አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
እገታ‼️
ዛሬ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ጠዋት ​ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በሰላም ይጓዙ የነበሩ 5 የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ራያ መሆኒ መግቢያ ላይ በህወሓት ሰራዊት መታገታቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
​የታጋቾቹ 96% የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው ሱሉ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ካለው ወታደራዊ አፈሳ ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መሃል ሀገር እየሸሹ ይገኛሉ።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢229👍6
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች 

ከጠዋቱ 2፡30-9፡30

👉ጎተራ ኮንዶሚኒየም ፣ወንጌላዊት ህንጻ፣ ዩኒማክ፣ መስቀል ፍላወር ፣ ተሻለ ጋራዥ፣ ዳኞችና አቃቢ ሕግ ቢሮ ፣ ኮስሞስ ሕንፃ፣ ድሪም ላይነር፣ ጎተራ ውሃ እና አካባቢው፣

👉የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም፣ ካራ ከብት ተራ፣ ጥሩ መናፈሻ፣ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል እና አካባቢው፣
 
👉ኖህ አደባባይ ፣ ካፒታል ሲሚንቶ፣ ፔትራም ጁስ፣ ሰበታ በከፊል፣ ዲማማ፣ ዓለም ገና ዳለቲ ሀምበሳ እና አካባቢው፣

👉ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ ጫፍ ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና ፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴል ፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ እና አካባቢው፣

👉ሰበታ ከተማ ፣ ቀበና ውሃ ማምረቻ ፣ ዲማ ሆስፒታል፣ ዋን ውሃ፣ አባሃዋ ትሬዲንግ ፣ ቦሌ ሁላሳ ፣ ሰበታ፣ ዓለም ገና፣ ጎጀብ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 3፡00-9፡00

👉አምባሳደር  ሪል እስቴት፣ አያት ቤቶች ዞን 1፣2፣8፣ መሪ 40/60፣ 72 ቤቶች በከፊል እና አካባቢው ፣ 

ከጠዋቱ 3፡00-10፡00

👉ጉርድ ሾላ፣ ትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት፣ ግብርና ምርምር፣ ጃክሮስ አደባባይ በስተጀርባ እና አካባቢው፣

👉ቦሌ ሚካኤል፣ ሩዋንዳ፣ ቦሌ ሚኪ ካፌ ቡልቡላ ሸክላ ቤቶች፣ አየርማረፊያ ራዳር፣ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ የቻይናዎች ከሬሸር፣ ግስላ ሰፈር፣ ሸገር ዳቦ እና አካባቢው የሃይል አቅርቦት ይቋረጣል።

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4👌1
ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸነፈ

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ። በዛሬው ዕለት በተገለጸው ውጤት መሠረት፣ ብልጽግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በክልል ምክር ቤቶች አብላጫ መቀመጫዎችን በማሸነፍ አብዛኛውን ድምፅ ማግኘቱ ተረጋግጧል።

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በማጠቃለያ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። ቦርዱ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ብልጽግና ፓርቲ በፌዴራል ደረጃ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል ምክር ቤቶች ከፍተኛውን የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት በመቆጣጠር በአብላጫ ድምፅ አሸናፊ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣47😡2417👍8🤷‍♂2🎉2🤪2🙉1
#Breaking
የኢራን ተደራዳሪዎች አዳራሽ ለቀው ወጡ‼️
በዛሬው ዕለት የአሜሪካ እና የኢራን ተደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ ተገናኝተው የነበረ ሲሆን አሁን በወጡ መረጃዎች መሰረት የኢራን ተደራዳሪዎች አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።

የኢራን ተደራዳሪዎች ከአሜሪካ ልዑካን ጋር የጋራ ፎቶ አንነሳም ብለዋል።

ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ 'ሆርሙዝን ከዘጋችሁ ሀገር አይኖራችሁም፣ሆርሙዝንም በሀይል እወስደዋለሁ' በማለታቸው ነው ተብሏል።

ሄዝቦላህን እያስታጠቃችሁ እስራኤል ስታጠቁ እኛ ደግሞ በቦንብ ኢራንን እንደበድባለን ሲሉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቀዋል።

ኢራን በሊባኖስ ያለው ጦርነት ካልቆመ ድርድር የለም ያለች ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ኢራን ለሄዝቦላህ የምታደርገውን ድጋፍ ካላቆመች ኢራንን እንደበድባለን ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2619😢3😡3🤔1🙊1
ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ቀረጥ ለመጣል ዛቱ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ፣ አሜሪካ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ የትራንዚት ታሪፍ እንደምትጥል አስጠነቀቁ።

ቅዳሜና እሁድን በካምፕ ዴቪድ እያሳለፉ የሚገኙት ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ጦርነትን ለማቆም የተደረሰው የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በዚህ ወሳኝ የውሃ መስመር ላይ ለ60 ቀናት ያህል ያለምንም ክፍያ በነፃ የመንቀሳቀስ መብትን እንደሚፈቅድ አስምረውበታል። ሆኖም ግን፣ ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ካልተጠናቀቀ አሜሪካ የራሷን ታሪፍ እንደምጥል  ገልጸዋል።

ትራምፕ አክለውም፣ ከዚህ ታሪፍ የሚሰበሰበው ገንዘብ አሜሪካ «ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላደረገችው፣ ለምታደርገውና ወደፊትም ለምታበረክተው አገልግሎት ወጪዎቿን ለመተካት የሚውል መሆኑን ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፕሬዝዳንቱ ከኢራን ጋር በተፈራረሙት ስምምነት ላይ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ታሪፍ ጉዳይን በተመለከተ በአሜሪካ  ከፍተኛ ትችት እየገጠማቸው ይገኛል።

የአሜሪካውያን ዋነኛ ስጋት ስምምነቱ ለ60 ቀናት ብቻ ከክፍያ ነፃ መሆንን የሚያረጋግጥና ወደፊት ሊጣሉ የሚችሉ ክፍያዎችን በግልጽ የማይከለክል መሆኑ ላይ ነው። ይህ ሁኔታ የዓለም አቀፉን የነዳጅና የንግድ መስመር ዋስትናን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል በሚል ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል። ዶናልድ ትራምፕ ግን የመጨረሻው ውሳኔ በአሜሪካ እጅ እንደሆነና ጥቅማቸውን ለማስከበር ወደኋላ እንደማይሉ በፅኑ አቋም እየተሟገቱ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🤣7👍2🕊2👌1
በ11 የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ እንዲደረግ በቦርዱ ተወሰነ።

አምስቱ የምርጫ ክልሎቹ በሶማሌ ክልል የሚገኙ መሆናቸዉን ቦርዱ ይፋ እያደረገ ባለዉ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዉጤት ማሳወቂያ መርሃ ግብር ላይ ተገልፆል።

ሀማሬ፥ ዳራቶሬ፥ ሀርገሌ፥ ባቱ ዝዋይ፥ ቤጊ፥ አርሆሳ፥ ጨንቻ፥ ሶሮ 1፥ ጠንባሮ ፥ ሀደካላ፥ ሀደካለ ምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ይደረግባቸዋል ተብሏል።

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ሶሬ1 እና ጠምባሮ ምርጫ ክልሎች ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይደረግላቸዋል።

ሀርገሌ ፥,ዳሮር፥ ሀደካላ ፥ ሀማሬ እና ዳራቶሬ የተባሉ በሶማሌ ክልል የሚገኙ የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ያደርጋሉ።

ባቱ ዝዋይ እና ቤጌ ምርጫ ክልሎች በኦሮሚያ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምረጫ የሚደረግበት ይሆናል ተብሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ጨንቻ ምርጫ ክልል ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይካሄዳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪9👍8🙊5🥱43
በ10 ብር የሞባይል ካርድ ሰበብ የጎረቤቱን 8 ጥርሶች ያረገፈው ግለሰብ በ8 ዓመት 9 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ!

አምቦ፡ በኦሮሚያ ክልል፣ አምቦ ከተማ አስተዳደር ቶርበን ኩታዬ ቀበሌ ውስጥ በአነስተኛ የገንዘብ መጠን በተነሳ አለመግባባት፤ በጎረቤቱ ላይ የከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰው የ54 ዓመቱ አቶ ተሬሣ ገመቹ የ8 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት ቅጣት ተላለፈበት።

የአምቦ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አቡሽ ማሞ እንደገለጹት፤ ክስተቱ የተፈጠረው ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡15 አካባቢ ነው።

ተከሳሽ አቶ ተሬሣ ለዓመታት በጎረቤትነት አብረዋቸው ከኖሩት ከአቶ ቱራ ታደሰ አነስተኛ ሱቅ የ10 ብር የሞባይል ካርድ ለመግዛት ብቅ ይላሉ። ካርዱን ከገዙ በኋላም "የተሞላ ካርድ ነው የሰጠኸኝ፤ ሌላ ቀይርልኝ" በማለት የ18 ዓመቱን የሱቁን ሻጭ (የባለቤቱን ልጅ) ይጠይቃሉ። ወጣቱ በበኩሉ "ካርዱ ትክክለኛ ነው፤ ችግሩ ያለው አንተ ጋር ነው" የሚል ምላሽ ሲሰጥ አለመግባባቱ ይጀምራል።
ተከሳሹ "ቆይ አሳይሀለሁ" በማለት ዛቻ ሰንዝረው የሄዱ ሲሆን፤ ትንሽ ቆይተውም ሁለት ሰዎችን አስከትለው ለፀብ ወደ ሱቁ ይመለሳሉ።

በሱቁ አካባቢ የተፈጠረውን ግርግር የተመለከቱት የአቶ ቱራ አባት (የሱቁ ባለቤት)፣ በልጃቸውና በጎረቤታቸው መካከል የተፈጠረውን ንትርክ በሰላም ለመፍታት ጥረት አድርገዋል። ሆኖም ተከሳሽ አቶ ተሬሣ አባትና ልጅን "አጭበርባሪዎች ናችሁ" በማለት ዘለፋ ውስጥ ገቡ። ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሲሆንም፤ ተከሳሹ ባነሱት ትልቅ ድንጋይ ገላጋይ የሆነውን የሱቁን ባለቤት አፋቸው ላይ ክፉኛ ይመቷቸዋል።

በዚህም አሳዛኝ ድርጊት ተበዳይ አቶ ቱራ የላይኛውና የታችኛው 8 ጥርሶቻቸው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ፤ በአምቦ ሆስፒታልም የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በሰጠው ፈጣን ጥቆማ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር በማዋል፣ የህክምና ማስረጃዎችን አጠናቆ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ልኳል። አቃቤ ህግም "ታስቦ በተፈጸመ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ" ክስ መስርቶበታል።

የምርመራ መዝገቡን የተመለከተው የአምቦ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት፣ ተከሳሽ አቶ ተሬሣ ገመቹ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የ8 ዓመት ከ9 ወር እስራት ውሳኔ አስተላልፎበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢6👍4👀1
ለጫካ ፕሮጀክት የሚፈርሱ መንደሮች‼️
በአዲስ አበባ በጫካ ፕሮጀክት ማስፋፊያ ምክንያት በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፥ 6 እና 7 ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ውጥረት እና ስጋት ሰፍኗል። ሰሞኑን በተካሄዱ የቀበሌ ስብሰባዎች ላይ የአካባቢው ባለስልጣናት ነዋሪዎች ቤቶቻቸውን በአስቸኳይ በአንድና በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲለቁና ምንም አይነት ድርድር የሌለው ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን መሰረት ሚዲያ ከነዋሪዎች አረጋግጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡35😢1513💔6👍3🙉2🤷‍♂1🙏1🕊1🤣1👀1
በ2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ብር ይረጋጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ለፓርላማ ገለጹ

​በዚህ በጀት ዓመት ብር በ15 በመቶ ቢቀንስም፣ በመጪው በጀት ዓመት የ9.8 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመዘገብ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ይህ ዕድገት በግብርና (7.1%)፣ በኢንዱስትሪ (11.6%) እና በአገልግሎት (8.5%) ዘርፎች የሚመራ ነው።

​ነገር ግን በሩቅ ምሥራቅ ግጭት ሳቢያ በጨመረው የነዳጅ ዋጋ ምክንያት የሀገሪቱ የገቢ ዕቃዎች ወጪ 25.8 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።

ከዚህ ውስጥ 6 ቢሊዮን ዶላሩ ለነዳጅ የሚውል ነው።

​መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለማረጋጋት አዳዲስ መመሪያዎችን እያወጣ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክ ጨረታዎችንና የንግድ ባንኮችን ሚና በማጠናከር በሕጋዊና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ወደ 11 በመቶ ማውረድ መቻሉን ገልጿል።

እንዲሁም የውጭ ዕዳን መልሶ ለማዋቀር ድርድሮች እየተደረጉ ነው።
ካፒታል ጋዜጣ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2813🤣10👍41😢1🙏1👌1
ግብፅ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ የመጀመሪያ ድሏን አገኘች።

ኒው ዚላንድን የገጠመችው ግብፅ በፊን ሱርማን ግብ ስትመራ ብትቆይም፤ ሙስጠፋ ዚኮ፣ ሙሐመድ ሳላህ እና ማህሙድ ትርዝጌት በሁለተኛው አጋማሽ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ግብፅ 3 ለ 1 አሸንፋለች።

ግብፅ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘችው ድል፤ ምድቡን በአራት ነጥብ እንድትመራ እና ወደ ጥሎ ማለፉ የመሸጋገር ዕድሏ ሰፊ እንዲሆን አድርጓል።

ለዓለም ዋንጫው እንግዳ የሆነችው አፍሪካዊት ደሴት ኬፕ ቨርዴ አሁንም ተጨማሪ ነጥብ አግኝታለች።

በመጀመሪያ የምድብ ስምንት ጨዋታዋ ከስፔን ጋር ያለ ግብ የተለያየችው ሀገር፤ ሌሊቱን ከሁለት ጊዜ ሻምፒዮኗ ኡራጓይ ጋር ሁለት አቻ ወጥታለች።

ባለመሸነፍ ጉዞዋ የቀጠለችው ኬፕ ቨርዴ፣ ሁለት ነጥብ በመያዝ በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ወደ ጥሎ ማለፉ የመሸጋገር ተስፋን ሰንቃለች።

በምድብ ሰባት ቤልጂየም ከኢራን ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍9🤯4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስራኤል በተገንጣይዋ የሶማሊያ ግዛት ሶማሊላንድ የበርበራ ወደብ የባሕር ኃይሏን ለማሠማራት እያጤነች እንደሆነ ተዘገበ

​እስራኤል 'የዶልፊን ደረጃ' ሰርጓጅ መርከቦቿን ጨምሮ የባሕር ኃይል ጦሯን በኤደን ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ በሚገኘው የበርበራ ወደብ ለማስፈር ማቀዷን የአውሮፓ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሁለቱ ሀገራት ግን ለዘገባው ይፋዊ ማረጋገጫ አልሰጡም።

ከዘገባዎቹ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 እስራኤል በርበራን እንደ ባሕር ኃይል ሥራ ማዕከል የመጠቀም ዕድሎችን እያጠናች ነው፣

🟠 ሶማሊላንድ ከእስራኤል ጋር ምንም ዓይነት የወታደራዊ ዕዝ ስምምነት አለማድረጓን በይፋ በማስተባበል የውጭ ኢንቨስትመንት እና ወደቦቿን ለባሕር አገልግሎት መዋላቸውን ቀደስታ እንደምትቀበል ገልጻለች፣

🟠 የእስራኤል ባለሥልጣናት በዘገባዎቹ ዙሪያ አስተያየት አልሰጡም፣

🟠 በርበራ በኤደን ባሕረ ሰላጤ ቁልፍ የባሕር መስመሮች ላይ ያላት መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ፤ ወደ የመን እና ቀይ ባሕር ቀጣና የሚያመሩ የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ ለመከታተል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖራታል።

✈️ በሕንድ ውቅያኖስ–ቀይ ባሕር ቁልፍ የባሕር መስመሮች ላይ የሚገኘው በርበራ ወደብ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂካዊ የንግድ እና ሎጅስቲክስ ማዕከል እየሆነ በመምጣቱ ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎቶችን እየቀሰቀሰ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍3😡3
ኢዜማ በ7ኛዉ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት ቀዳሚዉ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ማጠናቀቁን ገለፀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ ኢዜማ ሀገር አቀፉ ምርጫዉ ከነእንከኖቹም ቢሆን በሰላም በመጠናቀቁ ደስተኛ ነኝ ሲል መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ፓርቲዉ ለውድድር በቀረበባቸው ቦታዎች 13 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 73 የክልል እና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን በድምሩ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚው ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ማጠናቀቁን አስታዉቋል።

ኢዜማ ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ባሉት ዓመታት ጠንካራ ጎኖቹን በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩበትን ክፍተቶች በስትራቴጂ እና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራት በመሙላት ተጨባጭ የተፎካካሪ ፓርቲነት ሚናውን ጊዜ ሳያባክን የሚጀምረው ተግባር መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ፓርዉ አክሎም ገዢ ሆኖ እንዲቀጥል ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ እና ለውድድሩ ተሳታፊዎች የእንኳን ደስያላችሁ መልዕክቱን አሥተላልፏል፡፡

በተጨማሪም አሸናፊው ፓርቲ ከዛሬ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባትና ፍትሐዊ የፖለቲካ ምህዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲሠራ፤ አማራጭ ሃሳቦችን እንዲሰማ፤ እንዲሁም ትችቶችን በሆደ ሰፊነት እያስተናገደ የሀገሪቱን ዴሞክራሲ በጋራ ለመገንባት ቁርጠኛ እንዲሆን ጥሪዉን አቅርቧል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪1514👍4🤯2🤔1
ተኩስ‼️
ትናንት ሰኔ 14_10_2018 ዓ.ም ጀምሮ የህወሓት ታጣቂ ቡድን በአፋር ሰሜናዊው ዞን_2 (ክብላት ረሱ) መስተዳድር መጋሌ ወረዳ ሂዳና አራዱ ቀበሌዎች ላይ በከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍተው እንደነበር ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

👉ታጣቂዎቹ የያሎ_መጋሌ እና መጋሌ_አብአላ መስመር ለመቆጣጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑን መረጃው ያመላክታል።
👉ጥቃቱ በከባድ መሳሪያ(ዲሽቃና፣ሞርቴር ፣ብሬንና ስናይፔር) የተደገፈ ሲሆን ታጣቂዎቹ የደረሱበትን ቤት፣ ንብረትና ጫካን ጨምሮ በእሳት አቃጥለዋል።

ተኩሱ በአካባቢው በሚገኝ የአፋር የፀጥታ ሀይሎች ካምፕን ኢላማ ያደረገ ሲሆን በተኩሱ የደረሰውን ጉዳት ማወቅ አልተቻለም።

ታጣቂዎቹ የተለያዩ መንደሮችን (አፍዳባ፣ አሞማ፣ባዳኖይታ፣ አሸዴ፣ዒዲቦራና ሚስራ) የተቆጣጠሩ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በቦታው መደበኛ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የሌለ በመሆኑ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍9😢3
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
እገታ‼️ ዛሬ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ጠዋት ​ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በሰላም ይጓዙ የነበሩ 5 የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ራያ መሆኒ መግቢያ ላይ በህወሓት ሰራዊት መታገታቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ​የታጋቾቹ 96% የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው ሱሉ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ካለው ወታደራዊ አፈሳ ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መሃል ሀገር እየሸሹ ይገኛሉ። Via : አዩዘሀበሻ @Addis_Reporter…
ትናንት ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ ታግተው የነበሩ የ5 አውቶብስ መንገደኞች በከፊል መለቀቃቸው ተሰምቷል።

​ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ መሆኒ አካባቢ በህወሓት ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አምስት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች መለቀቃቸው የተለፀ ሲሆን መንገደኞቹም ከሰዓታት እገታ በኋላ በከፊል ተለቀዋል ተብሏል።ከፊሎቹ በታጣቂዎቹ እንደተወሰዱ ታውቋል

አብዝሃኞቹ መንገደኞች ወጣቶች ስለነበሩ ለወታደራዊ አፈሳ የተደረገ እንደነበር በትግርኛ ተዘግቦ ተመልክተናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍113
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
2👍2
የውጭ ሀገር ዜጎችን በማገት ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የጠየቁ ሦስት ፓኪስታናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው ዝሻን ካሊድ፣ ፍርዝ መሃመድ እና መሀመድ ጀናይድ የተባሉ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሰኔ 4 እና ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አትሌቶች መንደር ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በተከራዩት የመኖሪያ ቤት ውስጥ የህንድና የባንግላዴሽ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች በመያዣነት በመጠቀም የግል ተበዳዮችን በገመድ በማሰርና በፕላስተር በማፈን ከ15 እስከ 30 ሚሊየን ብር በመጠየቅ ጥቃት አድርሰውባቸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በዚህ ብቻ ሳያበቁ ሰኔ 11ቀን 2018 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የገቡ 4 የህንድ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ ከ15 እስከ 25 ሺህ የህንድ ሩፒ አስልኩ በማለት ድብደባ ሲፈጽሙባቸው እንደነበር የግል ተበዳዮች ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የወንጀሉ መፈጸም መረጃ የደረሠው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ተገቢውን የፍርድ ቤት መያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀሙበት ከነበረው ቢላዋ፣ ገመድና ፕላስተር እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13🤣8👍7