የገቢዎች ሚኒስቴር ለኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢዎች እስከ 250 ሺህ ዶላር የዋስትና ገደብ ጣለ‼️
የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመሰማራት በሚፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢዎች ላይ እንደየደረጃቸው እስከ 250,000 የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የፋይናንስ ዋስትና የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
በዚህ ወር አጋማሽ ላይ የወጣው መመሪያ በሀገሪቱ የታክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ የገበያ መግቢያ አዲስና ፈታኝ መስፈርት እንደሚሆን ይጠበቃል።
የዋስትናው መጠንም በአቅራቢው የአገልግሎት ዓይነትና በሚያገለግሉት ግብር ከፋዮች ልኬት ላይ ተመስርቶ በ10 ደረጃዎች የተከፋፈለ ነው።
በዚህም መሰረት የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አቅራቢዎች 30,000 ዶላር፣ የሶፍትዌር-አስ-አ-ሰርቪስ አቅራቢዎች 50,000 ዶላር፣ የኢ-ኮሜርስና ዲጂታል ገበያ አንቀሳቃሾች 25,000 ዶላር፣ እንዲሁም የራሳቸውን የውስጥ ደረሰኝ ሥርዓት የሚጠቀሙ ግብር ከፋዮች 15,000 ዶላር የባንክ ወይም የኢንሹራንስ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የዋስትናው መጠንም አቅራቢዎች የሚያገለግሏቸው ደንበኞች ቁጥር ወይም የሽያጭ ልውውጣቸው እያደገ ሲሄድ በየሁለት ዓመቱ የሚታደስ ሲሆን፣ ከ40 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮችን ለሚያገለግሉ ወይም ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ሽያጭ ላላቸው ድርጅቶች ከፍተኛው የዋስትና ጣሪያ 250,000 ዶላር ይደርሳል።
@Addis_Reporter

❤7👍3
በወላይታ ሶዶ ከተማ የ14 ሰዎችን ኤቲኤም ካርድ የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
በወላይታ ሶዶ ከተማ የኤቲኤም (ATM) ካርድ በመቀየር የማጭበርበር ወንጀል ለመፈጸም የሞከረው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ።የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት በወላይታ ሶዶ ከተማ አንድ የባንክ ደንበኛ ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ለማውጣት ሲሞክር ማሽኑ ችግር አጋጥሞት ነበር።
በወቅቱ በአቅራቢያው የነበረው ተጠርጣሪ ዳንኤል ደሳለኝ “ካርዱን ስጠኝ፣ በፀጉሬ ጠርጌ እሰጥሃለሁ” በሚል የማታለያ ዘዴ ካርዱን ተቀብሎ ወስዷል።በሰዓቱም የሚስጥር ቁጥሩን (PIN) ሲያስገባ በመመልከት ካርዱን ጠርጎ የመለሰ በማስመሰል ሌላ የተቀየረ የኤቲኤም ካርድ ሰጥቶ ዋናውን ካርድ ይዞ ለማምለጥ ሞክሯል።የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ፖሊስ ባደረገው ፈጣን ክትትል ተጠርጣሪውን እጅ ከፍንጅ በመያዝ ቁጥጥር ስር አውሏል።
ፖሊስ ምርመራውን በማስፋት በፍርድ ቤት በተሰጠ የብርበራ ትዕዛዝ በተጠርጣሪው የተጎጂውን ካርድ ጨምሮ 14 የተለያዩ ሰዎች የኤቲኤም ካርዶችን ይዞ መገኘቱ ተገልጿል።ፖሊስ ህብረተሰቡ ከኤቲኤም ማሽኖች ገንዘብ በሚያወጣበት ጊዜ የሚስጥር ቁጥሩን ለሌላ አካል እንዳያሳይ በማሽኑ አጠቃቀም ላይ ችግር ካጋጠመውም ከማያውቀው ሰው እርዳታ ከመጠየቅ ይልቅ የባንኩን ባለሙያዎች ወይም የጥበቃ አካላትን ብቻ እንዲያነጋግር አሳስቧል።(Dagu)

❤12🤣11👍7👀1🙉1
በቀጣይ 5 ዓመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶች ይገነባሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በቀጣይ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያ ባለፉት ሰባት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ቤቶች መገንባታቸውን ጠቅሰው በቀጣዩ አምስት ዓመታት ተጨማሪ 1.5 ሚሊዮን ቤቶች እንደሚገነቡ ተናግረዋል።
እንደ ገለጻቸው የቤቶቹ ግንባታ በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ ተሳትፎ እና በሌሎች የአጋርነት መንገዶች የሚከናወን ሲሆን ለዚህም የሚያግዝ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ መፅደቁን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ግብዓት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ምርት መጀመራቸውን፣ዘርፉን የሚደግፉ የሰው ኃይል ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን እና በከተማና በገጠር የቤት ግንባታ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።
የቤት ፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ የሞርጌጅ ስርዓት እየተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመው፣ ዜጎች ቤት በቀጥታ መግዛት ባይችሉም በረጅም ጊዜ ክፍያ ከገቢያቸው ጋር በሚጣጣም መንገድ ባለቤት እንዲሆኑ መንግሥት በተለያዩ አማራጮች ላይ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

🤣26❤21👍6🤪1
መረጃ‼️
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት፣ በኤርትራ የተመድ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተርን የጊዜ ቆይታ በ23 የድጋፍ ድምጽ በድጋሚ ላንድ ዓመት አራዘመ።
የምክር ቤቱ አባል የኾነችው ኢትዮጵያ፣ የልዩ ራፖርተሩን የጊዜ ቆይታ ለማራዘም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ደግፋ ድምጽ ሠጥታለች።
ኬንያንና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 17 አገራት ድምጸ ተዓቅቦ ሲያደርጉ፣ ግብጽ፣ ቻይና፣ ቡሩንዲ፣ ፓኪስታን እና ሕንድ የውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመዋል።
ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡት የአውሮፓ አገራት ነበሩ።
ኤርትራ፣ ከእንግዲህ በልዩ ራፖርተሩ ዙሪያ ከአጋር አገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደማታደርግ በቅርቡ ማሳወቋ አይዘነጋም።

❤11👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ ልውውጥ‼️
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ፤ " ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ ሶስት የንግድ እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽማለች " በማለት እንደ በስትራቴጂካዊ የኢራን ቦታዎች ላይ ከባድ የአየር ድብደባ ፈጽሟል።
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ዳግም በእጅጉ አገርሽቷል።
ኢራን፣ ዋሽንግተን ኦማን አቅራቢያ አዳዲስ የባህር መስመሮችን ለመክፈት ጥረት እያደረገች እንደሆነና ይህም የተደረሰውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) የሚጥስ እንደሆነ ትገልጻለች። ይህ እየተባለ ባለበት ሰዓትና ኢራንም መረከቦች በዛ እንዳያልፉ ባስጠነቀቀችበት ሰዓት ነው ኦማን አቅራቢያ 3 መርከቦች የተመቱ።
አሜሪካም ፣ ለተፈጸመው ጥቃት መላሽ ለመስጠት ወሳኝ ስትራቴጂካዊ የሚባሉ የኢራን ወደብ ቦታዎች ደብድባለች። ከዚህ ወታደራዊ እርምጃ ትንሽ ቀደም ብሎ፣ የአሜሪካው ግምጃ ቤት ለኢራን ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ የነዳጅ ማዕቀብ ማቃለያ በይፋ የሰረዘ ሲሆን ይህም ቴህራን በሕጋዊ መንገድ ነዳጅ ወደ ውጭ የመላክ አቅሟን ያግደዋል።
ኢራን፣ አሜሪካ " የተደረሰውን ስምምነት ጥሳለች " የሚል ክስ እያቀረበችባት ነው።
አሁን ላይ የተፈጠረው ሁኔታ ዓለም አቀፍ ነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል።

❤11👍7😢1
የቤት ኪራይ ጭማሪ ይፋ ሆነ
በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ውል ምዝገባ ተጀመረ፤ የጭማሪው ጣሪያ 11.5% ሆነ
በአዲስ አበባ ከተማ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ምዝገባ ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በይፋ ተጀምሯል።
ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የከተማዋ የቤቶች አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
ይህ አሰራር በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን ለመግታትና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ያለመ ነው።
ውሳኔው የነዋሪዎችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ አከራዮች ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ፣ ተከራዮች ደግሞ ከስነ-ልቦና ስጋትና መፈናቀል ድነው እንዲረጋጉ ይረዳል ተብሏል።
ይሁን እንጂ አዲሱ የዋጋ ተመን ከመጣሉ በፊት በርካታ አከራዮች በተከራዮቻቸው ላይ አስቀድመው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸው በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ እየቀሰቀሰ ይገኛል።

❤14🤔4👍2
የኤርትራ መንግስት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በፓርላማ ቀርበው ለሰጡት ማብራሪያ እና በተለይ ከኤርትራ (ሻዕቢያ)፣ ከሕወሓት እና ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ላነሷቸው ነጥቦች በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ፈጣንና ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥቷል።
ሁለቱ ወገኖች በቀጠናው ሰላምና በጎረቤት ሀገራት ጣልቃ ገብነት ዙሪያ እርስ በርሳቸው ተቃራኒ የሆኑ ክሶችን ሰንዝረዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ንግግራቸው በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወጣቶችን በጉልበት እያፈሱ ለሱዳን ጦርነት "እየሸጡ" መሆኑን ገልጸዋል።
"የትግራይ ወጣቶች በማያውቁት ጉዳይ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ህይወታቸውን እያጡ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ድርጊት የህዝቡን መከራ የሚያባብስ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
በተቃራኒው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ለሱዳን ግጭት መባባስ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ራሱ ነው ሲል ገልጿል።
ኢትዮጵያ ለሱዳኑ ፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (RSF) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሚስጥራዊ የጦር ሰፈርና ማሰልጠኛ በመስጠት በቀጥታ በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑንና ለዚህም "ግልጽ ማስረጃዎች አሉ" ሲል አጸፋዊ ክስ ሰንዝሯል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በንግግራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም አይነት "ትንኮሳ" ለመመከት መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ፣ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ህግጋትንና የቀጠናውን ሀገራት ሉዓላዊነት እየጣሰች ያለችው "የባህር በር ባለቤትነት" በሚል በምታሳየው የግዛት ማስፋፋት ፍላጎት ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ በኩል "ጥቃት አድራሽ" በሌላ በኩል ደግሞ "ተጠቂ" ሆኖ የመቅረብ ድራማ እየሰራ ነው ስትልም ወርፋለች።

👍8❤5🤔1😢1🤣1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

👍4❤2
ኢራናውያን በሽተኞች ናቸው-ትራምፕ‼️
የኢራን ሰዎች በሽተኞች ናቸው፣ ከእነሱ ጋር ስምምነት አላደርግም ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
የኢራን ሰዎች በሽተኞች ናቸው፣ ከእነሱ ጋር ስምምነት አላደርግም ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣11❤3👍2💯2🤡1
የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ተባለ
በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ማደያዎች ላይ በተከናወነው የመቅጃ ልኬት ምርመራ፣ የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ሲል የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አሳወቀ ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ወ/ሮ ሃላፊ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት፣ በሁለት ነዳጅ ማደያዎች የመቅጃ ማሽን የልኬት ችግር በመገኘቱ ከነዳጅ አቅርቦት ለሁለት ወራት እንዲታገዱ ተደርጓል። እርምጃ የተወሰደባቸው የነዳጅ ማደያዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘው ኖክ ነዳጅ ማደያ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አልፋ ነዳጅ ማደያ ናቸው ብለዋል።
እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ተባረክ ነዳጅ ማደያ ከነዳጅ አቅርቦት ለአንድ ወር እንዲታገድ ተደርጓል የተባለ ሲሆን፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ የሚገኘው የተባበሩት ነዳጅ ማደያ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ የሚገኘው ኦላ ነዳጅ ማደያ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አክለውም፣ ቢሮው በከተማው ውስጥ ልኬትን በማዛባት ፍትሃዊ የንግድ ውድድርን የሚያደናቅፉ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የጀመረውን የክትትልና የሕግ ማስከበር እርምጃ ይበልጥ በማጠናከር እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

❤20👍3🥱1
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የቀረበውን የሰብዓዊ መብት ውሳኔ ደገፈች‼️
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የሾመውን የልዩ ራፖርተር የሥራ ዘመን አራዘመ።
ኢትዮጵያ የውሳኔ ሃሳቡን ደግፋ ድምፅ ሰጥታለች
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኤርትራ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚከታተሉትን የልዩ ራፖርተር ዶ/ር መሐመድ አብደልሰላምን የሥራ ዘመን ለአንድ ተጨማሪ ዓመት ማራዘሙ ታውቋል።
ምክር ቤቱ የልዩ ራፖርተሩን የሥራ ዘመን ለማራዘም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ያሳለፈው በአብላጫ ድምፅ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት የውሳኔ ሃሳቡን በመደገፍ ድምፅ መስጠቱ ተረጋግጧል።
በምክር ቤቱ አባላት መካከል በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ የቀረበውን ረቂቅ ውሳኔ ኢትዮጵያን ጨምሮ 23 ሀገራት የደገፉት ሲሆን፣ 6 ሀገራት ደግሞ ተቃውመውታል።
ቀሪዎቹ 17 ሀገራት ደግሞ ድምፅ ከመስጠት መታቀባቸው ታውቋል።
ኢትዮጵያ ለውሳኔ ሃሳቡ ድጋፏን የቸረች ሲሆን፣ የኤርትራ መንግስት የዜጎቹን የሰብዓዊ መብት እንዲያከብርና ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ የበኩሏን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።
ይህ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቋም በቀጣናዊ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ውሳኔው በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት የወደፊት ግንኙነት እና በአጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካዊ ምህዳር ላይ የራሱ የሆነ ከፍተኛ አንድምታ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል።

❤8🤣7👍3
ልዩ መረጃ‼️
ዩክሬን ለራሺያ ሲዋጉ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገች‼️
የዩክሬይን የስለላ ተቋም በሩሲያ ጦርነት ‹‹ተሰልፈዋል›› ያላቸውን 34 ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡
በዩክሬይን መንግስት የስለላ ተቋም ስር የሚንቀሳቀሰው ‹‹አይ ወንት ቱ ሊቭ›› የተሰኘው ፕሮጀክት ዛሬ በሩሲያ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ያላቸውን 34 ኢትዮጵያዊያን ስም ይፋ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ ይህንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ‹‹የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጄ ላቭሮቭ ወደኢትዮጵያ የገቡት በአፍሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት አንዱ አካል አድርገው ነው፡፡ ይህ ጉብኝታቸው ደግሞ ሩሲያ በዩክሬይን ላይ በምታደርገው ጦርነት የአፍሪካ ዜጎችን ማሰለፏ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው›› ብሏል፡፡
ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባታቸውን ምክንያት በማድረግም ለሩሲያ ተሰልፈው የሚዋጉ 34 ኢትዮጵያዊያንን ስም ይፋ ለማድረግ መወሰኑን የጠቀሰው ፕሮጀክቱ ከእነዚህ መካከል ቢያንስ 3ቱ መሞታቸውን አስታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ እንደገለፀው እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ለሩሲያ ጦር ሀይል የፈረሙት በተለያየ ጊዜ ነው፡፡ እ.ኤ.አ ዲሴምበር 24 ቀን 2024 አ.ም 8ቱ ኮንትራት መፈረማቸውን ጠቅሶ፣ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2025 ደግሞ 10ሩ እንዲሁም ኦክቶበር 30 ቀን 2025 በተመሳሳይ 9 ሰዎች ኮንትራት መፈፀማቸውን አስረድቷል፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ኮንትራቱን የፈረሙት በቀጥታ ከሩሲያ ጦር ሀይል ጋር ሳይሆን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

❤13👍3🤔2😢2🥰1
አቶ ደሳለኝ ጫኔ ከቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ
ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አቶ ደሳለኝ ጫኔ፣ የፓርላማ ቆይታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መውጣታቸውን በይፋ ገለጹ።
በትናንትናው ዕለት የምክር ቤቱ ዘመን ማክተሙን ተከትሎ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አቶ ደሳለኝ፣ ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲ መምህርነት እና በሲቪክ ማኅበራት መሪነት ያገለገሉት ምሁር ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፖለቲካ አመራርነት እንዲሁም የባሕር ዳር ከተማ መራጮችን በመወከል በፓርላማ በንቁ ተቃዋሚነት አገልግለዋል።
በዚህ ጉዟቸው ወቅትም ለ45 ቀናት መታሰራቸውን ጠቅሰዋል።
ከ10 ዓመታት የፖለቲካ ድካም መልስ ወደ ግሉ ዘርፍ በመግባት በሙያቸው ሀገርን ለማገልገልና ለቤተሰባቸው ጊዜ ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
ከተቃውሞ ፖለቲካው ቢወጡም፣ በሀገራዊ የሰላም እና የብሔራዊ ውይይት ጉዳዮች ላይ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

❤28👍10😢8🤣1
የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ከሆስፒታል ያመለጠው ታራሚ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጂንካ ማረሚያ ተቋም በስርቆት ወንጀል ተከሶ የነበረውና በጤና ችግር ምክንያት ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ለህክምና የገባው ታራሚ ከሆስፒታል ካመለጠ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አስታወቀ ።
የተቋሙ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታራሚው በስርቆት ወንጀል ተከሶ መደበኛ ቀጠሮውን እየተከታተለ የነበረ ሲሆን በጤና ችግር ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ተልኮ ነበር ።
ታራሚው ሆስፒታል በነበረበት ወቅት በህክምና ላይ የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ሌሊት 2 ሰዓት አካባቢ ማምለጡ ተገልጿል ።
መረጃ የደረሳቸዉ የማረሚያ ተቋሙ አመራሮች ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ክትትል ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተይዞ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ።
ታራሚው በተከሰሰበትን ወንጀል በመፀፀት ህጉ የሚሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ መታረም ሲገባው ለህክምና በተላከበት ወቅት ማምለጡ በጉዳዩ ላይ በህግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ውሳኔ ይሰጣል ሲሉ ኮማንደር አሰቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤9👍6
ኢትዮጵያዊ አማካኝ ጋቶች ፓኖም ለኩዌት ክለብ ፈረመ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም ወደ ኩዌት ሊግ ማምራቱ ለማወቅ ተችሏል።
በሳውዲው ክለብ አል አረቢ ጥሩ ጊዜን በግሉ ያሳለፈው ጋቶች ፓኖም ለኩዌቱ አል ፋሂሊ ክለብ ፊርማውን ማኖር ችሏል።
ጋቶች ፓኖም በክለቡ ለአንድ አመት ለመቆየት ለአል ፋሂሊ ስፖርት ክለብ ፊርማውን አኑሯል።
ጋቶች ፓኖም ከሳምንታት በኃላ ወደ ግብፅ በማቅናት በቅድመ ውድድት ዝግጅት ቡድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።
ጋቶች ፓኖም ከሀገራችን ሊግ አልፎ :-
በሩሲያ
ኢራቅ
ግብፅ እና
ሳውዲ አረቢያ ሊጎች ላይ ባለፉት አመታት ተጫውቶ አሳልፏል።
“ ጭልፊቶቹ “ የሚል መጠርያ ያለው ክለቡ አስር ክለቦች በሚሳተፉበት የሀገሪቱ ሊግ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 6ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

❤22👍6🥰1
በትግራይ ክልል ለአንድ ሳምንት ብቻ አብረዉ የኖረችዉን የትዳር አጋሩን ገድሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
በትግራይ ክልል ፅራእ ወንበርታ ወረዳ ሓይቂ መስሓል ከተማ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የባለቤቱን የወይዘሮ ሸዊት አረጋዊን ህይወት በማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ የነበረው ግለሰብ ለአምስት ቀናት በተደረገ ጥብቅ ክትትል ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በትግራይ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
የክልሉ ፖሊስ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ያስመልጠኛል ወዳለው አካባቢ ሄዶ ተደብቆ የነበረ ቢሆንም የፖሊስ አባላቱ ባደረጉት ረቂቅ ክትትልና ህብረተሰቡ ባሳየው ያልተቆጠበ ትብብርና ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ፖሊስ ከተጠርጣሪው ባገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ቃል እንደተረጋገጠው ጥንዶቹ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጋብቻ ስርዓት የፈጸሙ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለያዩ ቤቶች ቆይተው ወንጀሉ ከመፈጸሙ ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር በአንድ ላይ መኖር የጀመሩት፤ይሁን እንጂ ሰኔ 25 ቀን ከምሽቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ተጠርጣሪው የባለቤቱን ህይወት ሊያጠፋ እንደቻለ ራሱ ለፖሊስ በሰጠው ቃል አምኗል።
በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪው ላይ የተጀመረውን ሙሉ የምርመራ ሂደት በማጠናቀቅ አስፈላጊውን መረጃ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

❤16💔9👍6