አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
416 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የባንኮች ፍላጎት ከአቅርቦቱ በሁለት እጥፍ በላይ በልጧል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የመደበ ቢሆንም፣ በባንኮች በኩል የቀረበው ፍላጎት ግን ከአቅርቦቱ በላይ በእጅጉ ጨምሮ ታይቷል። በጨረታው ላይ የተሳተፉት የፋይናንስ ተቋማት ለመግዛት የጠየቁት አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ማዕከላዊ ባንኩ ካቀረበው በሁለት እጥፍ በላይ በመብለጥ 236.30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል።

በተካሄደው በዚህ ጨረታ፣ አንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋው 158 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ላይ 16 የሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ቢሆንም፣ ካለው የተገደበ አቅርቦት እና ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የምንዛሬ ድልድሉን ማግኘት የቻሉት ግማሾቹ ወይም 8ቱ ባንኮች ብቻ መሆናቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍2💔2🤔1👌1
ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ አዲስ ጥቃት ሊከፍት ተዘጋጅቷል በማለት ከሠሠ።

መንግሥት የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም፣ ጦር ሠራዊቱን በማነቃነቅና በትግራይ ላይ እቀባ በማድረግ ሁለተኛ ዙር ጦርነት ሊያካሂድ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ያለው ሕወሃት፣ የፌደራል መንግስትቱ ባለስልጣናት የትግራይ ኃይሎችን በጦርነት ሰባኪነት የሚከሱት የጦርነት ዝግጅታቸውን አቅጣጫ ለማስቀየር ነው በማለት ተችቷል።

በትግራይ ስላለው ሁኔታ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን ሕዝብና ዓለማቀፉን ማኅበረሰብ እያሳሳቱ ይገኛሉ በማለት ጭምር ሕወሃት ወቅሷል።

ሕወሃት፣ ባለፉት ሦስት ወራት ለጦርነቱ ተፈናቃዮች ይቀርብ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡንም ገልጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍5🤣5
መርካቶ ላይ የፕላስቲክ ከረጢት የሚያሰራጩ 41 የጅምላ አከፋፋዮች ተጠያቂ ተደረጉ።
በአዲስ አበባ ከተማ ትልቁ የንግድ ማእከል በሆነው መርካቶ ሲኒማ ራስ አካባቢ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ሲያሰራጩ በነበሩ 41 የጅምላ አከፋፋይ የንግድ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ።

ይህ በድንገተኛ ፍተሻ የተከናወነው የተቀናጀ የክትትልና ቁጥጥር ዘመቻ የተመራው በአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ነው።

የከተማዋን ስነ-ምህዳር ለመጠበቅና የብክለት ምንጮችን ለመቀነስ የተወሰደው ይህ እርምጃ መነሻ ያደረገው፣ የፕላስቲክ ከረጢት አጠቃቀምን ለመገደብ በቅርቡ የወጣውን የአዋጅ ቁጥር 1383/2017 ድንጋጌን ነው።

እርምጃ የተወሰደባቸው ድርጅቶች ክልከላ የተጣለባቸውን እና ለአካባቢ ብክለት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በስፋት ሲያከፋፍሉ የተገኙ መሆናቸውን የቁጥጥር ቡድኑ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6
''የሰላም አማራጭን ችላ ብሎ ወደ ውጊያ ከገባ፣ አየር ኃይላችን ጠላትን እስከወዳኛው ይሸኛል''ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ''

ጠላት የሰላም አማራጭን ችላ ብሎ ወደ ውጊያ ከገባ፣ አየር ኃይላችን የጠላትን ህልውና እስከወዲያኛው የሚያከስም አስተማማኝ መቺ ኃይል መሆኑን በተግባር ያረጋግጣል ሲሉ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተደምጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣36👍167🫡2
በትግራይ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች አሰቃቂ እርምጃ እየወሰዱ ነው!

ቢቢሲ ትግረኛ በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ስላለው የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ አስደንጋጭ የምርመራ ሪፖርት ይዦ ወጥቷል፡፡ በወርቅ ማውጫ ስፍራዎች እና በሌሎች ስፍራዎች እየተፈጸመ ያለውን አፈሳ በዝርዝር የሚዳስሰው ዘገባው፤ ከህውሃት ታጣቂዎች ባለፈ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎችም በንጹሃን ላይ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡ እነዚህ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች የሕውሓት ወታደሮች ስለመሆናቸው ግን አልታወቀም፡፡

ግንቦት 17/2018 ዓ.ም. በዓብይ ዓዲ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ሁለት የወርቅ ማዕድን ማውጫዎች አባግባ እና ሩባኸዛ ከሚባሉ አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች አርሚ 60 አባላት እና ፊታቸውን የሸፈኑ ታጣቂዎች ከ700 ሰዎች በላይ ሰዎችን እንዳፈሱ ቢቢሲ ትግርኛ ከተጎጂዎች እና ከተጎጂ ቤተሰቦች መረጃ አግኝቷል።

የአራት ልጆች አባት የሆነው አቶ ሰለሞን ኃይለማርያም በዓብይ ዓዲ ከተማ ለሌሎች ሰዎች ድንጋይ እና አሸዋ በአህያ በመሸከም የቀን የጉልበት ሥራ ሠርቶ በሚያገኘው ገንዘብ ልጆቹን ያሳድግ ነበር። ነገር ግን እንደተለመደው ለሥራ ከወጣ በኋላ ከዛ በኋላ እሱ እና የአጎቱ ልጅ ወደ ቤት ሳይመለሱ መቅረታቸውን ቤተሰቡ ለቢቢሲ ገልጿል።

ባለቤቱ ወይዘሮ መድረኽ ኪዳነማርያም "ሰኞ ዕለት ወደ ሥራ እንደሄደ ጥዋት 3፡00 ሰዓት ላይ ነው ወሰዱት።. . . የምሠራበት ቦታ መንገድ ዳር ስለሆነ በግዳጅ ታፍሰው በመኪና ሲያልፉ አየሁኝ። 'እዚህ መኪና ላይ አለ' ሲሉኝ 500 ብር ተበድሬ ስጡልኝ ብየ ሰጥኋቸው" ብላለች።

ከዚያም በኋላ ባለቤቷ ከማይቅነጣል አልፎ ወደሚገኝ ወታደራዊ ማሠልጠኛ እንደተወሰደ መረጃ እንዳገኘችም ትገልፃለች። "በጣም ተጨንቀናል። ልጆቹ ናፍቀውታል። አባታችን እያሉ እያስቸገሩኝ ነው። ልጆቹን የሚረዳ አንድም የለም። ሰለሞንም ልጆቹን ትቶ እዚህ ውስጥ የመግባት ፍላጎት የለውም፤ በኃይል ነው የወሰዱት።"

ዘካርያስ* ከወርቅ ማውጫ አካባቢ "ፊታቸውን በሸፈኑ ታጣቂዎች" በኃይል ከታፈሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው።

በአፈሳው ወቅት ድብደባ፣ ማንገላታት እና ተኩስ ጭምር እንደነበር የሚናገረው ዘካሪያስ ከጣንቋ አበርገለ፣ ቀይሕ ተኽሊ እና ዓብይ ዓዲ ወረዳዎች የመጡ 500 ሰዎች ወደ ዓብይ ዓዲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት፤ ከቆላ ተምቤን የመጡ 200 ሰዎች ደግሞ በዓብይ ዓዲ ከተማ ነዳጅ ማደያ አቅራቢያ ወደሚገኘው ግንባታው ወዳላለቀ ሕንፃ በታጣቂዎቹ መወሰዳቸውን ይናገራል።

ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው ሌሎች ሰዎች ከታፈሱ በኋላ ለከተማው ፖሊስ እና ፀጥታ አካላት እንዲሁም ለዓብይ ዓዲ ከተማ እና ወረዳ አስተዳደር እንዳስረከቧቸው ይናገራሉ።

በዓብይ ዓዲ ከተማ ማዘጋጃቤት አዳራሽ የከተማዋ ከንቲባ እና ምክትሉ እንዲሁም የፀጥታ ኃላፊዎች በመምጣት 'ትዋጋላችሁ' እንዳሏቸው ጨምረው አስረድተዋል።

ከማዕድን ቁፋሮ የተያዙት ወጣቶች " 'ወድ ትግል ነው የምትሄዱት' አሉን። ልብስ ሳንለብስ ራቁታችን ነን ያለነው፣ እቃችን እና ሞባይላችን ሳንይዝ ከሥራ ላይ ነው ያፈሳችሁን፤ ልብሳችንን እንኳን እንልበስ አልናቸው። እነሱ ግን 'አያገባንም አትሄዱም አሉን" ብለዋል።

ዘካሪያስ በተለያየ ጊዜ በትግራይ ውስጥ በተካሄደ ጦርነት የቤተሰቡ አባላቱ መሰዋታቸውን ገልጾ ከተጣራ በኋላ መለቀቁን ተናግሯል።

ከዚያም በኋላ አውቶቡስ፣ ኦራል እና አይሱዙ መኪኖች አምጥተው ጭነው ወደ ሌላ ቦታ እንደወሰዷቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተጎጂዎች ይናገራሉ።

የአርሚ 60 የትግራይ ኃይሎች ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዘልዑል ማቲዮስ ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ የሚመሩት ቡድን በአባግባ አካባቢ ተሰማርቶ "እርምጃ" እንደወሰደ ገልጸዋል።

"በአካባቢው ሰፊ የማዕድን ወረራ አለ። እዚያ የነበሩትን ወጣቶች 'ኦፕሬሽን' በማካሄድ በትነናቸዋል። . . . በሩባኸዛ እና በአባግባ የነበረ ወጣት ለሌላ የፀጥታ ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ስለነበር እርምጃ ወስደናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ወጣቶቹ ማይቅነጣል እና ዕዳጋ ዓርቢ መካከል ወደሚገኘው ወታደራዊ ማሠልጠኛ እንደተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮሎኔሉ "... የማውቀው ነገር የለም" ሲሉ መልሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢4👍3🤷1
ወደ መቀሌ‼️
የአሜሪካ ኤምባሲ ልዑክ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ #መቐለ ሊያመራ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የ #አሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ መቐለ ከተማ ያቀናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ያገኘውነው መረጃ ያመለክታል።

ስለ ጉብኝቱ ዋና ዓላማ፣ ስለ ልዑካን ቡድኑ አባላት ማንነት እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። ይሁን እንጂ በመቐለ ከህወሓት አመራሮች ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ጉዞ በህወሓት እና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍7🍾1
የቻይና የገበያ ድርሻ በኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ላይ ወደ 4.4 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነገረ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያ ወደ ቻይና በመላክ ላይ የምትገኘው የምርት መጠንና ጥራት በመሻሻሉ በዘርፉ የ67.09 በመቶ አማካኝ ዓመታዊ ዕድገት ተመዝግቧል።

በዚህም መሰረት ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ የተለያዩ ምርቶቿን ወደ ቻይና ገበያ በመላክ በድምሩ 804.163 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት ችላለች።

በተጠናቀቀው የ2025 በጀት ዓመት የተመዘገበው አፈጻጸም ለዚህ ውጤት ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ በዓመቱ የተገኘው 369.4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ከቀደመው የ2024 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ251 በመቶ ታሪካዊ ዕድገት የታየበት እንደሆነ ተጠቅሷል።

ይህ አስደናቂ አፈጻጸም ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ካቀረበችው አጠቃላይ የ18.358 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ውስጥ የቻይናን የገበያ ድርሻ ወደ 4.4 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል። በዋናነትም ቡና እና ሰሊጥ ወደ ቻይና ከሚላኩ ምርቶች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄደው አጠቃላይ የንግድ ልውውጥ 29.12 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ፣ የሁለቱን ሀገራት የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር ጥንካሬ በግልጽ እንደሚያሳይ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍3
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
4👍4
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች አመልካቾችን መቀበል ጀምሯል፡፡
 
ዩኒቨርሲቲው ለ Masters ፕሮግራም በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች እንዲሁም ለ PhD ፕሮግራም በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች አመልካቾችን ይቀበላል፡፡

የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞቹን ዝርዝር በ https://admission.aau.edu.et/GraduatePrograms መመልከት ይችላሉ፡፡

አመልካቾች በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መውሰድና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የ GAT ማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍2
ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ አዲስ ጥቃት ሊከፍት ተዘጋጅቷል በማለት ከሠሠ።

መንግሥት የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም፣ ጦር ሠራዊቱን በማነቃነቅና በትግራይ ላይ እቀባ በማድረግ ሁለተኛ ዙር ጦርነት ሊያካሂድ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ያለው ሕወሃት፣ የፌደራል መንግስትቱ ባለስልጣናት የትግራይ ኃይሎችን በጦርነት ሰባኪነት የሚከሱት የጦርነት ዝግጅታቸውን አቅጣጫ ለማስቀየር ነው በማለት ተችቷል።

በትግራይ ስላለው ሁኔታ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን ሕዝብና ዓለማቀፉን ማኅበረሰብ እያሳሳቱ ይገኛሉ በማለት ጭምር ሕወሃት ወቅሷል።

ሕወሃት፣ ባለፉት ሦስት ወራት ለጦርነቱ ተፈናቃዮች ይቀርብ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡንም ገልጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13🤣8👍3
"አዲስ አበባ ጎርፍ ብትጠቃ አደጋው የደረሰበት ክፍለ ከተማ ይጠየቃል!"
 ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተያዘው ክረምት “በአዲስ አበባ ውስጥ ጎርፍ ቢያጋጥም ክፍለ ከተሞች ተጠያቂ እንደሚሆኑ” ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተያዘው ክረምት “የጎርፍ አደጋዎች አጋጥመው፣ ሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ቢያደርሱ፣ ከማንም በላይ ክፍለ ከተሞች ተጠያቂ እንደሚሆኑ” አስጠነቀቁ፡፡

ከንቲባዋ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳደር የ90 ቀናት መሪ እቅድ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

“ሕዝብ ውስጥ ትውላላችሁ፣ ታድራላችሁ፤ ትሰራላችሁ” ያሉት አዳነች፣ “ከማህበረሰቡ ጋር ተቀራርባችሁ፣ ችግሩን ታውቃላችሁ፣ ዋና ማእከል ሁሉንም ችግር ማወቅ አይጠበቅበትም” ብለዋል፡፡

መንግስት አሁን ያለውን የከተማ እድሳት አካሂዶ “የክረምት ጎርፍ ሰው አጠቃ
የሚል..አይገባንም (ዲዘርቭ አናደርግም)” ሲሉ የተደመጡት ከንቲባዋ፣ መንገዶች ሲሰሩ የታለፉ ቦታዎች ካሉ በአፋጣኝ መጠገን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ክፍለ ከተሞች በበጎ ፍቃድ ስራዎች አዳዲስ የጎርፍ መውረጃ መተላላፊያዎችን መጠገን፣ አዲስ ካስፈለገም መገንባት የግድ መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተው አስምረውበታል፡፡

በተጨማሪም በማብራሪያቸወው መንግስት የጀመራቸው ቤቶች ለመጨረስ ማቀዱን፣ የጭቃ ቤቶች ግንባታ መቆሙን፣ ጠጋግኖ ቁጥር ለማብዛት የሚደረገው አካሄድ እንደቀረም አስረድተዋል፡፡

ከዛ ይልቅ ክፍለ ከተሞች የተለያዩ በጎ ፍቃደኞች በማስተባባር የበጎ ፍቃድ ቤቶች እንዴት ሊሰሩ እንደሚችሉ ማሰብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23🤣15👍6🤪5😢3🤔1
ትራምፕ ስለ ህዳሴ ግድቡ‼️
ዶናልድ ትራምፕ ከ G7 ሀገራት ጋር በሚደረገው ስብሰባ ጎን ለጎን ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር  በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ ትስስር ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  ፕሮጀክት በግብፅ ላይ «ከፍተኛ ችግር» እያስከተለ መሆኑን በመጥቀስ ዋሽንግተን ለግብፅ ምላሽ ለመስጠት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ ዳግም ልትሳተፍ እንደምትችል አመላከቱ።

በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የቡድን 7 ጉባኤ ጎን ለጎን ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ውዝግብ ዙሪያ ግብፅ «በጣም ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ተስተናግዳለች» ያሉ ሲሆን፤ የናይል ውሃ ጉዳይ ሁለቱ መሪዎች ከሚወያዩባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡3113🤪6👍5
ለኢራን 300 ቢሊዮን ዶላር የስምምነቱ አካል ነው‼️
የአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት የሚከተሉትን ያጠቃልላል።
▪️ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ወታደራዊ ጥቃት ያበቃል። ይህ የስምምነት አካል እስራኤል በሊባኖስ ያለውን ጥቃት ታቆማለች ወይ የሚለው ጉዳይ አጣበቂኝ ውስጥ ከቶታል።
▪️አሜሪካ እና ኢራን የተጣሉ እገዳዎችን በፍጥነት ማንሳት ይጀምራሉ።
▪️ ለኢራን መልሶ ግንባታ 300 ቢሊዮን ዶላር እቅድ ተይዟል።
▪️አሜሪካ ሁሉንም አይነት የኢራን ማዕቀቦች 'በጊዜ ሰሌዳው መሰረት' ታነሳለች።
▪️አሜሪካ የታገዱ ሁሉንም የኢራን ንብረቶችን ትለቃለች።
ስምምነቱ 'በአጭር ጊዜ' ሊፈረም ነው ሲሉ ትራምፕ በ G7 ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። እስራኤል ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ባደረጉት ስምምነት መናደዷን በይፋ ገልፃለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍9🙏2🤪2👌1
የትግራይ ክልል መምህራን ማኅበር፣ በክልሉ የመምህራን ደመወዝ ለበርካታ ወራት ባለመክፈሉ መምህራን ከነቤተሰቦቻቸው በርሃብ ምክንያት እየታመሙ፣ እየተሠቃዩ እና አልፎ አልፎም ለሞት እየተዳረጉ ይገኛሉ ሲል ዛሬ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ።

ማኅበሩ፣ በፖለቲከኞች መካከል በተፈጠረ የሃሳብ ልዩነት ምክንያት የመምህራን ደመወዝ መከልከል ''የግፍ ግፍ" እና "በታሪክ የሚያስወቅስ" ተግባር ነው በማለት ኮንኗል።

የክልሉ መምህራን ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው ከዚህ ቀደም በደብዳቤና በሠማላዊ ሠልፍ ጭምር በተደጋጋሚ መጠየቁን የጠቀሠው ማኅበሩ፣ ኾኖም ለችግሩ ምላሽ የሚሠጥ አካል አልተገኘም ብሏል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ከፌዴራሉ መንግሥትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለችግሩ መፍትሔ እንዲያፈላልግም ማኅበሩ ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍2
ግብጽ በሱዳናዊያን ማዕድን አውጭዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።

በግብፅ እና በሱዳን መካከል ለረጅም ዘመናት አወዛጋቢ ሆኖ በቆየው "የሀላይብ ትሪያንግል" (Halaib Triangle) ግዛት ውስጥ የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በፈጸሙት ድንገተኛ የአየር ጥቃት ቢያንስ የሰባት ሱዳናዊያን ወርቅ አውጪዎች ሕይወት ማለፉ ተዘገበ።
ጥቃቱ የተፈጸመው በዚሁ አወዛጋቢ ቀጠና ውስጥ በሚገኘው "ጀበል አል ኡቃያት" በተሰኘው የወርቅ ማውጫ ስፍራ ላይ ነው። እንደ የአይን እማኞች እና የአካባቢው መረጃዎች ከሆነ፣ በጥቃቱ ወቅት የግብፅ የጦር ሄሊኮፕተሮች በስፋት የታዩ ሲሆን ከሰባቱ ሟቾች በተጨማሪ በአስር የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

በአሁኑ ሰዓት ሱዳን በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፣ የግብፅ መንግስት ደግሞ የጄነራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን የሚመራውን የሱዳን ጦር (SAF) በግልጽ በመደገፍ የቅርብ ወዳጅ ሆና እየሰራች ነው። ግብፅ ለሱዳን ወታደራዊ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ድጋፍ በምትሰጥበት በዚህ ወቅት ግን በድንበር አካባቢ የሚገኙ

ሱዳናዊያንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈጸሟ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ጥያቄን ጭሯል። የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ዜጎቹ በግብፅ ጦር መገደላቸው እየታወቀ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ይፋዊ መግለጫ አለመስጠቱ እና ዝምታን ጉዳዩን አስገራሚ አድርጎታል። ይህ ዝምታ በሱዳን ህዝብ ዘንድ "መንግስት ለወታደራዊ ድጋፍ ሲል የዜጎቹን ደህንነት ችላ ብሏል" የሚል ቅሬታን እየቀሰቀሰ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍7
"ሮናልዶ የድሮዉ ሮናልዶ አይደለም። እድሜዉ ጨምሯል።እሱን መከላከል ከባድ አልነበረም" ይህንን ያለዉ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎዉ ተከላካይ ሙካዉ ነዉ።

በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለምዋንጫ አፍሪካን ወክላ የተካፈለችዉ ኮንጎ ትናንት ምሽት ፖርቱጋልን በአለምዋንጫዉ ከብርቱ ተገዳዳሪነት በኋላ ነጥብ አስጥላ ወጥታለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤣3👍2
"ተመልሰን ቦምብ ልናዘንብ እንችላለን" - የትራምፕ ዛቻ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በስምምነቱ መሰረት ካልተጓዘች አዲስ ጥቃት አመራለሁ ሲሉ ዛቱ፡፡

በቡድን ሰባት ጉባዔ ፈረንሳይ የሚገኙት ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረሰው ስምምነት “ገና እንዳልተገባደደ” ጠቅሰው በመግባቢያ ሰነዱ አተገባበር ደስተኛ ካልሆኑ ቴህራን ላይ ጥቃት መፈጸም እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ኢራን ከእስራኤልና አሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ ከደረሰች በኋላ በሰጡት የመጀመሪያ አስተያየት "ጥቃቱ በዚሁ ከቀጠለ ጠንካራ ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል" ሲሉ ትራምፕ ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንቱ "ተመልሰን ቦምብ ልናዘንብ እንችላለን" ሲሉም ዝተዋል።

"የመግባቢያ ስምምነቱ አልተጠናቀቀም" ያሉት ትራምፕ "ካልወደድኩት ወታደራዊ እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉም የመፍረስ አደጋ እንዳለው ጠቁመዋል።

"ስምምነቱ በብዙ ምክንያት አስፈላጊ ነው" ካሉ በኋላ "99.9% የተስማማንበት ኢራን የኑክሌር መሳሪያ እንደማይኖራት ነው" ብለዋል።

ኢራን ለመልሶ ግንባታ የሚሆን 300 ዶላር ካሳ ይከፈላታል መባሉን "ውሸት ነው፣ ሳንቲም አናወጣም" ሲሉ አስተባብለዋል።   #thetimesofisrael

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🤔5🥱4👍3😡2
የፋርማሲ ተማሪዎች ቅሬታ‼️
የፋርማሲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች ፈተናው አስቀድሞ ተሰርቋል በማለት ቅሬታ አቀረቡ፤ የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ብሔራዊ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) አስቀድሞ ተሰርቆ ለተወሰኑ ተማሪዎች ተሰራጭቷል ሲሉ ተፈታኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተማሪዎች እንዳሉት፤ ለፈተናው በርካታ ልፋትና ዝግጅት ቢያደርጉም፣ ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት አማካኝነት ፈተናው ቀድሞ ወጥቶ መሰራጨቱን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሷቸው ገልጸዋል።

ይህ መሆኑም በከፍተኛ ጥረትና በራሳቸው ልፋት የተፈተኑ ተማሪዎችን ስነ-ልቦና በእጅጉ የጎዳና ፍትሃዊነትን ያጓደለ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

ተፈታኞቹ አያይዘውም፣ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም በኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር (EPA) በኩል በአስቸኳይ ታይቶ፣ አስፈላጊው ማጣሪያ እንዲደረግና ተገቢው ምላሽ እንዲሰጣቸው በትህትና ጠይቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍6🤯1👀1🙊1
የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 38.23 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈሪ መኮንን

በ2018 በጀት አመት በአስራ አንድ ወራት 42.49 ቢሊዮን ብር ጥቅል ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 38.23 ቢሊዬን ብር ገቢ መሰበሰቡን አስታውቀዋል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ3.97 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍6🤣21👌1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
👍53