የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤3👍2
ዛሬም ከባድ ጥቃት ይፈፀማል:-ትራምፕ‼️
ትራምፕ ዛሬም አራን ላይ ከባድ ጥቃት እንደሚፈፅሙ ገልፀዋል።
የኢራንን ሙሉ የሀይል ማመንጫ እና መሰረተልማቶች ለማውደም አቅጄ ነበር ግን የኢራን ህዝብ ይጎዳል ብለዋል።
አሁን አየር ሀይላችን በቴህራን በነፃነት እየተንቀሳቀሰ ነው፣ኢራን እራሷን መከላከል አትችልም ብለዋል።
ኢራንም አሜሪካ ጥቃቷን ከቀጠለች የምፈፅመው ጥቃት አድማሱን ያሰፋል ብላለች።
@Addis_Reporter

🤣14👍10❤3👏1🎉1
ጥቃቱ ተሰርዟል-ትሬምፕ‼️
ትራምፕ በዛሬው ዕለት ኢራን ላይ ሊፈፀም የነበረውን ከባድ ጥቃት መሰረዛቸውን አስታወቁ።
በድርድሩ የመጨረሻ ነጥቦች ላይ መላው የአረብ ሀገራትን ጨምሮ በሁሉም አካላት ተቀባይነት አግኝተዋል ያሉ ሲሆን ከኢራን ጋር የሚደረገው የስምምነት መፈረሚያ ጊዜ እና ቦታ በቅርቡ ይፋ ይሆናል' ብለዋል። ስምምነቱ እስከሚፈረም በኢራን ላይ የተጣለው የባህር ላይ እገዳ ይቀጥላል ብለዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👉ኢራን ወደ ስምምነት መጥታለች ብለዋል።

😁34❤11👍5👏1🤔1
በቀናት ውስጥ ወደ ጦርነት…!
ሬድዋን ሁሴን እና ጌታቸው ረዳ፤ "ህወሓት በቀናት ውስጥ ጦርነት ይከፍታል" አሉ።
"ህወሓት በቀናት ውስጥ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወስኗል" ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ አልጀዚራ ላይ ባስነበቡት ጽሑፍ አስጠንቅቀዋል፡፡
ሬድዋን እና ጌታቸው በጋራ ባስነበቡት ጽሑፍ፣ “ጽምዶ” በሚል ቅንጅት የፈጠሩ ኃይሎች ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ጎትተው ለማስገባት እየተንቀሳሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በአስመራ፣ በመቀሌ እና በሱዳን በድብቅና ግልጽ በሆኑ ስብሰባዎች የተፈጠረው የጽምዶ ጥምረት፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ማጥቃት ለመሸጋገር ተዘጋጅቷል ብለዋል።
ጌታቸው እና ሬድዋን "አክራሪና ርዝራዝ ቡድን ነው" ያሉት ህወሓት፣ በአስመራ ድጋፍና አጋዥነት፣ በሚቀጥሉት ቀናት ጥቃት ለመሰንሰር መወሰኑን አረጋግጠዋል፡፡
ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ህወሓትና የጦርነት አጀንዳውን በግልጽ ውድቅ ቢያደርግም፣ ቡድኑ የግጭት መቀስቀስ አባዜውን አልተወም ብለዋል፡፡
ህወሓት ከኤርትራ መንግስት በቀጥታ በሚያገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ ኃይል መመልመል፣ ማሰልጠን እና ማስታጠቅ ቀጥሏልም ሲሉም አክለዋል።

❤21🤪19👍2🤯1
የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርት በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ሊካተት ነው፡፡
የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በቀጣይ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ለማስተማር የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈፅሟል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክንደያ ገብረሕይወት (ፕ/ር) እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቺን ሃይ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በሁለቱ አገራት መካከል እያደገ የሚገኘውን የባህል፣ የትምህርት እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ያስችላል ተብሏል፡፡
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በቻይና ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርት ከሰርተፊኬት ስልጠና ጀምሮ እስከ 2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም እንደሚያስተምር ይታወቃል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስፋፋት ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮዎች ጋር በቅርቡ ስምምነት መፈፀሙ ይታወሳል።

❤16😁6😢6👍4🤔1
❤15🤣7👍3
አዲሱ የተሽከርካሪዎች ሰሌዳ አጠቃላይ መረጃዎችን የያዘ ቺፕስ በውስጡ መቀበሩ ተገለፀ
"ሰሌዳው በውስጡ ቻንሲ፣ ሞተር፣ የባለቤቱን ስም እና ሌሎች መረጃዎችን የያዘ ቺፕስ በውስጡ ተቀብሯል፡፡
ይህም አገራዊ የተሽከርካሪዎች የመረጃ ቋት ለመፍጠር ያግዛል" ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የቂርቆስ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ደረጄ አሰፋ ነግረውኛል ሲል ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል።
በክፍለ ከተማው ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ አገልግሎቱ መስጠት መጀመሩን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ፥አዲሱ ሰሌዳ የአገር ሃብትን ከብክነት ለመታደግ እና ሕገ-ወጥነትን ለመከላከል የላቀ እገዛ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

😢10❤9👍4
ለቤተሰቦቿ መልዕክት ልታደርስ የሄደችውን ታዳጊ በመጥለፍ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመፈጸም ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ
በጌዴኦ ዞን ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክልን በመጠቀም የጠለፋ እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመፈፀም ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል።
ተከሳሽ ዮሴፍ ምትኩ የተባለ ሲሆን የግል ተበዳይ ታዳጊ በረከት ተስፋዬ ለቤተሰቦቿ መልዕክት ልታደርስ ገበያ ስትሄድ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በያዙት ሞተር ሳይክል በመጠቀም የወንጀል ድርጊት መፈፀሙን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በዚህም ፖሊስ ተከሳሽ ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በፈፀመው የጠለፋ ወንጀል እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን በማረገጥ ክስ መስርቶ ለወናጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።
ጉዳዩን የተመለከተዉ የወናጎ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ሲመረምር ቆይቶ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሹ በተከሰሰበት በሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በማረጋገጥ ተከሳሽ ዮሴፍ ምትኩን በ9 ዓመት ከስምንት ወር እስር እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤7👍4
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944
👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !
👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further

👍3❤1
የፕላስቲክ መክተፊያና ተያያዥ ስጋቶች‼️
በየቀኑ በኩሽናችን ውስጥ የምንጠቀምባቸው የፕላስቲክ መክተፊያዎች (Cutting Boards) አብዛኞቹ ከፖሊኢቲሊን (Polyethylene) ወይም ፖሊፕሮፒሊን (Polypropylene) የተሰሩ ናቸው።
እነዚህ መክተፊያዎች ምግብ ስንከትፍ በሚፈጠር ግጭትና ጭረት ምክንያት በዓይን የማይታዩ ጥቃቅን የፕላስቲክ ቅንጣቶች (Microplastics) ወደ ምግባችን እንዲቀላቀሉ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።
የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ የፕላስቲክ መክተፊያዎችን አዘውትሮ መጠቀም በዓመት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጥቃቅን የፕላስቲክ ቅንጣቶችን ወደ ሰውነታችን እንዲገቡ ሊያደርግ ይችላል።
መክተፊያው ባረጀና በቢላዋ ጭረት በበዛበት ቁጥር የሚወጣው የፕላስቲክ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
ምንም እንኳን ወደ ሰውነታችን የሚገባው የፕላስቲክ መጠን ትክክለኛ ክብደት ላይ አሁንም ጥናቶች ቢቀጥሉም፣ ቅንጣቶቹ ወደ ደም ዝውውር የመቀላቀልና በረጅም ጊዜ ለጤና ስጋት የመሆን እድላቸው ግን አሳሳቢ ነው።
ይህ ሁኔታ በተለይ በህጻናት ላይ ጥንቃቄን ይሻል። ህጻናት እያደጉ ያሉ በመሆናቸውና የሰውነት ክብደታቸው አነስተኛ በመሆኑ፣ ወደ ሰውነታቸው የሚገቡ የኬሚካል ቅንጣቶች ከአዋቂዎች ይልቅ በእድገታቸውና በሆርሞን ስርዓታቸው ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ።
ማይክሮ ፕላስቲኮች ወደ ሰውነት ከገቡ በኋላ የሚከተሉትን ችግሮች ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ስጋቶች አሉ፦
1. በፕላስቲክ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች (እንደ BPA ያሉ) የተፈጥሮ ሆርሞኖችን ስራ ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ።
2. ጥቃቅን ቅንጣቶቹ በሴሎች ውስጥ በመከማቸት ለተለያዩ ብግነቶች መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
3. ፕላስቲኮች ሌሎች አካባቢያዊ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ስበው የመያዝ ባህሪ ስላላቸው ተጨማሪ ስጋት ይፈጥራሉ።
መፍትሄው :-
1. የእንጨት መክተፊያዎችን መጠቀም የእንጨት መክተፊያዎች ከተፈጥሮ (Cellulose) የተሰሩ በመሆናቸውና የመቆረጥ እድላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ተመራጭ ናቸው።
2. ያረጁ መክተፊያዎችን መቀየር የፕላስቲክ መክተፊያ የሚጠቀሙ ከሆነ ጥልቅ ጭረቶች ሲፈጠሩና ሲያረጅ በአዲስ መቀየር ያስፈልጋል።
3. ጥንቃቄ በተለይ በሆቴሎችና በስጋ ቤቶች ውስጥ ትልልቅ ቢላዎችና መጥረቢያዎች ስለሚጠቀሙ፣ መክተፊያዎቹ ላይ የሚፈጠሩ ጥልቅ ጭረቶች ለፕላስቲክ ቅንጣቶች መለቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው።
ጤናችንን ለመጠበቅ የለት ተለት ልምዶቻችንን ቆም ብለን ማጤንና የተሻሉ አማራጮችን መከተል ለነገው ደህንነታችን ወሳኝ ነው።
ይህ መረጃ ለሌሎችም ጠቃሚ ነው ብለው ካመኑ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ያካፍሉት (Share ያድርጉ)።"
Via ፍላቴ ጣሳው

❤14👍4👀2💊2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነው
እዉቅናን የሚያገኙት 100 ታዋቂ አፍሪካውያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ ላይ ነዉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ ማራኪሽ ላይ በሚካሄደዉ ታዋቂ አፍሪቃዉያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ ላይ መሆኑ ተዘግቧል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር፤ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ እና የቀድሞዋ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ዶ/ር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ዘንድሮ በሚካሄደው 100 ታዋቂ አፍሪቃውያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ በሞሮኮ ማራኬሽ ላይ፤ ክብር እና እውቅና ከሚሰጣቸዉ ታዋቂ የአፍሪቃ መሪዎች እና ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል።
ጉባኤዉ፤ በአህጉሪቱ እና ከአህጉሪቱ ዉጭ ባሉ ሀገራት መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ ዲፕሎማቶች እና ለውጥ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት እያደገ የመጣ ተሳትፎን ተከትሎ በማራኬሽ ሞሮኮ ከሰኔ 19 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2018 እንደሚካሄድ የዝግጅቱ አዘጋጆች አስታውቀዋል።
ይፋ በተደረገዉ ዘገባዉ መሰረት፤ በዳቭዳን የሰላም እና የጥብቅና ፋውንዴሽን እና በ100 በጣም ታዋቂ የሰላም ቁንጮ የአፍሪካ አጋሮች ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ይህ ዓመታዊ ጉባኤ፤ ልህቀትን ለማክበር፣ ፈጠራን ለማራመድ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስፈን፣ ድንበር ዘለል አጋርነቶችን ለማጠናከር እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት የሚሰራ የአፍሪቃ ግንባር ቀደም መድረኮች አንዱ ነው።

🤪43❤30😢5😡4👍3😁3👏1🎉1🤣1🙊1
አንዲት ፈረንሳዊ ጋዜጠኛ ከኢትዮጵያ ተባረረች!
«ላ ክሪክስ» በተሰኘ ጋዜጣ ላይ የምትሰራ አንዲት ፈረንሳዊት ጋዜጠኛ ከኢትዮጵያ መባረሯን ድርጅቷ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዛሬ ዘገበ።
የዜና አገልግሎቱ እንደገለፀዉ፤ ኢትዮጵያ በገለልተኛ ሚዲያዎች ላይ የምትወስደዉን እርምጃ አጠናክራ ቀጥላለች።
የ30 ዓመቷ ፈረንሳዊት ጋዜጠኛ አውጉስቲን ፓሲሊ፤ ከጎርጎረሳዉያኑ 2023 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ዘጋቢ ሆና እያገለገለች ነበር።
አንደ ፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት ፤ ጋዜጠኛ አዉጉስቲን የተባረረችበትን ምክንያት ከባለስልጣናት ግልጽ የሆነ ምክንያት አልተቀመጠም።
የጋዜጣው የውጭ ጉዳይ አዘጋጅ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለፀዉ ግን “ለመረዳት የማይቻል” እና “በፕሬስ ነፃነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው” ብሎታል።

❤14👍5
አሜሪካ የ‘ወሊድ ቱሪዝም’ ማጭበርበርን በምክንያትነት በመጥቀስ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካውያንን ቪዛ ሰረዘች - መግለጫ
🇺🇸🔍 በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ የአሜሪካ ኤምባሲ ከ100 በላይ የውጭ አገር ዜጎች የተጭበረበሩ ሰነዶችን እና የቪዛ ደላሎችን በመጠቀም ለዜግነት ዓላማ የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት የዘረጉትን የወሊድ ቱሪዝም መረብ ማጋለጡን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።
በሰሜን አፍሪካም በተመሳሳይ በተወሰደ እርምጃ ከ100 በላይ ቪዛዎች እንዲሰረዙ የተደረገ ሲሆን፣ የቆንስላ መኮንኖች እና የሕግ አስከባሪ አካላት እነዚህን መረቦች ለይተው በማወቅ እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተገልጿል።

“ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በአሜሪካ ምድር በመውለድ ለልጁ የአሜሪካን ዜግነት የማግኘት ቀዳሚ ዓላማ ይዞ የጎብኚ ቪዛ ማግኘት አይፈቀድለትም” ሲልም አክሏል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤3👍3
መንግስት የታክስ እፎይታን በማንሳት 78.9 ቢሊዮን ብር አዲስ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱ ተሰማ
የገንዘብ ሚኒስቴር ለፓርላማ ባቀረበው የ2019 ረቂቅ በጀት ላይ እንዳመለከተው፥ ከቀረጥ ነፃ እና የግብር እፎይታ አሰራሮች ከመጪው በጀት ዓመት ጀምሮ ይቀራሉ።
በዚህም ቀደም ሲል ከቀረጥ ነፃ ይገቡ የነበሩ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ የህክምና እና የአካል ጉዳተኞች መርጃ መሣሪያዎች በቅናሽ ምጣኔ እንዲስተናገዱ ተደርጎ 22.5 ቢሊዮን ብር ይሰበሰባል።
በተጨማሪም የገቢ ግብር እፎይታን በማንሳት ሌላ 22.5 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም አዲስ የኤክሳይዝ ታክስ የቴምብር ሥርዓት በመዘርጋት 33.8 ቢሊዮን ብር፤ በድምሩ 78.9 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ገቢ ለማግኘት ታቅዷል።
በአጠቃላይ መንግስት ከተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ ከታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ምንጮች በመጪው ዓመት 1.6 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዷል።
ምንጭ: ሸገር ራዲዮ

😡15❤8👍3🤔1
በፌስቡክ እና በሌሎች የሜታ (Meta) አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል አጋጠመ!
ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፌስቡክ፣ የኢንስታግራም እና የሜሴንጀር ተጠቃሚዎች ከፍተኛ የአገልግሎት መቋረጥ እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት እያደረጉ ይገኛሉ።
ምን ተከሰተ?
ብዙሃኑ ተጠቃሚዎች ከበይነ-መረብ አካውንቶቻቸው በራሱ ጊዜ Log out እየሆኑባቸው ሲሆን፥ ተመልሰው ለመግባት በሚሞክሩበት ወቅትም የሚከተሉትን የስህተት መልዕክቶች እያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፦
- Something went wrong” የሆነ የተሳሳተ ነገር ተከስቷል) *Query error” (የጥያቄ ስህተት) ከተለመደው የፌስቡክ መተግበሪያ በተጨማሪ የ Messenger እና የInstagram አገልግሎቶችም ተመሳሳይ እክል እንደገጠማቸው ታውቋል።
ምን ማድረግ ይኖርብዎታል? ችግሩ ከእርስዎ ስልክ ወይም የኢንተርኔት ግንኙነት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከራሱ ከሜታ (Meta) ሰርቨር የመነጨ በመሆኑ፦
1. አይደናገጡ፦አካውንቴ ተጠለፈ (Hack ተደረገ) ብለው እንዳይሰጉ።
2. ይጠብቁ፦የሜታ የቴክኒክ ባለሙያዎች ችግሩን ቀርፈው አገልግሎቱን ወደ ነበረበት እስኪመልሱ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ ብልህነት ነው።

❤12👍4🥱2🥰1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥
🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።
የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia

በ2026 የዓለም ዋንጫ የቲኬት ዋጋ መናር ስታዲዮሞችን ብዙ ወንበሮች ክፍት ማድረጉ አነጋጋሪ ሆኗል
በሜክሲኮ ጓዳላሃራ ስታዲዮም በደቡብ ኮሪያ እና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል በተደረገው ሁለተኛው የምድብ ጨዋታ (ኮሪያ 2 ለ 1 አሸንፋለች) በርካታ ወንበሮች ባዶ ሆነው ታይተዋል።
ይህ ሁኔታ በመክፈቻው ጨዋታ በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ከታየው የ80 ሺህ ደጋፊዎች ድምቀት የተለየና ቀዝቃዛ ነበር።
ለስታዲዮሙ መካከለኛ ወንበሮች መቅረት ዋነኛ ምክንያት የፊፋ እጅግ ውድ የቲኬት ዋጋ እንደሆነ እየተነገረ ነው።
በአሁኑ ወቅት በአማካይ የአንድ መደበኛ ወንበር ዋጋ 500 ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ከ180 ሺህ በላይ ቲኬቶች አሁንም በድጋሚ መሸጫ መድረኮች ላይ ሳይሸጡ ቀርተዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙዎች የስታዲዮሙን ባዶነት ተችተዋል።
የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ግን ከውድድሩ በፊት በሰጡት መግለጫ የዋጋው መናር ችግር እንደማይሆን ተከላክለዋል። "የቲኬት ዋጋችን ተመጣጣኝ ነው፤ ዋጋው በባለሙያዎች የተጠና ነው" ብለዋል።
ይሁን እንጂ ውድድሩ ገና በጅምሩ ላይ እያለ የታየው ባዶ ወንበር ፊፋን ማሸበሩና የቲኬት ዋጋው ውሳኔ በራሱ ላይ መውደቁ አይቀሬ ይመስላል።

❤17👍9😱2
አከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ብቻ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ
የቢሮው ኃላፊ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እንደገለጹት፣ የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በተጀመረው የዲጂታል ምዝገባ እስካሁን 500 ሺህ የሚጠጉ ቤቶች ወደ ሲስተሙ ገብተዋል።
ይህ አዲስ አሰራር ያለ አግባብና ያለ ምንም ምክንያታዊ መነሻ ይደረግ የነበረውን የዋጋ ጭማሪ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። መንግሥት በየዓመቱ የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የገበያ ጥናት ካካሄደ በኋላ፣ በየዓመቱ ሰኔ 30 ላይ በሚያወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት የዋጋ ጭማሪውን በፐርሰንት ይወስናል።
የውል ጊዜው በማብቃቱ ብቻ ተከራይን አስወጥቶ ዋጋ ጨምሮ ማከራየት አይቻልም። በአሁኑ ወቅት እንግልትን ለማስቀረት የውል ማደስ ሥራውን በኦንላይን ለማከናወን ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ በየሁለት ዓመቱ የኪራይ ውልን ማደስ ግዴታ መሆኑ ተገልጿል።

❤18👍13🤪7👏3👀2
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ መንግሥት ላይ ያቀረቡትን ከባድ ክስ ተከትሎ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ሬድዋን በሕወሓት እና በኤርትራ መካከል አዲስ ትብብር መጀመሩን በመጥቀስ በአልጀዚራ በኩል በነበራቸው ቆይታ በፌዴራል መንግሥቱ ላይ አዲስ ጦርነት ሊከፈት ተዘጋጅተዋል ሲሉ ክስ አቅርበው ነበር። በአልጀዚራ ጽሑፍ ላይ አቶ ጌታቸው ረዳም ተካተው እንደነበር ይታወቃል።
ይህንን ክስ ተከትሎ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ምላሽ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ንግግር በሐሰት፣ በማታለልና በተሳሳተ መረጃ የተሞላ ሲሉ ያጣጣሉ ሲሆን ይልቁንም ሁለቱ ወገኖች ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወራት በፊት በጅቡቲ እና ሲሸልስ በሚስጥር ተገናኝተው በኤርትራ ላይ የጋራ ወረራ ለመፈጸም ሲመክሩ ነበር ብለዋል። ይህንንም አቶ ጌታቸው ረዳ ራሳቸው ቀደም ብለው ተናግረዋል ሲሉ እንደ ማስረጃ አቅርበዋል።
በመጨረሻም የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ለሚታየው አለመረጋጋት መንስኤው የኢትዮጵያ መንግሥት ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ እያራመደው ያለው የባሕር በር መሻት የከፈተው የጠብ አጫሪነት ንግግር ነው ያሉት አቶ የማነ አሁን የቀረበው ክስ ይሄንኑ “የራሳቸውን” የጦርነት አጀንዳ ለመሸፈን የታለመ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው ሲሉ ምላሻቸውን ደምድመዋል።

❤24👍5🤪3