አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
3👍3
#ጀርመን በድንች ተጥለቀለቀች-ለፈለገው ሁሉ በነፃ እየታደለ ነው

በአውሮፓ ምድር ታይቶ የማይታወቅ አስገራሚ ክስተት ተከስቷል። ጀርመን ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ አይታው የማታውቀውን እጅግ ከፍተኛ የድንች ምርት በመሰብሰቧ፣ አገሪቱ በድንች ክምር ተጥለቀለቀች! ይህም ክስተት በአካባቢው "ካርቶፍል-ፍሉት" (የድንች ጎርፍ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ በአንድ የጀርመን የለንደን (ላይፕዚግ) አካባቢ የሚገኝ ገበሬ ያመረተውን 4 ሚሊዮን ኪሎ (4,000 ቶን) ድንች የሚገዛው ትልቅ ነጋዴ ውል በማፍረሱ፣ ምርቱ እንዳይበላሽና እንዳይበሰብስ ለአካባቢው ህዝብ በነፃ ለማደል ተገዷል።

ይህን ተከትሎም የበርሊን ጋዜጦችና "ኤኮሲያ" የተባለው የኢንተርኔት መፈለጊያ ተቋም ከተባባሪ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በዋና ከተማዋ በርሊን 174 የነፃ ድንች ማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቋቁመዋል።

አሁን ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የአረጋውያን መርጃ ማዕከላትና አልፎ ተርፎም የበርሊን የእንስሳት ማደሪያ (ዙ) በጆንያና በጋሪ እየመጡ የፈለጉትን ያህል ድንች በነፃ እያጋዙ ይገኛሉ።

አልፎ ተርፎም ሁለት ትላልቅ የጭነት መኪናዎች ሙሉ ድንች ለዩክሬን በዕርዳታ ተልኳል።

ይህ በነፃ የሚታደለው ድንች በገበያ ላይ ያለውን የድንች ዋጋ እንዳያረክሰውና ሌሎች ገበሬዎችን ኪሳራ ውስጥ እንዳይከት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

በአንድ በኩል በዓለም ዙሪያ የምግብ እጥረትና ረሃብ ባለበት በዚህ ዘመን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተረፈረፈ ምርት የሚጣልበት ቦታ አጥቶ በነፃ መታደሉ፤ የዓለማችን የምግብ ስርጭት ስርዓት ምን ያህል የተዛባ መሆኑን ትልቅ ማሳያ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍6🙏1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍21
በ20 ቀናት ለቃችሁ እንድትወጡ ተባለ‼️

በመርካቶ ከ200 በላይ ነጋዴዎች በ20 ቀናት ውስጥ ሱቆቻቸውን እንዲያስረክቡ መታዘዛቸው ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ መርካቶ ጣና የገበያ ማዕከል ፊት ለፊት የሚገኙ ከ200 በላይ ነጋዴዎች፣ በልማት ምክንያት በ20 ቀናት ውስጥ የንግድ ቤቶቻቸውን ጠቅልለው እንዲያስረክቡ ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።

ነጋዴዎቹ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ቤቶቹን በማያስረክቡ አካላት ላይ ለሚደርሰው የንብረት ጉዳት ኮርፖሬሽኑ ኃላፊነት እንደማይወስድ በደብዳቤው እንደገለፀላቸው ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19😢13👍6
#አሳዛኝ

ለራሱ ምርቃት የተገዛው በሬ ወግቶት ህይወቱ ያለፈው ተመራቂ 

በቅርቡ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ዘርፍ በታላቅ ስኬት ተመርቆ፣ ለነገው ህይወቱ ትልቅ ተስፋ ሰንቆ የነበረው ፍሰሐ አስማማው እጅግ ልብ በሚሰብር አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ይህ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ከሳምንት በፊት ነበር የምርቃት ካባውን የደረበው። 

ወላጆችና ዘመድ አዝማድም የምርቃቱን ደስታ አብረውት ለማሳለፍ ከጎንደር ጋይንት (ጎብጎብ) ከተማ ወደ ተወለደበት አካባቢ ይዘውት አምርተው ነበር።

ነገር ግን በትላንትናው ዕለት ለምርቃቱ ድግስ ተብሎ የተገዛው በሬ በድንገት ወግቶት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

የዚህ ወጣት ስኬትና ህልም በአጭር የተቀጨበት አሳዛኝ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በጋይንት ጎብጎብ ቀራኒዮ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የክፍል ጓደኞቹና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተፈፅሟል።

ለወላጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለጓደኞቹ በሙሉ ፈጣሪ ፍጹም መፅናናትን ይስጥልን። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢6419💔14👍4
ከ738 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) እንዳስታወቁት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 738.144 ቢሊዮን ብር  ተሰብስቧል።

የጉምሩክ ህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ሥራም 27 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 1.9 ቢሊዮን ብር የወጪ በአጠቃላይ 28.9 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 1 ሺህ 835 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ተናግረዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን በ2019 የበጀት ዓመት ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙንም ጨምረው ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🙊9👍3
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
በሶማሌ ክልል የታሸገ የግመል ወተት ለገበያ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ
 
በሶማሌ ክልል የታሸገ የግመል ወተት ለገበያ እየቀረበ እንደሚገኝ ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
 
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሚኒስቴሩ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የግመል ወተት ማሻሻያ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው አስቸጋሪ በመሆኑ ግመል የማዳቀል ሥራ እየተሠራ ባይሆንም፣ የግመል ወተትን ማሻሻል ላይ ግን ምርቱ በሚገኝባቸው አካባቢዎች በስፋት የተጀመሩ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
 
የግመል ወተት ምርትን ለማሻሻል እና በአያያዝና በመመገብ በኩል ያለውን ክፍተት በመሙላት ምርቱ እንዲጨምር እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ከአርብቶ አደሩ ምርቱን በመሰብሰብ በሶማሌ ክልል አካባቢ የታሸገ የግመል ወተት ለተጠቃሚው እንዲቀርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
 
በአገሪቱ የወተት ምርት በሌማት ትሩፋት በሰፊው እየተመረተ እንደሚገኝና በዘንድሮው ዓመት 15.7 ቢሊዮን ሊትር ወተት መመረቱንም ተናግረዋል። ቀደም ሲል ወተት በስፋት የሚመረትባቸው ጥቂት አካባቢዎች ብቻ እንደነበሩና አሁን ላይ ግን በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል እየተመረተ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ከወተት ጋር በተገናኘ በተለይም በምስራቁ ክፍል የግመል ወተት ተጠቃሚ በሰፊው መኖሩን በመጥቀስ፤ የግመል ወተትን ልክ እንደ ሌሎቹ ምርቶች በዘመናዊ መልኩ ለተጠቃሚው እንዲደርስ የማድረግ ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።
 
በመንደር ደረጃ የሚያመርቱት አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች ተደራጅተው በቀጣይ ፋብሪካ እንዲከፍቱ የሚያስችል አሠራር እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ምርቱን ከመጨመር ባለፈ ከተመረተበት ቦታ ወደ ፋብሪካ ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ፣ ከ10 ሺህ ሊትር በላይ የሚይዙ ቦቴዎች በየአካባቢው በማሰራጨት ምርቱን ወደ ፋብሪካ እንዲያመጡ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
 
ግብርና ሚኒስቴር በቀጣይም የወተት ምርትን በሰፊው በማምረት፣ ከፍላጎት አንጻር ያለውን ክፍተት ለመሙላት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታውቋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍4🙊3👀1🤪1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢራን አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች በሚል በኩዬት የአሜሪካ የጦር ካምፕ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ከፍተኛ ቃጠሎ ተነስቶ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ በዛሬው ዕለት አሜሪካ በኢራን ከ90 በላይ ኢላማዎችን መምታቷን አስታውቃለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍5
በሱዳን የኩርሙክ ግንባር የቀጠለው ጦርነት በርካታ ተዋጊዎች ያለቁበት መሆኑ ተሰማ፤ የአርሚ 70 ተዋጊዎችም ከባድ ጉዳት ድርሶባቸዋል‼️

አዲስ አበባ/ካርቱም | ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. በሱዳን የብሉ ናይል ክልል በሚገኘው ስትራቴጂካዊ የኩርሙክ አካባቢ ያለው የጦርነት ሁኔታ የኢትዮጵያን ትኩረት እየሳበ ነው። ኩርሙክ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ቁልፍ ስፍራ በመሆኗ፣ መንግሥት ጦርነቱን በንቃት እየተከታተለ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሱዳን የቀጠለው ግጭት በድንበር ደኅንነት፣ በሕዝብ እንቅስቃሴ፣ በስደተኞች ፍሰት እና በታጣቂ ቡድኖች እንቅስቃሴ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ በኢትዮጵያ በኩል ክትትል የሚሻው ጉዳይ ከመሆኑ ጎን ለጎን፣ በጦርነቱ በተሰለፉ የ”አርሚ 70″ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱም ተሰምቷል።

ከሕወሓት የጦር ክንፍ ጋር ቅርበት ካለው ከፍተኛ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አርሚ ሰባ ኩርሙክን ለመያዝ የጄነራል አልቡርሃን ጦር በሚያደርገው ውጊያ ላይ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፏል።

በዚሁ መረጃ መሠረት የአርሚ 70 አባላት በጦርነቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል። መረጃውን ያጋሩ ምንጮች በውጊያው ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ አባላት መገደላቸውንና መቁሰላቸውን አመልክተዋል። የቆሰሉ የአርሚ 70 አባላት በመኪና ወደ ካርቱም ተወስደዋል። ከቆሰሉት መካከል አንዳንዶቹ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8😱5👍4
እኛ በራሳችን ሀይል ነው የምንተማመነው - ህወሓት
 
ህወሓትኤርትራ እና ሱዳንን ያካተተ ጥምረት ፈጥሯል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያቀረቡበትን ክስ ውድቅ አደረገ፡፡
 
ቡድኑ ከየትኛውም የውጭ አካል ወታደራዊ ድጋፍ እንደማይፈልግ እና «በራሱ ኃይል እንደሚተማመን» ገልጿል።
 
ይህ ምላሽ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ላይ፥ ሱዳን፣ ሕወኃት እና ኤርትራ በጋራ እየሠሩ መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህንን ሁኔታ እ.ኤ.አ. በ1991 የደርግ ሥርዓት እንዲወድቅ ካደረገው ጥምረት ጋር በማመሳሰል ከሰጡት አስተያየት በኋላ ነው።
 
 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ጥምረት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚያመጣው አደጋ የለም ሲሉ ተናግረዋል።
 
ነገር ግን ስማቸውን ያልጠቀሷቸው የውጭ አካላት ከጀርባ ሆነው እየመሩት መሆኑን ጠቁመዋል።
 
ለእነዚህ ክሶች ምላሽ የሰጡት የሕወኃት ቃል አቀባይ ሚካኤል አስገዶም፤ ድርጅታቸው አብረውት ተሰልፈው እንዲዋጉለት የውጭ አካላትን በፍጹም ጋብዞ አያውቅም ብለዋል።
 
ተጨማሪ ለማንበብ አስታየት መስጫ ስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍9🤣8
ዓለማቀፉ የፍልሠት ድርጅት፣ ኢትዮጵያ ለኢቦላ ወረርሽኝ የመጋለጥ እድሏ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል አለ።

ድርጅቱ፣ አገሪቱ ለበሽታው ከመጋለጥ አንጻር በከፍተኛ ደረጃ "ቅድሚያ" ከሚሠጣቸው አገራት መካከል አንዷ መኾኗን ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ላይ ገልጧል።

ድርጅቱ ኢትዮጵያ ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ መኾኗን የገለጠው፣ ዓለማቀፍ ተጓዦች በብዛት የሚያልፉባት፣ ድንበር ተሻጋሪ የንግድና የመጓጓዣ ኮሪደሮች ያሉባትና በሽታው ከተከሠተባቸው አካባቢዎች ጋር ያላት ድንበር ክፍተት ያለበት መኾኑን በመጥቀስ ነው።

በድርጅቱ ሪፖርት መሠረት፣ ቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የድሬዳዋ፣ መቀሌ እና የባሕርዳር አውሮፕላን ማረፊያዎች፤ የሞያሌ፣ መተማ፣ ጋላፊ፣ ደዋሌ፣ ፓጋክ እና ኩርሙክ የድንበር መግቢያና መውጫዎች እንዲሁም የድሬዳዋ የባቡር ጣቢያ ቅድሚያ ትኩረት የሚሠጣቸው ቦታዎች ናቸው።

ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ፣ ምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ለ12 አገሮች በሽታውን ለመከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የ55 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር እቅድ የነደፈ ሲኾን፣ ከድጋፉ ውስጥ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላሩ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓትና በድንበርናና ኮሪደሮች አካባቢ የጤና ተቋማትን ለማጠናከር እንደሚውል ገልጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4😱2👀1🤪1
የኦፔክ ፕላስ አባል ሀገራት የነዳጅ ምርት መጠንን ለመጨመር ተስማሙ

​የነዳጅ ላኪ ሀገራት ድርጅት እና አጋሮቹ (የኦፔክ ፕላስ)፣ ከነሐሴ ወር ጀምሮ የነዳጅ ምርት መጠናቸውን በየቀኑ በ188,000 በርሜል ለመጨመር መወሰናቸውን አስታወቁ።

​ይህ ውሳኔ የተላለፈው በቡድኑ አባል ሀገራት (ሳዑዲ አረቢያ፣ ሩሲያ፣ ኢራቅ፣ ኩዌት፣ ካዛኪስታን፣ አልጄሪያ እና ኦማን) መካከል በዛሬው ዕለት በተካሄደው ስብሰባ ነው።

ውሳኔው የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ እየቀነሰ ባለበት እና በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ያለው የነዳጅ ማጓጓዣ እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት እየተመለሰ ባለበት ወቅት የመጣ ነው።

​ቡድኑ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የምርት መጠኑን በደረጃ ለመጨመር እቅድ ነድፎ ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን፣ በሰኔ እና ሐምሌ ወራትም ተመሳሳይ ጭማሪዎችን አድርጓል። ሆኖም በአሜሪካ እና በእስራኤል እንዲሁም በኢራን መካከል የተፈጠረው ግጭት የሆርሙዝ ባህር ሰላጤ ለበርካታ ቀናት በመዘጋቱ፣ የታቀደው የምርት ጭማሪ በተግባር ውጤታማ ሳይሆን ቆይቷል።

​በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እና ኢራን ግጭቱን ለማቆም የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ለነዳጅ ገበያው መረጋጋት ተስፋ ሰጥቷል። የነዳጅ ማጓጓዣ መርከቦች ወደ አካባቢው መመለስ መጀመራቸው የምርት አቅርቦቱን ወደ ቀድሞ ሁኔታው የመመለስ ተስፋን አጠናክሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍7
ባስ እንዳይወጣ ተከለከለ‼️
የህወሓት ታጣቂዎች ኬላ ዘርግተው ባዶ ባስን ጨምሮ ማንኛውም አውቶብስ ከራያ አላማጣ እንዳያልፍ ከልክለዋል።
ዛሬ ሀምሌ 3/2018 ዓ.ም ጠዋት ባዶ አውቶቡሶችን ጨምሮ መውጣት አይቻልም ብለው እየመለሱ መሆኑን ተሳፋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8😢2👀2🤪1
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል የማታለል (በተለምዶ ሿሿ) ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 1:40 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሪቼ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

የግል ተበዳይ ከአጎና ወደ እስታዲየም ለመሄድ በማሰብ ኮድ 3-83620 ኦሮ ነጭ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በማስቆም ትገባለች። ተጠርጣሪዎችም የግለሰቧን ወደ ተሽከርካሪው መግባት ተከትለው በማዋከብ እና ትኩረቷን በማሳጣት ይዛው ከነበረው ቦርሳ ውስጥ 32 ሺ ብር ግምት ያለው ሳምሰንግ ስልክ ሰርቀው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ይህን የተመለከቱ የትራፊክ ፖሊሶች ተሽከርካሪውን በማስቆም እና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ሰርተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 7 ስልኮች መገኘታቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ነፍሰ ጡር መኖሯ የተገለጸ ሲሆን የቀን ውሎ አበል በመክፈል እና ተሽከርካሪ በመከራየት ወንጀሉን የሚፈፅሙ ግለሰቦች እንዳሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ትራንስፖርት ሲጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍95
እንደገና ፈተና አለ‼️
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ የተመረቃችሁ ወይም የመውጫ ፈተና ሳትፈተኑ የዲግሪ ባለቤት የሆናችሁ በሙሉ እንደገና የትምህርት ማስረጃችሁን ለማረጋገጥ ሲባል ሊፈተኑ ነው ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት በኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የፌስቡክ ገጽ ላይ በተለቀቀው ሊንክ እየገባችሁ መሙላት ትችላላችሁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣5415👍4😢3🤷‍♂2😱2👀21🤪1🙉1🙊1