የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤4👍3
ቁፋሮ ማካሄድ ተከለከለ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በከተማዋ ክልል ውስጥ የሚካሄደውን የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፍለጋ፣ ምርት እና ስርጭት ሥርዓት ለማስያዝና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
በመመሪያው መሠረት የኅብረተሰቡን ደኅንነትና የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ፦
🛑የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲባል ከከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ፣
🛑ከመኖሪያ መንደሮችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በ500 ሜትር ራዲየስ ውስጥ፣
🛑ከወንዝ ዳርቻዎች በ30 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ቁፋሮ ማካሄድ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ነው።
"የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 191/2018" በሚል ተግባራዊ እንዲሆን የፀደቀው ይህ መመሪያ፤ ከማዕድን ቁፋሮ ጋር በተያያዘ በከተማዋ ይታዩ የነበሩ የአሠራር ክፍተቶችን በመድፈን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
@Addis_Reporter

❤9👍5
#ጤናመረጃ 🍋
10 አስገራሚ የሎሚ የጤና ጥቅሞች!
ሎሚን🍋 አዘውትሮ መጠቀም ከሚያስገኛቸው
ጥቅሞች ዋና ዋናዎቹን አጠር አድርገን እንያለን።
1) በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል፤ በቪታሚን ሲ የበለፀገ በመሆኑ ከጉንፋንና ከተለያዩ ተላላፊ ቫይረሶች ይከላከላል።
2) ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፤ ጠዋት በለጋ ውሃ መጠጣት በጉበት ውስጥ ያሉ መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድና አንጀትን ለማረጋጋት ይረዳል።
3) የቆዳን ውበት ይጠብቃል፤ የኮላጅን ምርትን በማፋጠን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፤ መልክን ያጠራል።
4) የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያለው ሲትሪክ አሲድ የካልሲየም ጠጠር እንዳይፈጠርና በሽንት እንዲወገድ ያደርጋል።
5) የደም ማነስን ይከላከላል፤ ሰውነታችን ከምግብ የሚያገኘውን የብረት (Iron) ንጥረ ነገር በቀላሉ እንዲመጥ ያግዛል።
6) ለአፍ ጠረን መፍትሔ ነው፤ በአፍ ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎችን በማጥፋት ጠረንን ያድሳል፤ የጥርስ ሕመምንም ያስታግሳል።
7) ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል፤ በውስጡ ያለው የፔክቲን ፋይበር የረሃብ ስሜትን የሚቀንስና ስብን ለማቃጠል የሚረዳ ነው።
8) የልብን ጤንነት ይጠብቃል፤ መጥፎ ኮሌስትሮልን በመቀነስ ለልብ ሕመም እና ለድንገተኛ ስትሮክ የመጋለጥ ዕድልን ያጠባል።
9) ካንሰርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያሉ ተፈጥሯዊ ውህዶች (Flavonoids) የካንሰር ሴሎች እንዳይፈጠሩና እንዳይስፋፉ ይረዳሉ።
10) የደም ግፊትን ያስተካክላል፤ በውስጡ የሚገኘው ፖታሲየም የደም ስሮችን በማዝናናት የደም ግፊት ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

❤29👍10🥰1👌1🤝1
የማይሞተው ብቸኛው የምድር ፍጡር
እርጅናን በመቀልበስ የሕይወት ዑደቱን ወደ ሕፃንነት በመመለስ ለዘላለም መኖር የሚችል “የማይሞት” አስገራሚ ፍጡር በባሕር ጥልቀት ውስጥ መገኘቱ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶችን አስደምሟል።
“ቱሪቶፕሲስ ዶርኒ” (Turritopsis dohrnii) የተባለውና በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ይህ የጄሊፊሽ (Jellyfish) ዝርያ በሕይወት ዘመኑ ላይ አደጋ፣ በሽታ ወይም እርጅና ሲደቅንበት የራሱን ሴሎች ሙሉ በሙሉ በማደስ ወደ መጀመሪያው የፅንስ (Polyp) ደረጃ የመመለስ አስደናቂ የተፈጥሮ ብቃት አለው።
ይህ ማለት ፍጡሩ ሲያረጅ ከመሞት ይልቅ ልክ እንደገና ተወልዶ ወደ ሕፃንነቱ ይመለሳል፤ ይህንን ሂደት ደግሞ ሳይሞት ለዘላለም ደጋግሞ ማከናወን ይችላል።
ተመራማሪዎች የዚህን ፍጡር የዲኤንኤ (DNA) ምስጢር ለመፍታት ሌሊትና ቀን እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን፣ ግኝቱ ለሰው ልጅ የእርጅና መከላከያ እና የካንሰር ሕክምና ምርምር ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ በመሆኑ በማኅበራዊ ሚዲያና በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

❤18👍9🤣5
በዘንድሮው ክረምት በጎፋ ከተማ የጎርፍ አደጋ ስጋት አይሆንም ተባለ
👉 ስጋት ባለባቸው አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር ስራ ተሰርቷል
በ2016 ዓ.ም በጎፋ ተከስቶ በነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። በመሆኑም በክረምት ወቅት ባለፉት ዓመታት በጎርፍ ምክንያት ሲከሰት የነበረውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ለመከላከል በተያዘው ዓመት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ የአደጋ ስጋት አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ያዕቆብ ዘካሪያስ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሜትሮሎጂ ባለሙያዎች የአካባቢውን የአየር ሁኔታ በመከታተል ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ስፍራ እንዲሰፍሩ የማድረግ ስራ መሰራቱን ነግረውናል። አክለውም የአደጋ ስጋት ሰራተኞች ከሜትሮሎጂ ባለሙያዎች ጋር በአጋርነት በመሆን አስፈላጊው ጥንቃቄ ስለተደረገ አስጊ በሆኑ ቦታዎች ላይ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ የተባሉ ቦታዎች ላይ ያሉ ነዋሪዎችን በማስነሳት አስተማማኝ ወደ ሆኑ ቦታዎች የማስፈር ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አቶ ያዕቆብ ዘካሪያስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤13👍7🙏3
የአሜሪካው ሴናተር ሊንድሴ ግራሃም በ71 ዓመታቸው ‹‹በድንገተኛ ህመም›› ማለፋቸውን ቢሯቸዉ አስታወቀ
ከደቡብ ካሮላይና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ግራሃም ከ2003 ጀምሮ በሴኔት ውስጥ አገልግለዋል
ቢሯቸዉ ባወጣው መግለጫ፤ ‹‹ቅዳሜ ምሽት የአሜሪካው ሴናተር ሊንድሴ ግራሃም በአጭር እና በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል›› ብሏል።
ከደቡብ ካሮላይና ግዛት የመጡት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባሉ ግራሃም፤ በ2002 ለሴኔት የተመረጡ ሲሆን በ2008፣ 2014 እና 2020 በድጋሚ ተመርጠዋል።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ወዳጅ የነበሩት ግራሃም፤ የሴኔት የበጀት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በህዳር ወር ምርጫ ለአምስተኛ ጊዜ ለስድስት ዓመት የሴኔት የሥራ ዘመን ለመወዳደር በዝግጅት ላይ ነበሩ።
ግራሃም በቅርቡ ወደ ኪቭ ተጉዘው የተመለሱ ሲሆን፤ ባለፈው አርብ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተው ነበር።

❤11👍7
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
❤3👍2
የኢራን አፀፋና የአሜሪካ ጥቃት
ኢራን የባህረ ሰላጤውን ሀገራት(ገልፍ) አጠቃች።
አሜሪካ አዳሯን በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ በኳታር፣ኩዌት፣ባህሬን ፣ዮርዳኖስ እና ኦማን ላይ ኢራን ጥቃት አድርሳለች ።
አረብ ኤሚሬቶችም ሚሳዔሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አክሽፋለች የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል።
በአሁኑ ሰዓት ኳታር ድርድር እያደረገች ብትገኝም ቴህራንና ዋሽንግተን ወደ መተኳኮሱ ገብተዋል።
ኢራን በሀገራቱ (የባህረ ሰላጤው) ላይ ከባድ ጥቃት ማድረሷን አሳውቃለች።
የአሜሪካ ጦር 140 ዒላማዎችን በሶስተኛው ዙር ጥቃቱ መምታቱንም አሳውቋል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሀይል በሆረወሙዝ ሰርጥ ላይ የቆጵሮስን ባንዲራ ያነገበች መርከብ መትቷል በሚል ነው ማዕከላዊ ዕዙ ኢራን ላይ ጥቃት የሰነዘርኩትም ብሏል።
በሶስት ቀናቱ ጥቃት ሴንትኮም ከ300 በላይ ዒላማዎችን መምታቱንም አሳውቋል።
አዳሩንም የሚሳዔል ማከማቻዎችን፣የድሮን ማዕከላትን፣የባህር ሀይሉን ሀብት ፣የመግባቢያ ትስስሮችን እና ሌሎች ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎችን ማጥቃቱን አሳውቋል።
ኢራንም የአሜሪካ ጦር ሰፈር ባለባቸው የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሷን ይፋ አድርጋለች።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን እና ቢቢሲ ነው።

❤15👍6🕊2💔2
በቀዶ ሕክምና የስፔሻሊቲ ትምህርትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሔደበት ወቅት ነው።
ጤና ሚኒስቴር ለስፔሻሊስት ሐኪሞች በሚሰጠው የቀዶ ሕክምና ትምህርት በAI የታገዙ ኮርሶችን አካቶ ለመተግበር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ደኤታ ሳህረላ አብደላ ገልፀዋል፡፡
የጤና ስርዓቱ በቴክኖሎጂ የተቃኘ እንዲሆን ሚኒስቴሩ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመሥራት ከስምምነት መድረሱን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ጤና ሚኒስቴር ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙ የጤና አገልግሎቶችን መተግበር መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሕክምና አሰጣጥን ለማሳለጥ፣ አንዳንድ የዲያግኖስቲክ ችግሮችን ለማወቅ የሚፈጀውን ጊዜ ለማሳጠር፣ የላቦራቶሪ ውጤት ትክክለኛነትን ለማሻሻል፣ በሰው ዓይን ሊታዩ የማይችሉ ነገሮች ጎልተው እንዲታዩ ለማድረግና በሌሎችም ሕክምናዎች ላይ ከፍተኛ ዕገዛ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ አብራርተዋል።
ይሁን እንጂ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚሰጣቸው መረጃዎችን የማጥራት እንዲሁም የቁጥጥር ሥራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ #ሪፖርተር

❤9👍6🙊3
የሀይል ስርቆትን በተመለከተ ጥቆማ ለሚሰጥ ከተጣለው ቅጣት የ25 በመቶ ኮሚሽን እንደሚያገኝ ተገለፀ
ሀምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ)፦ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆትን ለመግታት እና በመሰረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል የተቀናጀ የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል ።
በአገልግሎቱ የሽያጭና የደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ይሔይስ ስዩም
የሀይል ስርቆቱ በዋናነት የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች በትክክል እንዳይቆጥሩ በማድረግ ወይም መስመር ወደ ቆጣሪው ከመግባቱ በፊት በቀጥታ በመጥለፍ ወደ መኖሪያ ቤቶችና የኢንዱስትሪ ማሽኖች በመውሰድ እንደሚፈጸም ተናግረዋል ።
በ2017 በጀት ዓመት በተደረገው ከፍተኛ ክትትልና የቁጥጥር ስራ፣ የሃይል ስርቆት ጨምሮ ከባከነ ሃይል 259 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል።
የኤሌክትሪክ ሃይል ስርቆትን በዘላቂነት ለመከላከል ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሰጥ የተደራጀ የአሰራር ስርዓት፣ ፖሊሲና መመሪያ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን ጠቁመዋል ።
በዚህም መሰረት የሃይል ስርቆት ለሚጠቁሙ ደንበኞች ከተጣለው ቅጣት ላይ የ25 በመቶ ኮሚሽን ክፍያ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ አስረድተዋል ።
ለአብነትም አንድ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ በፈጸመው የቴክኒክ ስርቆት ምክንያት አንድ ሚሊዮን ብር ቢቀጣ፣ ጥቆማውን ያቀረበው ግለሰብ የ250 ሺህ ብር የገንዘብ ማበረታቻ በህጋዊ አሰራር ያገኛል።
የኤሌክትሪክ ኔትወርክ መሰረተ ልማት የጋራ ሀብት በመሆኑ ፣ የሃይል ስርቆት የሚፈጽሙ አካላትን በማጋለጥ ረገድ ህብረተሰቡ የበኩሉን ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

❤11👍9🤪3
የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ለአከራዩች የሰጠዉን መብት ግምት ዉስጥ እንዲያስገባ ተጠየቀ
በተከራይ እና በአከራይ መካከል የሚኖርን ሰላማዊ ግንኙነት ታሳቢ ያደረገ ስርአት እንዲኖርም ተጠይቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከዛሬ ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደራቸውን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። ሪፖርቱን ተከትሎ የምክር ቤት አባላት ምላሽ እና ማብራሪያ ያስፈልጓቸዋል ያሏቸዉን ጥያቄዎች አንስተዋል።
የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ መኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን የተመለከተ ጥያቄ አቅርበዋል።
ዶ/ር ሲሳይ "አዋጁ ክፍተቶች ያሉት ይመስለኛል። በፍጥነት የወጣ በመሆኑ የአከራዩንም ሆነ የተከራዩን ህብረተሰቡን ፍላጎት በማገናዘብ አማካኝ የሆነ ነገር ይዞ መቷል ብዬ አላምንም" ብለዋል።
መሻሻል የነበረባቸው ጉዳዩች ያሉ ቢሆንም ስልጣኑ የፌደራል መንግስት ስለሆነ ብዙ ልንል ባንችልም ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ አፈፃፀሙ ግን በደንብ መታየት ያለበት ነገር መሆኑን ማንሳት አለብን ሲሉ ለምክር ቤቱ ገልፀዋል።
የምክር ቤት አባሉ በቀረበዉ ሪፖርት መሠረት 5 መቶ ሺህ የአከራይ ተከራይ ዉል ተደርጓል የሚለዉን በማስታወስ ይህ 5 መቶ ሺህ አባወራ አለ እንደማለት መሆኑን ይገልፃሉ።
"ይህ 5 መቶ ሺህ አባወራ በስሩ አራት ሰዉ አለ ብንል ሁለት ሚሊዮን ህዝብ ማለት ነዉ፤ እያወራን ያለነዉ ስለዚህ ህዝብ ነዉ ትኩረት ሰጥተን ማየት አለብን" ብለዋል።
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ በየአመቱ የኪራይ መጠን እየተጠና ሊጨምር እንደሚችል ያስቀምጣል።
ዶ/ር ሲሳይ ይህንን በማስታወስ" ዘንድሮ ተጠንቶ ቀረበ የተባለዉ ጭማሪ በሁለት አመቱ ነዉ፤ አዋጁ እንኳን ለአከራዩች የሰጠዉን መብት እኛ እየነፈግን ነዉ።" ሲሉ አስረድተዋል።
ይህ የሚመለከተው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ጥናቱን በየአመቱ መስራት ይገባዋል ሲሉም አክለዋል።
አሁን ለዚህ በጀት አመት ተሰራ የተባለዉ ጥናት ምን ያህል መሠረታዊ ችግርን ይፈታል ወይ? የሚል ሀሳብ አለኝ ሲሉም ጠይቀዋል።
የማዕከላዊ ስታስቲክስ አገልግሎት በየአመቱ ከኑሮ ዉድነት እና የዋጋ ጭማሪዎች ጋር አያይዞ የሚያወጣዉን ጥናት መሠረት አድርጎ ሌላ ጥናት ሳያስፈልግ ጭማሪውን መወሠን ይቻላል ያሉት ዶ/ር ሲሳይ ለሌላ ጥናት ሀብት ማባከን አያስፈልግም ይላሉ።
ከተማ አስተዳደሩ ስለ ተከራዩች ብቻ ሳይሆን የአከራዩችን መብት ግምት ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል ተብሏል።
ለምክር ቤት አባሉ "አሁን ላይ በሁለት አመት ነዉ እያሰብን ያለነዉ ፤ አንድ አመት በዝምታ ነዉ የታለፈዉ ያ ማለት የአከራዩን መብት ከአዋጁ አንፃር የሚጥስ ነዉ" ሲሉ ገልጸዋል።
በምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዩርጊስ የስታትስቲክስ አገልግሎት ጥናት የሀገር አቀፍ ጥናት በመሆኑ ለከተማዉ ቤቶች ጥናቱን ለዋጋ ጭማሪ መሠረት በማድረግ መጠቀም አንችልም ብለዋል።
የከተማዋ አስተዳደሩ በዚህ አመት ለኪራይ ዋጋ ጭማሪ ያስጠናዉ ጥናት የስታቲስቲክስ አገልግሎት ያስጠናዉንም ያካተተ መሆኑን በመግለፅ ለሁለቱም አካላት እኩል ሊጠቅም የሚችል ነዉ ብለዋል።

❤18👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቻይና የጎርፍ አደጋ በአንድ የእርባታ ማዕከል ላይ ባደረሰው ውድመት ምክንያት ወደ 1,000 የሚጠጉ እባቦች አምልጠዋል።
በጣም መርዛማ የሆኑ የኮብራ ዝርያዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳቢ እንስሳት አሁን ባሉበት አይታወቅም።
በአሁኑ ጊዜ የአካባቢው ነዋሪዎች ከጎርፍ አደጋው ተርፈው ለመቆየት መታገል ብቻ ሳይሆን ከእባቦች ጋር እንዳይገናኙም ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

🤣11👍9❤4😱4👀2🙉2😢1🤪1
" አትገቡም !! "
ግብረሰዶማውያንን የጫነችው የቅንጦት መርከብ በቱርክና ግብፅ ወደቦች እንዳትገባ ተከለከለች።
ከሰሞኑን " አትላንቲስ ኢቨንትስ " በተባለ የአሜሪካ የጉዞ ድርጅት የተከራየችና 2,000 ገደማ ግብረሰዶማውያንን የጫነች " ስካርሌት ሌዲ " የተሰኘች የሜዲትራኒያን ባህር የቅንጦት መርከብ ወደ ቱርክ እና ግብፅ ወደቦች እንዳትገባ ተከልክላለች።
መርከቧ በቱርክ ኩሻዳሲ እና ኢስታንቡል ወደቦች እንዳታርፍ የተከለከለች ሲሆን፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ውሳኔው የጉዞው ዓላማ ከሀገሪቱ ሞራላዊና ሥነ-ምግባራዊ እሴቶች እንዲሁም ማኅበራዊ ደንቦችና እሴቶች ጋር ስለማይጣጣም መሆኑን ገልጸዋል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪች ካምቤል በኩባንያው 36 ዓመታት ታሪክ ውስጥ እንዲህ ያለው ንገረ ሲገጥማቸው የመጀመሪያ እንደሆነ ገልጸዋል።
መርከቧ ከቱርክ እገዳ በኋላ የጉዞ አቅጣጫዋን ወደ እስክንድርያ ግብፅ ብታዞርም፣ የግብፅ ባለሥልጣናትም መርከቧ ወደ ሀገሪቱ የባህር ክልል እንዳትገባ አግደዋታል።
ግብፅ ለእገዳው የሰጠችው ይፋዊ ማብራሪያ ባይኖርም፣ ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን አስታውሶ በውሳኔው መደነቁን ገልጿል።
በእነዚህ እገዳዎች ምክንያት ተሳፋሪዎች በግብፅ ሊያደርጓቸው የነበሩት የፒራሚድ እና የታሪክ ስፍራዎች ጉብኝቶች የተሰረዙ ሲሆን፣ መርከቧ መስመሯን ቀይራ ወደ ክሬት ግሪክ እና ኮቶር ሞንቴኔግሮ ለማምራት ተገድዳለች።
መረጃው ከ ' ዘ-ጋርዲያን ' ነው የተወሰደው።

👍47❤27👌2🤯1🌚1💯1🤪1
የዓለም ባንክ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ድጋፎች የፖሊሲ ለውጦች አደረገ
የዓለም ባንክ ከ2027 እስከ 2036 ያለውን የ10 ዓመታት የአጋርነት ማዕቀፍ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት 10ዓመታት ቅድሚያ ይሰጣቸው የነበሩ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ሙሉ በሙሉ ከዕቅዱ ውጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ሪፖርተር የተመለከተው የዓለም ባንክ አዲስ የስትራቴጂ ሰነድ ትኩረቱን በዋናነት በየዓመቱ ወደ ሥራው ዓለም ለሚቀላቀሉ ወደ ሁለት ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ላይ አድርጓል፡፡
ግዙፍ በመንግሥት የሚመሩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን፣ ዋና ዋና የአስፋልት መንገዶችንና የቱሪዝም ዘርፍን በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ሙሉ በሙሉ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች ዝርዝር ውጪ አድርጓቸዋል፡፡
👉የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ከዕቅዱ ውጪ እንዲሆኑ የተደረጉት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባደረገችው ኢንቨስትመንት በቂ የማመንጨት አቅም ስላላት ሲሆን፣ የቱሪዝም ዘርፍ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታና የመሠረተ ልማት ሁኔታ መሻሻል እስከሚታይበት ድረስ ከዝርዝሩ ውጪ እንዲሆን መደረጉን ጠቁሟል፡፡
የከተማ አውራ ጎዳናዎችን የመገንባት ዕቅድም ቀርቶ፣ በተመሳሳይ መልኩ የገጠር መንገዶችን ወደ ማስፋፋት እንዲዞር የተደረገ ሲሆን፣ ይህም አርሶአደሩ ምርቱን በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲያቀርብ ለማገዝ፣ የጉምሩክ አሠራርን ለማዘመንና የወጪ ንግድ ወጪን ለመቀነስ ያለመ አዲስ መዋቅራዊ አቅጣጫ መሆኑ ተመልክቷል።
👉ባንኩ በቀጣይ እቅዶቹ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ማስተካከል፣ የኃይል መቆራረጥን መቀነስና በሚሊዮኖች ለሚቆጠር ሕዝብ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን አስተማማኝ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

❤11👍8🤣6🤷2🤪1
🔴የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ ኩርስክ ግዛት የሚገኘውን ግዙፍ የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎች ዴፖ አወደሙ‼️
የዩክሬን ልዩ ኃይል በሩሲያ የድንበር ቀጠና በሆነው የኩርስክ (Kursk) ግዛት ውስጥ እስከዛሬ ከተሰነዘሩት እጅግ ስልታዊ የተባለውን ጥቃት መፈጸሙን የኪየቭ የጦር እዝ ይፋ አድርጓል።
በጥቃቱ የዩክሬን የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ድሮኖች የሩሲያ ጦር ለሰሜን ኮሪያ ሰራሽ ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና ለከባድ መሣሪያ ጥይቶች ማከማቻነት ይጠቀምበት የነበረን አንድ ግዙፍ ወታደራዊ መጋዘን ሙሉ በሙሉ አውድመዋል።
የወታደራዊ ደህንነት ተንታኞች እንደገለጹት፣ ድሮኖቹ መጋዘኑን በትክክል መምታታቸውን ተከትሎ በስፍራው የነበሩት ሚሳኤሎችና ፈንጂዎች እርስ በርሳቸው መፈንዳት በመጀመራቸው በአካባቢው ሰፊ የመሬት መንቀጥቀጥ መሰል ንዝረትና እስከ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ የሚታይ ግዙፍ የእሳት ነበልባል ተመዝግቧል።
ይህ ጥቃት ሩሲያ በዩክሬን ግንባር ላይ ለምታደርገው የክረምት ወራት ጥቃት ያዘጋጀችውን የትጥቅ አቅርቦት በእጅጉ የሚያስተጓጉልባት መሆኑ ተገልጿል።

❤16💔12👍4🤯1