አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲስ የቡና ጥናት‼️
ቡናን በየቀኑ አብዝቶ መጠጣት ለጉበት ጤንነት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተረጋገጠ።
አዩዘሀበሻ የጥናቱን ውጤት እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።
በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የሲናይ የሕክምና ማዕከል ከቡና ጋር በተያያዘ በተሰራው አዲስ ጥናት ቡናን አብዝቶ መጠቀም ጭምር  ለጉበት ጤንነት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተረጋገጠ።
ቡና የሚሰጠው ጥቅም በውስጡ ከያዘው ካፌይን ሳይሆን በያዘው ከፍተኛ አንቲ-ኦክሲዳንት ነው።
ቡና ከፍተኛ ፀረ-ኦክሳይድ(Antioxidant) ስላለው ተመራማሪዎቹ ቡናን በየቀኑ መጠቀም ዘላቂ የጉበት ጠባሳ፣ ለረጅም ጊዜ የጉበት በሽታዎች ሊከሰት ከሚችለው ጉዳት፣የሰባ የጉበት በሽታ፣ የቫይረስ ሄፓታይተስ፣ ከአልኮል ጋር የተያያዘ የጉበት በሽታ እና ሌሎችንም ጨምሮ ቡና የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቱ አሳይቷል።
ሲርሆሲስ የተባለው የጉበት በሽታ በዓለም ዙሪያ ከ58 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የሚያጠቃ የጉበት በሽታ ሲሆን በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ይገድላል። ሰዎች ቡናን በቀን አምስት ወይም ከዚያ በላይ ኩባያዎች ቢጠጡም እንኳ ዕለታዊ የቡና ኩባያዎ የጉበት በሽታ ወይም የጉበት ካንሰር የመያዝ እድልዎን ሊቀንስ እንደሚችል አዲሱ ጥናት አረጋግጧል።
እነዚህ ተመራማሪዎች 354,000 ናሙናዎችን/ሰዎችን) በመጠቀም ጥናቱን ከአስር አመታት በላይ ተከታትለውታል።
በዚህም የጥናቱ ውጤት ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም በክሊኒካል ጋስትሮኢንተሮሎጂ እና ሄፓቶሎጂ መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን ይህ ጥናት ምናልባት የቡናን ተጽእኖ በተመለከተ "ለረጅም ጊዜ ክትትል የተደረገበት ጥሩ ጥናት ነው” ሲሉ በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የሲዳርስ-ሲናይ የሕክምና ማዕከል የሄፓቶሎጂ ንቅለ ተከላ ባለሙያ የሆኑት የመጀመሪያ የጥናቱ ደራሲ ዶ/ር ህዩንሶክ ኪም ተናግረዋል።
በጥናቱ መሠረት ሄፓቶሴሉላር ካርሲኖማ የተባለው በጣም የተለመደው የጉበት ካንሰር ሲሆን በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 685,000 የሚጠጉ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን ከ597,000 በላይ ሰዎችን በየአመቱ ለሞት ይዳርጋል። ተመራማሪዎቹ ቡናን አብዝቶ መጠጣት የጉበትን ጤንነት ይበልጥ ይጨምራል ብለዋል።
👉በቀን ከአንድ እስከ ሁለት ኩባያ የሚጠጡ  ሰዎች:-
📌ለሲርሆሲስ የመጋለጥ እድላቸው በ 20% ይቀንሳል፣
📌ለጉበት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው በ 24% ይቀንሳል።
📌 በጉበት ምክንያት የመሞት እድልን በ31% ይቀንሳል።
👉በቀን ከሶስት እስከ አራት ኩባያዎች የሚጠጡ ሰዎች ደግሞ በሲርሆሲስ እና የጉበት ካንሰር ተጋላጭነትን በ35% ይቀንሳል፣ ከጉበት ጋር በተያያዘ የመሞት እድልን በ41% ይቀንሳል።
👉አምስት ኩባያዎች ወይም ከዚያ በላይ የሚጠጡ ሰዎች በሲርሆሲስ የመያዝ እድላቸው በ 32% ይቀንሳል፣ በጉበት ካንሰር የመያዝ አደጋን በ47% ይቀንሳል እና ከጉበት ጋር የተያያዘ ሞትን በ 42% እንደሚቀንስ ጥናቱ አረጋግጧል። ነገር ግን ቡናው በሚጠጣበት ጊዜ የስኳር መጠን እና የሚጨመሩ ሌሎች ማጣፈጫዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥናቱ መክሯል። ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍3🤣3
በድሬዳዋ ሐብታቸውን ለመውረስ  አባቱን  የገደለው  ግለሰብ በሞት ፍርድ ተፈረደበት

👉ተባባሪው ደግሞ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

​ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ አንደኛ ተከሳሽ ቤካ ኑረዲን ከአዲስ አበባ በምስጢር መጥቶ ከጓደኛው ሊበን ወንደሰን ጋር በመሆን አባቱን ማሪያም ኮንዶሚኒየም አካባቢ በጭካኔ ገድሏል።

ወንጀለኞቹ ድርጊቱን ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ በግል መኪና ቢሰወሩም፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ባደረገው ረቂቅ ክትትል በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

​የፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ያቀረበውን ጠንካራ የሰውና የሰነድ ማስረጃ የመረመረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ውሳኔውን አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት በዋና ወንጀለኛው ቤካ ላይ የሞት ፍርድ፣ በተባባሪው ሊበን ላይ ደግሞ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👌7👍4🙏3😱2
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የ3 ቢሊዮን ዶላር የቡና ወጪ ንግድ ዕቅዷን ማሳካቷን አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ

በባለፈው በጀት ዓመት 2.65 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን፤ ይህን ቁጥር ዓመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ማሻሻል መቻሉን ግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስታውቀዋል ፡፡

መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የቡናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎች መሠራታቸው በተለይም ለቡና ምርት ጥራት ትኩረት መደረጉ ለዕቅዱ ስኬት ድርሻው ከፍተኛ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣76👍6👌1🤪1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
2👍2
ኡጋንዳ የተዘጋጀ የሥጋ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ መላክ ጀመረች

ሬንቸርስ ፋይነስት (Ranchers Finest Ltd) የተባለው የኡጋንዳ ሥጋ አቀነባባሪ ኩባንያ የመጀመሪያውን ዙር የተዘጋጁ የሥጋ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ መላኩን አብስሯል።

በዚህም በሁለቱ አገራት የአግሮ-ቢዝነስ ዘርፍ አዲስ የንግድ ምዕራፍ መጀመሩ ተመላክቷል።

ይህ ምርት በኢትዮጵያ ለሚገኘው «ዳይመንድ ሆቴል እና ሬስቶራንት ግሩፕ» (Diamond Hotel and Restaurant Group) የሚቀርብ ሲሆን፣ በስምምነቱ መሠረት ኩባንያው በየወሩ 20 ቶን የሚጠጋ የሥጋ ምርት ያቀርባል።

ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩት የሥጋ ምርቶች፦

* የበሬ ሥጋ ቁርጮች (Beef cuts)
* ሶሴጅ (Sausages)
* ስቴክ (Steaks)
* የበግ ሥጋ ምርቶች (Lamb products)

የኡጋንዳ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፤ ይህ ንግድ አገሪቱ ጥሬ የቀጥታ ከብቶችን ከመላክ ወጥታ እሴት የተጨመረባቸውና ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ የተዘጋጁ የሥጋ ምርቶች ላይ ትኩረት ማድረጓን የሚያሳይ ትልቅ ስኬት ነው።

ንግዱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ያጠናክረዋል ተብሏል።

ምርቱ በየወሩ በተከታታይ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ይቀጥላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤔1513🤣7😢6👍3🙈2🥰1👀1🤪1😡1
#አትላንታ የሚገኙ ሐኪሞች ለልብ ሕክምና የሚውሉና ግምታዊ ዋጋቸው 2.6 ሚሊዮን ዶላር የሆኑ የሕክምና ቁሳቁሶችን ወደ ኢትዮጵያ ሊልኩ ነው

በአትላንታ ጆርጂያ የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን፤ ለ200 ታካሚዎች የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚውልና 2.6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የሕክምና ቁሳቁሶችን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ ፎክስ 5 አትላንታ ዘገበ።

ይህ የሕክምና ድጋፍ የሚመራው በትውልደ ኢትዮጵያዊው የፒድሞንት ሆስፒታል (Piedmont Hospital) የልብ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ እና በሞርሃውስ የሕክምና ትምህርት ቤት የምታገለግለው ባለቤታቸው ዶክተር ኦብሰኔት መሪድ ነው። ህክምናው የሚከናወነው «ኅርት አታክ ኢትዮጵያ» በተባለው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅታቸው በኩል መሆኑን የዜና ወኪሉ ጠቁሟል።

ሰባት የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሞች ጨምሮ ከስድስት ሀገራት የተወጣጡ 50 የሕክምና ባለሙያዎች ህክምናውን ለማከናወን ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ ተብሏል።

እንደ ፎክስ 5 አትላንታ ዘገባ፤ ይህ የበጎ አድራጎት ሥራ የተጀመረው ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ በኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩትን አጎታቸውን ኢንተርቬንሽናል ካርዲዮሎጂ ማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት በሞት ካጡ በኋላ ነው። ዶክተር ተስፋዬ ይህ አጋጣሚ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለውን የላቀ የልብ ሕክምና የማግኘት ዕድል ከፍተኛ ልዩነት ያመላክታል ብለዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ይህ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በከፍተኛ ሁኔታ ድጋፉን በማስፋፋት፤ በአሁኑ ወቅት የድርጅቱን የነፃ ሕክምና አገልግሎት ሥራ የሚደግፉ ከ600 በላይ ፈቃደኛ ሠራተኞች እንዳሉት ዘገባው አመልክቷል። ድርጅቱ አሁን ሊሰጥ ያቀደው ሕክምና ለአመስተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሚያከናውነው መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🙏6👍3🥰3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የእናቶች ለቅሶ‼️
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አፈሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ከላይ የሚታው ምስል ለወታደራዊ ስልጠና የታፈሱ ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ሲሳፈሩ የሚያሳይ ሲሆን ከጀርባው ልጆቻቸው የተወሰዱበቸው እናቶች ለቅሶ ይሰማል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢18💔18😡8👍41
መረጃ‼️

ኤርትራ፣ ከእንግዲህ በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ራፖርተር ዙሪያ ከአጋር አገራት ጋር መነጋገር እንደማትፈልግ አስታወቀች።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳለህ ትናንት አሥመራ ውስጥ ለዲፕሎማቶች በሠጡት ገለጻ ይህንኑ የመንግሥታቸውን አቋም በይፋ ለዲፕሎማቶች ነግረዋቸዋል።

በኤርትራ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ የኾነው የልዩ ራፖርተሩ የጊዜ ቆይታ መቀጠሉ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምንጮችን ጨምሮ ዓለማቀፉ ተቋማት በአገሪቱ ጉዳይ ላይ እንዲከፋፈሉና አገሪቱ ስሟ እንዲበላሽ መሳሪያ ኾኖ አገልግሏል በማለት ኦስማን ከሠዋል።

ባሁኑ ወቅት ጀኔቫ ውስጥ ዓመታዊ ጉባዔውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት፣ የልዩ ራፖርተሩን የጊዜ ቆይታ ለማራዘም በቀረበለት ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ሰሞኑን ድምጽ ይሠጣል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8🤣4👍3🤪1
የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ዓለማቀፍ ቅርስ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት፣ "ለታሪክ ግድ የሌላቸውና ችኩል አካላት" ታሪካዊውን የቅዱስ ላሊበላ አካባባቢን ማኅበረሰብ "ከልመና" ተግባር ጋር በማያያዝ ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ተነቀሳቃሽ ምስል አጋርተዋል ሲል ከሠሠ።

ቤት ለቤት እየዞሩ በዘፈን መልክ በልመና ለሚተዳደሩ "አባ ውዴ" ወይም "ሃሚና" ለተባሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የቅዱስ ላሊበላን ስም መስጠት "አሳፋሪ"፣ "የድንቁርና" እና "የታሪክ ፍልሠትን" የሚያስከትል ድርጊት ነው ሲል ጽሐፈት ቤቱ ወቅሷል።

ይህ ድርጊት በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል መኾኑ ሊታወቅ ይገባል ያለው ጽሕፈት ቤቱ፣ አርቲስቶችና አዝማሪዎች ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ የስፍራውን ስም ካልዋለበት በማዋል የታሪክ መዛባት ለመፍጠር እየሞከሩ ይገኛሉ ሲል ወቅሷል።

ጽሕፈት ቤቱ፣ በልመና የተሠማሩ ወገኖች ከላሊበላ አካባቢ ሕዝብ ባሕልና ስነ ልቦና ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም ብሏል።

በስም ማጥፋት ላይ የተሠማሩ አካላት ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ለስም ማጠልሸት ድርጊታቸው ይቅርታ እንዲጠይቁ ጽሕፈት ቤቱ ጠይቋል።

Via : ዋዜማ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍169🙏1👌1
እነሆ የልብ ጤናችሁን ለመጠበቅ ቁልፍ የሆኑ ምክሮች

የልብና የደም ሥር በሽታዎች በዓለም የሞት ዋና ምክንያቶች መካከል ቢሆኑም፣ በአንድነት ይህን መቀየር እንችላለን!

🔹 እንቅስቃሴ ያድርጉ፡ በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ መካከለኛ የሆነ እንቅስቃሴ ያድርጉ። መራመድ፣ ብስክሌት መንዳት ወይም በመደነስ መዝናናት የሚረዱ ናቸው።

🔹 ጤናማ ምግብ ይመገቡ፡ ብዙ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እህል እና ቀላል ፕሮቲኖችን በምግቦቻቹ ጨምሩ። ስብ፣ ስኳርና ጨውን ያስወግዱ።

🔹 ጭንቀትን ያስቀንሱ፡  ሜዲቴሽን፣ ዮጋ፣ ወይም ጥልቅ እስትንፋስ በመውሰድ ጭንቀትን ቀንሱ እና ልብን ጤናማ ያድርጉ።

🔹 ማጨስ ማቆም፡ ትምባሆን ማጨስ ማቆም በልብ በሽታ የመያዝ እድልን እጅግ ይቀንሳል።

🔹 መደበኛ ምርመራ ያድርጉ፡ የደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል መጠን እና አጠቃላይ የልብ ጤና በመደበኛ ምርመራ በማድረግ ጤናዎን ይከታተሉ።

🔹 በቂ ውሃ ይጠጡ፡  በስኳር የተሞሉ መጠጦችን ያስወግዱ። ይህ የሰውነት ተመጣጣኝ ክብደትን ለመጠበቅ ይረዳል።

እነዚህን ልምዶች በመከተል እና በጤና ጉዞአችን እርስ በርስ በመደጋገፍ እንትጋ።

አስታውሱ፤ ለጤናማ ነገ ዛሬ ልብዎን ይንከባከቡ !

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍8
ሲሚንቶ‼️
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውና በጠቅላይ ሚንስትሩ ተመርቆ ስራ ከጀመረ አመታትን ያስቆጠረው የመንግስት እና የግል ሽርክና የሆነው ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደላሎች እየተፈተነ ይገኛል።

ከወራት በፊት ከ1200-1500 ብር ይሸጥ የነበረው ይህ ሲሚንቶ አሁን ላይ ዋጋው በእጥፍ ጨምሮ ደብረብርሃን ከተማ ላይ እስከ 2500 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

ፋብሪካው እየተቋቋመበት ቦታ ለሚ ላይ 1900 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

የሲሚንቶ አስመጪዎች እና ነጋዴዎች አሁን ከፋብሪካው ሲሚንቶ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን እና በደላላ መሆኑን ገልፀውልናል።

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ ከጀመረ ጀምሮ የሀገሪቱን የሲሚንቶ እጥረት በመቅረፍ እና ገበያውን በማረጋጋት እረገድ አስተዋጽኦው የጎላ ቢሆንም አሁን በደላሎች እየተፈተነ በመሆኑን የሚመለከተው አካል መፍትሔ ቢሰጥበት መልካም ነው።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28👍8
በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የትንባሆ መሸጫ ክልከላ ርቀት ወደ 500 ሜትር ከፍ ተደረገ
 
የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የትንባሆ ምርቶች መሸጫ ክልከላ ርቀት ወደ 500 ሜትር ከፍ መደረጉን አስታውቋል፡፡ እርምጃው ህፃናትና ወጣቶችን ከትንባሆ ጭስና ሱስ አደጋ ለመከላከል እንዲሁም በትምህርት ቤቶች አካባቢ ጤናማ እና ንፁህ አካባቢ ለመፍጠር የተወሰደ የጤና ጥበቃ ፖሊሲ መሆኑ ተጠቅሷል።

አዲሱ ደንብ የትንባሆ ምርቶች በትምህርት ቤቶች በቅርብ ርቀት ላይ እንዳይገኙ በማድረግ የህፃናት መጋለጥን ለመቀነስ ያለመ ሲሆን  እርምጃው በተለይም በተማሪዎች ዘንድ የትንባሆ ምርት መዳረሻን ለመገደብ እና የሱስ መጀመሪያ ዕድሜን ለመቀነስ የሚያግዝ መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም በተካሄደ ሰፊ የቁጥጥር ዘመቻ 1.3 ሚሊዮን ሕገወጥ ሲጋራዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል። ይህ እርምጃ በገበያ ውስጥ የሚሰራጩ ሕገወጥ የትንባሆ ምርቶችን ለመቆጣጠር የተደረገ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ አካል ነው ተብሏል፡፡
 
በደንቡ መሠረት ትንባሆን የተከለከሉ ቦታዎች ላይ ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ እስከ 6 ወር ቀላል እስራት ወይም እስከ 5,000 ብር  የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተጠቁሟል።

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉ እመቤት ታደሰ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት
ይህ የቁጥጥር እርምጃ በከተማ አስተዳደሩ የጤና ፖሊሲ አቅጣጫ መሠረት በተደረገ ውሳኔ መተግበሩን አስረድተዋል።

ህብረተሰቡ የትንባሆ ቁጥጥር ሕጎችን በማክበር ከጭስ ነፃ፣ ንፁህና ጤናማ የከተማ አካባቢ ለመፍጠር ከመንግስት አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍4
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍21
የባሕር በር ለማግኘት በሚደረገው ጉዞ የጦር መኮንኖች ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችኋል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ‼️
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት በምታደርገው ጉዞ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችኋል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በስትራቴጂና ደኅንነት ጥናት ዘርፍ የላቀ ብቃት ያላቸውን 42 ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና ከሲቪል ደኅንነት ተቋማት የተውጣጡ መሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጉዞ ፈታኝ መስመሮችን ማለፍ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ተመራቂዎች ወደ ስራ ስትሰማሩ በትምህርት ቆይታችሁ የቀሰማችሁትን እውቀትና ክህሎት በተግባር ከሚገጥሟችሁ ሁኔታዎች ጋር በማዛመድ ለውጡ በግልፅ የሚታይ የአመራር ስራ መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ተደምጠዋል።

ሰራዊቱ ወሳኝ የዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህ ሂደት የላቀ አስተዋፅኦ ለማበርከት በከፍተኛ ተነሳሽነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍8🥱8🤪1
100 ኢትዮጵያውያን ነፃ የውጭ የትምህርት ዕድል ማግኘታቸውን የእስራኤል ኤምባሲ ገለጸ

የኢትዮጵያና እስራኤል የትብብር መስኮች ውስጥ አንዱ በሆነው የትምህርት ዕድል፣ በዚህ ዓመት 100 ተማሪዎች በመንግስት ለመንግስት በሚደረገው ግንኙነት ወደ እስራኤል ለትምህርት ማቅናታቸውን የእስራኤል ኤምባሲ ለአሐዱ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ፤ ተማሪዎቹ በተለያየ መስክ ሙያ ሰልጥነውና ልምድን ቀስመው የሚመለሱባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህም መካከል በመንግስት ለመንግስት በሚደረገው ግንኙነት፣ በእስራኤል የውጭ ግንኙነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚሰጠው የትምህርት ዕድል አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በግብርና፣ ቴክኖሎጂ፣ ህክምና እንዲሁም በሰላምና ፀጥታ ዘርፎች የረጅም እና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደሩ፤ ስልጠናው የሴቶች የአመራር ክህሎት እና የህፃናት ዕድገትንም የሚያካትት መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በግሉ ዘርፍ በሚደረግ ግንኙነት ባለሙያዎችን በተለያየ መንገድ በማሰልጠን ወደ ስራ የሚያስገቡበት ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል። ለአብነትም "Save a Child's Heart" የተባለው ድርጅት በእስራኤል ሀገር ለአምስት ዓመታት ለአምስት የህክምና ባለሙያዎች የትምህርት ዕድል በመስጠት፣ አሁን ላይ በኢትዮጵያ በስፔሻሊስትነት ደረጃ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍6🤣5
📢የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት🎯

ነገ እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ 132 ኪ.ቮ ሃይል አስተላላፊ መስመር ሰበታ ወጪ መስመር ላይ የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦                                         

ከንጋቱ 12፡00 እስከ ጠዋቱ 2፡00 ድረስ:-  

👉በልደታ ክፍለ ከተማ ዙሪያ እና በጭድተራ ፊት ለፊት፣መላው የመርካቶ ዙሪያ፣ ፔፕሲ ፋብሪካ፣ የድሮው አትክልት ተራ፣ ኤሊያና ሆቴል፣ ሰባራ ባቡር፣ አዲስ ከተማ ቴሌ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ኮል ሴንተር እና አካባቢው ፣

👉በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ዙሪያ፣ ሰንጋተራ፣ ጥቁር አንበሳ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ የደም ባንክ፣ ፋና ሚዲያ፣  ንብ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት እና ጎላ ሚካኤል ሙሉ፣ በህንፃ ኮሌጅ ዙሪያ፣ ኮካ፣ አብነት፣ መድር-ኃይል፣

👉ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እና ቶሎሳ ሰፈር፣ በልደታ ደሴ ሆቴል ዙሪያ፣ መላው ብስራተ ገብርኤል ዙሪያ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት (Commercial Bank of Ethiopia HQ)፣ ፍልውሃ፣ ዘውዲቱ ሆስፒታል፣

👉ጋንዲ ሆስፒታል፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ አራት ኪሎ (ባሻ ወልዴ፣1080)፣ ቅድስት ማርያም፣ አንድነት ፓርክ፣ መላው የጨርቆስ ዙሪያ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ በልደታ ፀበል ዙሪያ፣ በልደታ ኮንዶሚኒየም ዙሪያ እና አካባቢው ፣ 

👉ኮሜርስ  ኮሌጅ (Commerce)፣ ጥቁር አንበሳ፣ ቴሌ ዳታ ሴንተር፣ አድዋ ዜሮ ዜሮ (Adwa 00)፣ ወዳጅነት ፓርክ እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍62
ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️
በኢትዮጵያ ድንበር ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️

የሱዳን ጦር ኃይል  በደቡብ ምስራቅ ብሉ ናይል (ሰማያዊ አባይ) ግዛት የምትገኘውን እና ከኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ጋር የምታዋስነውን ስልታዊ የድንበር ከተማ ኩርሙክን መልሶ ለመቆጣጠር ከትናንት አንስቶ ሰፊ ማጥቃት መክፈቱን አናዶሉ የጦር ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ይህ ጥቃት የተሰነዘረው ከአማጺው የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና ከሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ጋር ከባድ ውጊያ ከተደረገ በኋላ ነው።

የዜና ጣብያው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉትን የጦር ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የሱዳን ጦር ኃይል እና አጋሮቹ በኩርሙክ ከተማ ዳርቻ በሚገኙት የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) የፊት መስመር ይዞታዎች ላይ ለሰዓታት ከቆየ ውጊያ በኋላ ከባድ ጥቃት ሰንዝረዋል።

ይህ ጥቃት ከተማዋን መልሶ ለመቆጣጠር ያለመ የኦፕሬሽን አካል ሲሆን፣ ከተማዋ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ በRSF እና በሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ጥምረት ቁጥጥር ስር ቆይታለች።

የመጨረሻው ጥቃት የተሰነዘረው በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሚደገፈው የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና አጋር ሚሊሻው የሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) የዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ ኩርሙክን ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ በብሉ ናይል ክልል ውስጥ ለወራት የቆየው ወታደራዊ ዘመቻ በበረታበት ወቅት ነው።

ይህ ሁኔታ ግጭቱ ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ ሊሻገር ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3🕊2
"ጥቆላዬን ስሰራ የቴክኒክ ችግር ገጥሞኝ ነበር" ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ኩዋኩ ቦንሳም

ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ኩዋኩ ቦንሳም ከጥቂት ቀናት በፊት ካቦ ቨርዴ አርጀንቲናን ረትታ ታልፋለች ፤የአርጀንቲናም የአለምዋንጫ ጉዞ ይጠናቀቃል "ታይቶኛል" ሲል ተናግሮ ነበር።

ትናንት ምሽት ታድያ አርጀንቲና ድል ካደረገች በኋላ ትንቢቱ ፉርሽ የሆነበት ይህ ጠንቋይ "ጥቆላዬን ስሰራ የቴክኒክ ችግር ገጥሞኝ ነበር" ሲል ተናግሯል።

ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለትም አይደል...

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣10012👍4🤯2👀1
እንዴት ያለ ድንቅ ምስል ነው?

በአንድ እጇ ልጇን አቅፋ በአንዱ እጇ ድንጋይ ጨብጣ በመወርወር ልጇን፣ ባሏን አልያም ወንድሟን ረብ የለሽ ሞት ከመሞት ለመታደግ የምታጣጥር ድንቅ የትግራይ  እናት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢3212💔9👍3🕊2
መረጃ‼️

ኢትዮጵያ ከብሪክስ ኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ 2 ሺሕ 945 አክሲዮኖችን ለመግዛት ማሠቧ ተሠማ።

የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 100 ሺሕ ዶላር እንደሚኾን ሚንስትሮች ምክር ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመራው የባንኩ የአባልነት ረቂቅ አዋጅ ላይ መመልከቱን ጠቅሶ የዘገበው ዘ ሪፖርተር ነው።

አገሪቱ ከአክሲዮን ድርሻዋ 20 በመቶውን ክፍያ ወዲያውኑ መክፈል የሚጠበቅባት ሲኾን፣ ቀሪውን በ13 ዓመታት ከመንፈቅ ውስጥ በ14 ዙር የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርባት ዘገባው ጠቅሷል።

ኢትዮጵያ የባንኩ አባል ከኾነች፣ ባንኩ በአገሪቱ ውስጥ የንብረት ባለቤት የመኾንና ከታክስ ነጻ የመኾን መብት ይኖረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍5🤣4🤪2