ወደ ሚዛን አማን የቅደመ ምረቃ በረራ ጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚዛን አማን ከተማ የሚያደርገውን የቅደመ ምረቃ በረራ በዛሬው ዕለት ጀምሯል።
አየር መንገዱ ወደ ሚዛን አማን ከተማ በሳምንት ሦስት ቀናት በረራ የሚያደርግ ሲሆን÷ ይህም ለማሕበረሰቡ ፈጣን፣ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ ያስችላል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኤርፖርቶች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጌታነህ አደራ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ ፍቅሬ አማን እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ሀገር ውስጥ የበረራ አድማሱን እያሰፋ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
@Addis_Reporter

❤13👍4😢1
መረጃ‼️
አብዛኛው አክሲዮኑ ለግል ባለሃብቶች የተሸጠው የፓኪስታን አየር መንገድ፣ የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ወልደ ማርያምን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አድርጎ ለመቅጠር ማሠቡን ብሉምበርግ ዘገበ።
አየር መንገዱ በመጪው እሁድ የተወልደን ሹመት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች እንደነገሩት የዜና ምንጩ ጠቅሷል።
የፓኪስታን አየር መንገድ "በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት" እና "በእዳ" ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራ ከተዳረገ በኋላ ለዓመታት በመንግሥት ሲደጎም የቆየ አየር መንገድ ነው።
ኾኖም ካለፈው ሚያዝያ ወዲህ ባለሃብቶች የአየር መንገዱን 75 በመቶ አክሲዮን የገዙት ሲኾን፣ ቀሪውን 25 በመቶ ከመንግሥት ለመግዛት እያሰቡ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

❤15👍4🥰1👌1
ኢትዮጵያ ለኬንያ 1 ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በ24 ብር ከ07 ሳንቲም ለማቅረብ የሚያስችላትን ስምምነት ተፈራረመች።
በስምምነቱ መሠረት፣ የኬንያው የኤሌክትሪክ ኃይል ኩባንያ በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል 24 ብር 07 ሳንቲም እንዲሁም ለዲማንድ ቻርጅ 1 ሺሕ 10 ብር ከ89 ሳንቲም እንደሚከፍል ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።
አዲሱ የኃይል ሽያጭ ስምምነት፣ በሁለቱ አገራት መካከል የኤሌክትሪክ ንግድን ለማጠናከር፣ በድንበር አካባቢዎች አስተማማኝ የሆነ የኃይል አቅርቦት ለማስፋፋትና የምሥራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከአራት ዓመት በፊት በደረሱበት 25 ዓመታት የሚዘልቅ የኃይል ሽያጭ ስምምነት መሠረት፣ ኬንያ አንድ ኬሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በ6 ነጥብ 50 የአሜሪካ ሳንቲም ስትገዛ ቆይታለች።
ኢትዮጵያ የኃይል መቨጫ ዋጋውን እንደገና ለመከለስ፣ ሦስት ዓመት መጠበቅ እንዳለባት በስምምነቱ ላይ ተገልጦ ነበር።

🤣11❤10👍6
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን ከግብፅ ተረከበች
በአዲስ አበባ በተካሄደው 22ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር የሚኒስትሮች ምክር መጠናቀቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ የተቋሙን የሊቀመንበርነት መንበር ከግብፅ በይፋ ተረክባለች።
ይህ የሥልጣን ሽግግር ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ገበያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የአባል ሀገራቱን የኃይል አውታሮች ማስተሳሰር፣ የኃይል ንግድን ማስፋፋት እና የታዳሽ ኃይል ልማትን ማበረታታት በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በተለይም በዓለም ባንክ የሚደገፈው የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የሪትሬድ-ኢኤ ፕሮጀክት ቀጣናዊ የኃይል ግብይትን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተጠቁሟል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ እንደተናገሩት፣ በጉባኤው ላይ የኤሌክትሪክ የኃይል ገበያ ማዕከል ዋና መቀመጫን ከመወሰን ጋር ተያይዞ ከግብፅ ጋር የነበሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ሰፊ ድርድር መደረጉን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ልዩነቶች የአባል ሀገራቱን አንድነት እንዳይከፋፍሉ የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከርና በጋራ መግባባት ላይ መድረስ ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ በአዲሱ የሊቀመንበርነት ዘመኗ ካላት የኃይል ትርፍ በመነሳት፣ እንደ ኬንያ፣ ሱዳንና ጅቡቲ ካሉ የጎረቤት ሀገራት ጋር የጀመረችውን የኮሪደር ትስስር ይበልጥ በማጠናከር የቀጣናውን የኃይል ደህንነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታውቃለች።

❤17👍8
#እንዲያውቁት‼️
የኪራይ ውል ማሻሻያው ለ2 ዓመታት ጸንቶ ይቆያል።
11.5 በመቶ ሆኖ የጸደቀዉ በአዲስ አበባ የ2019 በጀት ዓመት የቤት #ኪራይ ዓመታዊ የጭማሪ ጣሪያ ለ2 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ከዚህ ተመን በላይ መጨመር በጥብቅ የተከለከለ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
📣ከህጋዊ አሰራር ውጪ የሚደረጉ "የመንደር ውሎች" የተከለከሉ ሲሆን ውል በማያድሱና ህግ በሚተላለፉ አካላት ላይ ቅጣት ይጣላል።
የውል እድሳት ጊዜያቸው አልፎ አከራይም ተከራይም አብረው ኖረው እድሳት ሳይፈጽሙ የተገኙ፦
💸እስከ 2 ወር ከቆዩ የ1 ወር የቤት ኪራይ፣
💸3 ወር እና ከዚያ በላይ የቆዩ የ2 ወር የቤት ኪራይ ቅጣት ይከፍላሉ።
💸አዲስ ተከራይ አስገብተው ውል ያላደሱ እና ያላስመዘገቡ የ1 ወር የቤት ኪራይ ይቀጣሉ።
💸በጥቆማ ወይም በክትትል ውል ያላደሱ ወይም ያላስመዘገቡ መሆናቸው ከተረጋገጠ ደግሞ ከ1 እስከ 3 ወር የሚደርስ የኪራይ መጠን ቅጣት እንደሚጣልባቸው ቢሮው አሳውቋል።

👍5❤4🎉1
ህወሐት ሙሉ በሙሉ በራሱ ኃይል ላይ ብቻ እንደሚተማመን ቃል አቀባዩ ተናገሩ‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ላይ ሕወሓት፣ ኤርትራ እና ሱዳን በጋራ እየሠሩ መሆኑን በመጥቀስ ክስ ሰንዝረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ሁኔታ በ1983 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. በ1991) የደርግ ሥርዓት እንዲወድቅ ካደረገው ጥምረት ጋር በማመሳሰል የገለጹት ሲሆን፣ ጥምረቱ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚያመጣው አደጋ ባይኖርም ከጀርባው ግን ስማቸውን ያልጠቀሷቸው የውጭ አካላት እየመሩት መሆኑን አመልክተዋል።
ይሁን እንጂ ሕወሓት ኤርትራን እና ሱዳንን ያካተተ ጥምረት ፈጥሯል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡበትን ክስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓል። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሚካኤል አስገዶም ለክሱ በሰጡት ምላሽ፥ ድርጅታቸው አብረውት እንዲሰለፉና እንዲዋጉለት የውጭ አካላትን በፍጹም ጋብዞ እንደማያውቅ ገልጸዋል። ቡድኑ ከየትኛውም የውጭ ኃይል ወታደራዊ ድጋፍ እንደማይፈልግና ሙሉ በሙሉ በራሱ ኃይል ላይ ብቻ እንደሚተማመን አስታውቋል።

❤19👍2
አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአሜሪካ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ሕጋዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመ።
በአሜሪካ የአገር ውስጥ ደሕንነት መሥሪያ ቤት ሥር የሚገኘው የዜግነትና የፍልሰት አገልግሎት በአገሪቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠው ከለላ በመጪው ሐምሌ 10 ቀን 2018 እንደሚያበቃ ትላንት አርብ አስታውቋል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለሶርያ፣ ሶማሊያ፣ የመን፣ ደቡብ ሱዳን እና ምያንማር ዜጎች የተሰጠው ጊዜያዊ ከለላ በተመሣሣይ ቀን ያበቃል።
ውሳኔው የሚመለከታቸው የሔቲ ዜጎች ከቀሪዎቹ አምስት አገራት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በአሜሪካ ለመቆየትና ለመሥራት የሚፈቅድላቸውን ከለላ ያጣሉ።
ይህ ከለላ የተፈጥሮ አደጋ፣ የትጥቅ ግጭት ወይም ሌሎች ያልተለመዱ አስገዳጅ ሁኔታዎች ከገጠማቸው አገራት ወደ አሜሪካ የገቡ ሰዎች በአገሪቱ እንዲቆዩ እና በሕጋዊ መንገድ እንዲሠሩ የሚፈቅ ነው።
ከለላው የተሰጣቸው በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ቢመለሱ “በግል ደሕንነታቸው ብርቱ ሥጋት አይገጥማቸውም” በሚል አመክንዮ በአገሪቱ የመቆየትና የመሥራት ዕድላቸው እንዲያበቃ የተወሰነው ባለፈው ታኅሳስ 2018 ነበር።

❤6👍5😢1
ኢራን ትራምፕን ለመግደል‼️
እስራኤል ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በእሱ ላይ የግድያ ሙከራ ለማድረግ እያቀደች እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ እንዳላት አለምአቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የአሜሪካ መንግስት እና ኢራን በዚህ ሪፖርት ላይ ምላሽ አልሰጡም።
ነገር ግን ዋሽንግተን ቀደም ሲል ኢራን ትራምፕን ለመግደል ያደረጓቸውን በርካታ ሙከራዎች እንዳከሸፈች ተናግራለች።

👍14🤪6❤4
ከ11.5 በመቶ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ በላይ የሚጠይቁ አከራዮች እስከ ሦስት ወር የኪራይ ክፍያ ቅጣት ይጣልባቸዋል - የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዘንድሮው በጀት ዓመት የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5 በመቶ እንዲሆን ወስኗል፡፡
ይህንን ሕግ በሚተላለፉ አከራዮች ላይ ከባድ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣል ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ተናግረዋል::
ኃላፊዋ እንደገለጹት ይህ የጭማሪ ጣሪያ የተወሰነው የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ፣ የተከራዮችን የመክፈል አቅም፣ የኑሮ ውድነትን እና የዋጋ ግሽበትን ታሳቢ ያደረገ ጥልቅ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶበት ነው

❤14🤣11🤯3🤡3👍2
የዘውዲቱ ሆስፒታል በ90 ቀናት ውስጥ 17 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ነጻ ህክምና ለመስጠት እቅድ መያዙን አስታወቀ
የዘውዲቱ ሆስፒታል የአስተኝቶ ህክምና ዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ወንደሰን በላችሁ ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት ሆስፒታሉ በክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።በተለያዩ ቦታዎች በመገኘትና ድንኳን በመትከል ነጻ የህክምና እና የዕይታ ልየታ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በዚህም ክብር ለአረጋውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት ማቆያ ውስጥ በመገኘት አራት ሀኪሞች፣ ስድስት ነርሶች፣ የአይን፣ የጥርስ እና የስነ-አእምሮ ባለሙያዎችን ባካተተ ቡድን ለዜጎች ህክምና ሰጥቷል።200 ለሚሆኑ ሰዎች የዕይታ እና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።ከተጠቃሚዎቹ መካከል ከዚህ ቀደም የደም ግፊትና የስኳር ህመም የነበረባቸው ሰዎች የተገኙ ሲሆን እዛው ህክምናቸውን እንዲቀጥሉ ምክር ተሰጥቷቸዋል።
ዶክተር ወንደሰን አክለው እንደተናገሩት አራት ሰዎች በአይን ሞራ ግርዶሽ ፤ ሁለት ሰዎች በትራኮማ በሚመጣ የአይን ኢንፌክሽን ተጠቅተዋል።ሶስት ሰዎች ደግሞ የዕይታ ችግር ስላለባቸው መነጽር እንደሚያስፈልጋቸው ተለይተዋል። ይህ የነጻ ህክምና መርሃ ግብር ለ90 ቀናት ሲቆይ በሁለት የአረጋውያን መርጃ ድርጅቶች በቀጣይ ተመሳሳይ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷ ።17 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በነጻ ህክምናዉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

❤21👍4
“ለሻዕቢያ ከምገረድ፣ ለብልጽግና ብንበረከክ እመርጣለሁ”‼️
የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም መጠይቅ፣ ከህወሓት ጋር ተድርጎ ለሻዕቢያ ከመገረድ በብልጽግና አንገት መድፋት ይሻለኛል ብለዋል፡፡ ኬሪያ ከፋና ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ትግራይን በበላይ የተቆጣጠሩትን እነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን የትግራይን ሕዝብ ለሻዕቢያ አሳልፈው በመስጠት ወንጅለዋል፡፡
ኬሪያ የቀድሞ ድርጅታቸው ህወሓት ትግራይን ለማጥፋት ይመኛል ላሉት ሻዕቢያ “ተላላኪ ሆኖ እየተገረደ” ነው ብለዋል፡፡ ህወሓት “የብልጽግና ተንበርካኪ መሆን የለብንም ነው የሚለን” ያሉት ኬሪያ፣ “ለሻዕቢያ ከምገረድ እዚህ ብንበረከክ ነው የምመርጠው” ብለዋል፡፡

❤26🤪16🙉7👍3🤔3
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤4👍3
ቁፋሮ ማካሄድ ተከለከለ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በከተማዋ ክልል ውስጥ የሚካሄደውን የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፍለጋ፣ ምርት እና ስርጭት ሥርዓት ለማስያዝና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
በመመሪያው መሠረት የኅብረተሰቡን ደኅንነትና የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ፦
🛑የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲባል ከከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ፣
🛑ከመኖሪያ መንደሮችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በ500 ሜትር ራዲየስ ውስጥ፣
🛑ከወንዝ ዳርቻዎች በ30 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ቁፋሮ ማካሄድ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ነው።
"የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 191/2018" በሚል ተግባራዊ እንዲሆን የፀደቀው ይህ መመሪያ፤ ከማዕድን ቁፋሮ ጋር በተያያዘ በከተማዋ ይታዩ የነበሩ የአሠራር ክፍተቶችን በመድፈን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

❤9👍5
#ጤናመረጃ 🍋
10 አስገራሚ የሎሚ የጤና ጥቅሞች!
ሎሚን🍋 አዘውትሮ መጠቀም ከሚያስገኛቸው
ጥቅሞች ዋና ዋናዎቹን አጠር አድርገን እንያለን።
1) በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል፤ በቪታሚን ሲ የበለፀገ በመሆኑ ከጉንፋንና ከተለያዩ ተላላፊ ቫይረሶች ይከላከላል።
2) ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፤ ጠዋት በለጋ ውሃ መጠጣት በጉበት ውስጥ ያሉ መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድና አንጀትን ለማረጋጋት ይረዳል።
3) የቆዳን ውበት ይጠብቃል፤ የኮላጅን ምርትን በማፋጠን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፤ መልክን ያጠራል።
4) የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያለው ሲትሪክ አሲድ የካልሲየም ጠጠር እንዳይፈጠርና በሽንት እንዲወገድ ያደርጋል።
5) የደም ማነስን ይከላከላል፤ ሰውነታችን ከምግብ የሚያገኘውን የብረት (Iron) ንጥረ ነገር በቀላሉ እንዲመጥ ያግዛል።
6) ለአፍ ጠረን መፍትሔ ነው፤ በአፍ ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎችን በማጥፋት ጠረንን ያድሳል፤ የጥርስ ሕመምንም ያስታግሳል።
7) ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል፤ በውስጡ ያለው የፔክቲን ፋይበር የረሃብ ስሜትን የሚቀንስና ስብን ለማቃጠል የሚረዳ ነው።
8) የልብን ጤንነት ይጠብቃል፤ መጥፎ ኮሌስትሮልን በመቀነስ ለልብ ሕመም እና ለድንገተኛ ስትሮክ የመጋለጥ ዕድልን ያጠባል።
9) ካንሰርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያሉ ተፈጥሯዊ ውህዶች (Flavonoids) የካንሰር ሴሎች እንዳይፈጠሩና እንዳይስፋፉ ይረዳሉ።
10) የደም ግፊትን ያስተካክላል፤ በውስጡ የሚገኘው ፖታሲየም የደም ስሮችን በማዝናናት የደም ግፊት ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

❤29👍10🥰1👌1🤝1
የማይሞተው ብቸኛው የምድር ፍጡር
እርጅናን በመቀልበስ የሕይወት ዑደቱን ወደ ሕፃንነት በመመለስ ለዘላለም መኖር የሚችል “የማይሞት” አስገራሚ ፍጡር በባሕር ጥልቀት ውስጥ መገኘቱ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶችን አስደምሟል።
“ቱሪቶፕሲስ ዶርኒ” (Turritopsis dohrnii) የተባለውና በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ይህ የጄሊፊሽ (Jellyfish) ዝርያ በሕይወት ዘመኑ ላይ አደጋ፣ በሽታ ወይም እርጅና ሲደቅንበት የራሱን ሴሎች ሙሉ በሙሉ በማደስ ወደ መጀመሪያው የፅንስ (Polyp) ደረጃ የመመለስ አስደናቂ የተፈጥሮ ብቃት አለው።
ይህ ማለት ፍጡሩ ሲያረጅ ከመሞት ይልቅ ልክ እንደገና ተወልዶ ወደ ሕፃንነቱ ይመለሳል፤ ይህንን ሂደት ደግሞ ሳይሞት ለዘላለም ደጋግሞ ማከናወን ይችላል።
ተመራማሪዎች የዚህን ፍጡር የዲኤንኤ (DNA) ምስጢር ለመፍታት ሌሊትና ቀን እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን፣ ግኝቱ ለሰው ልጅ የእርጅና መከላከያ እና የካንሰር ሕክምና ምርምር ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ በመሆኑ በማኅበራዊ ሚዲያና በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

❤18👍9🤣5
በዘንድሮው ክረምት በጎፋ ከተማ የጎርፍ አደጋ ስጋት አይሆንም ተባለ
👉 ስጋት ባለባቸው አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር ስራ ተሰርቷል
በ2016 ዓ.ም በጎፋ ተከስቶ በነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። በመሆኑም በክረምት ወቅት ባለፉት ዓመታት በጎርፍ ምክንያት ሲከሰት የነበረውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ለመከላከል በተያዘው ዓመት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ የአደጋ ስጋት አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ያዕቆብ ዘካሪያስ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሜትሮሎጂ ባለሙያዎች የአካባቢውን የአየር ሁኔታ በመከታተል ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ስፍራ እንዲሰፍሩ የማድረግ ስራ መሰራቱን ነግረውናል። አክለውም የአደጋ ስጋት ሰራተኞች ከሜትሮሎጂ ባለሙያዎች ጋር በአጋርነት በመሆን አስፈላጊው ጥንቃቄ ስለተደረገ አስጊ በሆኑ ቦታዎች ላይ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ የተባሉ ቦታዎች ላይ ያሉ ነዋሪዎችን በማስነሳት አስተማማኝ ወደ ሆኑ ቦታዎች የማስፈር ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አቶ ያዕቆብ ዘካሪያስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤13👍7🙏3
የአሜሪካው ሴናተር ሊንድሴ ግራሃም በ71 ዓመታቸው ‹‹በድንገተኛ ህመም›› ማለፋቸውን ቢሯቸዉ አስታወቀ
ከደቡብ ካሮላይና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ግራሃም ከ2003 ጀምሮ በሴኔት ውስጥ አገልግለዋል
ቢሯቸዉ ባወጣው መግለጫ፤ ‹‹ቅዳሜ ምሽት የአሜሪካው ሴናተር ሊንድሴ ግራሃም በአጭር እና በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል›› ብሏል።
ከደቡብ ካሮላይና ግዛት የመጡት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባሉ ግራሃም፤ በ2002 ለሴኔት የተመረጡ ሲሆን በ2008፣ 2014 እና 2020 በድጋሚ ተመርጠዋል።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ወዳጅ የነበሩት ግራሃም፤ የሴኔት የበጀት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በህዳር ወር ምርጫ ለአምስተኛ ጊዜ ለስድስት ዓመት የሴኔት የሥራ ዘመን ለመወዳደር በዝግጅት ላይ ነበሩ።
ግራሃም በቅርቡ ወደ ኪቭ ተጉዘው የተመለሱ ሲሆን፤ ባለፈው አርብ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተው ነበር።

❤11👍7