‹‹TDF እየሸሸ ነው፤ አልዋጋም ብሏል›› ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ‼️
‹‹ቲዲኤፍ የሚባለው ጦር እየሸሸ ቤቱ ተቀምጧል፤ አልዋጋም ብሏል፤ ትግራይ ያሉ መሪዎች ከሻብያ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው የጦርነት ፍላጎታቸውን አልተዉም፤ ነገር ግን አቅማቸው ስለተመናመነ እየወላወሉ ነው፡፡ በፊት ማስተዳደር በቻሉበት አቅም ማስተዳደር ስላልቻሉ አፋኝ ሕግ አውጥተው ማስተዳደር ነው የሚፈልጉት፤ ቀደም ሲል የሰሩት ወንጀል ለመሸፈን ሌላ ወንጀል እየሰሩ እንዳለ ይሰማኛል፡፡
ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ በዛሬው ዕለት የተናገሩት
@Addis_Reporter

👍20❤8🤣6🤪4🙉2👌1
ታሞ ሊጠይቁት አስራ ሰባት ፍቅረኛሞቹ ሆስፒታል የመጡበት የቻይናዊው አስገራሚ ታሪክ
በፈረንጆቹ 2015 ሚስተር ዩዋን የተባለ ቻይናዊ ሰው በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ሆስፒታል ይገባል።
ይሁንና አደጋው በአካባቢው የዜና ማሰራጫዎች ላይ መተላለፉን ተከትሎ፣ ያላሰበው አስገራሚ ትዕይንት በሆስፒታሉ ውስጥ ተፈጠረ።
ሊጠይቁት የመጡ 17 ፍቅረኛሞቹ በአንድ ጊዜ አልጋው አጠገብ ተገኙ!
ሁሉም ሴቶች እርስ በርሳቸው በፍጹም አይተዋወቁም የነበረ ሲሆን፥ አንዳንዶቹ ከዩዋን ጋር ለዓመታት የዘለቀ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው ታውቋል።
ይህ ሚስጥር በአንድ አደጋ ምክንያት በአደባባይ በመጋለጡ፣ በሆስፒታሉ የነበሩ ታካሚዎችና ነርሶች በሁኔታው በእጅጉ ተገርመዋል።
ፍቅረኛሞቹም ጉዳዩን ሲረዱ በከፍተኛ ድንጋጤ እና ቁጣ ውስጥ ወድቀው ነበር።

🤣36❤15👍4🤪3😈2🤔1👀1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥
🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።
የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia

❤2👍2
ጥይት ወደውጪ መላክ ተጀመረ‼️
ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ጥይት በመሸጥ የውጪ ምንዛሬ እየተገኘ መሆኑ ተዘገበ።
ከወራት በፊት በአገር ውስጥ ጥይት ማምረት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ገልፀው ነበር፡፡
መከላከያ ሰራዊት ትናንት ባጋራው መረጃ በአገር ውስጥ የሚመረተው ጥይት የውጪ ምንዛሬ እያስገኘ መሆኑን ገልጧል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ በያዘችው የለውጥ ጉዞ የጸጥታ መዋቅሯን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማደራጀት እና ወታደራዊ ቁሶችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ለመገንባት የሚያስችል ታሪካዊ እርምጃ ወስዳለች›› የሚለው ሰራዊቱ፤ ይህ አካሄድ ሀገሪቱ በወታደራዊ አቅም ረገድ የነበራትን የውጭ ጥገኝነት በመቀነስ የራሷን የጸጥታ ፍላጎት በራሷ አቅም የምትፈታበትን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል ብሏል።
በዚህ ረገድ መንግሥት ድሮን ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ የማልማት እና የመገጣጠም ሥራን በስፋት እየተገበረ ይገኛል።
የድሮን ማዕከላት መቋቋም እና በሥራ ላይ መዋል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአየር ክልሉን በአስተማማኝ ሁኔታ በመቆጣጠር እና የጸጥታ ስጋቶችን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ አስችሎታል ብሏል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ለቀላል እና ለከባድ የጦር መሣሪያዎች የሚያስፈልጉ ጥይቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመራቸው ሌላው ትልቅ ስኬት ነው ያለም ሲሆን፤ ‹‹ይህም በድንገተኛ የጸጥታ ተግዳሮቶች ጊዜ የጦር መሣሪያ እና ጥይት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም ዋስትና ከመስጠቱም በላይ፣ ለውጭ ግዥ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማዳን አግዟል፤ ከዚያም አልፎ ሀገር ውስጥ የተመረተውን ጥይት ወደ ጎረቤት ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት ተጀምሯል›› በማለት አብራርቷል፡፡
Via : አንዳፍታ

🤣45❤19🌚6👍5🤪2👌1👀1
በኦሬንጅ ጁስ የታመሙት ተማሪዎች‼️
ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጉ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኦሬንጅ ጁስ ከሱቅ ገዝተው የጠጡ በሙሉ ራሳቸውን ስተው ህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል‼️
ዛሬ ሰኔ 19/2018 ዓ/ም በደቡብ ኣሪ ወረዳ በመፀር መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከአንድ ግለሰብ አነስተኛ ሱቅ የኦሬንጅ ጁስ ገዝተው የጠጡና ከኦሬንጁ ጋር ንክክ የነበራቸው ተማሪዎች ላይ በደረሰው የጤና መታወክ ምክንያት ቁጥራቸው 200 የሚጠጉ ተማሪዎች በጋዜር እና በጂንካ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ትምህርት ቤቱ አስታዉቋል።
በትምህርት ቤቱ አንድ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ከሱቅ የኦሬንጅ ጁስ ገዝታ ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ካመጣች በኃላ ኦሬንጁን የጠጡና ያሸተቱ በሙሉ ራሳቸውን ስተው መውደቅ መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ሀብታሙ ካልሚ ለኣሪ ማህበረሰብ ሬዲዮ ገልፀዋል።
ተማሪዎች ኦሬንጁን የቀመሱና ያሸተቱ በሙሉ መውደቅ ስጀምር በመፀር ጤና ጣቢያ ጊዜያዊ ማስታገሻ የሕክምና እርዳታ ቢሰጥም ከአቅም በላይ መሆን ሲጀምር ተማሪዎች ወደ ጋዜር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መላኩን ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል።
የደቡብ አሪ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ሀሴን ገዛኸኝ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተማሪዎች በጋዜር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ በመጥቀስ ከአቅም በላይ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ጂንካ ሆስፒታል መላካቸውን ተናግረዋል።
ተማሪዎች የጠጡት ኦሬንጅ ጁስ ምርምራ እንደሚደረግ እና ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንደሆነ በመግለፅ መረጃው ተጣርቶ ሲጠናቀቅ ለሕዝብ ለማሳወቅ እየሰሩ እንደሆነም ጠቅሰዋል።(አዩ)

❤22😢10👍6💔5🤯2😱2🙈2👀1🙉1
መረጃ‼️
ቻይና፣ የኢትዮጵያ የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ያዥ ኢንቨስተሮች በቦንዱ አከፋፈል ዙሪያ የተፈጠረውን ውዝግብ ወደ ፍርድ ቤት እንወስዳለን በማለት መዛታቸውን የፓሪስ ክለብ ሰሞኑን ባወጣው አንድ ሪፖርት ላይ ተቸ።
ፓሪስ ክለብ፣ ቡድን 20 የታዳጊ አገራትን እዳ መልሶ ለማዋቀር ያወጣውን ማዕቀፍ "የተፋጠነ ውሳኔ" እንዲሠጥ ለማድረግ ማሻሻያ እንዲደረግበት በሪፖርቱ ጠይቋል።
ኢትዮጵያ 40 በመቶ ቦንድ ያዥ ኢንቨስተሮችን ከሚወክል ኮሚቴ ጋር በቦንዱ አከፋፈል ዙሪያ ከወራት በፊት የደረሠችበትን ስምምነት፣ የአበዳሪ አገራት ኮሚቴ 'ሁሉም አበዳሪዎች በእኩል መታየት አለባቸው' ከሚለው የእዳ ማሸጋሸጊያ ማዕቀፍ መርህ ጋር ይጣረሳል በማለት ውድቅ እንዳደረገው አይዘነጋም።
ይህንኑ ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ አዲስ ሀሳብ ብታቀርብም፣ የቦንድ ያዦች ኮሚቴ ሀሳቡን አልተቀበለውም።
ኢትዮጵያና የአበዳሪ አገራት ኮሚቴ እዳን መልሶ ለማዋቀር ባለፈው ዓመት ሐምሌ በደረሱበት የመግባቢያ ስምምነት መሠረት፣ ፈረንሳይና ጣሊያን የአገሪቱን እዳ መልሠው ለማዋቀር ከመንግሥት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።

❤12😡3👍2
#NewsAlert ‼️
ለህውሃት ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ‼ የአሜሪካ ኤምባሲ የሰላም ሂደቱን በሚያደናቅፉ አካላት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼
የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ በትግራይ ክልል የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ አካላት ከአፍሪካ ህብረት የውይይት ጥረት ጋር በአስቸኳይ እንዲተባበሩና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳሰበ።
ይህ መግለጫ የወጣው አሜሪካ “አክራሪ” ባላቸው የህወሓት አባላት ላይ የቪዛ ገደብ በጣለች በሳምንቱ ሲሆን፣ ህወሓት በበኩሉ የፕሪቶሪያው ስምምነት መፍረሱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል።

👍11❤10🤪8🤷♂2👌1🤝1
ውሻዉን ያልገደለ ግለሰብ በ50000 ብር እና በእስራት እንዲቀጣ ታውጇል‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሆሳና ከተማ እያንዳንዱ ግለሰብ በቤቱ ያለዉን ዉሻ አውጥቶ እንዲገድል በታወጀው መሰረት
ዉሻ ያላቸው ግለሰቦች ዉሻቸውን ገመድ በማጥለቅ በንንጨት ላይ በማንጠልጠል ዉሾችን እየገደሉ ይገኛሉ።
በከተማው ከሰሞኑ በውሻ ምክንያት በሽታ ተከስቷል የተባለ ሲሆን ይህ የውሻ ግድያ ዘመቻ የተጀመረው አንድ ውሻ የ13 አመት ልጅ ነክሳው ከሞተ በኋላ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
Via : አዩዘሀበሻ

😢57💔28❤8🤷♂8🤣3👍1😱1👀1💊1
የቡና ኮንትሮባንድን ለመግታት እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣትና የንብረት መወረስ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በሆነው የቡና ምርት ላይ የሚፈጸመውን ህገ-ወጥ ዝውውር (ኮንትሮባንድ) ለመግታት፣ ከተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት እጅግ ጥብቅ የሆኑ የቁጥጥርና የቅጣት እርምጃዎችን መተግበር መጀመሩን አስታወቀ።
የቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዶር ሰፊሳ አባቡ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ የቡና ንግድ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በእጅጉ እየጎዳ በመሆኑ፣ ድርጊቱን በቁርጠኝነት ለመከላከል አዲስ የክትትል ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል
በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ ህገ-ወጥ የቡና ዝውውርን ለማስቆም ከፌዴራልና ክልል ፖሊስ፣ ከጉምሩክ ባለስልጣን እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።
በመሆኑም ያለ ህጋዊ ፈቃድና ሰነድ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የቡና ምርት ሙሉ በሙሉ ይወረሳል።
በህገ-ወጥ የቡና ሰንሰለት ውስጥ ተሳትፈው በሚገኙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ም እንደ ጥፋታቸው ደረጃ እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ይጣላል።
የኬላዎች ቁጥጥርን በተመለከተም በመረጃዎችን በፈጣን ቴክኖሎጂ በመለዋወጥ፣ በዋና ዋና የቡና አምራች ክልሎችና መውጫ ኬላዎች ላይ ፍተሻዎች ተጠናክረዋል ሲሉ ዶ/ር ሰፊሳ ተናግረዋል::
የኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ውጤታማ የሚሆነው ከመነሻው ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለገበያ ማቅረብ ሲቻል ነው" ያሉት ኃላፊው፣ ምርቱ መሬት ላይ እንዳይሰጣ እና በአልጋ ላይ እንዲደርቅ የማስተማርና የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተያያዘም የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ በሄክታር የሚገኘውን ምርት ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህ ጥራት ያለው ምርት በኮንትሮባንድ እንዳይባክን የቁጥጥር ስራው ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል

❤7👍2👀1🙈1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ወደ ብሄራዊ ፓርክ አደገ‼️
🇪🇹 በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ እንዲተዳደር ፀደቀ‼️
👉የአማራ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን በብሔራዊ ፓርኮች የአሥተዳደር ሥርዓት እንዲመራ የቀረበውን ጥያቄ አጽድቋል።
የአማራ ክልል የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን ኀላፊ ተስፋሁን ዓለምነህ የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ከ8 ሺህ 732 በላይ ሄክታር ስፋት ያለው በአንኮበር፣ በባሶና ወራና እና ጣርማ በር ወረዳዎች በሚገኙ 15 የገጠር ቀበሌዎች የሚዋሰን ደን መሆኑን ገልጸዋል።
ጥብቅ ደኑ የበርካታ የብዝኀ ሕይወት ሃብቶች መኖሪያ መሆኑን ተከትሎ ጥበቃና ልማት እየተደረገለት ወደ ብሔራዊ ፓርክ እንዲያድግ ተከታታይ ጥናት እየተካሄደ ቆይቷል ብለዋል።
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ጥብቅ ደኑ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት መሠረት በማድረግ የጥበቃና ልማት ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱንም ገልጸዋል።
በክልሉ እና እንደሀገርም ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች ጋር እንዲጠበቅና እንዲለማ የጥበቃና ልማት ደንብ በማዘጋጀት ለክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት አቅርበው ጥያቄውን እየተከታተሉ መቆየታቸውንና የመስተዳድር ምክር ቤቱም ከሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ እንዲተዳደር ማፅደቁን ገልጸዋል።
አካባቢው በብሔራዊ ፓርክነት ተመዝግቦ የቀጣይ የቱሪዝም ተስፋ እንዲኾን በመደረጉ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ኀላፊው
ለክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት ምስጋና አቅርበዋል።
ለመላው የክልሉ እና በተለይም ለሰሜን ሸዋና አካባቢው ማኅበረሰብም የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ በቀጣይ ለሚደረገው የተጠናከረ የጥበቃና ልማት ተግባራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በክልሉ አምስት ብሔራዊ ፓርኮችን እና ሰባት የማኅበረሰብ ጥብቅ ስፍራዎች ላይ የጥበቃና ልማት ተግባራት እያከናወነ ነው።

👍12❤10👌1
ባንኩ ከ9:00 በኋላ አገልግሎት አይሰጥም‼️
ማክሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (June 30, 2026) የዓመቱ በጀት መዝጊያ ቀን ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በዕለቱ ሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት እንደማይሰጡ አሳውቋል።
በዚህም ባንኩ ደንበኞቹ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እዲያደርጉ ያሳሰበ ሲሆን ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች አገልግሎት እንደማይቋረጥ ገልጿል።

❤7👍2✍1🥰1👌1🤝1
የ6 ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር የ6 ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን የገደለው ተከሳሽ ጀማል ሁሴን በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር ሀብት-ምንጭ ቀበሌ ውስጥ ከባለቤቱ ጋር በነበረ የፍትሐ ብሔር ክስ ምክንያት ቂም በመያዝ በስለታማ መሣሪያ በመውጋት
ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ክሱን ከጥርጣሬ በላይ እንደሚያስረዱ በመግለጽ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ሰጥቶ ነበር። ተከሳሹም "የመከላከያ ማስረጃ የለኝም" በማለቱ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎ ወስኗል።
በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየቶችን ከተቀበለ በኋላ ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉንየደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via_dagu

❤22👍13😱3😢2🙏1👌1💯1🤣1👀1
በትግራይ ክልል ከሚገኙ ከተሞች ተነስተው ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚጓዙ የሕዝብ ማጓጓዣ አውቶቡሶች ከምሽቱ 12:30 እስከ ንጋቱ 11:30 ድረስ የሌሊት ጉዞ እንዳያደርጉ እገዳ ተጣለ።
ከትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ይፋዊ የደብዳቤ ሰነድ መረዳት እንደተቻለው፣ እገዳው የተጣለው በሌሊት በሚደረጉ ጉዞዎች ሳቢያ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እና አጠቃላይ የሕዝብ ደኅንነት ስጋትን ለመቀነስ ነው። ከዚህ በተጨማሪም፣ በሌሊት በሚንቀሳቀሱ አውቶቡሶች ላይ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና መሰል ጥርጣሬዎች እየታዩ መሆኑን ከኅብረተሰቡ የደረሱ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ውሳኔው መተላለፉ ተገልጿል።
በትግራይ ክልል የትራፊክ ደኅንነት፣ አደጋ ቁጥጥርና ምርመራ መምሪያ ኃላፊ አብርሃ ወረደ ተፈርሞ የወጣው ይህ ይፋዊ መመሪያ፤ ከሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የሕዝብ ማጓጓዣ አውቶቡስ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ30 ደቂቃ እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ድረስ ጉዞ ማድረግን ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።
ይህ አዲስ የሌሊት ጉዞ እገዳ በክልሉ ትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ ቀደም ሲል ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የተላለፈውን የውሳኔ አቅጣጫ ተከትሎ የወጣ ሲሆን፣ በክልሉ የሚገኙ ሰባቱም የዞን ፖሊስ መዋቅሮች ትእዛዙን በመሬት ላይ ባሉ የትራፊክ ፍተሻዎች ላይ ጥብቅ በሆነ ሁኔታ እንዲያስፈጽሙና ክትትል እንዲያደርጉ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል።
ውሳኔው በለሊት ተነስተው ከትግራይ-አዲስአበባ የሚጓዙትን የህዝቢ ማመላለሻ አውቶብሶች ላይ ጫና ለማሳደር የተደረገ ይሁን አይሁን እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

❤19👍3🤔1😢1👀1
የቆሎ ተማሪዎች ጭምር ታፍሰው ተወሰዱ‼️
📌በመቀሌ ከተማ በቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የሚማሩ የፈለገ ሕይወት ተማሪዎች ከትናንት በስቲያ የወርሃዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል ዋዜማ በህወሕት ታጣቂዎች ተይዘው መወሰዳቸው ታውቋል። ከተወሰዱት መካከል የቅኔ፣ የቅዳሴ፣ የዜማና የአቋቋም ትምህርት የሚማሩ በርካታ ተማሪዎች ይገኙበታል።
በዚህ ጉዳይ የጉባኤው መምህራን ዛሬ ወደ ሚመለከተው ጣቢያ ሄደው ሲጠይቁ፣ “እንመልሳቸዋለን፤ ወደ ወረዳ ሄዳችሁ ጠይቁ” የሚል ግልጽ ያልሆነ ምላሽ እንደተሰጣቸው ተገልጿል። ወደ ወረዳም በሄዱ ጊዜ ወደ ዞን እንዲሄዱ ተነግሯቸዋል።
የበለጠ የሚያሳዝነው እነዚህ በካቴድራሉ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ከመቀሌ ወጥተው ወደ ሩቅ የሥልጠና ማዕከላት በፍጥነት መወሰዳቸው ነው
📌በተያያዘ ዜና ከላይ የሚታየው ምስል ከአዲግራት እና አከባቢዎች የታፈሱ ወጣቶች ዛንጎ ወደ ተባለ ማሰልጠኛ ገብተዋል።
አብዛኛው ወጣት ከቤቱ እየወጣ በቡድን በየጫካ ነው የሚያድረው ገጠራማ ከተሞች በጣም ከሸመገሉ ሰዎች በስተቀር ምንም ወጣት መንገድ ላይ አይታይም ተብሏል።

❤20💔11👍5🤪4😢3
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-
✅ ከጠዋቱ 4፡00-ቀኑ 9፡30
👉 ሜክስኮ፣ ብሔራዊ ፣ ሰንጋተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፣ ኩባ ፓርክ፣ ተ/ሃይማኖት፣ በርበሬ በረንዳ፣ ዲአፍሪካ እና አካባቢያቸው ፣
✅ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡00
👉ጎፋ ካምፕ፣ ጀርመን አደባባይ፣መከኒሳ አረቄ ፋብሪካ፣ላፍቶ፣ ቄራ፣ቆሼ፣ ዘነበወርቅ፣ጎፋ እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00-10፡30
👉ሸገር ዳቦ፣ ኤሞሌስ ፋብሪካ፣ ለገ ጣፎ ከተማ ፣ የካሰዴ፣የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም፣ወሰን ግሮሰሪ፣ ሲኤምሲ ሚካኤል፣ ካራሎ፣ለገጣፎ፣ ሲዲሲ ፣ ኮሰሮ፣ ለገዳዲ፣ ሰንዳፋ፣ 44 ማዞሪያ፣ ሲሬ ጎዩ፣ የካ ሰዴ፣ድሬ ሰኩር እና አካባቢያቸው፣
👉 ጁኒፐር ግላስ፣ ደጋ ውሃ፣ ቻንግልዶንግራን፣ ፊበላ፣ ቦልት ማልት፣ ሃዋ ትሬዲንግ፣ ብራውን ፉድ ፣ ማማ ዱኬት ፋብሪካዎች እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከለሊቱ 6፡00-ቀኑ 6፡00
👉 ድሬደዋ ውሃ፣ ፓይነር ሲሚንቶ፣ ቱሬ ሲሚንቶ፣ ሀረር ውሃ፣ ማረሚያ፣ ኩርቱ፣ በለዋ፣ ቃልቻ፣ ቢሻን በሄ፣ ሃሎብሳ፣ ለጎዳ፣ አሳሊሶ፣ ኢንዱስትሪ ኮንዶሚኒየም፣ ሻሎም ኢንጂነሪንግ፣ መልካ፣የኢንዱስትሪ እና አካባቢያቸው፣
✅ ከጠዋቱ 1፡30-5፡00
👉አዳማ ከወንጂ ቀበሌ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋት 12፡00-12፡00
👉በአሰላ፣ አዳሚቱሉ፣ ቡታጅራ፣ ወራቤ እና አካባቢው
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ውድ ደንበኞቻችን፤ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

❤10👍3
''ወላጅ እናቱ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ታዳጊ በቁጥጥር ስር ዋለ'' ደብረብርሃን ፖሊስ መምሪያ
በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፣ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ፣ አየር ጤና ቀበሌ ውስጥ ወላጅ እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተጠረጠረው ወጣት ዮሴፍ ከበደ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሟች ወ/ሮ ፍሬህይወት ገብረሚካኤል ተከራይታ ትኖርበት የነበረውን የተቆለፈ ቤት በር ሰብሮ በመግባት ባደረገው ፍተሻ፤ ሟች አንገቷ በቢላ ተቆርጦና ለብቻው በማዳበሪያ ተቋጥሮ መገኘቱን አስታውቋል።
በፖሊስ የመጀመሪያ ደረጃ ማጣራት ግድያው የተፈፀመው ሰኔ 08 ቀን 2018 ዓ.ም አካባቢ ሲሆን፣ የቤቱ የውጭ በርም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተቆልፎ ሰንብቷል።
ፖሊስ አስከሬኑን ካነሳ በኋላ ባደረገው ፈጣን ክትትል፣ ወንጀሉን ፈፅሞ ወደ አዲስ አበባ የሸሸውና የ"666" አባል እንደሆነ የተነገረለት የሟች ልጅ ዮሴፍ ከበደ፤ ተመልሶ አክስቱ ቤት ተደብቆ ሳለ ወንጀሉን ከፈፀመበት ቢላ ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።
የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እየተመኘ ይህ አሰቃቂ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ሌት ተቀን በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጧል።
Via:- ደብረብርሃን ፖሊስ መምሪያ

💔25😢12❤5😱5🤯2🙉2👍1
በአንዳንድ ክፍለከተሞች በቤት ኪራይ ዉል ላይ የተቀመጠዉ የዋጋ ተመን እና ቤቱ የማይጣጣም እንደሆነ እየታወቀ እንኳን ጭማሪዉ በዉሉ መሠረት እንዲሆን ተደርጓል ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ገለፀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ እንደገለፁት፥ "የ11.5 በመቶ የዋጋ ጭማሪ የተደረገዉ ዉሉ ላይ በተቀመጠዉ እንጂ በደበቃችሁት ላይ አይደለም "ሲሉ ከአከራይ ተከራይ ተወካዮች ጋር በተደረገ ዉይይት ላይ ተናግረዋል።
ሰኔ 30 ጀምሮ የሚተገበረዉ የቤት ኪራይ ዋጋን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናት በትናንትናው ዕለት ለዉይይት ቀርቧል።
ስለጥናቱ ገለፃ ያደረጉት በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ተመራማሪዉ አቶ ኑርአሁን አንዳርጌ፥በዚህ ጥናት የዋጋ ትመና ለማድረግ የተለያዩ መስፈርቶች መካተታቸውን ገልፀዋል።
የዋጋ ግሽበት፣ የቤቱ መገኛ እና የቤት ስፋት እንዲሁም ከመንገድ ያለ ርቀት ያሉ ከግምት ማስገባቱ ተገልጿል።
ተመራማሪዉ ጥናቱን ለማድረግ በከተማዋ ያለዉን የህዝብ ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ እንደነበር በመግለጽ የህዝቡ ቁጥር መብዛት የፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠን ፈጥሯል ብለዋል።
እስከአሁን ወጥ የሆነ አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት 28 በመቶ አከራዮች በየጊዜው በዘፈቀደ የዋጋ ማሻሻያ ያደርጉ እንደነበር በመድረኩ ተገልጿል።
በጥናቱ የተሳተፉት ተመራማሪዉ እንዳስረዱት አከራይ እንደፈለገ ዋጋ ቢጨምር አብዛኛውን ሰዉ በረንዳ ይወጣል ፤ ይህ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ የሚያስገድድበት አሰራር ሆኖል ብለዋል።
በአለምአቀፍ ደረጃ አንድ ሰዉ ከገቢዉ ለቤት ኪራይ 30 በመቶ መክፈል ያለበት ቢሆንም በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተገኘዉ ጥናት አንድ ሰዉ ከገቢ ላይ የቤት ኪራይ ወጪዉ ከ50 እስከ 80 በመቶ እንደሚደርስ ተጠቁሟል።
በትናንትናው የዉይይት መድረክ የተካፈሉ የአከራይ እና ተከራይ ተወካዮች በዋጋ ጭማሪዉ ዙሪያ ለአስተዳደሩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ከአራዳ ክፍለከተማ እንደመጡ የተናገሩት ተሳታፊ ሀሳባቸውን ሲገልፁ፥"አከራዩም ሆነ ተከራዩ የችግሩ አካል ነዉ፤ በዚህ ላይ የጋራ መግባባት ያስፈልጋል"ይላሉ።
የ11.5 በመቶ የዋጋ ጭማሪዉ ለአከራዩም ሆነ ለተከራዩ የዋጋ ተመኑ ሚዛናዊነት ላይ ጥያቄ አንስተዋል።
ሌላኛዉ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ እንደመጡ የገለፁ ተሳታፊ በቤት ኪራይ ዙሪያ በአከራይ እና በተከራይ በኩል የመደባበቅ ሂደቶች አሉ ፤ ይሄንን ግልፅ ማድረግ ካልተቻለ ፍትሀዊ የአከፋፈል ስርአት ማምጣት እንደማይቻል አንስተዋል።
በመድረኩ የ11.5 በመቶ ዋጋ ጭማሪ በመሀል ከተማ እና በማስፋፊያ አካባቢዎች ለምን እኩል ይጨመራል? ይህን ጭማሪ አሁንስ ተከራዩ ጨምሮ መክፈል ይችላል ወይ? የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።
ለተነሱ ሀሳብ እና ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የቢሮዉ ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ፥ በዉሉ መሠረት የተቀመጠዉን ዋጋ መነሻዉ ተንተርሶ በጥናቱ መሠረት ጭማሪ መደረጉን ገልፀዋል።
በአንዳንድ ክፍለከተሞች በቤት ኪራይ ዉል ላይ የተቀመጠዉ የዋጋ ተመን እና ቤቱ የማይጣጣም እና የማይገጣጠም እንደሆነ እየታወቀ እንኳን ዉሉ ህጋዊ አድርገን ጭማሪዉ ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል።
የ11.5 በመቶ የዋጋ ጭማሪ የተደረገዉ ዉሉ ላይ በተቀመጠዉ እንጂ በደበቃችሁት ላይ አይደለም በማለትም ገልፀዋል።
"ዋጋ ሲጨመር ዉሉ ላይ ባለዉ ነዉ የተጨመረዉ መጀመሪያ ስታከራዩ በማስፋፊያ እና በመሀል ከተማ በልዩነት እንዳከራያችሁ ሁሉ አሁን የተጠናዉ ጭማሪ በዉሉ መሠረት የሚጨምር ነዉ፤ ለማስፋፊያ አካባቢ ዝቅ ያለ ለመሀል ከተማ ከፍ ያለ ጥናት አልተጠናም "ሲሉ አስረድተዋል።
በመጪዉ አመት 11.5 በመቶ ጭማሪ የተደረገበትን አግባብ ያስረዱት ሀላፊዋ፥"ጭማሪዉ በጣም ከፍ ያለ ነዉ ብለን እኛ አልወሰድንም ቢያንስ የፌዴራል ጥናትን እንኳን ወስደን ተግባራዊ ብናደርግ እንደ ከተማ አስተዳደር ጥናት ዉስጥ ስናስገባዉ ትንሽ ነዉ የጋሸበዉ ፤ ይሄን ተከራዩ መክፈል ይችላል ብለን ነዉ የወሰድነዉ" ሲሉ አስረድተዋል።
በከተማዋ ከ50 ሺህ በላይ የኪራይ ቤቶች ተመዝግበዉ ወደ ሲስተም እንደገቡ ተገልጿል።

❤25👍4🥰2🤪2🤣1