አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.9K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ሰበር | ኢራን እስራኤል በወሰደችው እርምጃ ምክንያት የባብ አል ማንዳብ የባህር ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ መዝጋቷን አሳወቀች።

12% የሚሆነው የዓለም ንግድ በዚህ በኩል ያልፋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍107😁6🤔4😢4🤪3🕊1🙊1
አየር መንገዱ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ የአነስተኛ አውሮፕላኖች ግዥ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአገር ውስጥ እና ለጎረቤት ሀገራት በረራዎች የሚያገለግሉ አነስተኛ የክልል አውሮፕላኖችን  ለመግዛት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል። 

አዲሶቹ አውሮፕላኖች በአገር ውስጥ የበረራ መስመሮች እና በቅርብ ሀገራት ዙሪያ ያለውን የጉዞ ፍላጎት ይበልጥ ለማሳደግ ታስበው የሚገዙ ናቸው። አየር መንገዱ የትኞቹን የአውሮፕላን አይነቶች ለመግዛት እንዳቀደ እና ምን ያህል ወጪ እንደሚያደርግ በሚቀጥሉት ሳምንታት በሚያደርገው ግምገማ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍7
በኢትዮጵያ የጤና ስጋት የደቀነው የጫት ተጠቃሚነት መጨመር

በኢትዮጵያ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመጣው የጫት ሱስ ስርጭት፣ በአገሪቱ የአእምሮ ጤና ላይ ከባድ አደጋ እየደቀነ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የጫት ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ማደጉ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በሀገሪቱ የወጡ አዳዲስ የቁጥጥር ህጎችን ተከትሎ የአልኮል እና የሲጋራ ተጠቃሚነት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።

ይሁን እንጂ ይህ የቁጥጥር ስራ በጫት ላይ ባለመዘርጋቱ የችግሩን ስፋት አባብሶታል።

ማንኛውም የሱስ ችግር በቀጥታ ከአንጎል ባዮሎጂካዊ አወቃቀር ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለሙያዎቹ ያሳስባሉ።

በተጨማሪም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጫት ቁጥጥር ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1110😁3🤪2💯1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሱዳን
መንገደኞች በዶላር እንዲከፍሉ ወሰነ!


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሱዳን ለሚገዙ የአውሮፕላን ትኬቶች ክፍያ በአሜሪካ ዶላር ብቻ እንዲፈጸም ያሳለፈው ውሳኔ በሀገሪቱ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብትና የሕግ ክርክር አስነስቷል። አየር መንገዱ በፖርት ሱዳን የሱዳንን ፓውንድ መቀበል ያቆመው በሱዳን የገንዘብ ምንዛሬ አለመረጋጋትና ያገኘውን ገቢ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ለማስተላለፍ በመቸገሩ እንደሆነ ገልጿል።

ይህ አዲስ መመሪያ ተጓዦች እጥረት ያለበትን የዶላር ምንዛሬ በጥቁር ገበያ ፍለጋ እንዲንከራተቱ ያስገደደ ሲሆን፣ ይህም በተራው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ቀድሞውኑ የደከመውን የሀገሪቱን የሀገር ውስጥ ገንዘብ ዋጋ ይበልጥ ያዳክመዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

በሌላ በኩል፣ የሱዳን ባለሥልጣናትና የሕግ ባለሙያዎች የአየር መንገዱ ውሳኔ ከሀገሪቱ የፋይናንስ ደንብ ጋር ሊጋጭ ይችላል ሲሉ እየተከራከሩ ነው። እንደ እነሱ ገለጻ፣ ልዩ ፈቃድ ካልተሰጠ በስተቀር በማንኛውም የሀገሪቱ ክልል ውስጥ የሚደረጉ የንግድ ግብይቶች በሙሉ በሱዳን ፓውንድ መፈጸም አለባቸው የሚለውን የሀገር ውስጥ ሕግ የጣሰ ነው።

ይህ አወዛጋቢ እርምጃ በሱዳን ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሌሎች ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ላይም ተመሳሳይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየተነበዩ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15😢3👍2👌1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
4👍2😡1
ምርጫ ቦርድ ነገ በልዩ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ የመስጠት ሂደት እንደሚከናወን ገለጸ

በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች በሚገኙ ልዩ ጣቢያዎች ነገ በልዩ ሁኔታ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት ማስፈጸሙን አውስቷል።

በአሁን ሰዓት ቦርዱ ከምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ወደ ቦርዱ ማዕከል በመምጣት ላይ ያሉ ውጤቶችን የማረጋገጥ፣ የኦዲት ግኝት ያለባቸውን ውጤቶች የመመርመር እንዲሁም የተረጋገጡ ውጤቶችን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ሥራ ላይ እንደሚገኝም አመልክቷል።

በተጨማሪም በፖለቲካ ፓርቲዎችና በግል ዕጩዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን በሕግ ባለሙያ ጉባዔ አማካኝነት የማደራጀትና ምሥክር የመሥማት ሥራ እያከናወነ ነው።

በቀጣይም በተጠቀሰው ሂደት ያለፉ ውጤቶች ለቦርድ ውሣኔ በማቅረብ እና በማፀደቅ በሕጉ መሠረት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ቦርዱ አስታውቋል።

ቦርዱ “በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 17” በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን በማቋቋም የካምፑ ነዋሪዎችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዲሣተፉ በመራጭነት መመዝገቡ ይታወቃል።

በመሆኑም በካምፖቹ በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፅ የመስጠት ሂደት ነገ እንደሚከናወን ቦርዱ በመረጃው አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🤪7👍3😁1
ኢሰመኮ በአርሲ ለተፈጸመው ጥቃት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ተጠያቂ አደረገ፤ ታጣቂ ቡድኑ ክሱን አስተባብሏል!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ የተፈጸሙት ጥቃቶች መንግሥት «ሸኔ» ብሎ በሚጠራው በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የተከወኑ ናቸው ሲል ከሰሰ። ታጣቂ ቡድኑ በበኩሉ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት እንደማይወስድ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ምርመራ ማድረጉን ተከትሎ ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “በቦታው በአካል በመገኘት፣ ከዐይን እማኞች፣ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት መረጃዎችና ማስረጃዎች መሰብሰቡን ገልጿል። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪1513👍7
በሸረሪና የተፈፀመው የድሮን ጥቃት‼️
በዛሬው ዕለት በሱዳን ድንበር የድሮን ጥቃት ከመፈፀሙ በፊት በትናንትናው  እለት የትግራይ አርሚ 13 ኮር 2 ታጣቂዎች በኤርትራ አድርገው በእግር ተጉዘው ወደ ሱዳን ለመሄድ ሸረሪና ደርሰው ነበር።
ከዚህ በተጨማሪ ዛሬ ሁለት ኦራል እና አምስት FSR የጦር መሳሪያ እና ሎጅስቲክስ የጫኑ መኪኖች ወደ ሸረሪና አቅንተው ነበር። በሱዳን የሚገኘው የአርሚ 70 ጦር አዛዥ ታጣቂዎቹን ለመቀበል ለዛሬ ሰኔ 1/2018 ዓ.ም ቀጠሮ ይዘው ነበር።
ዛሬ 5:45 ላይ የኢትዮጵያ አየር ሀይል በድሮን ጥቃት የፈፀመው በዚህ ምክንያት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍139👏3🕊2👌1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
2👍2
ተኩስ‼️
በጋምቤላ ከተማ የክልሉ ፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት አጠገብ ከ 12:20 አንስቶ እስካሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ በከተማዋ የሚኖሩ የአዩዘሀበሻ ቤተሰቦች ገልፀዋል። የተኩሱ መነሻ በግልጽ አልታወቀም ብለዋል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3👍2😢2😱1🙏1
Updateጋምቤላ‼️
የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ተኩስ መክፈቱን ገለፀ‼️
👉
ለሰዓታት በቆየው የተኩስ ልውውጥ የደረሰ ጉዳት ይኑር/አይኑር የገለፀው ነገር የለም።

ከጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በተሰጠ ወቅታዊ መረጃ መሠረት፣ ዛሬ ማምሻውን በጋምቤላ ከተማ ውስጥ በአንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል የተነሳ ያልተጠበቀ የተኩስ ክስተት መፈጠሩን ገልጿል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ የክልሉና የፌዴራል ፀጥታ አካላት በቅንጅት በመንቀሳቀስ ሁኔታው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር ፈጣንና ተገቢ እንቅስቃሴ አድርጓል ብሏል።

በዚህም ሂደት የፀጥታ አካላት ሁኔታውን ለማረጋጋት ባደረጉት ጥረት የተኩስ ልውውጥ መኖሩ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ግን በተደረገው የተቀናጀ የፀጥታ ሥራ ውጥረቱ ሙሉ በሙሉ እንዲረግብ ማድረግ ተችሏል።

በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታም በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለስ ተችሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ በማንኛውም አይነት ወሬ፣ ያልተረጋገጠ መረጃ ወይም አሉባልታ ሳይደናገጥ የዕለት ተዕለት ሥራውንና ማህበራዊ እንቅስቃሴውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6🥰1👏1🤔1😢1👌1🕊1
መረጃ‼️

ከተያዘው ሰኔ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በአፍሪካ ቀንድ ከመደበኛው ያነሰ ዝናብ ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ፣ በተለይ በማዕከላዊ፣ በሰሜን ምስራቅና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ደቡባዊ ሱዳን፣ ሰሜናዊ ኡጋንዳ፣ ከመደበኛው ያነሰ ዝናብ ይጥላል የሚል ከፍ ያለ ትንበያ መኖሩን ጠቅሷል።

በተጠቀሱት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰኔ እና ሐምሌ የአዝመራ መዝሪያ ወቅቶች ናቸው።

ባንጻሩ፣ ደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ አንዳንድ የቀጠናው አካባቢዎች ከፍ ያለ ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ ማዕከሉ ተንብዩዋል።

በመደበኛው ጊዜ ወይም ቀድመው ዝናብ ያገኛሉ ከተባሉት የቀጠናው አካባቢዎች መካከል ደሞ፣ የሰሜናዊ መካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች ይገኙበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🙏7👍2
“ወ/ሮ በረከት ወርቁን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ለችሎት እንዲቀርቡ የጋዜጣ ጥሪ እንዲወጣ ታዘዘ።”

ፖሊስ የሙስና ወንጀል ተከሰው በፖሊስ የፍለጋ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱትን ወ/ሮ በረከት ወርቁን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን ፖሊስ ለፍርድ ቤት ማቅረብ አልቻለም።

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ በ13 ተከሳሾች ላይ የተመሰረተውን ክስ መርምሯል።

በዚህ መዝገብ ውስጥ የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎችም ተካተዋል።

አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ ስልጣናቸውን ከህግ ውጭ በመጠቀምና የመንግስት ሥራን ተገቢ ባልሆነ መንገድ በመምራት ጉዳት አድርሰዋል በሚል ክስ አቅርቧል።

ለዛሬ ተይዞ በነበረው ችሎት ከ6ኛ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር የተመዘገቡ ተከሳሾች ባለመገኘታቸው ሂደቱ ተራዝሟል። ፍርድ ቤቱም እነዚህ ግለሰቦች በጋዜጣ ጥሪ እንዲጠሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በተለይ ወ/ሮ በረከት ወርቁ ከሀገር ውጭ መገኘታቸው በማህበራዊ ሚዲያ በሚታዩ መረጃዎች መጠቆሙን ተከትሎ፣ ጥሪው በአዲስ ዘመን እና በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጦች እንዲታተም ተወስኗል።

ችሎቱ አቃቤ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በማዘዝ፣ የጉዳዩን ቀጣይ ሂደት ለመከታተል ለሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via ሸገር ኤፍኤም

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤪14😁5👍4👏1🤯1🤣1
በፓስተሩ ያልተገባ ድርጊት ህይወቱ ያለፈዉ ወጣት‼️
ዋቅጅራ ገነት ይባላል፡ በምዕራብ ወለጋ የቂልሹ ካራ ተወላጅ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ይኖር የነበረ ለሰርግ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ሰአት በህክምና የልብ ድካም እንዳለበት እና ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለበት ተወሰነ።

የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆነችዉ ፍቅረኛው ህክምናውን ትቶ ፓስተር መሰረት ታዬ የሚባል ግለሰብ ጋር  እንዲሄድ ምክር ትሰጠዋለችሽ። ግለሰቡም ወደ ፓስተሩ ሔዶ   መጀመሪያ የተገጠመለትን የኦክስጅን ገመድ ፓስትሩ አስወገደለት።

"አዲስ ልብ ሰጥቼሃለሁ ተፈውሰሃል" ብሎም ላከው። ዋቅጂራ የሕክምና ባለሙያዎችን ንግግር ችላ ብሎ የነቢዩን ምክር ተቀበለ። በሚያሳዝን ሁኔታም ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የመጣዉ ተስፈኛዉ ወጣት ወደ ቤቱ ለማረፍ እንደገባ እስከወዲያኛዉ አሸለበ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁48🙈28💔14👀138😢8🤔5🤯3🙊3👍2🆒1
በአለም ዋንጫ ታሪክ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ ዳኛ ለመሆን የታጨው ዑመር አርታን ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ተከለከለ

በአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እውቅና ያገኘውና በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ላይ እንዲዳኝ ተመርጦ የነበረው ዑመር አርታን፣ ወደ አሜሪካ ለመግባት ያደረገው የቪዛ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበታል።

ይህ ውሳኔ በሶማሊያ ስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።

​የቪዛው መከልከል ግልፅ ምክንያት ባይቀመጥም፣ ውሳኔው ዳኛው በታሪካዊው መድረክ ላይ የመሳተፍ ህልሙን አደጋ ላይ ጥሎታል።

ፊፋ እና የሶማሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ለማስቀየር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ ጥብቅ የሆነው የአሜሪካ የቪዛ ፖሊሲ ትልቅ ማነቆ ሆኗል።

በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው አርታን፣ ይህ እገዳ ካልተነሳለት ታላቁን የስፖርት መድረክ ያጣዋል።

ቢቢሲ ስፖርት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤣12💔9👍2🤔2
በቤት ጣራ ላይ ሶላር ፓኔል እንዲገጠም የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ

ለጊዜው የሚተገበረው አዲስ በሚገነቡ ቤቶች ላይ ነው ተብሏል።

አዲስ የመኖሪያ ቤቶችና ሕንፃዎችን በሚገነቡበት ወቅት በጣሪያቸው ላይ የሶላር ፓኔል ቴክኖሎጂን እንዲገጥሙ የሚያደርግ አዲስ ብሔራዊ መመሪያ መዘጋጀቱን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከመጪው ሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይህ መመሪያ፣ በሀገሪቱ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት በታዳሽ ኃይል ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ሕጉ ለጊዜው አስገዳጅ ባይሆንም የመጀመሪያ ምዕራፍ ትግበራው በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚጀመር ተገልጿል።

የሶላር ቴክኖሎጂዎች ዋጋ ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም፣ የመግዛት አቅም ለሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች እንደሚዘጋጁ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3021👍5👏1😡1
በመጪው ክረምት የተሻለ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እንደሚኖሩ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመጪው ክረምት ወቅት ሊኖር የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር አስቀድሞ ለመከላከል ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል ።

በአገልግሎቱ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ገበየሁ ሊካሳ የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በዕቅድ የሚቋረጥ የኃይል ማስተካከያ እንደሚኖር መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።

በአዲስ አበባ ከተማ 4ኛው ምዕራፍ የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ሲባል ከመጋቢት ወር ጀምሮ የኃይል መቆራረጥን ከፍ ማለታቸዉን የገለፀው አገልግሎቱ ይህም አስተማማኝና ጥራት ያለዉ የሀይል አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል ።

አብዛኛዉ የዲስትሪቢዩሽን መስመር ረጅም ጊዜ ያገለገለ በመሆኑ ለመልሶ ግንባታው ትልቅ የፋይናንስ አቅምና ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በዕቅድ የሚቋረጥ የኃይል ድግግሞሽ መብዛቱን  አገልግሎቱ ተናግሯል።

በመጪው የክረምት ወቅት የተሻለ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በዕቅድ የሚቋረጡ የፕሮጀክት ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ጨምሮ አስታውቋል ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍3🤔2🤪2😢1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
“ብቻሽን ልትቀሪ ትችያለሽ!” 👉  ዶናልድ ትራምፕ

ትራምፕ ለእስራኤል ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ተሰማ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ መለገሳቸውን ይፋ አድርገዋል። እስራኤል ከኢራን ጋር የምታደርገውን ጦርነት በድጋሚ የምትቀሰቅስ ከሆነ አሜሪካ እንደማትደግፋትና ብቻዋን ልትቀር እንደምትችል ትራምፕ ያስጠነቀቁ ሲሆን ለአክሲዮስ የዜና ወኪል በሰጡት መግለጫም “ቢቢ፤ ጥንቃቄ ብታደርግ ይሻላል፤ ካልሆነ ግን በቅርቡ ብቻህን ልትቀር ትችላለህ” ሲሉ በስልክ ጥሪያቸው ወቅት በግልጽ መናገራቸውን አረጋግጠዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን ማስጠንቀቂያ የሰጡት ቀጥተኛ ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ሳይሆን የኔታንያሁን ውሳኔ ለመገደብ መሆኑን ገልጸው እኔ ያልኩት ነገር ቢኖር አዕምሯችንን መጠቀም አለብን የሚል ብቻ ነው ካሉ በኋላ በአሁኑ ወቅት ከኢራን ጋር በጣም ጠንካራ እና ጥሩ ስምምነት ለመፈረም መቃረባቸውን ጠቁመዋል። በተጨማሪም እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከመፈጸሟ ጥቂት ቀደም ብሎ ለአሜሪካ መንግስት አጭር መረጃ መስጠቷን ትራምፕ ገልጸው ይሁን እንጂ የጦር አውሮፕላኖቹ ቀድሞውኑ ወደ ስምሪት አቅንተው በነበረበት በዚያ አጣዳፊ ሰዓት ጭምር ጣልቃ በመግባት ጥቃቱ ውስን እና የተገደበ እንዲሆን ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።

ይህ በትራምፕ እና በኔታንያሁ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ይፋ የሆነው አሜሪካ ከኢራን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ግፊት እያደረገች ባለችበት ወቅት ሲሆን በአንጻሩ ኔታንያሁ ኢራን በድጋሚ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ጠንካራ ወታደራዊ ርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን በገለጹበት ወቅት በመሆኑ በሁለቱ መሪዎች መካከል ያለው ስትራቴጂካዊ ልዩነት ከቀን ወደ ቀን እየሰፋ መምጣቱን ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🤣15👍6💯2🤪1
ወደ እንግሊዝ ሲያቀኑ የነበሩ 300 ስደተኞች ታግተው ኩላሊታቸዉ እንደሚወጣ እንደተዛተባቸዉ ተሰማ
 
ባለፈው ክረምት ወደ እንግሊዝ ሲያቀኑ የነበሩ ከ300 በላይ ስደተኞች አፈና፣ድብደባ እና በግዳጅ የአካል ክፍሎችን እንደሚነጠቁ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።ወጣቶቹ ከኢራቅ ኩርዲስታን የመጡ ሲሆን ሁሉም በሊቢያ በሚኙ ሚሊሻዎች ከእያንዳንዳቸው ቤተሰቦቻቸው 5,000 ዶላር ለማስለቀቅ የተጠየቁ ሲሆን ገንዘቡን በፍጥነት ካልከፈሉ ኩላሊቶቻቸዉን እንደሚያጡ ተዝቶባቸዉ ነበር፡፡
 
ከእስር የተፈቱትን አንዳንድ ታጋቾች የግዳጅ ስራዎች መፈጸማቸውንም የሚያሳዩ የፎቶ ማስረጃዎችን አጋርተዋል፡፡የቀድሞዎቹ ምርኮኞች የደረሰባቸዉን የስቃይ ማስረጃ አሳይተዋል፡፡ ወደ 180 የሚጠጉ ሰዎች በአንድ ክፍል ውስጥ በጠባብ ሁኔታ ውስጥ እንደቆዩ ተናግረዋል፡፡ቢያንስ አንድ ታጋች የተገደለ ሲሆን ምን ያህሉ በምርኮ እንደሚቀሩ የታወቀ ነገር የለም።
 
ሚሊሻዎቹ በሊቢያ በኩል ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ድረስ ፍልሰተኞቹ እየመራቸው ነበር ተብሏል። ሆኖም የስደተኞቹን ጉዞ ካደራጀው ከኢራቅ የኩርድ ህዝብ-ህገ-ወጥ አዘዋዋሪ ኖህ አሮን ጋር በክፍያ ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር።አሮን አሁን በፈረንሳይ በተለያዩ የገንዘብ ማጭበርበር እና የኮንትሮባንድ ወንጀሎች የ10 አመት እስራት ተፈርዶበታል።
Via_dagu

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢5👍3
ሿሿ ሲሰሩ የተያዙት ሴቶች‼️
የሿሿ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ሳሪስ አቦ የትራፊክ መብራት አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 A 02122 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪና ተጠቃሚ በመምሰል አዲሱ መኮንንና ኢሳያስ ደገፋ የተባሉ የግል ተበዳዮችን በመጫን ጥቂት እንደተጓዙ ኪሳቸው ውስጥ የነበረውን የሞባይል ስልክ እና ገንዘብ ለመውሰድ ሲሞክሩ የግል ተበዳዮች ወንጀሉን ለመከላከል በሚሞክሩበት ወቅት ገፍትረዋቸው በፍጥነት በመጓዝ ላይ ሳሉ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨት ቆመዋል።
በወቅቱ ድርጊቱን በተመለከተው የአካባቢው ህብረተሰብና በትራፊክ ፖሊስ አማካኝነት በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ትዕግስት ጌታቸው፣ ገነት ደሳለኝ፣ ሜላት ጌታቸው፣ እየሩሳሌም ጌታነህና መአዛ ማሞ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ከ6 የተለያዩ ስማርት ሞባይል ስልኮችና 11 ሚሞሪ ካርዶች ጋር ሊያዙ መቻላቸውን በወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተያዙ ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ምርመራ የማስፋት ተግባር እየተከናወነ ሲሆን ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን የሚፈፅሙ በመሆናቸው በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀል የተፈጸመባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በመቅረብ ስልኮቻቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍8🤣7🙉6