የሰው ፂም የሚመስል የተፈጥሮ ፀጉር ያላት ድመት በኢንተርኔት ዓለም መነጋገሪያ ሆነች!
ምንም ዓይነት ሰው ሰራሽ ቅብ፣ የፀጉር ማስተካከል ወይም የፎቶ ማጭበርበር ሳይደረግባት፣ በትክክል የሰውን ወፍራም ጥቁር ፂም የሚመስል የተፈጥሮ ፀጉር ይዛ የተወለደች ድመት በመላው ዓለም በሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ መደነቅን ፈጥራለች። ይህ በድመቷ አገጭ ላይ የሚታየው "ፂም" ሙሉ በሙሉ ተፈጥሯዊ ሲሆን፣ ድመቷ እያደገች ስትሄድ በጄኔቲክስ ምክንያት የተፈጠረ ልዩ የቆዳ ቀለም መዋቅር ውጤት ነው።
ድመቶች በጄኔቲክስ ስብጥር ምክንያት እንደ ፂም፣ ቅንድብ፣ ልብ ቅርጽ፣ ጭምብል እና የሰውን የፊት ገጽታ የሚመስሉ አስደናቂ የተፈጥሮ ምልክቶችን በፀጉራቸው ላይ ይዘው ሊወለዱ ይችላሉ። የዚህች ድመት ፂም ግን እጅግ ማራኪ እና የተለየ ያደረገው፣ ልክ እንደ ሰው ልጅ ፂም ግራና ቀኙ እኩል ተስተካክሎ እና በትክክል መሆን ባለበት ቦታ ላይ ተፈጥሮ ያቀለመችው በመሆኑ ነው።
የዚህ ዓይነቱ ድመት ፎቶዎች በኢንተርኔት ላይ በፍጥነት ታዋቂ የሚሆኑት ፓሬዶሊያ (Pareidolia) በሚባለው የስነ-ልቦናዊ ክስተት ምክንያት ነው። የሰው ልጅ አእምሮ በማንኛውም ነገር ላይ የሰውን መልክ ወይም የታወቁ ቅርጾችን ፈጥኖ የመለየት ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ስላለው፣ ድመቷን ስንመለከት አእምሯችን ወዲያውኑ ከሰው ፂም ጋር በማገናኘት ነገሩን እጅግ አስቂኝ እና የማይረሳ ያደርገዋል።
@Addis_Reporter

❤12🤔10👍3🤣2😢1🙊1
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል።
ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል። (ዝርዝሩን ከላይ በምስሉ ይመልከቱት)
#Grade12
#NationalExam

❤10👍3
ወገንተኛ እገዳ ሰላም ማምጣት ኣይችልም- ህወሓት‼️
ትግራይ ህዝብዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ
አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የሰላም አቋም እና የፕሪቶርያ ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲፈረም የነበራት መሪ ተዋናይነት እና ለትግራይ ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ ያሳየቺው ተነሳነት እንደሚያደንቅ ያመለከተው የህወሓት መግለጫ፤ በፌደራል መንግስት ተደጋግሞ የተጣሰው የፕሪቶርያው ስምምነት ሳይታይ ህወሓት ላይ የጉዞ እገዳ ማኖሩ ፍትሓዊነት የጎደለውና ኣሳሳቢ መሆኑን በአቋም መግለጫው አመላክቷል፡፡
ጥፋተኛው አካል ሳይጠየቅ በህወሓት ላይ ብቻ ያነጣጠረ እገዳ ፍትሓዊነት የጎደለው መሆኑን ያመለከተው መግለጫው ፤በእብደዚህ ዓይነት ኣድላዊ አቋም ሰላም ማስፈን እንደማይቻል አመልክቷል፡፡
እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ሕዳር 2 ቀን 2022 የተፈረመው የፕሪቶርያው ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምት፤ በሁለቱም ተፈራራሚ አካላት እንዲፈፀሙ በግልፅ ከተቀመጡ ነጥቦች መካከል፤ ህገመንግስታዊ ስርዓት ወደ ነበረበት መመለስ፣ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ወገኖች ወደቦታቸው መመለስ፣ ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ታጣቂዎች ከትግራይ ግዛቶች ማስወጣት፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱና የህወሓት ሕጋዊ እውቅና እንዲሁም ፖለቲካዊ ቁመና መመለስ መሆኑ ያስታወሰው መግለጫው፤ እነሲህ ስምምነቶች በፌደራል መንግስት ምክንያት ያልተተገበሩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡
የትግራይ ህዝብ ሰላም ወዳድና ተሎ ወደቄዬው እንዲመለስ እዲሁም የመልሶ ግንባታ ስራዎች ተሰርቶለት ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ ያለው ፍላጎት ተግባራዊ እንዲሆን የፕሪቶርያ ስምምነት ተግባራዊነት በጉጉት ሲጠባበቅ መቆየቱን የመለከተ መግለጫው፤ ስምምነቱ ከመተግበር ይልቅ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ኢ-ተገማቲእና አለመተማመን እንዲሰፍን ምክንያት ሆኖ መቆየቱ በፅሑፉ ተመላክቷል፡፡
ስምምነቱ ሶስት ዓመታት ያሳለፈ ቢሆንም፤ ወሳኝ የስምመነት ነጥቦቹ ሳይተገበሩ መቆየታቸውን ያመለከተው መግለጫው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተጋሩ ወደ ቂያቸው መመለስ እንዳልቻሉ፣ የተጠያቂነት ሂደት እንዳልተቋቋመና የኢትዮጵያ መንግስት በቅርብ ከተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ውጪ እንድትሆን መደረጉን ኣመላክቷል፡፡
የሰራተኞች ደመወዝ፣ ነዳጅ፣ የባንክ አገልግሎት እና ሰብአዊ እርዳታዎችን የመሳሰሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ምንግስተ በኩል እገዳ ተደርጎባቸው እንደሚገኝ እንዲሁም በመጠሊያዎች የሚገኙ ወገኖች በከፋ የኖሮ ሁኔታ ይገኛሉ ያለው መግለጫው፤ በረሃብ መሞትና መከላከል በሚቻሉ በታዎች እየተጠቁ መሆኑ ያስረዳል፡፡
የትግራይን ህዝብ አስርቦ ለማጥፋት በፖሊሲ ደረጃ እየሰራ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት አረሜናዊ ተግባር ሆኖ እየቀጠለ እንደሚገኝ ያስረዳው የህወሓት መግለጫ፣ የትግራይ ህዝብ ስቃይ ከህወሓት ጋር አያይዞ መገለፅ ተገቢነት የጎደለው መሆኑን አስረድቷል፡፡
በየመጠልያው የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ተፈናዮች ወደ ቦታቸው እንዳይመለሱ ዋነኛ ተጠያቂ ለማወቅ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች፣ እንደሁም በፕሪቶርያ ስምምነቶች የተቀመጡ የሰብኣዊ አገልግሎት ጉዳዮች እንዳይፈፀሙ በፖሊሲ ደረጃ ከልከሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ማወቅ በቂ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ዳሰሳ በማከናወን እውነታው መረዳት እንደሚቻል ያስረዳክል፡፡
የፌደራል መንግስት ወሳኝ የሚባሉ የፕሪቶርያው ዘላቂ ተኩስ ማቆም ስምምነቶች እንዳይፈፀሙ አንቆ መያዙን ለመረዳት የሚያወጣቸው የተለያዩ ደብዳቤዎችና በመሬት ላይ የሚታዩ ተግባሮቹ መመልከት በቂ ማስረጃዎች መሆናቸው ያመለከተው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ግለጫ፤ በትግራይ ህዝብ ላይ የተጣሉ ክልከላዎች አጠቃላይ ህዝቡ ከመጉዳታቸው በተጨማሪ በወታደራዊ ማስፈራራትና በተደጋጋሚ በፈፀማቸው የድሮን ድብደባዎች እንዲሁም ትግራይን ለማድቀቅ በተከተለው የፖለቲካ ተነጽሎ የትግራይ ህዝብ በፌደራል ስርዓቱ ያለ ውክልና እንዲቀር ማድረጉን አስረድቷል፡፡
ስምምነቱ እንዳይተገበር ሙሉ በሙሉ የዘጋ አከል አቅልሎ በማየት፤ ችግሩ ባልፈጠረ ተደራዳሪ ላይ ተጠያቂ በማድረግ የሰላም ሂደት ለመተግበር ያለው ዕድል አናሳ መሆኑ ያመለከተው መግለጫው፤ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚችለው ገለልተኛ፣ መርህን በመጠበቀና የጋራ ተጠያቂነት ሲኖር መሆኑን አስረድቷል፡፡
የትግራይ ህዝብ ሰላም ወዳድ በመሆኑ፤ ህወሓት በሰላም ጉዳይ ያለው አቋም የፀና በመሆኑ ያብራራው መግለጨው፤ የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር የፌደራል መንግስት ለስምምነቱ ተገዥ በመሆን የሰራተኞች ደመወዝ፣ የባንክ አገልግሎት፣ የነዳጅ አቅርቦት እና የሰብኣዊ ጉዳይ ተደራሽነት ማረጋገጥ ኣለበት ብሏል፡፡
በትግራይ ህገመንግስታዊ ግዛት የሚገኙ ወራሪዎች ሙሉ በሙሉ በማስወጣት፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቄያቸው ለመመለስ የሚያስችል የጊዜ ሰሌዳ ማኖር እንዲሁም የህወሓት ህጋዊነት ለመመለስ የፕሪቶርያው ስምምነት መተግበር ይኖርበታል ያለው የህወሓት መግለጫ፤ በትግራይ ህዝብ ስቃይና መከራ የተሳተፉ አካላት ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የፌደራል መንግስት ቁርጠኝነት መታየት ይኖርበታል ብሏል፡፡

❤9🤣6👍4😢1🕊1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

👍4❤3
አሜሪካ በሚቀጥለው ሳምንት የእስራኤልና ሌባኖስ አዲስ የሰላም ንግግር በዋሽንግተን እንደሚካሄድ አስታወቀች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤልና ሌባኖስ ከሰኔ 16 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ አዲስ የሰላም ንግግር እንደሚያካሂዱ አስታውቋል። መግለጫው የወጣው እስራኤልና ሄዝቦላህ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ካወጁ በኋላ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከሌባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት፥ ይህ ድርድር ለሌባኖስ መልሶ ግንባታና ለዘላቂ ሰላም ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል።
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረገው የመግባቢያ ሰነድ የሌባኖስን ሉዓላዊነት የሚያከብር ቢሆንም፥ በቅርቡ በእስራኤልና በሄዝቦላህ መካከል የቀጠለውና በደቡባዊ ሌባኖስ የ47 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ግጭት ስምምነቱን አደጋ ላይ ጥሎት ቆይቷል።

❤15👍3
ኢራን እስራኤልን ታወድማት ነበር-ትራምፕ‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን መሪዎች በጣም ምርጥ ሰዎች ናቸው፣ በጣም ብልጥ ናቸው።
እኛ ከእነሱ ጋር ጦርነት የገባነው የኑክሌር ቦንብ እንታጠቃለን በማለታቸው ነው ያሉ ሲሆን እኔ ባልኖር እስራኤልን ያወድሟት ነበር ብለዋል።

🤪31👍9🤯5💯4❤3🤣3🤩2😢1👌1👀1😎1
የማሸጊያ ፕላስቲኮችን በፌስታልነት መጠቀም በህግ ያስጠይቃል!
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 መሰረት፣ የማሸጊያ ፕላስቲኮችን ያለአግባብ ለንግድ ዓላማ የሚያውሉ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።
በአዋጁ መሰረት “የማሸጊያ ፕላስቲክ” ተብሎ የተገለጸው ዕቃዎችን ከብክለት ለመከላከል ወይም ከሌላ ነገር ጋር እንዳይቀላቀል ለማድረግ በአምራቾች ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል መጠቅለያ ነው። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የችርቻሮ ሱቆች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ ዳቦ ቤቶች እና ሌሎች ንግድ ተቋማት ይህንን የፕላስቲክ አይነት እንደ ፌስታል (የፕላስቲክ ከረጢት) ምትክ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ በመስክ ምልከታ ተረጋግጧል።
ይህ ተግባር በህግ ከተደነገገው ዓላማ ውጪ በመሆኑ፣ ማንኛውም ተቋም ወይም ግለሰብ ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠብ ባለስልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።
መመሪያውን በመተላለፍ የማሸጊያ ፕላስቲኮችን በህገ-ወጥ መንገድ የፌስታል ተኪ አድርጎ የሚጠቀም አካል ላይ በአዋጁ መሰረት አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎች እየተወሰደ እንደሚገኝ እና ይህ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

❤14🤯11🤔7👍6😢3🤣2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ ማስጠንቀቂያ ለሕወሓት!
በሰሜን ኢትዮጵያ አዲስ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ አስጠነቀቁ፡፡ ከሰሞኑ በአገረ እንግሊዝ በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ሚኒስትሩ፤ ሕወሓት ላይ ብርቱ ትችት ሰንዝረዋል፡፡
ከሶስት ቀናት በፊት በለንደን በተካሄደው የቻተም ሀውስ ውይይት ላይ የተሳተፉት ጌድዮን፤ በሰሜን ኢትዮጵያ በከባድ ትግል የተገኘው ሰላም በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሚኒስትሩ አክለውም፣ የትጥቅ መፍታትን ጨምሮ ዋና ዋና ቁርጠኝነቶች ችላ የሚባሉ ከሆነ፣ ወደ ግጭት የመመለስ እድል እንዳለ አስምረውበታል።
ሚኒስትሩ እንደሚሉት በህወሃት ውስጥ ያሉ ‹አክራሪ› አካላት የሰላም ስምምነቱን መንፈስ ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ተስኗቸዋል፡፡ በተለይም ወሳኝ በሆኑት የትጥቅ መፍታት፣ ታጣቂዎችን ማሰናበት እና የመልሶ ማቋቋም (DDR) ሂደቶች ላይ ቡድኑ እምቢተኝነት አሳይቷል ሲሉ ከሰዋል፡፡
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ሕወሓት አዳዲስ መሣሪያዎችን በስፋት እያከማቸ እና እየገዛ ሲሆን፣ ለሰብአዊ ዕርዳታ ማገገሚያና መልሶ ግንባታ የተመደቡ ሀብቶችንም ወደ ሌላ አቅጣጫ እያዞሩ ይገኛሉ በማለት ከሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀጠናው ከሚገኙ ኃይሎች ጋር ጥምረቶችን መፍጠራቸው በከፍተኛ ድርድርና በከባድ መስዋዕትነት የተገኘውን ሰላም እየቀለበሰው ነው ሲሉ ጌዲዮን ተናግረዋል።
የፌዴራል መንግሥቱ ከግጭት በኋላ ያሉ የመልሶ ግንባታ እና መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ሆኖም የሰላም ስምምነቶች ስኬታማነት የሚወሰነው ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ወገኖች ግዴታቸውን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ባላቸው ቁርጠኝነት ላይ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። ጌዲዮን “የሰላም ስምምነቶች ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት ሁሉም ወገኖች ለእርቅ ቅድሚያ ሰጥተው ሲሰሩ ብቻ ነው” ብለዋል።

❤24👍7🌚4👌1🤪1🙊1
መረጃ‼️
ዓለም ባንክ፣ ለጅቡቲ-ኢትዮጵያ የመንገድ ኮሪደርን ለማሻሻል ተጨማሪ 45 ሚሊዮን ዶላር ፈቀደ።
የአሁኑ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ፣ ባንኩ ለመንገድ ልማቱ እስካሁን የሠጠውን ገንዘብ 205 ሚሊዮን ዶላር ያደርሠዋል።
ባንኩ የገንዘብ ድጋፉ ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር፣ የሎጅስቲክ አቅምን ለማሳደግና የመንገድ ደኅንነትን ለማሻሻል እንደሚውል ገልጧል።
መንገዱ ከፍተኛ ሙቀትንና ዝናብን እንዲቋቋም ኾኖ እንደሚሻሻልም ባንኩ ጠቅሷል።
የመንገድ ኮሪደሩ ተሽከርካሪዎች ለጉዞ እና የድንበር ኬላ ለማለፍ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የትራፊክ አደጋዎችንም በ30 በመቶ ሊቀንስ ይችላል ተብሎለታል።

❤14👍5🥰2👌2
የታመመች ዶሮውን ለማሳከም ወደ ሰው ሆስፒታል የገሰገሰው የ12 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ
በአማራ ክልል ደንበጫ ከተማ የሚኖረው የ12 ዓመቱ ማርቆስ አባየ፥ ውድ ዶሮው በመታመሟ ምክንያት ወደ ደንበጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመውሰድ የብዙሃኑን ልብ ማርኳል።
ታዳጊው ሆስፒታሉ ለሰዎች ብቻ መሆኑን ባለማወቅ ዶሮዋን አቅፎ ከነርሶች ጋር ሲነጋገር የሚያሳየው ቪዲዮ በቲክቶክ ላይ ከ700 ሺህ በላይ እይታን አግኝቷል።
በወቅቱ በሆስፒታሉ የነበረው ነርስ ኡመር ጫኔ ታዳጊውን ወደ እንስሳት ሕክምና ቢመራውም፥ የማርቆስ ርኅራኄ ግን የአገር ውስጥና የውጭ ሚዲያዎችን ትኩረት ስቧል።
ማርቆስ በክልሉ በነበረው ግጭት ምክንያት ካያቶቹ ተለይቶ ወደ አጎቱ ሲመጣ ዶሮዋ በስጦታ የተሰጠችው ነበረች። ይህን የልጁን መልካምነት የተመለከተ አንድ የአገር ውስጥ የዶሮ እርባታ ኩባንያ ለታዳጊው 100 ዶሮዎችንና የእርባታ ስልጠና እንደሚለግስ አስታውቋል።

👍71❤50🥰5💔5😢2🙏1👌1
ኔዘርላንድ ስዊድን ላይ የጎል ናዳ አዘነበች
የኔዘርላንድ አጥቂዎች ኃያልነት እና የስዊድን ተከላካዮች መፈተን በታየበት ማራኪ ፍልሚያ ኔዘርላንድ የ5 ለ 1 ፍፁም አሸናፊ ሆናለች።
በእውነት የኔዘርላንድን ስለታም የአጥቂ መስመር የስዊድን ተከላካዮች ሊቋቋሙት ፈፅሞ አልቻሉም።
ጨዋታው ገና እንደተጀመረ ብሪያን ብሮቢ በ5ኛው እና በ17ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ፈጣን ግቦች ኔዘርላንዶች የጨዋታውን መንፈስ ቀድመው ተቆጣጥረውታል።
ከእረፍት መልስም ኮዲ ጋክፖ በ47ኛው እና በ54ኛው ደቂቃ መረቡን በማንቀጥቀጥ የግብ መጠኑን ከፍ አድርጎታል።
ምንም እንኳን አንቶኒ ኢላንጋ በ59ኛው ደቂቃ ለስዊድን አንዲት የማስተጽናኛ ግብ አስቆጥሮ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም፤ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በ89ኛው ደቂቃ ክሪሴንሲዮ ሰመርቪል ድንቅ የሆነች አምስተኛ ግብ በማስቆጠር የስዊድንን የሽንፈት ፅዋ አብዝቶታል።
ጎል አዳኝ የሚባሉት ዮከሬሽን እና አይዛክን የያዘው የስዊድን ብሄራዊ ቡድን ምንም ሳይፈይድ ከሜዳ ወጥቷል።

❤15👍8😡3👌2🎉1
መረጃ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀጣዩ በጀት ዓመት 502 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት አቀረበ።
ረቂቅ በጀቱ ከዘንድሮው በጀት የ43 በመቶ ብልጫ አለው።
ከበጀቱ ውስጥ፣ 71 በመቶው ለድህነት ቅነሳ እና ከዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተያያዙ እቅዶችን ለማሳካት እንደሚውል ተገልጧል።
በጀቱ፣ የልማት ስትራቴጂዎችን፣ የነዋሪዎችን የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት አቅርቦት ማሳደግን በተለይም መንገድን፣ ውሃን፣ መኖሪያ ቤትን፣ ጽዳትን፣ ትራንስፖርትንና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልን እንዲሁም ትምህርትን፣ ጤናን እና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች የሚደረግ ድጎማን ጨምሮ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ማሻሻልን ታሳቢ ያደረገ መኾኑን አስተዳደሩ አስታውቋል።
በተያዘው በጀት ዓመት የፌደራል ድጎማ ያላተመደበላት ከተማዋ፣ በቀጣዩ የፌደራሉ መንግሥት በጀት 74 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተይዞላታል።

❤14👍4🥱4🎉1
አጭበርባሪ ነህ:- ትራምፕ ለኔታንያሁ‼️
ዶናልድ ትራምፕ ለአንድ አማካሪያቸው ኔታንያሁ አጭበርባሪ (conman) ነው ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል።
Conman ማለት ሰዎችን በውሸት ወሬ በማሳመን ገንዘብ ለሚያጭበረብሩ የተሰጠ ስያሜ ነው።
ይህ የትራምፕ ስድብ በስልጣን ዘመናቸው ከአስቀያሚ ስድባቸው ውስጥ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
አሜሪካ እና ኢራን እስራኤልን ከድርድሩ ውጪ በማድረግ እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለውን ጦርነት የስምምነቱ አካል ሆኖ መቅረቡ እስራኤልን ያበሳጨ ሲሆን እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለውን ጥቃት ባለማቆማ የኢራን እና የአሜሪካ ስምምነት አደጋ ውስጥ ወድቋል።
በዚህ የተነሳ በኢራን በጋራ ጦርነት የጀመሩት አሜሪካ እስራኤል ግንኙነታቸው እየሻከረ መጥቷል።

🤣18❤14👍4🙈2🤯1👌1
አሪፍፔይ የገበያ መሪነቱን ለማጠናከር 4 የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ተቋማትን ገዛ
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ቀዳሚ የሆነው አሪፍፔይ፤ የገበያ መሪነቱን ይበልጥ ለማጠናከርና የአገልግሎት አድማሱን ለማስፋፋት በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ 4 ኩባንያዎችን መግዛቱን አስታወቀ።
ኩባንያው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ጃሚ ፣ መፍትሔ ማይክሮፋይናንስ እና አርትስፕላስ የተባሉ ሦስት ተለዋዋጭ ተቋማትን ወደ እህት ኩባንያነት የጠቅለለ ሲሆን፣ የአራተኛውን ኩባንያ ግዢ አጠናቆ ይፋዊ ማብሰሪያ መርሃ-ግብሩን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
ይህ የኩባንያዎች ውህደት ይፋ የሆነው አሪፍፔይ እ.ኤ.አ ከ2022 እስከ 2026 ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ 156.9 ቢሊዮን ብር የሚያንቀሳቅስ የዲጂታል ክፍያ ማስተናገዱን በገለፀበት መግለጫ ላይ ነው። ኩባንያው ለቅዳሜ ገበያ በላከዉ በዚህ መግለጫ እንዳመለከተው ፤ ይህንን ግዙፍ የግብይት መጠን ሊያሳካ የቻለው ከ425 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ክፍያ ትዕዛዞችን በማስተናገዱ ነዉ።
በአሁኑ ወቅት መሰረተ-ልማቱን ያሰፋው አሪፍፔይ፣ በ15 የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችና የምርት አማራጮቹ አማካኝነት ትልልቅ የንግድ ተቋማት፣ አነስተኛ ነጋዴዎችና ተጠቃሚዎች ያለምንም እንግልት የዘመናዊ ፋይናንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በር ከፍቷል።

👍9❤3