አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
414 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአሜሪካና ኢራን ጥቃት‼️
አዳሩን አሜሪካ በሆርሙዝ ሰርጥ ዳርቻ ላይ በሚገኘው የኢራን ቴሌኮሙኒኬሽን ተቋምና እና ሌሎች ወታደራዊ ማዕከላት ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ ኢራን በባህሬን እና በኩዬት በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም ከባድ ጉዳት አድርሳለች። ትራምፕ ኢራንን ከምድረገፅ አጠፋታለሁ የሚል ፅሁፍ ያሰፈሩ ሲሆን የኑክሌር ቦንብ ሊጠቀሙ ይሆን? የሚል ስጋት ደቅኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🤔5👍4
ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ‹‹ዘሐበሻ መረጃ የሚያገኘው ከየት እንደሆነ ይጣራልኝ›› ሲል ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረበ፡፡

በኢቢኤስ ቴሌቪዥንና የ‹‹በስንቱ›› ተከታታይ ድራማ ፕሮዲውሰር በሆነው አብሪኮም መልቲ ሚዲያ መካከል በተነሳው ውዝግብ የተነሳ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የክስ ሂደቱ ቀጥሎ ባለበት በዚህ ወቅት ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ዘ-ሐበሻን የክሱ አካል አድርጎታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የክስ ሂደቱን አስመልክቶ ዘሐበሻ ያቀረበው ዘገባ ነው፡፡

ይህንኑ ክስ በተመለከተ የፌዴራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የንግድና ኢንቨስትመንት ችሎት ያሳለፈውን ውሳኔ ከአንድ ወር በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ችሎቱ ግንቦት 4 ቀን 2018 በሰጠው ብይን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲታገድ ማድረጉን ዘግበን ነበር፡፡

ይህ መረጃ ይፋ በመሆኑ ቴሌቪዥን ጣቢያው ደስተኛ ባለመሆኑ በክሱ ውስጥ የዘሐበሻን ስም ጠርቶ አቤቱታ ማቅረቡን ሰምተናል፡፡ ከመረጃ ምንጮቻችን እንደሰማነውና ከፍርድ ቤት መዝገብ እንደተመለከትነው የኢቢኤስ ክስ ዋነኛ ጭብጥ ‹‹ዘሐበሻ ከየት መረጃውን እንዳገኘ ይጣራልኝ›› የሚል ነው፡፡ ኢቢኤስ በክሱ ላይ ፍርድ ቤቱን ከጠየቃቸው ነገሮች ውስጥ አንደኛው ይህንን በተመለከተ የተሰራጨው መረጃ ከማህበራዊ ሚዲያ እንዲጠፋ የሚል ነው፡፡ ይህንንም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትና የመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ተከታትለው እንዲያስፈፅሙለት ጠይቋል፡፡

በሁለተኛነት ያቀረበው ጥያቄ ደግሞ ‹‹ዘ-ሐበሻ ለወደፊቱ መሰል ህገ ወጥ ድርጊቶችን ከመፈፀም እንዲቆጠብ ይታዘዝልን›› የሚል መሆኑን ከመዝገቡ ላይ አይተናል፡፡

ሦስተኛው ነጥብ ደግሞ ‹‹ዘሐበሻ የተሰኘው ሚዲያ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ከማን በምን አግባብ ሊያገኝ እንደቻለ ከመግለፅ ጋር ለተከበረው ችሎት ምላሽ እንዲሰጥልን እንዲታዘዝ›› ያለው የኢቢኤስ አቤቱታ በመጨረሻም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ተገቢ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል፡፡

ኢቢኤስ ቴሌቪዝን በዚህ ብቻ ሳይወሰን የፌዴራል ወንጀል ምርመራ መምሪያና የፍትህ ሚኒስቴር በዘሐበሻ ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲያደርጉ ፍርድ ቤቱ መመሪያ እንዲሰጥም ጥያቄ ማቅረቡን ከመዝገቡ ላይ ተመልክተናል፡፡

ዘሐበሻ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችንና ድርጅቶችን የክስ ሂደትና የፍርድ ቤት ውሎ ለተከበሩ ተከታታዮቹ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በመነሳት የበስንቱ ድራማን የፍርድ ቤት ውሎ ጨምሮ የታዋቂ ሰዎችንና ድርጅቶችን የተመለከቱ የችሎት ዘገባዎችን የሰራ ሲሆን ያቀረባቸው ዘገባዎችም በግልፅ ችሎት የሚታዩ (ዝግ ያልሆኑ) ናቸው፡፡ ኢቢኤስ ቴሌቪዝን በዘሐበሻ ላይ የመሰረተው ክስ ‹‹የቀረበው መረጃ ትክክል አይደለም›› የሚል ሳይሆን ከየት መረጃውን አመጣ? የሚል መሆኑ ታዛቢዎችን አስገርሟል፡፡

via_Yenetube

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🤪8👍5
1300 ሰዎች በሙቀት ሳቢያ ሞቱ‼️
በመላው አውሮፓ በተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ ብቻ 1300 ሰዎች መሞታቸውን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።(አዩ)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔8😢4👍32
መረጃን የደበቀ የመንግሥት ኃላፊን 5 ዓመት የሚያሳስረው አዋጅ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነጻ መረጃ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።

-ዓላማው:- ሙስናን፣ ሕገ-ወጥ አሠራርን ወይም የሥራ ብቃት ማነስን ለመሸሸግ ሲሉ መረጃና ሰነድ የሚደብቁ ወይም እንዲጠፉ የሚያደርጉ የመንግሥት ኃላፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ነው።

- ቅጣቱ፦ ጥፋቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት የማንኛውም የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት የበላይ ኃላፊ፣ የመረጃ ኃላፊ ወይም ትዕዛዝ ሰጪ አካል እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ይላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍7🤣7🤪3👌1
አሜሪካ ተማሪዎቿን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነቡ ልታስደርግ ነው።

የቴክሳስ ግዛት ተማሪዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንዲያነቡ ሊያስገድድ መሆኑ ተዘግቧል።

በአሜሪካ የቴክሳስ ግዛት የትምህርት ምክር ቤት በግዛቲቱ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንዲያነቡ የሚያስገድድ አዲስ የንባብ ዕቅድ በ9 የድጋፍ በ5 የተቃውሞ ድምፅ አጽድቋል።

ከሦስት ዓመት በኋላ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ እቅድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ብቻ ሳይሆን የቻርልስ ዲከንስ “Great Expectations” እና የዊሊያም ሼክስፒር “The Tragedy of Julius Caesar” የመሳሰሉ ታዋቂ የእንግሊዝ ሥነ-ጽሑፍ ሥራዎችንም ያካትታል ነው የተባለው።

ውሳኔው በአሜሪካ ውስጥ በሃይማኖትና በመንግሥት መለያየት ላይ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል።

ደጋፊዎቹ የአይሁድ-ክርስትና እሴቶችና ባህሎች በአሜሪካ ታሪክና ምሥረታ ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው በመግለጽ ተማሪዎች ሊያውቋቸው ይገባል ይላሉ።

የቴክሳስ የትምህርት ቦርድ አባል ብራንደን ሆል “መጽሐፍ ቅዱስን ከ60 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤቶች እየመለስን ነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል ተቃዋሚዎች እቅዱ የሃይማኖት ነፃነትን የሚጎዳ፣ ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች በላይ የሚያቆም እና የአሜሪካን ባህላዊ ብዝሃነት የሚያቀል መሆኑን ይናገራሉ።

የ“Freedom Network” ዋና ዳይሬክተር ፌሊሺያ ማርቲን እቅዱ ሌሎች ሃይማኖቶችን፣ የቀደምት አሜሪካውያንን እና የተለያዩ ማህበረሰቦችን አስተዋፅኦ ችላ እንደሚል ተችታለች።

ተማሪዎች ከአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ኢየሱስ የሚናገሩ ክፍሎችን እና “የጠፋው ልጅ” የሚባለውን ምሳሌ እንዲማሩ በእቅዱ ተካትቷል።

እንዲሁም የቴክሳስ መምህራን ማህበር እቅዱ በጣም ሰፊ መሆኑን እና መምህራን ለተማሪዎቻቸው ተገቢ የሆኑ መጽሐፍትን የመምረጥ ነፃነታቸውን ሊያሳንስ እንደሚችል ገልጿል።

ይህ ውሳኔ በቴክሳስ ውስጥ ክርስቲያናዊ እሴቶችን በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ለማጠናከር ከተወሰዱ ተከታታይ እርምጃዎች አንዱ ሲሆን፤ ባለፈው ዓመትም በትምህርት ክፍሎች ውስጥ የአሥርቱ ትዕዛዛት እንዲሰቀሉ የሚያስገድድ ሕግ ተላልፎ ነበር፤ ይህም በፌዴራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ድጋፍ አግኝቷል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔውን በመደገፍ በአሜሪካ ውስጥ የሃይማኖት እሴቶችን ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፣ “ሃይማኖት ከቀድሞው የበለጠ ጠንካራ ሆኖ ወደ አገራችን ተመልሷል” ብለዋል።

በአጠቃላይ ውሳኔው በአሜሪካ የትምህርት፣ የሃይማኖት ነፃነት እና የመንግሥት-ሃይማኖት ግንኙነት ላይ ሰፊ ውይይት እንዲቀጥል አድርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
56👍8🤪6😡5🤔1🎉1👌1💯1
የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል

የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ሰኔ 22 ቀን ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በኃላ ይፋ ይደረጋል ሲል ቢሮው ማስታወቁን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ያስችላል። የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 11 እና 12 /2018 ዓ.ም  በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት ለ56,737 ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍5
"የቡና የውጭ ምንዛሬ ገቢ ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ይሰራል" ግብርና ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ቡና የውጭ ምንዛሬ ገቢን በቀጣይ አምስት ዓመት ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደሚሰራ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ተናገሩ፡፡

ለቀጣይ አምስት ዓመታት በሚተገበረው ሃገራዊ የቡና ልማት ፓኬጅ መተግበሪያ ሰነድ ይፋ ሆኗል።
አሁን ላይ የኢትዮጵያ ቡና የውጭ ምንዛሬ ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተጠቁሟል።

በቀጣይ አምስተ ዓመታት ይህንን ገቢ ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ይሰራል ሲሉ አቶ አቶ አዲሱ ገልፀዋል፡፡

እንደ ጋዜጣ ፕላስ ዘገበሰ አርሶ አደሩ አሁንም በባህላዊ እውቀት እያመረተ እንደሚገኝ ጠቅሰው በሄክታር 8 ኩንታል ምርታማነትን በቀጣይ አምስት ዓመታት ወደ 21 ኩንታል ማድረስ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2🤔2
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
2👍2
በአዲስ አበባ ከተማ የሲጋራ ቁራጭ መንገድ ላይ መጣል 2 ሺህ ብር ያስቀጣል ተባለ

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሲጋራ ቁራጭ በመንገድ፣ በአደባባይ ወይም በማንኛውም የህዝብ መገልገያ ቦታ ላይ የሚጥል ግለሰብ በ2 ሺህ ብር እንደሚቀጣ ገልጿል።ይህ እርምጃ የከተማዋን ንፅህና፣ የህዝብን ጤና ለመጠበቅ እና የትምባሆ ተጠቃሚነትን ለመቀነስ የሚደረገው የቁጥጥር አካል መሆኑ ተገልጿል።

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉእመቤት ታደሰ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ቅጣቱ የሚተገበረው በከተማ አስተዳደሩ ደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት ነው።ደንቡ የትምባሆ ምርቶችን አጠቃቀም ለመቆጣጠርና ከጭስ ነፃ የሆነ የከተማ አካባቢን ለመፍጠር የወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ 79 በመቶ የሚሆኑት የህዝብ መገልገያ ተቋማት ከጭስ ነፃ መሆናቸውን ገልጿል።በከተማዋ የአጫሾች መጠን ከ5.3 በመቶ ወደ 4.6 በመቶ መቀነሱን በመግለጽ እየተወሰዱ ያሉ የቁጥጥርና የግንዛቤ ማስጨበጫ እርምጃዎች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍7🤣4🤯1😢1🙏1👌1💯1👀1
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ገቡ፤ ጉብኝቱ በስድስት ወራት ውስጥ ለ4ኛ ጊዜ የተደረገ ነው!

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመወያየት ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።ይህ ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል በፍጥነት እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ተከትሎ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው አራተኛው ውይይት ሆኖ ተመዝግቧል።

ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ እና አብሯቸው የተጓዘው ልዑክ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ጉብኝቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን እና ስትራቴጂካዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፤ ውይይቱም በዋናነት በቀጠናዊ ደኅንነት፣ መረጋጋት እና በሶማሊያና በኢትዮጵያ የጋራ ጥቅሞች ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍4😢2
የአሜሪካው ግዙፍ የፈርኒቸር ኩባንያ ‘አሽሊ ፈርኒቸር’ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ከፈተ

በአሜሪካ የተመሰረተውና ለ80 ዓመታት ዓለም አቀፍ የፈርኒቸር ብራንድ ሆኖ የቆየው አሽሊ ፈርኒቸር  ለዩስራ ሆም በሰጠው የብቸኛ ወኪልነትና አቅራቢነት ፈቃድ መሠረት በኢትዮጵያ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በይፋ ከፍቷል።

በእለቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የዩስራ ሆም መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ዩስራ ኑርሁሴንን ጨምሮ የሁለቱ ድርጅቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና የንግድ ማኅበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የአሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ሆቴሎችና አልሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የፈርኒቸር ምርቶች ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር በመጓዝ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬና የትራንስፖርት ወጪ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ተጠቁሟል።

ከ155  ሀገራት  በላይ የሚገኘው አሽሊ ፈርኒቸር  የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስር በማጠናከርና የሀገሪቱን ገፅታ በመልካም ጎን በማሳየት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🥰4👍2
ህወሃት ምላሽ ሰጠ‼️
‹‹በትግራይ ዙሪያ የድሮን ክትትሉ ቀጥሏል›› ሕወሓት‼️

ሕወሓት ወታደራዊ ግዳጅ እየፈጸመ መሆኑን ካደ፡፡ ቡድኑ የአውሮፓ ህብረት ያወጣውን ማሳሰቢያ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፣ መሬት ላይ ያሉ እውታዎችን በመካድ፤ የፌዴራል መንግስቱ ላይ ተጨማሪ ክሶችን አቅርቧል፡፡

ህወሓት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያወጣውን መግለጫና የሰነዘረውን ወቀሳ ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ጠንከር ያለ ይፋዊ ምላሽ ሰጥቷል። የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ ህወሓት "ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት አቋቁሟል" እና "የግዳጅ ውትድርና ምልመላ እያካሄደ ነው" በማለት የሰነዘረውን ወቀሳ ያጣጣለው ድርጅቱ፣ ሕብረቱ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነታ ወደ ጎን በመተው በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሠረተ መግለጫ አውጥቷል ሲል ኮንኗል።

ህወሓት በትግራይ ውስጥ "ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት" አቋቁሟል የሚለው ወቀሳ ሙሉ በሙሉ መሠረተ ቢስ ነው ብሏል። በትግራይ ሕዝብ ስም የተቋቋመ ሌላ አዲስ ምክር ቤት እንደሌለ የገለጸው ድርጅቱ፣ ቀደም ሲል በሕግ የተመረጠው ብቸኛው የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት ከከተሞች እስከ ገጠር ማኅበረሰብ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ወደ መደበኛ ሥራው መመለሱንና ይህም በታችኛው መዋቅር በኩል ጭምር ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ አስገዳጅ ምልመላ እያካሄደ ነው መባሉ ግልጽ ያልሆነና በማስረጃ ያልተደገፈ ክስ ነው ሲል አጣጥሎታል። ይሁን እንጂ በትግራይ ዙሪያ ከፍተኛ የወታደራዊ ኃይል ስምሪት፣ ቀጣይነት ያለው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃቶችና የአየር ላይ ክትትሎች ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ፣ የክልሉ ባለሥልጣናት ሕዝቡን ከዳግም ጭፍጨፋና ከህልውና አደጋ የመጠበቅና ራሱን የመከላከል ሞራላዊና ሕጋዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18🤣4👍3🤔1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
4👍2
አፈሳው በጭምብል ሆኗል‼️
በትግራይ ክልል በሁሉም ቦታዎች አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ቀጥሏል።
ከላይ የሚታየው ምስል በዛሬው ዕለት ሰኔ 22/2018 ዓ.ም ከሺላናት የተያዙ ወጣቶች ወደ አዲ ጉዶም ፖሊስ ጣቢያ ሲወሰዱ የሚያሳይ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አፈሳውን የሚፈፅሙት ታጣቂዎች ጭምብል የለበሱ ናቸው። ህወሃት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስገዳጅ ወታደራዊ አፈሳ እያደረግሁ አይደለም ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔54🤷‍♂2👍2😢1
ተማሪዎች ውጤታቸው መመልከት ይችላሉ።

በ2018 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ይህንን ማስፈንጠሪያ https://aa.ministry.et/#/result በመጫን መመልከት ይችላሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ (ሰኔ 23) ይጀምራል‼️

የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በመላ ሀገራችን በ607 የፈተና ማዕከላት በስድስት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል::

ለፈተናው በድምሩ 563 ሺህ 501 ተፈታኞች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 257 ሺህ 45 የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው::

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3🎉3
ኢትዮጵያ ያለባትን የ1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ለመክፈል ከአበዳሪዎቿ ጋር ስምምነት ላይ ደረሰች!

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የግል አበዳሪዎች ተበድራው የነበረውን 1 ቢሊዮን ዶላር (ዩሮቦንድ) በወቅቱ መክፈል አቅቷት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ዕዳውን የምታቀልበት የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ከነበረባት 1 ቢሊዮን ዶላር ላይ የ12% ቅናሽ የተደረገላት ሲሆን በዚህ መሰረት የምትከፍለው ዕዳ ወደ 880 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሏል።

ይህንን 880 ሚሊዮን ዶላር እስከ 2029 ድረስ በ6.15% ወለድ በየደረጃው እንድትከፍል ጊዜ የተሰጣት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሳትከፍል ያሳለፈችውን 99.4 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ዕዳ ትከፍላለች።

ስምምነቱ ወደፊት ኢትዮጵያ ብድር ባስፈለጋት ጊዜ እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ድረስ በድጋሚ የመበደር መብት ወይም ዕድልን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ዋናዎቹ አበዳሪ ሀገራት (ቻይና እና ፈረንሳይ) ስምምነቱን የደገፉ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ገፅታ የሚያሻሽልና ተጨማሪ የውጭ ብድርና 1እርዳታ በቀላሉ እንድታገኝ በር የሚከፍት በመሆኑ .በገበያው ላይ ትልቅ ተስፋን ጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤪19👍7🥱4🥰1👌1🤣1
ዱባይ ለኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያ‼️
የዱባይ ፖሊስ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጨረሻ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️

​ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዲጂታል መድረኮች በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የዱባይ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በትውልድ ኢትዮጵያውያን መካከል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተደረጉ ያሉ አንዳንድ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ነው።

​የዱባይ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በጋራ ባዘጋጁት መድረክ እንደተገለጸው፣ በአረብ ኤምሬቶች የሳይበር ወንጀል ህግ መሰረት የሚከተሉት ድርጊቶች ከፍተኛ ቅጣት እንደሚያስከትሉ ተገልጿል፦

📌 ​የጥላቻ ንግግር: በማህበረሰቡ መካከል መከፋፈልን፣ ጥላቻን እና ንቀትን የሚያንጸባርቁ የብሄር ፖለቲካ ቅስቀሳዎችን ሶሻል ሚዲያ ላይ መለጠፍ።

📌 ​ስድብ እና ስም ማጥፋት: ግለሰቦችን ወይም ተቋማትን በቪዲዮ፣ በጽሁፍ ወይም በኮሜንት መዝለፍ እና ስም ማጥፋት ህግ የተከለከለ ነው።

📌 ​ያለ ፈቃድ መረጃ ማውጣት: የግለሰቦችን ግላዊነት የሚነኩ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም መረጃዎችን ያለ ፈቃድ ማሰራጨት በህግ የሚያስቀጣ ነው።

📌 ​የገንዘብ ማሰባሰብ: ያለ መንግስት ፈቃድ በማህበራዊ ሚዲያ በኩል በስምምነት ገንዘብ ማሰባሰብ በኢምሬትስ ህግ የተከለከለ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍109🤔1