አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በህወሓት የጦር መሳሪያ ካምፕ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ።
ዛሬ ጥዋት በሱዳን ሽረሪና አከባቢ ህወሓት የጦር መሳሪያ ካምፕ አድርጎታል በተባለ ቦታ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የህወሓት አርሚ 70 የሚባለው ጦር በዚሁ አካባቢ ትንኮሳ ፈፅሞ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍12😢2🎉1👌1
ኢትዮጵያ የራሷን ብር በሀገር ውስጥ ልታትም ነው በየዓመቱ ወደ 100 ሚ. ዶላር ገደማ ይታደጋል

ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የነበረባትን የውጭ ሀገራት ጥገኝነት በማቆም፣ እ.ኤ.አ. በ2030 የኢትዮጵያን ብር በሀገር ውስጥ ማተም ለመጀመር ማቀዷን አስታውቃለች። በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሚመራው ይህ አዲስ ንቅናቄ፣ ሀገሪቱ በየዓመቱ ለገንዘብ ማተሚያ የምታወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚያድን ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የብር ኖቶችን በውጭ ሀገር (በተለይም በእንግሊዝ) ለማሳተም በየዓመቱ ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታወጣ ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደገለጹት፣ ይህ ተነሳሽነት ኢትዮጵያ ሰፊ የኢኮኖሚ ራስን የመቻል አቅም ለመገንባት፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነትን ለማጠናከርና በሀገራዊ መገበያያ ገንዘብ መረጋጋት ላይ ያላትን ቁጥጥር ለማሳደግ ከምታደርገው ስትራቴጂካዊ ጉዞ ጋር የተያያዘ ነው። በአሁኑ ጊዜ ከ40 በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት አሁንም ድረስ  የገንዘብ ኖቶቻቸውን ለማተም በአውሮፓ በሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ጥገኛ መሆናቸው ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣1513👍11😢2🤪2👌1🆒1
ምርትና አገልግሎትዎን ለማስተዋወቅ ያናግሩን 👇
@Addis_reporter_bot
👍41👌1
ሆርሙዝ ተመልሶ ተዘጋ‼️
አሜሪካ ስምምነቱን ጥሳለች በሚል የኢራን አብዮታዊ መንግሥት ዘብ
የሆሬሙዝ ሰርጥን መልሶ መዝጋቱን አሳውቋል።

ኢራን እስራኤል በሊባኖስ እየፈፀመች ያለችውን ጥቃት ባለማቆሟ ስምምነቱን ጥሷል ያለች ሲሆን እስራኤል በሊባኖስ የምትፈፅመውን የማስቆም ሀላፊነት የአሜሪካ ነው ብላለች።

ይህንን ተከትሎ 75$ ደርሶ የነበረው የአንድ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቶ 81$ ዶላር ገብቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣1914😡13🤔4👍3🤪1🙊1
የሕወሓት ቡድን ለአሜሪካ መልስ ሰጠ!

የአሜሪካ መንግሥት በፓርቲው አመራሮች ላይ የጣለው የቪዛ ገደብ ያልተሟላ እና ሚዛናዊነት የጎደለው ግምገማ ላይ የተመሠረተ ነው ሲል የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ክፉኛ ኮነነ።

ሕወሓት ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የአሜሪካን ሚና እንደሚያከብር ቢገልጽም፤ አዲሱ የማዕቀብ ውሳኔ ግን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ያሉበትን ግዴታዎች በተደጋጋሚ አለመወጣቱን ወደ ጎን በመተው፣ ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ በሕወሓት ላይ ብቻ የሚጭን በመሆኑ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ከሦስት ዓመታት በላይ ቢያልፉም፣ የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት መመለስ፣ የተፈናቃዮች መዋቅራዊ ዕርዳታ፣ የውጭ (የፌደራል ያልሆኑ) ኃይሎች ከትግራይ መሬት መውጣት እና የህወሓት ሕጋዊና ፖለቲካዊ ሰውነት ዕውቅና ማግኘት የተባሉት ቁልፍ ድንጋጌዎች አሁንም አልተተገበሩም ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤣13👍2
ኢትዮጵያውያን የጥርስሳሙና አይጠቀሙም‼️
Worldpanel by Numerator የተሰኘ የገበያ አጥኝ ተቋም ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከ 10 ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ውስጥ ሰባቱ የጥርስ ሳሙና አይገዙም/አይጠቀሙም ብሏል፡፡

ይህም በአገሪቱ ከዘመናዊ የአፍ ንጽህና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ትልቅ ክፍተት እንዳለ አመላካች ነው ተብሏል፡፡

በፍሎራይድ የጥርስ ሳሙና ጥርስን በመደበኛነት ማጽዳት ከአፍ ጤና ጋር በተያያዘ የሚመከር ቢሆንም በኢትዮጵያ ግን ይህ ልምድ አናሳ ነው ይላል ዛሬ የወጣው አዲስ የገበያ ጥናት፡፡

ጥናቱ በአፍሪካ የጥርስ ማጽጃ በአፍሪካ እስከ 95 በመቶ በሚባል ደረጃ መደበኛ የቤተሰብ ወጪ መሆኑን አስታውሶ፡፡

የኢትዮጵያ ግን የተለየ ነው፤ አብዛኛው ቤተሰብ ለጥርስ ሳሙና ማጽጃ ገንዘቡን አያወጣም ብሏል፡፡

ጥናቱ የኢትዮጵያ ቤተሰቦች ዘመናዊ የትርስ ማፅጃ ለመጠቀም ፈቃደኝነት ይጎላቸዋል፡፡ በአንፃሩ ባህላዊ የእንጨት እና ስራስር መፋቂያዎችን መጠቀም ይመርጣሉ ነው ያለው፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🙉18👍11🎉1🙊1
የሰው ፂም የሚመስል የተፈጥሮ ፀጉር ያላት ድመት በኢንተርኔት ዓለም መነጋገሪያ ሆነች!
 
ምንም ዓይነት ሰው ሰራሽ ቅብ፣ የፀጉር ማስተካከል ወይም የፎቶ ማጭበርበር ሳይደረግባት፣ በትክክል የሰውን ወፍራም ጥቁር ፂም የሚመስል የተፈጥሮ ፀጉር ይዛ የተወለደች ድመት በመላው ዓለም በሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ መደነቅን ፈጥራለች። ይህ በድመቷ አገጭ ላይ የሚታየው "ፂም" ሙሉ በሙሉ ተፈጥሯዊ ሲሆን፣ ድመቷ እያደገች ስትሄድ በጄኔቲክስ ምክንያት የተፈጠረ ልዩ የቆዳ ቀለም መዋቅር ውጤት ነው።
 
ድመቶች በጄኔቲክስ ስብጥር ምክንያት እንደ ፂም፣ ቅንድብ፣ ልብ ቅርጽ፣ ጭምብል እና የሰውን የፊት ገጽታ የሚመስሉ አስደናቂ የተፈጥሮ ምልክቶችን በፀጉራቸው ላይ ይዘው ሊወለዱ ይችላሉ። የዚህች ድመት ፂም ግን እጅግ ማራኪ እና የተለየ ያደረገው፣ ልክ እንደ ሰው ልጅ ፂም ግራና ቀኙ እኩል ተስተካክሎ እና በትክክል መሆን ባለበት ቦታ ላይ ተፈጥሮ ያቀለመችው በመሆኑ ነው።
 
የዚህ ዓይነቱ ድመት ፎቶዎች በኢንተርኔት ላይ በፍጥነት ታዋቂ የሚሆኑት ፓሬዶሊያ (Pareidolia) በሚባለው የስነ-ልቦናዊ ክስተት ምክንያት ነው። የሰው ልጅ አእምሮ በማንኛውም ነገር ላይ የሰውን መልክ ወይም የታወቁ ቅርጾችን ፈጥኖ የመለየት ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ስላለው፣ ድመቷን ስንመለከት አእምሯችን ወዲያውኑ ከሰው ፂም ጋር በማገናኘት ነገሩን እጅግ አስቂኝ እና የማይረሳ ያደርገዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12🤔10👍3🤣2😢1🙊1
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል።

ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል። (ዝርዝሩን ከላይ በምስሉ ይመልከቱት)
#Grade12
#NationalExam

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
ወገንተኛ እገዳ ሰላም ማምጣት ኣይችልም- ህወሓት‼️
ትግራይ ህዝብዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ

አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የሰላም አቋም እና የፕሪቶርያ ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲፈረም የነበራት መሪ ተዋናይነት እና ለትግራይ ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ ያሳየቺው ተነሳነት እንደሚያደንቅ ያመለከተው የህወሓት መግለጫ፤ በፌደራል መንግስት ተደጋግሞ  የተጣሰው የፕሪቶርያው ስምምነት ሳይታይ ህወሓት ላይ የጉዞ እገዳ ማኖሩ ፍትሓዊነት የጎደለውና ኣሳሳቢ መሆኑን በአቋም መግለጫው አመላክቷል፡፡

ጥፋተኛው አካል ሳይጠየቅ በህወሓት ላይ ብቻ ያነጣጠረ እገዳ ፍትሓዊነት የጎደለው መሆኑን ያመለከተው መግለጫው ፤በእብደዚህ ዓይነት ኣድላዊ አቋም ሰላም ማስፈን እንደማይቻል አመልክቷል፡፡

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ሕዳር 2 ቀን 2022 የተፈረመው የፕሪቶርያው ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምት፤ በሁለቱም ተፈራራሚ አካላት እንዲፈፀሙ በግልፅ ከተቀመጡ ነጥቦች መካከል፤ ህገመንግስታዊ ስርዓት ወደ ነበረበት መመለስ፣ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ወገኖች ወደቦታቸው መመለስ፣ ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ታጣቂዎች ከትግራይ ግዛቶች ማስወጣት፣  መሰረታዊ አገልግሎቶች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱና የህወሓት ሕጋዊ እውቅና እንዲሁም ፖለቲካዊ ቁመና መመለስ መሆኑ ያስታወሰው መግለጫው፤ እነሲህ ስምምነቶች በፌደራል መንግስት ምክንያት ያልተተገበሩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡

የትግራይ ህዝብ ሰላም ወዳድና ተሎ ወደቄዬው እንዲመለስ እዲሁም የመልሶ ግንባታ ስራዎች ተሰርቶለት ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ ያለው ፍላጎት ተግባራዊ እንዲሆን የፕሪቶርያ ስምምነት ተግባራዊነት በጉጉት  ሲጠባበቅ መቆየቱን የመለከተ መግለጫው፤ ስምምነቱ ከመተግበር ይልቅ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ኢ-ተገማቲእና አለመተማመን እንዲሰፍን ምክንያት ሆኖ መቆየቱ በፅሑፉ ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱ ሶስት ዓመታት ያሳለፈ ቢሆንም፤ ወሳኝ የስምመነት ነጥቦቹ ሳይተገበሩ መቆየታቸውን ያመለከተው መግለጫው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተጋሩ ወደ ቂያቸው መመለስ እንዳልቻሉ፣ የተጠያቂነት ሂደት እንዳልተቋቋመና የኢትዮጵያ መንግስት በቅርብ ከተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ውጪ እንድትሆን መደረጉን ኣመላክቷል፡፡

የሰራተኞች ደመወዝ፣ ነዳጅ፣ የባንክ አገልግሎት እና ሰብአዊ እርዳታዎችን የመሳሰሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ምንግስተ በኩል እገዳ ተደርጎባቸው እንደሚገኝ እንዲሁም  በመጠሊያዎች የሚገኙ ወገኖች በከፋ የኖሮ ሁኔታ ይገኛሉ ያለው መግለጫው፤ በረሃብ መሞትና መከላከል በሚቻሉ በታዎች እየተጠቁ መሆኑ ያስረዳል፡፡

የትግራይን ህዝብ አስርቦ ለማጥፋት በፖሊሲ ደረጃ እየሰራ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት አረሜናዊ ተግባር ሆኖ እየቀጠለ እንደሚገኝ ያስረዳው የህወሓት መግለጫ፣ የትግራይ ህዝብ ስቃይ ከህወሓት ጋር አያይዞ መገለፅ  ተገቢነት የጎደለው መሆኑን አስረድቷል፡፡
በየመጠልያው የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ተፈናዮች ወደ ቦታቸው እንዳይመለሱ ዋነኛ ተጠያቂ ለማወቅ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች፣ እንደሁም በፕሪቶርያ ስምምነቶች የተቀመጡ የሰብኣዊ አገልግሎት ጉዳዮች እንዳይፈፀሙ በፖሊሲ ደረጃ ከልከሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ማወቅ በቂ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ዳሰሳ በማከናወን እውነታው መረዳት እንደሚቻል ያስረዳክል፡፡

የፌደራል መንግስት ወሳኝ የሚባሉ የፕሪቶርያው ዘላቂ ተኩስ ማቆም ስምምነቶች እንዳይፈፀሙ አንቆ መያዙን ለመረዳት የሚያወጣቸው የተለያዩ ደብዳቤዎችና በመሬት ላይ የሚታዩ ተግባሮቹ  መመልከት በቂ ማስረጃዎች መሆናቸው ያመለከተው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ግለጫ፤ በትግራይ ህዝብ ላይ የተጣሉ ክልከላዎች አጠቃላይ ህዝቡ ከመጉዳታቸው በተጨማሪ በወታደራዊ ማስፈራራትና በተደጋጋሚ በፈፀማቸው የድሮን ድብደባዎች እንዲሁም ትግራይን ለማድቀቅ በተከተለው የፖለቲካ ተነጽሎ የትግራይ ህዝብ በፌደራል ስርዓቱ ያለ ውክልና እንዲቀር ማድረጉን አስረድቷል፡፡

ስምምነቱ እንዳይተገበር ሙሉ በሙሉ የዘጋ አከል አቅልሎ በማየት፤ ችግሩ ባልፈጠረ ተደራዳሪ ላይ ተጠያቂ  በማድረግ የሰላም ሂደት ለመተግበር ያለው ዕድል አናሳ መሆኑ ያመለከተው መግለጫው፤ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚችለው ገለልተኛ፣ መርህን በመጠበቀና የጋራ ተጠያቂነት ሲኖር መሆኑን አስረድቷል፡፡

የትግራይ ህዝብ ሰላም ወዳድ በመሆኑ፤ ህወሓት በሰላም ጉዳይ ያለው አቋም የፀና በመሆኑ ያብራራው መግለጨው፤ የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር የፌደራል መንግስት ለስምምነቱ ተገዥ  በመሆን የሰራተኞች ደመወዝ፣ የባንክ አገልግሎት፣ የነዳጅ አቅርቦት እና የሰብኣዊ ጉዳይ ተደራሽነት ማረጋገጥ ኣለበት ብሏል፡፡

በትግራይ ህገመንግስታዊ  ግዛት የሚገኙ ወራሪዎች ሙሉ በሙሉ በማስወጣት፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቄያቸው ለመመለስ የሚያስችል የጊዜ ሰሌዳ ማኖር እንዲሁም የህወሓት ህጋዊነት ለመመለስ የፕሪቶርያው ስምምነት መተግበር ይኖርበታል ያለው የህወሓት መግለጫ፤ በትግራይ ህዝብ ስቃይና መከራ የተሳተፉ አካላት ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የፌደራል መንግስት ቁርጠኝነት መታየት ይኖርበታል ብሏል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9🤣6👍4😢1🕊1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍43
አሜሪካ በሚቀጥለው ሳምንት የእስራኤልና ሌባኖስ አዲስ የሰላም ንግግር በዋሽንግተን እንደሚካሄድ አስታወቀች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤልና ሌባኖስ ከሰኔ 16 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ አዲስ የሰላም ንግግር እንደሚያካሂዱ አስታውቋል። መግለጫው የወጣው እስራኤልና ሄዝቦላህ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ካወጁ በኋላ ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከሌባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት፥ ይህ ድርድር ለሌባኖስ መልሶ ግንባታና ለዘላቂ ሰላም ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረገው የመግባቢያ ሰነድ የሌባኖስን ሉዓላዊነት የሚያከብር ቢሆንም፥ በቅርቡ በእስራኤልና በሄዝቦላህ መካከል የቀጠለውና በደቡባዊ ሌባኖስ የ47 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ግጭት ስምምነቱን አደጋ ላይ ጥሎት ቆይቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3
ኢራን እስራኤልን ታወድማት ነበር-ትራምፕ‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን መሪዎች በጣም ምርጥ ሰዎች ናቸው፣ በጣም ብልጥ ናቸው።

እኛ ከእነሱ ጋር ጦርነት የገባነው የኑክሌር ቦንብ እንታጠቃለን በማለታቸው ነው ያሉ ሲሆን እኔ ባልኖር እስራኤልን ያወድሟት ነበር ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪31👍9🤯5💯43🤣3🤩2😢1👌1👀1😎1
የማሸጊያ ፕላስቲኮችን በፌስታልነት መጠቀም በህግ ያስጠይቃል!

​የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 መሰረት፣ የማሸጊያ ፕላስቲኮችን ያለአግባብ ለንግድ ዓላማ የሚያውሉ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።

​በአዋጁ መሰረት “የማሸጊያ ፕላስቲክ” ተብሎ የተገለጸው ዕቃዎችን ከብክለት ለመከላከል ወይም ከሌላ ነገር ጋር እንዳይቀላቀል ለማድረግ በአምራቾች ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል መጠቅለያ ነው። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የችርቻሮ ሱቆች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ ዳቦ ቤቶች እና ሌሎች ንግድ ተቋማት ይህንን የፕላስቲክ አይነት እንደ ፌስታል (የፕላስቲክ ከረጢት) ምትክ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ በመስክ ምልከታ ተረጋግጧል።

​ይህ ተግባር በህግ ከተደነገገው ዓላማ ውጪ በመሆኑ፣ ማንኛውም ተቋም ወይም ግለሰብ ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠብ ባለስልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።

መመሪያውን በመተላለፍ የማሸጊያ ፕላስቲኮችን በህገ-ወጥ መንገድ የፌስታል ተኪ አድርጎ የሚጠቀም አካል ላይ በአዋጁ መሰረት አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎች እየተወሰደ እንደሚገኝ እና ይህ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14🤯11🤔7👍6😢3🤣2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ ማስጠንቀቂያ ለሕወሓት!

በሰሜን ኢትዮጵያ አዲስ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ አስጠነቀቁ፡፡ ከሰሞኑ በአገረ እንግሊዝ በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ሚኒስትሩ፤ ሕወሓት ላይ ብርቱ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ከሶስት ቀናት በፊት በለንደን በተካሄደው የቻተም ሀውስ ውይይት ላይ የተሳተፉት ጌድዮን፤ በሰሜን ኢትዮጵያ በከባድ ትግል የተገኘው ሰላም በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሚኒስትሩ አክለውም፣ የትጥቅ መፍታትን ጨምሮ ዋና ዋና ቁርጠኝነቶች ችላ የሚባሉ ከሆነ፣ ወደ ግጭት የመመለስ እድል እንዳለ አስምረውበታል።
ሚኒስትሩ እንደሚሉት በህወሃት ውስጥ ያሉ ‹አክራሪ› አካላት የሰላም ስምምነቱን መንፈስ ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ተስኗቸዋል፡፡ በተለይም ወሳኝ በሆኑት የትጥቅ መፍታት፣ ታጣቂዎችን ማሰናበት እና የመልሶ ማቋቋም (DDR) ሂደቶች ላይ ቡድኑ እምቢተኝነት አሳይቷል ሲሉ ከሰዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ሕወሓት አዳዲስ መሣሪያዎችን በስፋት እያከማቸ እና እየገዛ ሲሆን፣ ለሰብአዊ ዕርዳታ ማገገሚያና መልሶ ግንባታ የተመደቡ ሀብቶችንም ወደ ሌላ አቅጣጫ እያዞሩ ይገኛሉ በማለት ከሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀጠናው ከሚገኙ ኃይሎች ጋር ጥምረቶችን መፍጠራቸው በከፍተኛ ድርድርና በከባድ መስዋዕትነት የተገኘውን ሰላም እየቀለበሰው ነው ሲሉ ጌዲዮን ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግሥቱ ከግጭት በኋላ ያሉ የመልሶ ግንባታ እና መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ሆኖም የሰላም ስምምነቶች ስኬታማነት የሚወሰነው ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ወገኖች ግዴታቸውን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ባላቸው ቁርጠኝነት ላይ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። ጌዲዮን “የሰላም ስምምነቶች ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት ሁሉም ወገኖች ለእርቅ ቅድሚያ ሰጥተው ሲሰሩ ብቻ ነው” ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍7🌚4👌1🤪1🙊1
መረጃ‼️

ዓለም ባንክ፣ ለጅቡቲ-ኢትዮጵያ የመንገድ ኮሪደርን ለማሻሻል ተጨማሪ 45 ሚሊዮን ዶላር ፈቀደ።

የአሁኑ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ፣ ባንኩ ለመንገድ ልማቱ እስካሁን የሠጠውን ገንዘብ 205 ሚሊዮን ዶላር ያደርሠዋል።

ባንኩ የገንዘብ ድጋፉ ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር፣ የሎጅስቲክ አቅምን ለማሳደግና የመንገድ ደኅንነትን ለማሻሻል እንደሚውል ገልጧል። 

መንገዱ ከፍተኛ ሙቀትንና ዝናብን እንዲቋቋም ኾኖ እንደሚሻሻልም ባንኩ ጠቅሷል።

የመንገድ ኮሪደሩ ተሽከርካሪዎች ለጉዞ እና የድንበር ኬላ ለማለፍ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የትራፊክ አደጋዎችንም በ30 በመቶ ሊቀንስ ይችላል ተብሎለታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5🥰2👌2
የታመመች ዶሮውን ለማሳከም ወደ ሰው ሆስፒታል የገሰገሰው የ12 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ

​በአማራ ክልል ደንበጫ ከተማ የሚኖረው የ12 ዓመቱ ማርቆስ አባየ፥ ውድ ዶሮው በመታመሟ ምክንያት ወደ ደንበጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመውሰድ የብዙሃኑን ልብ ማርኳል።

ታዳጊው ሆስፒታሉ ለሰዎች ብቻ መሆኑን ባለማወቅ ዶሮዋን አቅፎ ከነርሶች ጋር ሲነጋገር የሚያሳየው ቪዲዮ በቲክቶክ ላይ ከ700 ሺህ በላይ እይታን አግኝቷል።

​በወቅቱ በሆስፒታሉ የነበረው ነርስ ኡመር ጫኔ ታዳጊውን ወደ እንስሳት ሕክምና ቢመራውም፥ የማርቆስ ርኅራኄ ግን የአገር ውስጥና የውጭ ሚዲያዎችን ትኩረት ስቧል።

ማርቆስ በክልሉ በነበረው ግጭት ምክንያት ካያቶቹ ተለይቶ ወደ አጎቱ ሲመጣ ዶሮዋ በስጦታ የተሰጠችው ነበረች። ይህን የልጁን መልካምነት የተመለከተ አንድ የአገር ውስጥ የዶሮ እርባታ ኩባንያ ለታዳጊው 100 ዶሮዎችንና የእርባታ ስልጠና እንደሚለግስ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍7150🥰5💔5😢2🙏1👌1
ኔዘርላንድ ስዊድን ላይ የጎል ናዳ አዘነበች

የኔዘርላንድ አጥቂዎች ኃያልነት እና የስዊድን ተከላካዮች መፈተን በታየበት ማራኪ ፍልሚያ ኔዘርላንድ የ5 ለ 1 ፍፁም አሸናፊ ሆናለች።

በእውነት የኔዘርላንድን ስለታም የአጥቂ መስመር የስዊድን ተከላካዮች ሊቋቋሙት ፈፅሞ አልቻሉም።

ጨዋታው ገና እንደተጀመረ ብሪያን ብሮቢ በ5ኛው እና በ17ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ፈጣን ግቦች ኔዘርላንዶች የጨዋታውን መንፈስ ቀድመው ተቆጣጥረውታል።

ከእረፍት መልስም ኮዲ ጋክፖ በ47ኛው እና በ54ኛው ደቂቃ መረቡን በማንቀጥቀጥ የግብ መጠኑን ከፍ አድርጎታል።

ምንም እንኳን አንቶኒ ኢላንጋ በ59ኛው ደቂቃ ለስዊድን አንዲት የማስተጽናኛ ግብ አስቆጥሮ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም፤ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በ89ኛው ደቂቃ ክሪሴንሲዮ ሰመርቪል ድንቅ የሆነች አምስተኛ ግብ በማስቆጠር የስዊድንን የሽንፈት ፅዋ አብዝቶታል።

ጎል አዳኝ የሚባሉት ዮከሬሽን እና አይዛክን የያዘው የስዊድን ብሄራዊ ቡድን ምንም ሳይፈይድ ከሜዳ ወጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍8😡3👌2🎉1