‹‹በ4 አቅጣጫ የከበበንን ጠላት ብቻውን አስቀርተንዋል›› ጀነራል ጆን መዲድ
የሕወሓት ጀነራሎች እና ወታደራዊ መኮንኖች የሚያሰሙት ዛቻ እና ፉክራ ቀጥሏል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ለጦርነት ድቤ ድለቃቸው ጆሮውን ቢነፍጋቸውም በግድ በጦር ሜዳ ሊማግዱት በየአደባባዩ የ‹እናሸንፋለን› ፉከራ እያሰሙ ነው፡፡
ከትግራይ ጦር አዛዦች መሀል አንዱ የሆኑት ጀነራል ዩሀንስ ወልደጊዮርጊስ (ጆን መዲድ) በዎይን ሚዲያ በኩል የተለመደ ክስ እና የእናሸንፋለን ፉከራ አሰምቷል፡፡ ጀነራሉ፣ ‹‹በአራት አቅጣጫ የከበበንን ጠላት አሰላለፍ በጣጥሰን፣ ብልጽግናን ብቻውን አስቀርተንዋል›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ትናንት ተባብረው የዘመቱብንን ኃይሎችን በታትንን፣ በቀጠናው አዲስ አሰላለፍ ፈጥረናል የሚሉት የጦር አዛዡ፤ አልተቋጨም ያሉትን ህልውና ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን ነው ብለዋል፡፡“ጠላቶቻችን ብዙ ነገር እያሰቡ ነው፤ ብዙ ነገር ደግሞ ይፈርስባቸዋል” ሲሉም አክለዋል፡፡
ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ አዲስ የኃይል አሰላለፍ እንዲፈጠር አድርገናል የሚሉት ጀነራሉ፤ ‹‹በ2013 ከጎረቤት ሀገራት እሰከ ሀገር ውስጥ ኃይሎች አስተባብሮ የዘመተብንን ጠላት ብቻውን አስቀርተን፣ የራሳችን አሰላለፍ ፈጥረናል›› ብለዋል፡፡ “በዚያን ጊዜ ተፈጥሮ የነበረውን እኛን የማጥፋት አሰላለፍ በትነን፣ ከሀገር ውስጥ እና በምስራቅ አፍሪካ አዳዲስ የአሰላለፍ ለውጦች መፍጠር ችለናል›› ነው ያሉት። ጆን መዲድ አዲስ አሰላለፍ ፈጥረናል የሚሉት ጽምዶን ነው፡፡
@Addis_Reporter

❤19🤣6👍2🤔2😎2🤯1😢1
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤4👍2
ጋናዊዉ ጠንቋይ ፖርቱጋል የዘንድሮዉን የአለምዋንጫ ታሸንፋለች አለ
ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ክዋኩ ቦንሳም ፖርቱጋል የዘንድሮዉን የአለምዋንጫ እንደምታሸንፍ ተናግሯል። "ይህ የአለምዋንጫ የፖርቱጋል እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነዉ። ያሸንፋሉ" ሲል ተንብዮአል።
ይህ ጠንቋይ ከሰሞኑ ሀገሩ ጋና ከእንግሊዝ ጋር በነበራት ጨዋታ ሃሪ ኬን ጋና ላይ ግብ እንዳያስቆጥር እረግሜዋለሁ ብሎ ፤ እንግሊዛዊዉ አጥቂም ግብ ሳያስቆጥር ወጥቶ ነበር። ከዚህ ጨዋታ በኋላ ጋናዊዉ ጠንቋይ የአለማቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት ስቦ ቆይቷል።
ይህ ጠንቋይ በፈረንጆቹ 2014 ክርስቲያኖ ሮናልዶን እረግሞት ነበር። በወቅቱ በነበረዉ የአለምዋንጫ ወቅትም ሮናልዶ በጉዳት ነበር የተጫወተው ይባላል። ጠንቋዩም በእኔ እርግማን ነዉ ተጨዋቹ የተጎዳዉ ብሎ ነበር።
አሁን ደግሞ የዘንድሮዉን የአለምዋንጫ ፖርቱጋል ታሸንፋለች ብሏል። ይህ ጠንቋይ በአካን ቋንቋ የስሙ ትርጓሜ "የእሮቡ ሠይጣን" እንደማለት ነዉ።

🤣45❤20👍4👌1😎1
ጋዜጠኛ ሣህለገብርኤል ይትባረክ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ሰኔ 19/2018 ዓ.ም
ከጋዜጠኝነት ሙያው በተጨማሪ በማረሚያ ፖሊስ አባልነት እስከ ረዳት ኢንስፔክተርነት ማዕረግ የደረሰው ረዳት ኢንስፔክተር ሣህለገብርኤል፣ ሕይወቱ እስካለፈበት ዕለት ድረስ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የሚዲያ ማስተባበሪያ ኃላፊ በመሆን እያገለገለ ነበር።
በ18 ዓመቱ የማረሚያ ፖሊስን የተቀላቀለው ረዳት ኢንስፔክተር ሣህለገብርኤል ይትባረክ፣ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር።
በጋዜጠኛ ሣህለገብርኤል ይትባረክ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ አጋሮቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንመኛል።
የአብሥራ ተፈራ

😢24❤10👍6💔5
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

👍2
በሳውዲ አረቢያ በ12 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ፍርድ ተፈጸመ ፤ ሌሎች 63 ዜጎችም በሞት ስጋት ላይ ይገኛሉ።
በሳውዲ አረቢያ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት 2026 የመጀመሪያዎቹ ወራት ብቻ 12 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ፍርድ መፈጸሙ ተገለጸ። እንደ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ገለጻ፣ በደቡብ ምዕራብ ሳውዲ አረቢያ በሚገኘው ከሚስ ሙሻይት ማቆያ ማዕከል ውስጥ በአንድ ክፍል ብቻ የታሰሩ 63 ኢትዮጵያውያን ከዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ብቻ በማንኛውም ሰዓት የሞት ፍርድ ሊፈጸምባቸው እንደሚችል በከፍተኛ ስጋት ገልጿል።
ሳውዲ አረቢያ በዘንድሮው ዓመት ብቻ የሞት ፍርድ የፈጸመችባቸው ሰዎች ቁጥር 100 መድረሳቸው የተረጋገጠ ሲሆን በሳውዲ ባለሥልጣናት የሞት ፍርድ ከተፈጸመባቸው 100 ሰዎች መካከል 12ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 48 ሳውዲውያን፣ 7 ፓኪስታናውያን፣ 6 ሱዳናውያን፣ 4 የመናውያን እና 4 ሶርያውያን መሆናቸውን የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት ከመንግሥት መግለጫዎች በመነሳት ዘግቧል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ፣ በሳውዲ አረቢያ የሞት ቅጣት አፈጻጸም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን "አስፈሪ ምዕራፍ" ሲል የገለጸው ሲሆን፣ በተለይም የውጭ ሀገር ዜጎች ያልተገባ የፍርድ ሂደት ሰለባ እየሆኑ መሆናቸውን አጋልጧል።

💔20❤11👍4😢3
ብሪክስ ሀገራት ያቋቋሙት የልማት ባንክን፤ ኢትዮጵያ በአባልነት እንድትቀላቀል የሚያስችላት የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ።
ረቂቅ አዋጁ በፓርላማ ጸድቆ ለባንኩ የገዢዎች ቦርድ ሲገባ፤ ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ እና አልጄሪያ በመቀጠል አራተኛዋ አፍሪካዊት የልማት ባንኩ አባል አገር ትሆናለች።ዋና መስሪያ ቤቱን በቻይና ሻንጋይ ከተማ ያደረገው የብሪክስ የልማት ባንክ፤ “ኒው ዴቬሎፕመንት ባንክ” በሚል ስያሜ የሚጠራ ነው።
ይህንን ባንክ ኢትዮጵያ በአባልነት መቀላቀሏ “ለሀገራዊ የልማት ፋይናንስ፣ ለመሰረተ ልማት ድጋፍ እና ለማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት አማራጭ የገንዘብ ምንጮችን ለማግኘት” ያስችላታል ተብሎ እንደታመነበት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።በቀድሞዋ የብራዚል ፕሬዝዳንት ዲልማ ሮዜፍ የሚመራው “ኒው ዴቬሎፕመንት ባንክ” ባንክ፤ “ታዳጊ ሀገራት ለሚያከናውኗቸው የመሰረተ ልማት እና የዘላቂ ልማት ዕቅዶች” የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ የተቋቋመ ነው።
በ100 ቢሊዮን ዶላር የተፈቀደ እና በ52.7 ቢሊዮን ዶላር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው ይኸው ባንክ፤ ከሻንጋይ በተጨማሪ በብራዚሏ ሳኦ ፖሎ እና በህንድ ጉጅራት ከተሞች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አሉት።
ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የባንኩ መስራች አባላት ሲሆኑ፤ ባንግላዴሽ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ግብጽ፣ አልጄሪያ እና ኡዝቤኪስታን ባለፉት አምስት ዓመታት ባንኩን በአባልነት ተቀላቅለዋል።የ“ኒው ዴቬሎፕመንት ባንክ” የገዢዎች ቦርድ ኢትዮጵያን በዕጩ አባልነት የተቀበለው በጥቅምት 2015 ዓ.ም. ነበር።
Via Ethiopia Insider

❤6👍4
የቤት ኪራይ በተመን ሊወሰን ነው‼️
ከ2019 ጀምሮ የቤት ኪራይ ዋጋ በአዲስ መተመኛ ሊወሰን ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን ፍትሃዊ፣ ሳይንሳዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመወሰን የተዘጋጀ የዋጋ መተመኛ ጥናት ዛሬ ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ፊት ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ እንደገለጹት፣ ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ጫናን ለመቀነስ እና በቤት ኪራይ ገበያ ውስጥ የተስፋፉ ሕገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን ለመግታት በተከታታይ እየሰራ ነው።
እንደ ኃላፊዋ ገለጻ፣ በ2016 ዓ.ም. የተከናወነው ሰፊ የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባ በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ አሁን የቀረበው የኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናትም የውል ማደስ ሂደትን ፍትሃዊና ግልጽ ለማድረግ ያግዛል።
ጥናቱ የአከራዮችን ተገቢ ገቢ ከወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ተከራዮችም ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ እንዲከፍሉ እና የተረጋጋ የኢኮኖሚ ኑሮ እንዲመሩ እንደሚያስችል ተገልጿል።
እንዲሁም ጥናቱ የቤት ኪራይ ገበያውን ጤናማና ሊተነበይ በሚችል መልኩ በማደራጀት፣ በአከራይና ተከራይ መካከል ያለውን የእምነት ክፍተት ለመቀነስ እንዲሁም የሕገ-ወጥ ደላሎችን ጣልቃ ገብነት ለመግታት እንደሚረዳ ተጠቁሟል።
ጥናቱ በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ በ2019 በጀት ዓመት በተግባር እንደሚውል ተገልጿል።

❤39👍6
‹‹TDF እየሸሸ ነው፤ አልዋጋም ብሏል›› ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ‼️
‹‹ቲዲኤፍ የሚባለው ጦር እየሸሸ ቤቱ ተቀምጧል፤ አልዋጋም ብሏል፤ ትግራይ ያሉ መሪዎች ከሻብያ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው የጦርነት ፍላጎታቸውን አልተዉም፤ ነገር ግን አቅማቸው ስለተመናመነ እየወላወሉ ነው፡፡ በፊት ማስተዳደር በቻሉበት አቅም ማስተዳደር ስላልቻሉ አፋኝ ሕግ አውጥተው ማስተዳደር ነው የሚፈልጉት፤ ቀደም ሲል የሰሩት ወንጀል ለመሸፈን ሌላ ወንጀል እየሰሩ እንዳለ ይሰማኛል፡፡
ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ በዛሬው ዕለት የተናገሩት

👍20❤8🤣6🤪4🙉2👌1
ታሞ ሊጠይቁት አስራ ሰባት ፍቅረኛሞቹ ሆስፒታል የመጡበት የቻይናዊው አስገራሚ ታሪክ
በፈረንጆቹ 2015 ሚስተር ዩዋን የተባለ ቻይናዊ ሰው በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ሆስፒታል ይገባል።
ይሁንና አደጋው በአካባቢው የዜና ማሰራጫዎች ላይ መተላለፉን ተከትሎ፣ ያላሰበው አስገራሚ ትዕይንት በሆስፒታሉ ውስጥ ተፈጠረ።
ሊጠይቁት የመጡ 17 ፍቅረኛሞቹ በአንድ ጊዜ አልጋው አጠገብ ተገኙ!
ሁሉም ሴቶች እርስ በርሳቸው በፍጹም አይተዋወቁም የነበረ ሲሆን፥ አንዳንዶቹ ከዩዋን ጋር ለዓመታት የዘለቀ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው ታውቋል።
ይህ ሚስጥር በአንድ አደጋ ምክንያት በአደባባይ በመጋለጡ፣ በሆስፒታሉ የነበሩ ታካሚዎችና ነርሶች በሁኔታው በእጅጉ ተገርመዋል።
ፍቅረኛሞቹም ጉዳዩን ሲረዱ በከፍተኛ ድንጋጤ እና ቁጣ ውስጥ ወድቀው ነበር።

🤣36❤15👍4🤪3😈2🤔1👀1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥
🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።
የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia

❤2👍2
ጥይት ወደውጪ መላክ ተጀመረ‼️
ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ጥይት በመሸጥ የውጪ ምንዛሬ እየተገኘ መሆኑ ተዘገበ።
ከወራት በፊት በአገር ውስጥ ጥይት ማምረት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ገልፀው ነበር፡፡
መከላከያ ሰራዊት ትናንት ባጋራው መረጃ በአገር ውስጥ የሚመረተው ጥይት የውጪ ምንዛሬ እያስገኘ መሆኑን ገልጧል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ በያዘችው የለውጥ ጉዞ የጸጥታ መዋቅሯን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማደራጀት እና ወታደራዊ ቁሶችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ለመገንባት የሚያስችል ታሪካዊ እርምጃ ወስዳለች›› የሚለው ሰራዊቱ፤ ይህ አካሄድ ሀገሪቱ በወታደራዊ አቅም ረገድ የነበራትን የውጭ ጥገኝነት በመቀነስ የራሷን የጸጥታ ፍላጎት በራሷ አቅም የምትፈታበትን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል ብሏል።
በዚህ ረገድ መንግሥት ድሮን ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ የማልማት እና የመገጣጠም ሥራን በስፋት እየተገበረ ይገኛል።
የድሮን ማዕከላት መቋቋም እና በሥራ ላይ መዋል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአየር ክልሉን በአስተማማኝ ሁኔታ በመቆጣጠር እና የጸጥታ ስጋቶችን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ አስችሎታል ብሏል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ለቀላል እና ለከባድ የጦር መሣሪያዎች የሚያስፈልጉ ጥይቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመራቸው ሌላው ትልቅ ስኬት ነው ያለም ሲሆን፤ ‹‹ይህም በድንገተኛ የጸጥታ ተግዳሮቶች ጊዜ የጦር መሣሪያ እና ጥይት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም ዋስትና ከመስጠቱም በላይ፣ ለውጭ ግዥ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማዳን አግዟል፤ ከዚያም አልፎ ሀገር ውስጥ የተመረተውን ጥይት ወደ ጎረቤት ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት ተጀምሯል›› በማለት አብራርቷል፡፡
Via : አንዳፍታ

🤣45❤19🌚6👍5🤪2👌1👀1
በኦሬንጅ ጁስ የታመሙት ተማሪዎች‼️
ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጉ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኦሬንጅ ጁስ ከሱቅ ገዝተው የጠጡ በሙሉ ራሳቸውን ስተው ህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል‼️
ዛሬ ሰኔ 19/2018 ዓ/ም በደቡብ ኣሪ ወረዳ በመፀር መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከአንድ ግለሰብ አነስተኛ ሱቅ የኦሬንጅ ጁስ ገዝተው የጠጡና ከኦሬንጁ ጋር ንክክ የነበራቸው ተማሪዎች ላይ በደረሰው የጤና መታወክ ምክንያት ቁጥራቸው 200 የሚጠጉ ተማሪዎች በጋዜር እና በጂንካ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ትምህርት ቤቱ አስታዉቋል።
በትምህርት ቤቱ አንድ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ከሱቅ የኦሬንጅ ጁስ ገዝታ ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ካመጣች በኃላ ኦሬንጁን የጠጡና ያሸተቱ በሙሉ ራሳቸውን ስተው መውደቅ መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ሀብታሙ ካልሚ ለኣሪ ማህበረሰብ ሬዲዮ ገልፀዋል።
ተማሪዎች ኦሬንጁን የቀመሱና ያሸተቱ በሙሉ መውደቅ ስጀምር በመፀር ጤና ጣቢያ ጊዜያዊ ማስታገሻ የሕክምና እርዳታ ቢሰጥም ከአቅም በላይ መሆን ሲጀምር ተማሪዎች ወደ ጋዜር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መላኩን ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል።
የደቡብ አሪ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ሀሴን ገዛኸኝ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተማሪዎች በጋዜር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ በመጥቀስ ከአቅም በላይ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ጂንካ ሆስፒታል መላካቸውን ተናግረዋል።
ተማሪዎች የጠጡት ኦሬንጅ ጁስ ምርምራ እንደሚደረግ እና ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንደሆነ በመግለፅ መረጃው ተጣርቶ ሲጠናቀቅ ለሕዝብ ለማሳወቅ እየሰሩ እንደሆነም ጠቅሰዋል።(አዩ)

❤22😢10👍6💔5🤯2😱2🙈2👀1🙉1
መረጃ‼️
ቻይና፣ የኢትዮጵያ የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ያዥ ኢንቨስተሮች በቦንዱ አከፋፈል ዙሪያ የተፈጠረውን ውዝግብ ወደ ፍርድ ቤት እንወስዳለን በማለት መዛታቸውን የፓሪስ ክለብ ሰሞኑን ባወጣው አንድ ሪፖርት ላይ ተቸ።
ፓሪስ ክለብ፣ ቡድን 20 የታዳጊ አገራትን እዳ መልሶ ለማዋቀር ያወጣውን ማዕቀፍ "የተፋጠነ ውሳኔ" እንዲሠጥ ለማድረግ ማሻሻያ እንዲደረግበት በሪፖርቱ ጠይቋል።
ኢትዮጵያ 40 በመቶ ቦንድ ያዥ ኢንቨስተሮችን ከሚወክል ኮሚቴ ጋር በቦንዱ አከፋፈል ዙሪያ ከወራት በፊት የደረሠችበትን ስምምነት፣ የአበዳሪ አገራት ኮሚቴ 'ሁሉም አበዳሪዎች በእኩል መታየት አለባቸው' ከሚለው የእዳ ማሸጋሸጊያ ማዕቀፍ መርህ ጋር ይጣረሳል በማለት ውድቅ እንዳደረገው አይዘነጋም።
ይህንኑ ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ አዲስ ሀሳብ ብታቀርብም፣ የቦንድ ያዦች ኮሚቴ ሀሳቡን አልተቀበለውም።
ኢትዮጵያና የአበዳሪ አገራት ኮሚቴ እዳን መልሶ ለማዋቀር ባለፈው ዓመት ሐምሌ በደረሱበት የመግባቢያ ስምምነት መሠረት፣ ፈረንሳይና ጣሊያን የአገሪቱን እዳ መልሠው ለማዋቀር ከመንግሥት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።

❤12😡3👍2
#NewsAlert ‼️
ለህውሃት ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ‼ የአሜሪካ ኤምባሲ የሰላም ሂደቱን በሚያደናቅፉ አካላት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼
የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ በትግራይ ክልል የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ አካላት ከአፍሪካ ህብረት የውይይት ጥረት ጋር በአስቸኳይ እንዲተባበሩና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳሰበ።
ይህ መግለጫ የወጣው አሜሪካ “አክራሪ” ባላቸው የህወሓት አባላት ላይ የቪዛ ገደብ በጣለች በሳምንቱ ሲሆን፣ ህወሓት በበኩሉ የፕሪቶሪያው ስምምነት መፍረሱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል።

👍11❤10🤪8🤷♂2👌1🤝1
ውሻዉን ያልገደለ ግለሰብ በ50000 ብር እና በእስራት እንዲቀጣ ታውጇል‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሆሳና ከተማ እያንዳንዱ ግለሰብ በቤቱ ያለዉን ዉሻ አውጥቶ እንዲገድል በታወጀው መሰረት
ዉሻ ያላቸው ግለሰቦች ዉሻቸውን ገመድ በማጥለቅ በንንጨት ላይ በማንጠልጠል ዉሾችን እየገደሉ ይገኛሉ።
በከተማው ከሰሞኑ በውሻ ምክንያት በሽታ ተከስቷል የተባለ ሲሆን ይህ የውሻ ግድያ ዘመቻ የተጀመረው አንድ ውሻ የ13 አመት ልጅ ነክሳው ከሞተ በኋላ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
Via : አዩዘሀበሻ

😢57💔28❤8🤷♂8🤣3👍1😱1👀1💊1
የቡና ኮንትሮባንድን ለመግታት እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣትና የንብረት መወረስ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በሆነው የቡና ምርት ላይ የሚፈጸመውን ህገ-ወጥ ዝውውር (ኮንትሮባንድ) ለመግታት፣ ከተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት እጅግ ጥብቅ የሆኑ የቁጥጥርና የቅጣት እርምጃዎችን መተግበር መጀመሩን አስታወቀ።
የቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዶር ሰፊሳ አባቡ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ የቡና ንግድ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በእጅጉ እየጎዳ በመሆኑ፣ ድርጊቱን በቁርጠኝነት ለመከላከል አዲስ የክትትል ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል
በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ ህገ-ወጥ የቡና ዝውውርን ለማስቆም ከፌዴራልና ክልል ፖሊስ፣ ከጉምሩክ ባለስልጣን እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።
በመሆኑም ያለ ህጋዊ ፈቃድና ሰነድ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የቡና ምርት ሙሉ በሙሉ ይወረሳል።
በህገ-ወጥ የቡና ሰንሰለት ውስጥ ተሳትፈው በሚገኙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ም እንደ ጥፋታቸው ደረጃ እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ይጣላል።
የኬላዎች ቁጥጥርን በተመለከተም በመረጃዎችን በፈጣን ቴክኖሎጂ በመለዋወጥ፣ በዋና ዋና የቡና አምራች ክልሎችና መውጫ ኬላዎች ላይ ፍተሻዎች ተጠናክረዋል ሲሉ ዶ/ር ሰፊሳ ተናግረዋል::
የኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ውጤታማ የሚሆነው ከመነሻው ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለገበያ ማቅረብ ሲቻል ነው" ያሉት ኃላፊው፣ ምርቱ መሬት ላይ እንዳይሰጣ እና በአልጋ ላይ እንዲደርቅ የማስተማርና የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተያያዘም የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ በሄክታር የሚገኘውን ምርት ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህ ጥራት ያለው ምርት በኮንትሮባንድ እንዳይባክን የቁጥጥር ስራው ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል

❤7👍2👀1🙈1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ወደ ብሄራዊ ፓርክ አደገ‼️
🇪🇹 በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ እንዲተዳደር ፀደቀ‼️
👉የአማራ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን በብሔራዊ ፓርኮች የአሥተዳደር ሥርዓት እንዲመራ የቀረበውን ጥያቄ አጽድቋል።
የአማራ ክልል የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን ኀላፊ ተስፋሁን ዓለምነህ የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ከ8 ሺህ 732 በላይ ሄክታር ስፋት ያለው በአንኮበር፣ በባሶና ወራና እና ጣርማ በር ወረዳዎች በሚገኙ 15 የገጠር ቀበሌዎች የሚዋሰን ደን መሆኑን ገልጸዋል።
ጥብቅ ደኑ የበርካታ የብዝኀ ሕይወት ሃብቶች መኖሪያ መሆኑን ተከትሎ ጥበቃና ልማት እየተደረገለት ወደ ብሔራዊ ፓርክ እንዲያድግ ተከታታይ ጥናት እየተካሄደ ቆይቷል ብለዋል።
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ጥብቅ ደኑ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት መሠረት በማድረግ የጥበቃና ልማት ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱንም ገልጸዋል።
በክልሉ እና እንደሀገርም ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች ጋር እንዲጠበቅና እንዲለማ የጥበቃና ልማት ደንብ በማዘጋጀት ለክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት አቅርበው ጥያቄውን እየተከታተሉ መቆየታቸውንና የመስተዳድር ምክር ቤቱም ከሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ እንዲተዳደር ማፅደቁን ገልጸዋል።
አካባቢው በብሔራዊ ፓርክነት ተመዝግቦ የቀጣይ የቱሪዝም ተስፋ እንዲኾን በመደረጉ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ኀላፊው
ለክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት ምስጋና አቅርበዋል።
ለመላው የክልሉ እና በተለይም ለሰሜን ሸዋና አካባቢው ማኅበረሰብም የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ በቀጣይ ለሚደረገው የተጠናከረ የጥበቃና ልማት ተግባራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በክልሉ አምስት ብሔራዊ ፓርኮችን እና ሰባት የማኅበረሰብ ጥብቅ ስፍራዎች ላይ የጥበቃና ልማት ተግባራት እያከናወነ ነው።

👍12❤10👌1
ባንኩ ከ9:00 በኋላ አገልግሎት አይሰጥም‼️
ማክሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (June 30, 2026) የዓመቱ በጀት መዝጊያ ቀን ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በዕለቱ ሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት እንደማይሰጡ አሳውቋል።
በዚህም ባንኩ ደንበኞቹ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እዲያደርጉ ያሳሰበ ሲሆን ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች አገልግሎት እንደማይቋረጥ ገልጿል።

❤7👍2✍1🥰1👌1🤝1