ ቴሌቪዥን 850 ብር ታክስ‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከፌዴራል መገናኛ ብዙሃን ነው የተላክነው እያሉ ቤት ለቤት በመዞር የዲሽ ሳህን እየቆጠሩ በአንድ  ቴሌቪዥን 850 ብር ከእያንዳንዱ ሰው ታክስ እያስከፈሉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን አመታዊ የቴሌቪዥን ግብር 120 ሲሆን  ከመብራት ክፍያ ጋር አስር አስር ብር በየወሩ እንዲከፈል ተደርጓል። የአሁኑ ክፍያ መንግስት ያውቀዋል? የሚል ጥያቄ አስነስቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
3.69 ቢሊዮን ብር ያባከነው ተቋም
የፌዴራል ዋና ኦዲተር በ2018-2025 እ.ኤ.አ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ስር በተከናወኑት የዌልመል እና የጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት፣ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ ብክነትና የውል ጥሰት መፈጸሙን ይፋ አደረገ።

ዋና ዋና የኦዲት ግኝቶች፦

📌የገንዘብ ብክነት፦ "የዋጋ ማስተካከያ አይፈቀድም" የሚለው የውል ድንጋጌ ተጥሶ በተደረጉ ማሻሻያዎች 3.69 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ህገ-ወጥ ተጨማሪ ወጪ ተደርጓል።

📌የቅንጡ መኪናዎች ግዢ፦ በጨልጨል ፕሮጀክት ውስጥ በውል ያልተካተቱ፣ ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ የፈጁ የ2023 ሞዴል ቅንጡ ተሽከርካሪዎች (V6 እና Toyota Prado) ተገዝተው በተቋራጩ እጅ እንዲገቡ ተደርጓል።

📌የሰነድ ማጭበርበር፦ የ75 ሚሊዮን ብር የመስክ ተሽከርካሪዎች ግዢ የተጠናቀቀ ግንባታ ተደርጎ በተጭበረበረ ጊዜያዊ የክፍያ ማረጋገጫ ተፈጽሟል።

📌 ከፍተኛ መዘግየት፦ ፕሮጀክቶቹ ያለ አዋጭነት ጥናት በመጀመራቸውና በደካማ ክትትል ምክንያት ከ38 ወራት በላይ የዘገዩ ቢሆንም፣ በሚኒስቴሩ በኩል ምንም ዓይነት የመዘግየት ቅጣት አልተጣለም።

👉👉ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተሰጡትን የማስተካከያ ምክረ-ሃሳቦች በአስቸኳይ ተግባራዊ ካላደረገ፣ ጉዳዩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የሕግና የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ዋና ኦዲተሩ ማስጠንቀቁን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍5😢1
የአፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትሮችና የባንክ ገዥዎች በባንጁል የጋራ መግለጫ አወጡ

የአፍሪካ ሀገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የባንክ ገዥዎች ዓመታዊ ስብሰባ በባንጁል ተካሂዷል ። በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የብሬተን ዉድስ ተቋማት የአፍሪካ ገዥዎች፣ አህጉሪቱን ወደ ተሻለ ኢኮኖሚያዊ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ቁርጠኝነቶችን ይፋ አድርገዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሮቹ በዋናነት የሀገር ውስጥ የገቢ አሰባሰብን ማጠናከር፣ የመንግስት የገንዘብ አያያዝን ማሻሻል፣ የካፒታል ገበያዎችን ማሳደግ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋት የጋራ ግባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) እና የዓለም ባንክ (WBG) አፍሪካ የግብር ስርዓቷን ለማዘመን፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን ለመግታት እና በዲጂታላይዜሽን የታገዘ የግብር አስተዳደር ለመገንባት እያደረጉት ያለውን ጥረት በልዩ ትኩረት እንዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል።

የአፍሪካን መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማረጋገጥና የዕዳ ተጋላጭነትን ለመቋቋም፣ ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ምንጭ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት አመራሮቹ፤ ተቋማቱ በግሉ ዘርፍ ልማትና በተቋማዊ የመቋቋም አቅም ግንባታ ረገድ የሚያደርጉት ድጋፍ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍2🤯1