አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ውል ላይ ደረሰ

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ሰነድ መጽደቁን በሂደቱ ላይ ቁልፍ አስታራቂ የሆኑት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ አስታውቀዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት ለማቆም እና ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ ድጋሚ ለመክፈት ያለመውን ይህንን ስምምነት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሰላም እንደ አሁኑ ቀርቦ አያውቅም” ብለዋል።

ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚነዙ የሀሰት መረጃዎችን ወደ ጎን በመተው ፓኪስታን ቀጣይ እርምጃዎችን ለማጠናቀቅ ከሁለቱም ወገኖች ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጊቺም በበኩላቸው የጦርነቱ ማክተሚያ መቃረቡን አረጋግጠዋል።

ከሁለቱም ወገኖች ተስፋ ሰጪ መግለጫዎች ቢሰሙም፣ በአደባባይ ያላቸው የድርድር አቋም አሁንም የተራራቀ መሆኑ ይስተዋላል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን መገናኛ ብዙኃን የተናፈሰው የስምምነቱ ይዘት ከእውነታው የራቀ ነው ያሉ ሲሆን፣ ኢራናውያንን “በቅንነት ለመደራደር የማይመቹ” ሲሉ ተችተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍2🎉1
ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ላለማምረት ከአሜሪካ ጋር ከስምምነት ላይ ደረሰች!

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በደረሰችው የረቂቅ ስምምነት መሠረት የኑክሌር መሣሪያዎችን ላለማምረትም ኾነ ላለመታጠቅ መስማማቷን አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ገልጸዋል።

ቴህራን በረቂቅ የመግባቢያ ሰነዱ ላይ ባስቀመጠችው ስምምነት ማንኛውንም ዓይነት የኑክሌር መሣሪያ ከማምረት እና ከማግኘት ሙሉ በሙሉ ትቆጠባለች።።

ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ይኸው ከአሜሪካ ጋር የተደረገው የረቂቅ ስምምነት ሂደት መቋጫ ማግኘቱን ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

@Addis_reporter
@Addis_reporter
😁1716👍6
ኢራን ለእስራኤል ምላሽ ልሰጥ ነው‼️
እስራኤል በዛሬው ዕለት በቤሩት ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ ኢራን ምላሽ ለመስጠት እየተዘጋጀች መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ወኪል የሆነው ታስኒም ኒውስ ዘግቧል።

እስራኤል በቤሩት ላይ የፈፀመችው ጥቃት ትክክል አለመሆኑን ትራምፕ ገልፀዋል።

አሜሪካ እና ኢራን በሚቀጥሉት 2-3 ሰዓታት ውስጥ የስምምነት ፊርማ እንደሚያደርጉ ትራምፕ ቢገልፁም ኢራን ዛሬ የሚፈፀም ስምምነት የለም ብላለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍10😁1
የሜታ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ በቅርቡ በተከሰተው የሶፍትዌር መቋረጥ ዙሪያ የኩባንያውን ስህተት አመነ

​ማርክ ዙከርበርግ ለሠራተኞቹ ባስተላለፈው ውስጣዊ መልዕክት፣ ኩባንያው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ ላይ ባደረገው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይና የሠራተኞች መዋቅር ለውጥ ምክንያት ስህተቶች መፈጠራቸውን ገልጿል።

ሜታ ከኦፕንኤአይ እና ማይክሮሶፍት ጋር ለመወዳደር ቢሊዮን ዶላሮችን እያፈሰሰ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍5
ሶማሊያ ለቱርክ 3 የነዳጅ እና ጋዝ ፍለጋ ቀጠናዎችን ፈቀደች፤ ተጨማሪ ለመስጠትም ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ሀገራቸው ካሏት 12 የባህር ላይ የሃይድሮካርቦን (የነዳጅ እና ጋዝ) ፍለጋ ቀጠናዎች መካከል ሶስቱን ለቱርክ መስጠታቸውን አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ይህ አጋርነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ተጨባጭ እና ቀጣይነት ያለው የደህንነትና የልማት ድጋፍ የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል።

ቀሪዎቹ ዘጠኝ ብሎኮች ለምዕራባውያን ኩባንያዎች የተሰጡ ቢሆንም፣ አንደኛው ኩባንያ የኢንቨስትመንት አቅም ማነስን በመጥቀስ ሰባቱን ብሎኮች በቅርቡ መልሶ ማስረከቡ ተገልጿል። ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በሀገሪቱ ከሚገኝ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ቱርክ ካስፈለጋት በቀጣይም ከተሰጧት ሶስት ቀጠናዎችን በተጨማሪ ሌሎችንም ለመስጠት ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ከበርካታ አስርት ዓመታት ግጭት በኋላ ወደ መረጋጋት በተወሰነ ደረጃ እየተመለሰች የምትገኘው ሶማሊያ፣ የሃይድሮካርቦን ፍለጋ መርሃ ግብሯ ለኢኮኖሚ እድገቷ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ እንዳለው አምናበታለች። የሀገሪቱ የባህር ክልል ከፍተኛ ያልተነካ የነዳጅና ጋዝ ክምችት እንዳለው ቢገመትም፣ በንግድ ደረጃ ማውጣት ግን የረጅም ጊዜ እቅድ መሆኑ ተመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍7
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ከ40 ዓመታት በኋላ የነዳጅ ምርት ማጓጓዝ ጀመረ

​የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት (ኢባትሎ) ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን የነዳጅ ምርት የማጓጓዝ ሥራ ከ40 ዓመታት በኋላ በድጋሚ መጀመሩን አስታወቀ። ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከናይጄሪያ የተገዛን የኤቪዬሽን (የአውሮፕላን) እና የናፍጣ ነዳጅ በቻርተር መርከቦች ማጓጓዝ ችሏል።

​በሆርሙዝ ባህር ሰርጥ አካባቢ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በተፈጠረው የትራንስፖርት መስተጓጎል እና በሀገር ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት የነዳጅ ግዢ ምንጮቹን እያሰፋ ይገኛል።

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለበትን ከፍተኛ የአውሮፕላን ነዳጅ ፍላጎት ለማሟላትና አማራጭ መስመሮችን ለመጠቀም ከናይጄሪያው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ግዢ ተፈጽሟል።

​ኢባትሎ እንዳስታወቀው ተቋሙ መንግሥት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን እና የናፍጣ ነዳጅ በሦስት ተከታታይ ጉዞዎች ወደ ጅቡቲው ሆራይዘን ተርሚናል ማጓጓዝ ችሏል። ይህ ስኬት ነዳጅ የማጓጓዝ ልምድ ላልነበረውና "አቅም የለውም" ተብሎ ለሚታሰበው የሎጂስቲክስ ተቋም ትልቅ የሥራ ክንውን መሆኑን አስምሮበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4🥱3🤪3👏2
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የበኩር ልጆች ወይም የመጀመሪያ ልጆች ከፍ ያለ I.Q አላቸው ከታናናሽ ወንድም እና እህቶቻቸዉ በተሻለ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
29👍6🤝4😢3👌3👏1💯1🤷1
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ በነበረ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ነው።

ዛሬ ሰኔ 08/10/18ዓ.ም ማለዳ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ አውቶቡስ በተለምዶ ሐረጎ እየተባለ በሚጠራው መንገድ ላይ በደረሠበት አደጋ እስካሁን የ28 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባተቸዋል።

የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በግምት100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል ገብቶ ነው አደጋው የደረሠው።
በሕይወት የተረፉትን ወደ ሕክምና ቦታ ለማድረስ አሁንም ርብርብ እየተደረገ መኾኑን የገለጸው ፓሊስ የአደጋውን ምክንያት በመጣራት ላይ ነው ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢32💔267👍2🙏1🥱1
በመጨረሻም ተስማሙ‼️
አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ከስምምነቱ ደረሱ።
በመጪው አርብ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ ሊፈራረሙ ቀጠሮ ይዘዋል።
ይህን ተከትሎ ሆርሙዝ ክፈት መደረጉን፣ በኢራን ላይ የተጣለው የባህር ላይ እገዳ መነሳቱን ትራምፕ አስታውቀዋል።
ኢራንም ስምምነቱን መቀበሏን የገለፀች ሲሆን ሊባኖስን ጨምሮ ጦርነቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም ተስማምቻለሁ ብላለች። ይህ የትራምፕ ስምምነት እስራኤልን ከጨዋታው ውጪ ማድረጉ አነጋጋሪ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍23🕊7🎉32👏1
የተባበሩት አረብ #ኤምሬትስ የሚሰነዘሩባትን ጥቃቶች ለማስቆም #ለኢራን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር መክፈሏ ተዘገበ

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢራን የሚሰነዘሩባት ጥቃቶች እንዲቆሙላት ለቴህራን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር መክፈሏን ሮይተርስ ዘገበ።ኤምሬትስ እስካሁን 3 ቢሊዮን ዶላር ለኢራን የከፈለች ሲሆን የስምምነቱ ጠቅላላ መጠን እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ሲሉ ሁለት የቀጠናው የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ሌሎች ሁለት ምንጮች ደግሞ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ኤምሬትስ ለኢራን የምትከፍለው ጠቅላላ ገንዘብ 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል።

ክስተቱ አቡ ዳቢ እጅግ አስገራሚ በሆነ መልኩ የአቋም ለውጥ ማድረጓን የሚያሳይ ሲሆን፥ ኢራንም ከጦርነቱ ይበልጥ ጠንክራ መውጣቷን የሚያመላክት ሆኗል ሲል ዘገባው አመላክቷል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በጦርነቱ ወቅት በኢራን ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ ጥቃቶችን በመሰንዘር ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጎን ተሰልፋ የነበረች ሲሆን፥ በተጨማሪም ግጭቱን ለማስቆም ፓኪስታን የምታደርገውን የሽምግልና ጥረት እንድታቆም ሞክራ ነበር።
ሳዑዲ ዓረቢያ ለኢስላማባድ አዲስ ብድር ለመስጠት የተገደደችውም፥ ኤምሬትስ ፓኪስታን የውይይት መድረክ በማዘጋጀቷ እንደ ቅጣት በመቁጠር ያለባትን ዕዳ በአስቸኳይ እንድትከፍል መጠየቋን ተከትሎ ነው።

ባለፈው ሳምንት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሀገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና የአቡ ዳቢ ምክትል ገዥ ከሆኑት ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ለሚደረግ ስብሰባ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አባላትን ተቀብላለች። በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው እነዚህ የአብዮታዊ ዘብ ባለሥልጣናት ያረፉትም በታህኑን የክብር እንግዶች ማረፊያ ቤት ውስጥ ነበር።

ብሉምበርግ በዚህ ሳምንት እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ፥ ኤምሬትስ ውጥረቶችን ለማርገብ ከከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት ጋር ፊት ለፊት የሚደረጉ ውይይቶችን ለማካሄድ ዲፕሎማቶቿን ልካለች።

አንድ የባሕረ ሰላጤው ዲፕሎማት ለኤምኢኢ (MEE) እንደተናገሩት፥ መንግሥታቸው ይህ ስብሰባ የተካሄደው በቴህራን ውስጥ እንደሆነ የሚያምን ሲሆን ይህም ኤምሬትስ ጥቃት እንዳይሰነዘርባት ለማድረግ የተከናወነ ጥረት አካል ነው ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍5🙈4🤣1👀1🙊1
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገበ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢566🤯5💔4👍3😱2👏1🙏1🕊1
በአሰላ ከተማ በሽንኩርት እና ቲማቲም ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡን ሸማቾች ተናገሩ
 
በአሰላ ከተማ የምግብ ፍጆታ የሆኑት የሽንኩርት እና የቲማቲም ዋጋ በአጭር ቀናት ውስጥ ከፍተኛ  የሆነ ጭማሪ ማሳየቱን ነዋሪዎች ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በአሰላ ከተማ ከሳምንት በፊት 120 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ሽንኩርት በአሁኑ ሰዓት እስከ 200 ብር እየተሸጠ  ይገኛል።በተመሳሳይ የቲማቲም ዋጋ ከ110 ብር ወደ 150 ብር ከፍ ብሏል።
 
ይህ ድንገተኛ የዋጋ ንረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን መካከለኛ ገቢ ያለቸውን ጭምር  የኑሮ ጫና ውስጥ የከተተ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል።በተጨማሪም በከተማው በጤፍ ዋጋ ላይ ሳይቀር  ጭማሪ መታየቱን ነዋሪዎች ገልጸውልናል።ይህ በሽንኩርትና በሌሎች መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በአሰላ ከተማ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማም በተመሳሳይ ሁኔታ እየተስተዋለ ይገኛል።
 
 በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ባደረግነው የገበያ ምልከታ በአሁኑ ወቅት አንድ ኪሎ ሽንኩርት 180 ብር ድረስ ይሸጣል ። እንዲህ ላለው ድንገተኛ የዋጋ ጭማሪ እና የገበያ መዛባት ዋነኛ መንስኤዎችን ለማወቅ ብስራት ሬዲዮ በአሰላ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎችን አነጋግሯል።ችግሩ የመነጨው ከትራንስፖርት እጥረት እና ከጸጥታ ችግር  ጋር በተያያዘ መሆኑን የገለፁት ነጋዴዎቹ በተለይም የነዳጅ አቅርቦት እጥረት መኖር  የንግድ እንቅስቃሴው እንዲገታ አድርጎታል ብለዋል ።
 
በአካባቢው ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ መገታት ተከትሎ  ምርት በወቅቱና በበቂ ሁኔታ ወደ ገበያ እንዳይደርስ  አሉታዊ ጫና ማሳደሩን ነጋዴዎቹ  አብራርተዋል።እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተዳምረው በከተማው ያለው የእለት ተእለት የምግብ ፍጆታ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርገውታል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍5😢4😁3🤪1