አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.9K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ድንጋይ ሲወረውሩ በነበሩ እናቶች ላይ እርምጃ እንወስዳለን
‹‹በአውቶቡስ ላይ ድንጋይ በወረወሩት እናቶች ላይ እርምጃ እንወስዳለን›› ሲሉ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ተናገሩ፡፡ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ሀይሌ አረጋዊ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የመግለጫቸው ዋነኛ ማጠንጠኛም በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውና መነጋገሪያ የሆነው ቪዲዮ ነው፡፡ በዚህ ቪዲዮ በከተማው ቀበሌ 05 አካባቢ በግዳጅ ታፍነው ወደማሰልጠኛ ጣቢያ የሚወሰዱ ወጣቶችን በያዘው አውቶቡስ ላይ እናቶች በጩኸት ተቃውሞ ከማሰማታቸውም በላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ይታያል፡፡

ከንቲባው በመግለጫቸው ‹‹በከተማው ውስጥ የትግራይን አጀንዳ ለመጥለፍና ለማደናቀፍ የሚሰራ የተደራጀ ሴራ አለ›› ብለዋል፡፡ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ቢኖርም ሁሉም የከተማው ነዋሪ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም በጋራ መስራት እንዳለበት ያሳሰቡት ከንቲባው ነገር ግን አንድነቱን ለመሸርሸር የሚሰሩ አካላት እንዳሉ ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም ትልቁ ማሳያው ሰሞኑን በቀበሌ 05 የተከሰተው ድርጊት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በቀበሌ 05 የተፈጠረውና በማህበራዊ ሚደያ የተሰራጨውን ድርጊት መገምገማቸውን ያስታወቁት ከንቲባው ጨምረውም ‹‹የተፈጠረው ወጣቶችን የማስገደድና ያለማስገደድ ጉዳይ ሳይሆን የፀረ ትግል አካላት የተቀናጀ ተግባር ነው›› ብለዋል፡፡ በዚህ ድርጊት ላይ የተሳተፉት ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀውም ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል፡፡

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡4417🤔4😢3👍2🎉1💔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሱዳን የሚገኘው የህወሓት አርሚ 70 ሰራዊት አባላት ትናንት ሰኔ 28/2018 ዓ. ም ከሱዳን ተነስተው ትናንሽ ጀልባዎችን ​​ተጠቅመው ወደ ተከዜ ወንዝ ሲያመሩ ታይተዋል።
ከፍተኛ የጦር አዛዦችም አብረው ይታያሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር ጋር በመተባበር የህወሓት አርሚ 70 ጦር በሱዳን ጦርነት ውስጥ ስላላቸው ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ ተሳትፎ፣ እያደረጉት ስላለው ድጋፍ ወይም ስለፈጸሟቸው ጥሰቶች ጥብቅ ክትትል በማድረግ በየ6 ወሩ ለኮንግረሱ ሪፖርት እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ማሳለፉ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍4
ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ !

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን 97.48% የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።

የ2018 የትምህርት ዓመት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ 84,257 ተማሪዎች መካከል 82,137 የሚሆኑ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ሆኖ የተቆረጠውን 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበዋል።

768 ትምህርት ቤቶች ፈተና አስፈትነው 543 ያህሉ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ይህን ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍2
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍21🎉1
ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ስማርትፎን በፍጹም እንዳይጠቀሙ አዲስ ጥናት አስጠነቀቀ

በዩናይትድ ኪንግደም አራት ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ያካሄዱት ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ታዳጊዎችን ለዲጂታል ስክሪኖች አዘውትሮ ማጋለጥ በአካላዊ፣ አእምሯዊና ስሜታዊ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።

​ዋና ዋና የግኝቱ ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

የቋንቋና የማኅበራዊ ግንኙነት መዳከም፦ ስክሪን ማየት የሕፃናትን የቋንቋ የመማር ፍጥነት የሚገታ ሲሆን፣ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸውን ስሜታዊ ትስስር ያላላል።

የጤና እክሎች፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በመቀነስ ለእንቅልፍ እክል፣ ለውፍረት እና ለተለያዩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።

የስሜት መቃወስ፦ ሕፃናት ሲያለቅሱ ወይም ሲበሳጩ ስልኮችን መስጠት፣ ወደፊት ስሜታቸውን በራሳቸው የመቆጣጠር ብቃታቸውን ያሳጣቸዋል።

​የጥናቱ መሪ ሬፍ ክሌይተን እንደገለጹት፣ ወላጆች ግልጽ መመሪያ ስላላገኙ ሳያውቁት ልጆቻቸውን ለጉዳት እየዳረጉ ነው። በመሆኑም መንግስት ከጥንቃቄ መመሪያዎቹን እንዲከልስና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አሳሳች ማስታወቂያዎችን እንዲያቆሙ ጥሪ ቀርቧል።

ባለሙያዎች ወላጆች ከዲጂታል ስክሪን ይልቅ ከልጆቻቸው ጋር በመጫወት፣ በማውራትና ጥራት ያለው ጊዜ በማሳለፍ ላይ እንዲያተኩሩ መክረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍3
📍በቬንዙዌላ በርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር 3 ሺሕ 342 ደረሰ

ከ16 ሺሕ 740 በላይ መጎዳታቸው ተገልጿል። 6 ሺሕ 462 ሰዎችን ከአደጋ ማዳን ተችሏል።

17 ሺሕ 345 ቤታቸው ፈራርሷል። 79 ጊዚያዊ የመጠለያ ካምፖች ተዘጋጅተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ወደ 5 ሺሕ የሚጠጉ ተጎጂዎች ተፈናቃዮች የሰብዓዊ እርዳታ እያገኙ እንደሚገኙ ተመላክቷል። ከ4 ሺሕ በላይ የአደጋ ባለሙያዎች ተሰማርተዋል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢158👍2🤯1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
5👍2
በዛሬው ዕለት ሰኔ 29/2018 ዓ.ም #ከመቐለ ተነስተው ተሳፋሪ ጭነው ወደ አዲስ አበባ ሲያመሩ የነበሩ ሁለት ባሶች #ዓዲጉደም ሲደርሱ አስቁመዋቸዋል። ተሳፋሪዎች አስወርደው ወደ አዳራሽ እንዲገቡ አድርገዋቸዋል።
ከሳምንት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ከመቐለ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ሲያመሩ የነበሩ አምስት ባሶች መኾኒ ሲደርሱ አቁመው ተሳፋሪዎች አግተዋቸዋል። ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ወስደዋቸዋል።
የትግራይ ትራንስፖርት ቢሮ ግዮን እና ሀበሻ ባስን መከልከሉ ይታወሳል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢16👍96🤣1👀1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
👍31🤔1
4🤪3😢2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የጦር ወንጀል እየፈጸማችሁ ነው፤ ባፋጣኝ ዘመቻውን አቁሙ›› HRW‼️
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት የሆነው ሂውማን ራይትስ ዋች ይህን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ድርጅቱ የሕወሓትን የግዳጅ አፈሳ ‹የጦር ወንጀል› እንደሆነ በመጥቀስ ባፋጣኝ ይህን ዘመቻ እንዲያቆሙት ጠይቋል፡፡

የግዳጅ ምልመላውን በተመለከተ ምስክሮች፣ የታፈሱ ሰዎች ዘመዶች እና ያመለጡ ወጣቶችን ጨምሮ 18 ሰዎችን ያነጋገረው ተቋሙ፤ ከሚያዝያ አስቀድሞ በነበሩት ወራት የክልሉ ባለሥልጣናት "በሕዝብ ስብሰባዎች፣ ደብዳቤዎች እና የስልክ ጥሪዎች" አማካኝነት የቀድሞ የትግራይ ኃይሎች ተዋጊዎች መልሰው እንዲመዘገቡ ሲያደርጉ ነበር።

"በሚያዝያ መጨረሻ በመንገዶች፣ በገበያዎች እና በወርቅ ማውጫ ስፍራዎች የጅምላ ከበባ በማካሄድ ዘመቻው ተቀጣጠለ" ሲል መግለጫው አስፍሯል።

የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ፤ የበታች ባለሥልጣናት "የቀድሞ ተዋጊዎች ዝርዝር" እንዳላቸው እንዲሁም "ሊመለመሉ የሚችሉ ሰዎችን ለመለየት የአካባቢ መረጃ ሰጪዎችን" እንደሚጠቀሙ ቃለ መጠይቅ ካደረገላቸው ሰዎች መስማቱን ገልጿል።

"የትግራይ ኃይሎች እና ባለሥልጣናት የቀድሞ ተዋጊዎችን እንዲሁም ሌሎች ወንዶች እና ወንድ ልጆችን አፍነው እየወሰዱ" መሆኑን "በመላው" ትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ማኅበረሰቦች መናገራቸውም በመግለጫው ተጠቅሷል።

ነዋሪዎች እየተወሰዱ ያሉት "ከመንገድ፣ በምሽት የቤት ለቤት ፍተሻ እንዲሁም ከወርቅ ማውጫ ስፍራዎች" እንደሆነም ሂውማን ራይትስ ዎች ገልጿል።

የሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ላቲሺያ ባደር "የትግራይ ባለሥልጣናት ወንዶች እና ወንድ ልጆችን በግዳጅ ወደ ኃይላቸው ለማስገባት [የሚያካሂዱት] ዘመቻ ክልሉ በሙሉ የፍርሃት ድባብ ፈጥሯል" ሲሉ ተችተዋል።

በጄኔቫ ስምምነት መሠረት ይህ ዓይነቱ ተግባር የጄኔቫ ስምምነትን የሚጥስ እንደሆነ ተቋሙ አሳስቧል።

"በግዳጅም ሆነ በፈቃድ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን ለወታደራዊ ተግባር መመልመል ወይም መጠቀም ከፍተኛ የልጆች ሰብአዊ መብቶች ጥሰት" እንደሆነም ገልጿል።

ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ላይ ሲፈጸም ደግሞ ጦር ወንጀል እንደሆነ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍129👌1💯1🤷1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የፌደራል የታክስ አስተዳደርን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ይዟቸው የመጡ አዳዲስ ለውጦች ምንድናቸው?

የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008ን ለማሻሻል የወጣው ማሻሻያ አዋጅ በርካታ መሠረታዊ ለውጦችንና አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ ቀርቧል። ዋና ዋናዎቹ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. አዳዲስ ትርጓሜዎችና የተቋም ስም ለውጥ

👉🏽 መስማማት (Settlement)፡ የታክስ አለመግባባቶችን በውይይትና በስምምነት ለመፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በትርጓሜ ደረጃ ተካቷል።
👉🏽 የታክስ ማጭበርበር፡ ታክስን ለመሰወር የሚደረጉ እንደ ሐሰተኛ ደረሰኝ ማቅረብና ገቢን መደበቅ ያሉ ተግባራት በዝርዝር ተተርጉመዋል።

2. የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ሥርዓት

ይህ  አዋጁ ይዞት የመጣው ትልቁ ለውጥ ሲሆን፣ ክርክሮችን በፍርድ ቤት ወይም በይግባኝ ኮሚሽን ከመጨረስ ይልቅ በባለሥልጣኑና በታክስ ከፋዩ መካከል በሚደረግ ስምምነት እንዲቋጩ የሚያስችል ነው።
👉🏽 የአስማሚ ሚና፡ የታክስ ባለሥልጣኑ ነጻና ገለልተኛ "አስማሚ" በመመደብ ሂደቱን ያመቻቻል።
👉🏽 ሂደቱ፡ መስማማት የሚቻለው በታክስ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ከቀረበ በኋላ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት ለይግባኝ የተቀመጡ የጊዜ ገደቦች ታግደው ይቆያሉ።
👉🏽 ውጤቱ፡ የሚደረሰው ስምምነት በጽሁፍ ሆኖ በሁለቱም ወገኖች ከተፈረመ አስገዳጅና ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

3. በአዲስ ማስረጃ አቀራረብ ላይ የተጣለ ገደብ

👉🏽 ታክስ ከፋዮች የታክስ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በቅሬታ ወይም በይግባኝ ወቅት አዲስ ማስረጃ የማቅረብ መብታቸው ተገድቧል።
👉🏽 አዲስ ማስረጃ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ማስረጃው የታወቀው ከውሳኔ በኋላ ከሆነ ወይም አቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልቀረበ ብቻ ነው።
👉🏽 በዚህ መልክ የሚቀርብ አዲስ ማስረጃ በታክስ ዕዳው ላይ 20% ቅጣት እንዲከፈል ያደርጋል።

4. የታክስ ስሌት ማሻሻያና የይርጋ ጊዜ

👉🏽 የማጭበርበር ድርጊት፡ ባለሥልጣኑ የታክስ ማጭበርበር መኖሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካገኘ፣ የታክስ ስሌቱን የማሻሻያ ጊዜ (ይርጋ) እስከ 10 ዓመት እንዲራዘም ተደርጓል።
👉🏽 መደበኛው የታክስ ስሌት ማሻሻያ ጊዜ ግን በነበረበት 5 ዓመት ቀጥሏል።

5. በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የታክስ ክሊራንስ

👉🏽 የታክስ ዕዳ ያለባቸው ነገር ግን በክርክር ላይ ያሉ ወይም የክፍያ ስምምነት የፈጸሙ ታክስ ከፋዮች የንግድ ፈቃድ ለማደስ፣ በጨረታ ለመሳተፍና ብድር ለማግኘት የሚያስችላቸው "በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የታክስ የምስክር ወረቀት" ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቷል።

6. የታክስ ከፋዮች ምደባ

👉🏽 የታክስ ከፋዮች ምዝገባ ኢትዮጵያ በተቀበለችው የዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ምደባ ደረጃ (ISIC) መሠረት እንዲከናወንና ታክስ ከፋዮች በተለያዩ ምድቦች እንዲመደቡ ተደንግጓል።

7. የቅጣት ማስተካከያዎች

👉🏽 ደረሰኝ አለመስጠት፡ የታክስ ደረሰኝ ሳይሰጥ ሲቀር የሚጣለው አስተዳደራዊ ቅጣት በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እንዲሆን ተሻሽሏል።
👉🏽 የድርጅት ኃላፊዎች ተጠያቂነት፡ አንድ ድርጅት የታክስ ወንጀል ሲፈጽም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም የፋይናንስ ኃላፊ ወንጀሉ መፈጸሙን ካወቁ ወይም ካዘዙ ተጠያቂ ይሆናሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍2🤣1
" የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ይሰጣል " - ጤና ሚኒስቴር

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

መረጃቸውን ወደ ሲስተም ያላስገቡ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (FAN 16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንዲዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

መረጃ የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ተመዛኞች የስም ዝርዝራቸው በተማሩበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍3🤪1
የኢራን መሪዎች ከጥፋታቸዉ ካልተማሩ እንደምትገድላቸዉ እስራኤል ዛተች

👉 አሜሪካ የቤት እንስሶቿን ከቴል አቪቭ እንድታስወግድ ቃል ገብታለች ካልሆነ ፈጣን አጸፋ አለዉ ስትል ኢራን ተደምጣለች
 
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ሀገራቸው እስራኤልን “ለማጥፋት እቅድ” በመምራት አሊ ኻሜኔይን እንደገደለች እና እንደዚህ አይነት ድርጊቶችን ለማስተዋወቅ የሚሞክር ማንኛውንም የኢራን መሪ “እንደምታጠፋ” በድጋሚ ዝተዋል።ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትዝ በቴህራን በሚካሄደዉ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ በሰነዘሩት አስተያት ላይ ይህንኑ ተናግረዋል፡፡ ካትዝ እስራኤል በማንኛውም ጊዜ እና ማንኛውንም ስጋት ለመከላከል ዝግጁ መሆኗን አክለዋል።
 
ካትዝ ቀደም ሲል የካሜኔይ ልጅ እና ተተኪው ሞጅታባ “ለሞት ምልክት ተደርጎበታል” ሲሉ መናገራቸዉ ከቴህራን ተቃውሞ አስነስቷል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ትራምፕ “አሜሪካ የቤት እንስሶቿን ከቴል አቪቭ እንድታስወግድ ቃል ገብታለች” ሲሉ አክለዋል፣ “በሕዝባችን እና በአመራራችን ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ስጋት ፈጣን እና ኃይለኛ ምላሽ ያገኛል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
 
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተጀመረው እና በቀጣይ ቀናትም የሚካሄደው የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ የስንብት እና የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቶ ሺህዎች እየታደሙበት ቀጥሏል።ኻሜኒ ከአብዮታዊዋ እስላማዊት ሪፐብሊክ ኢራን መሪነታቸው በተጨማሪ በሺዓ እስልምና እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው መሪ ነበሩ።የቀድሞው መሪ የስንብት ሥነ ሥርዓት ከኢራን በተጨማሪ በኢራቅ ውስጥ ይከናወናል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5🥰2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
ሲሚንቶ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውና በጠቅላይ ሚንስትሩ ተመርቆ ስራ ከጀመረ አመታትን ያስቆጠረው የመንግስት እና የግል ሽርክና የሆነው ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደላሎች እየተፈተነ ይገኛል። ከወራት በፊት ከ1200-1500 ብር ይሸጥ የነበረው ይህ ሲሚንቶ አሁን ላይ ዋጋው በእጥፍ ጨምሮ ደብረብርሃን ከተማ ላይ እስከ 2500 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ፋብሪካው እየተቋቋመበት…
Update‼️ደላሎች ከፋብሪካው እንዲወጡ ተወሰነ‼️
የእንሳሮ ወረዳ አስተባባሪ አመራሮችና የለሚ  ናሽናል ሲሚንቶ  ፋብሪካ  አመራሮች  በፋብሪካው  ወቅታዊ  ሁኔታዎች ዙሪያ የምክክርና የውሳኔ  ሃሳብ ተቀመጠ።
በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ  የእንሳሮ ወረዳ አስተባባሪ አመራሮች ፣የሚመለከታቸው የተቋም ሃላፊዎችና  የለሚ ናሽናል  ሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች  በወቅታዊ  የፋብሪካው  ተግዳሮትና  ህገ  - ወጥ ደላሎች  መበራከት ላይ  የምክክርና የውሳኔ  ሃሳብ አስቀመጠ ።

የመጀመሪያው  በፋብሪካው  አመራሮች  ለማንሳት የተሞከረው  የመሰረተ ልማት  ጥበቃና  እንክብካቤ  በመንግስትና በህብረተሰቡ  እገዛ ቢደረግልን ፣ ሌላው     ፋብሪካው  በሙሉ አቅሙ  ማምረት  ያልቻለባቸው  ማነቆዎች  ሀገራዊ የነዳጅ እጥረት  ፣ በተፈለገው ልክ ከውጭ  ከሰል  መግባት ስላልቻለና  የላይም ስቶን  በበቂ ሁኔታ  ፋብሪካው ላይ እየቀረበ ስልሆነና  ተግባሩን ባለመረዳት  የሚዲያ   መራገቦች፣ እንዲሁም  መንገዱ  በአንድ በኩል ማለትም ከከተማው ውጪ  5 ኪሎ ሜትር ኮንክሪት አስቫልት   በተሰራው ላይ ብቻ  በመሆኑ የትራፊክ መጨናነቅ  ተፈጠረብን የሚሉ  ሃሳቦች   በዋናነት  ተነስተዋል ።
የተቀመጡ አዲስ ውሳኔዎች👇👇
👉 ሌላው  ሲሚንቶ ለመጫን  የሚመጡ  መኪኖች  መግቢያቸው  በከተማ ውስጥ  እና ሲሚንቶ ጭነው የሚወጡት ከከተማው ውጪ  በ5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስቫልት   መንገድ  መሄድ እንዳለባቸው  ውሳኔ ተሰጥቶበታል ።

👉 የትራፊክ መጨናነቅን  ለመቀነስ  ወቀሎ  አከባቢ  የተከለለው  የናሽናል ትራንስፖርት  የፓርኪንግ ቦታ  በአጭር ጊዜ  ይዞታውን  በማስከበርና በማልማት  ዘላቂ መፍትሄ  እንደሚሰጠውም  የውሳኔ ሃሳብ  ማስቀመጥ ተችሏል ።

👉 በመቀጠልም  ህጋዊም  ይሁን ህገ- ወጥ  ደላሎች  ከፋብሪካው  ቅጥር ግቢ  እንዲወገዱ  ጥብቅ ተልዕኮና ውሳኔ ተቀምጧል ።

👉 የትኛውም  መኪና  ካርድ ሳይሰጠው  ፋብሪካው  ቅጥር ግቢ  መግባት  እንደ ማይችል   ተወስኗል ።

👉 የተደራጁ  ወጣቶች  ወደ ወረዳው  የሚመጡ  ደንበኞችን  አግባብነት ባለው  ሁኔታ  ያለ እንግልት  አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውና  የክፍያ  መደራረቦች እንይኖሩ እንዲሁም  የስራ ቦታቸው  በእንሳሮ ወረዳ ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት  በአጭር ቀን እንዲፈታ   አቅጣጫ  ተቀምጧል ።

👉  በአጭር  ቀን  የሲሚንቶ  እጥረትን  ለመቅረፍና  ወደ  ሚፈለገው  የማምረት  ደረጃ  እንዲመጣ  ጅቡቲ  ወደብ 96000 ቶን  ከሰል  በ300 መኪና  እንደሚጓጓዝና  አንድ መርከብ የነበረው  1 መርከብ  በመጨመር  2 መርከቦች  ወደስራ ማስገባት መቻሉን  የብስራት ዜና  ማሰማት  ተችሏል ።

👉 በተያያዘም  የላይም ስቶን ጥሬ ዕቃ አቅርቦትን ለመቀነስ  ከትራንስፖርት  የግል ድርጅቶች  ጋር  የወረዳው መንግስትና ፋብሪካው የጋራ  ውይይት በማድረግ  ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል  መግባባት ላይ ተደርሷል ።

👉 የካርድ ሲስተሙ  24 ሰዓት የነበረው    ወደ 48 ሰዓት  እንዲሻሻል  ውሳኔ ተቀምጧል ። 

በመጨረሻም  በፋብሪካው ላይ  አላስፈላጊ የትኛውም ህገ- ወጥ  ተግባራት ሲፈፀሙ  የወረዳው የፀጥታ አካላት፣ ዐቃቢ ህግና የፋብሪካው  የሴኩሪቲ ሰዎች  አስተማሪ የሆነ  የእርምት እርምጃ    መወሰድ እንዳለበት  ጥብቅ ማሳሰቢያ  ተሰጥቷል ። ይህ በዚህ እንዳለ  ፋብሪካው  የሚያመርተው  የሲሚንቶ ምርት  ለየትኛውም አከባቢ  ፍትሃዊ  በሆነ መንገድ  እንዲደርስ  መሰራት እንዳለበት  ተነግሯል ። በመሆኑም  የተሰጡ  የውሳኔ  ነጥቦችንና የተሰጡ አቅጣጫዎችን  በዚሁ አጭር ቀን  ምን ውጤት እንዳመጡ  መገምገም  እንዳለበት  የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።
እንሳሮ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍3
የሆርሙዝ መስመር ተዘግቶባቸው የቆዩ መርከቦች በኦማን የባህር ዳርቻ በኩል ማለፍ መጀመራቸው ተጠቆመ
 
በዓለም-አቀፍ የነዳጅና የጋዝ ማጓጓዣ ዝውውር የላቀ ድርሻ ያለውና በአካባቢው በሰፈነው ውጥረት ሳቢያ ተዘግቶ የቆየው ሆርሙዝ ሰርጥ ከግጭቱ መርገብ ጋር ተያይዞ የመርከቦች እንቅስቃሴ እንደታየበት ከባህር ላይ ትራፊክ መከታተያ መረጃዎችን የጠቀሱ መገናኛ ብዙኃን አስነብበዋል።
 
ባለፉት ጥቂት ቀናት ወደ ወሽመጡ የተጠጉ ስምንት መርከቦች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ጉዟቸውን በማቋረጥ አቅጣጫ ቀይረው መመለሳቸውን ያወሳው የብሉምበርድ ዘገባ፣ ነገሮች ተቀይረው ባለፈው እሑድ ዕለት ብቻ ስድስት ግዙፍ የጭነት መርከቦች በኦማን የባህር ዳርቻ በኩል የተዘረጋውንና ጥበቃ የሚደረግለትን አማራጭ መተላለፊያ ተጠቅመው ማለፋቸውን አስነብቧል።
 
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል መርከቦች የደኅንነት ስጋትን ለመቀነስ በሚል የእንቅስቃሴ ማሳያቸውን አጥፍተው ስለሚጓዙ በወሽመጡ ላይ ያለውን ትክክለኛ የጉዞ ፍሰት ሙሉ በሙሉ ለማወቅ አዳጋች አድርጎታል ሲል የዘገበው አናዱሉ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
በመረጃ እጥረት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ሪፖርት ውስጥ ሳትካተት ቀረች

በቅርቡ የወጣው 10ኛው የአለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ሪፖርት 2026፣ በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ዋስትና ሁኔታ የሚያሳይ የተሟላ መረጃ ባለመገኘቱ ሀገሪቱ በሪፖርቱ ውስጥ ስሟ ሳይካተት መቅረቱን ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ በ2025 ዓ.ም. የሪፖርቱን ጥብቅ የቴክኒክ መስፈርቶች የሚያሟላ መረጃ ባለማቅረቧ፣ መረጃ ካልተካተተባቸው 18 ሀገራት አንዷ ሆናለች።

ይህ የመረጃ እጥረት መረጃ ለመሰብሰብ ፍቃድ ማግኘት በመቸገሩ፣ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ እና ለመረጃ አሰባሰብ ቅድሚያ ባለመሰጠቱ ምክንያት የተከሰተ ሲሆን፤ በሪፖርቱ የተካተቱ ሀገራት ቁጥር መቀነስ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋረጠባቸው ሰዎች ቁጥር በሪፖርቱ ላይ ዝቅ ብሎ እንዲታይ አድርጓል።

የኢትዮጵያ መረጃ ባይኖርም፣ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በአለማችን ትልቁን የምግብ ቀውስ እያስተናገደ መሆኑን የሚጠቁመው ሪፖርቱ፤ በሱዳን 25 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለችግር መዳረጋቸውን እና በኤል ፋሸር እና በካዱግሊ ረሃብ መከሰቱን፣ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን፣ በኬንያ እና በሶማሊያ በግጭት፣ በአየር ንብረት ተጽእኖ እና በምግብ ዋጋ ንረት ምክንያት የምግብ እጥረት ቀውሱ እየተባባሰ መምጣቱን አስታውቋል።

የሰብአዊ ድጋፍ ፋይናንስ ወደ ቀድሞው ዝቅተኛ ደረጃ መውረዱን የገለጸው ሪፖርቱ፣ በአስቸኳይ "የሰብአዊ ድጋፍ ዳግም ማስጀመሪያ" እንደሚያስፈልግ አሳስቦ፤ አስተማማኝ የመረጃ አሰባሰብ ለህይወት አድን ስራዎች ወሳኝ በመሆኑ ኢትዮጵያ የመረጃ ክፍተቷን መሙላት እንዳለባት ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤔64👍3🤯1
በዓለም ላይ ቀዳሚዎቹ የወርቅ አምራቾች ቻይና፣ አውስትራሊያ፣ ሩሲያ፣ ካናዳ እና አሜሪካ ናቸው።

በኩባንያ ደረጃ ደግሞ ከፍተኛውን ምርት የሚያቀርቡት እንደ ኒውሞንት (Newmont Corporation) እና ባሪክ ጎልድ (Barrick Gold) ያሉ ግዙፍ ዓለም አቀፍ የኮርፖሬት ማዕድን ኩባንያዎች ናቸው።

ከፍተኛ ወርቅ አምራች የሆኑት ቻይና፣አውስትራሊያ፣ሩሲያ፣ ካናዳ እና አሜሪካ ሲሆኑ

* ቻይና፦ በዓመት ከ370 ሜትሪክ ቶን በላይ በማምረት የዓለማችን ቀዳሚዋ ወርቅ አምራች አገር ናት።

* አውስትራሊያ፦ በየዓመቱ ከ300 ሜትሪክ ቶን በላይ ወጥ የሆነ ምርት በማውጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

* ሩሲያ፦ በዓመት በግምት ከ300 እስከ 330 ሜትሪክ ቶን በማምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስተኛውን ደረጃ ይዛለች።

* ካናዳ፦ በሰሜን አሜሪካ ዋነኛ አምራች ስትሆን፣ በዓመት ከ170 እስከ 200 ሜትሪክ ቶን ታመርታለች።

* አሜሪካ፦ በዋነኝነት በኔቫዳ ግዛት ከሚገኙ ማዕድናት የሚወጣ ሲሆን፣ በየዓመቱ በግምት ከ170 እስከ 200 ሜትሪክ ቶን ታመርታለች።

የኩባንያዎች ምርት በአብዛኛው በግል ባለሀብቶች እና በመንግሥት በሚተዳደሩ ግዙፍ ተቋማት የሚመራ ነው፦

* ኒውሞንት ኮርፖሬሽን (Newmont Corporation)፦ በአሜሪካ የሚገኘው ይህ ዓለም አቀፍ ኩባንያ በጠቅላላ የምርት መጠን የዓለማችን ትልቁ የወርቅ ማዕድን ኩባንያ ነው።

* ባሪክ ጎልድ (Barrick Gold)፦ በኔቫዳ የሚገኘውን ካርሊን ትሬንድ (Carlin Trend) ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ማዕድናት የሚያስተዳድር ግዙፍ የካናዳ ኩባንያ ነው።

* አግኒኮ ኢግል ማይንስ (Agnico Eagle Mines)፦ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ዕድገት እና በተረጋጋ የሥራ እንቅስቃሴ የሚታወቅ ሌላኛው የካናዳ ኩባንያ ነው።

* ፖሊየስ (Polyus)፦ በሳይቤሪያ የወርቅ ክምችት ላይ ሰፊ ይዞታ ያለው የሩሲያ ትልቁ ወርቅ አምራች ነው።

* ዚጂን ማይኒንግ (Zijin Mining)፦ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርቱን በፍጥነት እያሳደገ የመጣ የቻይና ሁለገብ ኩባንያ ነው።

* ናቮይ ማይኒንግ (NMMC)፦ በኡዝቤኪስታን ውስጥ ግዙፍ የማዕድን ሥራዎችን የሚያከናውን ትልቅ የመንግሥት የኢንዱስትሪ ተቋም ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍3🤩1
በአርሲ ግጭት 8 ሚሊሻ እና ፖሊሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 11 ሰዎች ናቸው የተገደሉት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ‼️

ለግጭቱ ሐይማኖታዊ መልክ ለመሰጠት የተደረገው ሙከራ ተገቢ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ተናግረዋል።

ሽፍቶች በአካባቢው ያለውን ሰላም ለማደብዘዝ ሙከራ እንዳደርጉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና ከተፈናቃዮች ውስጥ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑት መመለሳቸውን አንስተዋል፡፡
የአርሲ ሀገረ ስብከት 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልፆ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡579👍3