አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ተባለ

በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ማደያዎች ላይ በተከናወነው የመቅጃ ልኬት ምርመራ፣ የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ሲል የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አሳወቀ ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ወ/ሮ ሃላፊ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት፣ በሁለት ነዳጅ ማደያዎች የመቅጃ ማሽን የልኬት ችግር በመገኘቱ ከነዳጅ አቅርቦት ለሁለት ወራት እንዲታገዱ ተደርጓል። እርምጃ የተወሰደባቸው የነዳጅ ማደያዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘው ኖክ ነዳጅ ማደያ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አልፋ ነዳጅ ማደያ ናቸው ብለዋል። 

እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ተባረክ ነዳጅ ማደያ ከነዳጅ አቅርቦት ለአንድ ወር እንዲታገድ ተደርጓል የተባለ ሲሆን፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ የሚገኘው የተባበሩት ነዳጅ ማደያ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ የሚገኘው ኦላ ነዳጅ ማደያ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አክለውም፣ ቢሮው በከተማው ውስጥ ልኬትን በማዛባት ፍትሃዊ የንግድ ውድድርን የሚያደናቅፉ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የጀመረውን የክትትልና የሕግ ማስከበር እርምጃ ይበልጥ በማጠናከር እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍3🥱1
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የቀረበውን የሰብዓዊ መብት ውሳኔ ደገፈች‼️
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የሾመውን የልዩ ራፖርተር የሥራ ዘመን አራዘመ።

ኢትዮጵያ የውሳኔ ሃሳቡን ደግፋ ድምፅ ሰጥታለች

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኤርትራ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚከታተሉትን የልዩ ራፖርተር ዶ/ር መሐመድ አብደልሰላምን የሥራ ዘመን ለአንድ ተጨማሪ ዓመት ማራዘሙ ታውቋል።

ምክር ቤቱ የልዩ ራፖርተሩን የሥራ ዘመን ለማራዘም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ያሳለፈው በአብላጫ ድምፅ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት የውሳኔ ሃሳቡን በመደገፍ ድምፅ መስጠቱ ተረጋግጧል።

በምክር ቤቱ አባላት መካከል በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ የቀረበውን ረቂቅ ውሳኔ ኢትዮጵያን ጨምሮ 23 ሀገራት የደገፉት ሲሆን፣ 6 ሀገራት ደግሞ ተቃውመውታል።

ቀሪዎቹ 17 ሀገራት ደግሞ ድምፅ ከመስጠት መታቀባቸው ታውቋል።

ኢትዮጵያ ለውሳኔ ሃሳቡ ድጋፏን የቸረች ሲሆን፣ የኤርትራ መንግስት የዜጎቹን የሰብዓዊ መብት እንዲያከብርና ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ የበኩሏን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

ይህ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቋም በቀጣናዊ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ውሳኔው በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት የወደፊት ግንኙነት እና በአጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካዊ ምህዳር ላይ የራሱ የሆነ ከፍተኛ አንድምታ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8🤣7👍3
ልዩ መረጃ‼️
ዩክሬን ለራሺያ ሲዋጉ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገች‼️

የዩክሬይን የስለላ ተቋም በሩሲያ ጦርነት ‹‹ተሰልፈዋል›› ያላቸውን 34 ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡
በዩክሬይን መንግስት የስለላ ተቋም ስር የሚንቀሳቀሰው ‹‹አይ ወንት ቱ ሊቭ›› የተሰኘው ፕሮጀክት ዛሬ በሩሲያ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ያላቸውን 34 ኢትዮጵያዊያን ስም ይፋ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ ይህንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ‹‹የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጄ ላቭሮቭ ወደኢትዮጵያ የገቡት በአፍሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት አንዱ አካል አድርገው ነው፡፡ ይህ ጉብኝታቸው ደግሞ ሩሲያ በዩክሬይን ላይ በምታደርገው ጦርነት የአፍሪካ ዜጎችን ማሰለፏ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው›› ብሏል፡፡

ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባታቸውን ምክንያት በማድረግም ለሩሲያ ተሰልፈው የሚዋጉ 34 ኢትዮጵያዊያንን ስም ይፋ ለማድረግ መወሰኑን የጠቀሰው ፕሮጀክቱ ከእነዚህ መካከል ቢያንስ 3ቱ መሞታቸውን አስታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ እንደገለፀው እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ለሩሲያ ጦር ሀይል የፈረሙት በተለያየ ጊዜ ነው፡፡ እ.ኤ.አ ዲሴምበር 24 ቀን 2024 አ.ም 8ቱ ኮንትራት መፈረማቸውን ጠቅሶ፣ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2025 ደግሞ 10ሩ እንዲሁም ኦክቶበር 30 ቀን 2025 በተመሳሳይ 9 ሰዎች ኮንትራት መፈፀማቸውን አስረድቷል፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ኮንትራቱን የፈረሙት በቀጥታ ከሩሲያ ጦር ሀይል ጋር ሳይሆን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍3🤔2😢2🥰1
አቶ ደሳለኝ ጫኔ ከቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ

​ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አቶ ደሳለኝ ጫኔ፣ የፓርላማ ቆይታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መውጣታቸውን በይፋ ገለጹ።

በትናንትናው ዕለት የምክር ቤቱ ዘመን ማክተሙን ተከትሎ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አቶ ደሳለኝ፣ ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።

​ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲ መምህርነት እና በሲቪክ ማኅበራት መሪነት ያገለገሉት ምሁር ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፖለቲካ አመራርነት እንዲሁም የባሕር ዳር ከተማ መራጮችን በመወከል በፓርላማ በንቁ ተቃዋሚነት አገልግለዋል።

በዚህ ጉዟቸው ወቅትም ለ45 ቀናት መታሰራቸውን ጠቅሰዋል።

​   ከ10 ዓመታት የፖለቲካ ድካም መልስ ወደ ግሉ ዘርፍ  በመግባት በሙያቸው ሀገርን ለማገልገልና ለቤተሰባቸው ጊዜ ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

ከተቃውሞ ፖለቲካው ቢወጡም፣ በሀገራዊ የሰላም እና የብሔራዊ ውይይት ጉዳዮች ላይ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28👍10😢8🤣1
የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ከሆስፒታል ያመለጠው ታራሚ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጂንካ ማረሚያ ተቋም በስርቆት ወንጀል ተከሶ የነበረውና በጤና ችግር ምክንያት ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ለህክምና የገባው ታራሚ ከሆስፒታል ካመለጠ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አስታወቀ ።

የተቋሙ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታራሚው በስርቆት ወንጀል ተከሶ መደበኛ ቀጠሮውን እየተከታተለ የነበረ ሲሆን በጤና ችግር ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ተልኮ ነበር ።

ታራሚው ሆስፒታል በነበረበት ወቅት በህክምና ላይ የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ሌሊት 2 ሰዓት አካባቢ ማምለጡ ተገልጿል ።

መረጃ የደረሳቸዉ የማረሚያ ተቋሙ አመራሮች ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ክትትል ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተይዞ  ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ።

ታራሚው በተከሰሰበትን ወንጀል በመፀፀት ህጉ የሚሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ መታረም ሲገባው ለህክምና በተላከበት ወቅት ማምለጡ በጉዳዩ ላይ በህግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ውሳኔ ይሰጣል ሲሉ ኮማንደር አሰቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍6
ኢትዮጵያዊ አማካኝ ጋቶች ፓኖም ለኩዌት ክለብ ፈረመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም ወደ ኩዌት ሊግ ማምራቱ ለማወቅ ተችሏል።

በሳውዲው ክለብ አል አረቢ ጥሩ ጊዜን በግሉ ያሳለፈው ጋቶች ፓኖም ለኩዌቱ አል ፋሂሊ ክለብ ፊርማውን ማኖር ችሏል።

ጋቶች ፓኖም በክለቡ ለአንድ አመት ለመቆየት ለአል ፋሂሊ ስፖርት ክለብ ፊርማውን አኑሯል።

ጋቶች ፓኖም ከሳምንታት በኃላ ወደ ግብፅ በማቅናት በቅድመ ውድድት ዝግጅት ቡድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።

ጋቶች ፓኖም ከሀገራችን ሊግ አልፎ :-

በሩሲያ
ኢራቅ
ግብፅ እና
ሳውዲ አረቢያ ሊጎች ላይ ባለፉት አመታት ተጫውቶ አሳልፏል።

“ ጭልፊቶቹ “ የሚል መጠርያ ያለው ክለቡ አስር ክለቦች በሚሳተፉበት የሀገሪቱ ሊግ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 6ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22👍6🥰1
በትግራይ ክልል ለአንድ ሳምንት ብቻ አብረዉ የኖረችዉን የትዳር አጋሩን ገድሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
 
በትግራይ ክልል ፅራእ ወንበርታ ወረዳ ሓይቂ መስሓል ከተማ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም  የባለቤቱን የወይዘሮ ሸዊት አረጋዊን ህይወት በማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ የነበረው ግለሰብ ለአምስት ቀናት በተደረገ ጥብቅ ክትትል ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በትግራይ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
 
የክልሉ ፖሊስ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ያስመልጠኛል ወዳለው አካባቢ ሄዶ ተደብቆ የነበረ ቢሆንም የፖሊስ አባላቱ ባደረጉት ረቂቅ ክትትልና ህብረተሰቡ ባሳየው ያልተቆጠበ ትብብርና ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
 
ፖሊስ ከተጠርጣሪው ባገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ቃል እንደተረጋገጠው  ጥንዶቹ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጋብቻ ስርዓት የፈጸሙ ሲሆን  እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለያዩ ቤቶች ቆይተው ወንጀሉ ከመፈጸሙ ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር በአንድ ላይ መኖር የጀመሩት፤ይሁን እንጂ ሰኔ 25 ቀን  ከምሽቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ተጠርጣሪው የባለቤቱን ህይወት ሊያጠፋ እንደቻለ ራሱ ለፖሊስ በሰጠው ቃል አምኗል።
 
በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪው ላይ የተጀመረውን ሙሉ የምርመራ ሂደት በማጠናቀቅ  አስፈላጊውን መረጃ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16💔9👍6
መረጃ‼️

የግብጽ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የምሥራቅ አፍሪካ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን "በዘፈቀደ" እያሠረና ከአገሪቱ "እያባረረ" ይገኛል ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ከሠሠ።

የግብጽ ባለሥልጣናት ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከተያዘው ዓመት ጀምሮ እያሠሩ ያሉት፣ የመኖሪያ ፍቃዳቸውን እድሳት በማዘግየት መኾኑን ተቋሙ ገልጧል።

ፖሊስ ሕጋዊ የስደተኞች ሠነዶችን እንደሚነጥቅ መረዳቱን ተቋሙ ጠቅሷል።

ዘለግ ላለ ጊዜ እስር ከሚፈጸምባቸው ስደተኞች መካከል፣ ከኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ ኤርትራዊያን፣ ደቡብ ሱዳናዊያንና ሱዳናዊያን ይገኙበታል ተብሏል።

ተቋሙ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ከመኖሪያ ፍቃድ እድሳት መዘግየት ጋር በተያያዘ በስደተኞች ላይ የሚፈጽሙትን "የዘፈቀደ እስር" እና "ከአገር የማባረር" ድርጊት እንዲያቆሙ ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍2🤯2👌1🤪1
የኢትዮጵያ ላኪዎች የዩኬን የቀረጥ ነፃ የገበያ ዕድል እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ላኪዎች የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ታዳጊ ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የንግድ ሥርዓት በተሻለ ሁኔታ ተጠቅመው ወደ ዩኬ ገበያ የመግባት ዕድላቸውን እንዲያሰፉ ጥሪ ቀረበ። ይህ ጥሪ በአዲስ አበባ በተካሄደው የሥልጠና መድረክ ላይ የተላለፈ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ላኪዎች የዕድሉን፣ የመስፈርቶቹንና የተግባራዊ ሂደቶቹን ግንዛቤ እንዲያሳድጉ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከዩኬ የንግድና ልማት መሥሪያ ቤት፣ ከብሪታንያ ኤምባሲና ከኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፣ የዩኬ ገበያ ለመግባት የሚያስፈልጉ የጥራት ደረጃዎችና የቁጥጥር መስፈርቶች ተብራርተዋል።

አምባሳደር ብሩክ መኮንን እንደገለጹት፣ ቡና፣ የግብርና ምርቶችና ጨርቃጨርቅ በዚህ ሥርዓት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ የወጪ ንግድ ዘርፎች ናቸው።

ሆኖም፣ የቀረጥ ቅናሹ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ላኪዎች ተወዳዳሪና ቀጣይነት ያለው ምርት ለማቅረብ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የሥልጠናው ዓላማ የኢትዮጵያ ንግድ ተቋማት ወደ ዓለም አቀፍ የገበያ ሰንሰለቶች እንዲገቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸማቸውን በማሳደግ ለኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ማገዝ ነዉ ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍5
እናቱን ላጣው ተማሪ ካሊድ ቃሲም የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት ነው

​በቅርቡ እናቱን በሞት ላጣው ተማሪ ካሊድ ቃሲም፣ በሸገር ከተማ ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት መሆኑ ተነገረ። የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል የገባ ሲሆን፣ የኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለቤት ግንባታው የሚሆን መሬት በይፋ አዘጋጅቶ አስረክቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
43👍21🤔1
ከ 68 ዓመት በኋላ የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብር ወሰን ይሰበር ይሆን?

በዓለም ዋንጫ ታሪክ በአንድ መድረክ 13 ግቦችን በማስቆጠር በርቀት የተቀመጠው ተጨዋች ፈረንሳዊው ጀስት ፎንቴን ነው፡፡

በ1958 ዓለም ዋንጫ 13 ግቦችን ካስቆጠረ በኋላ የትኛውም ተጨዋች እዚህ ቁጥር ላይ መድረስ አይደልም ተጠግቶ አያውቅም፡፡

ሩብ ፍጻሜ ላይ በደረሰው የ2026 ዓለም ዋንጫ ሦስት ተጨዋቾች በጋራ 22 ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡

ሊዮኔል ሜሲ በ8 ግቦች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱነ ሲመራ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ኪሊያን ምባፔ በእኩል ሰባት ግቦች ሲከተሉ፣ ሃሪ ኬን በ6 ግቦች 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ምን አልባት ገና የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ሳይደርሱ እዚህ ቁጥር ላይ መድርሳቸው ለ68 ዓመታት ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን የሚሰብሩበት ዕድል ሊኖር እንደሚችል ማሳያ ነው፡፡

በተለይ ከቡድኖቻቸው ጋር እስከ ፍጻሜ የሚጓዙ ከሆነ ይህንን ለማድረግ ብዙም የሚቸገሩ አይመስሉም፡፡

ከዚህ በፊት በአንድ የዓለም ዋንጫ 8 እና ከዚያ በላይ ግቦችን ያስቆጠሩት ስምንት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው፡፡

ጀስት ፎንቴይን፣ ሳንዶር ኮሲስ፣ ገርድ ሙለር፣ አዴሚር፣ ኤውሴቢዮ፣ ጉለርሞ ስታቢሌ፣ ሮናልዶ እና ምባፔ በዚሀ ዓመት ደግሞ ሊዮኔል ሜሲ ብቻ ናቸው፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍7
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
3👍3
#ጀርመን በድንች ተጥለቀለቀች-ለፈለገው ሁሉ በነፃ እየታደለ ነው

በአውሮፓ ምድር ታይቶ የማይታወቅ አስገራሚ ክስተት ተከስቷል። ጀርመን ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ አይታው የማታውቀውን እጅግ ከፍተኛ የድንች ምርት በመሰብሰቧ፣ አገሪቱ በድንች ክምር ተጥለቀለቀች! ይህም ክስተት በአካባቢው "ካርቶፍል-ፍሉት" (የድንች ጎርፍ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ በአንድ የጀርመን የለንደን (ላይፕዚግ) አካባቢ የሚገኝ ገበሬ ያመረተውን 4 ሚሊዮን ኪሎ (4,000 ቶን) ድንች የሚገዛው ትልቅ ነጋዴ ውል በማፍረሱ፣ ምርቱ እንዳይበላሽና እንዳይበሰብስ ለአካባቢው ህዝብ በነፃ ለማደል ተገዷል።

ይህን ተከትሎም የበርሊን ጋዜጦችና "ኤኮሲያ" የተባለው የኢንተርኔት መፈለጊያ ተቋም ከተባባሪ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በዋና ከተማዋ በርሊን 174 የነፃ ድንች ማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቋቁመዋል።

አሁን ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የአረጋውያን መርጃ ማዕከላትና አልፎ ተርፎም የበርሊን የእንስሳት ማደሪያ (ዙ) በጆንያና በጋሪ እየመጡ የፈለጉትን ያህል ድንች በነፃ እያጋዙ ይገኛሉ።

አልፎ ተርፎም ሁለት ትላልቅ የጭነት መኪናዎች ሙሉ ድንች ለዩክሬን በዕርዳታ ተልኳል።

ይህ በነፃ የሚታደለው ድንች በገበያ ላይ ያለውን የድንች ዋጋ እንዳያረክሰውና ሌሎች ገበሬዎችን ኪሳራ ውስጥ እንዳይከት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

በአንድ በኩል በዓለም ዙሪያ የምግብ እጥረትና ረሃብ ባለበት በዚህ ዘመን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተረፈረፈ ምርት የሚጣልበት ቦታ አጥቶ በነፃ መታደሉ፤ የዓለማችን የምግብ ስርጭት ስርዓት ምን ያህል የተዛባ መሆኑን ትልቅ ማሳያ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍6🙏1