አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.9K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ከደብረማርቆስ ባህርዳር በረራ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደብረ ማርቆስ - ባሕር ዳር መደበኛ በረራ ሊጀምር ነው‼️
የደብረ ማርቆስ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ ለዓመታት ሲጠብቀው የነበረውና የልማት ምዕራፍ ማሳያ የሆነው የደብረ ማርቆስ (ንጉሥ ተክለሃይማኖት) አውሮፕላን ማረፊያ፣ የመጀመሪያውን ታሪካዊ በረራ ካስተናገደ በኋላ አሁን ደግሞ አዲስና ተደራሽ የበረራ መስመር ሊጀምር መሆኑ ታውቋል።

በመሆኑም የበረራ ቀናትን እንደሚከተለዉ አሳውቋል::
1.ከአዲስ አበባ ወደ ደበረ- ማረቆስ ደርሶ መልስ በየቀኑ:
2.ከደብረ ማረቆስ ወደ ባህር ዳር በሳምንት አራት ቀን (4) ሲሆን የበረራ ቀን ሰኞ፣ዕሮብ፣አርብና እሁድ ነው
3.ከባህር ዳር ወደ ደበረ ማረቆስ ደግሞ በሳምንት ሶስት ቀን (3) የበረራ ቀን ማክሰኞ፣ሃሙስና ቅዳሜ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ከሚቀጥለው አርብ ማለትም 19/10/2018ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎቱ እንደሚጀምር ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
30👍7💔3🎉1🙏1👌1🤪1
ጊቤ መርከብ መንገድ ጀመረች

ለአምስት ወራት ሻርጃ ወደብ አካባቢ የከረመችው ጊቤ መርከብ ትላንት ማምሻውን የሆርሙዝ ሰርጥን ማለፍ መቻሏ ታወቀ።

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የሆርሙዝ መተላለፊያ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች የፋርስ ባህረሰላጤ ወደቦች ላይ መህልቅ ጥለው እንዲጠባበቁ ተገደው ነበር።

ከነዚህም መካከል ጊቤ አንዷ ነበረች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍13🤡4🎉1🙏1👌1🤪1
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር የሚገኝ ቁልፍ ምሽግ ተቆጣጠረ
 
የሱዳን ጦር በብሉ ናይል ግዛት አዲስ በከፈተው ጥቃት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ አማፂያንን ምሽግ መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡
 
የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በተለያዩ ግንባሮች እየተጠናከረ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የሱዳን ሠራዊት በብሉ ናይል ክልል መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት በመክፈት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ ቁልፍ የዓማፂያን ምሽግ መቆጣጠሩን ገልጿል።
 
ሱዳን ትሪቢዩን እና የቻይናው «ዥንዋ» እንደዘገቡት፤ ወታደራዊ ዘመቻው ማክሰኞ ዕለት በጌሳን ወረዳ በ4ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ሥር በሚገኘው እግረኛ ብርጌድ የተካሄደ ሲሆን፤ ጥቃቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር በግምት አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙትን ከአቡ ዱግላ እና አሻምቦ ባሻገር ያሉ አካባቢዎችን ኢላማ ያደረገ ነው።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍7🤣4👀1🙊1
ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ባለሀብት ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በተለያዩ ሀገራት በበርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ስኬታማ ቢሆኑም በሞሮኮ ያፈሰሱት ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ ግን በአሁኑ ወቅት ከባድ ፈተና ገጥሞታል።

በተለይም በሀገሪቱ ብቸኛው የነዳጅ ማጣሪያ የሆነውና የባለሀብቱ ንብረት የሆነው ሳሚር ኩባንያ ወደ መንግሥት ይዞታነት እንዲዛወር የቀረበው የሕግ ረቂቅ በሞሮኮ ከፍተኛ ምክር ቤት ውድቅ ተደርጓል።

የሞሮኮ የከፍተኛ ምክር ቤት ይህ ኩባንያ በገጠሙት ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት ንብረቱ ተወርሶ ወደ መንግሥት እንዲዛወር የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በትኩረት ከመረመረ በኋላ ውድቅ ማድረጉ ታውቋል።

ይህ ውሳኔ በቢሊየነሩ እና በሞሮኮ መንግሥት መካከል ያለውን የከረረ ፍጥጫ ይበልጥ አባባሶታል።

ይህ ግዙፍ የማጣሪያ ፋብሪካ ላለፉት አሥርተ ዓመታት በታየበት የአስተዳደር ጉድለትና አስፈላጊው መዋዕለ ንዋይ ባለመፍሰሱ ምክንያት፣ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ የዕዳ ማጥ ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል። በዚህም ሳቢያ ፋብሪካው ከ2015 ጀምሮ ሥራውን ሙሉ በሙሉ ለማቆም ተገዷል።

በወቅቱ ሼክ አል-አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁም እስር ላይ መቆየታቸው ለኩባንያው አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ እንዳያገኙ በማድረግ ለፋብሪካው መዘጋት እንደ አንዱ ምክንያት ይጠቀሳል።

ይሁን እንጂ ሼክ አል-አሙዲ በኩባንያቸው (ኮራል ሞሮኮ ሆልዲንግ) አማካኝነት፣ ለፋብሪካው መዘጋት ተጠያቂው የሞሮኮ መንግሥት ነው የሚል ክስ መስርተዋል።

ባለሀብቱ ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት  በመውሰድ፣ ከሞሮኮ መንግሥት የ2.7 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እየጠየቁ ይገኛሉ።

የሞሮኮ መንግሥት በበኩሉ "ውድቀቱ የባለሀብቱ የአስተዳደር ድክመት ውጤት ነው" በሚል በሕግ እየተከራከረ ይገኛል።  

@Addis_Reporter
19🤔8👍2😢2🙊2
ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተወሰነ‼️
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው  በክልሉ በነበረው ግጭት በተለያየ ምክንያት ስራቸውን ለቀው ወደ ትጥቅ ትግል ገብተው ለነበሩ 2167 ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው 738 መምህራን፣ 92 የገቢ ተቋማት ሰራተኞች፣ 1337 (115  በማንነት ምክንያት በፈጠረ ግጭት ተሰናብተው የነበሩ) ሲቪል ሰርቢስ ሰራተኞች በድምሩ 2167 ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራ መደባቸው እንዲመለሱ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በውሳኔውም ከሚመደቡበት ቀን ጀምሮ የስራ መደባቸው የሚያስገኛቸውን ደሞዝ የሚያገኙ መሆናቸውን በግልፅ አመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤪15👍3👌1😎1
በጋምቤላ ክልል አጭር ቀሚስ የሚለብሱ ሴቶች 3ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እየተቀጡ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመቆጣጠርና የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ውሳኔዎች በመተግበር ላይ እንደሚገኙ  የክልሉ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን የአቦቦ ወረዳ ሴቶቸና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ውሳኔዎቹ ሊተላለፉ የቻሉት ልጆች ከወላጆች አቅም በላይ በመሆናቸው እና ትዕዛዝ ባለመስማታቸው ነው ሲል ፅ/ቤቱ አስታውቋል ።

ወላጆች መንግስት ይደግፈን ባሉት መሠረት ፕሮፖዛል ተቀርጾ እና ኮሚቴ ተዋቅሮ ፣ከፖሊስ ፣ከፍትህ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ውሳኔዎች ላይ እየተሰራ ይገኛል ። የአቦቦ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አዊሊ ኡጁሉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ሴቶች የሚለብሷቸው አጭር ቁመት ያላቸው ልብሶች የጥቃት ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲከታተሉና ልጆችም ከዚህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ የሚያስችሉ ጥብቅ መመሪያዎች መተላለፋቸውን ተናግሯል ።ይህንን ችግር ለመቅረፍ ለጥቃት አጋላጭ በሆነ መልኩ አጭር ልብሶችን ለብሰው በሚንቀሳቀሱ ሴቶች ላይ የ3ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መተላለፉን የተናገሩት ኃላፊዋ መመሪያውን ተላልፈው በተገኙት ላይ የቅጣት እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል ።

ዘገባው የብስራት ሬዲዮ ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22👍17🤔4🤷‍♂1👌1
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሐምሌ 8/2018 ዓ/ም ለሚጀመረው ሀገራዊ ጉባዔ ለምክክር የቀረጻቸውን 8 አጀንዳዎች ይፋ አድርጓል።

ምክክር የሚደረግባቸው 8 የተመረጡ አጀንዳዎች የትኞቹ ናቸው ?

1) አጀንዳ ቁጥር 1 የሀገር ግንባታ ጉዳይ፣

2) አጀንዳ ቁጥር 2 የፖለቲካ ስርዓት፣ የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ፣

3) አጀንዳ ቁጥር 3 የፌዴራል ከተሞች፥ አዲስ አበባና ድሬዳዋ

4) አጀንዳ ቁጥር 4 የሃይማኖት ጉዳዮች፣

5) አጀንዳ ቁጥር 5 የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣

6) አጀንዳ ቁጥር 6 ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ የአርሶ አደሮች እና የአርብቶ አደሮች ጉዳይ፣

7) አጀንዳ ቁጥር 7 ሙስና እና መልካም አስተዳደር

8) አጀንዳ ቁጥር 8 ሰላም ግንባታ

አጀንዳዎቹ በተለያዩ ክልሎች ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎችን በማመካከር የተገኙ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ ተናግረዋል።tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣147👍2
የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ዜጎች ወደ ምሥራቅ ሊቢያ ግዛት እንዳይገቡ ታገዱ።

ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ ወደ አውሮፓ መሻገር የሚፈልጉ የአራቱ አገራት ፍልሠተኞች በሊቢያ በኩል በሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሚያልፉ ይታወቃል።

የምሥራቅ ሊቢያ ባለሥልጣናት ይህን እገዳ የጣሉት፣ የውጭ ዜጎች ወደ አገሪቱ የሚገቡበትን ሁኔታ ለመቀየር በማስፈለጉ እንደሆነ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

እገዳው፣ ዲፕሎማቶችን፣ የቆንስላ ሠራተኞችንና ቤተሰቦቻቸውን እንዲኹም የቅጥር ፍቃድ ያላቸው በትምህርትና ሕክምና ዘርፍ የተሠማሩ የአገራቱን ሠራተኞች እንደማይመለከት ተገልጧል።

ባሁኑ ወቅት 900 ሺሕ ያህል የውጭ ዜግነት ያላቸው ፍልሠተኞች ሊቢያ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍43🤣3🤷‍♂1🥰1😢1👌1🤪1
ስምምነቱ 'የአሜሪካ ሽንፈት' መግለጫ ነው ስትል ኢራን ተናገረች
 
ጦርነቱን ለማቆም በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተደረገው ስምምነት "የአሜሪካ ሽንፈት መግለጫ" ነው ሲሉ የኢራን ተደራዳሪ ቡድን መሪ መሀመድ ባገር ጋሊባፍ ተናግረዋል።

ጋሊባፍ በአዘርባጃን በኢራን ቴሌቪዥን ስርጭት ላይ በተላለፈዉ መልዕክታቸዉ እንደተናገሩት "የኢስላማባድ ስምምነት የግፊት እና የማስገደድ ውጤት ሳይሆን የጀግናው የኢራን ህዝብ ተቃውሞ እና ስልጣን ውጤት ነው" ብለዋል።
 
በዚህም የኢስላማባድ የመግባቢያ ስምምነት የአሜሪካን ሽንፈት ማወጅ ሆኗል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከፍተኛ ተደራዳሪው መሀመድ ባገር ጋሊባፍ የመካከለኛው ምስራቅ የጸጥታ መዋቅርን የክልሉ ሀገራት ብቻ መወሰን አለባቸው ብለዋል።

"የውጭ ወታደራዊ ሃይሎችን ከአካባቢው መውጣት እንደ ስልታዊ አላማ እንቆጥረዋለን።

የቀጣናው የወደፊት እጣ ፈንታ በግጭት ሳይሆን በመስተጋብር እንዲወሰን በመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ ከክልል ውጭ ያሉ ወታደራዊ ኃይሎች የአለመረጋጋት መንስኤ ናቸው ሲሉ አክለዋል።
 
ጋሊባፍ ወደ ባኩ አዘርባጃን ባደረጉት ጉዞ እንደተናገሩት ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሀገራት ጋር "በውስጣዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ባለመግባት እና ሉዓላዊነትን በማክበር" ላይ ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ጥቃት እና ወረራ ማቆም አለባት በማለት የኢራንን አቋም ደግመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍9🤣3🤪2💯1
የተፈናቃዮቹ መሬት ለሚሊሻ ተሰጠ‼️

ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው አልተመለሱም በሚል መሬታቸው ለሚሊሻ መስጠት መጀመሩን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

👉ተፈናቃዮቹ ካልተመለሳችሁ መሬታቸሁ ለአካባቢው ሚሊሻ ሊሰጥ መሆኑን ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልፀው ነበር።

ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ተፈናቅለው በወሎ፣ ጃራ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ለቅቀው ወደ ወጡበት አካባቢ ባለመመለሳቸው መሬታቸውን ለሚሊሻና  ኮሬ ነጌኛ ለተባለው ኃይል እንዲሁም ለስራአጥ ወጣቶች ማከፋፈል መጀመሩን ገልፀውልናል።

እነዚህ ተፈናቃዮች በአካባቢው በነበረው ጥቃት ሸሽተው ወደ የወጡ ሲሆን ወደ ቀያቸው ለመመለስ አሁንም ስጋት እንዳለባቸው ይገልፃሉ።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢297🤔4💔3👍2🤣2🙊2
የቀድሞዋ  ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተሾሙ‼️

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ሳህለወርቅ ዘውዴን በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ (UNOWAS) የዋና ስትራቴጂያዊ ገምጋሚ አድርገው መድበዋል።

በቀጠናው ባላቸው ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ልምድ የተመረጡት ሳህለወርቅ፣ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ ለማካሄድ ኃላፊነታቸውን በዚህኛው ወር (ጁን) ማብቂያ ላይ በይፋ ይረከባሉ ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
59👍5😡5🥰2👌1💯1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍2
የማስተርስ ትምህርት አራት አመት‼️
"የማስተርስ ትምህርት ወደ 4 ዓመት ሊያድግ ይገባል " ተባለ‼️

የአሰራር ለውጥ ካልተደረገ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች እውቅና ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት ይፈጥራል ብሏል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጠው የሁለተኛ ዲግሪ (የማስተርስ) ትምህርት ፕሮግራም ከሁለት ዓመት ወደ አራት ዓመት ሊያድግ እንደሚገባ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ይህንን ያስታወቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰጠው ሙያዊ ማብራሪያ፣ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በሁለት ዓመት መደበኛ መርሃ ግብር እየተሰጠ ያለው የማስተርስ ትምህርት፣ አዲስ ከጸደቀው የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብና ከአለም አቀፍ በተለይም ከአውሮፓ ስታንዳርድ ጋር የማይገናኝ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህ ክፍተት በአስቸኳይ የማይስተካከል ከሆነ፣ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች የትምህርት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ወይም እውቅና (Authentication) ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት እንደሚሆን ባለስልጣኑ አስገንዝቧል።

ከእነዚህም መካከል በሀገራችን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ሳያመጡ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ከተማሩ በኋላ፣ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ የሚጠይቁት የብቃት ማረጋገጫ ጉዳይ ትልቅ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም ያጸደቀው የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብ፣ እውቅና ካላቸው የውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት የተገኙ የብቃት ማረጋገጫዎች በሀገሪቱ መመዘኛ መሰረት ተመዝነው እውቅና እንዲሰጣቸው ቢደነግግም፣ አሁን ያለው አሰራር ግን ይህንን ለመተግበር አስቸጋሪ አድርጎታል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዳመለከተው፣ ለአማራጭ የትምህርት ክሬዲት ስርአት (ECTS) በአውሮፓ (ከፍተኛ) የሆነው መስፈርት፣ በኢትዮጵያ ደንብ ውስጥ ' (ዝቅተኛ) ሆኖ ተቀምጧል። ይህንን ወደ ዓመት ሲተረጎም የማስተርስ ፕሮግራም ደንቡ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ የ4 ዓመት ፕሮግራም መሆን እንዳለበት ያስገድዳል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም ለትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ ቢገለጽም እስካሁን ምንም ምላሽ አልተገኘም ተብሏል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡2014🥱3👍2👀2😢1
ጄኔራል ባጫ ደበሌ የአፍሪካ ህብረት የህወሓትን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠየቁ

በቅርቡ ጊዜያዊ አስተዳደሩን በማፍረስ ወደ ፕሬዝዳንትነት የተመለሱት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ አሳሳቢ የተባለ አዋጅ በመላ ክልሉ ማወጃቸው ይታወሳል። ይህንኑ አዋጅ መመልከታቸውን የገለጹት በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ፤ “የክተት አዋጅ እና የግዳጅ ምልመላ” በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ የአዋጁ ዋነኛ ዓላማ ሕዝቡን ለጠቅላላ ጦርነት መቀስቀስ እንደሆነ አመልክተዋል።

ከዚህ ጦርነት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ በስተጀርባ የራስን ጦር እንደገና ማጠናከር እና ታጣቂዎችን እንደ "ቅጥረኛ ተዋጊ" ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ግጭት መላክ የሚሉ ግቦች እንዳሉ የገለጹት ጄኔራል ባጫ፤ የአፍሪካ ህብረት ይህን የህወሓት ድርጊት በአደባባይ እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ህብረቱ ይህ አዋጅ በአስቸኳይ እንዲሰረዝ፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመለስና የፖለቲካ ሂደቶች እንዲቀጥሉ ግፊት እንዲያደርግ አምባሳደሩ አሳስበዋል። ሊፈጠር የሚችለውን አላስፈላጊ ቀውስ ለመከላከልም የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2015🤣3👍2😎1
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እናት ወ/ሮ አዳነሽ በርሄ በ97 ዓመታቸው ማረፋቸውን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ። ከኤርትራ ነጻነት አንስቶ ከ35 ዓመታት በላይ በብቸኝነት ኤርትራን እየመሩ ያሉት የ80 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እናት ያረፉት ሰኞ ዕለት ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20😢11😱8🤣8👍3
በታዋቂው ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ እና በሚዲያ ባለሙያው ግሩም ጫላ መካከል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሰላ የቃላት ምልልስ ተካሂዷል።

ይህ ውጥረት የጀመረው ግሩም ጫላ በፌስቡክ ገጹ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ለማድመቅ ያደረገውን ጥረት አድንቆ፣ ሆኖም በህንጻዎች ላይ የተተከሉት መብራቶች እየጠፉ ከተማዋ ወደ ጨለማ እየተመለሰች መሆኗን በመተቸት ባወጣው ጽሁፍ ነው። ግሩም በጽሁፉ ይህ ስራ ጊዜያዊ ሳይሆን ቋሚ እንዲሆን ክትትል ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስቦ ነበር።

ይህንን የፌስቡክ ጽሁፍ ተከትሎ ጃዋር መሐመድ በኤክስ ገጹ ላይ የግሩምን ጽሁፍ በማያያዝ "ብልጭልጩ እየጨለመ ነው ይለናል ይህ ሞዴል ባለ ጊዜ" የሚል ፌዝ ያዘለ አስተያየት አስፍሯል።

ይህ የጃዋር አስተያየት ግሩምን ማስቆጣቱ አልቀረም። በግል የጽሁፍ መልዕክት  ግሩም ለጃዋር "አንተ ለመላው የኦሮሞ ማህበረሰብ ውርደት ነህ... በሁሉም መንፈስ የተሸጥክ ነህ" የሚል ከባድ ስድብ እንደላከለት፣ ጃዋር ያጋራው የስክሪን ሾት ማስረጃ ያሳያል።

ለዚህ የግሩም መልዕክት ጃዋር መሐመድ በይፋዊ የኤክስ ገጹ ላይ ጠንካራ ምላሽ ሰጥቷል። ጃዋር በመልዕክቱ "ግሩም ጫላ፣ የኦሮሞን አርሶ አደሮች የሚያፈናቅሉ፣ መሬታቸውን የሚሰርቁ እና ያገኙትን ገንዘብ በቅንጦት መኪናዎች ላይ የሚያባክኑና በዚህም የሚመጻደቁ እንዳንተ ያሉ ሌቦችን ማጋለጤ 'የተሸጥክ' የሚያስብለኝ ከሆነ፣ ያንን ስያሜ በክብር እለብሰዋለሁ" ሲል አስታውቋል።

ይህ በሁለቱ ግለሰቦች መካከል የተፈጠረው መካረር በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍13🤣4👌3🕊2🤪21🥱1🙊1
ከጅቡቲ የጫነውን ነዳጅ  አፋር ላይ ሲቀሽብ የነበረው አሽከርካሪ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
 
ከጅቡቲ የተጫነ ነዳጅን በሕ-ገወጥ መንገድ በመቀሸብ ላይ የነበረ የነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ በአፋር ክልል የፀጥታ ሃይሎችና በንግድ ቢሮ በተደረገ ክትትል እጅ ከፍንጅ መያዙን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል ።ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ነዳጅን ለማሠራጨት የተጣለበትን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተውና የግል ጥቅምን በማስቀደም ጅቡቲ የጫነውን ነዳጅ በሕ-ገወጥ መንገድ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲል የቀሸበው ግለሰብ መያዙን ባለስልጣኑ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ አድርጓል ።
 
ሃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች የሚፈጸሙ መሠል ተግባራት በነዳጅ ስርጭት ላይ ከሚያደርሱት መስተጓጎል በተጨማሪ የቀሸቡትን ነዳጅ በሕገ-ወጦች በኩል በውድ ዋጋ በመሸጥ በህብረተሰቡ ላይ ጫናን ይፈጥራሉ።በመሆኑም ግለሰቦቹ ለነዳጅ ብክነትና ለአደጋ ተጋላጭነት የሚዳርግ ተግባርን በቸልተኝነት እየፈፀሙ መሆኑ ተነግራል፡፡
 
ይህን ጥፋት በሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚደረገው ክትትልና የእርምት እርምጃ በፀጥታ አካላት፣በክልል ንግድ ቢሮዎችና በባለስልጣን መስሪያቤቱ በኩል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተቋሙ አሳስቧል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍8👌1
እስከ አምስት ዓመት እስራት የሚያስቀጡ ጥፋቶች የተካተቱበት አዲሱ የመረጃ ነጻነት አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ 

ለ15 ዓመታት በስራ ላይ ከቆየው “የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ” የመገናኛ ብዙኃንን የሚመለከተው ክፍል ተለይቶ ሌላ ራሱን የቻለ ህግ እንዲወጣለት የተደረገው በ2013 ዓ.ም ነበር።

የመረጃ ነጻነትን የሚመለከተው ቀሪው ክፍል በተመሳሳይ መልኩ አዋጅ ቢዘጋጅለትም፤ ለፓርላማ የሚቀርብበት ሂደት ተጓትቶ ቆይቷል።

ከዓመታት ጥበቃ በኋላ የመረጃ ነጻነትን ለመደንገግ የተዘጋጀው የአዋጅ ረቂቅ፤ ከሁለት ወራት በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ተደርጓል።

ምክር ቤቱ መጋቢት 29፤ 2018 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን ይህን የአዋጅ ረቂቅ፤ በዝርዝር እንዲታይ ለፓርላማው የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶት ነበር።

ቋሚ ኮሚቴው የአዋጅ ረቂቁን ለፓርላማ ለተወካዮች ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አምስት የሚደርሱ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጅቷል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን እና አዳዲስ ድንጋጌዎችን ያካተተው የውሳኔ ሃሳብ፤ ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18፤ 2018 በተካሄደ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ከቀረበ በኋላ አዋጁ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል። 

በረቂቅ አዋጁ ላይ የተደረጉት ማሻሻያዎች፤ በመግቢያው ላይ ከተቀመጠው የአዋጁን ዓላማዎች ከሚያብራራው ክፍል ጀምሮ “ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች” እስከተዘረዘሩበት ድረስ ያሉትን የሸፈኑ ናቸው።

ከእነዚህ ማሻሻያዎች መካከል ከመረጃ አሰጣጥ ጋር የተያያዙ እስከ አምስት እስራት የሚያስቀጡ የጥፋት አይነቶች ይገኙበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3🤣2😡2🤪1
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በበጀት ዓመቱ ካቀደው የገቢ እቅድ ማሳካት የቻለው 37 በመቶውን ብቻ መሆኑ ተገለፀ

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሊገባደድ በተቃረበው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ካቀደው 45 ቢሊየን ብር ውስጥ ማሳካት የቻለው 16.6 ቢሊየን ብር ወይም 37 በመቶውን ብቻ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ቢሮው በከፍተኛ አመራሮቹ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንደገለጸው፣ በበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባሰብን ጨምሮ ዝቅተኛ አፈፃፀም የተመዘገበባቸውን ተግባራት ለማካካስ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

በዚህም መሠረት የቀሩትን ተግባራት ለማከናወንና የተቀመጠውን የገቢ ግብ ለማሳካት የሚያስችል የዘጠና ቀን እቅድ ተነድፎ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

ይህ የዘጠና ቀናት የማካካሻ እቅድ እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ከመሬት ሊዝ ጨረታ፣ ከአገልግሎት ለውጥ፣ ከመብት ፈጠራና ይዞታ አገልግሎት፣ እንዲሁም በምደባ ከሚተላለፉ ቦታዎች የሚገኝ የሊዝ ቅድመ ክፍያን ጨምሮ ከ17.34 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍2🤪2🤣1
ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ቀን ሰራተኞች‼️
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ አስገዳጅ ሊሆን ነው
👉ይህ መመሪያ በሰራተኛች ብቃት ማነስ ምክንያት በንብረት እና በግንባት ጥራት ላይ የሚደርስን ችግር ለመቀነስ ነው ተብሏል።


የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ዘርፍ እየታየ ያለውን የጥራትና የደህንነት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አዲስ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን አስታውቋል።
​ይህ አዲስ መመሪያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ዕለት ተዕለት የሚሰሩ የቀን ሠራተኞችንም የብቃት ደረጃ ማረጋገጥን ግዴታ የሚያደርግ ነው። ሚኒስቴሩ በዘርፉ የተሻለ ጥራትና ደህንነትን ለማስፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል።

​እንደ አዲሱ መመሪያ ዝርዝር ሁኔታ፡-

📌​በየትኛውም የግንባታ ቦታ ላይ ለመስራት የሚፈልጉ ባለሙያዎች እና የቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ ግዴታ ይሆናል።

📌​ሕጋዊ የሰርተፊኬሽን ሥርዓት ያላሟላ እና ብቃቱ ያልተረጋገጠ ማንኛውም ባለሙያ ወይም ሠራተኛ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንዳይሳተፍ ሙሉ በሙሉ ይከለከላል።

📌​መመሪያው ሙሉ በሙሉ ሕግ ሆኖ ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የተወሰኑ ዓመታት ሊወስድ ይችላል።

📌 ​በአሁኑ ወቅት ግን የዚህ አሠራር የቅድመ ዝግጅት እና የሙከራ እንቅስቃሴዎች በይፋ መጀመራቸው ተገልጿል።

​የዚህ አሠራር ዋና ዓላማ የግንባታ ሥራዎችን ጥራትና የሥራ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ማሻሻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12🙊9👍3👌1