ኔዘርላንድ ስዊድን ላይ የጎል ናዳ አዘነበች
የኔዘርላንድ አጥቂዎች ኃያልነት እና የስዊድን ተከላካዮች መፈተን በታየበት ማራኪ ፍልሚያ ኔዘርላንድ የ5 ለ 1 ፍፁም አሸናፊ ሆናለች።
በእውነት የኔዘርላንድን ስለታም የአጥቂ መስመር የስዊድን ተከላካዮች ሊቋቋሙት ፈፅሞ አልቻሉም።
ጨዋታው ገና እንደተጀመረ ብሪያን ብሮቢ በ5ኛው እና በ17ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ፈጣን ግቦች ኔዘርላንዶች የጨዋታውን መንፈስ ቀድመው ተቆጣጥረውታል።
ከእረፍት መልስም ኮዲ ጋክፖ በ47ኛው እና በ54ኛው ደቂቃ መረቡን በማንቀጥቀጥ የግብ መጠኑን ከፍ አድርጎታል።
ምንም እንኳን አንቶኒ ኢላንጋ በ59ኛው ደቂቃ ለስዊድን አንዲት የማስተጽናኛ ግብ አስቆጥሮ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም፤ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በ89ኛው ደቂቃ ክሪሴንሲዮ ሰመርቪል ድንቅ የሆነች አምስተኛ ግብ በማስቆጠር የስዊድንን የሽንፈት ፅዋ አብዝቶታል።
ጎል አዳኝ የሚባሉት ዮከሬሽን እና አይዛክን የያዘው የስዊድን ብሄራዊ ቡድን ምንም ሳይፈይድ ከሜዳ ወጥቷል።
@Addis_Reporter

❤15👍8😡3👌2🎉1
መረጃ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀጣዩ በጀት ዓመት 502 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት አቀረበ።
ረቂቅ በጀቱ ከዘንድሮው በጀት የ43 በመቶ ብልጫ አለው።
ከበጀቱ ውስጥ፣ 71 በመቶው ለድህነት ቅነሳ እና ከዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተያያዙ እቅዶችን ለማሳካት እንደሚውል ተገልጧል።
በጀቱ፣ የልማት ስትራቴጂዎችን፣ የነዋሪዎችን የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት አቅርቦት ማሳደግን በተለይም መንገድን፣ ውሃን፣ መኖሪያ ቤትን፣ ጽዳትን፣ ትራንስፖርትንና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልን እንዲሁም ትምህርትን፣ ጤናን እና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች የሚደረግ ድጎማን ጨምሮ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ማሻሻልን ታሳቢ ያደረገ መኾኑን አስተዳደሩ አስታውቋል።
በተያዘው በጀት ዓመት የፌደራል ድጎማ ያላተመደበላት ከተማዋ፣ በቀጣዩ የፌደራሉ መንግሥት በጀት 74 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተይዞላታል።

❤14👍4🥱4🎉1
አጭበርባሪ ነህ:- ትራምፕ ለኔታንያሁ‼️
ዶናልድ ትራምፕ ለአንድ አማካሪያቸው ኔታንያሁ አጭበርባሪ (conman) ነው ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል።
Conman ማለት ሰዎችን በውሸት ወሬ በማሳመን ገንዘብ ለሚያጭበረብሩ የተሰጠ ስያሜ ነው።
ይህ የትራምፕ ስድብ በስልጣን ዘመናቸው ከአስቀያሚ ስድባቸው ውስጥ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
አሜሪካ እና ኢራን እስራኤልን ከድርድሩ ውጪ በማድረግ እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለውን ጦርነት የስምምነቱ አካል ሆኖ መቅረቡ እስራኤልን ያበሳጨ ሲሆን እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለውን ጥቃት ባለማቆማ የኢራን እና የአሜሪካ ስምምነት አደጋ ውስጥ ወድቋል።
በዚህ የተነሳ በኢራን በጋራ ጦርነት የጀመሩት አሜሪካ እስራኤል ግንኙነታቸው እየሻከረ መጥቷል።

🤣18❤14👍4🙈2🤯1👌1
አሪፍፔይ የገበያ መሪነቱን ለማጠናከር 4 የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ተቋማትን ገዛ
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ቀዳሚ የሆነው አሪፍፔይ፤ የገበያ መሪነቱን ይበልጥ ለማጠናከርና የአገልግሎት አድማሱን ለማስፋፋት በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ 4 ኩባንያዎችን መግዛቱን አስታወቀ።
ኩባንያው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ጃሚ ፣ መፍትሔ ማይክሮፋይናንስ እና አርትስፕላስ የተባሉ ሦስት ተለዋዋጭ ተቋማትን ወደ እህት ኩባንያነት የጠቅለለ ሲሆን፣ የአራተኛውን ኩባንያ ግዢ አጠናቆ ይፋዊ ማብሰሪያ መርሃ-ግብሩን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
ይህ የኩባንያዎች ውህደት ይፋ የሆነው አሪፍፔይ እ.ኤ.አ ከ2022 እስከ 2026 ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ 156.9 ቢሊዮን ብር የሚያንቀሳቅስ የዲጂታል ክፍያ ማስተናገዱን በገለፀበት መግለጫ ላይ ነው። ኩባንያው ለቅዳሜ ገበያ በላከዉ በዚህ መግለጫ እንዳመለከተው ፤ ይህንን ግዙፍ የግብይት መጠን ሊያሳካ የቻለው ከ425 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ክፍያ ትዕዛዞችን በማስተናገዱ ነዉ።
በአሁኑ ወቅት መሰረተ-ልማቱን ያሰፋው አሪፍፔይ፣ በ15 የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችና የምርት አማራጮቹ አማካኝነት ትልልቅ የንግድ ተቋማት፣ አነስተኛ ነጋዴዎችና ተጠቃሚዎች ያለምንም እንግልት የዘመናዊ ፋይናንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በር ከፍቷል።

👍9❤3
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው አውሮፕላን አምራች የገዛውን ‘ትዊን ኦተር ክላሲክ 300-ጂ’ ተረከበ
🤝 ይህም አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2025 ከዲ ሃቪላንድ ካናዳ ሁለት ትዊን ኦተር ክላሲክ 300-ጂ አውሮፕላኖፕችን ለመግዛት ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ የመጣ ነው።
አየር መንገዱ እነዚህን በአጭር ጊዜ የመነሳት እና የማረፍ አቅም ያላቸው አውሮፕላኖች፤ በኢትዮጵያ እና ምስራቅ አፍሪካ መሠረተ ልማት ባለተሟላባቸው አካባቢዎች እና በሐይቅ ዳርቻ የሚገኙ ከተሞች ላይ አተኩሮ ግልጋሎት ላይ ለማዋል እንደወጠነ አስታውቋል፡፡
👉 ሁለተኛውን ትዊን ኦተር ክላሲክ 300-ጂ አውሮፕላን በ2026 መገባደጃ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል።

❤13👍8🤪3
እገታ‼️
ዛሬ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ጠዋት ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በሰላም ይጓዙ የነበሩ 5 የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ራያ መሆኒ መግቢያ ላይ በህወሓት ሰራዊት መታገታቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
የታጋቾቹ 96% የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው ሱሉ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ካለው ወታደራዊ አፈሳ ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መሃል ሀገር እየሸሹ ይገኛሉ።
Via : አዩዘሀበሻ

😢22❤9👍6
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች
✅ከጠዋቱ 2፡30-9፡30
👉ጎተራ ኮንዶሚኒየም ፣ወንጌላዊት ህንጻ፣ ዩኒማክ፣ መስቀል ፍላወር ፣ ተሻለ ጋራዥ፣ ዳኞችና አቃቢ ሕግ ቢሮ ፣ ኮስሞስ ሕንፃ፣ ድሪም ላይነር፣ ጎተራ ውሃ እና አካባቢው፣
👉የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም፣ ካራ ከብት ተራ፣ ጥሩ መናፈሻ፣ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል እና አካባቢው፣
👉ኖህ አደባባይ ፣ ካፒታል ሲሚንቶ፣ ፔትራም ጁስ፣ ሰበታ በከፊል፣ ዲማማ፣ ዓለም ገና ዳለቲ ሀምበሳ እና አካባቢው፣
👉ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ ጫፍ ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና ፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴል ፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ እና አካባቢው፣
👉ሰበታ ከተማ ፣ ቀበና ውሃ ማምረቻ ፣ ዲማ ሆስፒታል፣ ዋን ውሃ፣ አባሃዋ ትሬዲንግ ፣ ቦሌ ሁላሳ ፣ ሰበታ፣ ዓለም ገና፣ ጎጀብ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3፡00-9፡00
👉አምባሳደር ሪል እስቴት፣ አያት ቤቶች ዞን 1፣2፣8፣ መሪ 40/60፣ 72 ቤቶች በከፊል እና አካባቢው ፣
✅ከጠዋቱ 3፡00-10፡00
👉ጉርድ ሾላ፣ ትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት፣ ግብርና ምርምር፣ ጃክሮስ አደባባይ በስተጀርባ እና አካባቢው፣
👉ቦሌ ሚካኤል፣ ሩዋንዳ፣ ቦሌ ሚኪ ካፌ ቡልቡላ ሸክላ ቤቶች፣ አየርማረፊያ ራዳር፣ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ የቻይናዎች ከሬሸር፣ ግስላ ሰፈር፣ ሸገር ዳቦ እና አካባቢው የሃይል አቅርቦት ይቋረጣል።
ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

❤9👍4👌1
ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸነፈ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ። በዛሬው ዕለት በተገለጸው ውጤት መሠረት፣ ብልጽግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በክልል ምክር ቤቶች አብላጫ መቀመጫዎችን በማሸነፍ አብዛኛውን ድምፅ ማግኘቱ ተረጋግጧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በማጠቃለያ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። ቦርዱ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ብልጽግና ፓርቲ በፌዴራል ደረጃ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል ምክር ቤቶች ከፍተኛውን የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት በመቆጣጠር በአብላጫ ድምፅ አሸናፊ ሆኗል።

🤣47😡24❤17👍8🤷♂2🎉2🤪2🙉1
#Breaking❗❗❗
የኢራን ተደራዳሪዎች አዳራሽ ለቀው ወጡ‼️
በዛሬው ዕለት የአሜሪካ እና የኢራን ተደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ ተገናኝተው የነበረ ሲሆን አሁን በወጡ መረጃዎች መሰረት የኢራን ተደራዳሪዎች አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።
የኢራን ተደራዳሪዎች ከአሜሪካ ልዑካን ጋር የጋራ ፎቶ አንነሳም ብለዋል።
ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ 'ሆርሙዝን ከዘጋችሁ ሀገር አይኖራችሁም፣ሆርሙዝንም በሀይል እወስደዋለሁ' በማለታቸው ነው ተብሏል።
ሄዝቦላህን እያስታጠቃችሁ እስራኤል ስታጠቁ እኛ ደግሞ በቦንብ ኢራንን እንደበድባለን ሲሉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቀዋል።
ኢራን በሊባኖስ ያለው ጦርነት ካልቆመ ድርድር የለም ያለች ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ኢራን ለሄዝቦላህ የምታደርገውን ድጋፍ ካላቆመች ኢራንን እንደበድባለን ብለዋል።

👍26❤19😢3😡3🤔1🙊1
ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ቀረጥ ለመጣል ዛቱ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ፣ አሜሪካ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ የትራንዚት ታሪፍ እንደምትጥል አስጠነቀቁ።
ቅዳሜና እሁድን በካምፕ ዴቪድ እያሳለፉ የሚገኙት ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ጦርነትን ለማቆም የተደረሰው የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በዚህ ወሳኝ የውሃ መስመር ላይ ለ60 ቀናት ያህል ያለምንም ክፍያ በነፃ የመንቀሳቀስ መብትን እንደሚፈቅድ አስምረውበታል። ሆኖም ግን፣ ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ካልተጠናቀቀ አሜሪካ የራሷን ታሪፍ እንደምጥል ገልጸዋል።
ትራምፕ አክለውም፣ ከዚህ ታሪፍ የሚሰበሰበው ገንዘብ አሜሪካ «ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላደረገችው፣ ለምታደርገውና ወደፊትም ለምታበረክተው አገልግሎት ወጪዎቿን ለመተካት የሚውል መሆኑን ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፕሬዝዳንቱ ከኢራን ጋር በተፈራረሙት ስምምነት ላይ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ታሪፍ ጉዳይን በተመለከተ በአሜሪካ ከፍተኛ ትችት እየገጠማቸው ይገኛል።
የአሜሪካውያን ዋነኛ ስጋት ስምምነቱ ለ60 ቀናት ብቻ ከክፍያ ነፃ መሆንን የሚያረጋግጥና ወደፊት ሊጣሉ የሚችሉ ክፍያዎችን በግልጽ የማይከለክል መሆኑ ላይ ነው። ይህ ሁኔታ የዓለም አቀፉን የነዳጅና የንግድ መስመር ዋስትናን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል በሚል ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል። ዶናልድ ትራምፕ ግን የመጨረሻው ውሳኔ በአሜሪካ እጅ እንደሆነና ጥቅማቸውን ለማስከበር ወደኋላ እንደማይሉ በፅኑ አቋም እየተሟገቱ ይገኛሉ።

❤11🤣7👍2🕊2👌1
በ11 የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ እንዲደረግ በቦርዱ ተወሰነ።
አምስቱ የምርጫ ክልሎቹ በሶማሌ ክልል የሚገኙ መሆናቸዉን ቦርዱ ይፋ እያደረገ ባለዉ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዉጤት ማሳወቂያ መርሃ ግብር ላይ ተገልፆል።
ሀማሬ፥ ዳራቶሬ፥ ሀርገሌ፥ ባቱ ዝዋይ፥ ቤጊ፥ አርሆሳ፥ ጨንቻ፥ ሶሮ 1፥ ጠንባሮ ፥ ሀደካላ፥ ሀደካለ ምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ይደረግባቸዋል ተብሏል።
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ሶሬ1 እና ጠምባሮ ምርጫ ክልሎች ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይደረግላቸዋል።
ሀርገሌ ፥,ዳሮር፥ ሀደካላ ፥ ሀማሬ እና ዳራቶሬ የተባሉ በሶማሌ ክልል የሚገኙ የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ያደርጋሉ።
ባቱ ዝዋይ እና ቤጌ ምርጫ ክልሎች በኦሮሚያ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምረጫ የሚደረግበት ይሆናል ተብሏል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ጨንቻ ምርጫ ክልል ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይካሄዳል።

🤪9👍8🙊5🥱4❤3
በ10 ብር የሞባይል ካርድ ሰበብ የጎረቤቱን 8 ጥርሶች ያረገፈው ግለሰብ በ8 ዓመት 9 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ!
አምቦ፡ በኦሮሚያ ክልል፣ አምቦ ከተማ አስተዳደር ቶርበን ኩታዬ ቀበሌ ውስጥ በአነስተኛ የገንዘብ መጠን በተነሳ አለመግባባት፤ በጎረቤቱ ላይ የከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰው የ54 ዓመቱ አቶ ተሬሣ ገመቹ የ8 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት ቅጣት ተላለፈበት።
የአምቦ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አቡሽ ማሞ እንደገለጹት፤ ክስተቱ የተፈጠረው ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡15 አካባቢ ነው።
ተከሳሽ አቶ ተሬሣ ለዓመታት በጎረቤትነት አብረዋቸው ከኖሩት ከአቶ ቱራ ታደሰ አነስተኛ ሱቅ የ10 ብር የሞባይል ካርድ ለመግዛት ብቅ ይላሉ። ካርዱን ከገዙ በኋላም "የተሞላ ካርድ ነው የሰጠኸኝ፤ ሌላ ቀይርልኝ" በማለት የ18 ዓመቱን የሱቁን ሻጭ (የባለቤቱን ልጅ) ይጠይቃሉ። ወጣቱ በበኩሉ "ካርዱ ትክክለኛ ነው፤ ችግሩ ያለው አንተ ጋር ነው" የሚል ምላሽ ሲሰጥ አለመግባባቱ ይጀምራል።
ተከሳሹ "ቆይ አሳይሀለሁ" በማለት ዛቻ ሰንዝረው የሄዱ ሲሆን፤ ትንሽ ቆይተውም ሁለት ሰዎችን አስከትለው ለፀብ ወደ ሱቁ ይመለሳሉ።
በሱቁ አካባቢ የተፈጠረውን ግርግር የተመለከቱት የአቶ ቱራ አባት (የሱቁ ባለቤት)፣ በልጃቸውና በጎረቤታቸው መካከል የተፈጠረውን ንትርክ በሰላም ለመፍታት ጥረት አድርገዋል። ሆኖም ተከሳሽ አቶ ተሬሣ አባትና ልጅን "አጭበርባሪዎች ናችሁ" በማለት ዘለፋ ውስጥ ገቡ። ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሲሆንም፤ ተከሳሹ ባነሱት ትልቅ ድንጋይ ገላጋይ የሆነውን የሱቁን ባለቤት አፋቸው ላይ ክፉኛ ይመቷቸዋል።
በዚህም አሳዛኝ ድርጊት ተበዳይ አቶ ቱራ የላይኛውና የታችኛው 8 ጥርሶቻቸው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ፤ በአምቦ ሆስፒታልም የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ በሰጠው ፈጣን ጥቆማ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር በማዋል፣ የህክምና ማስረጃዎችን አጠናቆ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ልኳል። አቃቤ ህግም "ታስቦ በተፈጸመ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ" ክስ መስርቶበታል።
የምርመራ መዝገቡን የተመለከተው የአምቦ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት፣ ተከሳሽ አቶ ተሬሣ ገመቹ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የ8 ዓመት ከ9 ወር እስራት ውሳኔ አስተላልፎበታል።

❤16😢6👍4👀1
ለጫካ ፕሮጀክት የሚፈርሱ መንደሮች‼️
በአዲስ አበባ በጫካ ፕሮጀክት ማስፋፊያ ምክንያት በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፥ 6 እና 7 ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ውጥረት እና ስጋት ሰፍኗል። ሰሞኑን በተካሄዱ የቀበሌ ስብሰባዎች ላይ የአካባቢው ባለስልጣናት ነዋሪዎች ቤቶቻቸውን በአስቸኳይ በአንድና በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲለቁና ምንም አይነት ድርድር የሌለው ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን መሰረት ሚዲያ ከነዋሪዎች አረጋግጧል።

😡35😢15❤13💔6👍3🙉2🤷♂1🙏1🕊1🤣1👀1
በ2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ብር ይረጋጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ለፓርላማ ገለጹ
በዚህ በጀት ዓመት ብር በ15 በመቶ ቢቀንስም፣ በመጪው በጀት ዓመት የ9.8 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመዘገብ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ይህ ዕድገት በግብርና (7.1%)፣ በኢንዱስትሪ (11.6%) እና በአገልግሎት (8.5%) ዘርፎች የሚመራ ነው።
ነገር ግን በሩቅ ምሥራቅ ግጭት ሳቢያ በጨመረው የነዳጅ ዋጋ ምክንያት የሀገሪቱ የገቢ ዕቃዎች ወጪ 25.8 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።
ከዚህ ውስጥ 6 ቢሊዮን ዶላሩ ለነዳጅ የሚውል ነው።
መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለማረጋጋት አዳዲስ መመሪያዎችን እያወጣ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክ ጨረታዎችንና የንግድ ባንኮችን ሚና በማጠናከር በሕጋዊና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ወደ 11 በመቶ ማውረድ መቻሉን ገልጿል።
እንዲሁም የውጭ ዕዳን መልሶ ለማዋቀር ድርድሮች እየተደረጉ ነው።
ካፒታል ጋዜጣ

🤪28❤13🤣10👍4✍1😢1🙏1👌1
ግብፅ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ የመጀመሪያ ድሏን አገኘች።
ኒው ዚላንድን የገጠመችው ግብፅ በፊን ሱርማን ግብ ስትመራ ብትቆይም፤ ሙስጠፋ ዚኮ፣ ሙሐመድ ሳላህ እና ማህሙድ ትርዝጌት በሁለተኛው አጋማሽ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ግብፅ 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ግብፅ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘችው ድል፤ ምድቡን በአራት ነጥብ እንድትመራ እና ወደ ጥሎ ማለፉ የመሸጋገር ዕድሏ ሰፊ እንዲሆን አድርጓል።
ለዓለም ዋንጫው እንግዳ የሆነችው አፍሪካዊት ደሴት ኬፕ ቨርዴ አሁንም ተጨማሪ ነጥብ አግኝታለች።
በመጀመሪያ የምድብ ስምንት ጨዋታዋ ከስፔን ጋር ያለ ግብ የተለያየችው ሀገር፤ ሌሊቱን ከሁለት ጊዜ ሻምፒዮኗ ኡራጓይ ጋር ሁለት አቻ ወጥታለች።
ባለመሸነፍ ጉዞዋ የቀጠለችው ኬፕ ቨርዴ፣ ሁለት ነጥብ በመያዝ በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ወደ ጥሎ ማለፉ የመሸጋገር ተስፋን ሰንቃለች።
በምድብ ሰባት ቤልጂየም ከኢራን ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል።

❤13👍9🤯4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስራኤል በተገንጣይዋ የሶማሊያ ግዛት ሶማሊላንድ የበርበራ ወደብ የባሕር ኃይሏን ለማሠማራት እያጤነች እንደሆነ ተዘገበ
እስራኤል 'የዶልፊን ደረጃ' ሰርጓጅ መርከቦቿን ጨምሮ የባሕር ኃይል ጦሯን በኤደን ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ በሚገኘው የበርበራ ወደብ ለማስፈር ማቀዷን የአውሮፓ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሁለቱ ሀገራት ግን ለዘገባው ይፋዊ ማረጋገጫ አልሰጡም።
ከዘገባዎቹ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 እስራኤል በርበራን እንደ ባሕር ኃይል ሥራ ማዕከል የመጠቀም ዕድሎችን እያጠናች ነው፣
🟠 ሶማሊላንድ ከእስራኤል ጋር ምንም ዓይነት የወታደራዊ ዕዝ ስምምነት አለማድረጓን በይፋ በማስተባበል የውጭ ኢንቨስትመንት እና ወደቦቿን ለባሕር አገልግሎት መዋላቸውን ቀደስታ እንደምትቀበል ገልጻለች፣
🟠 የእስራኤል ባለሥልጣናት በዘገባዎቹ ዙሪያ አስተያየት አልሰጡም፣
🟠 በርበራ በኤደን ባሕረ ሰላጤ ቁልፍ የባሕር መስመሮች ላይ ያላት መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ፤ ወደ የመን እና ቀይ ባሕር ቀጣና የሚያመሩ የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ ለመከታተል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖራታል።
✈️ በሕንድ ውቅያኖስ–ቀይ ባሕር ቁልፍ የባሕር መስመሮች ላይ የሚገኘው በርበራ ወደብ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂካዊ የንግድ እና ሎጅስቲክስ ማዕከል እየሆነ በመምጣቱ ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎቶችን እየቀሰቀሰ ይገኛል።

❤16👍3😡3
ኢዜማ በ7ኛዉ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት ቀዳሚዉ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ማጠናቀቁን ገለፀ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ ኢዜማ ሀገር አቀፉ ምርጫዉ ከነእንከኖቹም ቢሆን በሰላም በመጠናቀቁ ደስተኛ ነኝ ሲል መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ይህን ተከትሎም ፓርቲዉ ለውድድር በቀረበባቸው ቦታዎች 13 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 73 የክልል እና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን በድምሩ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚው ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ማጠናቀቁን አስታዉቋል።
ኢዜማ ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ባሉት ዓመታት ጠንካራ ጎኖቹን በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩበትን ክፍተቶች በስትራቴጂ እና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራት በመሙላት ተጨባጭ የተፎካካሪ ፓርቲነት ሚናውን ጊዜ ሳያባክን የሚጀምረው ተግባር መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ፓርዉ አክሎም ገዢ ሆኖ እንዲቀጥል ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ እና ለውድድሩ ተሳታፊዎች የእንኳን ደስያላችሁ መልዕክቱን አሥተላልፏል፡፡
በተጨማሪም አሸናፊው ፓርቲ ከዛሬ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባትና ፍትሐዊ የፖለቲካ ምህዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲሠራ፤ አማራጭ ሃሳቦችን እንዲሰማ፤ እንዲሁም ትችቶችን በሆደ ሰፊነት እያስተናገደ የሀገሪቱን ዴሞክራሲ በጋራ ለመገንባት ቁርጠኛ እንዲሆን ጥሪዉን አቅርቧል፡፡

🤪15❤14👍4🤯2🤔1