አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
412 videos
21 files
3K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ኢትዮጵያ ያለባትን የ1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ለመክፈል ከአበዳሪዎቿ ጋር ስምምነት ላይ ደረሰች!

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የግል አበዳሪዎች ተበድራው የነበረውን 1 ቢሊዮን ዶላር (ዩሮቦንድ) በወቅቱ መክፈል አቅቷት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ዕዳውን የምታቀልበት የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ከነበረባት 1 ቢሊዮን ዶላር ላይ የ12% ቅናሽ የተደረገላት ሲሆን በዚህ መሰረት የምትከፍለው ዕዳ ወደ 880 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሏል።

ይህንን 880 ሚሊዮን ዶላር እስከ 2029 ድረስ በ6.15% ወለድ በየደረጃው እንድትከፍል ጊዜ የተሰጣት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሳትከፍል ያሳለፈችውን 99.4 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ዕዳ ትከፍላለች።

ስምምነቱ ወደፊት ኢትዮጵያ ብድር ባስፈለጋት ጊዜ እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ድረስ በድጋሚ የመበደር መብት ወይም ዕድልን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ዋናዎቹ አበዳሪ ሀገራት (ቻይና እና ፈረንሳይ) ስምምነቱን የደገፉ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ገፅታ የሚያሻሽልና ተጨማሪ የውጭ ብድርና 1እርዳታ በቀላሉ እንድታገኝ በር የሚከፍት በመሆኑ .በገበያው ላይ ትልቅ ተስፋን ጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤪19👍7🥱4🥰1👌1🤣1
ዱባይ ለኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያ‼️
የዱባይ ፖሊስ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጨረሻ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️

​ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዲጂታል መድረኮች በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የዱባይ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በትውልድ ኢትዮጵያውያን መካከል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተደረጉ ያሉ አንዳንድ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ነው።

​የዱባይ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በጋራ ባዘጋጁት መድረክ እንደተገለጸው፣ በአረብ ኤምሬቶች የሳይበር ወንጀል ህግ መሰረት የሚከተሉት ድርጊቶች ከፍተኛ ቅጣት እንደሚያስከትሉ ተገልጿል፦

📌 ​የጥላቻ ንግግር: በማህበረሰቡ መካከል መከፋፈልን፣ ጥላቻን እና ንቀትን የሚያንጸባርቁ የብሄር ፖለቲካ ቅስቀሳዎችን ሶሻል ሚዲያ ላይ መለጠፍ።

📌 ​ስድብ እና ስም ማጥፋት: ግለሰቦችን ወይም ተቋማትን በቪዲዮ፣ በጽሁፍ ወይም በኮሜንት መዝለፍ እና ስም ማጥፋት ህግ የተከለከለ ነው።

📌 ​ያለ ፈቃድ መረጃ ማውጣት: የግለሰቦችን ግላዊነት የሚነኩ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም መረጃዎችን ያለ ፈቃድ ማሰራጨት በህግ የሚያስቀጣ ነው።

📌 ​የገንዘብ ማሰባሰብ: ያለ መንግስት ፈቃድ በማህበራዊ ሚዲያ በኩል በስምምነት ገንዘብ ማሰባሰብ በኢምሬትስ ህግ የተከለከለ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍109🤔1
እራሴን ችዬ እዋጋለሁ-እስራኤል‼️
የእስራኤል  መከላከያ ሚኒስትር ከኢራን ጋር ዳግም ወደ ጦርነት በቀናት ውስጥ ልንገባ እንችላለን አሉ።

አይ ዲ ኤፍ ዝግጅት እንዲያደርግም ትዕዛዝ ተሰጥቶታል ብለዋል ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ።

ኢራን ምንም ዓይነት ሚሳኤል ወደ እስራኤል ካስወነጨፈች አፀፋው የማያወላዳ ይሆናል ያሉት ካትዝ በቀናት ውስጥ “ምናልባትም ነገ”ወደ ጦርነቱ ልንመለስ እንችላለን በሚል አሳስበዋል።

ከአሜሪካ ጋር እየተደራደረች ወደ እስራኤል ጥቃት የማድረስ ፍላጎት ኢራን አላት ብለዋል እስራኤል ካትዝ።

"ኢራን ጥቃት ካደረሰች፤ሶስተኛው የኢራን ጦርነት ይሆናል፤ነገሩ እጅግ ግልፅም ነው”በሚል አፅንዖት ሰጥተዋል።

እስራኤል ሚሳዔል ሲወነጨፍባት አደገኛ ምላሽ ሳትሰጥ አታልፈውም የሚል መረጃም ሚኒስትሩ አጋርተዋል።

በኢራን ላይ ያለማንም ደጋፊ  ፣ራሳችንን ችለን ጥቃት ለማድረስ እንዲሁም ሰማያዊ እና ነጭ ዘመቻ(ብሉ ኤንድ ዋይት) ኢራን ውስጥ ለማድረግ ጦሩ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ ብለዋል።

ብሉ ኤንድ ዋይት ዘመቻ በእስራኤል ጦርና ፖለቲከኞች ራስን ችሎ ማጥቃት የሚል ትርጓሜ ይሰጠዋል መባሉን ፎክስ ኒውስን ጠቅሰው ኤን ቢሲ ዘግቧል ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🥱9👍3🤔1🙏1🤣1😎1
ደረቅ ቼክ ምንድን ነዉሼርር
**
ቼክ ማለት ገንዘብን ተክቶ የሚያገለግል ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ነው፡፡ ቼክ ሊፈርም የሚችለው በአንድ ባንክ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ያለው ሰው ነው፡፡ድርጅት ከሆነ ደግሞ ፈራሚው በድርጅቱ ቼክ ላይ የመፈረም ስልጣን የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

ቼክ ከመቀበላችሁ በፊት በቼኩ ላይ -የሚከፈለው የገንዘብ መጠን በአሀዝና በፊደል መፃፉን - የሚከፈለው ሰው ስም እና የባንኩ ቅርንጫፍ መፃፉን -ቼኩን የሰጠው ሰው ፊርማ መኖሩን -ቼኩ የተፃፈበት ቀን እና ቦታ መኖሩ ማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ መሆኑን የንግድ ህግ አንቀፅ 827 ይደነግጋል።

ቼኩ ለማን እንደሚከፈል ስም ካልተጠቀሰበት ማንኛውም ቼኩን ይዞ የቀረበ ሰው ይከፈለዋል። ቼኩ በስሙ የተፃፈለት ሰው ወይም በትዕዛዝ የሚል ካለበት ደግሞ በቀላሉ ከጀርባው በመፈረም ለሌላ ሰው ሊያስተላልፈው ይችላል ።ያም ሰው በጀርባው ፈርሞ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላል፡፡ -የገንዘብ መጠኑ ያልተጠቀሰበትን ቼክ ፈርሞ መስጠት አደገኛ ነው ፡፡ ቼኩ የተፃፈለት ወይም የተላለፈለት ሰው የፈለገውን ገንዘብ ሊሞላበት ይችላል፡፡

ቼኩ የሚከፈለው ለባንኩ ለክፍያ በቀረበ ቀን ነው። - ሆኖም ቼኩ በን/ሕ/ቁ 857 መሠረት የወጣበት ቀን ከግምት ሳይስገባ ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ለባንኩ ለክፍያ መቅረብ አለበት፡፡ -ቼኩን የሚፈርመው ሰው የክፍያውን ቀን ቼኩን ከፃፈበት ወይም ቼኩን ካወጣበት ቀን ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ሊያደርገው ይችላል። ለምሳሌ ዛሬ ቼኩን ሲፅፍ የተፃፈበት ቀን ወደኃላ 7 ወር አድርጎ ቀኑን ቢፅፈው ለክፍያ መቅረብ ያለበት 6 ወር ጊዜ ስላለፈ ባንኩ መክፈልም ሆነ ያልከፈለበትን ምክንያት ለመግለፅ ሳይገደድ ቼኩ ለክፍያ መቅረብ ባለበት ጊዜ ባለመቅረቡ ብቻ ይመልሰዋል፡፡

ዛሬ የሚሰጥ ቼክ ወደፊት የዛሬ 4 ወር አድርጎ ቀኑ ከተፃፈበት ለክፍያ መቅረብ የሚችለው ከአራት ወራት በኃላ ካለው ቀን ጀምሮ ባለው 6 ወራት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ቼክ ተቀባዬች የሚሰጣቸውን ቼክ ገንዘቡን መቀበል ከሚችሉበት ቀን አንፃር በጥንቃቄ የተፃፈበት ቀን ማየት ያስፈልጋል ::

-ቼክ የሰጠው ሰው ቼኩ ለባንኩ ለክፍያ ከመቅረቡ በፊት ባንኩን እንዳትከፍል ብሎ መከልከል ይችላል። ባንኩም የክፍያ መከልከያ ትእዛዝ ከደረሰው መክፈል የለበትም። 

ቼኩን ለባንክ አቅርበህ በቼኩ ላይ የተጠቀሰውን ያህል በቂ ገንዘብ ከሌለ በሂሳቡ ውስጥ ያለውን ያህል መቀበል ይቻላል። ለቀረው ገንዘብ ደግሞ ባንኩ ‘‘በቂ ስንቅ ለውም’’ የሚል የፅሁፍ ማስረጃ ቼኩን ይዞ ለቀረበው ሰው ይሰጠዋል። -በተለምዶ ‘‘ደረቅ ቼክ’’ የሚባለው ለክፍያ ሲቀርብ በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ከሌለው ሲሆን ባንኩ በሚሰጠው ማስረጃ መሰረት ቼክ ሰጪውን ወይም አውጭውን በወንጀል ያስጠይቃል። ሆን ተብሎ ከተፈፀመ ቼክ አውጪው በወንጀል ህግ አቀፅ 693 መሰረት በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ከሆነ ደግሞ ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስርና በመቀጮ ይቀጣል።

ደረቅ ቼኩ የተሰጠው በቸልተኝነት ከሆነ ደግሞ ሰጭው በመቀጮ ወይም ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስር ይቀጣል ፡፡ -ሳይከፈል የቀረውን የቼኩን ገንዘብ ና ወጭውን ቼኩ የተፃፈለት ወይም ተፈርሞ የተላለፈለት ሰው በፍትሀ ብሔር ከሶ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል፡፡ -በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ደረቅ ቼክ የሚሰጡ ሰዎች በጥፋታቸው በጥቁር መዝገብ ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ከገንዘብ መቀጮ አንስቶ በቼክ ሂሳብ የማንቀሳቀስ መብታቸውን እስከማሳጣት ቅጣት ይጣልባቸዋል፡፡

ለግብይት ቅልጥፍና እንዲሁም ለገንዘብ እንቅስቃሴ አመቺነት በቼክ መጠቀሙ ከጥሬ ገንዘብ የተሻለ ዘመናዊ አሰራር በመሆኑ ቼክ አስፈላጊና ልንጠቀምበት የሚገባ የገንዘብ ሰነድ ነው። ለማንኛውም ቼክ ስንሰጥም ሆነ ስንቀበል ከላይ የተነሱትን ነጥቦች ልብ ልንል ይገባል።
Via- መላኩ ፍቃዱ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍4🎉1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
2👍2
የጀነራል ጻድቃን ጥብቅ ወታደራዊ መረጃ!

ህወሓት ወደ መኸል ሀገር ሰብሮ ለመግባት ከውጭ ወደ ውስጥ በሱዳን በኩል በተለያዩ ግንባሮች ጥቃት ለመክፈት ሰፊ ወታደራዊ ስትራቴጂ መንደፉን ጀነራል ጻድቃን ገ/ተንሳኤ አጋልጠዋል፡፡

በወልቃይት ሲጠበቅ የነበረው የህወሓት ጥቃት፣ ባልተጠበቀበት ግንባር ሊፈነዳ እንደሚችል ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡ ጀነራሉ በህወሓት ወታደራዊ ዝግጅት ላይ በሰጡት ማብራሪያ በአፋር እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች የፈጸመው ህወሓት የትኩረት አቅጣጫውን ቀይሯል ብለዋል፡፡

በምራብ ኢትዮጵያ በኩል ጥቃት ከፍቶ ወደ ማኸል ሀገር ለመገስገስ አስቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጀነራሉ ጠቁመዋል፡፡ ጀነራሉ በምራዕብ ኢትዮጵያ በኩል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በኩል ማለታቸው ነው፡፡

የህወሓት ጀነራሎች በአሁኑ ወቅት ሰፊ ወታደራዊ ስትራቴጂ ነድፈው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የገለጹት ጀነራሉ፣ በተለይ ከውጭ ወደ ውስጥ ለማጥቃት ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡ ለዚህም ሱዳንን እንደ ዋና ወታደራዊ መንቀሳቀሻ እየተጠቀሙ መሆኑን ተጨባጫ መረጃዎችና እንቅስቃሴዎች መነራቸው ተናግረዋል፡፡

ሱዳን ውስጥ ለዓመታት የተደራጀው አርሚ 70 እንደ ቀጠናዊ ሚዛን ማስጠበቂያ ለመጠቀም እና ከውጭ ወደ ውስጥ ለማጥቃት ተጨማሪ ኃይል እያስገቡ ነው ብለዋል፡፡ በቅርቡ አርሚ 13 ወደ ሱዳን መሻገሩን ያረጋገጡት ጀነራሉ፣ ሌሎች ተጨማሪ አርሚዎችም ሊጨመሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

አርሚ 13 ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲንቀሳቀስ መንገድ ላይ ሁለት ጊዜ በድሮን ጥቃት ቢመታም፣ የተረፈው አርሚ 70ን ተቀላቅሏል ብለዋል፡፡ ሽራሮ ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት በህወሓት ማረጋጫ የተሰጠበት ቢሆንም፣ ሱዳን ከገባ በኋላ ሸረሪና ላይ ተጨማሪ ደብደባ መፈጸሙን ጀነራሉ ገልጸዋል፡፡
Andafta

@Addis_Reporter
👍43🤣3🤔2😢1🤪1
በቬንዙዌላ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የነፍስ አድን ስራው መዘግየት በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ

በቬንዙዌላ የተከሰተውን አስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ የመንግስት ምላሽ መዘግየትና ቸልተኝነት ህዝቡን ለከፍተኛ ቁጣና ቅሬታ ዳርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

እስካሁን በደረሰው አደጋ ቢያንስ 1ሺህ7መቶ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ባለስልጣናት የገለጹ ሲሆን፤ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ ክስተቱን በሀገሪቱ ታሪክ ‹‹እጅግ አስከፊው የተፈጥሮ አደጋ››ሲሉ ጠርተውታል።

ሆኖም በፈራረሱ የሪል ስቴት እና የመኖሪያ ህንፃዎች ፍርስራሽ ስር የተረፉ ሰዎችን ለመታደግ የሚደረገው ጥረት እጅግ አዝጋሚ መሆን ነዋሪዎችን እያስቆጣ ይገኛል።

የመንግስት እርዳታ እና የማዳኛ ማሽነሪዎች በፍጥነት አለመድረሳቸውን ተከትሎ በቤሎ ሆሪዞንቴ እና መሰል መንደሮች የሚገኙ ነዋሪዎች የራሳቸውን ደህንነት ለአደጋ አጋልጠው በባዶ እጃቸውና በዶማ  ፍርስራሹን እየቆፈሩ ሰዎችን ለማዳን ተገድደዋል።

ምንም እንኳን ከኮሎምቢያ፣ ኤል ሳልቫዶር እና አሜሪካ የመጡ የነፍስ አድን ቡድኖች ድጋፍ እያደረጉ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች የፍለጋ ስራው በይፋ መቋረጡ ተገልጿል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም በፍርስራሹ ስር ተቀብረው በመቅረታቸው የአደጋው እውነተኛ የጉዳት መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አክሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9😢3👍2💔1
#NationalExam
                             
በትግራይ ክልል 29,755 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

በ247 ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ለቀጣዮቹ 14 ቀናት የብሔራዊ ፈተና ይወስዳሉ።

ፈተናው በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በ8 የፈተና ማዕከላት ነው እየተሰጠ ያለው።

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ እንደገለጸው፣ ፈተናው ከፌደራል እና ከክልሉ ከተወጣጡ የጥበቃና የፈተና ባለሙያዎች ጋር ትብብር መጀመሩን ገልጿል።

ቢሮው ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጀመር አስተዋጽኦ ላደረጉ ፦
- ደመወዝ ሳይከፈላቸው ላስተማሩ መምህራን፣
- ለአገር አቀፍ ትምህር ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣
- ለዩኒቨርሲቲዎች፣
- ለትምህርት ባለሙያዎች፣
- ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣
- ለኢትዮ ቴሌኮም፣
- ለፌደራልና ለትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ እንዲሁም ከተለያዩ ክልሎች ለመጡ ሱፐርቫይዘሮች ምስጋና አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍76🥰2🍾1
በጋምቤላ ክልል ህፃናትን መጠጥ ቤት እንዲገቡ ማድረግ 5 ሺህ ብር ያስቀጣል ተባለ
 
ለአቅመ አዳም ያልደረሱና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ወደ መጠጥ ቤቶች እንዳይገቡ ለመጠጥ ቤት ባለቤቶች ጥብቅ መመሪያ መስጠቱን በጋምቤላ ክልል አኙዋ ብሔረሰብ ዞን የአቦቦ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ አዊሊ ኡጁሉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት መመሪያውን ተላልፈው በሚገኙ የመጠጥ ቤት ባለቤቶች ላይ የ5 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፋል ።
 
በተጨማሪም ወላጆች ህፃናትን ጫትና የአልኮል መጠጦችን ለመግዛት ወደ ተለያዩ የንግድ ቦታዎች እንዳይልኩ ጥብቅ መመሪያ መተላለፉን ኃላፊዋ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል። ህፃናት ለጤናቸው ሲባል የትኛውንም አይነት የአልኮል መጠጥ ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ እንዳለባቸው ተነግሯል ።
 
አልኮል የሚጠጣ ሰው ጤና አደጋ ላይ የሚወድቀው ከእያንዳንዱ መጠጥ የመጀመሪያ ጠብታ ጀምሮ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ ።የአልኮል መጠጥ የጉበት ካንሰርን ጨምሮ ጉበት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ፣የልብና የደም ሥር ችግሮች ፣የደም ግፊት ፣የልብ ህመም እንዲሁም የካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚጨምር ጥናቶች ይጠቁማሉ።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍5🥱1
ኢትዮጵያ በጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ አዳዲስ የባህር ትራንስፖርት መስመሮች ጀመረች

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ወደ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ አዳዲስ የጉዞ መስመሮችን በመክፈት የንግድ ትስስሩን እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የተቋሙ የኮርፖሬት ማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊና የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ተወካይ አቶ ደምሰው በንቲ፣ በኢንዶኔዥያና በጃፓን መስመሮች ላይ ከባድ ማሽነሪዎችን፣ ተሽከርካሪዎችንና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን የማጓጓዝ ሥራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ለጋዜጣ ፕላስ ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ ወደፊትም የደንበኞችንና የሀገሪቱን ጥቅም ማዕከል ያደረጉ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማስፋፋት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

እነዚህ አዳዲስ የባህር መስመር ጉዞዎች መጀመራቸው የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ያሻሽላል ያሉት አቶ ደምሰው፣ የወደብ ጭነቶች በአጭር ጊዜ ወደተፈለገው ቦታ እንዲደርሱ በማስቻል ጊዜንና ወጪን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቆጥብ አስገንዝበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍2🤣2😎1
#ሱዳን በተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣የ #ኢትዮጵያ እና የቀጠናው ባለሥልጣናት ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲደረግ ተጠየቀ‼️
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች እና የሕግ ድርጅቶች ጥምረት፤ በሱዳን ዳርፉር ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ለተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ፣ የኢትዮጵያን ጨምሮ የቻድ፣የሶማሊያ፣ የሊቢያ እና የኬኒያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲያደርግ ጠየቀ።

ሚድል ኢስት አይ ባወጣው ዘገባ መሠረት፤ ይህ ጥሪ ሰኞ ዕለት የቀረበው፤ ራውል ዋለንበርግ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል (RWCHR) ከተለያዩ የሕግ፣ የምርመራ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ጋር በመሆን የቀረበ ነው። አቤቱታው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዓቃቢያነ ሕግ የውጭ አገር ባለሥልጣናትና አሸማጋዮች በሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የተፈጸሙ ወንጀሎችን ሆን ብለው በማገዝ ወይም በማበረታታት ረገድ የተሳተፉ መሆኑን እንዲመረምሩ ይጠይቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍95🤯2🕊2🤣1🙊1
ለ200 ዜጎች ነጻ የልብ ሕክምና ሊሰጥ ነው

ኸርት አታክ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከሌሎች የመንግስት እና የግል አጋር አካላት ጋር በመተባበር ከ200 ለሚልቁ ዜጎች በነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል። 

ሕክምናው ከተለያዩ 6 ሀገራት በተወጣጡ 55 በጎፈቃደኛ ሀኪሞች ከእሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ  ሐምሌ 11 ቀን 2018 ድረስ እንደሚሰጥም ማህበሩ ገልጿል። 

ማህበሩ ከዚህ በፊት 4 ግዜ ነፃ የልብ ህክምና መስጠቱን አስታውሶ 481 ለሚሆኑ ታማሚዎች አገልግሎት መስጠቱን ገልጿል። 

ህክምናው በተለያዩ 4 የመንግስት እና የግል ሆስፒታሎች ውስጥ ወረፋ ሲጠባበቁ ለቆዩ አቅም ለሌላቸው ዜጎች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የልብ ህክምና ባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር የማህበሩ አንዱ ሥራ ሲሆን፤ 6 ሲፔሻሊስት የልብ  ሀኪሞች  ወደ ህንድ ተልከው ሰልጥነው እንዲመጡ ለማድረግ መታቀዱ ተሰምቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
31👍4🙏1👌1
#ሀሰተኛ - ይህ ከላይ በምስሉ የሚታየው " ፂም ያለው እና ሽማግሌ የሚመስል ሕጻን በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ተወለደ " እየተባለ የሚነገረው ሀሰት ነው።

በርካቶች መረጃውን ሳያረጋግጡ በችኮላና አንዳንዶች ደግሞ ሆን ብለው የሰዎችን እይታ ለማግኘት ሲሉ ብቻ " በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ ቦረዳ ወረዳ ጭላሼ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወቆ በተባለ ሥፍራ፣ ሙሉ ፂም ያለውና መልኩ ሽማግሌ የሚመስል ሕፃን ተወለደ " ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣226🤔5👍4👀2🙈2🥰1🤪1
ፀደቀ‼️
የታክስ ቅሬታ አጣሪው ተቀየረ፤ የታክስ ቅጣትም በግማሽ ተቀነሰ‼️
*ሰኔ 23/2018 ዓ/ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ላይ ጠቃሚ ማሻሻያዎችን አድርጎ በዛሬው ዕለት አጽድቋል። ማሻሻያው በተለይም ለታክስ ከፋይ ተቋማት የፍትህ አድማሱን የሚያሰፋና የቅጣት ጫናን የሚቀንስ ነው።

በአዋጁ የተካተቱት ዋና ዋና ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፦

ከዚህ ቀደም በታክስ ባለሥልጣኑ በራሱ ይሰየም የነበረው የታክስ "አስማሚ" (Mediator)፣ ከአሁን በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚሰየም ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ይተካል፡፡ ይህም የታክስ ክርክሮች ፍትሃዊ እና ገለልተኛ በሆነ መንገድ እንዲታዩ ያስችላል።

ታክስ ከፋዮች በታክስ አወሳሰን ወቅት ያልቀረቡ ነገር ግን በኋላ ላይ የዕዳ መጠን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ማስረጃዎችን ሲያቀርቡ ይጠብቃቸው የነበረው 20 በመቶ ቅጣት፣ በግማሽ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

የታክስ ህግን በመተላለፍ ወንጀል የሚፈጽሙ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ድንጋጌ ተካቷል። በዚህም መሰረት ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት በስልጣን ላይ የነበሩ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጆች ወይም የፋይናንስ ኃላፊዎች ለወንጀሉ በግል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ህጉ በግልጽ አስቀምጧል።

ይህ ማሻሻያ የታክስ አስተዳደርን ይበልጥ ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና ተጠያቂነት ያለው ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤪5👍3
ኢትዮጵያ በቀጣናው ከፍተኛ የገቢ ግብር በመጣል 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

በአፍሪካ ቀንድ እየተካሄደ ያለውን መጠነ-ሰፊ የፋይናንስ እና የግብር ማሻሻያ ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት መካከል በተቀጣሪ ሰራተኞች ደመወዝ ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል ሶስተኛዋ ሀገር መሆንዋ ታውቋል።

የቀጣናውን የቅጥር ገቢ ግብር (PAYE) ተመን ያነጻጸረው አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛውን የግብር ተመን 35 በመቶ አድርሶ እየተገበረ ይገኛል። ይህም ግልጽ የሆነ ከፍተኛ የግብር ጫና ካለባትና 40 በመቶ ከምትከፍለው ኡጋንዳ፣ እንዲሁም 35 በመቶ የመጨረሻ የግብር ተመን ካላትና ተጨማሪ ልዩ ልዩ ታክሶችን ከምትጥለው ኬንያ ቀጥሎ ኢትዮጵያን በሶስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

ይህ ደረጃ የመጣው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2025 ያከናወነችውን አጠቃላይ የግብር ማሻሻያ ተከትሎ ነው። መንግስት ቀደም ሲል በሀገር ቁጥጥር ስር የነበረውን የኢኮኖሚ ሞዴል ወደ ነፃ ገበያ ለመቀየር በሚያደርገው ሽግግር፣ የመሠረተ ልማት ጉድለቶችን ለመሙላትና የኢትዮጵያን ብር ለማረጋጋት መደበኛ ተቀጣሪዎችን ዋነኛ የገቢ ምንጭ አድርጓል።

ይህ የደረጃ ምደባ የወጣው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በሐምሌ 2025 ሰፊ የፊስካል እና የግብር ማሻሻያ ማድረጓን ተከትሎ ነው። መንግስት የኢኮኖሚ ሞዴሉን ከመንግስት ቁጥጥር ወደ ነፃ ገበያ መርህ ለመቀየር በሚያደርገው ጉዞ፣ የመሰረተ ልማት ጉድለቶችን ለመሙላት እና የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ለማረጋጋት በመደበኛው የስራ ዘርፍ ላይ በሚጣል የገቢ ግብር ላይ በእጅጉ ተደግፏል። ይሁን እንጂ የግብር እርከኑ የተቀረጸበት መንገድ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ ስራ አስኪያጆች እና ባለሙያዎች በፍጥነት ወደ ከፍተኛው 35 በመቶ የግብር ጣሪያ ውስጥ እንዲገቡ የሚያስገድድ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በአንጻሩ ጎረቤቶቹ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ከፍተኛውን የገቢ ግብር ተመናቸውን በ30 በመቶ የወሰኑ ሲሆን፣ ደቡብ ሱዳን ደግሞ በ15 በመቶ ዝቅተኛ ታክስ በቀጣናው የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።

​ይህ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የግብር ፖሊሲ ልዩነት በቀጣናው የሰለጠነ የሰው ኃይል ዝውውር ላይ ጫና እየፈጠረ ይገኛል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣1110🤔5👍1🙊1
"የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት የለውም!" -ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር

የፌዴራል መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት ወታደሮቹን ከምዕራብ ትግራይ ወደ ምስራቅ ትግራይ እያሠማራ መሆኑን የሕወሃት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር በዛሬው ማምሻ ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ቴሌቪዥን በተላለፈው በዚህ መግለጫ ላይ ኃላፊዋ አሜሪካ በ"አክራሪ" የሕወሃት አመራሮችና አባላት ላይ የጣለችውን የቪዛ እገዳ አስመልክተው የተናገሩ ሲሆን፥ እገዳው በግለሰቦች ላይ ሳይሆን በሕወሃት "መርሆች" ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ሕወሃት በመሠረታዊ መርሆዎቹ ላይ ፈጽሞ እንደማይደራደር አጽንዖት ሰጥተዋል።

ፈትለወርቅ አክለውም፥ የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት እንደሌለው ለአሜሪካ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብና የድርጅቱ ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕጣ ፈንታ በራስ የመወሰን መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዋ፥ የአሜሪካ ጥቅም ሊረጋገጥ የሚችለው ሕወሃትን በማስፈራራት ሳይሆን አብሮ በመስራት ብቻ እንደሆነ  አስገንዝበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18🤔8🤣7👍2
ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ70 ሚሊየን ዩሮ የረጅም ጊዜ ብድር ፈቀደች

የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱ የጀመረችውን ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለማስፈጸም የሚውል የ70 ሚሊየን ዩሮ የረጅም ጊዜ ቀላል የብድር ስምምነት ከጣሊያን ጋር ተፈራረመ።

የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በዛሬው ዕለት ተፈራርመውታል። ይህ ድጋፍ ጣሊያን ለኢትዮጵያ ለመስጠት ካቀደችው አጠቃላይ የ150 ሚሊየን ዩሮ የበጀት ድጋፍ ማዕቀፍ ውስጥ የመጀመሪያው ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።

በስምምነቱ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እንደገለጹት፤ ይህ የብድር ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነትና የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ ሁለተኛውን ምዕራፍ በስኬት ማጠናቀቋን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ይህ የገንዘብ ድጋፍም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ከጣሊያን መንግስት ጋር በኢነርጂ፣ በቡና እና በከተማ ልማት ዘርፎች ጠንካራ ትብብር እንዳላት ያወሱት አቶ አሕመድ፣ ይህ አዲስ ስምምነትም አጋር ሀገራት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሂደት ውጤታማነት ላይ ያላቸውን ከፍተኛ እምነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም፣ ኢትዮጵያ ለሶስተኛው የበጀት ድጋፍ ምዕራፍ ትግበራ ከዓለም ባንክ ጋር የአንድ ቢሊየን 450 ሚሊየን ዶላር ስምምነት መፈራረሟን በአብነት ጠቅሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1511👍2
የ29 አመቷ የአዲስ አበባ ልጅ ሜላት ኪሮስ የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክርቤት Congress በመሆን ተመርጣለች። የመጀመሪያዋ ትውልደ ኢትዮጵያ የኮንግሬስ ተመራጭ ናት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍6534🥱8🥰2🏆2🎉1👌1🤪1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
4👍2🤔1
የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ የቶታልኤነርጂስን የኢትዮጵያ ንብረቶች በሙሉ ጠቀለለ

​የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የፈረንሳዩ ቶታልኤነርጂስ ንብረቶች በሙሉ ለመጠቅለል የሚያስችለውን የግዢ ስምምነት በፓሪስ ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት ኦላ ኢነርጂ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ገበያ ውስጥ ትልቁ የውጭ ኩባንያ ያደርገዋል።

​ይህ ግዙፍ የአክሲዮን ግዢ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወደ 120 የሚጠጉ የነዳጅ ማደያዎችን፣ የ13 ሺህ ሜትር ኩብ አቅም ያለውን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እና ተያያዥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያጠቃልላል።

​በስምምነቱ ላይ የሊቢያ ዘይትና ጋዝ ሚኒስትር ከሊፋ አብዱልሳዲቅ እና የቶታልኤነርጂስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ፑያን ጨምሮ የሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ግዢው ሊቢያ በአፍሪካ አህጉር ያላትን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ እና የውጭ ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍6
አሳዛኝ ዜና
በሠሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሰዶማ ወይም ድሬ ሮቃ አካባቢ በቁጥር 23 ቀበሌ ቀስማ ጎጥ ላይ ምክኒያቱ በውል ባልታወቀ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ከ50 ያላነሱ የአርሶ አደራችን መኖሪያ ቤቶች በትላንትናው እለት ተቃጥለዋል።

የዚህ አከባቢ ህዝብ ጀግና እና አስተዋይ ህዝቦች ሲሆኑ ሀገር በፈለጋቸው ወቅትም ክንዳዘው ሳይዝል ከትላንት እስከ ዛሬ ፀንተው የቆሙ ህዝቦች ናቸው።

በመሆኑም ሁላችነም በጋራ ሆነን ወገኖቻችን አንገታቸውን መድፋት ስለሌለባቸው እንድናቋቁማቸው ጥሪየን አቀርባለሁ።

ዘመን ተሻጋሪው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24😢18💔9👍2