አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ሿሿ ሲሰሩ የተያዙት ሴቶች‼️
የሿሿ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ሳሪስ አቦ የትራፊክ መብራት አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 A 02122 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪና ተጠቃሚ በመምሰል አዲሱ መኮንንና ኢሳያስ ደገፋ የተባሉ የግል ተበዳዮችን በመጫን ጥቂት እንደተጓዙ ኪሳቸው ውስጥ የነበረውን የሞባይል ስልክ እና ገንዘብ ለመውሰድ ሲሞክሩ የግል ተበዳዮች ወንጀሉን ለመከላከል በሚሞክሩበት ወቅት ገፍትረዋቸው በፍጥነት በመጓዝ ላይ ሳሉ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨት ቆመዋል።
በወቅቱ ድርጊቱን በተመለከተው የአካባቢው ህብረተሰብና በትራፊክ ፖሊስ አማካኝነት በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ትዕግስት ጌታቸው፣ ገነት ደሳለኝ፣ ሜላት ጌታቸው፣ እየሩሳሌም ጌታነህና መአዛ ማሞ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ከ6 የተለያዩ ስማርት ሞባይል ስልኮችና 11 ሚሞሪ ካርዶች ጋር ሊያዙ መቻላቸውን በወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተያዙ ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ምርመራ የማስፋት ተግባር እየተከናወነ ሲሆን ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን የሚፈፅሙ በመሆናቸው በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀል የተፈጸመባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በመቅረብ ስልኮቻቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍8🤣7🙉6
ዘመናዊ ሄሊኮፕተር በኢራን ተመቷል-ትራምፕ‼️
Apache የተሰኘ የአሜሪካ ዘመኒዊ እና ቅንጡ ሄሊኮፍተር በትናትናው ዕለት በሆርሙዝ ፓትሮል እያደረገ ባለበት ሰዓት በኢራን ተመቶ መውደቁን ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው አስፍረዋል።
በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ ሁለቱም አብራሪዎች ከሞት ተርፈዋል ብለዋል።
ኢራን ለፈፀመችው ጥቃት ምላሽ እንሰጣለን ብለዋል። የዚህ ሄሊኮፕተር ዋጋ 67 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ይገመታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8😱4😁3🥰1👏1😢1
ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ተዋጊ ኃይል የበላይ አዛዥ ሆኑ!

ጊዜያዊ መንግስቱን በማፍረስ የራሱን አስተዳደር ያነበረው የሕወሓት ቡድን በትናንትናው ዕለት በክልሉ የሚተገበር አፋኝ ረቂቅ አዋጅ ማጽደቁ ይታወሳል። እንደ ሻብያ ሁሉ ወታደራዊ ግዳጅን ግዴታ የሚያደርገው ይህ አዋጅ ታድያ አንድ ልብ ያልተባለ ስልጣንን ለደብረጽዮን ገብረሚካኤል ሰጥቷል።

አንዳፍታ ሚዲያ በተመለከተው በዚህ አዋጅ ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት የክልሉ ተዋጊ ኃይሎች የበላይ አዛዥ እንዲሆኑ ደንግጓል። በዚህም መሰረት አዋጁ ደብረጽዮንን ከፕሬዝዳንትነታቸው ባለፈ የክልሉ ተዋጊ ኃይል የበላይ አዛዥ አድርጓቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁14👍98🤔5🤪4😢3🥰1🤯1🙈1🙊1
ኮንትሮባንድ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እንዲወረሱ ተወሰነ

መፍትሔ ወይስ ተጨማሪ ስጋት?

​የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮንትሮባንድ ማጓጓዣዎችን እስከ መውረስ የሚያደርስ የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ በሁለት ተቃውሞና በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

ቀደም ሲል የነበረው የ100 ሺህ ብር ቅጣት ማነስ ሕገ-ወጥ ንግዱን ሊያስቆም ባለመቻሉ ማሻሻያው ማስፈለጉ ተገልጿል።

​አዲሱ አዋጅ ዕቃ ለመደበቅ የተለወጡ ወይም ሙሉ በሙሉ ኮንትሮባንድ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ያለዋጋ ግምታቸው ተወርሰው ቀጥታ ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ በግልፅ ደንግጓል።

​የአስመጪዎችን የመከራከር መብት ለማስከበርም፣ ይግባኝ ለመጠየቅ ሙሉ ታክስ መክፈል የነበረበት አሰራር ተቀይሮ አከራካሪውን 50% ብቻ በማስያዝ እንዲከራከሩ ተፈቅዷል።

​ግዴታቸውን ባልተወጡ አጓጓዦችና መጋዘኖች ላይ ጠንከር ያለ አስተዳደራዊ ቅጣት የተጣለ ሲሆን፣ የጥንቃቄ ጉድለት ላሳዩ ባለቤቶችም የገንዘብ መቀጮ ተደንግጓል።

​ተንታኞች ግን አዋጁ የይግባኝ ቅድመ-ሁኔታን ማቃለሉ ለነጋዴው መብት መከበር ትልቅ እመርታ ቢሆንም፣ ተሽከርካሪን ሙሉ በሙሉ መውረስ ግን ንብረታቸው በሾፌሮች ወይም በባለገንዘቦች ለሕገ-ወጥ ተግባር ለሚበዘበዝባቸው  ባለቤቶች ላይ መራራና ያልተመጣጠነ ኪሳራ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤪7👍6👀3👏1
መረጃ‼️

የሚንስትሮች ምክር ቤት ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከ2 ትሪሊዮን 339 ቢሊዮን በላይ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ።

ረቂቅ በጀቱ፣ ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግሥታት ድጋፍ እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል መኾኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ረቂቅ በጀቱ የተዘጋጀው፣ የ2019 የፌዴራል መንግሥት በጀት የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የኾነው የ2019-2021 የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊሲካል ማዕቀፍን መሠረት በማድረግ መኾኑን ተገልጧል።

ለተያዘው በጀት ዓመት የተመደበው 1 ነጥብ 93 ትሪሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮኑ ለመደበኛ ወጪ እና 415 ነጥብ 2 ቢሊዮኑ ለካፒታል ወጪ የተመደበ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🤔14🤪9🙏2👍1👏1👀1
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተወሠኑ የአፍሪካ አገራት ጋር የተፈራረማቸው የጤና ስምምነቶች የሕይወት አድን ድጋፎችን ቁልፍ የጤና መረጃዎችን ለመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች አሳልፎ ከመስጠት ጋር የሚያስተሳስሩ ናቸው በማለት ወቀሠ።

ተቋሙ፣ አሜሪካ በቅርቡ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪይል፣ ሩዋንዳ፣ ላይቤሪያ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ጋር የተፈራረመቻቸውን ስምምነቶች መመርመሩን ገልጧል።

ተቋሙ፣ መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶችን አደጋ ላይ የሚጥሉ የጤና ስምምነቶችን እንዲቀበሉ አሜሪካ እያስገደደች መኾኗን ገልጧል።

የጤና ስምምነቶቹ በግለሰቦች የጤና መረጃዎች ሚስጢራዊነት ላይ ስጋት ሊደቅኑ የሚችሉ ናቸው ያለው ተቋሙ፣ የአሜሪካ መንግሥት ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ እና ኡጋንዳ ጋር የተፈራረማቸውን ስምምነቶች በድረገጹ ላይ ይፋ ካደረገ በኋላ መልሶ አንስቷቸዋል ብሏል።

አሜሪካ፣ ከስምምነቶቹ ጋር በተያያዘ ከአገራቱ ጋር በማዕድን ዙሪያ እያካሄደቻቸው ያሉትን ድርድሮች ይፋ እንድታደርግም ተቋሙ ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍5👏1🤔1😢1🙊1
አሜሪካ ቪዛ በፍጥነት ለማግኘት ለሚፈልጉ መንገደኞች የ750 ዶላር ተጨማሪ ክፍያ የሚጠይቅ አዲስ የሙከራ አሰራር ይፋ አደረገች

​የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰኔ 24 ቀን እስከ ታኅሣሥ 22 ቀን 2019 ዓ.ም የሚቆይ አዲስ የቪዛ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

ይህ አሰራር አመልካቾች ከመደበኛው 185 ዶላር በተጨማሪ 750 ዶላር በመክፈል በ10 ቀናት ውስጥ የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ እንዲያገኙ ያስችላል።

አላማውም በትራምፕ አስተዳደር ጥብቅ የቪዛ ቁጥጥር (የማህበራዊ ሚዲያ ፍተሻ እና እስከ 15,000 ዶላር ዋስትና ማስያዝን ጨምሮ) የመጣውን ከፍተኛ የቀጠሮ መዘግየት መቀነስ ነው።

​ ነገር ግን ይህንን ፕሪሚየም ክፍያ መክፈል የቪዛ መፈቀድን በፍጹም አያረጋግጥም ተብሏል።

​አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው የተመረጡ ኤምባሲዎች ዝርዝር በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍4😁3😢2😱1👀1🙉1🙊1
አሜሪካ ኢራንን ደበደበች‼️
የአሜሪካ ጦር ዛሬ ለሊቱን ኢራንን በመደብደብ 20 የተመረጡ ዒላማዎችን  አውድሟል።
ይህም ኢራን ትላንት በሰው አልባ አጥፍቶ ጠፊ በመጠቀም የአሜሪካንን ሄሊኮፍተር ከጣለች በኋላ የተሰጠ ምላሽ ነው ብለዋል።

ኢራን በበኩሏ ዮርዳኖስንና ሌሎች የዓረብ አገሮችን ደብድባለች።

አሜሪካ ይህንን ጥቃት የፈፀመችው በሶስት ዙር ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😡8👍5👏1🕊1
ወጣቶች እየሸሹ ነው‼️
በትግራይ ክልል በደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የክልሉ አመራር አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን የሚፈቅድና ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስት የሚያቋቁም ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ።
👉ይህን ተከተሎ በርካታ ወጣቶች እየሸሹ ነው።

ረቂቅ አዋጅ፤ ዕድሜው የደረሠ ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ በወታደራዊ ግዳጅ እንዲሳተፍ ግዴታ የሚጥል ሲሆን፤ ጥሪውን የማይቀበል ከ10 ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚጣልበት ደንግጓል።

የክተት ጥሪውን መሸሽ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ሀሰተኛ የሕክምና ማስረጃ የሚሠጡ የጤና ባለሙያዎችም እስከ 50 ሺሕ ብር ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በረቂቁ ላይ ሠፍሯል። ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስቱን በበላይነት የሚመራው የክልሉ ፕሬዝዳንት፣ የተዋጊ ኃይሎች የበላይ አዛዥ እንደሚኾን ተጠቅሷል።

በጦር ግንባር የተከፈለውን መስዋዕትነትና የሕዝቡን ትግል የሚያሳንስ ወይም የሚያጠለሽ ጽሑፍ፣ ንግግር ወይም ምስል ማሰራጨት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣም ተደንግጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13💔11👍3😢3😈3🕊21💋1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ከ3 ጊዜ በላይ ጥቆማ የሚቀርብባቸውና ከታሪፍ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።

ከነዳጅ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ አጠቃላይ ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ የታሪፍ ማሻሻያ ቢደረግም፣ በርካታ አሽከርካሪዎች ከተቀመጠው ታሪፍ ውጪ እያስከፈሉ መሆኑ በጥናት መረጋገጡን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ በሰጠው ገለፃ አስታውቋል።

በመዲናዋ የሚገኙ የሚኒባስ አሽከርካሪዎች ከታሪፍ ውጪ ከማስከፈልም ባለፈ፣ ከተሰጣቸው ስምሪት ውጪ እንደሚያሽከረክሩ የተናገሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው፤ ይህንን ችግር ለመፍታት ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ችግሩን ለመፍታት ካሁን ቀደም በኪሎ ሜትር ይገለጽ የነበረው የጉዞ ታሪፍ ተሳፋሪውን ያወዛግብ እንደነበር አስታውሰው፤ በተያዘው ሰኔ ወር በመነሻና መዳረሻ ላይ ያለውን የጉዞ ታሪፍ የሚገልጽ ዝርዝር እንደሚለጠፍ አስታውቀዋል።

ቢሮው ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ የሚሰራውን የቁጥጥር ስራ በይበልጥ ማሻሻሉን ገልጸው፤ ከ3 ጊዜ በላይ ጥቆማ የሚቀርብባቸውና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ባለፈው የግንቦት ወር ብቻ ከታሪፍ በላይ በማስከፈልና የተቀመጠውን የታሪፍ ዝርዝር ባለመስቀላቸው ከ3 ሺህ 300 በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያመለከቱት ምክትል ኃላፊው፤ የቁጥጥር ስራውን በይበልጥ ለማጠናከር በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት ጊዜያት በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 9417 አጭር የስልክ መስመር አሁን ላይ በርካታ ጥቆማዎችን እየተቀበለበት መሆኑን አቶ ዳኛቸው ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው ግንቦት ወር ብቻ ወደ 400 የሚጠጉ ጥቆማዎችን ማስተናገድ መቻሉንና በ300ዎቹ ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አብራርተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍10👏4👌1🤪1
በኦሮሚያ ክልል ፤ አርሲ ውስጥ በጥቃት አድራሾች የተቃጠለው ቤተክርስቲያን ሊሠራ ነው ተባለ!

«በአርሲ የተቃጠለውን ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን መልሰን እንሠራለን።» -የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከአንድ ሳምንት በፊት ስለተፈጸመው የኦርቶዶክሳውያን ግድያና የቤተ ክርስቲያን መቃጠል ኃዘናቸውን በመግለጥ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ፈቃደኛ መሆናቸውን ማሳወቃቸው ተዘግቧል ።

በኦሮሚያ ክልል፤ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ቀን እና በዋዜማው ግንቦት 23 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በተፈጸመው ጥቃት ንጹሐን ምእመናን መገደላቸው ተዘግቧል ። ከተፈጸመው ግድያ በተጨማሪ ከመቶ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንደተቃጠለ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍9🤪7🥰3🤔3🙏2👏1😍1
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብድር አገኘ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና አለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ጋር ነው የ80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የብድር ስምምነት የተፈራረመው።

በስምምነቱ መሰረት ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የረዥም ጊዜ ብድር ያቀርባል ።

የብድር ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድና የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የአፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮዺስ ተፈራ በኬንያ ናይሮቢ ተፈራርመዋል።

ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በሚገኘው ገንዘብ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ዘመኑን በሚመጥን መልኩ የሚታደስ ሲሆን በሸራተን የንግድ ምልክት የሚጠራ ተጨማሪ አዲስ ሆቴልም ይገነባል።

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የብድር አቅርቦት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነውን የሸራተን አዲስን ገጽታ በእጅጉ እንደሚለውጠው ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍6🤪3👏1😁1🤔1🤯1🙊1
በአገራችን የባንክ ሂሳብ ሊኖራቸው ከሚገባ አዋቂዎች መካከል የባንክ ሂሳብ ያላቸው ከ50 በመቶ በታች ናቸው ተባለ

በ2025 የወጣ የፋይናንሻል ኢንዴክስ ሪፖርት እንዳሳየው በአገራችን የባንክ ሂሳብ ያላቸው አዋቂዎች ቁጥር 49 በመቶ ነው።

በአገራችን በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች የባንክ ሂሳብ የላቸውም ተብሏል።

ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን የማስፋት ንቅናቄ መድረክ ባዘጋጀበት ወቅት ነው።

ከሰኔ 18/2018 እስከ መጋቢት 2019 ዓ.ም የሚቆየው ይህ ንቅናቄ" አካታች የባንክ አገልግሎት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

ይህ አገልግሎት ከፋይናንስ አገልግሎት ተገልለው ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የተዘጋጀ ነው።

በአፋር ፣ ኦሮሚያ ፣ ሶማሌ፣ አማራ እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚገኙ 2መቶ 41 ወረዳዎች ላይ ይተገበራል።

ከግማሽ ሚሊየን በላይ አዳዲስ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ተደራሽ ለማድረግ ይሰራል ያሉት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ናቸው።

በተያዘው ዕቅድ መሰረት 3መቶ 50 ሺህ የሚሆነው የባንክ ሂሳብ በባንክ በኩል ቀሪው 1መቶ 50 ሺው ደግሞ በሲቢኢ ብር በኩል የሚከፈት ይሆናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍3🤪2🙊2
'በአዲስ አበባ በጥበቃ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት ደረሶች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታወቀ‼️
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መጅሊስ በሁለት ደረሶች አሰቃቂ ግድያ ዙሪያ ህብረተሰቡ መግለጫ እስኪሰጥ በትዕግስት እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፏል።

​በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 (ሰሚት ጨርቆስ ኮንዶሚኒየም መግቢያ) በጥበቃ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት ደረሶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው መገኘታቸውን ተከትሎ፣ የክፍለ ከተማው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መረጃዎችን አጠናቅሮ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ ህብረተሰቡ በትዕግሥት እንዲጠብቅ አሳሰበ።

​ሟቾቹ ሙሐመድ አደም እና ሙሐመድ ዓሊ የተባሉ የጥበቃ ሰራተኞች ሲሆኑ፣ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ በመልካም ስነ-ምግባራቸው የሚታወቁ የዲን ተማሪዎች (ደረሶች) እንደነበሩ ተገልጿል። ከሟቾቹ መካከል ሙሐመድ ዓሊ የልጆች አባት መሆኑም ታውቋል።

​ግድያው የተፈፀመው ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ል ሌሊት እንደሆነ የተገመተ ሲሆን፣ አስክሬናቸው ከሁለት ቀናት በኋላ ሰኞ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ል መገኘቱ ተጠቁሟል። ሟቾች የጥበቃ ስራ በሚሰሩበት ስፍራ ምንም ዓይነት የንብረት ስርቆት ወይም የዘረፋ ምልክት አለመገኘቱ የግድያውን አሰቃቂነት አጉልቶታል።

​የሟቾች የቀብር ስነ-ስርዓት ትላንት ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ል በኮልፌ የሙስሊሞች መቃብር ስፍራ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በጉዳዩ ዙሪያ ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ጠቁሞ፣ መረጃዎችን አጠናቅሮ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ በማስታወቅ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በትዕግሥት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢3210👍7😁1🤯1
📍አፍሪካ ህብረት አቅራቢያ መሀል ቡልጋሪያ አዲሱ ትልቁ መስጂድ ጋር ቢፈልጉ በዶላር የሚያከራዩት አልያም በመሃል ከተማ የመኖር ህልምዎን የሚያሳኩበት !
🔥15% ቅድሚያ | 🔥 20% ቅናሽ
☎️ 0928384058 | 0914976944

👉🛏️ባለ 1መኝታ 53 ካሬ =4.2ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ
 👉 🛏️ባለ 1መኝታ 69ካሬ =5.2ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ ባለ 2መኝታ 105 ካሬ =9.2 ሚሊዮን አጠቃላይ ዋጋ
👉🛏️ባለ 3መኝታ 160 =12 ሚሊየን አጠቃላይ ዋጋ

🔥ቅድመ ክፍያ 750,000 ብር !

👉በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ከ20 ካሬ ጀምሮ ከ1-3ኛ ወለል ማግኘት ይችላሉ።
for further
☎️ 0928384058 | 0914976944
6👍2
የጭቃ ቤት ግንባታ ተከለከለ

አሁን ላይ ተፈፃሚ የሆነው በአንድ ክልል ነው በቀጣይ ግን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚተገበር ተነግሯል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ከተሞችን ለማዘመን እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተጣጣመ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት አዲስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል።

ደብዳቤው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በማንኛውም ማዘጋጃ ቤት በኩል የጭቃ ቤት ግንባታ ፈቃድ ማጽደቅ ሙሉ በሙሉ ታግዷል።

በእንጨትና ጭቃ ግንባታ ሳቢያ የሚመጣውን የደን መመናመን ለመግታት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የድርቅና የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ነው።

ማንኛውም ግንባታ ከተማን በሚያዘምኑና ደረጃቸውን በጠበቁ ግብዓቶች ማለትም በብሎኬት፣ በጡብ እና በተሻሻሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቻ መከናወን እንዳለበት ታዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪35🤣2311👍9👀2🤯1😱1🥱1🙊1
ኩዬት ለኢትዮጵያውያን ፈቀደች‼️
ኩዌት ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከ10 ሀገራት የቤት ሰራተኞችን ለመቅጠር ፈቀደች።

የኩዌት የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የቤት ሰራተኞች ቅጥርን የሚቆጣጠር አዲስ መመሪያ ማውጣቱን ዘገባ አመላከተ።

​በአዲሱ መመሪያ መሰረት ኩዌት ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨምሮ ከ10 ሀገራት የቤት ሰራተኞችን (ወንድም ሴትም) ለመቅጠር ፈቅዳለች።

የተፈቀደላቸው ቀሪዎቹ ሀገራት ደቡብ አፍሪካ፣ ቤኒን፣ ፊሊፒንስ፣ ስሪላንካ፣ ሕንድ፣ ቪየትናም፣ ኔፓል እና ሴኔጋል (ለወንዶች ብቻ) ናቸው።

​የቅጥር ሂደቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግም ማመልከቻዎች በየግዛቱ በሚገኙ የአገልግሎት ማዕከላት በኩል እንደሚስተናገዱ የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26👍16😢2🤪2👏1
የደቡብ አፍሪካው ስታንቢክ ባንክ በኢትዮጵያ በብቸኝነት በባለቤትነት የሚያስተዳድረውን ራሱን የቻለ ባንክ ለማቋቋም እያሰበ መኾኑ ተሠማ።

ባንኩ ራሱን የቻለ ባንክ ለማቋቋም ያሰበው፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ የኢንቨስትመንት ወጪ እየቀነሠና ገቢው እየጨመረ መሄዱን እንደ ጥሩ ምሳሌ በመውሠድ እንደኾነ የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ስታንቢክ ባንክ የግዙፉ የደቡብ አፍሪካ ስታንዳርድ ባንክ አንድ ካል ነው።

ብሄራዊ ባንክ ያወጣው ሕግ፣ በአገር ውስጥ ባንክ የአክሲዮን ድርሻ መግዛት የሚፈልጉ የውጭ ባንኮች ድርሻቸው ከ49 በመቶ እንዳይበልጥ ገደብ ይጥላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍3👏1👌1😡1
ብልፅግና ፓርቲ የተወዳደረባቸውን ወንበሮች በሙሉ አሸነፈ

👉 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም የግል ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)  ምንም መቀመጫ አላሸነፉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት እወጃ በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሌሎች 22 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፣ ከተገለጹት ጠቅላላ 48 የምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል ከአንዱ በስተቀር የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች ያሸነፉ ሲሆን፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ዕጩ ደግሞ በሶማሌ የክልል ምክር ቤት አንድ ወንበር ማሸነፉ ታውቋል። በደገ ሀቡር አንዱን ወንበር የኦጋዴን ግንባር ዕጩ የነበሩት አቶ መሀሙድ ሀሰን ሁሴን አሸንፈዋል።

ለክልል ምክር ቤቶች በጠቅላላው የ12 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ውጤቶች ተነግረዋል። የክልል ምክር ቤት ምርጫዎች በየምርጫ ክልሉ ብዙ መቀመጫዎች ያሏቸው በመሆኑ፣ በድምሩ የ38 መቀመጫዎች ውጤት የታወጀ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ ብልፅግና ፓርቲ 37ቱን አሸንፏል።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላላው የ10 የምርጫ ክልሎች/ወንበሮች ውጤት የተገለጸ ሲሆን (1 ከአማራ፣ 3 ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና 6 ከኦሮሚያ)፣ 10ሩንም መቀመጫዎች በሙሉ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች አሸንፈዋል። ውጤታቸው የተገለጹት የምርጫ ክልሎችም በአማራ ክልል ጎዛምን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀዲዳ ጋሜላ 2፣ ጉመር 1 እና እዣ 2 ሲሆኑ፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ሀብሮ 1፣ ቅንበቢት፣ ጥቁር እንጭኒ፣ ጀልዱ፣ ወሊሶ 2 እና ወሊሶ 1 የምርጫ ክልሎች ናቸው።

በውጤት እወጃው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም የግል ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)  ምንም መቀመጫ አላሸነፉም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣7625👍6😁3😢2🤪2👀1🙈1