በቻይና የሙቀትን ለመቋቋም የዘረጋችው የውሃ ማፍሰስ ቴክኖሎጂ መነጋገሪያ ሆኗል!
በአውሮፓና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አስከፊ የሙቀት ማዕበል በተከሰተበት በዚህ ወቅት፣ በቻይና የመኖሪያ መንደሮች ውስጥ የተዘረጉ አስደናቂ ከቤት ውጪ ማቀዝቀዣ ሥርዓቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የብዙዎችን ቀልብ እየሳቡ ይገኛሉ።
በተለይም ሰፊ የመኖሪያ ሕንፃዎች ግቢዎችን፣ መናፈሻዎችንና የእግር መንገድ ቦታዎችን ለማቀዝቀዝ የተዘረጉት የውሃ ማፍሰስ ሥርዓቶች ትልቅ መነጋገሪያ ሆነዋል።
ምዕራባውያን አገራት ከሙቀት ማዕበል ጋር እየታገሉ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ይህ ቴክኖሎጂ የቻይናን ዘመናዊና ፈጣን የሕዝብ መሠረተ-ልማት አቅም የሚያሳይ ነው በሚል በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን እያተረፈ ነው።
የዚህ ቴክኖሎጂ መሠረታዊ ሳይንስ ፈሳሽን ወደ ትነት የመቀየር ሂደት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ ይህም ልክ የሰውነታችን ላብ በሚተንበት ጊዜ ቆዳችንን እንደሚያቀዘቅዝልን ዓይነት ተፈጥሯዊ ሳይንስ ነው።
ሥርዓቱ ከፍተኛ ግፊት ያላቸው ፓምፖችንና ልዩ ማፋሰሻዎችን በመጠቀም በጣም ጥቃቅን የውሃ ጠብታዎችን ወደ አየር ይረጫል።
@Addis_Reporter

❤43👍4
አዲስ አበባ ክልል ልትሆን? ሕገ መንግስቱም ሊቀየር ነው?
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከሰሞኑ በአዳማ ከተማ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማድረጉ እየተሰማ ነው፡፡
ፓርቲው በይፋዊ ገጹ ላይ ባያረጋግጠው ስብሰባ መቀመጡን የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
አንዳንድ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳመላከቱት ብልጽግና በዚህ ስብሰባው ሕገ መንግስቱን ለመቀየር፣ አዲስአበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ክልል ለማድረግ፣ የመሬት ፖሊሲን ለመቀየር፣ ስርአቱ ከፓርላሜንታዊ ወደ ፕሬዝዳንታዊ እንዲሆን መወሰኑ እየተሰማ ነው፡፡
እነዚህን መረጃዎችን በተመለከተ በይፋ የተረጋገጠ መረሃ ማግኘት ባይቻልም፤ እነዚህ ውሳኔዎች እውነተኛ ከሆኑ ግን ማርሽ ቀያሪ ውሳኔዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

❤30😡22👍5🤣4😢2
የቬኔዙዌላ ሰማይ‼️
ከሰሞኑ በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ከ2300 በላይ ዜጎቿን በሞት ያጣችሁ እንዲሁም ከ68000 በላይ ዜጎች የደረሱበት ያልታወቀ እና ከ2500 በላይ ህንፃዎቿ የፈራረሱባት በደቡብ አሜሪካ አህጉር የምትገኘው ቬኒዚዮላ ከትናንትናው ዕለት ሰማይዋ በድንገት ወደ ቀይ ተቀይሯል።
ለዚህ እንደምክንያት የተቀመጠው ከሰሃራ በረሃ የተነሳ ቀይ ብናኝ እንደሆነ ተገልጿል።

❤8👀8😱5😢3👍2🤔1
የመንግሥት ሰራተኞች ታክስ አይቀነስም‼️
በጊዜው እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ
#የመንግስት_ሰራተኛ ታክስ ሊቀነስ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል ወይ? የሚል ጥያቄ ለአቶ አህመድ ሽዴ ቀርቦላቸው 'በመጀመሪያ መንግስት የሰራተኛውን ዝቅተኛ ኑሮ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ስለሆነ አይታሰብም' የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

😢14❤3👍2🤔1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

❤2👍2
በአርባ ምንጭ ከተማ የ12 ዓመቷን የገዛ ሚስቱ እህትን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
ተከሳሽ አቶ ኃይማኖት ዮሐንስ የተባለው ግለሰብ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት ሰዓቱ በውል በማይታወቅበት በአርባ ምንጭ ከተማ ሼቻ ክፍለ ከተማ ዶይሳ ቀበሌ ልዩ ስፍራው አሻም ሆቴል ጀርባ አከባቢ የባለቤቱ እህት በሆነች ታዳጊ ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል መፈፀሙ ተገልጿል።
ተከሳሽ ከእሱ እና ከባለቤቱ ጋር በአንድ ቤት በሥራ አጋዥነት የምትኖረውን ዕድሜዋ 12 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይን ባለቤቱ ለስራ በሄደችበት ምሽት አጋጣሚውን በመጠቀም የፖርኖግራፊ (ልቅ የወሲብ) ፊልም በቴለቪዥን በመክፈት እንድትመለከት ካደረገ በኋላ የግል ተበዳይ የለበሰችውን ልብስ አውልቆ በመራቢያ አካሏ እና በመቀመጫዋ በተደጋጋሚ ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀመባት እና ድርጊቱን ለሰዎች እንዳትናገር ያስጠነቀቃት ቢሆንም በድርጊቱ ምክንያት በግል ተበዳይ ላይ በተከሰተ ህመም ተበዳይ ጉዳዩን ለጎረቤት በመንገሯ የወንጀል ምርመራ ሂደቱ ተጀምሮ ለውጤት በቅቷል ሲል የዓቃቤ ክስ መዝገብ ያስረዳል።
የወንጀል ድርጊቱ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው የከተማው ፖሊስ መምሪያ የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ልዩ መርማሪ ከዐ/ሕግ ጋር በመቀናጀት የምርመራ መዝገቡን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ ክስ ይመሰርታል።ጉዳዩን የተመለከተው የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ብይን ሰጥቷል ።

❤16🤯8👍4😢4
በሰነዶች ማረጋገጫ ንብረት ገዝተው ስም ያላዛወሩ ዜጎች በአስቸኳይ ይዞታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተጠየቀ
ቀደም ባሉ ጊዜያት ከሪል እስቴት አልሚዎችም ሆነ ከግለሰቦች ጋር የቤት ወይም የመሬት ግብይት ፈጽመው፣ በሰነዶች ማረጋገጫ ብቻ የያዙና እስካሁን የስመ-ንብረት ዝውውር ያላደረጉ አካላት በአስቸኳይ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ ።
የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ እንደገለጹት፤ ግዢ ፈጽመው የስም ዝውውር ያላደረጉ ወገኖች ለከፍተኛ ጉዳትና ለአደጋ እየተጋለጡ ይገኛሉ።
የስመ-ንብረት ዝውውር ዋና ዓላማ አንድ ግለሰብ ያፈራውን ንብረት ለሌላ አካል የሚያስተላልፍበት ሕጋዊ ሥርዓት መሆኑንና የመጨረሻው መዳረሻም የይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ) ማግኘት መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል።
በመሆኑም ባለንብረቶች መብታቸውን ለማስከበርና ንብረታቸውን ከማንኛውም ሕጋዊ ስጋት ለመጠበቅ ሲሉ፣ ሳይዘገዩ ወደ መሬት ተቋማት በመቅረብ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

❤13👍2
አራት ልጆቻቸውን እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አስተምረው የልጅ ልጆችም ያዩት የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ እናት
ከላይ በምስሉ የምታያቸው ወ/ሮ አልማዝ አሻራው ይባላሉ። በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በቤተሰብ ጫና ምክንያት በ1982 ዓ.ም ከ4ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ይገልጻሉ።
በ1983 ዓ.ም ትዳር የመሰረቱት ወ/ሮ አልማዝ የስምንት ልጆች እናት ናቸው። አራት ልጆቻቸውን እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አስተምረዋል፣ የልጅ ልጆችም አይተዋል።
የቀሩት አራት ልጆቻቸው ደግሞ ከ5ኛ እሰከ 12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ትምህርታቸውን ዳግም መማር ያሰቡት ትላንት ያላሳኩትን፣ ያልኖሩትን ህልማቸውን ዳግም ለመኖር እንደሆነ ወ/ሮ አልማዝ ይገልጻሉ።
እኚህ ብርቱ እናት ዘንድሮ እየተሰጠ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው፣ በመጀመሪያው ዙር በበይነ መረብ ፈተናቸውን መውሰድ ጀምረዋል። ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ተምረው መመረቅ ህልማቸው እንደሆነም ይናገራሉ።

❤39👍5👌1
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በመስረቅ ያከማቸ ግለሰብ በ6 ዓመት እስራት ተቀጣ
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመስረቅ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በ6 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት አሰታውቋል፡፡
ግለሰቡ ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ አልሙኒየሞችና መዳቦች በመስረቅ ባሳለፍነው መጋቢት ወር መጨረሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ያሰታወሰው አግልግሎቱ፤ በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ባደረገው ክርክር በግለሰቡ ላይ የ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲወሰን ማደረግ መቻሉን ለጣቢያችን የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተያያዘም በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ኬብሮን መድኃኒት ቤት አካባቢ በግንባታ ላይ ከሚገኝ ህንፃ ላይ የወደቀ ህንፃ መወጣጫ ዊንች በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብልና በትራንስፎርመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የገለጸው አገልግሎቱ፤ ተቋሙ ጉዳት የደረሰበትን የኤሌክትሪክ ኬብልና ትራንስፎርመር በመተካት ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከ1 ሚሊየን 9 መቶ ሺሕ ብር በላይ እንዲከፍል በፍርድ ቤት ስለመወሰኑ ገልጿል፡፡

❤9👍3
ትምህርት መስከረም 5 ይጀመራል!
የትምህርት ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ ወጥነት ያለው የማስተማር ሂደት እንዲኖር ለማስቻል ያዘጋጀውን የ2019 ዓ.ም አጠቃላይ የትምህርት ዘመን ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ (ካላንደር) ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች አስተላልፏል።
በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፦
- ከነሐሴ 26 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይከናወናል።
- መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ትምህርት ይጀምራል።

❤12👍8🤔4👌1
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አፈሳ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ምክንያት ይህንን ድርጊት በመቃወም በዛሬው ዕለት መቀሌን ጨምሮ በአዲጉደምና በሌሎች ከተሞች ከሰዎች እንቅስቃሴ ታቃበው ውለዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10👍7🤣5😢3💔3
መረጃ‼️
የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ባለሥልጣን፣ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ያለ ሕጋዊ ፍቃድ አንዳንድ የሕክምና መሳሪያዎችን የማስተዋወቅ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ሲል ከሠሠ።
ባለሥልጣኑ ዩትዩብንና ቲክቶክን ጨምሮ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ሕጋዊ ማረጋገጫ እና ፍቃድ ያልተሠጠባቸውን የሕክምና መሳሪያዎች ያስተዋወቁ አካላት ማስታወቂያዎቹን ባስቸኳይ እንዲያነሱ አሳስቧል።
አንዳንድ የሕክምና መሳሪያዎች ለሕዝብ በማስታወቂያ መልክ እንዳይቀርቡ በሕግ የተከለከሉ ናቸው ያለው ባለስልጣኑ፣ ማሳሰቢያውን በመጣስ ያለ ሕጋዊ ፍቃድ የሕክምና መሳሪያዎችን ማስተዋወቅ በሚቀጥሉ አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

❤17👍2