አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኢራን መሪዎች ከጥፋታቸዉ ካልተማሩ እንደምትገድላቸዉ እስራኤል ዛተች

👉 አሜሪካ የቤት እንስሶቿን ከቴል አቪቭ እንድታስወግድ ቃል ገብታለች ካልሆነ ፈጣን አጸፋ አለዉ ስትል ኢራን ተደምጣለች
 
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ሀገራቸው እስራኤልን “ለማጥፋት እቅድ” በመምራት አሊ ኻሜኔይን እንደገደለች እና እንደዚህ አይነት ድርጊቶችን ለማስተዋወቅ የሚሞክር ማንኛውንም የኢራን መሪ “እንደምታጠፋ” በድጋሚ ዝተዋል።ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትዝ በቴህራን በሚካሄደዉ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ በሰነዘሩት አስተያት ላይ ይህንኑ ተናግረዋል፡፡ ካትዝ እስራኤል በማንኛውም ጊዜ እና ማንኛውንም ስጋት ለመከላከል ዝግጁ መሆኗን አክለዋል።
 
ካትዝ ቀደም ሲል የካሜኔይ ልጅ እና ተተኪው ሞጅታባ “ለሞት ምልክት ተደርጎበታል” ሲሉ መናገራቸዉ ከቴህራን ተቃውሞ አስነስቷል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ትራምፕ “አሜሪካ የቤት እንስሶቿን ከቴል አቪቭ እንድታስወግድ ቃል ገብታለች” ሲሉ አክለዋል፣ “በሕዝባችን እና በአመራራችን ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ስጋት ፈጣን እና ኃይለኛ ምላሽ ያገኛል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
 
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተጀመረው እና በቀጣይ ቀናትም የሚካሄደው የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ የስንብት እና የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቶ ሺህዎች እየታደሙበት ቀጥሏል።ኻሜኒ ከአብዮታዊዋ እስላማዊት ሪፐብሊክ ኢራን መሪነታቸው በተጨማሪ በሺዓ እስልምና እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው መሪ ነበሩ።የቀድሞው መሪ የስንብት ሥነ ሥርዓት ከኢራን በተጨማሪ በኢራቅ ውስጥ ይከናወናል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5🥰2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
ሲሚንቶ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውና በጠቅላይ ሚንስትሩ ተመርቆ ስራ ከጀመረ አመታትን ያስቆጠረው የመንግስት እና የግል ሽርክና የሆነው ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደላሎች እየተፈተነ ይገኛል። ከወራት በፊት ከ1200-1500 ብር ይሸጥ የነበረው ይህ ሲሚንቶ አሁን ላይ ዋጋው በእጥፍ ጨምሮ ደብረብርሃን ከተማ ላይ እስከ 2500 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ፋብሪካው እየተቋቋመበት…
Update‼️ደላሎች ከፋብሪካው እንዲወጡ ተወሰነ‼️
የእንሳሮ ወረዳ አስተባባሪ አመራሮችና የለሚ  ናሽናል ሲሚንቶ  ፋብሪካ  አመራሮች  በፋብሪካው  ወቅታዊ  ሁኔታዎች ዙሪያ የምክክርና የውሳኔ  ሃሳብ ተቀመጠ።
በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ  የእንሳሮ ወረዳ አስተባባሪ አመራሮች ፣የሚመለከታቸው የተቋም ሃላፊዎችና  የለሚ ናሽናል  ሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች  በወቅታዊ  የፋብሪካው  ተግዳሮትና  ህገ  - ወጥ ደላሎች  መበራከት ላይ  የምክክርና የውሳኔ  ሃሳብ አስቀመጠ ።

የመጀመሪያው  በፋብሪካው  አመራሮች  ለማንሳት የተሞከረው  የመሰረተ ልማት  ጥበቃና  እንክብካቤ  በመንግስትና በህብረተሰቡ  እገዛ ቢደረግልን ፣ ሌላው     ፋብሪካው  በሙሉ አቅሙ  ማምረት  ያልቻለባቸው  ማነቆዎች  ሀገራዊ የነዳጅ እጥረት  ፣ በተፈለገው ልክ ከውጭ  ከሰል  መግባት ስላልቻለና  የላይም ስቶን  በበቂ ሁኔታ  ፋብሪካው ላይ እየቀረበ ስልሆነና  ተግባሩን ባለመረዳት  የሚዲያ   መራገቦች፣ እንዲሁም  መንገዱ  በአንድ በኩል ማለትም ከከተማው ውጪ  5 ኪሎ ሜትር ኮንክሪት አስቫልት   በተሰራው ላይ ብቻ  በመሆኑ የትራፊክ መጨናነቅ  ተፈጠረብን የሚሉ  ሃሳቦች   በዋናነት  ተነስተዋል ።
የተቀመጡ አዲስ ውሳኔዎች👇👇
👉 ሌላው  ሲሚንቶ ለመጫን  የሚመጡ  መኪኖች  መግቢያቸው  በከተማ ውስጥ  እና ሲሚንቶ ጭነው የሚወጡት ከከተማው ውጪ  በ5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስቫልት   መንገድ  መሄድ እንዳለባቸው  ውሳኔ ተሰጥቶበታል ።

👉 የትራፊክ መጨናነቅን  ለመቀነስ  ወቀሎ  አከባቢ  የተከለለው  የናሽናል ትራንስፖርት  የፓርኪንግ ቦታ  በአጭር ጊዜ  ይዞታውን  በማስከበርና በማልማት  ዘላቂ መፍትሄ  እንደሚሰጠውም  የውሳኔ ሃሳብ  ማስቀመጥ ተችሏል ።

👉 በመቀጠልም  ህጋዊም  ይሁን ህገ- ወጥ  ደላሎች  ከፋብሪካው  ቅጥር ግቢ  እንዲወገዱ  ጥብቅ ተልዕኮና ውሳኔ ተቀምጧል ።

👉 የትኛውም  መኪና  ካርድ ሳይሰጠው  ፋብሪካው  ቅጥር ግቢ  መግባት  እንደ ማይችል   ተወስኗል ።

👉 የተደራጁ  ወጣቶች  ወደ ወረዳው  የሚመጡ  ደንበኞችን  አግባብነት ባለው  ሁኔታ  ያለ እንግልት  አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውና  የክፍያ  መደራረቦች እንይኖሩ እንዲሁም  የስራ ቦታቸው  በእንሳሮ ወረዳ ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት  በአጭር ቀን እንዲፈታ   አቅጣጫ  ተቀምጧል ።

👉  በአጭር  ቀን  የሲሚንቶ  እጥረትን  ለመቅረፍና  ወደ  ሚፈለገው  የማምረት  ደረጃ  እንዲመጣ  ጅቡቲ  ወደብ 96000 ቶን  ከሰል  በ300 መኪና  እንደሚጓጓዝና  አንድ መርከብ የነበረው  1 መርከብ  በመጨመር  2 መርከቦች  ወደስራ ማስገባት መቻሉን  የብስራት ዜና  ማሰማት  ተችሏል ።

👉 በተያያዘም  የላይም ስቶን ጥሬ ዕቃ አቅርቦትን ለመቀነስ  ከትራንስፖርት  የግል ድርጅቶች  ጋር  የወረዳው መንግስትና ፋብሪካው የጋራ  ውይይት በማድረግ  ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል  መግባባት ላይ ተደርሷል ።

👉 የካርድ ሲስተሙ  24 ሰዓት የነበረው    ወደ 48 ሰዓት  እንዲሻሻል  ውሳኔ ተቀምጧል ። 

በመጨረሻም  በፋብሪካው ላይ  አላስፈላጊ የትኛውም ህገ- ወጥ  ተግባራት ሲፈፀሙ  የወረዳው የፀጥታ አካላት፣ ዐቃቢ ህግና የፋብሪካው  የሴኩሪቲ ሰዎች  አስተማሪ የሆነ  የእርምት እርምጃ    መወሰድ እንዳለበት  ጥብቅ ማሳሰቢያ  ተሰጥቷል ። ይህ በዚህ እንዳለ  ፋብሪካው  የሚያመርተው  የሲሚንቶ ምርት  ለየትኛውም አከባቢ  ፍትሃዊ  በሆነ መንገድ  እንዲደርስ  መሰራት እንዳለበት  ተነግሯል ። በመሆኑም  የተሰጡ  የውሳኔ  ነጥቦችንና የተሰጡ አቅጣጫዎችን  በዚሁ አጭር ቀን  ምን ውጤት እንዳመጡ  መገምገም  እንዳለበት  የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።
እንሳሮ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍3
የሆርሙዝ መስመር ተዘግቶባቸው የቆዩ መርከቦች በኦማን የባህር ዳርቻ በኩል ማለፍ መጀመራቸው ተጠቆመ
 
በዓለም-አቀፍ የነዳጅና የጋዝ ማጓጓዣ ዝውውር የላቀ ድርሻ ያለውና በአካባቢው በሰፈነው ውጥረት ሳቢያ ተዘግቶ የቆየው ሆርሙዝ ሰርጥ ከግጭቱ መርገብ ጋር ተያይዞ የመርከቦች እንቅስቃሴ እንደታየበት ከባህር ላይ ትራፊክ መከታተያ መረጃዎችን የጠቀሱ መገናኛ ብዙኃን አስነብበዋል።
 
ባለፉት ጥቂት ቀናት ወደ ወሽመጡ የተጠጉ ስምንት መርከቦች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ጉዟቸውን በማቋረጥ አቅጣጫ ቀይረው መመለሳቸውን ያወሳው የብሉምበርድ ዘገባ፣ ነገሮች ተቀይረው ባለፈው እሑድ ዕለት ብቻ ስድስት ግዙፍ የጭነት መርከቦች በኦማን የባህር ዳርቻ በኩል የተዘረጋውንና ጥበቃ የሚደረግለትን አማራጭ መተላለፊያ ተጠቅመው ማለፋቸውን አስነብቧል።
 
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል መርከቦች የደኅንነት ስጋትን ለመቀነስ በሚል የእንቅስቃሴ ማሳያቸውን አጥፍተው ስለሚጓዙ በወሽመጡ ላይ ያለውን ትክክለኛ የጉዞ ፍሰት ሙሉ በሙሉ ለማወቅ አዳጋች አድርጎታል ሲል የዘገበው አናዱሉ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
በመረጃ እጥረት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ሪፖርት ውስጥ ሳትካተት ቀረች

በቅርቡ የወጣው 10ኛው የአለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ሪፖርት 2026፣ በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ዋስትና ሁኔታ የሚያሳይ የተሟላ መረጃ ባለመገኘቱ ሀገሪቱ በሪፖርቱ ውስጥ ስሟ ሳይካተት መቅረቱን ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ በ2025 ዓ.ም. የሪፖርቱን ጥብቅ የቴክኒክ መስፈርቶች የሚያሟላ መረጃ ባለማቅረቧ፣ መረጃ ካልተካተተባቸው 18 ሀገራት አንዷ ሆናለች።

ይህ የመረጃ እጥረት መረጃ ለመሰብሰብ ፍቃድ ማግኘት በመቸገሩ፣ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ እና ለመረጃ አሰባሰብ ቅድሚያ ባለመሰጠቱ ምክንያት የተከሰተ ሲሆን፤ በሪፖርቱ የተካተቱ ሀገራት ቁጥር መቀነስ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋረጠባቸው ሰዎች ቁጥር በሪፖርቱ ላይ ዝቅ ብሎ እንዲታይ አድርጓል።

የኢትዮጵያ መረጃ ባይኖርም፣ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በአለማችን ትልቁን የምግብ ቀውስ እያስተናገደ መሆኑን የሚጠቁመው ሪፖርቱ፤ በሱዳን 25 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለችግር መዳረጋቸውን እና በኤል ፋሸር እና በካዱግሊ ረሃብ መከሰቱን፣ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን፣ በኬንያ እና በሶማሊያ በግጭት፣ በአየር ንብረት ተጽእኖ እና በምግብ ዋጋ ንረት ምክንያት የምግብ እጥረት ቀውሱ እየተባባሰ መምጣቱን አስታውቋል።

የሰብአዊ ድጋፍ ፋይናንስ ወደ ቀድሞው ዝቅተኛ ደረጃ መውረዱን የገለጸው ሪፖርቱ፣ በአስቸኳይ "የሰብአዊ ድጋፍ ዳግም ማስጀመሪያ" እንደሚያስፈልግ አሳስቦ፤ አስተማማኝ የመረጃ አሰባሰብ ለህይወት አድን ስራዎች ወሳኝ በመሆኑ ኢትዮጵያ የመረጃ ክፍተቷን መሙላት እንዳለባት ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤔64👍3🤯1
በዓለም ላይ ቀዳሚዎቹ የወርቅ አምራቾች ቻይና፣ አውስትራሊያ፣ ሩሲያ፣ ካናዳ እና አሜሪካ ናቸው።

በኩባንያ ደረጃ ደግሞ ከፍተኛውን ምርት የሚያቀርቡት እንደ ኒውሞንት (Newmont Corporation) እና ባሪክ ጎልድ (Barrick Gold) ያሉ ግዙፍ ዓለም አቀፍ የኮርፖሬት ማዕድን ኩባንያዎች ናቸው።

ከፍተኛ ወርቅ አምራች የሆኑት ቻይና፣አውስትራሊያ፣ሩሲያ፣ ካናዳ እና አሜሪካ ሲሆኑ

* ቻይና፦ በዓመት ከ370 ሜትሪክ ቶን በላይ በማምረት የዓለማችን ቀዳሚዋ ወርቅ አምራች አገር ናት።

* አውስትራሊያ፦ በየዓመቱ ከ300 ሜትሪክ ቶን በላይ ወጥ የሆነ ምርት በማውጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

* ሩሲያ፦ በዓመት በግምት ከ300 እስከ 330 ሜትሪክ ቶን በማምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስተኛውን ደረጃ ይዛለች።

* ካናዳ፦ በሰሜን አሜሪካ ዋነኛ አምራች ስትሆን፣ በዓመት ከ170 እስከ 200 ሜትሪክ ቶን ታመርታለች።

* አሜሪካ፦ በዋነኝነት በኔቫዳ ግዛት ከሚገኙ ማዕድናት የሚወጣ ሲሆን፣ በየዓመቱ በግምት ከ170 እስከ 200 ሜትሪክ ቶን ታመርታለች።

የኩባንያዎች ምርት በአብዛኛው በግል ባለሀብቶች እና በመንግሥት በሚተዳደሩ ግዙፍ ተቋማት የሚመራ ነው፦

* ኒውሞንት ኮርፖሬሽን (Newmont Corporation)፦ በአሜሪካ የሚገኘው ይህ ዓለም አቀፍ ኩባንያ በጠቅላላ የምርት መጠን የዓለማችን ትልቁ የወርቅ ማዕድን ኩባንያ ነው።

* ባሪክ ጎልድ (Barrick Gold)፦ በኔቫዳ የሚገኘውን ካርሊን ትሬንድ (Carlin Trend) ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ማዕድናት የሚያስተዳድር ግዙፍ የካናዳ ኩባንያ ነው።

* አግኒኮ ኢግል ማይንስ (Agnico Eagle Mines)፦ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ዕድገት እና በተረጋጋ የሥራ እንቅስቃሴ የሚታወቅ ሌላኛው የካናዳ ኩባንያ ነው።

* ፖሊየስ (Polyus)፦ በሳይቤሪያ የወርቅ ክምችት ላይ ሰፊ ይዞታ ያለው የሩሲያ ትልቁ ወርቅ አምራች ነው።

* ዚጂን ማይኒንግ (Zijin Mining)፦ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርቱን በፍጥነት እያሳደገ የመጣ የቻይና ሁለገብ ኩባንያ ነው።

* ናቮይ ማይኒንግ (NMMC)፦ በኡዝቤኪስታን ውስጥ ግዙፍ የማዕድን ሥራዎችን የሚያከናውን ትልቅ የመንግሥት የኢንዱስትሪ ተቋም ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍3🤩1
በአርሲ ግጭት 8 ሚሊሻ እና ፖሊሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 11 ሰዎች ናቸው የተገደሉት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ‼️

ለግጭቱ ሐይማኖታዊ መልክ ለመሰጠት የተደረገው ሙከራ ተገቢ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ተናግረዋል።

ሽፍቶች በአካባቢው ያለውን ሰላም ለማደብዘዝ ሙከራ እንዳደርጉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና ከተፈናቃዮች ውስጥ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑት መመለሳቸውን አንስተዋል፡፡
የአርሲ ሀገረ ስብከት 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልፆ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡579👍3
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
2👍2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደርግ ዘመንን ጥምረት በማንሳት ሱዳን፣ ሕወሓት እና ኤርትራ በጋራ እየሠሩ መሆኑን ገለጹ!

- ስማቸው ያልተጠቀሱ ሌሎች የውጭ ተዋናዮች ተሳትፎ መኖሩንም ጠቆሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፥ ሱዳን፣ ሕወሓት እና ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ በጋራ እየሠሩ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ድርጊቱን የደርግን ሥርዓት ለመጣል ከነበረው ጥምረት ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ ስማቸው ያልተጠቀሱ የውጭ ኃይሎች ከጀርባ እየተሳተፉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፤ ይህ ጥምረት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚደቅነው ምንም ዓይነት ሥጋት እንደሌለ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለምክር ቤቱ ሲናገሩ «ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ሱዳን ይቅርና ሌሎችም ቢጨመሩ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ቅንጣት ታህል ሥጋት የላቸውም» ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1412🤣10🤪1
ያልታከመ የማህፀን ኢንፌክሽን መካንነትን ሊያስከትል ይችላል ተባለ
 
በባክቴሪያ ፣በፈንገስ እና በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት የሴቶች የመራቢያ አካል ወይንም የማህፀን ኢንፌክሽን ህክምና ካላገኘ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ መካንነትን ሊያስከትል እንደሚችል ከብስራት ሬዲዮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ታዘባቸዉ ዉዴ ገልፀዋል።
 
የማህፀን ወይንም ብልት አካባቢ የሚከሰት ኢንፌክሽን በርካታ ሰዎችን ከሚያጠቁ የኢንፌክሽን አይነቶች መካከል ዋነኛዉ መሆኑ ተገልጿል ።ለማህፀን ኢንፌክሽን አጋላጭ የሚሆኑ በርካታ ምክንያቶች መኖራቸዉን የሚገልፁት ዶክተር ታዘባቸዉ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ እንደ ክላሚዲያ እና ጎኖሪያ ያሉ ባክቴሪያዎች ዋነኞቹ መሆናቸዉን አስገንዝበዋል ።
 
በአብዛኛዉ መካንነትን ሊያስከትሉ የሚችሉትም በባክቴሪያ አማካኝነት የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች ናቸዉ። የማህፀን ኢንፌክሽን ከመከሰቱ አስቀድሞ መከላከል ዋነኛዉ መፍትሄ መሆኑን ዶክተር ታዘባቸዉ  ገልፀው ብልት አካባቢ የማሳከክ ፣የመቁሰል ፣የሆድ ህመም እና ሽንት በሚሸናበት ወቅት የማቃጠል ስሜት ሲኖር ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ እና ህክምና ማግኘት ተገቢ ነዉ ብለዋል ።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍4
ኢትዮጵያን ከሶማሊላንድ ሪፐብሊክ በርበራ ወደብ የሚያገናኝ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የኤሌክትሪክ ባቡር ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል ተባለ። የግንባታው አጠቃላይ ወጪ $3.47 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ወጪው በኢትዮጵያ እና በኢሜሬትስ የሚሸፈን ይሆናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1912🤣8🤝2🤔1👌1🤪1
የፌደራል መንግስት የ2019 በጀት 2 ነጥብ 34 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2019 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል፡፡

በዚህም መሰረት 2 ነጥብ 34 ትሪሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የፌደራል መንግስት የ2019 በጀት ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የፀደቀው ጠቅላላ በጀት ከ2018 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ411 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወይም 21 ነጥብ 3 በመቶ እድገት እንዳለው ተመላክቷል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍4😡2
የገቢዎች ሚኒስቴር ለኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢዎች እስከ 250 ሺህ ዶላር የዋስትና ገደብ ጣለ‼️

የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመሰማራት በሚፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢዎች ላይ እንደየደረጃቸው እስከ 250,000 የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የፋይናንስ ዋስትና የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

በዚህ ወር አጋማሽ ላይ የወጣው መመሪያ በሀገሪቱ የታክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ የገበያ መግቢያ አዲስና ፈታኝ መስፈርት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የዋስትናው መጠንም በአቅራቢው የአገልግሎት ዓይነትና በሚያገለግሉት ግብር ከፋዮች ልኬት ላይ ተመስርቶ በ10 ደረጃዎች የተከፋፈለ ነው።

በዚህም መሰረት የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አቅራቢዎች 30,000 ዶላር፣ የሶፍትዌር-አስ-አ-ሰርቪስ አቅራቢዎች 50,000 ዶላር፣ የኢ-ኮሜርስና ዲጂታል ገበያ አንቀሳቃሾች 25,000 ዶላር፣ እንዲሁም የራሳቸውን የውስጥ ደረሰኝ ሥርዓት የሚጠቀሙ ግብር ከፋዮች 15,000 ዶላር የባንክ ወይም የኢንሹራንስ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

የዋስትናው መጠንም አቅራቢዎች የሚያገለግሏቸው ደንበኞች ቁጥር ወይም የሽያጭ ልውውጣቸው እያደገ ሲሄድ በየሁለት ዓመቱ የሚታደስ ሲሆን፣ ከ40 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮችን ለሚያገለግሉ ወይም ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ሽያጭ ላላቸው ድርጅቶች ከፍተኛው የዋስትና ጣሪያ 250,000 ዶላር ይደርሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3
በወላይታ ሶዶ ከተማ የ14 ሰዎችን ኤቲኤም ካርድ የሰረቀው  ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
 
በወላይታ ሶዶ ከተማ የኤቲኤም (ATM) ካርድ በመቀየር የማጭበርበር ወንጀል ለመፈጸም የሞከረው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ።የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት በወላይታ ሶዶ ከተማ አንድ የባንክ ደንበኛ ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ለማውጣት ሲሞክር ማሽኑ ችግር አጋጥሞት ነበር።
 
በወቅቱ በአቅራቢያው የነበረው ተጠርጣሪ ዳንኤል ደሳለኝ “ካርዱን ስጠኝ፣ በፀጉሬ ጠርጌ እሰጥሃለሁ” በሚል የማታለያ ዘዴ ካርዱን ተቀብሎ ወስዷል።በሰዓቱም የሚስጥር ቁጥሩን (PIN) ሲያስገባ በመመልከት  ካርዱን ጠርጎ የመለሰ በማስመሰል ሌላ የተቀየረ የኤቲኤም ካርድ ሰጥቶ ዋናውን ካርድ ይዞ ለማምለጥ ሞክሯል።የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ፖሊስ ባደረገው ፈጣን ክትትል ተጠርጣሪውን እጅ ከፍንጅ በመያዝ ቁጥጥር ስር አውሏል።
 
ፖሊስ ምርመራውን በማስፋት በፍርድ ቤት በተሰጠ የብርበራ ትዕዛዝ በተጠርጣሪው የተጎጂውን ካርድ ጨምሮ 14 የተለያዩ ሰዎች የኤቲኤም ካርዶችን ይዞ መገኘቱ ተገልጿል።ፖሊስ ህብረተሰቡ ከኤቲኤም ማሽኖች  ገንዘብ በሚያወጣበት ጊዜ የሚስጥር ቁጥሩን ለሌላ አካል እንዳያሳይ በማሽኑ አጠቃቀም ላይ ችግር ካጋጠመውም ከማያውቀው ሰው እርዳታ ከመጠየቅ ይልቅ የባንኩን ባለሙያዎች ወይም የጥበቃ አካላትን ብቻ እንዲያነጋግር አሳስቧል።(Dagu)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12🤣11👍7👀1🙉1
በቀጣይ 5 ዓመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶች ይገነባሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በቀጣይ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያ ባለፉት ሰባት ዓመታት 1.2 ሚሊዮን ቤቶች መገንባታቸውን ጠቅሰው በቀጣዩ አምስት ዓመታት ተጨማሪ 1.5 ሚሊዮን ቤቶች እንደሚገነቡ ተናግረዋል።

እንደ ገለጻቸው  የቤቶቹ ግንባታ በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ ተሳትፎ እና በሌሎች የአጋርነት መንገዶች የሚከናወን ሲሆን ለዚህም የሚያግዝ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ መፅደቁን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ግብዓት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ምርት መጀመራቸውን፣ዘርፉን የሚደግፉ የሰው ኃይል ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን እና በከተማና በገጠር የቤት ግንባታ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የቤት ፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ የሞርጌጅ ስርዓት እየተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመው፣ ዜጎች ቤት በቀጥታ መግዛት ባይችሉም በረጅም ጊዜ ክፍያ ከገቢያቸው ጋር በሚጣጣም መንገድ ባለቤት እንዲሆኑ መንግሥት በተለያዩ አማራጮች ላይ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2621👍6🤪1
መረጃ‼️

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት፣ በኤርትራ የተመድ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተርን የጊዜ ቆይታ በ23 የድጋፍ ድምጽ በድጋሚ ላንድ ዓመት አራዘመ።

የምክር ቤቱ አባል የኾነችው ኢትዮጵያ፣ የልዩ ራፖርተሩን የጊዜ ቆይታ ለማራዘም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ደግፋ ድምጽ ሠጥታለች።

ኬንያንና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 17 አገራት ድምጸ ተዓቅቦ ሲያደርጉ፣ ግብጽ፣ ቻይና፣ ቡሩንዲ፣ ፓኪስታን እና ሕንድ የውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመዋል።

ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡት የአውሮፓ አገራት ነበሩ።

ኤርትራ፣ ከእንግዲህ በልዩ ራፖርተሩ ዙሪያ ከአጋር አገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደማታደርግ በቅርቡ ማሳወቋ አይዘነጋም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ ልውውጥ‼️
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ፤ " ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ ሶስት የንግድ እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽማለች " በማለት እንደ በስትራቴጂካዊ የኢራን ቦታዎች ላይ ከባድ የአየር ድብደባ ፈጽሟል።

የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ዳግም በእጅጉ አገርሽቷል።

ኢራን፣ ዋሽንግተን ኦማን አቅራቢያ አዳዲስ የባህር መስመሮችን ለመክፈት ጥረት እያደረገች እንደሆነና ይህም የተደረሰውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) የሚጥስ እንደሆነ ትገልጻለች። ይህ እየተባለ ባለበት ሰዓትና ኢራንም መረከቦች በዛ እንዳያልፉ ባስጠነቀቀችበት ሰዓት ነው ኦማን አቅራቢያ 3 መርከቦች የተመቱ።

አሜሪካም ፣ ለተፈጸመው ጥቃት መላሽ ለመስጠት ወሳኝ ስትራቴጂካዊ የሚባሉ የኢራን ወደብ ቦታዎች ደብድባለች። ከዚህ ወታደራዊ እርምጃ ትንሽ ቀደም ብሎ፣ የአሜሪካው ግምጃ ቤት ለኢራን ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ የነዳጅ ማዕቀብ ማቃለያ በይፋ የሰረዘ ሲሆን ይህም ቴህራን በሕጋዊ መንገድ ነዳጅ ወደ ውጭ የመላክ አቅሟን ያግደዋል።

ኢራን፣ አሜሪካ " የተደረሰውን ስምምነት ጥሳለች " የሚል ክስ እያቀረበችባት ነው።
አሁን ላይ የተፈጠረው ሁኔታ ዓለም አቀፍ ነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍7😢1
የቤት ኪራይ ጭማሪ ይፋ ሆነ

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ውል ምዝገባ ተጀመረ፤ የጭማሪው ጣሪያ 11.5% ሆነ

​በአዲስ አበባ ከተማ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ምዝገባ ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በይፋ ተጀምሯል።

ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የከተማዋ የቤቶች አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

​ይህ አሰራር በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን ለመግታትና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ያለመ ነው።

ውሳኔው የነዋሪዎችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ አከራዮች ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ፣ ተከራዮች ደግሞ ከስነ-ልቦና ስጋትና መፈናቀል ድነው እንዲረጋጉ ይረዳል ተብሏል።

​ይሁን እንጂ አዲሱ የዋጋ ተመን ከመጣሉ በፊት በርካታ አከራዮች በተከራዮቻቸው ላይ አስቀድመው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸው በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ እየቀሰቀሰ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14🤔4👍2
የኤርትራ መንግስት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በፓርላማ ቀርበው ለሰጡት ማብራሪያ እና በተለይ ከኤርትራ (ሻዕቢያ)፣ ከሕወሓት እና ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ላነሷቸው ነጥቦች በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ፈጣንና ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥቷል።

ሁለቱ ወገኖች በቀጠናው ሰላምና በጎረቤት ሀገራት ጣልቃ ገብነት ዙሪያ እርስ በርሳቸው ተቃራኒ የሆኑ ክሶችን ሰንዝረዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ንግግራቸው በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወጣቶችን በጉልበት እያፈሱ ለሱዳን ጦርነት "እየሸጡ" መሆኑን ገልጸዋል።

"የትግራይ ወጣቶች በማያውቁት ጉዳይ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ህይወታቸውን እያጡ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ድርጊት የህዝቡን መከራ የሚያባብስ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

በተቃራኒው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ለሱዳን ግጭት መባባስ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ራሱ ነው ሲል ገልጿል።

ኢትዮጵያ ለሱዳኑ ፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (RSF) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሚስጥራዊ የጦር ሰፈርና ማሰልጠኛ በመስጠት በቀጥታ በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑንና ለዚህም "ግልጽ ማስረጃዎች አሉ" ሲል አጸፋዊ ክስ ሰንዝሯል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በንግግራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም አይነት "ትንኮሳ" ለመመከት መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ፣ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ህግጋትንና የቀጠናውን ሀገራት ሉዓላዊነት እየጣሰች ያለችው "የባህር በር ባለቤትነት" በሚል በምታሳየው የግዛት ማስፋፋት ፍላጎት ነው ብሏል። 

የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ በኩል "ጥቃት አድራሽ" በሌላ በኩል ደግሞ "ተጠቂ" ሆኖ የመቅረብ ድራማ እየሰራ ነው ስትልም ወርፋለች።

@Addis_Reporter
👍85🤔1😢1🤣1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍42
ኢራናውያን በሽተኞች ናቸው-ትራምፕ‼️
የኢራን ሰዎች በሽተኞች ናቸው፣ ከእነሱ ጋር ስምምነት አላደርግም ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣113👍2💯2🤡1
የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ተባለ

በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ማደያዎች ላይ በተከናወነው የመቅጃ ልኬት ምርመራ፣ የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ሲል የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አሳወቀ ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ወ/ሮ ሃላፊ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት፣ በሁለት ነዳጅ ማደያዎች የመቅጃ ማሽን የልኬት ችግር በመገኘቱ ከነዳጅ አቅርቦት ለሁለት ወራት እንዲታገዱ ተደርጓል። እርምጃ የተወሰደባቸው የነዳጅ ማደያዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘው ኖክ ነዳጅ ማደያ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አልፋ ነዳጅ ማደያ ናቸው ብለዋል። 

እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ተባረክ ነዳጅ ማደያ ከነዳጅ አቅርቦት ለአንድ ወር እንዲታገድ ተደርጓል የተባለ ሲሆን፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ የሚገኘው የተባበሩት ነዳጅ ማደያ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ የሚገኘው ኦላ ነዳጅ ማደያ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አክለውም፣ ቢሮው በከተማው ውስጥ ልኬትን በማዛባት ፍትሃዊ የንግድ ውድድርን የሚያደናቅፉ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የጀመረውን የክትትልና የሕግ ማስከበር እርምጃ ይበልጥ በማጠናከር እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍3🥱1