አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
📢የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት🎯

ነገ እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ 132 ኪ.ቮ ሃይል አስተላላፊ መስመር ሰበታ ወጪ መስመር ላይ የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦                                         

ከንጋቱ 12፡00 እስከ ጠዋቱ 2፡00 ድረስ:-  

👉በልደታ ክፍለ ከተማ ዙሪያ እና በጭድተራ ፊት ለፊት፣መላው የመርካቶ ዙሪያ፣ ፔፕሲ ፋብሪካ፣ የድሮው አትክልት ተራ፣ ኤሊያና ሆቴል፣ ሰባራ ባቡር፣ አዲስ ከተማ ቴሌ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ኮል ሴንተር እና አካባቢው ፣

👉በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ዙሪያ፣ ሰንጋተራ፣ ጥቁር አንበሳ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ የደም ባንክ፣ ፋና ሚዲያ፣  ንብ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት እና ጎላ ሚካኤል ሙሉ፣ በህንፃ ኮሌጅ ዙሪያ፣ ኮካ፣ አብነት፣ መድር-ኃይል፣

👉ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እና ቶሎሳ ሰፈር፣ በልደታ ደሴ ሆቴል ዙሪያ፣ መላው ብስራተ ገብርኤል ዙሪያ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት (Commercial Bank of Ethiopia HQ)፣ ፍልውሃ፣ ዘውዲቱ ሆስፒታል፣

👉ጋንዲ ሆስፒታል፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ አራት ኪሎ (ባሻ ወልዴ፣1080)፣ ቅድስት ማርያም፣ አንድነት ፓርክ፣ መላው የጨርቆስ ዙሪያ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ በልደታ ፀበል ዙሪያ፣ በልደታ ኮንዶሚኒየም ዙሪያ እና አካባቢው ፣ 

👉ኮሜርስ  ኮሌጅ (Commerce)፣ ጥቁር አንበሳ፣ ቴሌ ዳታ ሴንተር፣ አድዋ ዜሮ ዜሮ (Adwa 00)፣ ወዳጅነት ፓርክ እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍62
ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️
በኢትዮጵያ ድንበር ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️

የሱዳን ጦር ኃይል  በደቡብ ምስራቅ ብሉ ናይል (ሰማያዊ አባይ) ግዛት የምትገኘውን እና ከኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ጋር የምታዋስነውን ስልታዊ የድንበር ከተማ ኩርሙክን መልሶ ለመቆጣጠር ከትናንት አንስቶ ሰፊ ማጥቃት መክፈቱን አናዶሉ የጦር ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ይህ ጥቃት የተሰነዘረው ከአማጺው የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና ከሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ጋር ከባድ ውጊያ ከተደረገ በኋላ ነው።

የዜና ጣብያው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉትን የጦር ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የሱዳን ጦር ኃይል እና አጋሮቹ በኩርሙክ ከተማ ዳርቻ በሚገኙት የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) የፊት መስመር ይዞታዎች ላይ ለሰዓታት ከቆየ ውጊያ በኋላ ከባድ ጥቃት ሰንዝረዋል።

ይህ ጥቃት ከተማዋን መልሶ ለመቆጣጠር ያለመ የኦፕሬሽን አካል ሲሆን፣ ከተማዋ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ በRSF እና በሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ጥምረት ቁጥጥር ስር ቆይታለች።

የመጨረሻው ጥቃት የተሰነዘረው በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሚደገፈው የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና አጋር ሚሊሻው የሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) የዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ ኩርሙክን ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ በብሉ ናይል ክልል ውስጥ ለወራት የቆየው ወታደራዊ ዘመቻ በበረታበት ወቅት ነው።

ይህ ሁኔታ ግጭቱ ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ ሊሻገር ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3🕊2
"ጥቆላዬን ስሰራ የቴክኒክ ችግር ገጥሞኝ ነበር" ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ኩዋኩ ቦንሳም

ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ኩዋኩ ቦንሳም ከጥቂት ቀናት በፊት ካቦ ቨርዴ አርጀንቲናን ረትታ ታልፋለች ፤የአርጀንቲናም የአለምዋንጫ ጉዞ ይጠናቀቃል "ታይቶኛል" ሲል ተናግሮ ነበር።

ትናንት ምሽት ታድያ አርጀንቲና ድል ካደረገች በኋላ ትንቢቱ ፉርሽ የሆነበት ይህ ጠንቋይ "ጥቆላዬን ስሰራ የቴክኒክ ችግር ገጥሞኝ ነበር" ሲል ተናግሯል።

ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለትም አይደል...

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣10012👍4🤯2👀1
እንዴት ያለ ድንቅ ምስል ነው?

በአንድ እጇ ልጇን አቅፋ በአንዱ እጇ ድንጋይ ጨብጣ በመወርወር ልጇን፣ ባሏን አልያም ወንድሟን ረብ የለሽ ሞት ከመሞት ለመታደግ የምታጣጥር ድንቅ የትግራይ  እናት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢3212💔9👍3🕊2
መረጃ‼️

ኢትዮጵያ ከብሪክስ ኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ 2 ሺሕ 945 አክሲዮኖችን ለመግዛት ማሠቧ ተሠማ።

የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 100 ሺሕ ዶላር እንደሚኾን ሚንስትሮች ምክር ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመራው የባንኩ የአባልነት ረቂቅ አዋጅ ላይ መመልከቱን ጠቅሶ የዘገበው ዘ ሪፖርተር ነው።

አገሪቱ ከአክሲዮን ድርሻዋ 20 በመቶውን ክፍያ ወዲያውኑ መክፈል የሚጠበቅባት ሲኾን፣ ቀሪውን በ13 ዓመታት ከመንፈቅ ውስጥ በ14 ዙር የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርባት ዘገባው ጠቅሷል።

ኢትዮጵያ የባንኩ አባል ከኾነች፣ ባንኩ በአገሪቱ ውስጥ የንብረት ባለቤት የመኾንና ከታክስ ነጻ የመኾን መብት ይኖረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍5🤣4🤪2
ሚሊዮኖች ኢራናውያን በቴህራን ከተማ

የቀድሞውን የሀገሪቱን ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሚኒን ለመሸኘት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢራናውያን  በቴህራን ከተማ ታድመዋል።

ሀገሪቱ ብሄራዊ የሀዘን ወቅት ላይ በገባችበት በዚህ ወቅት፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የውጭ ሀገራት መሪዎች እንዲሁም ዲፕሎማቶች በተገኙበት የተከናወነው ይህ የቀብር ስነ-ስርዓት በኢራን ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተገኘበት ትልቅ ህዝባዊ ስብስብ ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ ይፋዊ የቀብር ስነ-ስርዓት በተለያዩ ከተሞች የሚቀጥል  ሲሆን፣ በመጨረሻም የአሊ ኻሚኒ አስከሬን በማሽሃድ  ከተማ በሚገኘው የመጨረሻ ማረፊያቸው እንደሚያርፍ ታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍10🤣6
በኃይል ሥልጣን የያዘው የትግራይ ክልል ካቢኔ፣ ለዘንድሮው የ12 ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ለወረቀት ፈተና የተዘጋጁ የክልሉ ተማሪዎች ትምህርት ቢሮው ባላወቀው ምክንያት ከወረቀት ፈተና እንዲገለሉ ተደርጓል ሲል ተቃውሞ አሠማ።

ለወረቀት ፈተና ለተመረጡ ተፈታኞች ያልተዘጋጁበትን የአፈታተን ሥርዓት መተግበር ተቀባይነት የለውም ያለው ካቢኔው፣ ተፈታኞቹ የወረቀት ፈተና እንዳይወስዱ የሚከለክል ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት እንደሌለ ገልጧል።

ካቢኔው፣ የተማሪዎቹን መብት ለማክበር ሁሉንም አማራጮች እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ትምህርት ሚንስቴር ቀደም ሲል በተደረሠው ስምምነት መሠረት ወደ መጀመሪያው የፈተና አሠጣጥ ሥርዓት ካልተመለሠ፣ ተማሪዎቹ ፈተናውን በኮምፒውተር መውሠድ እንደማይጠበቅባቸው ካቢኔው አስታውቋል።

ከክልሉ 29 ሺሕ 755 ተፈታኞች መካከል፣ 15 ሺሕ 349ኙ ለወረቀት ፈተና የተለዩ ናቸው ተብሏል።

የተፈጥሮ ሳይንስ የወረቀት ፈተና በመላ አገሪቱ የሚሠጠው፣ ከሐምሌ 1 እስከ 8 ባሉት ቀናት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20🤪8👍3🤩1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብፅ በዓለም ላይ ትልቁን የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤት ይፋ አደረገች።
ይህ የሀገሪቱ የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ከአሜሪካ ፔንታጎን ይበልጣል።
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው መርቀውታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪22🌚9👍87😎3🤷‍♂1🤯1😱1🤣1👀1🫡1
አመጋገብ ባለሙያዎች እንደሚሉት ለወጣት ቆዳ የሚረዱ 7 ምግቦች

የቆዳችን ጤና እና ውበት በተለያዩ ነገሮች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፣ የምንመገባቸው ምግቦች ግን ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። አመጋገብ ባለሙያዎች ቆዳን ወጣት እና የሚያብረቀርቅ ለማድረግ የሚረዱ 7 ምግቦችን ይመክራሉ።

1. ኤዳማሜ (Edamame)
ኤዳማሜ በመባል የሚታወቀው አረንጓዴ አኩሪ አተር isoflavones የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል። እነዚህም በቆዳ ላይ የሚታዩ መጨማደዶችን እና ድርቀትን ለመቀነስ ይረዳሉ። ቶፉ እና የአኩሪ አተር ወተትም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ይሰጣሉ።

2. ስኳር ድንች
ስኳር ድንች በቫይታሚን ሲ የበለጸገ ሲሆን፣ ይህም ኮላጅን እንዲመረት ይረዳል። ኮላጅን ደግሞ ለቆዳ ጥንካሬ እና ለጤናማነት ወሳኝ ነው። በተጨማሪም በውስጡ ያለው ቤታ ካሮቲን (beta carotene) ቆዳን ከፀሐይ ጨረር ለመከላከል ይረዳል።

3. ቲማቲም
ቲማቲም በፀሐይ መጎዳት ላይ የሚከላከል lycopene የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ ይዟል። ይህም የቆዳ መጨማደድን እና ሽፍታዎችን ለመቀነስ ይረዳል። ቲማቲምን ማሞቅ የ lycopeneን ጥቅም ስለሚጨምር፣ በተጠበሰ ቲማቲም ውስጥ ጥቅሙን በተሻለ ሁኔታ ማግኘት ይቻላል።

4. ብርቱካን ጭማቂ
100% ንጹህ ብርቱካን ጭማቂ በቫይታሚን ሲ የተሞላ ሲሆን፣ ይህም ኮላጅን እንዲመረት በማድረግ ቆዳ ለስላሳ እና ጠንካራ እንዲሆን ይረዳል። እንዲሁም በውስጡ ያለው ከፍተኛ የውሃ መጠን ቆዳን እርጥበትማ ያደርገዋል።

5. ከፊር (Kefir)
ከፊር ለሆድ ጤና ብቻ ሳይሆን ለቆዳም እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህ እርጎ የሚመስል መጠጥ ቆዳ የውሃ ይዘቱን እንዲጠብቅ ይረዳል። ከፊር ውስጥ የሚገኙት ባክቴሪያዎች የቆዳን የተፈጥሮ መከላከያ በመጠበቅ ድርቀትን ይቀንሳሉ።

6. የዱባ ፍሬ (Pumpkin Seeds)
የዱባ ፍሬ ዚንክ የተባለ ማዕድን በውስጡ ይዟል። ዚንክ ደግሞ ቁስል ለመፈወስ እና በቆዳ ላይ የሚፈጠሩ እብጠቶችን ለመቀነስ ወሳኝ ነው። ዚንክ የብጉር ችግርን ለመቀነስም ሊረዳ ይችላል።

7. ሳልሞን (Salmon)
ሳልሞን ለልብ እና ለአእምሮ ጤና ከሚሰጠው ጥቅም በተጨማሪ ለቆዳ ውበትም እጅግ ጠቃሚ ነው። በውስጡ ያሉት Omega-3 fatty acids በቆዳ ላይ የሚከሰት እብጠትን በመቀነስ ቆዳ እርጥበቱን እንዲጠብቅ ይረዳሉ።

ጤናማ እና ወጣት ቆዳ ለመያዝ ውድ ክሬሞች ብቻ ሳይሆኑ የምንመገባቸው ምግቦችም ትልቅ ድርሻ አላቸው። ከላይ የተዘረዘሩትን ምግቦች በአመጋገብዎ ውስጥ በማካተት የቆዳዎን ጤንነት ይጠብቁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍6
መርጌታ ነን ገንዘብህን እናስመልሳለን በማለት ከ8 መቶ ሺህ ብር በላይ ያጭበረበሩ ወንድማማቾች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር በሉማሜ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ስመኝ አባትነህ እና ያዛቸው አባትነህ የተባሉት ወንድማማቾች በአርባ ምንጭ ከተማ በቡና ንግድ ስራ ከተሰማራ ግለሠብ ላይ ከፍተኛ ገንዘብ አጭበርብረው መውሠዳቸውን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሠው እንደገለጹት አካሉ መለሰ የተባለው ተበዳይ ቡና ያስረከበው ደንበኛ ብሩን ሊመልስለት ባለመቻሉ ተጠርጣሪወች የሐሰት ሰነድ በማዘጋጀት መርጌታ ነን ያልተመለሠልህን ገንዘብ እናስመልሳለን በማለት አታለው መውሠዳቸውን ተናግረዋል።

ፖሊስ በተጠርጣሪወች ላይ ክትትል በማድረግ በቁጥጥር ሥር አውሎ የተጭበረበረው ገንዘብ በከተማ አስተዳደሩ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በግዜዊነት ኤግዚቢት ሆኖ እንዲቆይ በማድረግ አጭበርባሪ ግለሠቦች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ  በትኩረት እየሠራ መሆኑን ፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍4🤪4
በስፔን ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች ጥገኝነት መጠየቃቸው ተገለጸ።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ የስደተኞች ጥቅም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጠቃሚ መሆኑን በመረዳት የስደተኞች ፖሊሲያቸውን ክፍት አድርገዋል።

የሶሻሊስት መንግስት መሪው ሳንቼዝ ውሳኔ በቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ነቀፌታ ገጥሞታል ተብሏል።

በስፔን በተለይ በግንባታ ዘርፍ የሰው ሀይልን ለማጠናከር ስደተኞችን መጠቀም የተለመደ መሆኑ ተነግሯል። ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባሉት ወራት ውስጥ ማመልከቻ ያስገቡ ስደተኞች ቁጥር 1 ሚሊዮን 174 ሺሕ 978 መሆናቸው ተመላክቷል።

ከእነዚህ መካከል ከ600 ሺሕ በላይ ጥያቂያቸው መታየት መጀመሩ ተገልጿል።

የስፔን የስደተኞች ቢሮ ዋና ፀሐፊ ፒላር ካንሴላ በማድሪድ በሰጡት መግለጫ ከአመልካቾቹ ውስጥ 67% የሚሆኑት ከላቲን አሜሪካ፣ 22.9 የሚሆኑት ከአፍሪካ የመጡ ስደተኞች ናቸው ብለዋል።

በሀገር ደረጃ ኮሎምቢያ 25.9%፣ ሞሮኮ 12.3%፣ ቬንዙዌላ 11.8% እንድሁም ፔሩ 8.8% ስደተኞች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

አብዛኞቹ አመልካች ስደተኞች ወጣቶች ሲሆኑ፣ በፆታ ደረጃ 57% ወንድ እና 42% ሴቶች ናቸው። ካንሴላ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄዎችን ገምግሞ ውሳኔ ለመስጠት ሶስት ወራት እንደሚፈጅበት አስታውቀዋል። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍5
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍2
የአሜሪካ 250ኛው የነፃነት በዓል በአዲስ አበባ ደምቆ ተከበረ

የአሜሪካ የተመሰረተችበትን 250ኛ ዓመት የነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ፣ በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶችና የአሜሪካ ዜጎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ተላልፏል።

ዕለቱን ልዩ ለማድረግም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ በአሜሪካ ብሔራዊ ባንዲራ ቀለማት (በቀይ፣ ነጭና ሰማያዊ) ደምቆ እንዲታይ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣4012👍5😡4🤷‍♂3🥰1👌1
ከነዳጅ ወደ ኤሌክትሪክ፡ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ አስደናቂ የቴክኖሎጂ ስኬት

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በሀገር ውስጥ የታየ ትልቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማብሰሪያ የሆነ አዲስ የፈጠራ ስኬት ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ ቀደም ሲል በነዳጅ (በቤንዚን) ይንቀሳቀስ የነበረውን 'Sandstorm S24' የተሰኘ የፒክአፕ ተሽከርካሪ ሞዴል ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪነት (EV) የመቀየር ሥራን በስኬት አጠናቋል።

​ይህ አረንጓዴ እና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት በዩኒቨርሲቲው የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ተመራማሪዎች ቡድን በግንባር ቀደምትነት የተመራ ነው።

​ወደ ኤሌክትሪክ የተቀየረው ይህ ተሽከርካሪ በአንድ ጊዜ ሙሉ ቻርጅ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት የመጓዝ ከፍተኛ አቅም አለው።

ከዚህም በላይ አሠራሩ ሙሉ በሙሉ ለአካባቢ ተስማሚ በመሆኑ ምንም ዓይነት የጭስ ልቀት (Zero Emission) የማያስመዘግብና የአየር ብክለትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚከላከል ነው።

​የዚህ ፕሮጀክት ትልቁ ስኬት በኢኮኖሚ ረገድ የሚሰጠው ጥቅም ሲሆን፥ የተሽከርካሪውን የሥራ ማስኬጃ እና የነዳጅ ወጪ በ88 በመቶ ያህል በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ለለውጥ ሥራው የወጣው ጠቅላላ የፕሮጀክት ወጪም ተሽከርካሪው በሚሰጠው አገልግሎትና በሚያስገኘው ቁጠባ አማካኝነት ከ4 እስከ 5 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ መሆን ይችላል።

​ለዚህ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ተመራማሪዎቹ 70 ኪሎዋት የPMSM ኤሌክትሪክ ሞተር እና 65 ኪሎዋት ሰዓት የሊቲየም-አዮን ባትሪ በውስጡ ገጥመዋል።

በተጨማሪም ቀልጣፋ የ3.3 ኪሎዋት AC/DC የቻርጂንግ ሥርዓት እና በሚያዝበት ጊዜ ኃይል የሚቆጥብ የRegenerative Braking ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ ተተግብሮበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍3🫡3🤪1
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከነገ በስቲያ ማክሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት፤ የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የቀጣዩን ዓመት በጀት አስመልክቶ ከተሰናባቾቹ የፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

የፓርላማ አባላቱ ጥያቄዎቻቸውን እንዲያስገቡ ቀነ ገደብ የተሰጣቸው እስካለፈው ሰኞ እኩለ ቀን ድረስ እንደነበር ምንጮቹ ገልጸዋል።

በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚያዝላቸው ፕሮግራም መሰረት የመንግስትን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በዓመት ሁለት ጊዜ ለፓርላማው ማቅረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የፌደራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሪፖርትን ለተወካዮች ምክር ቤት የላኩት ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ላይ ነበር።

በተመሳሳይ መልኩ የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ባለፈው ሳምንት አርብ ለፓርላማ አባላት ደርሷቸዋል።

በ32 ገጽ የተዘጋጀው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ይህ ሪፖርት፤ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ልማት፣ በፍትህ እና አስተዳደር ዘርፎች ያሉ የስራ ክንውኖች በዝርዝር የያዘ ነው።

ሪፖርቱ የሰላምና ደህንነት ግንባታ ስራዎች፣ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈጻጸሞችንም ዳስሷል። የሰባተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጉዳይም በሪፖርቱ በአጭሩ ተካትቷል።

Via Ethiopia Insider

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤪8👍4
ተወዳጇ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

በበርካታ የባህል ሙዚቃ ዜማዎቿ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ድምፃዊቷ ያጋጠማትን የጤና እክል ተከትሎ በሕክምና ስትረዳ ቆይታለች።

ራሔል ዮሐንስ በግሏ እናከተለያዩ ድምፃውያን ጋር በመሆን በርካታ ተወዳጅነት ያገኙ ሙዚቃዎችን ሠርታለች።

በሙዚቃዎቿ ከድምፃዊነቷ ባለፈ፣ በአንዳንዶቹ ላይ በግጥም እና በዜማ ድርሰትም አስተዋፅኦ ታደርግ ነበር።

ራሔል ዮሐንስ ከሠራቻቸው ሙዚቃዎቿ መካከል እንደ "ኢትዮጵያ"፣ "አራዳ"፣ "እንደ ኢየሩሳሌም"፣ "ትዝታ"፣ "አንቺ ባለድሪ"እና "አየር ኃይላችን" የመሳሰሉት ተወዳጅነት አግኝተውላታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14😢9👍3🕊1💔1
ብርቱዎቹ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ እናቶች

እንዚህ እናቶች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተገኙ ተማሪዎች ናቸው፡፡

የእናትነት ኃላፊነትን እየተወጡ በተመሳሳይ ጊዜ የትምህርት ህልማቸውን ለማሳካት ያሳዩት ጥንካሬና ትጋት ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረው ነው። 👏👏

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍13👌1