አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
3👍2
በ2026 የዓለም ዋንጫ የቲኬት ዋጋ መናር ስታዲዮሞችን ብዙ ወንበሮች ክፍት ማድረጉ አነጋጋሪ ሆኗል

በሜክሲኮ ጓዳላሃራ ስታዲዮም በደቡብ ኮሪያ እና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል በተደረገው ሁለተኛው የምድብ ጨዋታ (ኮሪያ 2 ለ 1 አሸንፋለች) በርካታ ወንበሮች ባዶ ሆነው ታይተዋል።

ይህ ሁኔታ በመክፈቻው ጨዋታ በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ከታየው የ80 ሺህ ደጋፊዎች ድምቀት የተለየና ቀዝቃዛ ነበር።

​ለስታዲዮሙ መካከለኛ ወንበሮች መቅረት ዋነኛ ምክንያት የፊፋ እጅግ ውድ የቲኬት ዋጋ እንደሆነ እየተነገረ ነው።

በአሁኑ ወቅት በአማካይ የአንድ መደበኛ ወንበር ዋጋ 500 ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ከ180 ሺህ በላይ ቲኬቶች አሁንም በድጋሚ መሸጫ መድረኮች ላይ ሳይሸጡ ቀርተዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙዎች የስታዲዮሙን ባዶነት ተችተዋል።
​የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ግን ከውድድሩ በፊት በሰጡት መግለጫ የዋጋው መናር ችግር እንደማይሆን ተከላክለዋል። "የቲኬት ዋጋችን ተመጣጣኝ ነው፤ ዋጋው በባለሙያዎች የተጠና ነው" ብለዋል።

ይሁን እንጂ ውድድሩ ገና በጅምሩ ላይ እያለ የታየው ባዶ ወንበር ፊፋን ማሸበሩና የቲኬት ዋጋው ውሳኔ በራሱ ላይ መውደቁ አይቀሬ ይመስላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍9😱2
አከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ብቻ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ

የቢሮው ኃላፊ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እንደገለጹት፣ የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በተጀመረው የዲጂታል ምዝገባ እስካሁን 500 ሺህ የሚጠጉ ቤቶች ወደ ሲስተሙ ገብተዋል።

​ይህ አዲስ አሰራር ያለ አግባብና ያለ ምንም ምክንያታዊ መነሻ ይደረግ የነበረውን የዋጋ ጭማሪ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። መንግሥት በየዓመቱ የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የገበያ ጥናት ካካሄደ በኋላ፣ በየዓመቱ ሰኔ 30 ላይ በሚያወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት የዋጋ ጭማሪውን በፐርሰንት ይወስናል።

​የውል ጊዜው በማብቃቱ ብቻ ተከራይን አስወጥቶ ዋጋ ጨምሮ ማከራየት አይቻልም። በአሁኑ ወቅት እንግልትን ለማስቀረት የውል ማደስ ሥራውን በኦንላይን ለማከናወን ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ በየሁለት ዓመቱ የኪራይ ውልን ማደስ ግዴታ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍13🤪7👏3👀2
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ መንግሥት ላይ ያቀረቡትን ከባድ ክስ ተከትሎ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ሬድዋን በሕወሓት እና በኤርትራ መካከል አዲስ ትብብር መጀመሩን በመጥቀስ በአልጀዚራ በኩል በነበራቸው ቆይታ በፌዴራል መንግሥቱ ላይ አዲስ ጦርነት ሊከፈት ተዘጋጅተዋል ሲሉ ክስ አቅርበው ነበር። በአልጀዚራ ጽሑፍ ላይ አቶ ጌታቸው ረዳም ተካተው እንደነበር ይታወቃል።

ይህንን ክስ ተከትሎ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ምላሽ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ንግግር በሐሰት፣ በማታለልና በተሳሳተ መረጃ የተሞላ ሲሉ ያጣጣሉ ሲሆን ይልቁንም ሁለቱ ወገኖች ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወራት በፊት በጅቡቲ እና ሲሸልስ በሚስጥር ተገናኝተው በኤርትራ ላይ የጋራ ወረራ ለመፈጸም ሲመክሩ ነበር ብለዋል። ይህንንም አቶ ጌታቸው ረዳ ራሳቸው ቀደም ብለው ተናግረዋል ሲሉ እንደ ማስረጃ አቅርበዋል።

በመጨረሻም የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ለሚታየው አለመረጋጋት መንስኤው የኢትዮጵያ መንግሥት ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ እያራመደው ያለው የባሕር በር መሻት የከፈተው የጠብ አጫሪነት ንግግር ነው ያሉት አቶ የማነ አሁን የቀረበው ክስ ይሄንኑ “የራሳቸውን” የጦርነት አጀንዳ ለመሸፈን የታለመ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው ሲሉ ምላሻቸውን ደምድመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍5🤪3
መረጃ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ ቅድመ-ምረቃ በረራዎችን ከዛሬ ሰኔ 6 ጀምሮ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

አየር መንገዱ፣ ወደ ደብረ ማርቆስ መጓዝ የሚፈልጉ መንገደኞች የበረራ ቲኬቶችን በሁሉም የቲኬት መሸጫ ቢሮዎች ማግኘት እንደሚችሉ ዛሬ ባሠራጨው መረጃ ላይ ገልጧል።

ኾኖም አየር መንገዱ ወደ ደብረ ማርቆስ በሳምንት ስንት በረራዎችን ለማድረግ እንዳሰበ አልገለጠም።

አዲሱ የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ከሦስት ሳምንት በፊት አንድ የሙከራ በረራ ማስተናገዱ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍4👏1🎉1🙏1
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ አዳዲስ አካባቢዎችና የስደተኞች መጠለያ እየተስፋፋ ነው

አርብ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባወጣው መግለጫ፤ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በሰዎች ወደተጨናነቀ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ጭምር በመስፋፋት ይበልጥ አደገኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታውቋል።

ወረርሽኙ ከተከሰተበት ግንቦት 7 ቀን ጀምሮ በሀገሪቱ 676 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ የ136 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

«ቡንዲቡግዮ» በተባለውና እስካሁን ክትባትም ሆነ ሕክምና በሌለው የቫይረሱ ዝርያ ሳቢያ በኢቱሪ ግዛት በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።

በአካባቢው ያለው የቆየ የእርስ በርስ ግጭት፣ የሕዝቡ ከፍተኛ መፈናቀልና የንጽህና መሠረተ ልማት መውደም ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እጅግ ፈታኝ አድርጎታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍2😢1
ቤጂንግ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲወድሙ ጥሪ አቀረበች

በከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊ መግለጫ፣ ቻይና ለዓለም አቀፍ ሰላም መረጋገጥ እና ለሦስተኛው የዓለም ጦርነት መከላከል ብቸኛው መንገድ አጠቃላይ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ማስወገድ መሆኑን በይፋ አስታወቀች።

የቻይና ባለሥልጣናት እንደ አሜሪካ ያሉ ታላላቅ ኃያላን ሀገራት እና የእስራኤልን ተሳትፎ የሚያካትተው የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ተዋናዮች የኒውክሌር ዛቻዎችን በአስቸኳይ ማቆም እና ሙሉ በሙሉ ወደ ዲ-ኤስካሌሽን (ውጥረትን ወደ መቀነስ) ማምራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ቤጂንግ ይህንን ዓለም አቀፋዊ ለውጥ በይፋ ብታስተዋውቅም፣ ተቺዎች ቻይና እራሷ የራሷን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ክምችት በከፍተኛ ፍጥነት እያሳደገች መሆኑን በስፋት እየነቀፉ ይገኛሉ።

እ.ኤ.አ. በ2026 የዓለም አቀፍ የኒውክሌር ወጪ ከፍተኛ ታሪካዊ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት፣ የጦር መሣሪያዎችን ማስወገድ ተፈጻሚ ሊሆን የሚችል እውነተኛ ግብ ነው ወይስ ፈጽሞ የማይሳካ ምናባዊ ምኞት? የሚለው ክርክር ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በሁለት መከፈሉን ቀጥሏል።

በኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች ሙሉ በሙሉ መጥፋት የዓለም ሰላም ይረጋገጣል ብለው ያምናሉ ወይስ አሁን ያለው የጦር መሣሪያ እሽቅድምድም የማይቀር ነው?

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍11
አድዋ በአሜሪካ‼️
የአሜሪካዋ ግዛት ምክር ቤት ለአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሰየመ‼️
#በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት 2' በግዛቱ የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን እንዲሆን የቀረበን የውሳኔ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ አፀደቀ።

ይህ 'ኤችአር 441' የተሰኘው የውሳኔ ሐሳብ የፀደቀው ባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ነው።

በአሜሪካ የግዛቶች ምክር ቤት አሠራር መሠረት፣ ይህ ውሳኔ በግዛቲቱ የሕግ መዝገብ ላይ የአድዋ ድል በይፋ ዕውቅና ያገኘበት ታሪካዊ ሰነድ ሆኖ በቋሚነት ይቀመጣል።
ይህ የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ፣ የአውሮፓውያኑ 'ማርች 2 ቀን 2026' የ130ኛ 'የአድዋ ድል ቀን' ሆኖ በፔንሲልቬኒያ ግዛት ዕውቅና እንዲሰጠው የሚደነግግ ነው።

ውሳኔው በሪፐብሊካን እና በዲሞክራቲክ ፓርቲ እንደራሴዎች በተሰጠ 195 ከፍተኛ የድጋፍ ድምጽ እና በ6 ተቃውሞ ብቻ ነው የፀደቀው።

ረቂቁ የቀረበው ከወራት በፊት ቢሆንም የምክር ቤቱን የውስጥ አሠራሮችን አልፎ፣ ውይይቶች ተደርገውበት ከቆየ በኋላ የውሳኔ ድምጽ የተሰጠበት ግን ባለፈው ሳምንት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
45🤔9👍4🙏4
በአዲሱ በጀት ዓመት የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ይደረግ እንደሆነ በግልጽ እንዲታወቅ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ ዓመት 25ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የፌደራል መንግስትን የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

​ጥያቄያቸውን ለምክር ቤቱ ካቀረቡት አባላት መካከል የአብን (የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ) ፓርቲን ወክለው የምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ይገኙበታል።

​ዶክተር ደሳለኝ በጥያቄያቸው፤ መንግስት ለ2019 በጀት ዓመት ለመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ያደርጋል ወይ? የሚለው ጉዳይ በግልጽ እንዲታወቅ ጠይቀዋል።

​የምክር ቤት አባሉ ጥያቄውን ባቀረቡበት ወቅት ባለፈው ዓመት የታዘቡትን አጋጣሚ በማስታወስ፤ "ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጥያቄ ለምክር ቤቱ አቅርቤ 'የደመወዝ ጭማሪ የለም' የሚል ምላሽ ከተሰጠኝ ከአንድ ወር በኋላ ጭማሪ ተደርጓል" ብለዋል። በመቀጠልም "ዘንድሮስ ጭማሪ የለም ካሉኝ ከአንድ ወር በኋላ ጭማሪ ይኖራል ወይ?" ሲሉ በሚኒስትሩ አገላለጽ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ በፈገግታ የታጀበ ጥያቄ በማስከተል ሰንዝረዋል።

​ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፤ መንግስት ቀደም ሲል በሁለት ዙር የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

​ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በክልሎች በኩል በፐርሰንት ተሰርቶ የቀረበው የደመወዝ ጭማሪ ተመን እና ለጉዳዩ ከተመደበው በጀት ጋር ባለመመጣጠኑ ምክንያት፣ አሁንም ድረስ ተጨማሪ የማጥራትና የማስተካከል ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ለአባላቱ አስገንዝበዋል።

አቤል እስጢፋኖስ ethio fm 107.8


@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍7👏2
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍2
የቀድሞው የኢራን ከፍተኛ መሪ አሊ ኻመናይ የቀብር ሥነስርዓት ሐምሌ 2 ይፈፀማል።

በእስራኤል የአየር ጥቃት የተገደሉት የቀድሞው የኢራን ከፍተኛ መሪ አሊ ኻመናይ የቀብር ሥነስርዓት የፊታችን ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈጸም የሐገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።

የኢራን መንግስታዊ የመገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የአያቶላህ ኻመናይ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚፈጸመው በሰሜን ምስራቅ የሐገሪቱ ግዛት በምትገኘው የማሻህድ ከተማ ነው።

ባለፈው የካቲት ወር የተገደሉት ኻመናይ በብሔራዊ ደረጃ በሚደረገው የቀብር ሥነሥርዓት በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9🤔4👍3😁3😢1👀1🙈1
አስቸኳይ የፋብሪካ ስራ በፖላንድ

የቀን ሰራተኞችን ወደ ዱባይ በመላክ በተለያዩ የስራ መስኮች ሲያሰማራ የነበረው ኤጀንሲያችን አድማሱን በማስፋት በ ፓላንድ በተለያዩ ፋብሪካዎች ሰራተኞችን በብዛት እያስገባ ስለሚገኝ ተመዝግበው የእድሉ ተካፋይ እንዲሆኑ እናሳስባለን::


💼የስራ አይነት; የፋብሪካ ሰራተኛ

📎 መስፈርት፡ እድሜ 18+ ,ለሰአታት ቆሞ መስራት የሚችል ታታሪ ሰራተኛ
📎 ሙሉ ስልጠና ይሰጣል።

💰  አስደሳች ወርሃዊ ደመወዝ ከ ምግብ እና መኖሪያ ዶርም ጋር

📍 ቦታ፡ ፖላንድ በተለያዩ ፋብሪካዎች

ማሳሰቢያ
በዱባይ እየሰራችሁ የምትገኙ ሰራተኞች ኩንትራታችሁን ሳትጨርሱ ማመልከት አትችሉም!!

📥ታች ባለው ሊንክ አሁኑኑ ይመዝገቡ

https://forms.gle/q5SqQvNtFkKDDSeh7

Our Telegram channel
https://t.me/Tpa_spark

Spark® travel agency
10🙏10
#የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር እና በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና በማግኘት ማህበሩን የሚመሩ አስፈጻሚዎች በማስመረጥ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ ይገኛል።

በዚህ መሰረት ማህበሩ የመምህራንን መብት ለማስጠበቅ እና ከመምህራን የሚቀርቡ ጥያቄዎች በቅድሚያ ምላሽ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮችን በመለየት ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በቁጥር EUTA 0037/18 በቀን 14/09/2018 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ከቀረቡት ጉዳዮች ውስጥ የመምህራን የመኖሪያ ቤት አንዱና ዋነኛው ጉዳይ መሆኑን እየገለጽን ይህንን ችግር በቀጣይ መፍትሔ ለመስጠት እንዲቻል በዩኒቨርሲቲያችሁ ያሉ መምህራን በሚገኙበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ያልተሰጣቸው መምህራን ስም ዝርዝር ይህ ደብዳቤ ወጪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲላክ ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍2🥰1😁1🤪1
የውጭ ዜጎች በሪል ስቴትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ንብረት እንዲያፈሩ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ‼️

የኢትዮጵያና የአሜሪካ የጋራ ኤክስፖ በአሜሪካ ይካሄዳል ተብሏል

የውጭ ዜጎች በሪል ስቴትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ንብረት እንዲያፈሩ የሚያስችል ስምምነት፣ የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበርና ሃርቨስት ሰርክል ኢንክ ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በአሜሪካና በአፍሪካ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የሪል ስቴት ትስስር ለማጠናከር በሚሠራውና ዋና መሥሪያ ቤቱ አሜሪካ በሆነው ሃርቨስት ሰርክል ኢንክ (Harvest Circle Inc.) አማካይነት፣ በሪል ስቴትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ያተኮረ የንግድና የኢንቨስትመንት ኤክስፖ በመጪው ሐምሌ 18 እና 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ በተገለጸበት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

በመግለጫው የአገር ውስጥ ሪል ስቴት አልሚዎች የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በአሜሪካ የቤት ሽያጭ እንዲፈጽሙ እንደሚያስችል ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበር ዋና ጸሐፊ ዝናቡ ተበጀ (ኢንጂነር)፣ የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲኖራቸው የሚያስችል አዋጅ መውጣቱን አስታውሰዋል።

የውጭ ዜጎች እስከ 150 ሺሕ ዶላር ድረስ ሀብት ማፍራት እንደሚችሉ ያወሱት ዝናቡ (ኢንጂነር)፣ በስምምነቱ መሠረት የሚደረገው ኤክስፖ የውጭ አገር ዜጎችና ዳያስፖራዎች በዘርፉ የሕዝብ አመኔታ ኖሯቸው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ግዥ እንዲፈጽሙ ለማድረግ እንደሚያገለግል ተናግረዋል።

ለዚህም ሪል ስቴት ሲመርጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከማድረግ ጀምሮ፣ ዋና ዋና የብቃት አመላካቾችን በማየት ውሳኔያቸውን እንዲያሳልፉ ለማድረግ ከሀርቨስት ሰርክል ጋር የጋራ ስራዎች እንደሚከናወኑ ዋና ወሃፊዋ ገልፀዋል።
ሪፖርተር

@Addis_Reporter
12👍2😢2🕊1
እገታ ተፈፀመ‼️
በዛሬው ዕለት ሰኔ 6/2018 ዓ.ም  ጠዋት በምስራቅ አርሲ ከአቦምሳ ከተማ ወደ አስኮ እየመጣ ያለ አንድ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ ሙሉ ተሳፋሪዎችን ከቀኑ 6:00 ላይ ባለፈው ጥቃት የፈፀሙት የሸኔ ታጣቂዎች እግተዉ ይዘው መሄዳቸውን የአካባቢው የአይን እማኞች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

እገታው የተፈፀመው ከከተማው ጥቂት ኪሎሜትር እርቀት ላይ ሲሆን የፀጥታ ሀይሎች እዛው አከባቢ ነበሩ ብለዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በዚህ አካባቢ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት መፈፀሙ የሚታወስ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔52😢2310😡8🤯3🕊3👍2
ከነዳጅ 235 ቢሊየን ብር ታክስ ለመሰብሰብ ታቅዷል

በ 2019 በጀት አመት መንግስት ቀጠኛ ያልሆነ ታክስ ከነዳጅ ለመሰብበስ ነው ያቀደው።

👉109.6 ቢሊየን ብር ከኤክሳይስ ታክስ

👉126 ቢሊየን ብር ቫት ለመሰብሰብ ነው የታቀደው

👉ይህም በጥቅሉ ወደ ሩብ  ትሪሊየን ብር የሚጠጋ ነው

👉ይህም ለመሰብሰብ ከታሰበው ጠቅላላ 1.5 ትሪሊየን ብር ወደ 15.7 በመቶ የሚጠጋ ነው።

ከዘርፉ ቀጥተኛ  ያልሆነ ግብር ከ2018 አንስቶ ለመሰብሰብ መታቀዱ የሚታወስ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢17😁149👍7🤯1👀1🤪1🙊1
ሰበር-መረጃ‼️
የኢራን ሰላም ስምምነት ነገ ይፈረማል - ትራምፕ።

ስምምነቱ እንደተፈረመ የሆርሙዝ ስርጥ ወዲያውኒ ሙሉ ለሙሉ ይከፈታል ብለዋል።

ነገሮች ሲረጋጉ አሜሪካ ወደ ኢራን ገብታ ለኑክሌር የበለፀገውን የዩራኒየም አቧራ እንወስዳለን ብለዋል።

ከኢራን ጋር አሁን ላይ የተሻለ ግንኙነት አለን ያሉ ሲሆን ከመሬት በታች ምሽግ ደርማሽ ቦንብ በመጣል የሚታወቀውን የአሜሪካ B-2 የጦር አውሮፕላን አመስግነዋል።

ነገ የኢራን እና የአሜሪካ አመራሮች በመይነመረብ ስብሰባ ያደርጋሉ፣ፊርማው ኤሌክትሮኒካሊ ይፈረማል።

ኢራን አልስማማም ካለች ይህን እድል መቼም እንደማታገኘው አስጠንቅቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1813🤣10🙏4👏2🤔1👌1👀1🤪1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦

ከጠዋቱ 2፡00 – 8፡30

👉አፍንጮ በር መስጊድ፣ ደጃች ውቤ፣ ጊዮርጊስ እሳት አደጋ፣ ችሎት አደባባይ፣ ዘበኛ ሰፈር፣ ሾላ፣ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ሰሜን ሆቴል ጫፍ፣ ቀለመወርቅ ት/ቤት፣ ዶሮ ተራ፣ ራስ ደስታ አካባቢ፣ አርበኞች ት/ቤት፣ ዕንቁላል ፋብሪካ አደባባይ እና አካባቢቸው፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 9፡30

👉ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም፣ ጀርመን አደባባይ፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ትግሬ ሰፈር፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ ጀርባ እና አካባቢቸው፣

👉ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ ጫፍ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴል፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ እና አካባቢቸው፣

ከጠዋቱ 3፡00 – 9፡30

👉ድሬ ከአስፋልት በታች፣ ጉዳ፣ ኬላ፣ ጉዮ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር በከፊል፣ ቶልቻ፣ ሰንጎታ፣ ገፋርሳ ሰብስቴሽን እና አካባቢቸው፣ 

ከጠዋቱ 3፡00 – 9፡30

👉በአዳማ አዳማ ሆስፒታል፣ ፖስታ ቤት አካባቢ፣ ሁሩታ ከተማ፣ ሰኞ ገብያ እና አካባቢያቸው ፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡30

👉በመቋሌ ኢትዮ-ሸዊት ብረት ስራ እና አካባቢዎቻው የኃይል አቅርቦት ይቋረጠል፡፡


ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍2
ኔታንያሁ የአሜሪካ ባለስልጣናት ስጋት‼️
አሜሪካ ከኢራን ጋር ስምምነት ከተፈራረመች የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ስምምነቱን ሊያፈርስብን ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንደገባቸው የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ አክሲዎስ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍7🥰2🙊2👏1
በሚገኙበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ያልተሰጣቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራን ስም ዝርዝርን እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉንም የመንግሥት ዩኒቨርሲዎች ጠይቋል።

በቀን 04/10/2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ኮራ ጡሹ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲዎች የተጻፈ ደብዳቤ፣ ከሰኔ 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የመምህራኑ ዝርዝር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲላክ አዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍5🥰1👏1