አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የአማራ ወጣቶች እንዲታገሉ አቶ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ‼️
የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ ለአማራ ወጣቶች የትግል ጥሪ አቀረቡ፡፡ ‹‹አመራሮቹን ሄዳችሁ ታገሏቸው›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አረጋ ይህን ያሉት “ባህር ዳርን ወደ ላቀ ከፍታ ለመውሰድ የወጣቶች ሚና የማይተካ ነው” በሚሉ መሪ ቃላት  ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቾት አልባ የሚያደርገው የአስተዳደር ብልሽት መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ አመራሩ በቀላሉ የሚገኝ፣ ቀላልና ውሳኔ መስጠት የሚችል መሆን እንዳለበት አጽንኦት የሰጡ ሲሆን በተለይም በሕዝብና በሀገር ላይ የሚፈጸሙ የሌብነት ድርጊቶችን ወጣቱ በግንባር ቀደምትነት ሊታገላቸው ይገባል ብለዋል።

“ሌብነት ውስጥ የመሬት ስርቆት፣ የግብር ስርቆት፣ የኮንትራት ስርቆት ውስጥ የሚገባ፣ ግን መስረቅ ሳያንስ የሚመራውን ደሃ ሕዝብ የጎሪጥ የሚያይ አመራር ላይ በጽናት መታገል ያስፈልጋል።” ሲሉ የባህር ዳር ወጣቶች በተሰበሰቡበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24😁20🤪8👍7🤯2🥰1👏1🤔1👌1
አሜሪካ ለኢራን‼️😯
25 ቢሊዮን ዶላር ጦርነት ላቆመችበት ይሰጣታል።
300 ቢሊዮን ዶላር በጦርነቱ ለወደመባት መልሶ ግንባታ እንደሚሰጣት የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ቫንስ አረጋግጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪48👍2119🙉9👏3👀2😎2😁1👌1🤝1
ብሔራዊ ባንክ በቴክኒክ ችግር ተሰርዞ የነበረውን የ100 ሚሊዮን ዶላር ልዩ ጨረታ ነገ በድጋሚ ያካሂዳል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባልታሰቡ የቴክኒክ ችግሮች ምክንያት መሰረዙን ያስታወቀውን ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ ነገ ማክሰኞ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በድጋሚ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ባንኩ ይፋ ባደረገው አዲስ መርሃ-ግብር መሠረት፣ ለዚህ ጨረታ የቀረበው የገንዘብ መጠን 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው የሀገሪቱ የንግድ ባንኮች በተቀመጠው ዝርዝር መመሪያ መሠረት ዝግጅት በማድረግ በጨረታው ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍2
የበጀት ቁጥሮች!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍8😁7👀51🙊1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትናንት ምሽት #የአሜሪካ B-52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላን ከካሊፎርኒያ #ኤድዋርድስ ማዘዣ ጣቢያ ከተነሳ በኃላ ብዙም ሳይቆይ በመከስከሱ የ8 ሰዎች ህይወት ልያልፍ ችሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍8😢7🤪3😎2🤣1💔1🙈1
በአዲስ አበባ ከተማ ፍቃዳቸውን ያላደሱ የጤና ተቋማት ከመስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም ተባለ‼️
 
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት የጤና ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ እድሳትን በወቅቱ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ አቅርቧል።ከ4 ሺህ በላይ የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት እድሳታቸውን ከሐምሌ 1 እስከ ነሐሴ 30 ቀን ድረስ በኦንላይን ሥርዓት ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል።
 
በአዲስ አበባ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን የጤና ተቋማትና ጤና ባለሙያዎች ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ወርዶፋ ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት ከነሐሴ 30 እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ  ፍቃዳቸውን ያላደሱ ተቋማት በቅጣት ማደስ ይችላሉ። ከመስከረም 30 በኋላ ግን የብቃት ማረጋገጫቸው ወይም የሥራ ፍቃዳቸው ተሰርዞ አገልግሎት መስጠት እንደማችሉ ገልፀዋል።
 
በተጨማሪም ተቋማቱ የጤና ባለሙያዎች ሲቀጠሩ ወይም ሥራ ሲለቁ ለባለሥልጣኑ በወቅቱ ማሳወቅ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል።ከ2 ዓመት በላይ ከሙያ ውጪ የነበሩ ባለሙያዎች የሙያ ፍቃዳቸውን ሳያስተካክሉ መቅጠር እንደማይገባ አንስተዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
ባለስልጣናቱ “ህወሓት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወስኗል” ሲሉ፣ ህወሓትም በተመሳሳይ ትግራይ ላይ ጦርነት ሊከፈት ነው ሲል ተናገረ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የፌደራል መንግስት ገዢ ፓርቲ ብልፅግና፣ የሚያራምደው ሥርዓት በትግራይ ሕዝብ ላይ ድጋሚ ጦርነት ለመክፈት የሚያደርገውን ዝግጅት “በማታለልና በማጭበርበር ለመደበቅ እየሞከረ ነው” በማለት ኮንኖታል።

ህወሓት በትናንትላው ዕለት ባወጣው መግለጫ ገዥው ፓርቲ ልዩነቶችን በኃይል ለመፍታት በማመን ቀደም ሲል በትግራይ ህዝብ ላይ ፈጽሞታል ያለውን “የጅምላ ግድያ” በሁለተኛ ዙር ለመፈፀም አሁንም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል ብሏል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን በኃይል የተቆጣጠረው፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ህጋዊ ሰውነቱ የተሰረዘው ህወሓት፣ ገዥው ፓርቲን በጦርነት ዝግጅት እና በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ከስሷል፤ በመግለጫው፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት፣ በህወሓት ላይ ሰፊ ትችቶችን በመሰንዘር የጋራ ጽሁፋቸውን ያስነበቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ሚኒስትር እና የቀድሞው የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር  የነበሩት ጌታቸው ረዳ እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ ሬድዋን ሁሴን “ህወሓት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወስኗል” ሲሉ መክሰሳቸው ይታወሳል።

አክለዉም በትግራይ ክልል የፕሪቶሪያውን የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት የሚቃወመው የህወሓት ስብስብ፣ ስምምነቱን በይፋ በመሻር ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ለቀጥታ ወታደራዊ ግጭት እየተዘጋጀ መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተው ነበር፡፡
ከዚህ በተቸማሪም “ጽምዶ” የተሰኘው ጥምረት በአስመራ፣ በመቀሌ እንዲሁም በሱዳን ተደጋጋሚ ስብሰባ እያደረጉ መሆኑን በመጥቀስ ህወሓት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ መገለጹ አይዘነጋም፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍6🕊2
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍3
የሸኔ ጥቃት‼️
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በዛሬው እለት ለሊት የሸኔ ታጣቂዎች በጉንደ መስቀል ጎለልቻ ገብተው አባት ከነ ልጁ ገድለዋል።

8 ሰው አቁስለው ሆስፒታል ገብተዋል፣ብዙዎች ታግተዋል የጠፉም መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

በርካታ የቀንድ ከብቶች በጥይት ተመተው ሞተዋል የተረፉትን ወስደዋቸዋል።

ሰኔ 6/2018 በዚሁ ወረዳ ከአባዶ ወደ ጉንደ መስቀል ሲጓዝ የነበረ አንድ የህዝብ መኪና ሙሉ ተሳፋሪው ከነ ሹፌሩ ታግተዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።(ayu)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢265👍4💔2🕊1😡1
የላቁ ቴክኖሎጂዎች በነባር ጉድጓዶች ውስጥ የ42 ትሪሊዮን ዶላር የነዳጅ ዕድል እየፈጠሩ መሆኑ ተገለጠ

አዳዲስ የነዳጅ ክምችቶችን ፍለጋ ሳያስፈልግ፣ እስካሁን ሳይወጣ በነባር የነዳጅ ማውጫዎች ውስጥ ተቀብሮ የሚገኘውንና አሁን ባለው የዓለም ገበያ ዋጋ ከ42 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ድፍድፍ ነዳጅ በላቁ የቴክኖሎጂ አማራጮች ማውጣት የሚያስችል አዲስ የኢነርጂ ዘመን መጀመሩን የዘርፉ ተንታኞች ጠቆሙ።

የኢነርጂ ዘርፍ ጥናት አድራጊው ‘ዉድ ማኬንዚ’ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ “ኢንሃንስድ ኦይል ሪከቨሪ” (EOR) የተባሉ የላቁ የነዳጅ ማውጫ ቴክኖሎጂዎችን (እንደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና ፖሊመር መርጫዎችን) በመጠቀም በዓለም ዙሪያ ተጨማሪ 470 ቢሊዮን በርሜል ነዳጅ ማውጣት የሚቻል ሲሆን፣ ይህም ስልት አጠቃላይ የነዳጅ ኢንዱስትሪውን ዋነኛ የዕድገት አቅጣጫ እየቀየረው ይገኛል።

የዚህ ሽግግር ዋነኛ ምክንያት የዓለም ትላልቅ የነዳጅ ኩባንያዎች እ.ኤ.አ. በ2040 ሊያጋጥማቸው የሚችለውን በቀን የ22 ሚሊዮን በርሜል የምርት እጥረት ለመሙላት ባህላዊው የፍለጋ ቁፋሮ አስቸጋሪ እና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት እንደ ኤክሶን ሞቢል እና ኦክሲዴንታል ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች እንዲሁም የተለያዩ አገራት መንግስታት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ EOR ቴክኖሎጂዎች እያፈሰሱ ይገኛሉ።

ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆነው በትሪኒዳድ የሚንቀሳቀሰው ‘ግሪንፍሌም ሪሶርስስ’ የተባለው ኩባንያ 81 ሚሊዮን በርሜል ክምችት ኖሮት እስካሁን 1% ብቻ በወጣበት ‘ፓሪላንድስ ብሎክ ኢ’ በተባለው ይዞታ ላይ ያሉትን 110 ነባር ጉድጓዶች እና መሰረተ ልማቶች በመጠቀም የላቁ የማውጫ ስልቶችን ለመተግበር የጀመረው ስራ ሲሆን፣ ይህ አዝማሚያ እንደ ቤከር ሂውዝ እና ሃሊበርተን ያሉ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችን የገበያ ተጠቃሚነት በእጅጉ እያሳደገው ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍3
ሕወሓትን የተቃወሙት የ76 አመት አዛውንት ታሰሩ‼️
በትግራይ ክልል የእንደርታ ተወላጅ የሆኑት የ76 ዓመቷ ነባር ታጋይ አኸዛ ሕሉፍ፣ በክልሉ ስላለው የፍትህ እጦት፣ የመልካም አስተዳደር እክል እና የፖለቲካ ብልሽት አስመልክተው ከሶስት ቀናት በፊት የሰጡት ቃለመጠይቅ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ በህወሓት ታጣቂዎች ታግተው መታሰራቸው ተሰማ።

የወረዳ 70 እንደርታ የፈለግማያት ጣቢያ ነዋሪ የሆኑት እናት ለምን ተነፈስሽ? ለምንስ ተናገርሽ?” በሚል ዛሬ መታሰራቸውን ተረጋግጧል።

እንደ መረጃዎች ገለጻ ለእስራታቸው ዋነኛ ምክንያት የሆነው “ለምን ልጆች ወደ ጦርነት ይገባሉ?” በማለት ሰላማዊ ጥሪ ማቅረባቸውና እንደሌሎቹ የጦርነት ነጋሪት ለመጎሰም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ሲሆን፣ የቀድሞው ህወሓት እስከ እድሜ ልክ የሚያስቀጣ አፋኝ ህግ ማውጣቱ በሚታወስበት በዚህ ወቅት የ76 ዓመት አዛውንት በአመለካከታቸው ማሰሩ ከፍተኛ ቁጣንና ትዝብትን እየቀሰቀሰ ይገኛል።

እስካሁንም እናት አኸዛ ሕሉፍ በታጣቂዎች ተወስደው የት ቦታ እንደታሰሩና አሁን ያሉበት ሁኔታ በትክክል አለመታወቁ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1914💔5👍4🕊2🤪1🙉1
ምርትና አገልግሎትዎን ማስተዋወቅ ለምትፈልጉ ( ማስታወቂያ ለማሰራት)  በተመጣጣኝ ዋጋ
ከታች ባለው ቦት አዋሩን
👇👇
@Addis_reporter_bot
👍31
በኢትዮጵያ በዓመት 63 ሚሊዮን እንቁላል የማሳቀፍ አቅም ያለው የጫጩት መፈልፈያ ሊገነባ ነው

ግብርና ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የዶሮ ምርት አቅም ለማሳደግ የሚያስችል፣ በአመት 63 ሚሊዮን እንቁላል የማሳቀፍ አቅም ያለው ዘመናዊ የዶሮ ጫጩት መፈልፈያ ተቋም ለመገንባት ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 10.15 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የዶሮ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮግራም ሥር የተከናወነው ይህ ስምምነት፣ በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ጥራት ያለውን የምርት ግብዓት ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

በስምምነቱ መሠረት አግሪፋም ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግንባታውን ውሉ ከጸና በኋላ በአንድ ሳምንት ውስጥ እንደሚጀምር ይጠበቃል፤ በ12 ወራት ውስጥም ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ካፒታል ከሚኒስትሩ ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9🤔5👍4👏2🤣2🥰1🤯1👌1
ከአብይ ጎን እቆማለሁ-ጄኔራሉ‼️
የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ልጅ የሆኑት እና የዩጋንዳ ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ሙኡዚ በቲውተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል።

'በትግራይ ሌላ ጦርነት እንዳይነሳ እለምናለሁ፣በጣም እወዳቸዋለሁ ግን ጦርነት ሰልችቶናል ብሏል።

ጦርነት ከተነሳ ግን ወንድሜን  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን እደግፋለሁ"ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪44😁17👍12🫡86🌚5🙉2👏1🤔1👀1🙊1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦

ከጠዋቱ 2:00-9:30

👉ችሎት አደባባይ፣ ዘበኛ ሰፈር፣ ሾላ፣ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ሰሜን ሆቴል ጫፍ፣ ቀለመወርቅ ት/ቤት፣ ዶሮ ተራ፣ ራስ ደስታ አካባቢ፣ አርበኞች ት/ቤት፣ ዕንቁላል ፋብሪካ አደባባይ እና አካባቢው ፣

👉ፊሊጶስ ቤ/ክ፣ እስላም መቃብር፣ ሎሚ ሜዳ ፣ ጠሮ መስጊድ፣ጠሮ ሥላሴ፣ አወልያ፣ ካኦጄጄ፣ አበነሃብተማርያም፣ አስኮ ጨረታ እና አካባቢው፣

👉ኮተቤ አንቆርጫ አካባቢ፣ ጨለቆ፣ አቡ ሱቅ፣ ውሃ ታንከር፣ ጫካ ፕሮጀክት እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 3:00-8:00

👉ቦሌ ግሪክ ት/ቤት አካባቢ፣ ኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ፓላስ አካባቢ፣ፒኮክ ፓርክ እና አካባቢው ፣

👉ሴቶች አደባባይ፣ ካሳንቺስ መብራት ኃይል፣ ሂልተን ሆል ጀርባ፣ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል፣ ሐናን ዳቦ፣ ኢሊሌ ሆቴል፣ እናት ባንክ  እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 4:00-12:30

👉አትላስ ሆቴል፣ ሻላ መናፈሻ፣ ኤስኦኤስ፣ ደሳለኝ ሆተል ጀርባ፣ ደሳለኝ ሆቴል፣ ፕሬዚደንሺያል ሆቴል፣ ወደ ሩዋንዳ ኦቨርፓስ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 4:40- ምሽቱ 11:00

👉ቡራዩ ድሬ ከአስፋልት በላይ፣ ገፈርሳ ውሀ ግድብ እና አካባቢው፣ ሲሊ፣ ከረላ፣ መናገሻ፣ ጉዳ፣ ኬላ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር በከፊል፣ቶልቻ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 5:00-10:30

👉ዓለም ገና፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ፉሪ ሬዲዮ ጣቢያ፣ ፉሪ፣ ሃጂ ሪልስቴት አካባቢ፣ ወርዶፋ ሎጅ፣ ዳርፉር ሰፈር፣ ጀሞ 2 እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2:00-10:00

👉አቃቂ ዓለም ባንክ፣አርሴማ ጸበል እና አካባቢው

ከጠዋቱ 2:30-8:30

ጋምቤላ ፋኚዶ፣ ኡኩና ቀበሌ፣ መንደር 14 እና አካባቢው፣

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
የአሜሪካ እና እስራኤል ተቃርኖ‼️
አሜሪካ ባትኖር እስራኤል የምትባል ሀገር አትኖርም ነበር' - ትራምፕ‼️
ኔታንያሁ ጥሩ ጓደኛዬ ነው ነገር ግን  በሊባኖስ ላይ እየፈፀመ ያለው አስፈሪ የቦንብ ጥቃት አበሳጭቶኛል ብለዋል።
ኔታንያሁ በበኩላቸው ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነው፣እኔ  የእስራኤል መሪ ነኝ፣ለእስራኤል የሚጠቅማትን የማውቀው እኔ ነኝ ብለዋል። እስራኤል ዛሬም በሊባኖስ ጥቃት ፈፅማለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2918👍3🥰1🕊1
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የባንኮች ፍላጎት ከአቅርቦቱ በሁለት እጥፍ በላይ በልጧል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የመደበ ቢሆንም፣ በባንኮች በኩል የቀረበው ፍላጎት ግን ከአቅርቦቱ በላይ በእጅጉ ጨምሮ ታይቷል። በጨረታው ላይ የተሳተፉት የፋይናንስ ተቋማት ለመግዛት የጠየቁት አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ማዕከላዊ ባንኩ ካቀረበው በሁለት እጥፍ በላይ በመብለጥ 236.30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል።

በተካሄደው በዚህ ጨረታ፣ አንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋው 158 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ላይ 16 የሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ቢሆንም፣ ካለው የተገደበ አቅርቦት እና ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የምንዛሬ ድልድሉን ማግኘት የቻሉት ግማሾቹ ወይም 8ቱ ባንኮች ብቻ መሆናቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍2💔2🤔1👌1
ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ አዲስ ጥቃት ሊከፍት ተዘጋጅቷል በማለት ከሠሠ።

መንግሥት የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም፣ ጦር ሠራዊቱን በማነቃነቅና በትግራይ ላይ እቀባ በማድረግ ሁለተኛ ዙር ጦርነት ሊያካሂድ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ያለው ሕወሃት፣ የፌደራል መንግስትቱ ባለስልጣናት የትግራይ ኃይሎችን በጦርነት ሰባኪነት የሚከሱት የጦርነት ዝግጅታቸውን አቅጣጫ ለማስቀየር ነው በማለት ተችቷል።

በትግራይ ስላለው ሁኔታ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን ሕዝብና ዓለማቀፉን ማኅበረሰብ እያሳሳቱ ይገኛሉ በማለት ጭምር ሕወሃት ወቅሷል።

ሕወሃት፣ ባለፉት ሦስት ወራት ለጦርነቱ ተፈናቃዮች ይቀርብ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡንም ገልጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍5🤣5
መርካቶ ላይ የፕላስቲክ ከረጢት የሚያሰራጩ 41 የጅምላ አከፋፋዮች ተጠያቂ ተደረጉ።
በአዲስ አበባ ከተማ ትልቁ የንግድ ማእከል በሆነው መርካቶ ሲኒማ ራስ አካባቢ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ሲያሰራጩ በነበሩ 41 የጅምላ አከፋፋይ የንግድ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ።

ይህ በድንገተኛ ፍተሻ የተከናወነው የተቀናጀ የክትትልና ቁጥጥር ዘመቻ የተመራው በአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ነው።

የከተማዋን ስነ-ምህዳር ለመጠበቅና የብክለት ምንጮችን ለመቀነስ የተወሰደው ይህ እርምጃ መነሻ ያደረገው፣ የፕላስቲክ ከረጢት አጠቃቀምን ለመገደብ በቅርቡ የወጣውን የአዋጅ ቁጥር 1383/2017 ድንጋጌን ነው።

እርምጃ የተወሰደባቸው ድርጅቶች ክልከላ የተጣለባቸውን እና ለአካባቢ ብክለት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በስፋት ሲያከፋፍሉ የተገኙ መሆናቸውን የቁጥጥር ቡድኑ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6
''የሰላም አማራጭን ችላ ብሎ ወደ ውጊያ ከገባ፣ አየር ኃይላችን ጠላትን እስከወዳኛው ይሸኛል''ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ''

ጠላት የሰላም አማራጭን ችላ ብሎ ወደ ውጊያ ከገባ፣ አየር ኃይላችን የጠላትን ህልውና እስከወዲያኛው የሚያከስም አስተማማኝ መቺ ኃይል መሆኑን በተግባር ያረጋግጣል ሲሉ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተደምጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣36👍167🫡2
በትግራይ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች አሰቃቂ እርምጃ እየወሰዱ ነው!

ቢቢሲ ትግረኛ በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ስላለው የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ አስደንጋጭ የምርመራ ሪፖርት ይዦ ወጥቷል፡፡ በወርቅ ማውጫ ስፍራዎች እና በሌሎች ስፍራዎች እየተፈጸመ ያለውን አፈሳ በዝርዝር የሚዳስሰው ዘገባው፤ ከህውሃት ታጣቂዎች ባለፈ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎችም በንጹሃን ላይ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡ እነዚህ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች የሕውሓት ወታደሮች ስለመሆናቸው ግን አልታወቀም፡፡

ግንቦት 17/2018 ዓ.ም. በዓብይ ዓዲ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ሁለት የወርቅ ማዕድን ማውጫዎች አባግባ እና ሩባኸዛ ከሚባሉ አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች አርሚ 60 አባላት እና ፊታቸውን የሸፈኑ ታጣቂዎች ከ700 ሰዎች በላይ ሰዎችን እንዳፈሱ ቢቢሲ ትግርኛ ከተጎጂዎች እና ከተጎጂ ቤተሰቦች መረጃ አግኝቷል።

የአራት ልጆች አባት የሆነው አቶ ሰለሞን ኃይለማርያም በዓብይ ዓዲ ከተማ ለሌሎች ሰዎች ድንጋይ እና አሸዋ በአህያ በመሸከም የቀን የጉልበት ሥራ ሠርቶ በሚያገኘው ገንዘብ ልጆቹን ያሳድግ ነበር። ነገር ግን እንደተለመደው ለሥራ ከወጣ በኋላ ከዛ በኋላ እሱ እና የአጎቱ ልጅ ወደ ቤት ሳይመለሱ መቅረታቸውን ቤተሰቡ ለቢቢሲ ገልጿል።

ባለቤቱ ወይዘሮ መድረኽ ኪዳነማርያም "ሰኞ ዕለት ወደ ሥራ እንደሄደ ጥዋት 3፡00 ሰዓት ላይ ነው ወሰዱት።. . . የምሠራበት ቦታ መንገድ ዳር ስለሆነ በግዳጅ ታፍሰው በመኪና ሲያልፉ አየሁኝ። 'እዚህ መኪና ላይ አለ' ሲሉኝ 500 ብር ተበድሬ ስጡልኝ ብየ ሰጥኋቸው" ብላለች።

ከዚያም በኋላ ባለቤቷ ከማይቅነጣል አልፎ ወደሚገኝ ወታደራዊ ማሠልጠኛ እንደተወሰደ መረጃ እንዳገኘችም ትገልፃለች። "በጣም ተጨንቀናል። ልጆቹ ናፍቀውታል። አባታችን እያሉ እያስቸገሩኝ ነው። ልጆቹን የሚረዳ አንድም የለም። ሰለሞንም ልጆቹን ትቶ እዚህ ውስጥ የመግባት ፍላጎት የለውም፤ በኃይል ነው የወሰዱት።"

ዘካርያስ* ከወርቅ ማውጫ አካባቢ "ፊታቸውን በሸፈኑ ታጣቂዎች" በኃይል ከታፈሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው።

በአፈሳው ወቅት ድብደባ፣ ማንገላታት እና ተኩስ ጭምር እንደነበር የሚናገረው ዘካሪያስ ከጣንቋ አበርገለ፣ ቀይሕ ተኽሊ እና ዓብይ ዓዲ ወረዳዎች የመጡ 500 ሰዎች ወደ ዓብይ ዓዲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት፤ ከቆላ ተምቤን የመጡ 200 ሰዎች ደግሞ በዓብይ ዓዲ ከተማ ነዳጅ ማደያ አቅራቢያ ወደሚገኘው ግንባታው ወዳላለቀ ሕንፃ በታጣቂዎቹ መወሰዳቸውን ይናገራል።

ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው ሌሎች ሰዎች ከታፈሱ በኋላ ለከተማው ፖሊስ እና ፀጥታ አካላት እንዲሁም ለዓብይ ዓዲ ከተማ እና ወረዳ አስተዳደር እንዳስረከቧቸው ይናገራሉ።

በዓብይ ዓዲ ከተማ ማዘጋጃቤት አዳራሽ የከተማዋ ከንቲባ እና ምክትሉ እንዲሁም የፀጥታ ኃላፊዎች በመምጣት 'ትዋጋላችሁ' እንዳሏቸው ጨምረው አስረድተዋል።

ከማዕድን ቁፋሮ የተያዙት ወጣቶች " 'ወድ ትግል ነው የምትሄዱት' አሉን። ልብስ ሳንለብስ ራቁታችን ነን ያለነው፣ እቃችን እና ሞባይላችን ሳንይዝ ከሥራ ላይ ነው ያፈሳችሁን፤ ልብሳችንን እንኳን እንልበስ አልናቸው። እነሱ ግን 'አያገባንም አትሄዱም አሉን" ብለዋል።

ዘካሪያስ በተለያየ ጊዜ በትግራይ ውስጥ በተካሄደ ጦርነት የቤተሰቡ አባላቱ መሰዋታቸውን ገልጾ ከተጣራ በኋላ መለቀቁን ተናግሯል።

ከዚያም በኋላ አውቶቡስ፣ ኦራል እና አይሱዙ መኪኖች አምጥተው ጭነው ወደ ሌላ ቦታ እንደወሰዷቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተጎጂዎች ይናገራሉ።

የአርሚ 60 የትግራይ ኃይሎች ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዘልዑል ማቲዮስ ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ የሚመሩት ቡድን በአባግባ አካባቢ ተሰማርቶ "እርምጃ" እንደወሰደ ገልጸዋል።

"በአካባቢው ሰፊ የማዕድን ወረራ አለ። እዚያ የነበሩትን ወጣቶች 'ኦፕሬሽን' በማካሄድ በትነናቸዋል። . . . በሩባኸዛ እና በአባግባ የነበረ ወጣት ለሌላ የፀጥታ ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ስለነበር እርምጃ ወስደናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ወጣቶቹ ማይቅነጣል እና ዕዳጋ ዓርቢ መካከል ወደሚገኘው ወታደራዊ ማሠልጠኛ እንደተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮሎኔሉ "... የማውቀው ነገር የለም" ሲሉ መልሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢4👍3🤷1