አዲስ ሪፖርተር - NEWS
እገታ‼️ ዛሬ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ጠዋት ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በሰላም ይጓዙ የነበሩ 5 የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ራያ መሆኒ መግቢያ ላይ በህወሓት ሰራዊት መታገታቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። የታጋቾቹ 96% የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው ሱሉ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ካለው ወታደራዊ አፈሳ ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መሃል ሀገር እየሸሹ ይገኛሉ። Via : አዩዘሀበሻ @Addis_Reporter…
ትናንት ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ ታግተው የነበሩ የ5 አውቶብስ መንገደኞች በከፊል መለቀቃቸው ተሰምቷል።
ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ መሆኒ አካባቢ በህወሓት ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አምስት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች መለቀቃቸው የተለፀ ሲሆን መንገደኞቹም ከሰዓታት እገታ በኋላ በከፊል ተለቀዋል ተብሏል።ከፊሎቹ በታጣቂዎቹ እንደተወሰዱ ታውቋል
አብዝሃኞቹ መንገደኞች ወጣቶች ስለነበሩ ለወታደራዊ አፈሳ የተደረገ እንደነበር በትግርኛ ተዘግቦ ተመልክተናል።
@Addis_Reporter

👍11❤3
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

❤2👍2
የውጭ ሀገር ዜጎችን በማገት ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የጠየቁ ሦስት ፓኪስታናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ
የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው ዝሻን ካሊድ፣ ፍርዝ መሃመድ እና መሀመድ ጀናይድ የተባሉ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሰኔ 4 እና ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አትሌቶች መንደር ነው።
ተጠርጣሪዎቹ በተከራዩት የመኖሪያ ቤት ውስጥ የህንድና የባንግላዴሽ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች በመያዣነት በመጠቀም የግል ተበዳዮችን በገመድ በማሰርና በፕላስተር በማፈን ከ15 እስከ 30 ሚሊየን ብር በመጠየቅ ጥቃት አድርሰውባቸዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በዚህ ብቻ ሳያበቁ ሰኔ 11ቀን 2018 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የገቡ 4 የህንድ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ ከ15 እስከ 25 ሺህ የህንድ ሩፒ አስልኩ በማለት ድብደባ ሲፈጽሙባቸው እንደነበር የግል ተበዳዮች ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
የወንጀሉ መፈጸም መረጃ የደረሠው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ተገቢውን የፍርድ ቤት መያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀሙበት ከነበረው ቢላዋ፣ ገመድና ፕላስተር እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።

❤13🤣8👍7
ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእስራኤል ወታደሮች በሶማሊላንድ መሰማራታቸው ተገለጸ
እስራኤል ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና መስጠቷን ተከትሎ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ወታደሮቿን በሃርጌሳ ማሰማራቷ ተሰምቷል። እንደ ዘገባው ከሆነ፣ እስራኤል በአሁኑ ወቅት 50 የሚጠጉ ወታደሮችን በሶማሊላንድ ያሰፈረች ሲሆን፣ እነዚህ ወታደሮችም በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረሰው የሁለትዮሽ የጸጥታ ስምምነት መሠረት የተሰማሩ ናቸው።
ወታደራዊ ስምሪቱ በዋናነት ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የእስራኤል ዜጎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ለዚህም እንደ ስልታዊ ምክንያት የቀረበው ወታደሮቹ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ እንዲቀላቀሉ እና የውጭ ኃይል መኖሩን በግልጽ እንዳይታወቅ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ ተመልክቷል።
እነዚህ የጦር አባላት በአሁኑ ወቅት በሁለት ዋና ዋና ተግባራት ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ተገልጿል፤ እነሱም የሶማሊላንድን ፖሊስ እና የጦር ኃይል የማሰልጠን ስራ እንዲሁም በእስራኤልና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን የጸጥታ ስምምነት የማስፈጸም ስራ ናቸው።
እስራኤል ሶማሊላንድን በይፋ እውቅና ከሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗ የሚታወስ ሲሆን፣ በቀጣይም በሶማሊላንድ ያላትን የወታደራዊ አባላት ቁጥር የመጨመር እና ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው ወታደራዊ ጣቢያ የመገንባት ፍላጎት እንዳላት ተጠቁሟል። ይህ እንቅስቃሴ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ካደረገችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በኋላ በቀጣናው እየታዩ ካሉ ጂኦ-ፖለቲካዊ ለውጦች ጋር ተያይዞ ትኩረትን ስቧል።

❤9👍5🥰3👀2😡2🤔1👌1🫡1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥
🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።
የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia

❤6
አርቲስት ካሙዙ ካሳ ምርጫውን ማሸነፉን አስታወቀ
በየካ ክፍለ ከተማ በብልፅግና ፓርቲ ለምርጫ ቀርቦ የነበረው አርቲስት ካሙዙ ካሳ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ድምፅ ተሰጥቶት ማሸነፉን ይፋ አድርጓል። አርቲስቱ የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ ለመራጮች ምስጋናውን አቅርቧል።
ታዋቂው አርቲስት ካሙዙ ካሳ፣ በየካ ክፍለ ከተማ በተካሄደው ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን ወክሎ በመወዳደር፣ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
አርቲስቱ ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፣ ለምርጫው መሳካት ላደረጉት ድጋፍ የአካባቢውን ነዋሪዎች እና መራጮቹን አመስግኗል። “እንደ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘታችን እና በአካባቢው ማሸነፋችን ታላቅ ድል ነው” ሲል የገለጸው አርቲስት ካሙዙ፣ በድል አድራጊነት ስሜት ኢትዮጵያ አሸንፋለች የሚል መልዕክት አስተላልፏል።

🤣64❤15🤔5😢3👍2🤝1
“ቤት ያላገኘ ተፈናቃይ ካለ ሥልጣኔን እለቃለሁ” — አቶ ግርማ ሰይፉ
የአዲስ አበባ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በከተማዋ በነበረው የኮሪደር ልማት ምክንያት ተፈናቅሎ ምትክ ቤት ወይም መሬት ያላገኘ አንድም ሕጋዊ ሰው አለመኖሩን አስታወቁ።
ካርታ ወይም የቀበሌ ቤት ኖረውት ምትክ ያጣ ሰው ካለ በገዛ ፈቃዳቸው ከሥልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ ልማቱ ለሀገር ጥቅም የተሠራ መሆኑን ገልጸው፤ ሆኖም ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በደል የደረሰባቸው ወገኖች መኖራቸውን አልሸሸጉም።
በሌላ በኩል፣ የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ ዘመናዊነትና ውበት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም፤ በሂደቱ ወቅት በቂ ዝግጅት፣ ግልጽነትና ተመጣጣኝ ምትክ አላገኘንም የሚሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ መቆየታቸው ይታወቃል።
@Seledadotio

🤣36❤14👍6🤪3🙉3
ሊዮኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫ ታሪክ አዲስ ንጉሥ
የአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ ተጫዋች በመሆን አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ። ሜሲ ይህንን ታሪካዊ ድል ያሳካው አሁን በአርጀንቲና እና በኦስትሪያ መካከል እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ ባስቆጠረው ግብ ነው።
በጨዋታው 38ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ የሜሲን የዓለም ዋንጫ የግብ መጠን ወደ 17 ከፍ በማድረግ፣ የጀርመኑን አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዜ የነበረውን የ16 ግቦች ክብረ ወሰን በይፋ እንዲያፈርስ አስችሎታል።
በጨዋታው 10ኛው ደቂቃ ላይ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት መቶ ሳይጠቀምበት ቀርቶ የነበረ ቢሆንም፣ በመቀጠል ባሳየው ብቃት ኳሷን መረብ ላይ በማሳረፍ አዲስ ታሪክ መጻፍ ችሏል። ይህ ድል ሜሲ በ6ኛው ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ያመዘገበው ሲሆን፣ የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ድንቅ አጀማመር በይበልጥ ደምቆ እንዲታይ አድርጎታል።
ሜሲ ከዚህ ቀደም የነበረውን የክሎዜን ክብረ ወሰን ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ያደረገው በአልጄሪያ ላይ በነበረው የምድብ ጨዋታ ላይ ነበር። አሁን ግን ይህንን ክብረ ወሰን ብቻውን በመቆጣጠር የእግር ኳስ ዓለሙን የ"GOAT" ደረጃውን በይበልጥ አጠናክሯል።

👍23❤18🤣8⚡2🤪2
“ኢራን ጦርነቱን አሸንፋለች!”— 92 በመቶው እስራኤላዊ‼️
በዕብራይስጥ ዩኒቨርሲቲ እና በአጋም ላብስ በጋራ የተካሄደ አዲስ የሕዝብ አስተያየት ጥናት እንደሚያሳየው፣ 92 በመቶ የሚሆነው የእስራኤል ሕዝብ ከአሜሪካና ከእስራኤል ጋር በተደረገው ጦርነት ኢራን የበላይነቱን አግኝታ አሸናፊ ሆና ወጥታለች ብሎ ያምናል።
በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደራዳሪነት በዚህ ሳምንት በአሜሪካና በኢራን መካከል የተደረሰውንና በሊባኖስ ያለውን የሒዝቦላህ ተኩስ አቁም የሚያካትተውን ስምምነት አብዛኛው የእስራኤል ማህበረሰብ በአሉታዊ ጎኑ ነው የተመለከተው። በጥናቱ መሠረት 82.9 በመቶው እስራኤላውያን በኢራን ላይ የተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ የእስራኤልን የረጅም ጊዜ ደህንነት አዳክሟል ብለው የሚያምኑ ሲሆን፣ 86 በመቶዎቹ ደግሞ የጦርነቱን ውጤት በፍፁም አልወደዱትም።
ይህ የሕዝብ አስተያየት ጥናት ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እጅግ መጥፎ ዜና ይዞ የመጣ ሲሆን፣ 72.5 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መሪው “እስራኤል ትልቅ ድል ተቀዳጅታለች፣ የህልውና ስጋቱንም አስወግዳለች” ሲሉ የተናገሩትን ንግግር ፈጽሞ አላመናቸውም። ይልቁኑ 87.8 በመቶው ማህበረሰብ ሀገሪቱ ያስቀመጠችውን ወታደራዊ ግብ ሙሉ በሙሉ አላሳካችም ወይም ጥቂቱን ብቻ ነው ያሳካችው የሚል እምነት አለው።
በሀገር ውስጥ እየበረታ የመጣው የፖለቲካ ጫና ኔታንያሁ የትራምፕን የሰላም ጥረት እንዲያደናቅፉ ሊያስገድዳቸው እንደሚችል የአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች የገለጹ ሲሆን፣ የእስራኤል ቀኝ አክራሪው የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር “ለእያንዳንዱ የእስራኤላዊት እናት እንባ፣ አንድ ሺህ የሊባኖስ እናቶች ማልቀስ አለባቸው፤ መላው ሊባኖስ መቃጠል አለበት!” ሲሉ ይበልጥ ጦርነቱ እንዲቀጥል እየገፋፉ ነው።

❤15👍7🙉3🤣1🙊1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው የአውሮፕላን አምራች ዲ ሃቪላንድ ኩባንያ ካዘዛቸው ዘመናዊ የዲ.ኤች.ሲ-6 ትዊን ኦተር ክላሲክ 300-ጂ አውሮፕላኖች ውስጥ የመጀመሪያውን ተረከበ
እነዚህ ልዩ አውሮፕላኖች የአየር መንገዱን የቀጠና አገልግሎት ከማጠናከራቸው ባሻገር አስቸጋሪ በሆኑ መልክአ ምድራዊ አቀማመጦች ውስጥ በቀላሉ መብረር የሚችሉ በመሆናቸው ለቱሪዝም፣ ለአየር ላይ ቅኝቶች፣ ለጤና አገልግሎቶች እና ለሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖራቸዋል ተብሏል።

❤18👍2
"መርጌታ ነኝ እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለሁ" በማለት 625 ሺህ ብር ያጭበረበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
ገንዘቡን የተጭበረበረው ግለሰብ በደረሰበት የሥነ ልቡና ቀውስ ፀበል ገብቶ ነበር። አብርሀም ሰርኬ የሚባለው ግለሰብ በሐሰት መር ጌታ ነኝ በማለት አቶ ደነቀው ሙሉቀን ከተባለና በዳንሻ ከተማ በሆቴል ስራ ላይ ከተሰማራ ግለሰብ 625ሺህ ብር አታሎ መውሰዱን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሰው ተናግረዋል።
ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ "እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለው" በማለት ታህሳስ 2018ዓ.ም ብሩን አታሎ መስዷል።
ይህን ብር ከወሰደ በኋላ በተጨማሪ ሦስት መቶ ሺህ ብር ካልጨመረክ "ቤተሰብህን በሙሉ በመተት አጠፋብሃለው" በማለት በተበዳይ ላይ አደገኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም መቆየቱ ተመላክቷል።
የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የፍ/ቤት መያዥያ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪው በተገኘበት በቁጥጥር ስር እንዲውል በፃፈው የትብብር ደብዳቤ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክትትል ቡድን ጋር በመተባበር ግለሰቡ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በሉማሜ ከተማ አስተዳደር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎል።
አቶ ደነቀው ሙሉቀን በደረሰበት የማታለል ወንጀል ምክንያት ለከፍተኛ አምዕሮዊ ሥነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጦ በፀበል ቦታ እንደቆየ ተሰምቷል።

🤣41❤12👍3🤔2
ኢትዮጵያን ለቆ ሊወጣ ነው‼️
ቶታል ነዳጅ ማደያ ኢትዮጵያን ለቆ ሊወጣ ነው‼️
በኢትዮጵያ ውስጥ ከ75 አመታት በላይ በነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የቆየው ቶታል ኢነርጂስ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ማቀዱ ተገለፀ፡፡
በመላው ኢትዮጵያ ወደ120 ያህል ማደያዎች ያሉት ይህ ተቋም ንብረቱን በሙሉ ለኦላ ኢነርጂ ወይንም ለቀድሞው ኦይልሊቢያ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
አፍሪካ ቢዝነስ ባቀረበው ዘገባ ሁለቱ ድርጅቶች በሽያጩ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልፆ በምን ያህል ዋጋ ግብይቱ እንደተከናወነ ያለው ነገር የለም፡፡
ቶታል ኢነርጂስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከብራዚል፣ ፓኪስታንና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት የነዳጅ ማደያዎቹን ሸጦ የወጣ ሲሆን ይህ እርምጃውም የዚህ አካል እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

❤9🤔6👍5👀2
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
❤6👍2
"መርጌታ ነኝ እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለሁ" በማለት 625 ሺህ ብር ያጭበረበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
ገንዘቡን የተጭበረበረው ግለሰብ በደረሰበት የሥነ ልቡና ቀውስ ፀበል ገብቶ ነበር። አብርሀም ሰርኬ የሚባለው ግለሰብ በሐሰት መር ጌታ ነኝ በማለት አቶ ደነቀው ሙሉቀን ከተባለና በዳንሻ ከተማ በሆቴል ስራ ላይ ከተሰማራ ግለሰብ 625ሺህ ብር አታሎ መውሰዱን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሰው ተናግረዋል።
ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ "እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለው" በማለት ታህሳስ 2018ዓ.ም ብሩን አታሎ መስዷል።
ይህን ብር ከወሰደ በኋላ በተጨማሪ ሦስት መቶ ሺህ ብር ካልጨመረክ "ቤተሰብህን በሙሉ በመተት አጠፋብሃለው" በማለት በተበዳይ ላይ አደገኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም መቆየቱ ተመላክቷል።
የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የፍ/ቤት መያዥያ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪው በተገኘበት በቁጥጥር ስር እንዲውል በፃፈው የትብብር ደብዳቤ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክትትል ቡድን ጋር በመተባበር ግለሰቡ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በሉማሜ ከተማ አስተዳደር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎል።
አቶ ደነቀው ሙሉቀን በደረሰበት የማታለል ወንጀል ምክንያት ለከፍተኛ አምዕሮዊ ሥነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጦ በፀበል ቦታ እንደቆየ ተሰምቷል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
ገንዘቡን የተጭበረበረው ግለሰብ በደረሰበት የሥነ ልቡና ቀውስ ፀበል ገብቶ ነበር። አብርሀም ሰርኬ የሚባለው ግለሰብ በሐሰት መር ጌታ ነኝ በማለት አቶ ደነቀው ሙሉቀን ከተባለና በዳንሻ ከተማ በሆቴል ስራ ላይ ከተሰማራ ግለሰብ 625ሺህ ብር አታሎ መውሰዱን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሰው ተናግረዋል።
ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ "እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለው" በማለት ታህሳስ 2018ዓ.ም ብሩን አታሎ መስዷል።
ይህን ብር ከወሰደ በኋላ በተጨማሪ ሦስት መቶ ሺህ ብር ካልጨመረክ "ቤተሰብህን በሙሉ በመተት አጠፋብሃለው" በማለት በተበዳይ ላይ አደገኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም መቆየቱ ተመላክቷል።
የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የፍ/ቤት መያዥያ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪው በተገኘበት በቁጥጥር ስር እንዲውል በፃፈው የትብብር ደብዳቤ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክትትል ቡድን ጋር በመተባበር ግለሰቡ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በሉማሜ ከተማ አስተዳደር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎል።
አቶ ደነቀው ሙሉቀን በደረሰበት የማታለል ወንጀል ምክንያት ለከፍተኛ አምዕሮዊ ሥነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጦ በፀበል ቦታ እንደቆየ ተሰምቷል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣14❤6👍3
ጋምቤላ‼️
በትናንትናው ዕለት ሰኞ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ሁለት ወጣቶች በጩቤ ተወግተው ተገደሉ።
ትናንት ሰኞ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:15 አካባቢ በጋምቤላ ከተማ ወሎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአኙዋክ ተወላጅ አንጅ ሀበሻ በስለት ተወግቶ ሞቷል።
አሁንም በትናንትናው ዕለት ምሽት 11:00 አካባቢ አደባባይ ላይ ሌላ አንድ ወጣት ገድለዋል።
ግድያውን ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ ነበር።
ምክንያታቸው ደግሞ ባለፈው ሳምንት አንድ የአኝዋክ ቤሄር ተወላጅ የሆነ በፌደራል ፖሊሰ ተገድሎ ነበር።
በዚህ ምክንያት ሁሉም መከላከያና ፌደራል ፖሊሰ ሀበሻ ነው የኛን ሰው የገደለ ብለው ሰለሚያሰቡ እነዚህን ወጣቶች በቀን በጩቤ ወግተው የገደሏቸው ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

❤10👍3😢2🤯1
ውጤትዎን ይመልከቱ!
ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት መታየት ጀምሯል።
ውጤትዎን ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et
ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

❤12👍3💔3🥰1
አቤል ብርሃኑ ከዩኤኢ የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ ተበረከተለት!
ታዋቂው የቪዲዮ ይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ (Golden Visa) ተበርክቶለታል።
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የረጅም ጊዜ መኖሪያ ፍቃድ ማግኘት፣ በተለይም ደግሞ ሙሉ መብትን የሚያጎናጽፈውን የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ ባለቤት መሆን በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ታዋቂ እና ከባድ ከሚባሉ የነዋሪነት እውቅናዎች መካከል አንዱ ነው።
ይህ ታላቅ እድል አብዛኛውን ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ 2 ሚሊዮን ድርሃም ወይም በግምት ከ95 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ ኢንቨስት ላደረጉ ትልልቅ ባለሀብቶች፣ በከፍተኛ የትምህርት ደረጃቸው እና ማህበራዊ አቅማቸው የወር ገቢያቸው ከ30 ሺህ ድርሃም በላይ ለሆኑ ባለሙያዎች፣ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ግለሰቦች፣ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እንዲሁም ለሰብአዊ መብት እና ለበጎ አድራጎት ሰራተኞች የሚሰጥ ልዩ ስጦታ ነው።
ይሁን እንጂ ስኬታማውና በብዙ ሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ኢትዮጵያዊው የዲጂታል ይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ፤ ይህንን ታላቅ ዕድል በማህበራዊ ሚዲያ ባለው ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና በፈጠራ ስራ አቅራቢነት ዘርፍ ከኤምሬትስ መንግስት ለመቀበል በቅቷል።

👍52❤28🎉4🥰2👌2
የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን በበጀት አመቱ የግብይት መጠኑን ወደ 13.9 ቢሊዮን ብር ማድረሱን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት የኅብረት ሥራ ማህበራትን የግብይት ድርሻ ለማሳደግ ባከናወናቸው የተቀናጁ ስራዎች የግብይት መጠናቸውን 13 ቢሊዮን 950 ሚሊዮን 502 ሺህ 752 ብር ማድረስ መቻሉን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ እንደገለጸው፤ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በማህበራቱ መደበኛ ሱቆች፣ በሰንበት ገበያዎች፣ በበዓላት ባዛሮችና በተቋማቱ አማካኝነት ለነዋሪው ቀርበዋል።
ለዚህ ስኬት መገኘትም ማህበራቱ ያከናወኗቸው 200 የገበያ ትስስሮች እና የተዘጋጁ 52 ኤግዚቢሽኖችና ባዛሮች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ጠቁሟል።
እንደ ኮሚሽኑ ከሆነ በበጀት አመቱ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት 206 አዳዲስ የህብረት ስራ ማህበራት የተደራጁ ሲሆን፣ 31 ሺህ 957 አዳዲስ አባላትን ማቀፍ ተችሏል። ከዚህ ጎን ለጎን 101 ሺህ 747 አባላትን ወደ ነባር ማህበራት የመቀላቀል እና የ41 ማህበራትን አቅም በውህደት የማጠናከር ስራ መሰራቱን አመልክቷል።

❤10👍3
#Tesla
ባለፈው አርብ በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የቴስላ (ሞዴል 3) ተሽከርካሪ ከመንገድ ወጥቶ ከመኖሪያ ቤት ጋር በመጋጨቱ በቤት ውስጥ የነበረች የአንዲት ሴት ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
የአሜሪካ ብሔራዊ የመንገዶች ትራፊክ ደኅንነት አስተዳደር (NHTSA) በተሽከርካሪው ላይ ልዩ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።
ፖሊስ የመኪናው ሹፌር በአደጋው ወቅት በአደገኛ ዕጽም ሆነ በአልኮል ተጽእኖ ስር አልነበረም።
አሽከርካሪው ለመርማሪዎች እንደተናገረው አደጋው የደረሰው መኪናው #አውቶማቲክ ሆኖ በራሱ እየተሽከረከረ በነበረበት ጊዜ ነው።
በመንግሥት አካላት እየተካሄደ ስላለው የቴክኒክ ምርመራ ማብራሪያ የተጠየቀው የቴስላ ኩባንያ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

❤5👍2