የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ከሆስፒታል ያመለጠው ታራሚ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጂንካ ማረሚያ ተቋም በስርቆት ወንጀል ተከሶ የነበረውና በጤና ችግር ምክንያት ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ለህክምና የገባው ታራሚ ከሆስፒታል ካመለጠ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አስታወቀ ።
የተቋሙ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታራሚው በስርቆት ወንጀል ተከሶ መደበኛ ቀጠሮውን እየተከታተለ የነበረ ሲሆን በጤና ችግር ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ተልኮ ነበር ።
ታራሚው ሆስፒታል በነበረበት ወቅት በህክምና ላይ የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ሌሊት 2 ሰዓት አካባቢ ማምለጡ ተገልጿል ።
መረጃ የደረሳቸዉ የማረሚያ ተቋሙ አመራሮች ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ክትትል ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተይዞ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ።
ታራሚው በተከሰሰበትን ወንጀል በመፀፀት ህጉ የሚሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ መታረም ሲገባው ለህክምና በተላከበት ወቅት ማምለጡ በጉዳዩ ላይ በህግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ውሳኔ ይሰጣል ሲሉ ኮማንደር አሰቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
@Addis_Reporter

❤9👍6
ኢትዮጵያዊ አማካኝ ጋቶች ፓኖም ለኩዌት ክለብ ፈረመ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም ወደ ኩዌት ሊግ ማምራቱ ለማወቅ ተችሏል።
በሳውዲው ክለብ አል አረቢ ጥሩ ጊዜን በግሉ ያሳለፈው ጋቶች ፓኖም ለኩዌቱ አል ፋሂሊ ክለብ ፊርማውን ማኖር ችሏል።
ጋቶች ፓኖም በክለቡ ለአንድ አመት ለመቆየት ለአል ፋሂሊ ስፖርት ክለብ ፊርማውን አኑሯል።
ጋቶች ፓኖም ከሳምንታት በኃላ ወደ ግብፅ በማቅናት በቅድመ ውድድት ዝግጅት ቡድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።
ጋቶች ፓኖም ከሀገራችን ሊግ አልፎ :-
በሩሲያ
ኢራቅ
ግብፅ እና
ሳውዲ አረቢያ ሊጎች ላይ ባለፉት አመታት ተጫውቶ አሳልፏል።
“ ጭልፊቶቹ “ የሚል መጠርያ ያለው ክለቡ አስር ክለቦች በሚሳተፉበት የሀገሪቱ ሊግ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 6ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

❤22👍6🥰1
በትግራይ ክልል ለአንድ ሳምንት ብቻ አብረዉ የኖረችዉን የትዳር አጋሩን ገድሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
በትግራይ ክልል ፅራእ ወንበርታ ወረዳ ሓይቂ መስሓል ከተማ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የባለቤቱን የወይዘሮ ሸዊት አረጋዊን ህይወት በማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ የነበረው ግለሰብ ለአምስት ቀናት በተደረገ ጥብቅ ክትትል ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በትግራይ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
የክልሉ ፖሊስ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ያስመልጠኛል ወዳለው አካባቢ ሄዶ ተደብቆ የነበረ ቢሆንም የፖሊስ አባላቱ ባደረጉት ረቂቅ ክትትልና ህብረተሰቡ ባሳየው ያልተቆጠበ ትብብርና ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ፖሊስ ከተጠርጣሪው ባገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ቃል እንደተረጋገጠው ጥንዶቹ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጋብቻ ስርዓት የፈጸሙ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለያዩ ቤቶች ቆይተው ወንጀሉ ከመፈጸሙ ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር በአንድ ላይ መኖር የጀመሩት፤ይሁን እንጂ ሰኔ 25 ቀን ከምሽቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ተጠርጣሪው የባለቤቱን ህይወት ሊያጠፋ እንደቻለ ራሱ ለፖሊስ በሰጠው ቃል አምኗል።
በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪው ላይ የተጀመረውን ሙሉ የምርመራ ሂደት በማጠናቀቅ አስፈላጊውን መረጃ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

❤16💔9👍6
መረጃ‼️
የግብጽ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የምሥራቅ አፍሪካ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን "በዘፈቀደ" እያሠረና ከአገሪቱ "እያባረረ" ይገኛል ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ከሠሠ።
የግብጽ ባለሥልጣናት ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከተያዘው ዓመት ጀምሮ እያሠሩ ያሉት፣ የመኖሪያ ፍቃዳቸውን እድሳት በማዘግየት መኾኑን ተቋሙ ገልጧል።
ፖሊስ ሕጋዊ የስደተኞች ሠነዶችን እንደሚነጥቅ መረዳቱን ተቋሙ ጠቅሷል።
ዘለግ ላለ ጊዜ እስር ከሚፈጸምባቸው ስደተኞች መካከል፣ ከኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ ኤርትራዊያን፣ ደቡብ ሱዳናዊያንና ሱዳናዊያን ይገኙበታል ተብሏል።
ተቋሙ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ከመኖሪያ ፍቃድ እድሳት መዘግየት ጋር በተያያዘ በስደተኞች ላይ የሚፈጽሙትን "የዘፈቀደ እስር" እና "ከአገር የማባረር" ድርጊት እንዲያቆሙ ጠይቋል።

❤13👍2🤯2👌1🤪1
የኢትዮጵያ ላኪዎች የዩኬን የቀረጥ ነፃ የገበያ ዕድል እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ
የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ላኪዎች የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ታዳጊ ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የንግድ ሥርዓት በተሻለ ሁኔታ ተጠቅመው ወደ ዩኬ ገበያ የመግባት ዕድላቸውን እንዲያሰፉ ጥሪ ቀረበ። ይህ ጥሪ በአዲስ አበባ በተካሄደው የሥልጠና መድረክ ላይ የተላለፈ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ላኪዎች የዕድሉን፣ የመስፈርቶቹንና የተግባራዊ ሂደቶቹን ግንዛቤ እንዲያሳድጉ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከዩኬ የንግድና ልማት መሥሪያ ቤት፣ ከብሪታንያ ኤምባሲና ከኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፣ የዩኬ ገበያ ለመግባት የሚያስፈልጉ የጥራት ደረጃዎችና የቁጥጥር መስፈርቶች ተብራርተዋል።
አምባሳደር ብሩክ መኮንን እንደገለጹት፣ ቡና፣ የግብርና ምርቶችና ጨርቃጨርቅ በዚህ ሥርዓት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ የወጪ ንግድ ዘርፎች ናቸው።
ሆኖም፣ የቀረጥ ቅናሹ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ላኪዎች ተወዳዳሪና ቀጣይነት ያለው ምርት ለማቅረብ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የሥልጠናው ዓላማ የኢትዮጵያ ንግድ ተቋማት ወደ ዓለም አቀፍ የገበያ ሰንሰለቶች እንዲገቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸማቸውን በማሳደግ ለኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ማገዝ ነዉ ተብሏል።

❤6👍5
እናቱን ላጣው ተማሪ ካሊድ ቃሲም የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት ነው
በቅርቡ እናቱን በሞት ላጣው ተማሪ ካሊድ ቃሲም፣ በሸገር ከተማ ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት መሆኑ ተነገረ። የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል የገባ ሲሆን፣ የኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለቤት ግንባታው የሚሆን መሬት በይፋ አዘጋጅቶ አስረክቧል።

❤43👍21🤔1
ከ 68 ዓመት በኋላ የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብር ወሰን ይሰበር ይሆን?
በዓለም ዋንጫ ታሪክ በአንድ መድረክ 13 ግቦችን በማስቆጠር በርቀት የተቀመጠው ተጨዋች ፈረንሳዊው ጀስት ፎንቴን ነው፡፡
በ1958 ዓለም ዋንጫ 13 ግቦችን ካስቆጠረ በኋላ የትኛውም ተጨዋች እዚህ ቁጥር ላይ መድረስ አይደልም ተጠግቶ አያውቅም፡፡
ሩብ ፍጻሜ ላይ በደረሰው የ2026 ዓለም ዋንጫ ሦስት ተጨዋቾች በጋራ 22 ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
ሊዮኔል ሜሲ በ8 ግቦች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱነ ሲመራ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ኪሊያን ምባፔ በእኩል ሰባት ግቦች ሲከተሉ፣ ሃሪ ኬን በ6 ግቦች 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ምን አልባት ገና የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ሳይደርሱ እዚህ ቁጥር ላይ መድርሳቸው ለ68 ዓመታት ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን የሚሰብሩበት ዕድል ሊኖር እንደሚችል ማሳያ ነው፡፡
በተለይ ከቡድኖቻቸው ጋር እስከ ፍጻሜ የሚጓዙ ከሆነ ይህንን ለማድረግ ብዙም የሚቸገሩ አይመስሉም፡፡
ከዚህ በፊት በአንድ የዓለም ዋንጫ 8 እና ከዚያ በላይ ግቦችን ያስቆጠሩት ስምንት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው፡፡
ጀስት ፎንቴይን፣ ሳንዶር ኮሲስ፣ ገርድ ሙለር፣ አዴሚር፣ ኤውሴቢዮ፣ ጉለርሞ ስታቢሌ፣ ሮናልዶ እና ምባፔ በዚሀ ዓመት ደግሞ ሊዮኔል ሜሲ ብቻ ናቸው፡፡

❤21👍7
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤3👍3
#ጀርመን በድንች ተጥለቀለቀች-ለፈለገው ሁሉ በነፃ እየታደለ ነው❗
በአውሮፓ ምድር ታይቶ የማይታወቅ አስገራሚ ክስተት ተከስቷል። ጀርመን ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ አይታው የማታውቀውን እጅግ ከፍተኛ የድንች ምርት በመሰብሰቧ፣ አገሪቱ በድንች ክምር ተጥለቀለቀች! ይህም ክስተት በአካባቢው "ካርቶፍል-ፍሉት" (የድንች ጎርፍ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ በአንድ የጀርመን የለንደን (ላይፕዚግ) አካባቢ የሚገኝ ገበሬ ያመረተውን 4 ሚሊዮን ኪሎ (4,000 ቶን) ድንች የሚገዛው ትልቅ ነጋዴ ውል በማፍረሱ፣ ምርቱ እንዳይበላሽና እንዳይበሰብስ ለአካባቢው ህዝብ በነፃ ለማደል ተገዷል።
ይህን ተከትሎም የበርሊን ጋዜጦችና "ኤኮሲያ" የተባለው የኢንተርኔት መፈለጊያ ተቋም ከተባባሪ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በዋና ከተማዋ በርሊን 174 የነፃ ድንች ማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቋቁመዋል።
አሁን ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የአረጋውያን መርጃ ማዕከላትና አልፎ ተርፎም የበርሊን የእንስሳት ማደሪያ (ዙ) በጆንያና በጋሪ እየመጡ የፈለጉትን ያህል ድንች በነፃ እያጋዙ ይገኛሉ።
አልፎ ተርፎም ሁለት ትላልቅ የጭነት መኪናዎች ሙሉ ድንች ለዩክሬን በዕርዳታ ተልኳል።
ይህ በነፃ የሚታደለው ድንች በገበያ ላይ ያለውን የድንች ዋጋ እንዳያረክሰውና ሌሎች ገበሬዎችን ኪሳራ ውስጥ እንዳይከት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
በአንድ በኩል በዓለም ዙሪያ የምግብ እጥረትና ረሃብ ባለበት በዚህ ዘመን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተረፈረፈ ምርት የሚጣልበት ቦታ አጥቶ በነፃ መታደሉ፤ የዓለማችን የምግብ ስርጭት ስርዓት ምን ያህል የተዛባ መሆኑን ትልቅ ማሳያ ሆኗል።

❤25👍6🙏1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

👍2❤1
በ20 ቀናት ለቃችሁ እንድትወጡ ተባለ‼️
በመርካቶ ከ200 በላይ ነጋዴዎች በ20 ቀናት ውስጥ ሱቆቻቸውን እንዲያስረክቡ መታዘዛቸው ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ መርካቶ ጣና የገበያ ማዕከል ፊት ለፊት የሚገኙ ከ200 በላይ ነጋዴዎች፣ በልማት ምክንያት በ20 ቀናት ውስጥ የንግድ ቤቶቻቸውን ጠቅልለው እንዲያስረክቡ ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
ነጋዴዎቹ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ቤቶቹን በማያስረክቡ አካላት ላይ ለሚደርሰው የንብረት ጉዳት ኮርፖሬሽኑ ኃላፊነት እንደማይወስድ በደብዳቤው እንደገለፀላቸው ጠቁመዋል።

❤19😢13👍6
#አሳዛኝ
ለራሱ ምርቃት የተገዛው በሬ ወግቶት ህይወቱ ያለፈው ተመራቂ
በቅርቡ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ዘርፍ በታላቅ ስኬት ተመርቆ፣ ለነገው ህይወቱ ትልቅ ተስፋ ሰንቆ የነበረው ፍሰሐ አስማማው እጅግ ልብ በሚሰብር አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ይህ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ከሳምንት በፊት ነበር የምርቃት ካባውን የደረበው።
ወላጆችና ዘመድ አዝማድም የምርቃቱን ደስታ አብረውት ለማሳለፍ ከጎንደር ጋይንት (ጎብጎብ) ከተማ ወደ ተወለደበት አካባቢ ይዘውት አምርተው ነበር።
ነገር ግን በትላንትናው ዕለት ለምርቃቱ ድግስ ተብሎ የተገዛው በሬ በድንገት ወግቶት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
የዚህ ወጣት ስኬትና ህልም በአጭር የተቀጨበት አሳዛኝ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በጋይንት ጎብጎብ ቀራኒዮ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የክፍል ጓደኞቹና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተፈፅሟል።
ለወላጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለጓደኞቹ በሙሉ ፈጣሪ ፍጹም መፅናናትን ይስጥልን።

😢64❤19💔14👍4
ከ738 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) እንዳስታወቁት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 738.144 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል።
የጉምሩክ ህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ሥራም 27 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 1.9 ቢሊዮን ብር የወጪ በአጠቃላይ 28.9 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 1 ሺህ 835 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ተናግረዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን በ2019 የበጀት ዓመት ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙንም ጨምረው ገልጸዋል።

❤10🙊9👍3
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
በሶማሌ ክልል የታሸገ የግመል ወተት ለገበያ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ
በሶማሌ ክልል የታሸገ የግመል ወተት ለገበያ እየቀረበ እንደሚገኝ ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሚኒስቴሩ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የግመል ወተት ማሻሻያ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው አስቸጋሪ በመሆኑ ግመል የማዳቀል ሥራ እየተሠራ ባይሆንም፣ የግመል ወተትን ማሻሻል ላይ ግን ምርቱ በሚገኝባቸው አካባቢዎች በስፋት የተጀመሩ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
የግመል ወተት ምርትን ለማሻሻል እና በአያያዝና በመመገብ በኩል ያለውን ክፍተት በመሙላት ምርቱ እንዲጨምር እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ከአርብቶ አደሩ ምርቱን በመሰብሰብ በሶማሌ ክልል አካባቢ የታሸገ የግመል ወተት ለተጠቃሚው እንዲቀርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በአገሪቱ የወተት ምርት በሌማት ትሩፋት በሰፊው እየተመረተ እንደሚገኝና በዘንድሮው ዓመት 15.7 ቢሊዮን ሊትር ወተት መመረቱንም ተናግረዋል። ቀደም ሲል ወተት በስፋት የሚመረትባቸው ጥቂት አካባቢዎች ብቻ እንደነበሩና አሁን ላይ ግን በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል እየተመረተ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ከወተት ጋር በተገናኘ በተለይም በምስራቁ ክፍል የግመል ወተት ተጠቃሚ በሰፊው መኖሩን በመጥቀስ፤ የግመል ወተትን ልክ እንደ ሌሎቹ ምርቶች በዘመናዊ መልኩ ለተጠቃሚው እንዲደርስ የማድረግ ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በመንደር ደረጃ የሚያመርቱት አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች ተደራጅተው በቀጣይ ፋብሪካ እንዲከፍቱ የሚያስችል አሠራር እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ምርቱን ከመጨመር ባለፈ ከተመረተበት ቦታ ወደ ፋብሪካ ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ፣ ከ10 ሺህ ሊትር በላይ የሚይዙ ቦቴዎች በየአካባቢው በማሰራጨት ምርቱን ወደ ፋብሪካ እንዲያመጡ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
ግብርና ሚኒስቴር በቀጣይም የወተት ምርትን በሰፊው በማምረት፣ ከፍላጎት አንጻር ያለውን ክፍተት ለመሙላት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታውቋል።

❤14👍4🙊3👀1🤪1