አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ኩዬት ለኢትዮጵያውያን ፈቀደች‼️
ኩዌት ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከ10 ሀገራት የቤት ሰራተኞችን ለመቅጠር ፈቀደች።

የኩዌት የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የቤት ሰራተኞች ቅጥርን የሚቆጣጠር አዲስ መመሪያ ማውጣቱን ዘገባ አመላከተ።

​በአዲሱ መመሪያ መሰረት ኩዌት ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨምሮ ከ10 ሀገራት የቤት ሰራተኞችን (ወንድም ሴትም) ለመቅጠር ፈቅዳለች።

የተፈቀደላቸው ቀሪዎቹ ሀገራት ደቡብ አፍሪካ፣ ቤኒን፣ ፊሊፒንስ፣ ስሪላንካ፣ ሕንድ፣ ቪየትናም፣ ኔፓል እና ሴኔጋል (ለወንዶች ብቻ) ናቸው።

​የቅጥር ሂደቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግም ማመልከቻዎች በየግዛቱ በሚገኙ የአገልግሎት ማዕከላት በኩል እንደሚስተናገዱ የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26👍16😢2🤪2👏1
የደቡብ አፍሪካው ስታንቢክ ባንክ በኢትዮጵያ በብቸኝነት በባለቤትነት የሚያስተዳድረውን ራሱን የቻለ ባንክ ለማቋቋም እያሰበ መኾኑ ተሠማ።

ባንኩ ራሱን የቻለ ባንክ ለማቋቋም ያሰበው፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ የኢንቨስትመንት ወጪ እየቀነሠና ገቢው እየጨመረ መሄዱን እንደ ጥሩ ምሳሌ በመውሠድ እንደኾነ የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ስታንቢክ ባንክ የግዙፉ የደቡብ አፍሪካ ስታንዳርድ ባንክ አንድ ካል ነው።

ብሄራዊ ባንክ ያወጣው ሕግ፣ በአገር ውስጥ ባንክ የአክሲዮን ድርሻ መግዛት የሚፈልጉ የውጭ ባንኮች ድርሻቸው ከ49 በመቶ እንዳይበልጥ ገደብ ይጥላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍3👏1👌1😡1
ብልፅግና ፓርቲ የተወዳደረባቸውን ወንበሮች በሙሉ አሸነፈ

👉 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም የግል ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)  ምንም መቀመጫ አላሸነፉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት እወጃ በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሌሎች 22 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፣ ከተገለጹት ጠቅላላ 48 የምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል ከአንዱ በስተቀር የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች ያሸነፉ ሲሆን፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ዕጩ ደግሞ በሶማሌ የክልል ምክር ቤት አንድ ወንበር ማሸነፉ ታውቋል። በደገ ሀቡር አንዱን ወንበር የኦጋዴን ግንባር ዕጩ የነበሩት አቶ መሀሙድ ሀሰን ሁሴን አሸንፈዋል።

ለክልል ምክር ቤቶች በጠቅላላው የ12 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ውጤቶች ተነግረዋል። የክልል ምክር ቤት ምርጫዎች በየምርጫ ክልሉ ብዙ መቀመጫዎች ያሏቸው በመሆኑ፣ በድምሩ የ38 መቀመጫዎች ውጤት የታወጀ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ ብልፅግና ፓርቲ 37ቱን አሸንፏል።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላላው የ10 የምርጫ ክልሎች/ወንበሮች ውጤት የተገለጸ ሲሆን (1 ከአማራ፣ 3 ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና 6 ከኦሮሚያ)፣ 10ሩንም መቀመጫዎች በሙሉ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች አሸንፈዋል። ውጤታቸው የተገለጹት የምርጫ ክልሎችም በአማራ ክልል ጎዛምን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀዲዳ ጋሜላ 2፣ ጉመር 1 እና እዣ 2 ሲሆኑ፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ሀብሮ 1፣ ቅንበቢት፣ ጥቁር እንጭኒ፣ ጀልዱ፣ ወሊሶ 2 እና ወሊሶ 1 የምርጫ ክልሎች ናቸው።

በውጤት እወጃው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም የግል ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)  ምንም መቀመጫ አላሸነፉም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣7625👍6😁3😢2🤪2👀1🙈1
የበረራ ፈቃድ ሳይኖረው ለ17 ዓመታት «ኤር ካናዳን» ሲያበር የነበረው ካፒቴን ተያዘ

ረቡዕ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የካናዳ ፖሊስ የ59 ዓመቱ የ«ኤር ካናዳ» ካፒቴን ጄፍሪ ዎል አስፈላጊው የበረራ ፈቃድ ሳይኖረው ለ17 ዓመታት በማጭበርበር በመስራቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።

ግለሰቡ ከ2009 እስከ 2025 ባሉት ዓመታት ውስጥ የሀሰት ሰነዶችን በመጠቀም ቦይንግ 767፣ 777 እና 787 አውሮፕላኖችን በመያዝ ከ900 በላይ በረራዎችን የመራ ሲሆን፣ ወደ 3 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ አግኝቷል።

ኤር ካናዳ ጉዳዩን በጥብቅ እየመረመረው መሆኑን ገልጾ፣ አብራሪዎች በየስድስት ወሩ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ስለሚያልፉ የመንገደኞች ደህንነት አደጋ ላይ እንዳልወደቀ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👏248👍6😢3👌1😍1👀1🙈1
ትራምፕ ለኢራን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጡ‼️
👉ሆርሙዝ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል-ኢራን‼️
#አሜሪካ በኢራን ላይ አዳሯን ከባድ ጥቃት አደረሠች።

# ዋሽንግተን በቶማሃውክ ሚሳኤል ጭምር እስከ #ቴህራን አቅራቢያ ጥቃት ማድረሷን በፕሬዚዳንቷ በኩል ገልፃለች።

#ኢራንም በምላሹ በጆርዳን እና ኩዬት በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ቤዞች ላይ ከ12 በላይ ሚሳይል እና ድሮን በመጠቀም ጥቃት ሰንዝራለች።

በሆርሙዝ ሰርጥም ሁለት መርከቦችን መትቻለሁ” ብላለች።

የአሜሪካን ጥቃት ተከትሎ ኢራን #በሆርሙዝ ሰርጥ የሚያልፍ የትኛውም ዓይነት መርከብ አይኖርም ያለችው ሰርጡ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል ስትል በጦር ቃል አቀባያዋ በኩል ይፋ አድርጋለች።

ኢራን ሆርሙዝ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቧል ካለች በኋላ አለምአቀፍ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ የ 2 ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።

የአሜሪካ የቀጠናው ዕዝ ግን የንግድ መርከቦች አሁንም በሆርሙዝ እያለፉ ነው ሲል መግለጫ  ሰጥቷል።

አሜሪካ በምሽቱ ጥቃት 49 አቶማሃውክ ሚሳዔሎችን በመጠቀም 18 ኢላማዎችን መምታታቸውን ትራምፕ አሳውቀዋል።

ዛሬ ሰኔ 4/2018 ዓ.ም ኢራን ወደ ስምምነት ካልመጣች ከምድረ ገፅ ይጠፋሉ ሲሉ ትራምፕ ማስጠንቀቂያ ልከዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13🤣8👍2🥰2🥱2
MEXC በድንገት የኢትዮጵያን ብር (ETB) ከP2P ላይ አስወገደ።

ዓለም አቀፉ የክሪፕቶ ምንዛሬ መድረክ የሆነው MEXC የኢትዮጵያ ብርን (ETB) ከP2P ሥርዓቱ ላይ ሙሉ በሙሉ በድንገት ማስወገዱ ተረጋገጠ።

ኩባንያው ቀደም ሲል ይህን አገልግሎት የሚያቆመው እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2026 መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም ከተቀመጠው ቀነ-ገደብ ሃያ ቀናት ቀድሞ ውሳኔውን በተግባር አውሏል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ብር ምርጫ ከፕላትፎርሙ ላይ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን የፋይናንስ ህግ መሰረት አድርገው ፦
- ቴሌግራም ዋሌት
- ቢትጌት
- ባይናንስ
- ኦኬኤክስ
- ባይቢት ... የመሳሳሉ መድረኮች በኢትዮጵያን ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶች (P2P) ማቆማቸው ይታወሳል።

ብሔራዊ ባንክ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሥርዓት ያለው የዲጂታል ፋይናንስ ተሳትፎ እንዲኖር የሚያስችል አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከዓለም አቀፍ አቻ ተቆጣጣሪዎችና ከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ መሆኑን መግለጹም ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔92👍2🕊2
አዲሱ ሰሌዳ እስከ 56,000 ብር ዋጋ ተቆርጦለታል የሚለው መረጃ እያነጋገረ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ መግለጫ እየሰጠ ነው።ከመግለጫው ቀድሞ የወጣው ሰነድ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

አዲስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) መሸጫ ዋጋ እስከ 56000 ብር ዋጋ ተቆርጦለታል ይላል ሰነዱ። የቀረቡት ዋጋዎች የፊትና የኋላ ሰሌዳዎችን እንዲሁም ቫትን (VAT) ያካተቱ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

አነጋጋሪ ነው በተባለው ሰነድ ለግል መገልገያ (የቤት)፣ ለንግድ፣ ለዲፕሎማት፣ ለዕርዳታ ድርጅቶች፣ ለዓለም አቀፍ ተቋማት እና ለልዩ ተንቀሳቃሽ ተሽከርካሪዎች፦
📌በነዳጅ የሚሰሩ ከሆነ፦ 56,000 ብር
📌 በኤሌክትሪክ እና በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ከሆነ፦ 44,500 ብር
ለድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች፦
📌 በነዳጅ የሚሰሩ ከሆነ፦ 28,500 ብር
📌 በኤሌክትሪክ እና በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ከሆነ፦ 15,200 ብር
ለሕዝብ ታክሲ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች፦
📌 በነዳጅ የሚሰሩ ከሆነ፦ 11,700 ብር
📌በኤሌክትሪክ እና በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ከሆነ፦ 9,400 ብር
ለከተማና የሀገር አቋራጭ አውቶቡስ፣ ለመንግሥት፣ ለአካል ጉዳተኛ (PD) እና ለባለሦስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች፦
📌በነዳጅ የሚሰሩ ከሆነ፦ 9,400 ብር
📌 በኤሌክትሪክ እና በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ከሆነ፦ 7,100 ብር
ለባለሁለት እግር (ሞተርሳይክል) ተሽከርካሪዎች፦
📌 በነዳጅ የሚሰሩ ከሆነ፦ 4,700 ብር
📌 በኤሌክትሪክ እና በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ከሆነ፦ 3,550 ብር መሆኑን ከመግለጫው ቀድሞ የወጣው ሰነድ ያስረዳል።የመግለጫው ሙሉ ይዘት ከቆይታ በኋላ ይቀርባል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍5😢5🤷‍♂3🤯3👀2👏1🤪1😎1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
3👍3🙉1
ኦባሳንጆ መቀሌ ገቡ‼️
የፕሪቶሪያ ስምምነት አደራዳሪ ከነበሩት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የአውስትራሊያና የኢንግሊዝ ተወካዮች ያካተቱ የልኡካን ቡድን ከትግራይ ክልላዊ መንግስት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ለመወያየት መቐለ ከተማ ገብተዋል። ህወሓት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን ወታደራዊ አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1310😁6👏4😢3🤪2🤔1🤯1👌1
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) መሰጠት ጀምሯል፡፡
 
ፈተናው ከዛሬ ሰኔ 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ቀናት (ቅዳሜ እና እሑድ ሳይጨምር) በኦንላይን ይሰጣል፡፡
 
ለመጀመሪያ ጊዜ እና በድጋሜ ለመውጫ ፈተናው የሚቀመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት እና የግል ተፈታኞች ፈተናውን ይወስዳሉ፡፡
 
ተፈታኞች ስለፈተናው አጠቃላይ ገለጻ ዛሬ ጠዋት የተሰጣቸው ሲሆን፤ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን የፈተና ውሎ በጠዋት እና ከሰዓት መርሐግብር (ከ5፡00-7፡00 እና ከ8፡30-11፡00) የ62 ትምህርት አይነት ፈተናዎች እንደሚሰጡ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የወጣው መርሐግብር ያሳያል፡፡
 
የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3😁1
🚨 አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ 🚨

በቅርብ ጊዜ በቴሌግራም ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የአካውንት ጠለፋ እና የማጭበርበር ዘዴ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

ጠላፊዎች አሳሳች ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም አስደንጋጭ መልዕክቶችን በመጠቀም አደገኛ ሊንኮችን (Links) ይልካሉ።

እነዚህ መልዕክቶች ከማታውቋቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን፣ አካውንታቸው ከተጠለፈ ጓደኞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁ ወይም የምታምኗቸው ሰዎች ሊመጡ ይችላሉ።

ሊንኩን ጠቅ እንዳደረጋችሁ ወይም እንደከፈታችሁት፣ የቴሌግራም አካውንታችሁ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር ሊገባ ይችላል።

📤ለምሳሌ :-"እዚህ ዌብሳይት ላይ ፎቶህን አየሁት" የሚል መልዕክት ደርሷችሁ ይሆናል

🔒 ራሳችሁን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ያድርጉ፦

1️⃣ Settings → Privacy and Security → Devices ውስጥ ገብታችሁ የማታውቁትን ወይም አጠራጣሪ የሆኑ ስልኮች (Sessions) Terminate ወይም Terminate All Other Sessions በማድረግ ያስወግዱ።

2️⃣ Two-Step Verification ከአሁኑ ይክፈቱ።
Settings → Privacy and Security → Two-Step Verification ውስጥ በመግባት ጠንካራ የይለፍ ቃል (Password) ያስቀምጡ።

Hint ላይ ሌላ ነገር አስገቡ ብዙ ሰው ፖስዎርዱን መልሶ ሲያስገባ አይቻለው

🙏 ይህን ማስጠንቀቂያ ለጓደኞቻችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ እና ለሌሎች የምታምኗቸው ሰዎች በማጋራት ከዚህ አደገኛ ጥቃት እንዲጠነቀቁ አድርጉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
27👍11🙏3
በህወሓት ላይ እርምጃ ይወሰድ-ኢዜማ‼️
የፌዴራል መንግሥቱ ሕውሓት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ኢዜማ ጠየቀ‼️
አካሄዱ ‹መኢሶንን ይመስላል› በሚል የሚተቸው ኢዜማ በትግራይ ያንዣበበውን ወታደራዊ ውጥረት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የፌዴራል መንግስቱ ሕውሓት ላይ እርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል፡፡ ሕውሓት ደርግን ጥሎ ስልጣን ከተቆጣጠረ አንስቶ የሰራቸውን ጥፋቶች የሚዘረዝረው መግለጫው፤ አሁን ላለው አገራዊ ችግር መንስኤው ሕውሓት ያሠፈነው የብሔር ፖለቲካ እንደሆነ አንስቷል፡፡

ለፕሪቶሪያ ስምምነት አለመተግበር እና ለተፈናቃዮች አለመመለስ ሕውሓትን ብቻ ተጠያቂ ያደገው የፓርቲው መግለጫ፤ ‹‹ይህንን ኃይል በቃህ ማለት እና በትግራይ ያሉ ወገኖቻችንን ከማያባራ መከራ መታደግ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን የጋራ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል፤ ጦርነትን ሳይጀመር በፊት ማስቆም ይገባናል›› ሲል ጠይቋል፡፡

‹‹እንደ ሕወሓት ዓይነት ደም የማይጠረቃ አካል እና እሱን የሚዘውሩ ጥቂት ግለሰቦች በቃችሁ ብሎ ለማስቆም እና የትግራይ ህዝብን ካላስፈላጊ መከራ ለመታደግ በህዝብ ላይ ምንም አይነት መስዋዕትነት በማያስከትል መልኩ በሕገወጥ ቡድኑ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አስፈላጊ ሕጋዊ እርምጃ በመንግሥት እና ከመንግሥት ጋር በጋራ በሚቆሙ ማንኛውም ለትግራይ ማኅበረሰብ በሚቆረቆር አካል ሊወሰድ እንደሚገባ ያምናል›› በማለት ሕውሃት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍10🤪9🌚3👏2🎉1👌1💯1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
3👍2
ዛሬም ከባድ ጥቃት ይፈፀማል:-ትራምፕ‼️
ትራምፕ ዛሬም አራን ላይ ከባድ ጥቃት እንደሚፈፅሙ ገልፀዋል።
የኢራንን ሙሉ የሀይል ማመንጫ እና መሰረተልማቶች ለማውደም አቅጄ ነበር ግን የኢራን ህዝብ ይጎዳል ብለዋል።
አሁን አየር ሀይላችን በቴህራን በነፃነት እየተንቀሳቀሰ ነው፣ኢራን እራሷን መከላከል አትችልም ብለዋል።
ኢራንም አሜሪካ ጥቃቷን ከቀጠለች የምፈፅመው ጥቃት አድማሱን ያሰፋል ብላለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣14👍103👏1🎉1
ጥቃቱ ተሰርዟል-ትሬምፕ‼️
👉ኢራን ወደ ስምምነት መጥታለች ብለዋል።

ትራምፕ በዛሬው ዕለት ኢራን ላይ ሊፈፀም የነበረውን ከባድ ጥቃት መሰረዛቸውን አስታወቁ።
በድርድሩ የመጨረሻ ነጥቦች ላይ መላው የአረብ ሀገራትን ጨምሮ በሁሉም አካላት ተቀባይነት አግኝተዋል ያሉ ሲሆን ከኢራን ጋር የሚደረገው የስምምነት መፈረሚያ ጊዜ እና ቦታ በቅርቡ ይፋ ይሆናል' ብለዋል። ስምምነቱ እስከሚፈረም በኢራን ላይ የተጣለው የባህር ላይ እገዳ ይቀጥላል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁3411👍5👏1🤔1
በቀናት ውስጥ ወደ ጦርነት…!

ሬድዋን ሁሴን እና ጌታቸው ረዳ፤ "ህወሓት በቀናት ውስጥ ጦርነት ይከፍታል" አሉ።

"ህወሓት በቀናት ውስጥ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወስኗል" ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ አልጀዚራ ላይ ባስነበቡት ጽሑፍ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሬድዋን እና ጌታቸው በጋራ ባስነበቡት ጽሑፍ፣ “ጽምዶ” በሚል ቅንጅት የፈጠሩ ኃይሎች ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ጎትተው ለማስገባት እየተንቀሳሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአስመራ፣ በመቀሌ እና በሱዳን በድብቅና ግልጽ በሆኑ ስብሰባዎች የተፈጠረው የጽምዶ ጥምረት፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ማጥቃት ለመሸጋገር ተዘጋጅቷል ብለዋል።

ጌታቸው እና ሬድዋን "አክራሪና ርዝራዝ ቡድን ነው" ያሉት ህወሓት፣ በአስመራ ድጋፍና አጋዥነት፣ በሚቀጥሉት ቀናት ጥቃት ለመሰንሰር መወሰኑን አረጋግጠዋል፡፡

ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ህወሓትና የጦርነት አጀንዳውን በግልጽ ውድቅ ቢያደርግም፣ ቡድኑ የግጭት መቀስቀስ አባዜውን አልተወም ብለዋል፡፡

ህወሓት ከኤርትራ መንግስት በቀጥታ በሚያገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ ኃይል መመልመል፣ ማሰልጠን እና ማስታጠቅ ቀጥሏልም ሲሉም አክለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤪19👍2🤯1