አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.9K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
IMF በኢራን ጦርነት ሳቢያ ለኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በቅርቡ በነበረው የኢራን ጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን የኤኮኖሚ ቀውስ ለመታደግ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተወሰኑ የአፍሪቃ ሃገራት
የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ሊያሳድግ ነው።

ድጋፉን ከማሳደግ በተጨማሪ ገንዘቡን በፍጥነት ለማቅረብ ማቀዱ ተሰምቷል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጁሊ ኮዛክ እንዳሉት በድጋፉ ኢትዮጵያ፣ ጋምቢያ እና ቡርኪና ፋሶ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ በተጨማሪ ማላዊ አዲስ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ ከተቋሙ ጋር የተፋጠነ ውይይት እያደረገች መሆኑን ጠቁመዋል።

የIMF የአፍሪካ ዳይሬክተር ዘይን ዘይዳን በዋሽንግተን በሰጡት መግለጫ፣ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የአፍሪካ ቀጠና "ከባድ ፈተና" ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አሁን የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም በጦርነቱ ምክንያት የተስተጓጎለው የባህረ ሰላጤው  ሀገራት የኃይል እና የነዳጅ ምርት ወደ ቀድሞ ቦታው ለመመለስ ከ6 እስከ 7 ወራት ሊፈጅ እንደሚችል ጠቁመዋል።

የነዳጅ ምርት አቅርቦቱ መቋረጥ በአፍሪካ ሀገራት ላይ ከፍተኛ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋ ንረትን አስከትሏል።

በተጨማሪ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔም የ25 ሚሊዮን ዶላር የትብብር መርሃግብር አካል የሆነውን 6.1 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ከስምምነት ደርሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍8
የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ስራ ላይ ያዋሉትን “ጨቋኝ ሕግ” እንዲሽሩ ሂውማን ራይትስ ዎች ጥሪ አቀረበ

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች “የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ” ለማካሄድ እና “ተቃውሞን ለመቅጣት ስልጣን ይሰጣል”  ያለውን በትግራይ ክልል ስራ ላይ የዋለ ህግ እንዲሻር ለክልሉ ባለስልጣናት ጥሪ አቀረበ።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ያጸደቀው  ህግ፤ “ኤርትራ ከምትከተለው አስገዳጅ የብሔራዊ አገልግሎት ጋር ምስስሎሽ ያለው ነው” ሲልም ድርጅቱ ተችቷል።

መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች ባለፉት ሳምንታት አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተውን ሕግ በተመለከተ ጠንከር ያለ ጥሪ ያቀረበው ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 16፤ 2018 ባወጣው መግለጫ ነው።

የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ምክትል ኃላፊ ላቴሺያ ባድር የክልሉ ባለስልጣናት “ሲቪል ሰዎችን ለውትድርና በመመልመልና የሚቃወሙትን በመቅጣት” ለቀጠለው ፖለቲካዊ ውጥረት ምላሽ መስጠት እንደማይኖርባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍94👌1🤝1
ፖርቹጋል የመጀመሪያ ድሏን አሳካች

ፖርቹጋል ከኡዝቤክስታን ጋር ያደረገችውን የአለም ዋንጫ ሁለተኛ ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች።

የፖርቹጋልን የድል ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልዶ 2x ፣ ኑኖ ሜንዴዝ ፣ ራፋኤል ሊያኦ እና ኩሳኖቭ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ አስረኛ የአለም ዋንጫ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ፖርቹጋል ማሸነፏን ተከትሎ ነጥቧን አራት በማድረስ ምድቡን መምራት ጀምራለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍6🤣5
ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የሸቀጦች ዋጋ በበለጠ ከመንግስት ለሚያገኙት አገልግሎት የሚከፍሉት ክፍያ እየፈተናቸው ነው ተባለ።

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት አገልግሎቶች ላይ የሚታየው የታሪፍ ማሻሻያ እና ተገልጋዩ አገልግሎት ለማግኘት የሚጠየቀው ወጪ ከፍተኛ መሆን የነዋሪውን ኑሮ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎበታል።

በዚህ ምክንያትም የሸማቹ መብት እየተጣሰ በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል።

የመንግሥት አገልግሎቶች ትርፍ ማጋበሻ ሳይሆኑ ዜጎችን ለመደገፍ፣ ማኅበራዊ ፍትሕን ለማረጋገጥና በሕግ የተጣሉ ግዴታዎችን ለመወጣት የሚቀርቡ መሠረታዊ አገልግሎቶችና መብቶች ቢሆኑም በአሁኑ ወቅት በጅምላ እየታዩ ያሉ የዋጋ ጭማሪዎች ሸማቹን ማኅበረሰብ ተስፋ የሚያስቆርጡ፣ ወደ ከፋ ድህነት የሚገፉና ዜጎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ በማድረግ በሚከፍሉት ግብር የመገልገል የዜግነት መብታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ብሏል ድርጅቱ፡፡

የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ያደረጓቸው የዋጋ ጭማሪዎች የማክሮ-ኢኮኖሚውን ሕመምና የሕዝቡን የደመወዝ ወለል ያላገናዘቡ፣ የሸማቹን ኪስ ሙሉ በሙሉ የሚያራቁቱ መሆናቸውን ያነሳ ሲሆን ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአዲስ ፓስፖርት ክፍያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ዋጋ፣ የቴሌኮም አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች ላይ የታወጣን ጭማሬ እንደማሳያ አንስቷል፡፡

በእነዚህ እና በሌሎች የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ጭማሬዎች አገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ እየፈተነው እንደሆነ ተመልክተናል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል፡፡

ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
35👍15💯6👌2
በደቡብ አፍሪካ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተሰጠውን የሰኔ 30 (June 30) የመጨረሻ ቀነ-ገደብ ተከትሎ ሊነሱ የሚችሉ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር መንግሥት ከ600 ሚሊዮን ራንድ በላይ ወጪ የሚጠይቅ መጠነ-ሰፊ የጸጥታ ጥበቃ ዘመቻ ይፋ ማድረጉን eNCA ዘገበ።

የሀገሪቱ ፖሊስ ለማንኛውም ዓይነት ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፣ የመከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ግጭትና ሁከት የሚቀሰቀስ ከሆነ እንዳስፈላጊነቱ ጦሩ ሊሰማራ እንደሚችል ጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት በርካታ የአገር ውስጥ ቡድኖች ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ከሰኔ 30 በፊት ደቡብ አፍሪካን ለቀው እንዲወጡ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎቻቸውን የማስወጣት ስራ እየሰሩ ናቸው።

በሌላ በኩል ፤ " ስደተኞች ጓዛችሁን ጠቅልላችሁ ውጡልን " እያሉ የሚገኙት ቡድኖች ከዚህ ቀደም ዶክመንት የሌላቸውን ብቻ ሳይሆን ህጋዊ ዶክመንት ያላቸውን ጭምር ኢለማ ያደረጉ ጥቃቶችን እንደሚፈጸሙ ከነዋሪዎች የተገኙ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20😡8👍2😢1
አፈሳው ደርግን ያስንቃል-ጄኔራሉ‼️
«በትግራይ የወጣው አዋጅ አንድ መንግስት ወደ ፋሽሽትነት ካልተቀየረ በቀር አያወጣውም»‼️
👉“የነ ደብረፅዮን ቡድን በትግራይ ክልል እየተከተሉት ያሉት ስልት ሻዕብያ እና ደርግን የሚያስንቅ አፈና ነው‼️”-ጀነራል ገ/ፃድቃን
«አንዲት ላም የወለደችው ጥጃዋ ድንገት ሲሞት ነገር ግን ወተቷን ማለብ ስትፈልግ የሟችዋ ጥጃ ቆዳ ገለባ ሞልተህ ለእናቲቱ ታሳያታለህ። ይህ የምታደርገው ለሟ ወተት እንድትሰጥህ ነው። ከዚያ በኃላ ታልባታለህ። 'ዓርሲ' ይባላል፤ ሁሉም ሰው ያውቀዋል። በትግራይም እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ነው። የፖለቲካና የወታደራዊ መሪዎች፣ በወታደራዊ መሪዎች ጫና የቀድሞዋ ህወሓት ለህዝቡ ያሳዩትና ህዝቡን ይበዘብዙታል፣ ትግራይም ያልቧታል። አልቧታልም። ስንት ወንጀል ፈጽመዋል። በወንጀላቸው መቀጠልና መጠየቅም ይፈራሉ»

ጋዜጠኛ «ይህን በማድረግ በስልጣን መቀጠል ይችላሉ?»
«ደርግ እንዳልቀጠለ ሁሉ እነዚህም አይቀጥሉም»
ጀነራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ ለ #TBS የሰጠው ቃለ መጠይቅ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍2
ሰርተፊኬት የሌላቸው የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች በስራ ላይ እንዳይሳተፉ የሚከለክል አሰራር ሊተገበር ነው።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎችን ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስገድድ አዲስ አሰራር እያዘጋጀ ነው።

አሰራሩ ደረጃ በደረጃ የሚተገበር ሲሆን፣ ወደፊት ሰርተፊኬት የሌለው ማንኛውም ባለሙያ በየትኛው ደረጃ በኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ እንዳይሳተፍ ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።

ምንም እንኳን ሂደቱ ዓመታትን ሊወስድ ቢችልም፣ በአሁኑ ወቅት የዝግጅትና የተግባር እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍95
የኢሎን ማስክ የሀብት ማሽቆልቆል፦ በሳምንት ውስጥ 350 ቢሊዮን ዶላር አጣ!

​የስፔስ ኤክስ  አክሲዮን በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ፣ ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ የግል ሀብት ኪሳራ አስተናገደ።

ኩባንያው ለመጀመሪያ ጊዜ የቦንድ ሽያጭ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የአክሲዮን ዋጋው በ30% አካባቢ በመውረዱ፣ ማስክ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ የ350 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል።

​በፎርብስ ስሌት መሠረት፣ የባለሀብቱ ጠቅላላ ሀብት ከ1.45 ትሪሊዮን ዶላር ወደ 1.1 ትሪሊዮን ዶላር ወርዷል።

ማስክ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ኩባንያው ይፋዊ የአክሲዮን ሽያጭ (IPO) ባደረገ ማግስት የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር መሆን ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ባለፉት ቀናት የስፔስ ኤክስ አክሲዮን በ16.4% በመውደቁ የኩባንያውን የገበያ ዋጋ በ928 ቢሊዮን ዶላር አሳንሶታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🙊4👍3👀1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍21
በሳዑዲ በምሕረት አዋጅ የተለቀቁ 320
ኢትዮጵያውያን በሰላም ሀገራቸው ገቡ!


መንግሥት ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ምክንያት በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1 ሺህ 655 ኢትዮጵያውያን መካከል የመጀመሪያዎቹ 320 ተመላሾች አዲስ አበባ ገብተዋል። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ ይህ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት በሪያድ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና በጂዳ የሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በቅንጅት ባከናወኑት ጥረት የተመዘገበ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም መንግሥት ኅብረተሰቡ በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሐሰት የማህበራዊ ሚዲያ ማታለያዎች ሳይደለል ከሕገወጥ የውጭ ሀገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል። ዜጎችን ለከፍተኛ ችግር የሚዳርጉ ሕገወጥ ደላሎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩት የተቀናጁ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ አረጋግጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍7😡2🙏1👌1
በ5 ቀናት ብቻ 40 ዜጎች ውሃ ውስጥ ሰምጠው መሞታቸውን የፈረንሳይ መንግስት አስታወቀ።

የበጋው/ሰመር ሙቀት ከቁጥጥር ውጭ ያደረጋቸው ዜጎች ባገኙት የውሃ አካላት ለመዋኘት እየሞከሩ ነው ያለው የሚዲያ መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ 40 የሚሆኑ ሰዎች በመስመጥ ብቻ ህይወታቸውን አጥተዋል ብሏል።

በፈረንሳይ ሆነ በአውሮፓ በዚህ ሰሞን ለፍተኛ ሙቀት እንሰሚከሰትና ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መንግስታት ሲያሳስቡ ቆይተዋል።

እንደሚባለው የሚቀት መጠኑ ለዚህ ቀደም ከተመዘገበው ከፍ ያለ ነው። በፈረንሳይ ዛሬ በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 40 ዲግሪ ሴሊሺየስ ሙቀት መመዝገቡ ተገልጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢54👍2
የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች ከኢራን ጦርነት እንዲወጡ የሚያስችል ውሳኔ ተላለፈ

የአሜሪካ ሴኔት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱን ወታደራዊ ሀይሎች ከኢራን ጦርነት እንዲያስወጡ የሚያዘውን ውሳኔ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የውሳኔ ሀሳቡ የተላለፈው የአሜሪካ እና የኢራን ተደራዳሪዎች ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በስዊዘርላንድ እየተወያዩ ባለበት እና በቴክኒካል ድርድሮች ላይ ከስምምነት በደረሱበት ወቅት ነው፡፡

ውሳኔው በስዊዘርላንድ እየተካሄደ ያለው ድርድር ባይሳካ ሀገሪቱ ተመልሳ ወደ ጦርነት እንዳትገባ እና ለኢራን ጦርነት ተልዕኮ የተሰማራው ወታደራዊ ኃይል በአስገዳጅነት ከአባቢው እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ50 የሴኔቱ አባላት 48ቱ ውሳኔውን በድምፅ የደገፉ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ከሚመሩት የሪፐብሊካን ፓርቲ አራት ሰዎች ፕሬዚዳንቱ ወታደራዊ ኃይላቸውን ከኢራን እንዲያስወጡ የሚያዘውን ውሳኔ ደግፈዋል ተብሏል፡፡

እንደ አር ቲ ዘገባ፤ ውሳኔው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራንን በተመለከተ የሚከተሉት ፖሊሲ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ሴናተሮች የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ጥረቴን እያከበዱብኝ ነው ሲሉ ገልፀው፤ ውሳኔ የዘገየ እና ትርጉም አልባ ነው ማለታቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍106🤝2👌1
ከደብረማርቆስ ባህርዳር በረራ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደብረ ማርቆስ - ባሕር ዳር መደበኛ በረራ ሊጀምር ነው‼️
የደብረ ማርቆስ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ ለዓመታት ሲጠብቀው የነበረውና የልማት ምዕራፍ ማሳያ የሆነው የደብረ ማርቆስ (ንጉሥ ተክለሃይማኖት) አውሮፕላን ማረፊያ፣ የመጀመሪያውን ታሪካዊ በረራ ካስተናገደ በኋላ አሁን ደግሞ አዲስና ተደራሽ የበረራ መስመር ሊጀምር መሆኑ ታውቋል።

በመሆኑም የበረራ ቀናትን እንደሚከተለዉ አሳውቋል::
1.ከአዲስ አበባ ወደ ደበረ- ማረቆስ ደርሶ መልስ በየቀኑ:
2.ከደብረ ማረቆስ ወደ ባህር ዳር በሳምንት አራት ቀን (4) ሲሆን የበረራ ቀን ሰኞ፣ዕሮብ፣አርብና እሁድ ነው
3.ከባህር ዳር ወደ ደበረ ማረቆስ ደግሞ በሳምንት ሶስት ቀን (3) የበረራ ቀን ማክሰኞ፣ሃሙስና ቅዳሜ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ከሚቀጥለው አርብ ማለትም 19/10/2018ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎቱ እንደሚጀምር ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
30👍7💔3🎉1🙏1👌1🤪1
ጊቤ መርከብ መንገድ ጀመረች

ለአምስት ወራት ሻርጃ ወደብ አካባቢ የከረመችው ጊቤ መርከብ ትላንት ማምሻውን የሆርሙዝ ሰርጥን ማለፍ መቻሏ ታወቀ።

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የሆርሙዝ መተላለፊያ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች የፋርስ ባህረሰላጤ ወደቦች ላይ መህልቅ ጥለው እንዲጠባበቁ ተገደው ነበር።

ከነዚህም መካከል ጊቤ አንዷ ነበረች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍13🤡4🎉1🙏1👌1🤪1
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር የሚገኝ ቁልፍ ምሽግ ተቆጣጠረ
 
የሱዳን ጦር በብሉ ናይል ግዛት አዲስ በከፈተው ጥቃት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ አማፂያንን ምሽግ መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡
 
የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በተለያዩ ግንባሮች እየተጠናከረ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የሱዳን ሠራዊት በብሉ ናይል ክልል መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት በመክፈት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ ቁልፍ የዓማፂያን ምሽግ መቆጣጠሩን ገልጿል።
 
ሱዳን ትሪቢዩን እና የቻይናው «ዥንዋ» እንደዘገቡት፤ ወታደራዊ ዘመቻው ማክሰኞ ዕለት በጌሳን ወረዳ በ4ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ሥር በሚገኘው እግረኛ ብርጌድ የተካሄደ ሲሆን፤ ጥቃቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር በግምት አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙትን ከአቡ ዱግላ እና አሻምቦ ባሻገር ያሉ አካባቢዎችን ኢላማ ያደረገ ነው።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍7🤣4👀1🙊1
ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ባለሀብት ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በተለያዩ ሀገራት በበርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ስኬታማ ቢሆኑም በሞሮኮ ያፈሰሱት ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ ግን በአሁኑ ወቅት ከባድ ፈተና ገጥሞታል።

በተለይም በሀገሪቱ ብቸኛው የነዳጅ ማጣሪያ የሆነውና የባለሀብቱ ንብረት የሆነው ሳሚር ኩባንያ ወደ መንግሥት ይዞታነት እንዲዛወር የቀረበው የሕግ ረቂቅ በሞሮኮ ከፍተኛ ምክር ቤት ውድቅ ተደርጓል።

የሞሮኮ የከፍተኛ ምክር ቤት ይህ ኩባንያ በገጠሙት ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት ንብረቱ ተወርሶ ወደ መንግሥት እንዲዛወር የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በትኩረት ከመረመረ በኋላ ውድቅ ማድረጉ ታውቋል።

ይህ ውሳኔ በቢሊየነሩ እና በሞሮኮ መንግሥት መካከል ያለውን የከረረ ፍጥጫ ይበልጥ አባባሶታል።

ይህ ግዙፍ የማጣሪያ ፋብሪካ ላለፉት አሥርተ ዓመታት በታየበት የአስተዳደር ጉድለትና አስፈላጊው መዋዕለ ንዋይ ባለመፍሰሱ ምክንያት፣ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ የዕዳ ማጥ ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል። በዚህም ሳቢያ ፋብሪካው ከ2015 ጀምሮ ሥራውን ሙሉ በሙሉ ለማቆም ተገዷል።

በወቅቱ ሼክ አል-አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል በቁም እስር ላይ መቆየታቸው ለኩባንያው አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ እንዳያገኙ በማድረግ ለፋብሪካው መዘጋት እንደ አንዱ ምክንያት ይጠቀሳል።

ይሁን እንጂ ሼክ አል-አሙዲ በኩባንያቸው (ኮራል ሞሮኮ ሆልዲንግ) አማካኝነት፣ ለፋብሪካው መዘጋት ተጠያቂው የሞሮኮ መንግሥት ነው የሚል ክስ መስርተዋል።

ባለሀብቱ ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት  በመውሰድ፣ ከሞሮኮ መንግሥት የ2.7 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እየጠየቁ ይገኛሉ።

የሞሮኮ መንግሥት በበኩሉ "ውድቀቱ የባለሀብቱ የአስተዳደር ድክመት ውጤት ነው" በሚል በሕግ እየተከራከረ ይገኛል።  

@Addis_Reporter
19🤔8👍2😢2🙊2
ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተወሰነ‼️
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው  በክልሉ በነበረው ግጭት በተለያየ ምክንያት ስራቸውን ለቀው ወደ ትጥቅ ትግል ገብተው ለነበሩ 2167 ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው 738 መምህራን፣ 92 የገቢ ተቋማት ሰራተኞች፣ 1337 (115  በማንነት ምክንያት በፈጠረ ግጭት ተሰናብተው የነበሩ) ሲቪል ሰርቢስ ሰራተኞች በድምሩ 2167 ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራ መደባቸው እንዲመለሱ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በውሳኔውም ከሚመደቡበት ቀን ጀምሮ የስራ መደባቸው የሚያስገኛቸውን ደሞዝ የሚያገኙ መሆናቸውን በግልፅ አመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤪15👍3👌1😎1
በጋምቤላ ክልል አጭር ቀሚስ የሚለብሱ ሴቶች 3ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እየተቀጡ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመቆጣጠርና የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ውሳኔዎች በመተግበር ላይ እንደሚገኙ  የክልሉ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን የአቦቦ ወረዳ ሴቶቸና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ውሳኔዎቹ ሊተላለፉ የቻሉት ልጆች ከወላጆች አቅም በላይ በመሆናቸው እና ትዕዛዝ ባለመስማታቸው ነው ሲል ፅ/ቤቱ አስታውቋል ።

ወላጆች መንግስት ይደግፈን ባሉት መሠረት ፕሮፖዛል ተቀርጾ እና ኮሚቴ ተዋቅሮ ፣ከፖሊስ ፣ከፍትህ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ውሳኔዎች ላይ እየተሰራ ይገኛል ። የአቦቦ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አዊሊ ኡጁሉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ሴቶች የሚለብሷቸው አጭር ቁመት ያላቸው ልብሶች የጥቃት ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲከታተሉና ልጆችም ከዚህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ የሚያስችሉ ጥብቅ መመሪያዎች መተላለፋቸውን ተናግሯል ።ይህንን ችግር ለመቅረፍ ለጥቃት አጋላጭ በሆነ መልኩ አጭር ልብሶችን ለብሰው በሚንቀሳቀሱ ሴቶች ላይ የ3ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መተላለፉን የተናገሩት ኃላፊዋ መመሪያውን ተላልፈው በተገኙት ላይ የቅጣት እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል ።

ዘገባው የብስራት ሬዲዮ ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22👍17🤔4🤷‍♂1👌1
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሐምሌ 8/2018 ዓ/ም ለሚጀመረው ሀገራዊ ጉባዔ ለምክክር የቀረጻቸውን 8 አጀንዳዎች ይፋ አድርጓል።

ምክክር የሚደረግባቸው 8 የተመረጡ አጀንዳዎች የትኞቹ ናቸው ?

1) አጀንዳ ቁጥር 1 የሀገር ግንባታ ጉዳይ፣

2) አጀንዳ ቁጥር 2 የፖለቲካ ስርዓት፣ የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ፣

3) አጀንዳ ቁጥር 3 የፌዴራል ከተሞች፥ አዲስ አበባና ድሬዳዋ

4) አጀንዳ ቁጥር 4 የሃይማኖት ጉዳዮች፣

5) አጀንዳ ቁጥር 5 የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣

6) አጀንዳ ቁጥር 6 ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ የአርሶ አደሮች እና የአርብቶ አደሮች ጉዳይ፣

7) አጀንዳ ቁጥር 7 ሙስና እና መልካም አስተዳደር

8) አጀንዳ ቁጥር 8 ሰላም ግንባታ

አጀንዳዎቹ በተለያዩ ክልሎች ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎችን በማመካከር የተገኙ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ ተናግረዋል።tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣147👍2