አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አመጋገብ ባለሙያዎች እንደሚሉት ለወጣት ቆዳ የሚረዱ 7 ምግቦች

የቆዳችን ጤና እና ውበት በተለያዩ ነገሮች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፣ የምንመገባቸው ምግቦች ግን ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። አመጋገብ ባለሙያዎች ቆዳን ወጣት እና የሚያብረቀርቅ ለማድረግ የሚረዱ 7 ምግቦችን ይመክራሉ።

1. ኤዳማሜ (Edamame)
ኤዳማሜ በመባል የሚታወቀው አረንጓዴ አኩሪ አተር isoflavones የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል። እነዚህም በቆዳ ላይ የሚታዩ መጨማደዶችን እና ድርቀትን ለመቀነስ ይረዳሉ። ቶፉ እና የአኩሪ አተር ወተትም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ይሰጣሉ።

2. ስኳር ድንች
ስኳር ድንች በቫይታሚን ሲ የበለጸገ ሲሆን፣ ይህም ኮላጅን እንዲመረት ይረዳል። ኮላጅን ደግሞ ለቆዳ ጥንካሬ እና ለጤናማነት ወሳኝ ነው። በተጨማሪም በውስጡ ያለው ቤታ ካሮቲን (beta carotene) ቆዳን ከፀሐይ ጨረር ለመከላከል ይረዳል።

3. ቲማቲም
ቲማቲም በፀሐይ መጎዳት ላይ የሚከላከል lycopene የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ ይዟል። ይህም የቆዳ መጨማደድን እና ሽፍታዎችን ለመቀነስ ይረዳል። ቲማቲምን ማሞቅ የ lycopeneን ጥቅም ስለሚጨምር፣ በተጠበሰ ቲማቲም ውስጥ ጥቅሙን በተሻለ ሁኔታ ማግኘት ይቻላል።

4. ብርቱካን ጭማቂ
100% ንጹህ ብርቱካን ጭማቂ በቫይታሚን ሲ የተሞላ ሲሆን፣ ይህም ኮላጅን እንዲመረት በማድረግ ቆዳ ለስላሳ እና ጠንካራ እንዲሆን ይረዳል። እንዲሁም በውስጡ ያለው ከፍተኛ የውሃ መጠን ቆዳን እርጥበትማ ያደርገዋል።

5. ከፊር (Kefir)
ከፊር ለሆድ ጤና ብቻ ሳይሆን ለቆዳም እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህ እርጎ የሚመስል መጠጥ ቆዳ የውሃ ይዘቱን እንዲጠብቅ ይረዳል። ከፊር ውስጥ የሚገኙት ባክቴሪያዎች የቆዳን የተፈጥሮ መከላከያ በመጠበቅ ድርቀትን ይቀንሳሉ።

6. የዱባ ፍሬ (Pumpkin Seeds)
የዱባ ፍሬ ዚንክ የተባለ ማዕድን በውስጡ ይዟል። ዚንክ ደግሞ ቁስል ለመፈወስ እና በቆዳ ላይ የሚፈጠሩ እብጠቶችን ለመቀነስ ወሳኝ ነው። ዚንክ የብጉር ችግርን ለመቀነስም ሊረዳ ይችላል።

7. ሳልሞን (Salmon)
ሳልሞን ለልብ እና ለአእምሮ ጤና ከሚሰጠው ጥቅም በተጨማሪ ለቆዳ ውበትም እጅግ ጠቃሚ ነው። በውስጡ ያሉት Omega-3 fatty acids በቆዳ ላይ የሚከሰት እብጠትን በመቀነስ ቆዳ እርጥበቱን እንዲጠብቅ ይረዳሉ።

ጤናማ እና ወጣት ቆዳ ለመያዝ ውድ ክሬሞች ብቻ ሳይሆኑ የምንመገባቸው ምግቦችም ትልቅ ድርሻ አላቸው። ከላይ የተዘረዘሩትን ምግቦች በአመጋገብዎ ውስጥ በማካተት የቆዳዎን ጤንነት ይጠብቁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍6
መርጌታ ነን ገንዘብህን እናስመልሳለን በማለት ከ8 መቶ ሺህ ብር በላይ ያጭበረበሩ ወንድማማቾች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር በሉማሜ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ስመኝ አባትነህ እና ያዛቸው አባትነህ የተባሉት ወንድማማቾች በአርባ ምንጭ ከተማ በቡና ንግድ ስራ ከተሰማራ ግለሠብ ላይ ከፍተኛ ገንዘብ አጭበርብረው መውሠዳቸውን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሠው እንደገለጹት አካሉ መለሰ የተባለው ተበዳይ ቡና ያስረከበው ደንበኛ ብሩን ሊመልስለት ባለመቻሉ ተጠርጣሪወች የሐሰት ሰነድ በማዘጋጀት መርጌታ ነን ያልተመለሠልህን ገንዘብ እናስመልሳለን በማለት አታለው መውሠዳቸውን ተናግረዋል።

ፖሊስ በተጠርጣሪወች ላይ ክትትል በማድረግ በቁጥጥር ሥር አውሎ የተጭበረበረው ገንዘብ በከተማ አስተዳደሩ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በግዜዊነት ኤግዚቢት ሆኖ እንዲቆይ በማድረግ አጭበርባሪ ግለሠቦች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ  በትኩረት እየሠራ መሆኑን ፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍4🤪4
በስፔን ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች ጥገኝነት መጠየቃቸው ተገለጸ።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ የስደተኞች ጥቅም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጠቃሚ መሆኑን በመረዳት የስደተኞች ፖሊሲያቸውን ክፍት አድርገዋል።

የሶሻሊስት መንግስት መሪው ሳንቼዝ ውሳኔ በቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ነቀፌታ ገጥሞታል ተብሏል።

በስፔን በተለይ በግንባታ ዘርፍ የሰው ሀይልን ለማጠናከር ስደተኞችን መጠቀም የተለመደ መሆኑ ተነግሯል። ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባሉት ወራት ውስጥ ማመልከቻ ያስገቡ ስደተኞች ቁጥር 1 ሚሊዮን 174 ሺሕ 978 መሆናቸው ተመላክቷል።

ከእነዚህ መካከል ከ600 ሺሕ በላይ ጥያቂያቸው መታየት መጀመሩ ተገልጿል።

የስፔን የስደተኞች ቢሮ ዋና ፀሐፊ ፒላር ካንሴላ በማድሪድ በሰጡት መግለጫ ከአመልካቾቹ ውስጥ 67% የሚሆኑት ከላቲን አሜሪካ፣ 22.9 የሚሆኑት ከአፍሪካ የመጡ ስደተኞች ናቸው ብለዋል።

በሀገር ደረጃ ኮሎምቢያ 25.9%፣ ሞሮኮ 12.3%፣ ቬንዙዌላ 11.8% እንድሁም ፔሩ 8.8% ስደተኞች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

አብዛኞቹ አመልካች ስደተኞች ወጣቶች ሲሆኑ፣ በፆታ ደረጃ 57% ወንድ እና 42% ሴቶች ናቸው። ካንሴላ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄዎችን ገምግሞ ውሳኔ ለመስጠት ሶስት ወራት እንደሚፈጅበት አስታውቀዋል። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍5
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍2
የአሜሪካ 250ኛው የነፃነት በዓል በአዲስ አበባ ደምቆ ተከበረ

የአሜሪካ የተመሰረተችበትን 250ኛ ዓመት የነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ፣ በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶችና የአሜሪካ ዜጎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ተላልፏል።

ዕለቱን ልዩ ለማድረግም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ በአሜሪካ ብሔራዊ ባንዲራ ቀለማት (በቀይ፣ ነጭና ሰማያዊ) ደምቆ እንዲታይ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣4012👍5😡4🤷‍♂3🥰1👌1
ከነዳጅ ወደ ኤሌክትሪክ፡ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ አስደናቂ የቴክኖሎጂ ስኬት

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በሀገር ውስጥ የታየ ትልቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማብሰሪያ የሆነ አዲስ የፈጠራ ስኬት ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ ቀደም ሲል በነዳጅ (በቤንዚን) ይንቀሳቀስ የነበረውን 'Sandstorm S24' የተሰኘ የፒክአፕ ተሽከርካሪ ሞዴል ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪነት (EV) የመቀየር ሥራን በስኬት አጠናቋል።

​ይህ አረንጓዴ እና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት በዩኒቨርሲቲው የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ተመራማሪዎች ቡድን በግንባር ቀደምትነት የተመራ ነው።

​ወደ ኤሌክትሪክ የተቀየረው ይህ ተሽከርካሪ በአንድ ጊዜ ሙሉ ቻርጅ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት የመጓዝ ከፍተኛ አቅም አለው።

ከዚህም በላይ አሠራሩ ሙሉ በሙሉ ለአካባቢ ተስማሚ በመሆኑ ምንም ዓይነት የጭስ ልቀት (Zero Emission) የማያስመዘግብና የአየር ብክለትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚከላከል ነው።

​የዚህ ፕሮጀክት ትልቁ ስኬት በኢኮኖሚ ረገድ የሚሰጠው ጥቅም ሲሆን፥ የተሽከርካሪውን የሥራ ማስኬጃ እና የነዳጅ ወጪ በ88 በመቶ ያህል በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ለለውጥ ሥራው የወጣው ጠቅላላ የፕሮጀክት ወጪም ተሽከርካሪው በሚሰጠው አገልግሎትና በሚያስገኘው ቁጠባ አማካኝነት ከ4 እስከ 5 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ መሆን ይችላል።

​ለዚህ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ተመራማሪዎቹ 70 ኪሎዋት የPMSM ኤሌክትሪክ ሞተር እና 65 ኪሎዋት ሰዓት የሊቲየም-አዮን ባትሪ በውስጡ ገጥመዋል።

በተጨማሪም ቀልጣፋ የ3.3 ኪሎዋት AC/DC የቻርጂንግ ሥርዓት እና በሚያዝበት ጊዜ ኃይል የሚቆጥብ የRegenerative Braking ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ ተተግብሮበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍3🫡3🤪1
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከነገ በስቲያ ማክሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት፤ የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የቀጣዩን ዓመት በጀት አስመልክቶ ከተሰናባቾቹ የፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

የፓርላማ አባላቱ ጥያቄዎቻቸውን እንዲያስገቡ ቀነ ገደብ የተሰጣቸው እስካለፈው ሰኞ እኩለ ቀን ድረስ እንደነበር ምንጮቹ ገልጸዋል።

በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚያዝላቸው ፕሮግራም መሰረት የመንግስትን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በዓመት ሁለት ጊዜ ለፓርላማው ማቅረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የፌደራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሪፖርትን ለተወካዮች ምክር ቤት የላኩት ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ላይ ነበር።

በተመሳሳይ መልኩ የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ባለፈው ሳምንት አርብ ለፓርላማ አባላት ደርሷቸዋል።

በ32 ገጽ የተዘጋጀው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ይህ ሪፖርት፤ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ልማት፣ በፍትህ እና አስተዳደር ዘርፎች ያሉ የስራ ክንውኖች በዝርዝር የያዘ ነው።

ሪፖርቱ የሰላምና ደህንነት ግንባታ ስራዎች፣ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈጻጸሞችንም ዳስሷል። የሰባተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጉዳይም በሪፖርቱ በአጭሩ ተካትቷል።

Via Ethiopia Insider

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤪8👍4
ተወዳጇ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

በበርካታ የባህል ሙዚቃ ዜማዎቿ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ድምፃዊቷ ያጋጠማትን የጤና እክል ተከትሎ በሕክምና ስትረዳ ቆይታለች።

ራሔል ዮሐንስ በግሏ እናከተለያዩ ድምፃውያን ጋር በመሆን በርካታ ተወዳጅነት ያገኙ ሙዚቃዎችን ሠርታለች።

በሙዚቃዎቿ ከድምፃዊነቷ ባለፈ፣ በአንዳንዶቹ ላይ በግጥም እና በዜማ ድርሰትም አስተዋፅኦ ታደርግ ነበር።

ራሔል ዮሐንስ ከሠራቻቸው ሙዚቃዎቿ መካከል እንደ "ኢትዮጵያ"፣ "አራዳ"፣ "እንደ ኢየሩሳሌም"፣ "ትዝታ"፣ "አንቺ ባለድሪ"እና "አየር ኃይላችን" የመሳሰሉት ተወዳጅነት አግኝተውላታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14😢9👍3🕊1💔1
ብርቱዎቹ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ እናቶች

እንዚህ እናቶች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተገኙ ተማሪዎች ናቸው፡፡

የእናትነት ኃላፊነትን እየተወጡ በተመሳሳይ ጊዜ የትምህርት ህልማቸውን ለማሳካት ያሳዩት ጥንካሬና ትጋት ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረው ነው። 👏👏

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍13👌1
የኢራን ጠቅላይ መሪ የነበሩት አያቶላህ አሊ ካሜኔይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ከአራት ወራት በኋላ በዛሬው ዕለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢራናውያን በተገኙበት የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈፅሟል።
ይህንን የሽኝት ፕሮግራም ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ሁሉ የኢራን ህዝብ ለካሜኔይ መሰብሰቡ አስደንግጦኛል፣ መሪያቸውን ይጠሉት ነበር የመሰለኝ ያሉ ሲሆን ግን የውሸት እንባ ነው ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2114🤣8🙉6😢4🤷3👍2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ በጀት ያላቸው 48 መሥሪያ ቤቶች ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነጻ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ (eGP) ሥርዓት ብቻ እንዲጠቀሙ ትእዛዝ አስተላለፈ።

ይህ ውሳኔ ከአስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች 22 በመቶውን የሚሸፍን ሲሆን፥ ዓላማውም ሌብነትን መዋጋትና ከ5 እስከ 25 በመቶ የሚሆነውን የግዥ በጀት ማዳን ነው።

እርምጃው ከተማዋ ካጸደቀችው ታሪካዊ የ502 ቢሊዮን ብር በጀት ጋር ይገጣጠማል።

​ይህ አዲሱ ሥርዓት የጉዞና የወረቀት ወጪን በማስቀረት ለሁሉም አቅራቢዎች እኩል ዕድል ይፈጥራል የተባለ ሲሆን  የኢንተርኔት መቆራረጥ እና የሠራተኞች የቴክኖሎጂ እውቀት ማነስ እንደ ስጋት ታይተውበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍6🎉2🤪2🌚1
ተጠንቀቁ

ያስደነግጣል ስልኩ ላይ ለረጅም ሰዓታት አቀርቅሮ በማሳለፉ ፓራላይዝ የሆነው የ19 ዓመት ወጣት

ቻይናዊው የ19 ዓመቱ ሻዮ ዶንግ ለረጅም ሰዓታት ስልኩ ላይ አቀርቅሮ በማሳለፉ የተነሳ በከፊል ፓራላይዝ ሆኗል።

ስልኩ ላይ ማኀበራዊ ሚዲያዎችን በመከታተል ሙሉ ጊዜውን በሚባል ደረጃ ላይ የሚያሳልፈው ወጣቱ  ከጊዜ በኋላ በአንገቱ፣ በእጆቹ እና በእግሮቹ ላይ የመደንዘዝ ስሜት ይሰማው ጀመር።
ነገሮችም እየተባባሱ ሄደው አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ እግሩ መንቀሳቀስ አቅቶት እንደነበር ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ዶክተሮችም በፍጥነት ወደ ቀዶ ጥገና ወስደውት በአከርካሪው ላይ ከፍተኛ የደም መርጋት መኖሩ አረጋገጡ።
ወጣቱ ያለማቋረጥ ስልኩ ላይ አቀርቅሮ ማሳለፉ በአከርካሪው ውስጥ ያለውን የደም ቧንቧ ተሰብሯል። ይህም ደም በውስጡ እንዲረጋ እና በከፊል ሽባ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል ዶክተሮቹ።

እንደ ዕድል ሆኖ ግን፣ ሻዮ ዶንግ አሁን ላይ ቀስ በቀስ እንቅስቃሴን እያደረገ ሲሆን፤ ዶክተሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚድን ያምናሉ።
አንገትን ለረጅም ጊዜ አቀርቅሮ ስልክ ላይ ማሳለፍ የደም ዝውውርን በመዝጋት ራስ ምታትን፣ ማዞርን፣ ድካምን እና መደንዘዝን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።
ሁኔታዎች እየከፉ ሲሄዱ ደግሞ ወደ ስትሮክ ወይም ፓራላይዝ እስከመሆን ሊዳርግም ይችላል ይላሉ

#ቤት_እየዋለ_ወይም / ስልክ #ለሚያበዛ ጓደኛቹ ላኩለት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28👍5
የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ጠዋት ይፋ ይሆናል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ጠዋት ይፋ ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018  የትምህርት ዘመንን  የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ አርሞ ይፋ ማድረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 8 እስከ10  ቀን 2018  ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 199 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍3🙏1
ድንጋይ ሲወረውሩ በነበሩ እናቶች ላይ እርምጃ እንወስዳለን
‹‹በአውቶቡስ ላይ ድንጋይ በወረወሩት እናቶች ላይ እርምጃ እንወስዳለን›› ሲሉ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ተናገሩ፡፡ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ሀይሌ አረጋዊ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የመግለጫቸው ዋነኛ ማጠንጠኛም በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውና መነጋገሪያ የሆነው ቪዲዮ ነው፡፡ በዚህ ቪዲዮ በከተማው ቀበሌ 05 አካባቢ በግዳጅ ታፍነው ወደማሰልጠኛ ጣቢያ የሚወሰዱ ወጣቶችን በያዘው አውቶቡስ ላይ እናቶች በጩኸት ተቃውሞ ከማሰማታቸውም በላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ይታያል፡፡

ከንቲባው በመግለጫቸው ‹‹በከተማው ውስጥ የትግራይን አጀንዳ ለመጥለፍና ለማደናቀፍ የሚሰራ የተደራጀ ሴራ አለ›› ብለዋል፡፡ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ቢኖርም ሁሉም የከተማው ነዋሪ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም በጋራ መስራት እንዳለበት ያሳሰቡት ከንቲባው ነገር ግን አንድነቱን ለመሸርሸር የሚሰሩ አካላት እንዳሉ ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም ትልቁ ማሳያው ሰሞኑን በቀበሌ 05 የተከሰተው ድርጊት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በቀበሌ 05 የተፈጠረውና በማህበራዊ ሚደያ የተሰራጨውን ድርጊት መገምገማቸውን ያስታወቁት ከንቲባው ጨምረውም ‹‹የተፈጠረው ወጣቶችን የማስገደድና ያለማስገደድ ጉዳይ ሳይሆን የፀረ ትግል አካላት የተቀናጀ ተግባር ነው›› ብለዋል፡፡ በዚህ ድርጊት ላይ የተሳተፉት ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀውም ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል፡፡

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡4417🤔4😢3👍2🎉1💔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሱዳን የሚገኘው የህወሓት አርሚ 70 ሰራዊት አባላት ትናንት ሰኔ 28/2018 ዓ. ም ከሱዳን ተነስተው ትናንሽ ጀልባዎችን ​​ተጠቅመው ወደ ተከዜ ወንዝ ሲያመሩ ታይተዋል።
ከፍተኛ የጦር አዛዦችም አብረው ይታያሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር ጋር በመተባበር የህወሓት አርሚ 70 ጦር በሱዳን ጦርነት ውስጥ ስላላቸው ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ ተሳትፎ፣ እያደረጉት ስላለው ድጋፍ ወይም ስለፈጸሟቸው ጥሰቶች ጥብቅ ክትትል በማድረግ በየ6 ወሩ ለኮንግረሱ ሪፖርት እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ማሳለፉ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍4