አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኦፔክ ፕላስ አባል ሀገራት የነዳጅ ምርት መጠንን ለመጨመር ተስማሙ

​የነዳጅ ላኪ ሀገራት ድርጅት እና አጋሮቹ (የኦፔክ ፕላስ)፣ ከነሐሴ ወር ጀምሮ የነዳጅ ምርት መጠናቸውን በየቀኑ በ188,000 በርሜል ለመጨመር መወሰናቸውን አስታወቁ።

​ይህ ውሳኔ የተላለፈው በቡድኑ አባል ሀገራት (ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ፣ ኢራቅ፣ ኩዌት፣ ካዛኪስታን፣ አልጄሪያ እና ኦማን) መካከል በዛሬው ዕለት በተካሄደው ስብሰባ ነው።

ውሳኔው የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ እየቀነሰ ባለበት እና በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ያለው የነዳጅ ማጓጓዣ እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት እየተመለሰ ባለበት ወቅት የመጣ ነው።

​ቡድኑ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የምርት መጠኑን በደረጃ ለመጨመር እቅድ ነድፎ ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን፣ በሰኔ እና ሐምሌ ወራትም ተመሳሳይ ጭማሪዎችን አድርጓል። ሆኖም በአሜሪካ እና በእስራኤል እንዲሁም በኢራን መካከል የተፈጠረው ግጭት የሆርሙዝ ባህር ሰላጤ ለበርካታ ቀናት በመዘጋቱ፣ የታቀደው የምርት ጭማሪ በተግባር ውጤታማ ሳይሆን ቆይቷል።

​በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እና ኢራን ግጭቱን ለማቆም የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ለነዳጅ ገበያው መረጋጋት ተስፋ ሰጥቷል። የነዳጅ ማጓጓዣ መርከቦች ወደ አካባቢው መመለስ መጀመራቸው የምርት አቅርቦቱን ወደ ቀድሞ ሁኔታው የመመለስ ተስፋን አጠናክሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍7
ባስ እንዳይወጣ ተከለከለ‼️
የህወሓት ታጣቂዎች ኬላ ዘርግተው ባዶ ባስን ጨምሮ ማንኛውም አውቶብስ ከራያ አላማጣ እንዳያልፍ ከልክለዋል።
ዛሬ ሀምሌ 3/2018 ዓ.ም ጠዋት ባዶ አውቶቡሶችን ጨምሮ መውጣት አይቻልም ብለው እየመለሱ መሆኑን ተሳፋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8😢2👀2🤪1
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል የማታለል (በተለምዶ ሿሿ) ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 1:40 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሪቼ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

የግል ተበዳይ ከአጎና ወደ እስታዲየም ለመሄድ በማሰብ ኮድ 3-83620 ኦሮ ነጭ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በማስቆም ትገባለች። ተጠርጣሪዎችም የግለሰቧን ወደ ተሽከርካሪው መግባት ተከትለው በማዋከብ እና ትኩረቷን በማሳጣት ይዛው ከነበረው ቦርሳ ውስጥ 32 ሺ ብር ግምት ያለው ሳምሰንግ ስልክ ሰርቀው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ይህን የተመለከቱ የትራፊክ ፖሊሶች ተሽከርካሪውን በማስቆም እና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ሰርተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 7 ስልኮች መገኘታቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ነፍሰ ጡር መኖሯ የተገለጸ ሲሆን የቀን ውሎ አበል በመክፈል እና ተሽከርካሪ በመከራየት ወንጀሉን የሚፈፅሙ ግለሰቦች እንዳሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ትራንስፖርት ሲጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍95
እንደገና ፈተና አለ‼️
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ የተመረቃችሁ ወይም የመውጫ ፈተና ሳትፈተኑ የዲግሪ ባለቤት የሆናችሁ በሙሉ እንደገና የትምህርት ማስረጃችሁን ለማረጋገጥ ሲባል ሊፈተኑ ነው ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት በኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የፌስቡክ ገጽ ላይ በተለቀቀው ሊንክ እየገባችሁ መሙላት ትችላላችሁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣5415👍4😢3🤷‍♂2😱2👀21🤪1🙉1🙊1
ባለፉት አስራ አንድ ወራት አማራ ክልልን ከጎበኙ ቱሪስቶች  ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

የክልሉን ገጽታ ለመገንባት በክልሉ የሚከበሩ ባህላዊ፣ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ ክብረ በዓላትን በማስተባበር፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማትና  የማስተዋወቅ ስራ መከናወኑን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ባለፉት አስራ አንድ ወራት በርካታ ቱሪስቶች ክልሉን ጎብኝተዋል፡፡ከ17 ሚሊዮን የሚበልጡ  የአገር ውስጥ እና ከ53 ሺህ በላይ የሚሆኑ የውጭ አገር ቱሪስቶች ክልሉን እንደጎበኙ  ተናግረዋል፡፡

ከአገር ውስጥ እና ከውጪ ሃገር ቱሪስቶች  በድምሩ 15 ቢሊዮን  418 ሚሊዮን 520 ሺህ 694 ብር ገቢ ተገኝቷል ሲሉ አክለዋል፡፡

ዘርፋን ለማበረታታት ቁጥራቸው ከ25 ሺህ  በላይ ለሚሆኑ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የድጋፍና የክትትል ስራ ተከናውኗል ያሉት አቶ አበበ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ ሙያተኞች የአጭር ጊዜ የስራ ላይ ስልጠና ተሰጥቶአቸዋል በማለት አስረድተዋል።

እንዲሁም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያሻሽሉ የማድረግ ስራ ተከናውኗል ሲሉ አቶ አበበ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በክረምት ወቅት በክልሉ የሚከበሩ ክብረ በዓላት በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ የማድረግ ስራ  መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤔9👍4🙉3😢2🤷‍♂1👌1🌚1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ስለመጠቀም (በመመሪያ ቁጥር 1142/2018 መሠረት)‼️

1/ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የሆነ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት መጠቀም በታክስ ሕጉ መሰረት የሂሳብ መዝገብ በሚይዙ ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ነው።

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የተደነገግው ቢኖርም ማንኛውም ታክስ ከፋይ በፈቃደኝነት ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የሆነ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት መጠቀም ይችላል።

3/ በአባሪ ሁለት በተዘረዘሩት ዘርፎች የተሰማሩ ታክስ ከፋዮች የሚጠቀሙት የሽያጭ መመዝገቢያ ስርዓት ግዴታ ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ የሚሰራ መሆን ይኖርበታል።

4/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ የተደነገግው ቢኖርም የታክስ ባለስልጣኑ ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ የሚሰራ የሽያጭ መመዝገቢያ ስርዓት የመጠቀም ግዴታ የሚሆንባቸውን ዘርፎች ማሻሻል ይችላል።

5/ ግብር ከፋይ ፈቃድ የተሰጠውን የኤሌክትሮኒክ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት/ሶፍትዌር ወይም የኤሌክትሮኒክ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አገልግሎት ወይም ታክስ ከፋዩ ለራሱ ብቻ የሚጠቀምበት የኤሌክትሮኒክስ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ለመጠቀም፦
ሀ) በባለስልጣኑ የታክስ ከፋይ የድረ-ገጽ አገልግሎት ማዕከል ለኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ተጠቃሚነት በመመዝገብ የስርዓት መለያ ቁጥር ፣ የግንኙነት ቁልፍ እና የተጠቃሚ የሚስጥር ቁልፍ መውሰድ ይኖርበታል፣
ለ) በታክስ ከፋዩ ስም/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና በተመዘገበው ሶፍትዌር/ስርዓት መለያ ቁጥር በመጠቀም የዲጂታል ፊርማ ሰርተፍኬት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወይም ፈቃድ ካለው አካል መውሰድ ይኖርበታል፣
ሐ) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 “ሀ” እና “ለ” የተገኘውን መረጃ በመጠቀም የኤሌክትሮኒክ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት/ሶፍትዌር ለስራ ዝግጁ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።

6/ ታክስ ከፋይ በተሰጠው የደረሰኝ ሶፍትዌር ፈቃድ በኢኮሜርስ ወይም ዲጂታል ገበያ ቦታ ለመጠቀም፦
ሀ) በባለስልጣኑ የታክስ ከፋይ የድረ-ገጽ አገልግሎት ማዕከል ለኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ተጠቃሚነት መመዝገብና የሚጠቀመውን ኢኮሜርስ ወይም ዲጂታል ገበያ ቦታ በማመላከት የተጠቃሚ የሚስጥር ቁልፍ ቃል መውሰድ ይኖርበታል፣
ለ) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ ሀ የተገኘውን መረጃ በመጠቀም ኢኮሜርስ ወይም ዲጂታል ገበያ ቦታ ሥርዓት/ሶፍትዌር ለስራ ዝግጁ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍4
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ለቀድሞ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ግድያ በቀል እንደሚፈጸም ቃል ገባ
 
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ አዛዥ የጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ግድያ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ ቃል ገብተዋል፣ “ከታሪካዊው ትውስታ አይጠፋም” ሲሉ ግድያዉን አዉግዘዋል።ብርጋዴር ጄኔራል አህመድ ቫሂዲ “ፍትህ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋገጥ እና ለወንጀለኞቹ፣ በተለይም ለህፃናት ገዳይ የአሜሪካ ጦር፣ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥ” ጥሪ አቅርበዋል።
 
“የአሜሪካ ወንጀለኛ መሪዎች እና የኢራን አብዮት ጠላቶች በሙሉ እና የተቃውሞ ግንባር በዚህ መለኮታዊ መሪ ላይ በፈሪነት በመገደል፣ የመቋቋም ኃይላችንን ወደ መሬት እንደማያወርዱትማወቅ አለባቸው” ሲሉ ቫሂዲ በሴፓህ የዜና ወኪል ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።“ሰማዕታትን መበቀል እና የጥፋተኞቹን ቅጣት፣ ህጋዊ እና የማይረሳ ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል።” ሲሉ አክለዋል፡፡
 
የቫሂዲ አስተያየት የተሰደማዉ ካሜኒ ሐሙስ ዕለት በትውልድ ከተማቸው ማሽሃድ ከተቀበሩ በኋላ ነው፣ የካሜኒ አራት የቤተሰብ አባላት በአሜሪካ እና በእስራኤል የአየር ጥቃት ከሞቱ ከአራት ወራት በኋላ የቀብር ስነስርዓታቸዉ ተፈጽሟል።የኢራን ሚዲያዎች 43 ሚሊዮን ሰዎች የመሪውን የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደተከታተሉ ዘግበዋል።
 
የኢራን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከ41 እስከ 43 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በስድስት ቀናት ውስጥ የቀድሞ የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።የኢራን ፕሬስ ቲቪ የካሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓትን “በዓለም ላይ እስካሁን ካየናቸው ትላልቅ ሰልፎች” ሲል ጠርቶታል። ሥነ ሥርዓቱ የተካሄደው በአምስት ከተሞች ማለትም ቴህራን፣ ኩም፣ ናጃፍ፣ ካርባላ እና ማሽሃድ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍138🫡5
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
👍4🤪2
ለአልጋ 5% ታክስ ተጣለ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በሆቴሎች እና ተመሳሳይ ተቋማት የመኝታ አገልግሎት ላይ የ5 በመቶ ማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ ተጣለ።

⚫️ በአዲሱ ደንብ ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም የመኝታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም የመኝታ ክፍሎቹን ብዛትና የእያንዳንዱን ክፍል የቀን የዋጋ ዝርዝር በገቢዎች ቢሮ በአካል ቀርቦ በልዩ ቅጽ መሙላትና ማሳወቅ ይኖርበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሆቴሎች፣ በሪዞርቶች፣ በሞቴሎች እና በሌሎች መሰል የመኝታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ አዲስ የማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ የሚጥል ደንብ አወጣ።

"የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የመኝታ አገልግሎት ማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ ደንብ ቁጥር 204/2018" በሚል የወጣው ይህ ደንብ፣ የከተማዋን የገቢ አቅም ለማሳደግና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በደንቡ አንቀጽ 6 መሠረት፣ ማንኛውም የመኝታ አገልግሎት ተጠቃሚ ለክፍል አገልግሎት ከሚከፍለው ዋጋ ላይ 5 በመቶ (5%) የማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ እንዲከፍል ይደረጋል።

ይህ የታክስ ተመን የሚሰላው የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሳይታከልበት ባለው መደበኛ የክፍል ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆኑ ተደንግጓል።

ይህ አዲስ የታክስ ሕግ በከተማዋ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም የመኝታ አገልግሎት ሰጪዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ እነዚህም፦

• ከ1 እስከ 7 ኮከብ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች እና ኮከብ የሌላቸው ሆቴሎች፣
• ሪዞርቶች፣ ሎጆች እና ሞቴሎች፣
• የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች (Guest Houses) እና ፔንሲዮኖችን ያጠቃልላል።

አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ በየወሩ ወይም በየሦስት ወሩ (እንደ ግብር ከፋይ ደረጃቸው) የሰበሰቡትን ታክስ ለከተማው ገቢዎች ቢሮ ሪፖርት የማድረግና ገቢ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች  በየወሩ ሪፖርት አድርገው ገቢ የሚያደርጉ ሲሆን ደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ደግሞ በየሦስት ወሩ ሪፖርት አድርገው ገቢ ያደርጋሉ።

ደንቡን በማይተገብሩ፣ ሪፖርት በሚያዘገዩ ወይም የገቢ መረጃ በሚደብቁ ተቋማት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ቅጣት እንደሚጣል ተመልክቷል።

ለማሳያም ሪፖርት ያዘገየ ተቋም ካለበት ዕዳ ላይ እስከ 50 በመቶ የሚደርስ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችልና የታክስ መረጃ መደበቅ ደግሞ በወንጀል እንደሚያስጠይቅ ተደንግጓል።

እንደ ደንቡ ድንጋጌ፣ ማንኛውም የመኝታ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በገቢዎች ቢሮ በአካል ቀርቦ የመመዝገብ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ በሚመዘገብበት ወቅትም የተቋሙን የክፍሎች ብዛትና የእያንዳንዱን ክፍል የቀን የዋጋ ዝርዝር በልዩ ቅጽ መሙላትና ማሳወቅ ይኖርበታል።

ይህ የታክስ አከፋፈል ሂደት ከተቋማቱ የንግድ ፈቃድ እድሳት ጋርም በቀጥታ የተያያዘ ነው።

የከተማዋ የቱሪዝም ኮሚሽን የሆቴሎችን የሙያ ብቃት ፈቃድ የሚያድሰው ተቋማቱ ታክሱን በአግባቡ መክፈላቸውን የሚገልጽ ማረጋገጫ ደብዳቤ ከገቢዎች ቢሮ ሲያቀርቡ ብቻ መሆኑ በደንቡ ላይ በግልጽ ተቀምጧል።

የታክስ አሰባሰቡን ግልጽነት ለማረጋገጥም፣ ተቋማቱ በሚሰጡት የሽያጭ ደረሰኝ ላይ "የማዘጋጃ ቤታዊ መኝታ አገልግሎት ታክስ" የሚለው ሐረግ በግልጽ እንዲሰፍር ታዟል።

የሒሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለባቸው ግብር የሚከፍሉ ተቋማት ደግሞ ከሚሰጡት አገልግሎት 70 በመቶው ላይ የ5 በመቶ ታክስ ታስቦ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

በተጨማሪም ተቋማቱ የሰበሰቡትን የታክስ ገቢ በየወሩ ጠቅልለው ሪፖርት ከማድረጋቸው ባለፈ፣ ሰብስበው ባጠናቀቁ በ30 ቀናት ውስጥ ለዚሁ ተብሎ ወደተከፈተ የባንክ ሒሳብ ገቢ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም በታክስ አሰባሰብና በአሠራር ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በየደረጃው ለሚገኝ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የማቅረብ መብት አላቸው።

ኮሚቴው ቅሬታውን ተቀብሎ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት ያለበት ሲሆን፣ በውሳኔው ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ለከተማ አስተዳደሩ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አቤቱታውን ማቅረብ ይችላል።

ማንኛውም የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ከመኝታ አገልግሎት የተገኘን ገቢ ወቅቱን ጠብቆ ሪፖርት አለማሳወቅ ለዘገየበት በየወሩ 5 ከመቶ ከክፍያው ከ50 ከመቶ ያልበለጠ ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል።

በተጨማሪም የታክስ ገቢውን በወቅቱ ገቢ ያላደረገ ተቋም በወቅታዊ የባንክ ብድር ወለድ ተመን መሠረት ወለድና በወለዱ ላይ ተጨማሪ 15 በመቶ ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል።

አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻነቷ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፣ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለከተማዋ የልማት ስራዎች ለማዋል ታስቦ የወጣ መሆኑን የመግቢያው ክፍል ያስረዳል።

ይህም የከተማዋን የገቢ መሠረት በማስፋት የንግድ እንቅስቃሴው ለከተማዋ እድገት የሚኖረውን ድርሻ ከፍ ያደርጋል ተብሏል።

ይህ ደንብ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተፈርሞ የወጣ ሲሆን፣ ከሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🤪7👍2🤔2🎉1
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ሰራቆ ቀበሌ በግ ሰር'ቆ ሲያ'ርድ በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለው ሌባ መቀጣጫ ሆነ።
ሰ'ርቆ በመግፈፍ ላይ የነበረውን በግ ተሸክ'ሞ ከተማውን እንዲዞር ተደርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣37👍126🤔6😎2🥰1🤯1👌1💯1
ከጀሞ 1 ወደ ጀሞ 3 የሚወስደው መንገድ ከነገ ጀምሮ ለትራፊክ ዝግ ይሆናል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በላፍቶ ሆስፒታል አካባቢ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል አስቸኳይ የቦክስ ከልቨርት ግንባታ መጀመሩን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ እንደገለጸው የግንባታ ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ከነገ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በመሆኑም ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በላፍቶ ሆስፒታል ጀርባ በኩል እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል።

እንዲሁም ከጀሞ ሦስት አደባባይ ወደ ጀሞ አንድ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በሀጫሉ ሁንዴሳ ጎዳና በኩል በቫርኔሮ አደባባይ አድርገው እንዲጓዙ መመሪያ ተሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የግንባታ ሥራው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አሽከርካሪዎች በተለዋጭ መንገዶች በመጠቀም የተለመደውን ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4😱1👌1
ወደ ሚዛን አማን የቅደመ ምረቃ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚዛን አማን ከተማ የሚያደርገውን የቅደመ ምረቃ በረራ በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

አየር መንገዱ ወደ ሚዛን አማን ከተማ በሳምንት ሦስት ቀናት በረራ የሚያደርግ ሲሆን÷ ይህም ለማሕበረሰቡ ፈጣን፣ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ ያስችላል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኤርፖርቶች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጌታነህ አደራ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ ፍቅሬ አማን እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ሀገር ውስጥ የበረራ አድማሱን እያሰፋ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍4😢1
መረጃ‼️

አብዛኛው አክሲዮኑ ለግል ባለሃብቶች የተሸጠው የፓኪስታን አየር መንገድ፣ የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ወልደ ማርያምን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አድርጎ ለመቅጠር ማሠቡን ብሉምበርግ ዘገበ።

አየር መንገዱ በመጪው እሁድ የተወልደን ሹመት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች እንደነገሩት የዜና ምንጩ ጠቅሷል።

የፓኪስታን አየር መንገድ "በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት" እና "በእዳ" ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራ ከተዳረገ በኋላ ለዓመታት በመንግሥት ሲደጎም የቆየ አየር መንገድ ነው።

ኾኖም ካለፈው ሚያዝያ ወዲህ ባለሃብቶች የአየር መንገዱን 75 በመቶ አክሲዮን የገዙት ሲኾን፣ ቀሪውን 25 በመቶ ከመንግሥት ለመግዛት እያሰቡ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍4🥰1👌1
ኢትዮጵያ ለኬንያ 1 ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በ24 ብር ከ07 ሳንቲም ለማቅረብ የሚያስችላትን ስምምነት ተፈራረመች።

በስምምነቱ መሠረት፣ የኬንያው የኤሌክትሪክ ኃይል ኩባንያ በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል 24 ብር 07 ሳንቲም እንዲሁም ለዲማንድ ቻርጅ 1 ሺሕ 10 ብር ከ89 ሳንቲም እንደሚከፍል ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።

አዲሱ የኃይል ሽያጭ ስምምነት፣ በሁለቱ አገራት መካከል የኤሌክትሪክ ንግድን ለማጠናከር፣ በድንበር አካባቢዎች አስተማማኝ የሆነ የኃይል አቅርቦት ለማስፋፋትና የምሥራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከአራት ዓመት በፊት በደረሱበት 25 ዓመታት የሚዘልቅ የኃይል ሽያጭ ስምምነት መሠረት፣ ኬንያ አንድ ኬሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በ6 ነጥብ 50 የአሜሪካ ሳንቲም ስትገዛ ቆይታለች።

ኢትዮጵያ የኃይል መቨጫ ዋጋውን እንደገና ለመከለስ፣ ሦስት ዓመት መጠበቅ እንዳለባት በስምምነቱ ላይ ተገልጦ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣1110👍6
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን ከግብፅ ተረከበች

በአዲስ አበባ በተካሄደው 22ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር የሚኒስትሮች ምክር መጠናቀቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ የተቋሙን የሊቀመንበርነት መንበር ከግብፅ በይፋ ተረክባለች።

ይህ የሥልጣን ሽግግር ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ገበያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የአባል ሀገራቱን የኃይል አውታሮች ማስተሳሰር፣ የኃይል ንግድን ማስፋፋት እና የታዳሽ ኃይል ልማትን ማበረታታት በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በተለይም በዓለም ባንክ የሚደገፈው የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የሪትሬድ-ኢኤ ፕሮጀክት ቀጣናዊ የኃይል ግብይትን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተጠቁሟል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ እንደተናገሩት፣ በጉባኤው ላይ የኤሌክትሪክ የኃይል ገበያ ማዕከል ዋና መቀመጫን ከመወሰን ጋር ተያይዞ ከግብፅ ጋር የነበሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ሰፊ ድርድር መደረጉን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ልዩነቶች የአባል ሀገራቱን አንድነት እንዳይከፋፍሉ የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከርና በጋራ መግባባት ላይ መድረስ ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ በአዲሱ የሊቀመንበርነት ዘመኗ ካላት የኃይል ትርፍ በመነሳት፣ እንደ ኬንያ፣ ሱዳንና ጅቡቲ ካሉ የጎረቤት ሀገራት ጋር የጀመረችውን የኮሪደር ትስስር ይበልጥ በማጠናከር የቀጣናውን የኃይል ደህንነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታውቃለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍8