አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.9K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኢሎን ማስክ የሀብት ማሽቆልቆል፦ በሳምንት ውስጥ 350 ቢሊዮን ዶላር አጣ!

​የስፔስ ኤክስ  አክሲዮን በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ፣ ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ የግል ሀብት ኪሳራ አስተናገደ።

ኩባንያው ለመጀመሪያ ጊዜ የቦንድ ሽያጭ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የአክሲዮን ዋጋው በ30% አካባቢ በመውረዱ፣ ማስክ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ የ350 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል።

​በፎርብስ ስሌት መሠረት፣ የባለሀብቱ ጠቅላላ ሀብት ከ1.45 ትሪሊዮን ዶላር ወደ 1.1 ትሪሊዮን ዶላር ወርዷል።

ማስክ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ኩባንያው ይፋዊ የአክሲዮን ሽያጭ (IPO) ባደረገ ማግስት የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር መሆን ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ባለፉት ቀናት የስፔስ ኤክስ አክሲዮን በ16.4% በመውደቁ የኩባንያውን የገበያ ዋጋ በ928 ቢሊዮን ዶላር አሳንሶታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🙊4👍3👀1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍21
በሳዑዲ በምሕረት አዋጅ የተለቀቁ 320
ኢትዮጵያውያን በሰላም ሀገራቸው ገቡ!


መንግሥት ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ምክንያት በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1 ሺህ 655 ኢትዮጵያውያን መካከል የመጀመሪያዎቹ 320 ተመላሾች አዲስ አበባ ገብተዋል። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ ይህ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት በሪያድ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና በጂዳ የሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በቅንጅት ባከናወኑት ጥረት የተመዘገበ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም መንግሥት ኅብረተሰቡ በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሐሰት የማህበራዊ ሚዲያ ማታለያዎች ሳይደለል ከሕገወጥ የውጭ ሀገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል። ዜጎችን ለከፍተኛ ችግር የሚዳርጉ ሕገወጥ ደላሎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩት የተቀናጁ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ አረጋግጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍7😡2🙏1👌1
በ5 ቀናት ብቻ 40 ዜጎች ውሃ ውስጥ ሰምጠው መሞታቸውን የፈረንሳይ መንግስት አስታወቀ።

የበጋው/ሰመር ሙቀት ከቁጥጥር ውጭ ያደረጋቸው ዜጎች ባገኙት የውሃ አካላት ለመዋኘት እየሞከሩ ነው ያለው የሚዲያ መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ 40 የሚሆኑ ሰዎች በመስመጥ ብቻ ህይወታቸውን አጥተዋል ብሏል።

በፈረንሳይ ሆነ በአውሮፓ በዚህ ሰሞን ለፍተኛ ሙቀት እንሰሚከሰትና ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መንግስታት ሲያሳስቡ ቆይተዋል።

እንደሚባለው የሚቀት መጠኑ ለዚህ ቀደም ከተመዘገበው ከፍ ያለ ነው። በፈረንሳይ ዛሬ በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 40 ዲግሪ ሴሊሺየስ ሙቀት መመዝገቡ ተገልጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢54👍2
የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች ከኢራን ጦርነት እንዲወጡ የሚያስችል ውሳኔ ተላለፈ

የአሜሪካ ሴኔት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱን ወታደራዊ ሀይሎች ከኢራን ጦርነት እንዲያስወጡ የሚያዘውን ውሳኔ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የውሳኔ ሀሳቡ የተላለፈው የአሜሪካ እና የኢራን ተደራዳሪዎች ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በስዊዘርላንድ እየተወያዩ ባለበት እና በቴክኒካል ድርድሮች ላይ ከስምምነት በደረሱበት ወቅት ነው፡፡

ውሳኔው በስዊዘርላንድ እየተካሄደ ያለው ድርድር ባይሳካ ሀገሪቱ ተመልሳ ወደ ጦርነት እንዳትገባ እና ለኢራን ጦርነት ተልዕኮ የተሰማራው ወታደራዊ ኃይል በአስገዳጅነት ከአባቢው እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ50 የሴኔቱ አባላት 48ቱ ውሳኔውን በድምፅ የደገፉ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ከሚመሩት የሪፐብሊካን ፓርቲ አራት ሰዎች ፕሬዚዳንቱ ወታደራዊ ኃይላቸውን ከኢራን እንዲያስወጡ የሚያዘውን ውሳኔ ደግፈዋል ተብሏል፡፡

እንደ አር ቲ ዘገባ፤ ውሳኔው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራንን በተመለከተ የሚከተሉት ፖሊሲ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ሴናተሮች የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ጥረቴን እያከበዱብኝ ነው ሲሉ ገልፀው፤ ውሳኔ የዘገየ እና ትርጉም አልባ ነው ማለታቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍106🤝2👌1
ከደብረማርቆስ ባህርዳር በረራ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደብረ ማርቆስ - ባሕር ዳር መደበኛ በረራ ሊጀምር ነው‼️
የደብረ ማርቆስ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ ለዓመታት ሲጠብቀው የነበረውና የልማት ምዕራፍ ማሳያ የሆነው የደብረ ማርቆስ (ንጉሥ ተክለሃይማኖት) አውሮፕላን ማረፊያ፣ የመጀመሪያውን ታሪካዊ በረራ ካስተናገደ በኋላ አሁን ደግሞ አዲስና ተደራሽ የበረራ መስመር ሊጀምር መሆኑ ታውቋል።

በመሆኑም የበረራ ቀናትን እንደሚከተለዉ አሳውቋል::
1.ከአዲስ አበባ ወደ ደበረ- ማረቆስ ደርሶ መልስ በየቀኑ:
2.ከደብረ ማረቆስ ወደ ባህር ዳር በሳምንት አራት ቀን (4) ሲሆን የበረራ ቀን ሰኞ፣ዕሮብ፣አርብና እሁድ ነው
3.ከባህር ዳር ወደ ደበረ ማረቆስ ደግሞ በሳምንት ሶስት ቀን (3) የበረራ ቀን ማክሰኞ፣ሃሙስና ቅዳሜ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ከሚቀጥለው አርብ ማለትም 19/10/2018ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎቱ እንደሚጀምር ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
30👍7💔3🎉1🙏1👌1🤪1
ጊቤ መርከብ መንገድ ጀመረች

ለአምስት ወራት ሻርጃ ወደብ አካባቢ የከረመችው ጊቤ መርከብ ትላንት ማምሻውን የሆርሙዝ ሰርጥን ማለፍ መቻሏ ታወቀ።

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የሆርሙዝ መተላለፊያ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች የፋርስ ባህረሰላጤ ወደቦች ላይ መህልቅ ጥለው እንዲጠባበቁ ተገደው ነበር።

ከነዚህም መካከል ጊቤ አንዷ ነበረች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍13🤡4🎉1🙏1👌1🤪1
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር የሚገኝ ቁልፍ ምሽግ ተቆጣጠረ
 
የሱዳን ጦር በብሉ ናይል ግዛት አዲስ በከፈተው ጥቃት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ አማፂያንን ምሽግ መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡
 
የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በተለያዩ ግንባሮች እየተጠናከረ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የሱዳን ሠራዊት በብሉ ናይል ክልል መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት በመክፈት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ ቁልፍ የዓማፂያን ምሽግ መቆጣጠሩን ገልጿል።
 
ሱዳን ትሪቢዩን እና የቻይናው «ዥንዋ» እንደዘገቡት፤ ወታደራዊ ዘመቻው ማክሰኞ ዕለት በጌሳን ወረዳ በ4ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ሥር በሚገኘው እግረኛ ብርጌድ የተካሄደ ሲሆን፤ ጥቃቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር በግምት አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙትን ከአቡ ዱግላ እና አሻምቦ ባሻገር ያሉ አካባቢዎችን ኢላማ ያደረገ ነው።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍7🤣4👀1🙊1
ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ባለሀብት ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በተለያዩ ሀገራት በበርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ስኬታማ ቢሆኑም በሞሮኮ ያፈሰሱት ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ ግን በአሁኑ ወቅት ከባድ ፈተና ገጥሞታል።

በተለይም በሀገሪቱ ብቸኛው የነዳጅ ማጣሪያ የሆነውና የባለሀብቱ ንብረት የሆነው ሳሚር ኩባንያ ወደ መንግሥት ይዞታነት እንዲዛወር የቀረበው የሕግ ረቂቅ በሞሮኮ ከፍተኛ ምክር ቤት ውድቅ ተደርጓል።

የሞሮኮ የከፍተኛ ምክር ቤት ይህ ኩባንያ በገጠሙት ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት ንብረቱ ተወርሶ ወደ መንግሥት እንዲዛወር የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በትኩረት ከመረመረ በኋላ ውድቅ ማድረጉ ታውቋል።

ይህ ውሳኔ በቢሊየነሩ እና በሞሮኮ መንግሥት መካከል ያለውን የከረረ ፍጥጫ ይበልጥ አባባሶታል።

ይህ ግዙፍ የማጣሪያ ፋብሪካ ላለፉት አሥርተ ዓመታት በታየበት የአስተዳደር ጉድለትና አስፈላጊው መዋዕለ ንዋይ ባለመፍሰሱ ምክንያት፣ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ የዕዳ ማጥ ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል። በዚህም ሳቢያ ፋብሪካው ከ2015 ጀምሮ ሥራውን ሙሉ በሙሉ ለማቆም ተገዷል።

በወቅቱ ሼክ አል-አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁም እስር ላይ መቆየታቸው ለኩባንያው አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ እንዳያገኙ በማድረግ ለፋብሪካው መዘጋት እንደ አንዱ ምክንያት ይጠቀሳል።

ይሁን እንጂ ሼክ አል-አሙዲ በኩባንያቸው (ኮራል ሞሮኮ ሆልዲንግ) አማካኝነት፣ ለፋብሪካው መዘጋት ተጠያቂው የሞሮኮ መንግሥት ነው የሚል ክስ መስርተዋል።

ባለሀብቱ ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት  በመውሰድ፣ ከሞሮኮ መንግሥት የ2.7 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እየጠየቁ ይገኛሉ።

የሞሮኮ መንግሥት በበኩሉ "ውድቀቱ የባለሀብቱ የአስተዳደር ድክመት ውጤት ነው" በሚል በሕግ እየተከራከረ ይገኛል።  

@Addis_Reporter
19🤔8👍2😢2🙊2
ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተወሰነ‼️
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው  በክልሉ በነበረው ግጭት በተለያየ ምክንያት ስራቸውን ለቀው ወደ ትጥቅ ትግል ገብተው ለነበሩ 2167 ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው 738 መምህራን፣ 92 የገቢ ተቋማት ሰራተኞች፣ 1337 (115  በማንነት ምክንያት በፈጠረ ግጭት ተሰናብተው የነበሩ) ሲቪል ሰርቢስ ሰራተኞች በድምሩ 2167 ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራ መደባቸው እንዲመለሱ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በውሳኔውም ከሚመደቡበት ቀን ጀምሮ የስራ መደባቸው የሚያስገኛቸውን ደሞዝ የሚያገኙ መሆናቸውን በግልፅ አመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤪15👍3👌1😎1
በጋምቤላ ክልል አጭር ቀሚስ የሚለብሱ ሴቶች 3ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እየተቀጡ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመቆጣጠርና የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ውሳኔዎች በመተግበር ላይ እንደሚገኙ  የክልሉ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን የአቦቦ ወረዳ ሴቶቸና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ውሳኔዎቹ ሊተላለፉ የቻሉት ልጆች ከወላጆች አቅም በላይ በመሆናቸው እና ትዕዛዝ ባለመስማታቸው ነው ሲል ፅ/ቤቱ አስታውቋል ።

ወላጆች መንግስት ይደግፈን ባሉት መሠረት ፕሮፖዛል ተቀርጾ እና ኮሚቴ ተዋቅሮ ፣ከፖሊስ ፣ከፍትህ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ውሳኔዎች ላይ እየተሰራ ይገኛል ። የአቦቦ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አዊሊ ኡጁሉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ሴቶች የሚለብሷቸው አጭር ቁመት ያላቸው ልብሶች የጥቃት ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲከታተሉና ልጆችም ከዚህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ የሚያስችሉ ጥብቅ መመሪያዎች መተላለፋቸውን ተናግሯል ።ይህንን ችግር ለመቅረፍ ለጥቃት አጋላጭ በሆነ መልኩ አጭር ልብሶችን ለብሰው በሚንቀሳቀሱ ሴቶች ላይ የ3ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መተላለፉን የተናገሩት ኃላፊዋ መመሪያውን ተላልፈው በተገኙት ላይ የቅጣት እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል ።

ዘገባው የብስራት ሬዲዮ ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22👍17🤔4🤷‍♂1👌1
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሐምሌ 8/2018 ዓ/ም ለሚጀመረው ሀገራዊ ጉባዔ ለምክክር የቀረጻቸውን 8 አጀንዳዎች ይፋ አድርጓል።

ምክክር የሚደረግባቸው 8 የተመረጡ አጀንዳዎች የትኞቹ ናቸው ?

1) አጀንዳ ቁጥር 1 የሀገር ግንባታ ጉዳይ፣

2) አጀንዳ ቁጥር 2 የፖለቲካ ስርዓት፣ የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ፣

3) አጀንዳ ቁጥር 3 የፌዴራል ከተሞች፥ አዲስ አበባና ድሬዳዋ

4) አጀንዳ ቁጥር 4 የሃይማኖት ጉዳዮች፣

5) አጀንዳ ቁጥር 5 የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣

6) አጀንዳ ቁጥር 6 ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ የአርሶ አደሮች እና የአርብቶ አደሮች ጉዳይ፣

7) አጀንዳ ቁጥር 7 ሙስና እና መልካም አስተዳደር

8) አጀንዳ ቁጥር 8 ሰላም ግንባታ

አጀንዳዎቹ በተለያዩ ክልሎች ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎችን በማመካከር የተገኙ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ ተናግረዋል።tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣147👍2
የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ዜጎች ወደ ምሥራቅ ሊቢያ ግዛት እንዳይገቡ ታገዱ።

ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ ወደ አውሮፓ መሻገር የሚፈልጉ የአራቱ አገራት ፍልሠተኞች በሊቢያ በኩል በሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሚያልፉ ይታወቃል።

የምሥራቅ ሊቢያ ባለሥልጣናት ይህን እገዳ የጣሉት፣ የውጭ ዜጎች ወደ አገሪቱ የሚገቡበትን ሁኔታ ለመቀየር በማስፈለጉ እንደሆነ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

እገዳው፣ ዲፕሎማቶችን፣ የቆንስላ ሠራተኞችንና ቤተሰቦቻቸውን እንዲኹም የቅጥር ፍቃድ ያላቸው በትምህርትና ሕክምና ዘርፍ የተሠማሩ የአገራቱን ሠራተኞች እንደማይመለከት ተገልጧል።

ባሁኑ ወቅት 900 ሺሕ ያህል የውጭ ዜግነት ያላቸው ፍልሠተኞች ሊቢያ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍43🤣3🤷‍♂1🥰1😢1👌1🤪1
ስምምነቱ 'የአሜሪካ ሽንፈት' መግለጫ ነው ስትል ኢራን ተናገረች
 
ጦርነቱን ለማቆም በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተደረገው ስምምነት "የአሜሪካ ሽንፈት መግለጫ" ነው ሲሉ የኢራን ተደራዳሪ ቡድን መሪ መሀመድ ባገር ጋሊባፍ ተናግረዋል።

ጋሊባፍ በአዘርባጃን በኢራን ቴሌቪዥን ስርጭት ላይ በተላለፈዉ መልዕክታቸዉ እንደተናገሩት "የኢስላማባድ ስምምነት የግፊት እና የማስገደድ ውጤት ሳይሆን የጀግናው የኢራን ህዝብ ተቃውሞ እና ስልጣን ውጤት ነው" ብለዋል።
 
በዚህም የኢስላማባድ የመግባቢያ ስምምነት የአሜሪካን ሽንፈት ማወጅ ሆኗል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከፍተኛ ተደራዳሪው መሀመድ ባገር ጋሊባፍ የመካከለኛው ምስራቅ የጸጥታ መዋቅርን የክልሉ ሀገራት ብቻ መወሰን አለባቸው ብለዋል።

"የውጭ ወታደራዊ ሃይሎችን ከአካባቢው መውጣት እንደ ስልታዊ አላማ እንቆጥረዋለን።

የቀጣናው የወደፊት እጣ ፈንታ በግጭት ሳይሆን በመስተጋብር እንዲወሰን በመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ ከክልል ውጭ ያሉ ወታደራዊ ኃይሎች የአለመረጋጋት መንስኤ ናቸው ሲሉ አክለዋል።
 
ጋሊባፍ ወደ ባኩ አዘርባጃን ባደረጉት ጉዞ እንደተናገሩት ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሀገራት ጋር "በውስጣዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ባለመግባት እና ሉዓላዊነትን በማክበር" ላይ ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ጥቃት እና ወረራ ማቆም አለባት በማለት የኢራንን አቋም ደግመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍9🤣3🤪2💯1
የተፈናቃዮቹ መሬት ለሚሊሻ ተሰጠ‼️

ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው አልተመለሱም በሚል መሬታቸው ለሚሊሻ መስጠት መጀመሩን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

👉ተፈናቃዮቹ ካልተመለሳችሁ መሬታቸሁ ለአካባቢው ሚሊሻ ሊሰጥ መሆኑን ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልፀው ነበር።

ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ተፈናቅለው በወሎ፣ ጃራ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ለቅቀው ወደ ወጡበት አካባቢ ባለመመለሳቸው መሬታቸውን ለሚሊሻና  ኮሬ ነጌኛ ለተባለው ኃይል እንዲሁም ለስራአጥ ወጣቶች ማከፋፈል መጀመሩን ገልፀውልናል።

እነዚህ ተፈናቃዮች በአካባቢው በነበረው ጥቃት ሸሽተው ወደ የወጡ ሲሆን ወደ ቀያቸው ለመመለስ አሁንም ስጋት እንዳለባቸው ይገልፃሉ።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢297🤔4💔3👍2🤣2🙊2
የቀድሞዋ  ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተሾሙ‼️

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ሳህለወርቅ ዘውዴን በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ (UNOWAS) የዋና ስትራቴጂያዊ ገምጋሚ አድርገው መድበዋል።

በቀጠናው ባላቸው ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ልምድ የተመረጡት ሳህለወርቅ፣ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ ለማካሄድ ኃላፊነታቸውን በዚህኛው ወር (ጁን) ማብቂያ ላይ በይፋ ይረከባሉ ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
59👍5😡5🥰2👌1💯1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍2
የማስተርስ ትምህርት አራት አመት‼️
"የማስተርስ ትምህርት ወደ 4 ዓመት ሊያድግ ይገባል " ተባለ‼️

የአሰራር ለውጥ ካልተደረገ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች እውቅና ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት ይፈጥራል ብሏል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጠው የሁለተኛ ዲግሪ (የማስተርስ) ትምህርት ፕሮግራም ከሁለት ዓመት ወደ አራት ዓመት ሊያድግ እንደሚገባ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ይህንን ያስታወቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰጠው ሙያዊ ማብራሪያ፣ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በሁለት ዓመት መደበኛ መርሃ ግብር እየተሰጠ ያለው የማስተርስ ትምህርት፣ አዲስ ከጸደቀው የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብና ከአለም አቀፍ በተለይም ከአውሮፓ ስታንዳርድ ጋር የማይገናኝ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህ ክፍተት በአስቸኳይ የማይስተካከል ከሆነ፣ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች የትምህርት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ወይም እውቅና (Authentication) ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት እንደሚሆን ባለስልጣኑ አስገንዝቧል።

ከእነዚህም መካከል በሀገራችን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ሳያመጡ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ከተማሩ በኋላ፣ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ የሚጠይቁት የብቃት ማረጋገጫ ጉዳይ ትልቅ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም ያጸደቀው የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብ፣ እውቅና ካላቸው የውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት የተገኙ የብቃት ማረጋገጫዎች በሀገሪቱ መመዘኛ መሰረት ተመዝነው እውቅና እንዲሰጣቸው ቢደነግግም፣ አሁን ያለው አሰራር ግን ይህንን ለመተግበር አስቸጋሪ አድርጎታል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዳመለከተው፣ ለአማራጭ የትምህርት ክሬዲት ስርአት (ECTS) በአውሮፓ (ከፍተኛ) የሆነው መስፈርት፣ በኢትዮጵያ ደንብ ውስጥ ' (ዝቅተኛ) ሆኖ ተቀምጧል። ይህንን ወደ ዓመት ሲተረጎም የማስተርስ ፕሮግራም ደንቡ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ የ4 ዓመት ፕሮግራም መሆን እንዳለበት ያስገድዳል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም ለትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ ቢገለጽም እስካሁን ምንም ምላሽ አልተገኘም ተብሏል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡2014🥱3👍2👀2😢1
ጄኔራል ባጫ ደበሌ የአፍሪካ ህብረት የህወሓትን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠየቁ

በቅርቡ ጊዜያዊ አስተዳደሩን በማፍረስ ወደ ፕሬዝዳንትነት የተመለሱት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ አሳሳቢ የተባለ አዋጅ በመላ ክልሉ ማወጃቸው ይታወሳል። ይህንኑ አዋጅ መመልከታቸውን የገለጹት በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ፤ “የክተት አዋጅ እና የግዳጅ ምልመላ” በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ የአዋጁ ዋነኛ ዓላማ ሕዝቡን ለጠቅላላ ጦርነት መቀስቀስ እንደሆነ አመልክተዋል።

ከዚህ ጦርነት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ በስተጀርባ የራስን ጦር እንደገና ማጠናከር እና ታጣቂዎችን እንደ "ቅጥረኛ ተዋጊ" ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ግጭት መላክ የሚሉ ግቦች እንዳሉ የገለጹት ጄኔራል ባጫ፤ የአፍሪካ ህብረት ይህን የህወሓት ድርጊት በአደባባይ እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ህብረቱ ይህ አዋጅ በአስቸኳይ እንዲሰረዝ፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመለስና የፖለቲካ ሂደቶች እንዲቀጥሉ ግፊት እንዲያደርግ አምባሳደሩ አሳስበዋል። ሊፈጠር የሚችለውን አላስፈላጊ ቀውስ ለመከላከልም የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2015🤣3👍2😎1