ኢትዮጵያ፣ አውሮፓ ኅብረት ወደ አገራቸው ሊባረሩ የማይችሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጣቸው አገራት መካከል አንዷ መኾኗን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጠ።
ተቋሙ፣ ኅብረቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሦስተኛ አገራት ለመላክ አዲስ ስልቶችን እየቀየሠ ይገኛል በማለት ወቅሷል።
ጀርመን፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ፣ ግሪክ እና ኔዘርላንድስ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጧቸው አገራት መካከል፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቱኒዚያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ እና ሞሪቴኒያ እንደሚገኙበት ተቋሙ ጠቅሷል።
ተቋሙ፣ ተቀባይ አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎቹን ሰብዓዊ መብት ያከብሩ፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ይመልሷቸው ወይም ያስሯቸው እንደኾነ ግልጽ አይደለም ሲል ስጋቱን ገልጧል።
የኅብረቱ አገራት ይህንኑ እቅድ እንዲተውት ያሳሰበው ተቋሙ፣ ይህ ካልሆነ ግን እቅዱ ተግባራዊ ከመኾኑ በፊት ኅብረቱ ቢያንስ በተቀባይ አገራት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ጥብቅ ግምገማ እንዲያደርግ እቅዱን የሚቃወሙት የፈረንሳይና ስፔን መሪዎች ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
@Addis_Reporter

❤20👍4🤣3🤔1🙊1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
69000 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም‼️
📌1500+ ሞተዋል፣69000 የደረሱበት አልታወቀም።
በቬኔዝዌላ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 1,500+ ደርሷል።
በዚህ ሳምንት በቬኔዝዌላ በተከሰተው አውዳሚ ድርብ የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ ከ 1,500 በላይ መድረሱን የሀገሪቱ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆርጌ ሮድሪጌዝ (Jorge Rodríguez) ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ 69,000 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።

❤15💔15😢4👍3😱2
ፔን ኢንተርናሽናል፣ የኤርትራ መንግሥት ዳዊት ይስሃቅንና አማኑኤል አስራትን ጨምሮ ላለፉት 25 ዓመታት ያሠራቸው 12 ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች "በሕይወት ስለመኖራቸው" ማረጋገጫ እንዲሠጥና "ተጠያቂነት" እና "ፍትሕ" እንዲያሠፍን አዲስ በጀመረው ዓለማቀፍ ዘመቻ ጠየቀ።
ጋዜጠኞቹና ጦማሪዎቹ የታሠሩት፣ "ሀሳባቸውን በመግለጣቸው" እና "መንግሥታዊ ማሻሻያ" እንዲደረግ በመጠየቃቸው መኾኑን ተቋሙ ገልጧል።
ተቋሙ፣ በሚስጢራዊ እስር ቤት የታሠሩት ጋዜጠኞቹና ጦማሪዎቹ ከጠበቃ ወይም ቤተሰብ ጋር ተገናኝተውም ኾነ የሕክምና ድጋፍ አግኝተው እንደማያውቁ ጠቅሷል።
የኤርትራ መንግሥት ታሳሪዎቹ በሕይወት መኖራቸውን እንዲያረጋግጥና ያሉበትን ቦታ እንዲያሳውቅ ለመጠየቅ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሚላክ ግልጽ ደብዳቤ ላይ የመብት ተቆርቋሪ ወገኖች ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ጠይቋል።

❤11👍6🤔1👌1
መረጃ‼️
አውሮፓ ኅብረት፣ ሕወሃት በተናጥል የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ይጥሳል ሲል ትናንት ባወጣው አጭር መግለጫ ስጋቱን ገለጠ።
ኅብረቱ፣ ሕወሓት "ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት" ለማቋቋም የወሠደውን ርምጃ ጨምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው "ውጥረት" እንዳሳሰበው ገልጧል።
ሁሉም ወገኖች በግጭት ማቆም ስምምነቱ ተጨባጭ አተገባበር ዙሪያ ንግግር የመጀመራቸው ጉዳይ "አጣዳፊ" መኾኑን ኅብረቱ አጽንዖት ሠጥቷል።
ኅብረቱ፣ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ "ሰላም" እና "መረጋጋት" እንዲሠፍን የሚያደርጉትን ጥረት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍም አረጋግጧል።

❤6🤣3👍2🙊1
ትራምፕ በምስላቸው ያጌጠ አዲስ ፓስፖርት ይፋ አደረጉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሀገሪቱን 250ኛ የነጻነት በዓል ለማዘከር የተዘጋጀ ልዩና ውስን የፓስፖርት ዲዛይን ይፋ አድርገዋል።
“አርበኛዊ ባዊ ፓስፖርት” (Patriotic Passport) የተሰኘው ይህ ፓስፖርት፣ በትራምፕ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ የቀረበ ሲሆን የፕሬዝዳንቱን ምስል እና ፊርማ አካትቷል።
በጀርባው ላይ ደግሞ የ1776ቱ የነጻነት አዋጅ ፊርማ ስነ-ስርዓት ምስል እና “Welcome, but be good!” (እንኳን ደህና መጡ፣ ግን መልካም ሁኑ!) የሚል መልዕክት ተጽፎበታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በትራምፕ የታሪፍ ዛቻ ዙሪያ ከአውሮፓ ህብረት ጠንከር ያለ ምላሽ ተሰጥቷል።
ህብረቱ ትራምፕ ታሪፍ ከጣሉ ፈጣንና ወሳኝ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

❤15🤪13👍3🥰2
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

❤3👍2
የሆሳዕናው የውሻ ግድያ 2 ህጻናት ተማሪዎች በእብድ ውሻ በሽታ መሞታቸውን ተከቶሎ የተፈፀመ ነው‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በራቢስ (የእብድ ውሻ) በሽታ ምክንያት ከአንድ ቤት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ጨምሮ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ፣ በነዋሪዎችና በእድር አማካኝነት ሰፊ የውሻ ግድያ ዘመቻ መጀመሩ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። በከተማዋ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት መረጃ መሠረት በሆሳዕና ከተማ ውስጥ በአጠቃላይ ከ 10,500 በላይ ውሾች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 7,500 የሚሆኑት ባለቤት ያላቸው ሲሆኑ 7,200 ያህሉ የተከተቡ ናቸው።
ይሁን እንጂ ቀሪዎቹ 3,000 የሚጠጉት ውሾች ባለቤት የሌላቸውና በየአደባባዩ የሚገኙ በመሆናቸው ለበሽታው መስፋፋትና ለሕዝብ ስጋት ዋነኛ ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል።
የሰው ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ በተፈጠረ ድንጋጤ ነዋሪዎች ጤነኛ የሆኑና የተከተቡ የቤት ውሾችን ጭምር በገመድ በማነቅና በተለያዩ መሣሪያዎች በጭካኔ እየገደሉ መሆኑን የገለጹት የከተማው ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ለፋሞ፣ ይህ ዓይነቱ ድርጊት የእንስሳትን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1376/2017 የሚጻረርና በሕግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ድርጊቱን የማስቆም ሥራ እየተሠራ መሆኑንና ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጥፋተኞችን ለመለየት መረጃ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

❤14😡11👍5😢2💔2
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ!
አሸናፊዎቹ ወደ ካናዳ ያመራሉ!
የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከጆርካ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ከ200 በላይ ድንቅ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።
ከሰኔ 17 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ የቆየዉ ይህ ታላቅ ብሔራዊ ውድድር፣ ዛሬ በተደረገው ማራኪና አጓጊ የጎዳና ላይ ፉክክር ፍጻሜውን አግኝቷል።
ይህ ውድድር በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና (ሀCI) ላይ ሀገራችንን ወክለው የሚሳተፉ ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ የተደረገ ዋና መድረክ በመሆኑ በከፍተኛ የፉክክር መንፈስ የተከናወነ ሲሆን፣ ዛሬ በወንዶችም በሴቶችም አሸናፊ የሆኑት ስፖርተኞች ወደ ካናዳ የሚያመሩ ይሆናል።
ዛሬ ረፋድ ላይ መነሻውን ቦሌ ኤድናሞል (ከሸገር ሕንፃ አጠገብ) አድርጎ በተካሄደው የፍጻሜ ውድድር ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርየስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዩ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን እና የአፍሪካ ብስክሌት ኮንፌደሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ሐይሌ፣ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ኃላፊዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በስፍራው ተገኝተው ውድድሩን አስጀምረዋል።
እልህ አስጨራሽ በነበረውና 80 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የሴቶች ኤሊት የመንገድ ውድድር፣ በተለይም የመጨረሻዎቹን ሦስት ዙሮች ብቻዋን በሰፊ ልዩነት በመምራት ብስክሌተኛዋ ቤተልሔም ዳንኤል አንደኛ በመሆን ዉድድሩን አጠናቃለች።
በሌላ በኩል፣ 140 ኪሎ ሜትር በሸፈነውና ከፍተኛ ትንቅንቅ በታየበት የወንዶች ኤሊት የመንገድ ውድድር ብስክሌተኛው ፊሊሞን ዘርአ ብሩክ ተፎካካሪዎቹን በብቃት በመቅደም በአንደኝነት አጠናቋል።
ባለፉት ዓመታት በተደረጉ መሰል ብሔራዊ ሻምፒዮናዎች ላይ የተገኙ ውጤቶች ስፖርተኞቻችን በጀርመን እና በቻይና ፕሮፌሽናል ክለቦችን እንዲቀላቀሉ ዕድል የፈጠሩ ሲሆን፣ የዛሬው ውድድርም ለአሸናፊዎቹ የዓለም ሻምፒዮና በርከመክፈቱ ባሻገር ለቀጣይ ዓለም አቀፍ የፕሮፌሽናል ዕድሎች ትልቅ መሠረት እንደሚሆን ተጠቅሷል።
በውድድሩ ማጠቃለያ ላይም ለዚህ ታላቅ ብሔራዊ ስፖርታዊ ኩነት መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የተለያዩ አካላትና ደጋፊዎች የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።

👍8❤5👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአሜሪካና ኢራን ጥቃት‼️
አዳሩን አሜሪካ በሆርሙዝ ሰርጥ ዳርቻ ላይ በሚገኘው የኢራን ቴሌኮሙኒኬሽን ተቋምና እና ሌሎች ወታደራዊ ማዕከላት ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ ኢራን በባህሬን እና በኩዬት በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም ከባድ ጉዳት አድርሳለች። ትራምፕ ኢራንን ከምድረገፅ አጠፋታለሁ የሚል ፅሁፍ ያሰፈሩ ሲሆን የኑክሌር ቦንብ ሊጠቀሙ ይሆን? የሚል ስጋት ደቅኗል።

❤11🤔5👍4
ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ‹‹ዘሐበሻ መረጃ የሚያገኘው ከየት እንደሆነ ይጣራልኝ›› ሲል ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረበ፡፡
በኢቢኤስ ቴሌቪዥንና የ‹‹በስንቱ›› ተከታታይ ድራማ ፕሮዲውሰር በሆነው አብሪኮም መልቲ ሚዲያ መካከል በተነሳው ውዝግብ የተነሳ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የክስ ሂደቱ ቀጥሎ ባለበት በዚህ ወቅት ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ዘ-ሐበሻን የክሱ አካል አድርጎታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የክስ ሂደቱን አስመልክቶ ዘሐበሻ ያቀረበው ዘገባ ነው፡፡
ይህንኑ ክስ በተመለከተ የፌዴራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የንግድና ኢንቨስትመንት ችሎት ያሳለፈውን ውሳኔ ከአንድ ወር በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ችሎቱ ግንቦት 4 ቀን 2018 በሰጠው ብይን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲታገድ ማድረጉን ዘግበን ነበር፡፡
ይህ መረጃ ይፋ በመሆኑ ቴሌቪዥን ጣቢያው ደስተኛ ባለመሆኑ በክሱ ውስጥ የዘሐበሻን ስም ጠርቶ አቤቱታ ማቅረቡን ሰምተናል፡፡ ከመረጃ ምንጮቻችን እንደሰማነውና ከፍርድ ቤት መዝገብ እንደተመለከትነው የኢቢኤስ ክስ ዋነኛ ጭብጥ ‹‹ዘሐበሻ ከየት መረጃውን እንዳገኘ ይጣራልኝ›› የሚል ነው፡፡ ኢቢኤስ በክሱ ላይ ፍርድ ቤቱን ከጠየቃቸው ነገሮች ውስጥ አንደኛው ይህንን በተመለከተ የተሰራጨው መረጃ ከማህበራዊ ሚዲያ እንዲጠፋ የሚል ነው፡፡ ይህንንም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትና የመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ተከታትለው እንዲያስፈፅሙለት ጠይቋል፡፡
በሁለተኛነት ያቀረበው ጥያቄ ደግሞ ‹‹ዘ-ሐበሻ ለወደፊቱ መሰል ህገ ወጥ ድርጊቶችን ከመፈፀም እንዲቆጠብ ይታዘዝልን›› የሚል መሆኑን ከመዝገቡ ላይ አይተናል፡፡
ሦስተኛው ነጥብ ደግሞ ‹‹ዘሐበሻ የተሰኘው ሚዲያ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ከማን በምን አግባብ ሊያገኝ እንደቻለ ከመግለፅ ጋር ለተከበረው ችሎት ምላሽ እንዲሰጥልን እንዲታዘዝ›› ያለው የኢቢኤስ አቤቱታ በመጨረሻም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ተገቢ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል፡፡
ኢቢኤስ ቴሌቪዝን በዚህ ብቻ ሳይወሰን የፌዴራል ወንጀል ምርመራ መምሪያና የፍትህ ሚኒስቴር በዘሐበሻ ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲያደርጉ ፍርድ ቤቱ መመሪያ እንዲሰጥም ጥያቄ ማቅረቡን ከመዝገቡ ላይ ተመልክተናል፡፡
ዘሐበሻ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችንና ድርጅቶችን የክስ ሂደትና የፍርድ ቤት ውሎ ለተከበሩ ተከታታዮቹ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በመነሳት የበስንቱ ድራማን የፍርድ ቤት ውሎ ጨምሮ የታዋቂ ሰዎችንና ድርጅቶችን የተመለከቱ የችሎት ዘገባዎችን የሰራ ሲሆን ያቀረባቸው ዘገባዎችም በግልፅ ችሎት የሚታዩ (ዝግ ያልሆኑ) ናቸው፡፡ ኢቢኤስ ቴሌቪዝን በዘሐበሻ ላይ የመሰረተው ክስ ‹‹የቀረበው መረጃ ትክክል አይደለም›› የሚል ሳይሆን ከየት መረጃውን አመጣ? የሚል መሆኑ ታዛቢዎችን አስገርሟል፡፡
via_Yenetube

❤10🤪8👍5
1300 ሰዎች በሙቀት ሳቢያ ሞቱ‼️
በመላው አውሮፓ በተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ ብቻ 1300 ሰዎች መሞታቸውን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።(አዩ)
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
በመላው አውሮፓ በተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ ብቻ 1300 ሰዎች መሞታቸውን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።(አዩ)
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔8😢4👍3❤2
መረጃን የደበቀ የመንግሥት ኃላፊን 5 ዓመት የሚያሳስረው አዋጅ ጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነጻ መረጃ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
-ዓላማው:- ሙስናን፣ ሕገ-ወጥ አሠራርን ወይም የሥራ ብቃት ማነስን ለመሸሸግ ሲሉ መረጃና ሰነድ የሚደብቁ ወይም እንዲጠፉ የሚያደርጉ የመንግሥት ኃላፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ነው።
- ቅጣቱ፦ ጥፋቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት የማንኛውም የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት የበላይ ኃላፊ፣ የመረጃ ኃላፊ ወይም ትዕዛዝ ሰጪ አካል እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ይላል።

❤14👍7🤣7🤪3👌1
አሜሪካ ተማሪዎቿን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነቡ ልታስደርግ ነው።
የቴክሳስ ግዛት ተማሪዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንዲያነቡ ሊያስገድድ መሆኑ ተዘግቧል።
በአሜሪካ የቴክሳስ ግዛት የትምህርት ምክር ቤት በግዛቲቱ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንዲያነቡ የሚያስገድድ አዲስ የንባብ ዕቅድ በ9 የድጋፍ በ5 የተቃውሞ ድምፅ አጽድቋል።
ከሦስት ዓመት በኋላ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ እቅድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ብቻ ሳይሆን የቻርልስ ዲከንስ “Great Expectations” እና የዊሊያም ሼክስፒር “The Tragedy of Julius Caesar” የመሳሰሉ ታዋቂ የእንግሊዝ ሥነ-ጽሑፍ ሥራዎችንም ያካትታል ነው የተባለው።
ውሳኔው በአሜሪካ ውስጥ በሃይማኖትና በመንግሥት መለያየት ላይ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል።
ደጋፊዎቹ የአይሁድ-ክርስትና እሴቶችና ባህሎች በአሜሪካ ታሪክና ምሥረታ ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው በመግለጽ ተማሪዎች ሊያውቋቸው ይገባል ይላሉ።
የቴክሳስ የትምህርት ቦርድ አባል ብራንደን ሆል “መጽሐፍ ቅዱስን ከ60 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤቶች እየመለስን ነው” ብለዋል።
በሌላ በኩል ተቃዋሚዎች እቅዱ የሃይማኖት ነፃነትን የሚጎዳ፣ ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች በላይ የሚያቆም እና የአሜሪካን ባህላዊ ብዝሃነት የሚያቀል መሆኑን ይናገራሉ።
የ“Freedom Network” ዋና ዳይሬክተር ፌሊሺያ ማርቲን እቅዱ ሌሎች ሃይማኖቶችን፣ የቀደምት አሜሪካውያንን እና የተለያዩ ማህበረሰቦችን አስተዋፅኦ ችላ እንደሚል ተችታለች።
ተማሪዎች ከአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ኢየሱስ የሚናገሩ ክፍሎችን እና “የጠፋው ልጅ” የሚባለውን ምሳሌ እንዲማሩ በእቅዱ ተካትቷል።
እንዲሁም የቴክሳስ መምህራን ማህበር እቅዱ በጣም ሰፊ መሆኑን እና መምህራን ለተማሪዎቻቸው ተገቢ የሆኑ መጽሐፍትን የመምረጥ ነፃነታቸውን ሊያሳንስ እንደሚችል ገልጿል።
ይህ ውሳኔ በቴክሳስ ውስጥ ክርስቲያናዊ እሴቶችን በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ለማጠናከር ከተወሰዱ ተከታታይ እርምጃዎች አንዱ ሲሆን፤ ባለፈው ዓመትም በትምህርት ክፍሎች ውስጥ የአሥርቱ ትዕዛዛት እንዲሰቀሉ የሚያስገድድ ሕግ ተላልፎ ነበር፤ ይህም በፌዴራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ድጋፍ አግኝቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔውን በመደገፍ በአሜሪካ ውስጥ የሃይማኖት እሴቶችን ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፣ “ሃይማኖት ከቀድሞው የበለጠ ጠንካራ ሆኖ ወደ አገራችን ተመልሷል” ብለዋል።
በአጠቃላይ ውሳኔው በአሜሪካ የትምህርት፣ የሃይማኖት ነፃነት እና የመንግሥት-ሃይማኖት ግንኙነት ላይ ሰፊ ውይይት እንዲቀጥል አድርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

❤56👍8🤪6😡5🤔1🎉1👌1💯1
የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል
የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ሰኔ 22 ቀን ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በኃላ ይፋ ይደረጋል ሲል ቢሮው ማስታወቁን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ያስችላል። የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 11 እና 12 /2018 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት ለ56,737 ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

❤13👍5
"የቡና የውጭ ምንዛሬ ገቢ ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ይሰራል" ግብርና ሚኒስቴር
የኢትዮጵያ ቡና የውጭ ምንዛሬ ገቢን በቀጣይ አምስት ዓመት ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደሚሰራ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ተናገሩ፡፡
ለቀጣይ አምስት ዓመታት በሚተገበረው ሃገራዊ የቡና ልማት ፓኬጅ መተግበሪያ ሰነድ ይፋ ሆኗል።
አሁን ላይ የኢትዮጵያ ቡና የውጭ ምንዛሬ ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተጠቁሟል።
በቀጣይ አምስተ ዓመታት ይህንን ገቢ ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ይሰራል ሲሉ አቶ አቶ አዲሱ ገልፀዋል፡፡
እንደ ጋዜጣ ፕላስ ዘገበሰ አርሶ አደሩ አሁንም በባህላዊ እውቀት እያመረተ እንደሚገኝ ጠቅሰው በሄክታር 8 ኩንታል ምርታማነትን በቀጣይ አምስት ዓመታት ወደ 21 ኩንታል ማድረስ ይጠበቃል።

❤9👍2🤔2
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
❤2👍2
በአዲስ አበባ ከተማ የሲጋራ ቁራጭ መንገድ ላይ መጣል 2 ሺህ ብር ያስቀጣል ተባለ
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሲጋራ ቁራጭ በመንገድ፣ በአደባባይ ወይም በማንኛውም የህዝብ መገልገያ ቦታ ላይ የሚጥል ግለሰብ በ2 ሺህ ብር እንደሚቀጣ ገልጿል።ይህ እርምጃ የከተማዋን ንፅህና፣ የህዝብን ጤና ለመጠበቅ እና የትምባሆ ተጠቃሚነትን ለመቀነስ የሚደረገው የቁጥጥር አካል መሆኑ ተገልጿል።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉእመቤት ታደሰ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ቅጣቱ የሚተገበረው በከተማ አስተዳደሩ ደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት ነው።ደንቡ የትምባሆ ምርቶችን አጠቃቀም ለመቆጣጠርና ከጭስ ነፃ የሆነ የከተማ አካባቢን ለመፍጠር የወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ 79 በመቶ የሚሆኑት የህዝብ መገልገያ ተቋማት ከጭስ ነፃ መሆናቸውን ገልጿል።በከተማዋ የአጫሾች መጠን ከ5.3 በመቶ ወደ 4.6 በመቶ መቀነሱን በመግለጽ እየተወሰዱ ያሉ የቁጥጥርና የግንዛቤ ማስጨበጫ እርምጃዎች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን አመልክቷል።

❤19👍7🤣4🤯1😢1🙏1👌1💯1👀1
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ገቡ፤ ጉብኝቱ በስድስት ወራት ውስጥ ለ4ኛ ጊዜ የተደረገ ነው!
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመወያየት ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።ይህ ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል በፍጥነት እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ተከትሎ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው አራተኛው ውይይት ሆኖ ተመዝግቧል።
ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ እና አብሯቸው የተጓዘው ልዑክ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ጉብኝቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን እና ስትራቴጂካዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፤ ውይይቱም በዋናነት በቀጠናዊ ደኅንነት፣ መረጋጋት እና በሶማሊያና በኢትዮጵያ የጋራ ጥቅሞች ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

❤5👍4😢2
የአሜሪካው ግዙፍ የፈርኒቸር ኩባንያ ‘አሽሊ ፈርኒቸር’ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ከፈተ።
በአሜሪካ የተመሰረተውና ለ80 ዓመታት ዓለም አቀፍ የፈርኒቸር ብራንድ ሆኖ የቆየው አሽሊ ፈርኒቸር ለዩስራ ሆም በሰጠው የብቸኛ ወኪልነትና አቅራቢነት ፈቃድ መሠረት በኢትዮጵያ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በይፋ ከፍቷል።
በእለቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የዩስራ ሆም መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ዩስራ ኑርሁሴንን ጨምሮ የሁለቱ ድርጅቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና የንግድ ማኅበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
የአሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ሆቴሎችና አልሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የፈርኒቸር ምርቶች ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር በመጓዝ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬና የትራንስፖርት ወጪ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ተጠቁሟል።
ከ155 ሀገራት በላይ የሚገኘው አሽሊ ፈርኒቸር የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስር በማጠናከርና የሀገሪቱን ገፅታ በመልካም ጎን በማሳየት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

❤11🥰4👍2