አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
414 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በመስረቅ ያከማቸ ግለሰብ በ6 ዓመት እስራት ተቀጣ

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመስረቅ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በ6 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት አሰታውቋል፡፡

ግለሰቡ ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ አልሙኒየሞችና መዳቦች በመስረቅ ባሳለፍነው መጋቢት ወር መጨረሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ያሰታወሰው አግልግሎቱ፤ በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ባደረገው ክርክር በግለሰቡ ላይ የ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲወሰን ማደረግ መቻሉን ለጣቢያችን የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተያያዘም በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ኬብሮን መድኃኒት ቤት አካባቢ በግንባታ ላይ ከሚገኝ ህንፃ ላይ የወደቀ ህንፃ መወጣጫ ዊንች በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብልና በትራንስፎርመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የገለጸው አገልግሎቱ፤ ተቋሙ ጉዳት የደረሰበትን የኤሌክትሪክ ኬብልና ትራንስፎርመር በመተካት ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከ1 ሚሊየን 9 መቶ ሺሕ ብር በላይ እንዲከፍል በፍርድ ቤት ስለመወሰኑ ገልጿል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍3
ትምህርት መስከረም 5 ይጀመራል!

የትምህርት ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ ወጥነት ያለው የማስተማር ሂደት እንዲኖር ለማስቻል ያዘጋጀውን የ2019 ዓ.ም አጠቃላይ የትምህርት ዘመን ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ (ካላንደር) ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች አስተላልፏል።

​በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፦

- ከነሐሴ 26 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይከናወናል።

- መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ትምህርት ይጀምራል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍8🤔4👌1
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አፈሳ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ምክንያት ይህንን ድርጊት በመቃወም በዛሬው ዕለት መቀሌን ጨምሮ በአዲጉደምና በሌሎች ከተሞች ከሰዎች እንቅስቃሴ ታቃበው ውለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍7🤣5😢3💔3
መረጃ‼️

የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ባለሥልጣን፣ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ያለ ሕጋዊ ፍቃድ አንዳንድ የሕክምና መሳሪያዎችን የማስተዋወቅ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ሲል ከሠሠ።

ባለሥልጣኑ ዩትዩብንና ቲክቶክን ጨምሮ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ሕጋዊ ማረጋገጫ እና ፍቃድ ያልተሠጠባቸውን የሕክምና መሳሪያዎች ያስተዋወቁ አካላት ማስታወቂያዎቹን ባስቸኳይ እንዲያነሱ አሳስቧል።

አንዳንድ የሕክምና መሳሪያዎች ለሕዝብ በማስታወቂያ መልክ እንዳይቀርቡ በሕግ የተከለከሉ ናቸው ያለው ባለስልጣኑ፣ ማሳሰቢያውን በመጣስ ያለ ሕጋዊ ፍቃድ የሕክምና መሳሪያዎችን ማስተዋወቅ በሚቀጥሉ አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍2
አማራ ባንክ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ አስመዘገበ

ባንኩ ያስመዘገበው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ከ3 እጥፍ በላይ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍8🥰1👌1
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በአምስተኛው የኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ማጠናቀቂያ ለኢትዮጵያ የ464 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የብድር ክፍያ ፈቀደ

ይህም አጠቃላይ የገንዘብ ድጋፉን 2.647 ቢሊዮን ዶላር አድርሶታል።

ድርጅቱ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የተመዘገቡትን የወጪ ንግድ እና የታክስ ገቢ እድገቶች ያደነቀ ቢሆንም፣ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መናር ያሳደረውን ጫና ለመቋቋም 200 ሚሊዮን ዶላር ቀድሞ እንዲለቀቅ ማድረጉን ገልጿል።

​በተጨማሪም IMF ሁለተኛ ዙር የዋጋ ንረት ከተከሰተ ብሔራዊ ባንክ ፖሊሲውን ይበልጥ ሊያጠብቅ እንደሚገባ አሳስቧል።

ባንኩ በወርቅ ግብይት ላይ ያለውን ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲያቆም፣ ድጎማዎች ሲነሱ ተጋላጭ ወገኖች እንዲጠበቁ፣ እና አዳዲስ ገለልተኛ የቦርድ አባላትን በመሾም የባንኩን ገለልተኝነት እንዲያጠናክር መክሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢115🤪4👍2
🚨 እስራኤል የኢራንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤውን ለመግደል አቅዳ ነበር" — ኒው ዮርክ ታይምስ

አሜሪካ ከኢራን ጋር እጅግ ስሱ የሆኑ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮችን በምታደርግበት ወቅት፣ እስራኤል የኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺን እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሀመድ ባቄር ቃሊባፍን  ለመግደል አቅዳ እንደነበር የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

እንዲህ ዓይነቱ የደህንነት እርምጃ የተጀመረውን የዲፕሎማሲ ሂደት ሙሉ በሙሉ ያከሽፈዋል በሚል የሰጉት የአሜሪካ ባለስልጣናት፣ ለሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጥቃት ሊሰነዘርባቸው እንደሚችል ለኢራን ሚስጥራዊ ማስጠንቀቂያ እንዲያስተላልፉ በርካታ የቀጠናውን ሀገራት ጠይቀው ነበር። በተጨማሪም ዋሽንግተን ድርድሩ በሚካሄድበት ወቅት እንዲህ ዓይነቱን ጥቃት እንዳትፈጽም እስራኤልን አጥብቃ አሳስባለች።

እስራኤል አራግቺን እና ቃሊባፍን በግድያ ኢላማ ስም ዝርዝሯ  ውስጥ አስገብታቸው የነበረ ቢሆንም፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ውይይት ሲጀመር ግን ለጊዜው ከዝርዝሩ አንስታቸው ነበር። የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳሉት፣ ሁለቱ ግለሰቦች በንቁ ጦርነት ወቅት እንደ ህጋዊ ወታደራዊ ኢላማ ሊቆጠሩ የሚችሉ ቢሆንም፣ የሰላም ንግግሩ ባለፈው ሚያዝያ  ከተጀመረ በኋላ ግን እነሱን መግደል ውይይቱን ሙሉ በሙሉ የሚያስቆምና ጦርነቱን በድጋሚ የሚቀሰቅስ ይሆን ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🥱3👍2🥰2🤣1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍2
ኦሮሚያ ክልል የመዋቅር ለውጥ ሊያደርግ ነው

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከዚህ ቀደም በቢሮ ደረጃ የነበሩ መዋቅሮችን በኮሚሽን፣ በኢንስቲትዩት፣ በባለሥልጣን፣ በአገልግሎት ዘርፍ እንዲሁም 5 ተቋማትን በልዩ ሁኔታ ለማደራጀት ረቂቅ ሰነድ ማዘጋጀቱ ተነግሯል።

በዚህም መሠረት:-
📌 የፐብሊክ ሰርቪስና ማረሚያ ቤቶች በኮሚሽን ደረጃ፤ የቁጥጥር፣ የኮንስትራክሽንና የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በባለሥልጣን ደረጃ እንዲዋቀሩ ተወስኗል።

📌 የመንግሥት ኮሙኒኬሽንና የሰነዶች ምዝገባን ጨምሮ 4 መሥሪያ ቤቶች በአገልግሎት ደረጃ፣ እንዲሁም የእርሻና የኦሮሞ ባህል ጥናትና ምርምርን ጨምሮ 4 መሥሪያ ቤቶች በኢንስቲትዩት ደረጃ ተደራጅተዋል።

📌የክልሉ ዩኒቨርሲቲዎች አስተዳደር፣ ኦቢኤን፣ ቡሳ ጎኖፋ፣ ፖሊስና ሉዓላዊ ፈንድ ደግሞ በልዩ ሁኔታ የተዋቀሩ ተቋማት ሆነዋል።

📌በትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና እና ገቢዎች ቢሮዎች የሚመሩ 21 ዋና ዋና ቢሮዎች ባሉበት የሚቀጥሉ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ መሥሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች ግን በእነዚህ ዋና ቢሮዎች ሥር ተጠቃለው እንዲተዳደሩ በረቂቁ ተመልክቷል ሰል ዋዜማ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🤣7👍5🤪1
አዲስ የቡና ጥናት‼️
ቡናን በየቀኑ አብዝቶ መጠጣት ለጉበት ጤንነት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተረጋገጠ።
አዩዘሀበሻ የጥናቱን ውጤት እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።
በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የሲናይ የሕክምና ማዕከል ከቡና ጋር በተያያዘ በተሰራው አዲስ ጥናት ቡናን አብዝቶ መጠቀም ጭምር  ለጉበት ጤንነት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተረጋገጠ።
ቡና የሚሰጠው ጥቅም በውስጡ ከያዘው ካፌይን ሳይሆን በያዘው ከፍተኛ አንቲ-ኦክሲዳንት ነው።
ቡና ከፍተኛ ፀረ-ኦክሳይድ(Antioxidant) ስላለው ተመራማሪዎቹ ቡናን በየቀኑ መጠቀም ዘላቂ የጉበት ጠባሳ፣ ለረጅም ጊዜ የጉበት በሽታዎች ሊከሰት ከሚችለው ጉዳት፣የሰባ የጉበት በሽታ፣ የቫይረስ ሄፓታይተስ፣ ከአልኮል ጋር የተያያዘ የጉበት በሽታ እና ሌሎችንም ጨምሮ ቡና የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቱ አሳይቷል።
ሲርሆሲስ የተባለው የጉበት በሽታ በዓለም ዙሪያ ከ58 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የሚያጠቃ የጉበት በሽታ ሲሆን በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ይገድላል። ሰዎች ቡናን በቀን አምስት ወይም ከዚያ በላይ ኩባያዎች ቢጠጡም እንኳ ዕለታዊ የቡና ኩባያዎ የጉበት በሽታ ወይም የጉበት ካንሰር የመያዝ እድልዎን ሊቀንስ እንደሚችል አዲሱ ጥናት አረጋግጧል።
እነዚህ ተመራማሪዎች 354,000 ናሙናዎችን/ሰዎችን) በመጠቀም ጥናቱን ከአስር አመታት በላይ ተከታትለውታል።
በዚህም የጥናቱ ውጤት ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም በክሊኒካል ጋስትሮኢንተሮሎጂ እና ሄፓቶሎጂ መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን ይህ ጥናት ምናልባት የቡናን ተጽእኖ በተመለከተ "ለረጅም ጊዜ ክትትል የተደረገበት ጥሩ ጥናት ነው” ሲሉ በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የሲዳርስ-ሲናይ የሕክምና ማዕከል የሄፓቶሎጂ ንቅለ ተከላ ባለሙያ የሆኑት የመጀመሪያ የጥናቱ ደራሲ ዶ/ር ህዩንሶክ ኪም ተናግረዋል።
በጥናቱ መሠረት ሄፓቶሴሉላር ካርሲኖማ የተባለው በጣም የተለመደው የጉበት ካንሰር ሲሆን በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 685,000 የሚጠጉ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን ከ597,000 በላይ ሰዎችን በየአመቱ ለሞት ይዳርጋል። ተመራማሪዎቹ ቡናን አብዝቶ መጠጣት የጉበትን ጤንነት ይበልጥ ይጨምራል ብለዋል።
👉በቀን ከአንድ እስከ ሁለት ኩባያ የሚጠጡ  ሰዎች:-
📌ለሲርሆሲስ የመጋለጥ እድላቸው በ 20% ይቀንሳል፣
📌ለጉበት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው በ 24% ይቀንሳል።
📌 በጉበት ምክንያት የመሞት እድልን በ31% ይቀንሳል።
👉በቀን ከሶስት እስከ አራት ኩባያዎች የሚጠጡ ሰዎች ደግሞ በሲርሆሲስ እና የጉበት ካንሰር ተጋላጭነትን በ35% ይቀንሳል፣ ከጉበት ጋር በተያያዘ የመሞት እድልን በ41% ይቀንሳል።
👉አምስት ኩባያዎች ወይም ከዚያ በላይ የሚጠጡ ሰዎች በሲርሆሲስ የመያዝ እድላቸው በ 32% ይቀንሳል፣ በጉበት ካንሰር የመያዝ አደጋን በ47% ይቀንሳል እና ከጉበት ጋር የተያያዘ ሞትን በ 42% እንደሚቀንስ ጥናቱ አረጋግጧል። ነገር ግን ቡናው በሚጠጣበት ጊዜ የስኳር መጠን እና የሚጨመሩ ሌሎች ማጣፈጫዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥናቱ መክሯል። ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍3🤣3
በድሬዳዋ ሐብታቸውን ለመውረስ  አባቱን  የገደለው  ግለሰብ በሞት ፍርድ ተፈረደበት

👉ተባባሪው ደግሞ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

​ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ አንደኛ ተከሳሽ ቤካ ኑረዲን ከአዲስ አበባ በምስጢር መጥቶ ከጓደኛው ሊበን ወንደሰን ጋር በመሆን አባቱን ማሪያም ኮንዶሚኒየም አካባቢ በጭካኔ ገድሏል።

ወንጀለኞቹ ድርጊቱን ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ በግል መኪና ቢሰወሩም፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ባደረገው ረቂቅ ክትትል በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

​የፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ያቀረበውን ጠንካራ የሰውና የሰነድ ማስረጃ የመረመረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ውሳኔውን አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት በዋና ወንጀለኛው ቤካ ላይ የሞት ፍርድ፣ በተባባሪው ሊበን ላይ ደግሞ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👌7👍4🙏3😱2
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የ3 ቢሊዮን ዶላር የቡና ወጪ ንግድ ዕቅዷን ማሳካቷን አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ

በባለፈው በጀት ዓመት 2.65 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን፤ ይህን ቁጥር ዓመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ማሻሻል መቻሉን ግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስታውቀዋል ፡፡

መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የቡናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎች መሠራታቸው በተለይም ለቡና ምርት ጥራት ትኩረት መደረጉ ለዕቅዱ ስኬት ድርሻው ከፍተኛ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣76👍6👌1🤪1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
2👍2