አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
#TPLF

አሜሪካ በህወሓት (TPLF) አባላት እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የእገዳ ጣለች

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ እንዲሁም በመላ ቀጠና ያለውን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥለዋል ባሏቸው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላት እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ገደብ መጣሉን አስታውቀዋል።

ውሳኔው የተላለፈው በስደተኞችና ዜግነት አዋጅ አንቀጽ 212(a)(3)(C) በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ እገዳው በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በሚያስተጓጉሉ " አክራሪ አቋም " ባላቸው አባላትና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ በህወሓት አመራሮችና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የሰሜን ኢትዮጵያን ሰላም ዳግም ስጋት ላይ መጣሉን ጠቅሷል።

በተለይም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች (TSF) እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) መካከል የተከሰተው ቀጥተኛ ግጭት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተገኘውን አንጻራዊ መረጋጋት የሚፈታተን መሆኑ አመልክቷል።

አሜሪካ በሰላምና በክብር መኖር የሚፈልገውን የትግራይን ጨምሮ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መደገፏን እንደምትቀጥል የገለጸው መግለጫው፤ በክልሉ ሰላምና መረጋጋትን በሚያናጉ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን ያሉትን አማራጮች ሁሉ ጥቅም ላይ እንደምታውል አስታውቃለች።

የቪዛ ማዕቀብ የተጣለባቸው የህወሓት (TPLF) አመራሮች እና ቤተሰቦቻቸው ስም በይፋ አልተገለጸም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
32👍9🤪4💯2👌1
ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የተላከ 63 ኪሎ ግራም ጫት ተያዘ

የዩናይትድ ስቴትስ የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ መኮንኖች ሐሙስ ጁን 4 ቀን በዋሽንግተን ዱለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በስተርሊንግ የግብርና ስፔሻሊስቶች ወደ ሳክራሜንቶ ፣ ካሊፎርኒያ የሚጓዘውን የአየር ጭነት ከመረመሩ በኋላ ጫቱ መያዙን ባለሥልጣናቱ አስታወቁ።

የጉዞው ዋጋ ወደ 17,000 ዶላር የሚገመት ጫት መሆኑን ገልፀዋል። ጭነቱ በተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ውስጥ የተሸሸገ ሲሆን በ102 ሣጥኖች ውስጥ የተካተተ መሆኑን ኃላፊዎቹ ተናግረዋል። ጫት በተለምዶ በምስራቅ አፍሪካ እና በአረብ ባሕረ ገብ መሬት ይበቅላ።

አንዳንድ ተጠቃሚዎች አበረታች ሻይ ለማዘጋጀት የደረቁ የጫት ቅጠሎችን ያፈላሉ። እፅዋቱ ካቲኖን እና ካቲን የተባሉ ሁለት የማዕከላዊ የነርቭ ሥርዓት አነቃቂዎች እንደያዘ አሜሪካ ማስታወቋን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

የፌደራል ባለስልጣናት እንዳሉት ጫት መነቃቃት ይፈጥራል፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የመተንፈስ ችግር፣ የደም ግፊት መጨመር እና የልብ ምት መጨመር ያስከትላል። የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ወደብ ዳይሬክተር የሆኑት ክሪስቲን ዋው "ጫት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ተከልክሏል ያሉ ሲሆን ምክንያቱም በውስጡ ያሉት የኬሚካል ንጥረነገሮች ቁጥጥር የሚደረግባቸው ንጥረ ነገሮች ናቸው" ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14😡5👍2🤔2🥰1👀1🙊1
አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ40 አገራት ለሰብዓዊ ዕርዳታና ለአደጋ ምላሽ የሚውል 1 ቢሊዮን ዶላር ለተመድ ሕጻናት ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና ለዓለም ምግብ ፕሮግራም ለመስጠት ወሠነች።

ከገንዘብ ድጋፉ 800 ሚሊዮን ዶላሩ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚሠጥ ሲሆን፣ 218 ሚሊዮን ዶላር ደሞ ለዩኒሴፍ እንደሚሠጥ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ገልጧል።

ገንዘቡ ለሁለቱ ድርጅቶች የተፈቀደው፣ የእርዳታ አሠጣጣቸው ሊለካ የሚችል ውጤት የሚያስመዘግብና ተጠያቂነትን የሚያሠፍን በመኾኑ እንደኾነ መስሪያ ቤቱ ጠቅሷል።

ድርጅቶቹ፣ ገንዘቡን ለምግብ እርዳታ፣ ለአልሚ ምግብ አቅርቦት፣ ለጤና፣ ለሕጻናት እንክብካቤ፣ ለሎጅስቲክ እንዲሁም ለውሃና ንጽህና አጠባበቅ እንዲያውሉት ተፈቅዶላቸዋል።

ከገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚ ከሚኾኑት አገራት መካከል ከኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ በርማ እና ዩክሬን ይገኙበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍8😡3😢1🙏1
መረጃ‼️

የቀይ ባሕር አፋሮች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የዓለም መንግሥታት የኤርትራ መንግሥት ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተር ጋር እንዲተባበርና ልዩ ራፖርተሩ ወደ ኤርትራ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ተጽዕኖ እንዲያደርጉ ጠየቀ።

ልዩ ራፖርተሩ በኤርትራ ዙሪያ ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ሰሞኑን ያቀረቡትን ሪፖርት እንደሚደግፍ የገለጠው ድርጅቱ፣ ምክር ቤቱ የልዩ ራፖርተሩን ተልዕኮ እንዲያጠናክርና የልዩ ራፖርተሩን የጊዜ ቆይታ እንዲያራዝም ጠይቋል።

ድርጅቱ፣ አባል አገራት ኤርትራዊያን ስደተኞችን፣ ጋዜጠኞችንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ከኤርትራ መንግሥት የድንበር-ዘለል "ማስፈራሪያዎች" እና "ዛቻዎች" እንዲከላከሉ ጭምር ጥሪ አድርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍4🤪3
"በምድር ላይ ከኖሩት ሁሉ እጅግ ኃያሉ ሰው እኔ ነኝ’" ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት ተከታታይ መልዕክቶች፣ "በዚህች ፕላኔት ላይ ከተራመዱት ሰዎች ሁሉ እጅግ ኃያሉ ሰው እኔ ነኝ" የሚል ይዘት ያለውን ጽሑፍ በማጋራት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነዋል።

ትራምፕ ያጋሩት ጽሑፍ "የፕሬዝዳንታዊ ታሪክ ምሁር ዴቭ ኪንግ" በተባሉ ሰው የተጻፈ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱን እንደ ታላቁ እስክንድር፣ ጄንጊስ ካን እና ናፖሊዮን ካሉ ታዋቂ የዓለም ታሪክ መሪዎች ጋር በማነጻጸር ከሁሉም እንደሚበልጡ ይገልጻል።

ይህ መግለጫ ይፋ የሆነው ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ከአሜሪካ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የኢራን ጦርነት ለማቆም የሚያስችለውን ስምምነት በፈረሙ ማግስት ነው። ምንም እንኳን ይህ የሰላም ስምምነት በብዙ ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ትችት ቢሰነዘርበትም፣ ትራምፕ ግን እሳቸው ይህንን ስምምነት ባያደርጉ ኖሮ ዓለም "ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ" ውስጥ ትወድቅ እንደነበር በመግለጽ ውሳኔያቸውን ተከላክለዋል።

ጽሑፉን ያዘጋጁት የታሪክ ምሁሩ ዴቭ ኪንግ፣ ትራምፕን እንደ አቲላ ዘ ሁን (Attila the Hun) እና ዊሊያም ዘ ኮንከረር ካሉ ታሪካዊ ኃያላን መሪዎች ጋር ጭምር በማወዳደር የእሳቸው ተፅዕኖ የላቀ እንደሆነ ይሞግታሉ። ይህ የትራምፕ የሌሊት ማኅበራዊ ሚዲያ ፖስት በአሜሪካ ፖለቲካና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ አሁንም ከፍተኛ ክርክርና መነጋገሪያነቱን ቀጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3515🤡5👍4🥱2🤷‍♂1🥰1🤔1😢1😎1
ወደ ካናዳ የሥራ ስምሪት ተጀምሯል የሚሉ ማስታወቂያዎች ሀሰተኛ  መረጃዎች ናቸው ተባለ
 
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ ካናዳ የሚደረግ የሥራ ስምሪትም ሆነ ምዝገባ እስካሁን አልተጀመረም ሲል አስታውቋል።ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ፣ ወደ ካናዳ የሥራ ስምሪት ተጀምሯል በሚል ስም የሚሰራጩ ማስታወቂያዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን ገልጾ ዜጎች እንዳይታለሉ አሳስቧል።
 
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ከጆርዳን፣ ከኳታር እና ከሊባኖስ ጋር ባላት የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት ብቻ ህጋዊ የሥራ ስምሪት እየተካሄደ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
 
መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል ጋር ስምምነት የፈጸመው ሚኒስቴሩ ወጣቶችን በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግና የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ለማመቻቸት መሆኑን ጠቅሷል።በተጨማሪም ወደ ካናዳ እንልክዎታለን በሚል ሰበብ ገንዘብ የሚጠይቁ አካላት አጭበርባሪዎች መሆናቸውን ጠቁሞ  ለማንኛውም ፕሮግራም ክፍያ እንደማይጠየቅ መግለፁን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል ።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8
የቴዲ አፍሮ የቀድሞው ማናጀር አቶ አዲስ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የጃኖ ባንድ መስራች የነበሩት እና የሙዚቀኛ ገሰሰ ዘለቀ ወንድም የሆኑት ታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲዮሰርና ማኔጀር አቶ አዲስ ገሰሰ በአሜሪካን ሀገር ህይወታቸው ማለፉን የቅርብ ወዳጆቻቸው ለመዝናኛ ሚዲያ አስታወቁ።

አቶ አዲስ ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፉትን የቦብ ማርሊ ልጆችንእና በርከት ያሉ ታዋቂ ሙዚቀኞችን የማማከርና የማስተዳደር ስራ የሰሩ ጉምቱ የሙዚቃ አስተዳደር ባለሞያ ነበሩ። አቶ አዲስ የቴዲ አፍሮ ማኔጀር በመሆንም ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።

በትላንትናው እለት አመሻሹ ላይ በኒው ጀርሲ ግዛት ህይወታቸው ያለፈው አቶ አዲስ ገሰሰ ፣ የሞታቸው ምክንያት ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን አስከሬናቸውን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ እንደታሰበ የደረሰን መረጃ ያመለከታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19😢9👍4💔2
አሜሪካ በኢራን ላይ ጥላ የነበረውን የባሕር ኃይል እገዳ አንሳች

በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል በቅርቡ የተፈረመው ስምምነት ወደ ትግበራ ምዕራፍ መሸጋገሩን ተከትሎ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ ጥላ የነበረውን የባሕር ኃይል እገዳ በይፋ አነሳች።

ይህም የንግድ እና የነዳጅ ጭነቶች በባሕረ ሰላጤው እና በኦማን ባህረ ሰላጤ በኩል ዳግም መንቀሳቀስ እንዲጀምሩ አስችሏል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ የአሜሪካ ኃይሎች ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡትንም ሆነ የሚወጡትን የንግድ መርከቦች ማገድ ማቆማቸውን አረጋግጧል።

የኢራን የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን እና የጭነት መርከቦችን ጨምሮ የባሕር ላይ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ንብረቶች ስምምነቱ መከበሩን ለመቆጣጠር አሁንም በአካባቢው ተሰማርተው ይገኛሉ።

ይህ የእገዳ መነሳት የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት ተከትሎ እገዳው እንዲነሳ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ካስታወቁ በኋላ ነው።

የኢራን መገናኛ ብዙኃን እና ባለሥልጣናት ውጤቱን ለቴህራን እንደ ስትራቴጂካዊ ድል አድርገው ገልፀዉታል።
17👍5
ስዊዘርላንድ ሊካሄድ የነበረው የአሜሪካ እና የኢራን ውይይት ተራዘመ

በዛሬው ዕለት ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በስዊዘርላንድ ቡርገንሥቶክ ሪዞርት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የአሜሪካ እና የኢራን ስብሰባ መራዘሙን የስዊዘርላንድ እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ። ይህ እርምጃ በቅርቡ የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ለማስቆም እና ቁልፍ የሆኑ ቀጠናዊ የንግድ መስመሮችን ዳግም ለመክፈት የተደረሰውን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ላይ አለመተማመንን ፈጥሯል።

ሮይተርስ እንደዘገበው፤ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ለስብሰባ ወደ ስዊዘርላንድ እንደማይጓዙ ዋይት ሐውስ ያረጋገጠ ሲሆን፣ የስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በበኩሉ የቡርገንሥቶክ ስብሰባ በታቀደው መሠረት እንደማይካሄድ አስታውቋል። ለስብሰባው ሌላ አማራጭ ቀን አልተቆረጠም።

ይህ ውይይት በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል በሰኔ 10 እና 11 ቀናት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የተደረሰውን ጊዜያዊ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ተብሎ ሲጠርበቅ ነበር። በአንዳንድ ሪፖርቶች “የእስላማባድብ ሜሞረንደም” (Islamabad Memorandum) ተብሎ የተጠቀሰው ይህ መግባቢያ፤ ከኢራን ጋር የተያያዙ የቅርብ ጊዜ ወታደራዊ ፍጥጫዎችን ለማቆም፣ አሜሪካ የጣለችውን የባሕር ኃይል እገዳ ለማንሳት፣ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት እና የኢራንን የኑክሌር መርሃ ግብር፣ የማዕቀብ መነሳትን እንዲሁም መልሶ የመገንባት ጥረቶችን የሚያካትት ሰፊ ስምምነት ላይ ለመድረስ የ60 ቀናት የድርድር ሂደት ለመጀመር ያለመ ማዕቀፍ  ነው።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት የስብሰባውን መራዘም ከሎጂስቲክስ ውስብስብነት እና ከዝግጅት ጉድለት ጋር ያያዙት መሆኑን የገለጹ ቢሆንም፤ ሌሎች ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ግን የኢራን የድርድር ቡድን የጉዞ ዕቅዱን ያሰረዘው በቀጠለው ቀጠናዊ ውጥረት እና በሄዝቦላህ ይዞታዎች ላይ እስራኤል በምትፈጽመው ወታደራዊ ዘመቻ ሳቢያ ነው።

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፤ የስብሰባው መሰረዝ የተሰማው የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በስዊዘርላንድ ተገናኝተው መደበኛ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ያካሂዳሉ ወይም የመጀመሪያ ደረጃ መግባቢያውን ወደ አጠቃላይ ስምምነት ለመቀየር የሚያስችሉ የቴክኒክ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት በተሰጠበት ወቅት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5🙏1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
4👍2
የመንግስት ንብረት ምዝበራ ኦዲት ሪፖርት

በከ800 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ላይ የስወራ፣ የከፍተኛ አያያዝ እና የሊብሬ ችግሮች ተገኙ።

በመንግስት ተቋማት ላይ የተደረገው የኦዲት ፍተሻ አስገራሚ ግኝቶችን ይፋ አድርጓል።

የጠፉና በሌላ ድርጅት ስም የተመዘገቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውም ተረጋግጧል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በቅርቡ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችን የተሽከርካሪ አያያዝና ስምሪት አስመልክቶ ባደረገው ጥብቅ የኦዲት ምርመራ፣ ከፍተኛ የንብረት አያያዝ ጉድለትና ግድፈቶች ማግኘቱን አስታወቀ።

በኦዲት ሪፖርቱ ላይ የተመለከቱት በተለያዩ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ስር የሚገኙ 9 መኪናዎች እና 6 ሞተር ብስክሌቶች ፈፅሞ የት እንዳሉ ሳይታወቅ የጠፉ መሆኑ ተረጋግጧል።

በአስገራሚ ሁኔታ የ595 የመንግስት ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ) በሌሎች መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ስም ተመዝግቦ ተገኝቷል።

ምንም ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር ሳይኖራቸው በተቋማቱ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ 13 መኪኖች፣ 10 ሞተር ብስክሌቶች እና 20 ትራክተሮች በምርመራው ተለይተዋል።

ይህ የኦዲት ሪፖርት በመንግስት ተቋማት ዘንድ ያለውን የንብረት ቁጥጥር መላላትና የተጠያቂነት ክፍተት በግልጽ የሚያሳይ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍4😢2🤣2🙊1
የእናቱን አስክሬን ቤት አስቀምጦ የእናቱን ቃል ለማክበር የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ከቀብር በፊት እና በኃላ ለፈተና የተቀመጠው ካሊድ

ይሕ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታዳጊ ካሊድ ይባላል ገና የአስራ አራት ዓመት ልጅ ነው።ከሑለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር በሸገር ከተማ አስተዳደር ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ከእናቱ ጋር ይኖራል።

ካሊድ ከእናቱ ጋር ሲኖር ወላጅ አባቱ ከእነርሱ ርቆ ሌላ ትዳር መስርቶ ጅጅጋ ከተማ ይኖራል። ካሊድ ሠሞኑን እናቱ ታምወው በነበረበት ወቅት እኔ አንድ ነገር ብሆን ምንም ቢፈጠር አመት የለፋሕበትን ፈተና እንዳታቋርጥ ብለው ቃል ያስገቡታል።

እናትም በነጋታው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ሊሲጥ ሠዓታት ሲቀረው ሕይወታቸው ያልፋል።ካሊድ በእናቱ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ቢሰማውም ለእናቱ የገባው ቃል አክብሮ የእናቱን አስክሬን እቤት ጥሎ የጥዋት ፈተናውን ተፈተነ።

ካሊድ ከሠዓት እናቱን አልቅሶ ቀብሮ ተመልሶ የከሰዓት ፈተናውን ተፈተነ።የዚሕ የአስራ አራት አመት ታዳጊ የሕይወት ፈተና ብዙዎችን በሐዘን ማስለቀሱን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢10025💔14🫡3🤪3👍2🥰1
ታክስ ከፋዮች ከደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ

የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ሕጉ መሠረት የሒሳብ መዝገብ የሚይዙ ታክስ ከፋዮች፣ ራሱ ካበለፀገው የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት እንዲጠቀሙ የሚያዝ መመርያ ተግባራዊ አደረገ።

ገቢዎች ሚኒስቴር የራሳቸውን የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አበልፅገው ወይም ከአልሚዎች ገዝተው በማስፈቀድ ለሚጠቀሙ ታክስ ከፋዮች ዕውቅና እንዲያገኙ፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋትና አሠራራቸውን በሕግ ለመወሰን የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ሥርዓት መመርያ ቁጥር 1142/2018ን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ስለመጠቀም በሚደነግገው የመመርያው አንቀጽ 19፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ካዘጋጀው የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት፣ የሒሳብ መዝገብ በሚይዙ ሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት፣ ታክስ ከፋዮች ሽያጫቸውን ለመመዝገብና የሽያጭ መረጃዎችን በቀጥታ በኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ለማስተላለፍና ለመመዝገብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በፈቃደኝነት ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት መጠቀም እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡

ሆኖም በርካታ ደረሰኞችን የሚያመነጩና አሠራራቸው ለኦዲትና ለክትትል አመቺ የሆኑ ባንኮች፣ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያዎች፣ የዲጂታል ከፍያ አሳላጮች፣ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ለሸማች ወይም ለግል አገልግሎት በሚውሉ ግብይቶችና አገልግሎቶች ላይ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር በቀጥታ መገናኘት ሳያስፈልጋቸው፣ ደረሰኝ የሚሰጡበትን አሠራር ሚኒስቴሩ በልዩ ሁኔታ ሊፈቅድ ይችላል ተብሏል፡፡

አጠቃላይ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታን በሚመለከት በተደነገገው የመመርያው ከፍል፣ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሶፍትዌር ደኅንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሊያቀርብ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪም በኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓቱ ውስጥ የተተገበሩ የማንነት ማረጋገጫ፣ የግንኙነት መመስጠሪያና ሌሎች የደኅንነት አሠራሮችን መተግበሩና በዲጂታል ፊርማ የተረጋገጠ ግንኙነትና የመረጃ መላላክን ማስቻሉ ሊረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከቷል፡፡

Via : ሪፖርተር

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍4
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
7👍2
በህወሓት የጦር መሳሪያ ካምፕ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ።
ዛሬ ጥዋት በሱዳን ሽረሪና አከባቢ ህወሓት የጦር መሳሪያ ካምፕ አድርጎታል በተባለ ቦታ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የህወሓት አርሚ 70 የሚባለው ጦር በዚሁ አካባቢ ትንኮሳ ፈፅሞ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍12😢2🎉1👌1
ኢትዮጵያ የራሷን ብር በሀገር ውስጥ ልታትም ነው በየዓመቱ ወደ 100 ሚ. ዶላር ገደማ ይታደጋል

ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የነበረባትን የውጭ ሀገራት ጥገኝነት በማቆም፣ እ.ኤ.አ. በ2030 የኢትዮጵያን ብር በሀገር ውስጥ ማተም ለመጀመር ማቀዷን አስታውቃለች። በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሚመራው ይህ አዲስ ንቅናቄ፣ ሀገሪቱ በየዓመቱ ለገንዘብ ማተሚያ የምታወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚያድን ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የብር ኖቶችን በውጭ ሀገር (በተለይም በእንግሊዝ) ለማሳተም በየዓመቱ ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታወጣ ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደገለጹት፣ ይህ ተነሳሽነት ኢትዮጵያ ሰፊ የኢኮኖሚ ራስን የመቻል አቅም ለመገንባት፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነትን ለማጠናከርና በሀገራዊ መገበያያ ገንዘብ መረጋጋት ላይ ያላትን ቁጥጥር ለማሳደግ ከምታደርገው ስትራቴጂካዊ ጉዞ ጋር የተያያዘ ነው። በአሁኑ ጊዜ ከ40 በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት አሁንም ድረስ  የገንዘብ ኖቶቻቸውን ለማተም በአውሮፓ በሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ጥገኛ መሆናቸው ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣1513👍11😢2🤪2👌1🆒1
ምርትና አገልግሎትዎን ለማስተዋወቅ ያናግሩን 👇
@Addis_reporter_bot
👍41👌1
ሆርሙዝ ተመልሶ ተዘጋ‼️
አሜሪካ ስምምነቱን ጥሳለች በሚል የኢራን አብዮታዊ መንግሥት ዘብ
የሆሬሙዝ ሰርጥን መልሶ መዝጋቱን አሳውቋል።

ኢራን እስራኤል በሊባኖስ እየፈፀመች ያለችውን ጥቃት ባለማቆሟ ስምምነቱን ጥሷል ያለች ሲሆን እስራኤል በሊባኖስ የምትፈፅመውን የማስቆም ሀላፊነት የአሜሪካ ነው ብላለች።

ይህንን ተከትሎ 75$ ደርሶ የነበረው የአንድ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቶ 81$ ዶላር ገብቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣1914😡13🤔4👍3🤪1🙊1
የሕወሓት ቡድን ለአሜሪካ መልስ ሰጠ!

የአሜሪካ መንግሥት በፓርቲው አመራሮች ላይ የጣለው የቪዛ ገደብ ያልተሟላ እና ሚዛናዊነት የጎደለው ግምገማ ላይ የተመሠረተ ነው ሲል የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ክፉኛ ኮነነ።

ሕወሓት ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የአሜሪካን ሚና እንደሚያከብር ቢገልጽም፤ አዲሱ የማዕቀብ ውሳኔ ግን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ያሉበትን ግዴታዎች በተደጋጋሚ አለመወጣቱን ወደ ጎን በመተው፣ ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ በሕወሓት ላይ ብቻ የሚጭን በመሆኑ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ከሦስት ዓመታት በላይ ቢያልፉም፣ የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት መመለስ፣ የተፈናቃዮች መዋቅራዊ ዕርዳታ፣ የውጭ (የፌደራል ያልሆኑ) ኃይሎች ከትግራይ መሬት መውጣት እና የህወሓት ሕጋዊና ፖለቲካዊ ሰውነት ዕውቅና ማግኘት የተባሉት ቁልፍ ድንጋጌዎች አሁንም አልተተገበሩም ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤣13👍2