ኢትዮጵያ በቀጣናው ከፍተኛ የገቢ ግብር በመጣል 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች
በአፍሪካ ቀንድ እየተካሄደ ያለውን መጠነ-ሰፊ የፋይናንስ እና የግብር ማሻሻያ ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት መካከል በተቀጣሪ ሰራተኞች ደመወዝ ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል ሶስተኛዋ ሀገር መሆንዋ ታውቋል።
የቀጣናውን የቅጥር ገቢ ግብር (PAYE) ተመን ያነጻጸረው አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛውን የግብር ተመን 35 በመቶ አድርሶ እየተገበረ ይገኛል። ይህም ግልጽ የሆነ ከፍተኛ የግብር ጫና ካለባትና 40 በመቶ ከምትከፍለው ኡጋንዳ፣ እንዲሁም 35 በመቶ የመጨረሻ የግብር ተመን ካላትና ተጨማሪ ልዩ ልዩ ታክሶችን ከምትጥለው ኬንያ ቀጥሎ ኢትዮጵያን በሶስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
ይህ ደረጃ የመጣው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2025 ያከናወነችውን አጠቃላይ የግብር ማሻሻያ ተከትሎ ነው። መንግስት ቀደም ሲል በሀገር ቁጥጥር ስር የነበረውን የኢኮኖሚ ሞዴል ወደ ነፃ ገበያ ለመቀየር በሚያደርገው ሽግግር፣ የመሠረተ ልማት ጉድለቶችን ለመሙላትና የኢትዮጵያን ብር ለማረጋጋት መደበኛ ተቀጣሪዎችን ዋነኛ የገቢ ምንጭ አድርጓል።
ይህ የደረጃ ምደባ የወጣው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በሐምሌ 2025 ሰፊ የፊስካል እና የግብር ማሻሻያ ማድረጓን ተከትሎ ነው። መንግስት የኢኮኖሚ ሞዴሉን ከመንግስት ቁጥጥር ወደ ነፃ ገበያ መርህ ለመቀየር በሚያደርገው ጉዞ፣ የመሰረተ ልማት ጉድለቶችን ለመሙላት እና የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ለማረጋጋት በመደበኛው የስራ ዘርፍ ላይ በሚጣል የገቢ ግብር ላይ በእጅጉ ተደግፏል። ይሁን እንጂ የግብር እርከኑ የተቀረጸበት መንገድ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ ስራ አስኪያጆች እና ባለሙያዎች በፍጥነት ወደ ከፍተኛው 35 በመቶ የግብር ጣሪያ ውስጥ እንዲገቡ የሚያስገድድ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በአንጻሩ ጎረቤቶቹ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ከፍተኛውን የገቢ ግብር ተመናቸውን በ30 በመቶ የወሰኑ ሲሆን፣ ደቡብ ሱዳን ደግሞ በ15 በመቶ ዝቅተኛ ታክስ በቀጣናው የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።
ይህ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የግብር ፖሊሲ ልዩነት በቀጣናው የሰለጠነ የሰው ኃይል ዝውውር ላይ ጫና እየፈጠረ ይገኛል ተብሏል።
@Addis_Reporter

🤣11❤10🤔5👍1🙊1
"የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት የለውም!" -ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር
የፌዴራል መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት ወታደሮቹን ከምዕራብ ትግራይ ወደ ምስራቅ ትግራይ እያሠማራ መሆኑን የሕወሃት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር በዛሬው ማምሻ ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ቴሌቪዥን በተላለፈው በዚህ መግለጫ ላይ ኃላፊዋ አሜሪካ በ"አክራሪ" የሕወሃት አመራሮችና አባላት ላይ የጣለችውን የቪዛ እገዳ አስመልክተው የተናገሩ ሲሆን፥ እገዳው በግለሰቦች ላይ ሳይሆን በሕወሃት "መርሆች" ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ሕወሃት በመሠረታዊ መርሆዎቹ ላይ ፈጽሞ እንደማይደራደር አጽንዖት ሰጥተዋል።
ፈትለወርቅ አክለውም፥ የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት እንደሌለው ለአሜሪካ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብና የድርጅቱ ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕጣ ፈንታ በራስ የመወሰን መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዋ፥ የአሜሪካ ጥቅም ሊረጋገጥ የሚችለው ሕወሃትን በማስፈራራት ሳይሆን አብሮ በመስራት ብቻ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

❤18🤔8🤣7👍2
ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ70 ሚሊየን ዩሮ የረጅም ጊዜ ብድር ፈቀደች
የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱ የጀመረችውን ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለማስፈጸም የሚውል የ70 ሚሊየን ዩሮ የረጅም ጊዜ ቀላል የብድር ስምምነት ከጣሊያን ጋር ተፈራረመ።
የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በዛሬው ዕለት ተፈራርመውታል። ይህ ድጋፍ ጣሊያን ለኢትዮጵያ ለመስጠት ካቀደችው አጠቃላይ የ150 ሚሊየን ዩሮ የበጀት ድጋፍ ማዕቀፍ ውስጥ የመጀመሪያው ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።
በስምምነቱ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እንደገለጹት፤ ይህ የብድር ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነትና የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።
ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ ሁለተኛውን ምዕራፍ በስኬት ማጠናቀቋን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ይህ የገንዘብ ድጋፍም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ከጣሊያን መንግስት ጋር በኢነርጂ፣ በቡና እና በከተማ ልማት ዘርፎች ጠንካራ ትብብር እንዳላት ያወሱት አቶ አሕመድ፣ ይህ አዲስ ስምምነትም አጋር ሀገራት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሂደት ውጤታማነት ላይ ያላቸውን ከፍተኛ እምነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም፣ ኢትዮጵያ ለሶስተኛው የበጀት ድጋፍ ምዕራፍ ትግበራ ከዓለም ባንክ ጋር የአንድ ቢሊየን 450 ሚሊየን ዶላር ስምምነት መፈራረሟን በአብነት ጠቅሰዋል።

😢15❤11👍2
የ29 አመቷ የአዲስ አበባ ልጅ ሜላት ኪሮስ የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክርቤት Congress በመሆን ተመርጣለች። የመጀመሪያዋ ትውልደ ኢትዮጵያ የኮንግሬስ ተመራጭ ናት።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍65❤34🥱8🥰2🏆2🎉1👌1🤪1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

❤4👍2🤔1
የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ የቶታልኤነርጂስን የኢትዮጵያ ንብረቶች በሙሉ ጠቀለለ
የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የፈረንሳዩ ቶታልኤነርጂስ ንብረቶች በሙሉ ለመጠቅለል የሚያስችለውን የግዢ ስምምነት በፓሪስ ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት ኦላ ኢነርጂ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ገበያ ውስጥ ትልቁ የውጭ ኩባንያ ያደርገዋል።
ይህ ግዙፍ የአክሲዮን ግዢ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወደ 120 የሚጠጉ የነዳጅ ማደያዎችን፣ የ13 ሺህ ሜትር ኩብ አቅም ያለውን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እና ተያያዥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያጠቃልላል።
በስምምነቱ ላይ የሊቢያ ዘይትና ጋዝ ሚኒስትር ከሊፋ አብዱልሳዲቅ እና የቶታልኤነርጂስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ፑያን ጨምሮ የሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ግዢው ሊቢያ በአፍሪካ አህጉር ያላትን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ እና የውጭ ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።

❤9👍6
አሳዛኝ ዜና
በሠሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሰዶማ ወይም ድሬ ሮቃ አካባቢ በቁጥር 23 ቀበሌ ቀስማ ጎጥ ላይ ምክኒያቱ በውል ባልታወቀ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ከ50 ያላነሱ የአርሶ አደራችን መኖሪያ ቤቶች በትላንትናው እለት ተቃጥለዋል።
የዚህ አከባቢ ህዝብ ጀግና እና አስተዋይ ህዝቦች ሲሆኑ ሀገር በፈለጋቸው ወቅትም ክንዳዘው ሳይዝል ከትላንት እስከ ዛሬ ፀንተው የቆሙ ህዝቦች ናቸው።
በመሆኑም ሁላችነም በጋራ ሆነን ወገኖቻችን አንገታቸውን መድፋት ስለሌለባቸው እንድናቋቁማቸው ጥሪየን አቀርባለሁ።
ዘመን ተሻጋሪው

❤24😢18💔9👍2
አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት‼️
በእጅ ስልካችን ረቂቅ እና ያልተፈቀዱ ግብይቶችን የሚፈፅሙ እና በስፋት እየተሰራጩ የሚገኙ ጎጂ መተግበሪያዎችን ስለማሳወቅ‼️
ጥቃት አድራሾች የጥቃት ዘዴያቸውን በመቀያየርና ጎጂ መተግበሪያዎችን በማበለፀግ ወይም በመጠቀም ከሞባይል ላይ የግል መረጃ ስርቆትን ጨምሮ ያልተፈቀዱ የገንዘብ ዝውውሮችን ይፈፅማሉ።
የሚከተሉት እጅግ ውስብስብ፣ ረቂቅ እና አደገኛ የሆኑ ጎጂ መተግበሪያዎችም በስፋት እየተሰራጩ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።
1. ትረስት መተግበሪያ (Trust.Apk)
ትረስት የተሰኘው ጎጂ መተግበሪያ https://trust--application በሚል ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህን ጎጂ መተግበሪያ ተጠቂዎች ስልካቸው ላይ በሚጭኑበት ወቅት የሞባይል ስክሪናቸውን ማየት/ማንበብ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስልካቸውን በመቆጣጠር እንደ ይለፍ ቃል/ፒን የመሳሰሉ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በመመንተፍ ከሞባይሉ ባለቤት እውቅና ውጪ የሞባይል መተግበሪያም ይሁን የአጭር ኮድ (*889*) አገልግሎቶችን በመጠቀም ያልተፈቀደ ግብይቶችን መፈፅም የሚችል አደገኛ መተግበሪያ ነው።
2. ጎግል ቲቪ (Google TV)
ጎግል ቲቪ (Google TV) የተሰኘውን ጎጂ መተግበሪያ በሊንክ አማካኝነት ወደ ጎግል ክሮም (Google Chrome) በመግባት ተጠቂው በሚጭንበት ጊዜ እንደ ይለፍ ቃል/ፒን ያሉ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በመመንተፍ፣ ከተጠቂው እውቅና ውጪ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍም ሆነ በርቀት መቆጣጠር (Remote Access) ችሎታን በመጠቀም ጥቃት መሰንዘር የሚችል ነው።
3. ኖውን (Known)
ሶስተኛው ጎጂ መተግበሪያ በማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች ላይ እየተዘዋወረ ሲገኝ ከላይ እንደ ጠቀስናቸው መተግበሪያዎች ከጎግል ክሮም (Google Chrome) እየወረዱ ይገኛሉ። ይህን መተግበሪያ ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው አንዴ ስልካችን ላይ ከተጫነና እንደ ተደራሽነት (Accessibility)፣ የመሳሪያ ፍቃድ አስተዳደር (Device Administrator Rights) ያሉ ፍቃዶችን ከተቸረው ሙሉ በሙሉ ስልካችንን በመቆጣጠር “Installing system update...” የሚል መልዕክት ብቻ ጥቁር ስክሪን ላይ የሚያሳይ ሲሆን ተጠቃሚው ይህንን መተግበሪያ ለማጥፋት ግዴታ ሴፍ ሞድ (Safe Mode) በኩል መግባት ይኖርበታል። ሌላው ይሄን መተግበሪያ ለየት የሚያደርገው ከፍተኛ የሆነ የኔትዎርክ አጠቃቀም ሲኖረው፣እምነት ለመገንባትና ተጠቂዎችን ለማታለል Google Play Store የሚመስል ሀሰተኛ ገፅ በመፍጠር ተጠቃሚዎች የማሳመን ስራን ይሰራል። በዋነኝነት ደግሞ ከተጠቂው እውቅና ውጪ ገንዘብ ያስተላልፋል።
በመሆኑም፣ ይህንን የጥንቃቄ መልዕክት በአግባቡ በመገንዘብ ራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን እና በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን ለደርሱ ከሚችሉ ጥቃቶች እንድትጠብቁ ጥሪያችንን እያቀረብን ከታች የተቀመጡትን የጥንቃቄ መልዕክቶች በአግባቡ እንድተገብሩ እናሳስባለን።
ደንበኞች ከዚህ መሰል ጥቃት እንዴት እራሳቸውን መከላከል ይችላሉ?
👉 ካልታመኑ ምንጮች (ጎግል ክሮም የመሳሰሉ ብሮውዘሮች ፣ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ) ላይ መተግበሪያዎችን ከማውረድ ይቆጠቡ።
👉 እንደ ጎግል ፕሌይ፣ አማዞን አፕስቶር ወይም ሳምሰንግ ጋላክሲ ስቶር ጥብቅ የደህንነት ፍተሻዎችን የሚያደርጉ ይፋዊ የመተግበሪያ ማከማቻዎችን ይጠቀሙ።
👉 ለሁሉም የባንኩ መተግበሪያዎች እንደ አሻራ ያሉ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ ይጠቀሙ።
👉 በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎ ላይ የአሻራ (Biometrics) እና PIN ማረጋገጫን ባንድ ላይ ይጠቀሙ።
ይህን ለማድረግ፡
👉 መተግበሪያዎችን ተአማኒ ካልሆኑ ድረ-ገፆች ላይ አውርዳችሁ ለመጫን ስትሞክሩ ስልካችሁ የሚልክላችሁን እንደ ‘File May be Harmful’ የመሳሰሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ችላ አይበሉ።
👉 ከአጠራጣሪ ኢ-ሜይሎች የሚላኩ ማስፈንጠሪያም (suspicious links) ሆነ ፋይል (Attachment) ሳያረጋግጡ ከመክፈት ይቆጠቡ።
👉 ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ፍቃዶችን (Permission) የሚጠይቁ መተግበሪያዎች ላይ አስፈላጊ ነው ወይንስ አያስፈልግም ሚለውን የራስዎን ጥናት በማድረግ ፍቃዱን ይገድቡ።
#CBE

❤40👍10🙏2🥰1🤯1👌1
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፌደራል መንግስት ጋር የሚደራደር ከሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ሳይሆን “በሌላ ሶስተኛ ሀገር” እንደሚሆን ለአሜሪካ ማሳወቁን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ተናገሩ።
የአሜሪካ መንግስት “ቪዛ መከልከል ይቅር እና ሌላ ቢያደርግም”፤ “የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማረጋገጥ” ህወሓት “እስከ መጨረሻ እንደሚታገል” ኃላፊዋ ገልጸዋል።
“ሞንጆሪኖ” በሚለው የቅጽል ስማቸው ይበልጡኑ የሚታወቁት ፈትለወርቅ ይህንን የገለጹት፤ ትላንት ማክሰኞ ሰኔ 23፤ 2018 በመቐለ ከተማ በሚገኘው የህወሓት ጽህፈት ቤት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው።
በትላንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል የፕሪቶሪያ ስምምነት ሁኔታ፣ የጦርነት ስጋት፣ የወጣቶች አፈሳ፣ የአሜሪካ ቪዛ እገዳ እንዲሁም ትግራይን በተመለከተ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ያወጧቸው መግለጫዎች ይገኙበታል።
የፕሪቶሪያ ስምምነት “መፍረሱን” በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ያሳወቀው ህወሓት፤ ለዚህም ዋነኛው ተጠያቂ የፌደራል መንግስት መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።
የህወሓት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በትላንቱ መግለጫቸው፤ የፕሪቶሪያ ስምምነትን “የፌደራል መንግስት እንደ መሳርያ ነው የተጠቀመበት” ሲሉ ተመሳሳይ አቋም አንጸባርቀዋል።
“የፕሪቶሪያ ውል እንዲፈጸም ህወሓት ጥረት አድርጓል። ውሉን የሚጥሱ በርካታ ነገሮች ቢሰሩም፤ ‘የፕሪቶርያ ስምምነት ፈርሷል’ ሳይል በትእግስት ቆይቷል። በዚህ ጉዳይ ህወሓት እንደ ፓርቲ ትልቅ ትልቅ መስዋእትነት ከፍሏል” ሲሉም ፈትለወርቅ ለፓርቲው ልሳናት እና ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።
Via Ethiopia Insider

❤9🤣6👍5💯1🤪1
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ተተርጉሞ ለንባብ ሊበቃ ነው
2018 የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቅርቡ ለንባብ ሊበቃ ነው፡፡
በ2010 ዓ.ም የነበረውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የኢትዮጵያ የነገ ጉዞ ፍኖተ ካርታ ሆኖ የተወለደውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተጻፈው የ«መደመር» መጽሐፍ የቻይንኛ ቋንቋ ትርጉም ሥራው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
መደመር ባለፉት አሥርት ዓመታት ከአፍሪካ አህጉር ፈልቀው ወደ ዓለም መድረክ ከተሻገሩ ጥቂት ሀገር በቀል ፍልስፍናዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው፡፡

🤪59🤣15❤14👍4🤔2
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤5👍2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሊዮን በረራ ጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንይ ሊዮን ከተማ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት ማስጀመሩን ይፋ አድርጓል።
ይህም ለአየር መንገዱ በፈረንሳይ 3ኛ፣ በአውሮፓ 23ኛ እንዲሁም የዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ቁጥር 146 የሚያደርሰው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በወቅቱ እንዳሉት፤ የበረራ አገልግሎቱ መጀመር አየር መንገዱ አፍሪካን ከዓለም ጋር የማገናኘት ጉዞው ተጨማሪ ስኬት ነው።
ወደ ሊዮን የጀመረው በረራ ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ተጨማሪ ዕድል የሚፈጥር ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡
መንገደኞችን ከማመላለስ ባሻገር የሀገራት ሁለንተናዊ ትስስሮች እንዲጠናከሩ አቅም መፍጠር እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

❤9👍6🥰2
በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊው ነጋዴ ጠመንጃ
ታጥቆ በመታየቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጠረ
በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ አንድ ማኅበረሰብ ውስጥ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የተነገረለት ግለሰብ በከፈተው ሱቅ ውስጥ ጠመንጃ ታጥቆ ሲሠራ ታይቷል መባሉን ተከትሎ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ እየጠየቁ ነው።
በአካባቢው የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ግለሰቡ የጦር መሣሪያውን በግልጽ ይዞ መታየቱ በነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ስጋትና ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው የሕግ አካላት መሣሪያው በሕጋዊ መንገድ የተያዘ መሆኑንና አለመሆኑን እንዲሁም የተጣሰ ሕግ ካለ አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ማኅበረሰቡ በጥብቅ እየወተወተ ይገኛል።

❤36🫡24👍17👌1😎1
መረጃ‼️
የኤርትራ ብሄራዊ ባንክ፣ ኤርትራዊያን በእጃቸው ላይ የሚገኝ ገንዘብን እስከ ሐምሌ 23 ወደ ባንክ እንዲያስገቡ አዘዘ።
ከባንክ ውጪ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መያዝ የተከለከለ መኾኑን ያስታወቀው ባንኩ፣ ማንኛውም ዜጋ ወይም ተቋም ለግብይት መጠቀም የሚችለው ናቅፋ ብቻ መኾን አለበት ብሏል።
የባንክ ሂሳብ የሌላቸው ዜጎች እስከ ሐምሌ 23 የባንክ ሂሳብ ከፍተው ገንዘባቸውን እንዲያስቀምጡ ባንኩ ያሳሰበ ሲሆን፣ ትዕዛዙን ተግባራዊ በሚያደርጉ ዜጎችና ተቋማት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንሚወስድ አስጠንቅቋል።

❤13🤣12👍6🙊2🤔1
ማኑዋል መኪና መንዳት የአንጎልን የመሥራት ብቃት እንደሚያሳድግ አዲስ ጥናት አመለከተ
የማኑዋል መኪና አነዳድ ከተለመደው የመንዳት ልምድ ባለፈ ለአእምሮ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጃፓን የተደረገ አዲስ ጥናት ጠቆመ። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ማኑዋል መኪናዎችን ማዘወር ለአውቶማቲክ መኪናዎች ከሚሰጠው ትኩረት ይልቅ ለአንጎል የማስታወስ፣ ትኩረትን የመሰብሰብ እና ውሳኔ የመስጠት ብቃትን በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃል።
ይህ ግኝት ይፋ የሆነው በጃፓኑ “ቤስት ካር ዌብ” (Best Car Web) የጋዜጠኝነት መድረክ ሲሆን፣ ጥናቱን ያካሄዱት ደግሞ በቶሆኩ ዩኒቨርሲቲ የልማት፣ እርጅና እና ካንሰር ምርምር ተቋም ፕሮፌሰር የሆኑት ርዩታ ካዋሺማ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ቀደም ሲል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈውን የኒንቴንዶ “ብሬይን ኤጅ” የአእምሮ ማሳያ ጨዋታዎች በስተጀርባ ያለውን የሳይንስ መሠረት ያዘጋጁ ታዋቂ የነርቭ ሳይንቲስት ናቸው። በሳቸው ምርምር መሠረት ማኑዋል መኪና በሚነዳበት ወቅት የሚፈለጉት ተከታታይ ተግባራት ከፍተኛ የእውቀት ተግባራትን የሚያከናውነውን የአንጎል የፊት ክፍል ያነቃቁታል።
የማኑዋል መኪና አሽከርካሪዎች ክላች መርገጥን፣ ማርሽ መቀየርን፣ የነዳጅ መቆጣጠሪያን (throttle) ማስተካከልን እና በተመሳሳይ ሰዓት የትራፊክ ፍሰቱን መከታተልን በአንድ ላይ ማቀናጀት ይጠበቅባቸዋል። ተመራማሪዎቹ እንዳረጋገጡት ይህ በአንድ ጊዜ በርካታ ሥራዎችን የመሥራት ሂደት አእምሮ ያለማቋረጥ ንቁ ሆኖ መረጃዎችን እንዲያሰላስል የሚያስገድደው በመሆኑ፣ ለአንጎል የፊት ክፍል ታላቅ የዕለት ተዕለት የስፖርት እንቅስቃሴ ሆኖ ያገለግላል።

❤12👍8
በቻይና የሙቀትን ለመቋቋም የዘረጋችው የውሃ ማፍሰስ ቴክኖሎጂ መነጋገሪያ ሆኗል!
በአውሮፓና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አስከፊ የሙቀት ማዕበል በተከሰተበት በዚህ ወቅት፣ በቻይና የመኖሪያ መንደሮች ውስጥ የተዘረጉ አስደናቂ ከቤት ውጪ ማቀዝቀዣ ሥርዓቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የብዙዎችን ቀልብ እየሳቡ ይገኛሉ።
በተለይም ሰፊ የመኖሪያ ሕንፃዎች ግቢዎችን፣ መናፈሻዎችንና የእግር መንገድ ቦታዎችን ለማቀዝቀዝ የተዘረጉት የውሃ ማፍሰስ ሥርዓቶች ትልቅ መነጋገሪያ ሆነዋል።
ምዕራባውያን አገራት ከሙቀት ማዕበል ጋር እየታገሉ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ይህ ቴክኖሎጂ የቻይናን ዘመናዊና ፈጣን የሕዝብ መሠረተ-ልማት አቅም የሚያሳይ ነው በሚል በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን እያተረፈ ነው።
የዚህ ቴክኖሎጂ መሠረታዊ ሳይንስ ፈሳሽን ወደ ትነት የመቀየር ሂደት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ ይህም ልክ የሰውነታችን ላብ በሚተንበት ጊዜ ቆዳችንን እንደሚያቀዘቅዝልን ዓይነት ተፈጥሯዊ ሳይንስ ነው።
ሥርዓቱ ከፍተኛ ግፊት ያላቸው ፓምፖችንና ልዩ ማፋሰሻዎችን በመጠቀም በጣም ጥቃቅን የውሃ ጠብታዎችን ወደ አየር ይረጫል።

❤43👍4
አዲስ አበባ ክልል ልትሆን? ሕገ መንግስቱም ሊቀየር ነው?
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከሰሞኑ በአዳማ ከተማ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማድረጉ እየተሰማ ነው፡፡
ፓርቲው በይፋዊ ገጹ ላይ ባያረጋግጠው ስብሰባ መቀመጡን የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
አንዳንድ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳመላከቱት ብልጽግና በዚህ ስብሰባው ሕገ መንግስቱን ለመቀየር፣ አዲስአበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ክልል ለማድረግ፣ የመሬት ፖሊሲን ለመቀየር፣ ስርአቱ ከፓርላሜንታዊ ወደ ፕሬዝዳንታዊ እንዲሆን መወሰኑ እየተሰማ ነው፡፡
እነዚህን መረጃዎችን በተመለከተ በይፋ የተረጋገጠ መረሃ ማግኘት ባይቻልም፤ እነዚህ ውሳኔዎች እውነተኛ ከሆኑ ግን ማርሽ ቀያሪ ውሳኔዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

❤30😡22👍5🤣4😢2