አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
እገታ ተፈፀመ‼️
በዛሬው ዕለት ሰኔ 6/2018 ዓ.ም  ጠዋት በምስራቅ አርሲ ከአቦምሳ ከተማ ወደ አስኮ እየመጣ ያለ አንድ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ ሙሉ ተሳፋሪዎችን ከቀኑ 6:00 ላይ ባለፈው ጥቃት የፈፀሙት የሸኔ ታጣቂዎች እግተዉ ይዘው መሄዳቸውን የአካባቢው የአይን እማኞች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

እገታው የተፈፀመው ከከተማው ጥቂት ኪሎሜትር እርቀት ላይ ሲሆን የፀጥታ ሀይሎች እዛው አከባቢ ነበሩ ብለዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በዚህ አካባቢ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት መፈፀሙ የሚታወስ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔52😢2310😡8🤯3🕊3👍2
ከነዳጅ 235 ቢሊየን ብር ታክስ ለመሰብሰብ ታቅዷል

በ 2019 በጀት አመት መንግስት ቀጠኛ ያልሆነ ታክስ ከነዳጅ ለመሰብበስ ነው ያቀደው።

👉109.6 ቢሊየን ብር ከኤክሳይስ ታክስ

👉126 ቢሊየን ብር ቫት ለመሰብሰብ ነው የታቀደው

👉ይህም በጥቅሉ ወደ ሩብ  ትሪሊየን ብር የሚጠጋ ነው

👉ይህም ለመሰብሰብ ከታሰበው ጠቅላላ 1.5 ትሪሊየን ብር ወደ 15.7 በመቶ የሚጠጋ ነው።

ከዘርፉ ቀጥተኛ  ያልሆነ ግብር ከ2018 አንስቶ ለመሰብሰብ መታቀዱ የሚታወስ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢17😁149👍7🤯1👀1🤪1🙊1
ሰበር-መረጃ‼️
የኢራን ሰላም ስምምነት ነገ ይፈረማል - ትራምፕ።

ስምምነቱ እንደተፈረመ የሆርሙዝ ስርጥ ወዲያውኒ ሙሉ ለሙሉ ይከፈታል ብለዋል።

ነገሮች ሲረጋጉ አሜሪካ ወደ ኢራን ገብታ ለኑክሌር የበለፀገውን የዩራኒየም አቧራ እንወስዳለን ብለዋል።

ከኢራን ጋር አሁን ላይ የተሻለ ግንኙነት አለን ያሉ ሲሆን ከመሬት በታች ምሽግ ደርማሽ ቦንብ በመጣል የሚታወቀውን የአሜሪካ B-2 የጦር አውሮፕላን አመስግነዋል።

ነገ የኢራን እና የአሜሪካ አመራሮች በመይነመረብ ስብሰባ ያደርጋሉ፣ፊርማው ኤሌክትሮኒካሊ ይፈረማል።

ኢራን አልስማማም ካለች ይህን እድል መቼም እንደማታገኘው አስጠንቅቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1813🤣10🙏4👏2🤔1👌1👀1🤪1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦

ከጠዋቱ 2፡00 – 8፡30

👉አፍንጮ በር መስጊድ፣ ደጃች ውቤ፣ ጊዮርጊስ እሳት አደጋ፣ ችሎት አደባባይ፣ ዘበኛ ሰፈር፣ ሾላ፣ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ሰሜን ሆቴል ጫፍ፣ ቀለመወርቅ ት/ቤት፣ ዶሮ ተራ፣ ራስ ደስታ አካባቢ፣ አርበኞች ት/ቤት፣ ዕንቁላል ፋብሪካ አደባባይ እና አካባቢቸው፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 9፡30

👉ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም፣ ጀርመን አደባባይ፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ትግሬ ሰፈር፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ ጀርባ እና አካባቢቸው፣

👉ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ ጫፍ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴል፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ እና አካባቢቸው፣

ከጠዋቱ 3፡00 – 9፡30

👉ድሬ ከአስፋልት በታች፣ ጉዳ፣ ኬላ፣ ጉዮ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር በከፊል፣ ቶልቻ፣ ሰንጎታ፣ ገፋርሳ ሰብስቴሽን እና አካባቢቸው፣ 

ከጠዋቱ 3፡00 – 9፡30

👉በአዳማ አዳማ ሆስፒታል፣ ፖስታ ቤት አካባቢ፣ ሁሩታ ከተማ፣ ሰኞ ገብያ እና አካባቢያቸው ፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡30

👉በመቋሌ ኢትዮ-ሸዊት ብረት ስራ እና አካባቢዎቻው የኃይል አቅርቦት ይቋረጠል፡፡


ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍2
ኔታንያሁ የአሜሪካ ባለስልጣናት ስጋት‼️
አሜሪካ ከኢራን ጋር ስምምነት ከተፈራረመች የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ስምምነቱን ሊያፈርስብን ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንደገባቸው የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ አክሲዎስ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍7🥰2🙊2👏1
በሚገኙበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ያልተሰጣቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራን ስም ዝርዝርን እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉንም የመንግሥት ዩኒቨርሲዎች ጠይቋል።

በቀን 04/10/2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ኮራ ጡሹ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲዎች የተጻፈ ደብዳቤ፣ ከሰኔ 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የመምህራኑ ዝርዝር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲላክ አዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍5🥰1👏1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥ ጀነራል ምግበይ ከሰሞኑ በድንበር አካባቢዎች የተፈጸሙት የድሮን ጥቃቶች የትግራይን የመከላከል አቅም ለማዳከም የታለሙ ቢሆንም ዓላማቸው ግን ሳይሳካ ቀርቷል ሲሉ ተናገሩ።

ጀነራል ምግበይ በሽራሮ ከተማ ባደረጉት ንግግር፣ በቅርቡ በተሰነዘሩት የድሮን ጥቃቶች ሳቢያ የሰራዊት አባላት መስዋዕትነት መክፈላቸውን አረጋግጠዋል።

"መስዋዕትነት እየከፈልን ያለነው ለታላቅ ዓላማ ነው" ያሉት ጀነራሉ፣ ጥቃቱ በትግራይ ህዝብና ሰራዊት መካከል ያለውን አንድነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ጀነራል ምግበይ በንግግራቸው በአሁኑ ወቅት ወሳኝ በሆነ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ሲሉ ጠቁመው "ያለን ምርጫ ገመዱን በጥሰን መውጣት አልያም በዚያው ገመድ ታንቀን በድንግርግር ውስጥ መኖር ነው። ይሄ ደግሞ ምርጫችን አይደለም።” ብለዋል።

ይህ ንግግራቸውም አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥ እስከ መጨረሻው መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን የሚያመላክት እንደሆነ ተተርጉሟል።

የመከላከል አቅም አለን ጠላቶቻችንም እናሸንፋለን ሲሉ የገለጹት ጀነራሉ ሰራዊቱ ግንባር ላይ እየተዋደቀ፣ አመራሩ እየመራ፣ ህዝቡ ደግሞ ደጀን ሆኖ በጋራ በመቆም ድልን እንቀናጃለን ሲሉም ተናግረዋል።

ይህ ንግግራቸውም አካባቢው ወደ ወታደራዊ ግጭት እያመራ መሆኑን የሚያመላክት ጠንካራ መልዕክት አዘል እንደሆነ ተመልክቷል።

ይህ የጀነራል ምግበይ ወታደራዊ ዝግጁነትን የሚያንፀባርቅ ንግግር የተሰማው፣ በፌደራል መንግስቱና በህወሃት መካከል እየታየ ያለውን ውጥረት ለማርገብ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ መሆኑ ጉዳዩን ልዩ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል። የፌደራል መንግስቱ እስካሁን በትግራይ ስላለው የጸጥታ ሁኔታም ሆነ ስለ ድሮን ጥቃቱ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም

Via : times mereja

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁138👍8😢2🤪2👏1🕊1😎1
ኒጀር ግብረ-ሰዶማዊነትን በህግ ከከለከሉ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ተቀላቅላለች ። 

የኒጀር ወታደራዊ  ሁንታ  ግብረ-ሰዶማዊነትን በወንጀል የሚቀጣ አዲስ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ማውጣቱን አስታወቀ።

ከሀገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አዲሱ ህግ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ጀምሮ ገቢራዊ ተደርጓል። 

ስራ ላይ የዋለው አዲሱ ህግ  ግብረ-ሰዶማዊነትን ወይም መሰል ድርጊቶችን የፈጸመ ወይም ለመፈጸም የሞከረ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስራት እና በገንዘብ ይቀጣል።

ቅጣቱ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸውን ሰዎች ጋብቻ ያስፈጸሙ ሰዎችን፣ ምስክሮችን፣ ጋብቻው እንዲፈጸም ፍቃድ የሰጡትን እንዲሁም የሰርጉን አዘጋጆች በሙሉ ያጠቃልላል ነው የተባለው።

ከዚህ ቀደም በኒጀር ግብረ-ሰዶማዊነት በህግ የተከለከለ ባይሆንም፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ማግለል ይደርስበት ነበር።

ኒጀር ይህንን እርምጃ በመውሰድ ግብረ-ሰዶማዊነትን በህግ ከከለከሉ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ተቀላቅላለች። 

ግብረሰዶማዊነት በሴኔጋል፣ ኬንያ፣ ሴራሊዮን እና ታንዛኒያ እስከ 10 ዓመት እና ከዚያ በላይ በሆነ እስራት ያስቀጣል።

በሶማሊያ፣ ዩጋንዳ እና ሞሪታኒያ ደግሞ የወንጀሉ ቅጣት እስከ ሞት ፍርድ ሊደርስ እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2418👏4🎉1👌1💯1🤝1🆒1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍3
የምግብ ዋጋ 14.6 በመቶ ጨመረ

የግንቦት ወር 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ደግሞ 13.4 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።

የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.6 በመቶ የጨመረ ሲሆን በዋናነት አትክልት፣ ስጋ ፣ የወተት ተዋፅኦዎች፣ እንቁላል፣ ፍራፍሬ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመጨመራቸው የተመዘገበ ነው።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 11.1 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንሰፖርት (12.1 በመቶ)፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ (14.6 በመቶ)፣ በኮሙዩኒኬሽን (9.1 በመቶ) ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች (10.5 በመቶ) እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች (17.9 በመቶ) ሆነው ተመዝግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢87👍2😱2👀1
ጥርስን እንደገና የሚያሳድገው መድሃኒት‼️
ሳይንቲስቶች የሰው ልጆች በተፈጥሮ የጠፉ ጥርሶችን እንደገና እንዲያሳድጉ የሚያስችል መድሃኒት ፈጠሩ‼️
በህክምና ምርምር ኢንስቲትዩት ኪታኖ ሆስፒታል በዶ/ር ካትሱ ታካሃሺ የሚመራው የጃፓን ተመራማሪዎች የጥርስን ተፈጥሯዊ እድገት የሚያነቃቃ ፈር ቀዳጅ የሆነ መድሃኒት ፈጥረዋል።

መድሃኒቱ የሚሠራው የጥርስን እድገት የሚከላከለውን ዩኤስኤግ-1 የተባለውን ፕሮቲን በመግታት ነው።

ይህ መድሃኒት በአይጦች ላይ ሙከራ ተደርጎ አዲስ-ጥርሶችን በተሳካ ሁኔታ በማሳደጉ የምርምር ቡድኑ አሁን ይህን ለውጥ የሚያመጣ ህክምና በአስር አመታት ውስጥ ወደ ገበያ ለማውጣት በሰዎች ላይ ክሊኒካዊ ሙከራዎችን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👏8👍2
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ውል ላይ ደረሰ

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ሰነድ መጽደቁን በሂደቱ ላይ ቁልፍ አስታራቂ የሆኑት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ አስታውቀዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት ለማቆም እና ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ ድጋሚ ለመክፈት ያለመውን ይህንን ስምምነት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሰላም እንደ አሁኑ ቀርቦ አያውቅም” ብለዋል።

ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚነዙ የሀሰት መረጃዎችን ወደ ጎን በመተው ፓኪስታን ቀጣይ እርምጃዎችን ለማጠናቀቅ ከሁለቱም ወገኖች ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጊቺም በበኩላቸው የጦርነቱ ማክተሚያ መቃረቡን አረጋግጠዋል።

ከሁለቱም ወገኖች ተስፋ ሰጪ መግለጫዎች ቢሰሙም፣ በአደባባይ ያላቸው የድርድር አቋም አሁንም የተራራቀ መሆኑ ይስተዋላል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን መገናኛ ብዙኃን የተናፈሰው የስምምነቱ ይዘት ከእውነታው የራቀ ነው ያሉ ሲሆን፣ ኢራናውያንን “በቅንነት ለመደራደር የማይመቹ” ሲሉ ተችተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍2🎉1
ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ላለማምረት ከአሜሪካ ጋር ከስምምነት ላይ ደረሰች!

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በደረሰችው የረቂቅ ስምምነት መሠረት የኑክሌር መሣሪያዎችን ላለማምረትም ኾነ ላለመታጠቅ መስማማቷን አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ገልጸዋል።

ቴህራን በረቂቅ የመግባቢያ ሰነዱ ላይ ባስቀመጠችው ስምምነት ማንኛውንም ዓይነት የኑክሌር መሣሪያ ከማምረት እና ከማግኘት ሙሉ በሙሉ ትቆጠባለች።።

ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ይኸው ከአሜሪካ ጋር የተደረገው የረቂቅ ስምምነት ሂደት መቋጫ ማግኘቱን ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

@Addis_reporter
@Addis_reporter
😁1716👍6
ኢራን ለእስራኤል ምላሽ ልሰጥ ነው‼️
እስራኤል በዛሬው ዕለት በቤሩት ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ ኢራን ምላሽ ለመስጠት እየተዘጋጀች መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ወኪል የሆነው ታስኒም ኒውስ ዘግቧል።

እስራኤል በቤሩት ላይ የፈፀመችው ጥቃት ትክክል አለመሆኑን ትራምፕ ገልፀዋል።

አሜሪካ እና ኢራን በሚቀጥሉት 2-3 ሰዓታት ውስጥ የስምምነት ፊርማ እንደሚያደርጉ ትራምፕ ቢገልፁም ኢራን ዛሬ የሚፈፀም ስምምነት የለም ብላለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍10😁1
የሜታ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ በቅርቡ በተከሰተው የሶፍትዌር መቋረጥ ዙሪያ የኩባንያውን ስህተት አመነ

​ማርክ ዙከርበርግ ለሠራተኞቹ ባስተላለፈው ውስጣዊ መልዕክት፣ ኩባንያው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ ላይ ባደረገው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይና የሠራተኞች መዋቅር ለውጥ ምክንያት ስህተቶች መፈጠራቸውን ገልጿል።

ሜታ ከኦፕንኤአይ እና ማይክሮሶፍት ጋር ለመወዳደር ቢሊዮን ዶላሮችን እያፈሰሰ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍5