አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ በነበረ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ነው።

ዛሬ ሰኔ 08/10/18ዓ.ም ማለዳ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ አውቶቡስ በተለምዶ ሐረጎ እየተባለ በሚጠራው መንገድ ላይ በደረሠበት አደጋ እስካሁን የ28 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባተቸዋል።

የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በግምት100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል ገብቶ ነው አደጋው የደረሠው።
በሕይወት የተረፉትን ወደ ሕክምና ቦታ ለማድረስ አሁንም ርብርብ እየተደረገ መኾኑን የገለጸው ፓሊስ የአደጋውን ምክንያት በመጣራት ላይ ነው ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢32💔267👍2🙏1🥱1
በመጨረሻም ተስማሙ‼️
አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ከስምምነቱ ደረሱ።
በመጪው አርብ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ ሊፈራረሙ ቀጠሮ ይዘዋል።
ይህን ተከትሎ ሆርሙዝ ክፈት መደረጉን፣ በኢራን ላይ የተጣለው የባህር ላይ እገዳ መነሳቱን ትራምፕ አስታውቀዋል።
ኢራንም ስምምነቱን መቀበሏን የገለፀች ሲሆን ሊባኖስን ጨምሮ ጦርነቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም ተስማምቻለሁ ብላለች። ይህ የትራምፕ ስምምነት እስራኤልን ከጨዋታው ውጪ ማድረጉ አነጋጋሪ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍23🕊7🎉32👏1
የተባበሩት አረብ #ኤምሬትስ የሚሰነዘሩባትን ጥቃቶች ለማስቆም #ለኢራን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር መክፈሏ ተዘገበ

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢራን የሚሰነዘሩባት ጥቃቶች እንዲቆሙላት ለቴህራን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር መክፈሏን ሮይተርስ ዘገበ።ኤምሬትስ እስካሁን 3 ቢሊዮን ዶላር ለኢራን የከፈለች ሲሆን የስምምነቱ ጠቅላላ መጠን እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ሲሉ ሁለት የቀጠናው የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ሌሎች ሁለት ምንጮች ደግሞ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ኤምሬትስ ለኢራን የምትከፍለው ጠቅላላ ገንዘብ 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል።

ክስተቱ አቡ ዳቢ እጅግ አስገራሚ በሆነ መልኩ የአቋም ለውጥ ማድረጓን የሚያሳይ ሲሆን፥ ኢራንም ከጦርነቱ ይበልጥ ጠንክራ መውጣቷን የሚያመላክት ሆኗል ሲል ዘገባው አመላክቷል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በጦርነቱ ወቅት በኢራን ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ ጥቃቶችን በመሰንዘር ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጎን ተሰልፋ የነበረች ሲሆን፥ በተጨማሪም ግጭቱን ለማስቆም ፓኪስታን የምታደርገውን የሽምግልና ጥረት እንድታቆም ሞክራ ነበር።
ሳዑዲ ዓረቢያ ለኢስላማባድ አዲስ ብድር ለመስጠት የተገደደችውም፥ ኤምሬትስ ፓኪስታን የውይይት መድረክ በማዘጋጀቷ እንደ ቅጣት በመቁጠር ያለባትን ዕዳ በአስቸኳይ እንድትከፍል መጠየቋን ተከትሎ ነው።

ባለፈው ሳምንት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሀገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና የአቡ ዳቢ ምክትል ገዥ ከሆኑት ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ለሚደረግ ስብሰባ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አባላትን ተቀብላለች። በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው እነዚህ የአብዮታዊ ዘብ ባለሥልጣናት ያረፉትም በታህኑን የክብር እንግዶች ማረፊያ ቤት ውስጥ ነበር።

ብሉምበርግ በዚህ ሳምንት እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ፥ ኤምሬትስ ውጥረቶችን ለማርገብ ከከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት ጋር ፊት ለፊት የሚደረጉ ውይይቶችን ለማካሄድ ዲፕሎማቶቿን ልካለች።

አንድ የባሕረ ሰላጤው ዲፕሎማት ለኤምኢኢ (MEE) እንደተናገሩት፥ መንግሥታቸው ይህ ስብሰባ የተካሄደው በቴህራን ውስጥ እንደሆነ የሚያምን ሲሆን ይህም ኤምሬትስ ጥቃት እንዳይሰነዘርባት ለማድረግ የተከናወነ ጥረት አካል ነው ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍5🙈4🤣1👀1🙊1
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገበ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢566🤯5💔4👍3😱2👏1🙏1🕊1
በአሰላ ከተማ በሽንኩርት እና ቲማቲም ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡን ሸማቾች ተናገሩ
 
በአሰላ ከተማ የምግብ ፍጆታ የሆኑት የሽንኩርት እና የቲማቲም ዋጋ በአጭር ቀናት ውስጥ ከፍተኛ  የሆነ ጭማሪ ማሳየቱን ነዋሪዎች ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በአሰላ ከተማ ከሳምንት በፊት 120 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ሽንኩርት በአሁኑ ሰዓት እስከ 200 ብር እየተሸጠ  ይገኛል።በተመሳሳይ የቲማቲም ዋጋ ከ110 ብር ወደ 150 ብር ከፍ ብሏል።
 
ይህ ድንገተኛ የዋጋ ንረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን መካከለኛ ገቢ ያለቸውን ጭምር  የኑሮ ጫና ውስጥ የከተተ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል።በተጨማሪም በከተማው በጤፍ ዋጋ ላይ ሳይቀር  ጭማሪ መታየቱን ነዋሪዎች ገልጸውልናል።ይህ በሽንኩርትና በሌሎች መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በአሰላ ከተማ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማም በተመሳሳይ ሁኔታ እየተስተዋለ ይገኛል።
 
 በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ባደረግነው የገበያ ምልከታ በአሁኑ ወቅት አንድ ኪሎ ሽንኩርት 180 ብር ድረስ ይሸጣል ። እንዲህ ላለው ድንገተኛ የዋጋ ጭማሪ እና የገበያ መዛባት ዋነኛ መንስኤዎችን ለማወቅ ብስራት ሬዲዮ በአሰላ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎችን አነጋግሯል።ችግሩ የመነጨው ከትራንስፖርት እጥረት እና ከጸጥታ ችግር  ጋር በተያያዘ መሆኑን የገለፁት ነጋዴዎቹ በተለይም የነዳጅ አቅርቦት እጥረት መኖር  የንግድ እንቅስቃሴው እንዲገታ አድርጎታል ብለዋል ።
 
በአካባቢው ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ መገታት ተከትሎ  ምርት በወቅቱና በበቂ ሁኔታ ወደ ገበያ እንዳይደርስ  አሉታዊ ጫና ማሳደሩን ነጋዴዎቹ  አብራርተዋል።እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተዳምረው በከተማው ያለው የእለት ተእለት የምግብ ፍጆታ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርገውታል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍5😢4😁3🤪1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
4👍2
ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ሱዳን በሚሄዱ የህወሓት አርሚ 13 ታጣቂዎች ላይ ሽራሮ አካባቢ የኢትዮጵያ አየር ሃይል በድሮን ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ህወሓት ኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ተሳቢ መኪኖችን ወደ መሃል ሀገር እያንቀሳቀሰ መሆኑን ኮንፍሊክት ዞን ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ። ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ በነበረ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል። አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ነው። ዛሬ ሰኔ 08/10/18ዓ.ም ማለዳ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ አውቶቡስ…
የሟቾች ቁጥር 31 ደረሰ🕯🕯

በተከሰተው የመኪና አደጋ የሟቾች ቁጥር 31 መድረሱን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ዛሬ ጠዋት በደሴ እና  ኮምቦልቻ መካከል ሐረጎ በተባለ ሥፍራ በደረሰ የመኪና አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን መዘገባችን ይታወሰል።

አሁን ደግሞ  የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ፖሊስ አስታውቋል። የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ እንደገለጸው  በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች 31 ደርሷል።

አደጋው የደረሰው በተለምዶ ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ በሚወስደው ሐረጎ "S" መንገድ መታጠፊያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከንጋቱ 12:00 መኾኑን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው ሙህዬ ተናግረዋል።

ተሽከርካሪው ከ100 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ገደል ውስጥ በመግባቱ ሹፌሩን ጨምሮ የ31 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ33 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንም ኮማንደር ጌታቸው ለአሚኮ ገልጸዋል። 

ተሽከርካሪው 64 ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እንደነበር ያነሱት ኮማንደር ጌታቸው ተጎጅዎች በደሴ እና በኮምቦልቻ ሆስፒታሎች  ሕክምና እየተደረገላቸው እንደኾነም  አንስተዋል።

የአደጋው  መንስኤም  እየተጣራ መኾኑን አስታውቀዋል።

ለተጎጅ ቤተሰቦችም መጽናናትን እንመኛለን።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔22😢149👍2🙏1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
 
ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00

👉መድሓኒዓለም ቤ/ክ ፣ ኤድናሞል ፣ ሸገር ህንፃ ፣ ፍሬንድሺፕ ሆቴል ፣ ዳውንታውን ሆቴል፣ አውራሪስ ሆቴል፣ አዲሱ ስታዲየም፣ ካልዲስ ቡና፣ ኢምፔሪያል እና አካባቢው፣
22 ቃል ገስት ሀውስ ጎላጎል ኤጂ ግሬስ ኤምፔሪያል አትላስ ሆቴል እና አካባቢው፣
 
👉ከጎፋ ገብርኤል ከፍ ብሎ ቀበሌ 43 መዝናኛ አጠገብ ፣ አልማዝዬ ሜዳ፣ ሶፍያ ሞል አካባቢ፣ ሐመልማል ቤት፣ ቄራ በረት፣ ጎፋ ፖሊስ፣ ጎፋ ገብርኤል እና አካባቢው፣

👉ቡልቡላ ማሪያም፣ ኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ ፣ ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ ዋልያ ቢራ እና አካባቢው፣
 
ከጠዋቱ 2፡00 – 9፡30

👉 ገፋ ኮንዶሚኒየም፣ ጀርመን አደባባይ፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ትግሬ ሰፈር፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ ጀርባ ወይራ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢው፣                                                                                                                            👉አቡነ እጨጌ ቤተክርስትያን፣ ጦር ኃሎች ሆስፒታል፣ መኮንኖች ክበብ፣ ገዳመ ኢየሱስ፣ አውጉስታ እና አካባቢው፣


ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡30

👉ዳውንታውን ሆቴል፣ አውራሪስ ሆቴል፣ አዲሱ ስታዲየም፣ ካልዲስ ቡና፣ መድሓኒዓለም ቤ/ክ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 4፡00 – 11፡00

👉በላይነህ ክንዴ፣ በስተቀኝ ያሉ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ፣ ካፍ ማደያ እና አካባቢው፣
 
ከጠዋቱ 4፡00 – 10፡30

👉አየር ጤና፣ ሳሚ ካፈ ፣ ታቦት ማደሪያ፣ መሐንዲስ ሰፈር፣ ቴሌ፣ ኤሞሌስ ፋብሪካ፣ ካሰዴ፣ ጣፎ፣ 44 ማዞሪያ ፣ ሰንዳፋ ጫፍ፣ ቦሌ ሁላሳ ፣ ሰበታ፣ ዓለም ገና፣ ዋን ውሃ ፣ አባሃዋ ትሬዲንግ እና አካባቢው፣
 
 
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን ሲል ገልጿል ፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😡3👍2🎉2
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
7👍4🕊1
የአማራ ወጣቶች እንዲታገሉ አቶ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ‼️
የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ ለአማራ ወጣቶች የትግል ጥሪ አቀረቡ፡፡ ‹‹አመራሮቹን ሄዳችሁ ታገሏቸው›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አረጋ ይህን ያሉት “ባህር ዳርን ወደ ላቀ ከፍታ ለመውሰድ የወጣቶች ሚና የማይተካ ነው” በሚሉ መሪ ቃላት  ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቾት አልባ የሚያደርገው የአስተዳደር ብልሽት መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ አመራሩ በቀላሉ የሚገኝ፣ ቀላልና ውሳኔ መስጠት የሚችል መሆን እንዳለበት አጽንኦት የሰጡ ሲሆን በተለይም በሕዝብና በሀገር ላይ የሚፈጸሙ የሌብነት ድርጊቶችን ወጣቱ በግንባር ቀደምትነት ሊታገላቸው ይገባል ብለዋል።

“ሌብነት ውስጥ የመሬት ስርቆት፣ የግብር ስርቆት፣ የኮንትራት ስርቆት ውስጥ የሚገባ፣ ግን መስረቅ ሳያንስ የሚመራውን ደሃ ሕዝብ የጎሪጥ የሚያይ አመራር ላይ በጽናት መታገል ያስፈልጋል።” ሲሉ የባህር ዳር ወጣቶች በተሰበሰቡበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24😁20🤪8👍7🤯2🥰1👏1🤔1👌1
አሜሪካ ለኢራን‼️😯
25 ቢሊዮን ዶላር ጦርነት ላቆመችበት ይሰጣታል።
300 ቢሊዮን ዶላር በጦርነቱ ለወደመባት መልሶ ግንባታ እንደሚሰጣት የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ቫንስ አረጋግጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪48👍2119🙉9👏3👀2😎2😁1👌1🤝1
ብሔራዊ ባንክ በቴክኒክ ችግር ተሰርዞ የነበረውን የ100 ሚሊዮን ዶላር ልዩ ጨረታ ነገ በድጋሚ ያካሂዳል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባልታሰቡ የቴክኒክ ችግሮች ምክንያት መሰረዙን ያስታወቀውን ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ ነገ ማክሰኞ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በድጋሚ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ባንኩ ይፋ ባደረገው አዲስ መርሃ-ግብር መሠረት፣ ለዚህ ጨረታ የቀረበው የገንዘብ መጠን 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው የሀገሪቱ የንግድ ባንኮች በተቀመጠው ዝርዝር መመሪያ መሠረት ዝግጅት በማድረግ በጨረታው ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍2
የበጀት ቁጥሮች!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍8😁7👀51🙊1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትናንት ምሽት #የአሜሪካ B-52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላን ከካሊፎርኒያ #ኤድዋርድስ ማዘዣ ጣቢያ ከተነሳ በኃላ ብዙም ሳይቆይ በመከስከሱ የ8 ሰዎች ህይወት ልያልፍ ችሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍8😢7🤪3😎2🤣1💔1🙈1