አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.9K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የመካከለኛው ምስራቅ ሰማይ እሳት ለብሷል!

ኢራን በደርዘን የሚቆጠሩ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷ ቀጣናው ወደ ከባድ ጦርነት እያመራ ነው።

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ወደለየለት ቀውስ ተቀይሯል።

የኢስራኤል መከላከያ ሰራዊት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በሰጠው እጅግ አስቸኳይ መግለጫ ኢራን በርካታ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን በቀጥታ ወደ እስራኤል መተኮሷን ይፋ አድርጓል።

በአሁኑ ሰአት በሰሜናዊ የእስራኤል ከተሞች የአየር አደጋ ማስጠንቀቂያ ደወሎች በከፍተኛ ሁኔታ እያስተጋቡ ሲሆን ህዝቡ በአስቸኳይ ወደ መከላከያ መጠለያዎች እንዲገባ ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል።

ይህ መጠነ-ሰፊ ጥቃት የተሰነዘረው እስራኤል ዛሬ ማለዳ ላይ በሊባኖስ ቤይሩት ዳሂዬህ አካባቢ ላይ ለፈጸመችው ከባድ የአየር ድብደባ ማዕበል ኢራን የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ በይፋ ከዛተች በኋላ ነው።

ሁኔታውን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ትኩረት የሳበ ሲሆን እንደ ኳታር ያሉ የጎረቤት ሀገራት የንግድ አውሮፕላኖቻቸው የኢራንን የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲቀይሩና እንዲርቁ በአስቸኳይ እያዘዙ ነው።

ይህ የኢራን እርምጃ የቀጣናውን ጦርነት ወዴት ሊመራው ይችላል? እስራኤልስ ምን ዓይነት ከባድ የአጸፋ እርምጃ ትወስድ ይሆን የሚለው መላውን ዓለም በስጋት ውስጥ ጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
36👍5🕊3👏1😢1💔1🤪1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስራኤል የአፀፋ ምላሽ ሰጠች‼️
በትናንትናው ዕለት ምሽት ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳይል መተኮሷን ተከትሎ
በቀጠናው የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ቤዞች እና እስራኤል በጋራ በመሆን በኢራን አስራ አምስት ቦታዎች እንዲመቱ ፔንታጐን ይፋ አድርጓል።
📌ቴህራን አየር ማረፊያ
📌ናጃፋባድ ድሮን መሰብሰቢያ ቦታ
📌በመሪዎች ላይ የግድያ ሙከራዎች / IRGC ግቢ
📌የታብሪዝ የባለስቲክ ሚሳኤል ጣቢያ እንዲመቱ ፔንታጐን አሳውቋል።
እስራኤል በቴህራን የተለያዩ ቦታዎች ላይ ድብደባ ፈፅማለች።
ምስል:- ቴህራን

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
32👍4🤔3🥱3😡3👏1👌1
የነዳጅ ዋጋ በሶስት ዶላር ጨመረ።

የኢራን እና የእስራኤል ግጭት ማገርሸቱን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

ኢራን ትናንት በእስራኤል ላይ የፈፀመችው ጥቃት ለነዳጅ ዋጋው መጨመር "ቀዳሚ" ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም አንድ በርሚል ያልተጣራ ነዳጅ ሲሸጥበት ከነበረው 93.41 ዶላር ወደ 96.24 ዶላር ከፍ ብሏል።

የነዳጅ ዋጋ ከባለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ በ50% ጭማሪ አሳይቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍2😢2🙏2
ሰበር | ኢራን እስራኤል በወሰደችው እርምጃ ምክንያት የባብ አል ማንዳብ የባህር ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ መዝጋቷን አሳወቀች።

12% የሚሆነው የዓለም ንግድ በዚህ በኩል ያልፋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍107😁6🤔4😢4🤪3🕊1🙊1
አየር መንገዱ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ የአነስተኛ አውሮፕላኖች ግዥ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአገር ውስጥ እና ለጎረቤት ሀገራት በረራዎች የሚያገለግሉ አነስተኛ የክልል አውሮፕላኖችን  ለመግዛት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል። 

አዲሶቹ አውሮፕላኖች በአገር ውስጥ የበረራ መስመሮች እና በቅርብ ሀገራት ዙሪያ ያለውን የጉዞ ፍላጎት ይበልጥ ለማሳደግ ታስበው የሚገዙ ናቸው። አየር መንገዱ የትኞቹን የአውሮፕላን አይነቶች ለመግዛት እንዳቀደ እና ምን ያህል ወጪ እንደሚያደርግ በሚቀጥሉት ሳምንታት በሚያደርገው ግምገማ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍7
በኢትዮጵያ የጤና ስጋት የደቀነው የጫት ተጠቃሚነት መጨመር

በኢትዮጵያ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመጣው የጫት ሱስ ስርጭት፣ በአገሪቱ የአእምሮ ጤና ላይ ከባድ አደጋ እየደቀነ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የጫት ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ማደጉ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በሀገሪቱ የወጡ አዳዲስ የቁጥጥር ህጎችን ተከትሎ የአልኮል እና የሲጋራ ተጠቃሚነት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።

ይሁን እንጂ ይህ የቁጥጥር ስራ በጫት ላይ ባለመዘርጋቱ የችግሩን ስፋት አባብሶታል።

ማንኛውም የሱስ ችግር በቀጥታ ከአንጎል ባዮሎጂካዊ አወቃቀር ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለሙያዎቹ ያሳስባሉ።

በተጨማሪም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጫት ቁጥጥር ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1110😁3🤪2💯1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሱዳን
መንገደኞች በዶላር እንዲከፍሉ ወሰነ!


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሱዳን ለሚገዙ የአውሮፕላን ትኬቶች ክፍያ በአሜሪካ ዶላር ብቻ እንዲፈጸም ያሳለፈው ውሳኔ በሀገሪቱ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብትና የሕግ ክርክር አስነስቷል። አየር መንገዱ በፖርት ሱዳን የሱዳንን ፓውንድ መቀበል ያቆመው በሱዳን የገንዘብ ምንዛሬ አለመረጋጋትና ያገኘውን ገቢ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ለማስተላለፍ በመቸገሩ እንደሆነ ገልጿል።

ይህ አዲስ መመሪያ ተጓዦች እጥረት ያለበትን የዶላር ምንዛሬ በጥቁር ገበያ ፍለጋ እንዲንከራተቱ ያስገደደ ሲሆን፣ ይህም በተራው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ቀድሞውኑ የደከመውን የሀገሪቱን የሀገር ውስጥ ገንዘብ ዋጋ ይበልጥ ያዳክመዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

በሌላ በኩል፣ የሱዳን ባለሥልጣናትና የሕግ ባለሙያዎች የአየር መንገዱ ውሳኔ ከሀገሪቱ የፋይናንስ ደንብ ጋር ሊጋጭ ይችላል ሲሉ እየተከራከሩ ነው። እንደ እነሱ ገለጻ፣ ልዩ ፈቃድ ካልተሰጠ በስተቀር በማንኛውም የሀገሪቱ ክልል ውስጥ የሚደረጉ የንግድ ግብይቶች በሙሉ በሱዳን ፓውንድ መፈጸም አለባቸው የሚለውን የሀገር ውስጥ ሕግ የጣሰ ነው።

ይህ አወዛጋቢ እርምጃ በሱዳን ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሌሎች ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ላይም ተመሳሳይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየተነበዩ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15😢3👍2👌1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
4👍2😡1
ምርጫ ቦርድ ነገ በልዩ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ የመስጠት ሂደት እንደሚከናወን ገለጸ

በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች በሚገኙ ልዩ ጣቢያዎች ነገ በልዩ ሁኔታ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት ማስፈጸሙን አውስቷል።

በአሁን ሰዓት ቦርዱ ከምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ወደ ቦርዱ ማዕከል በመምጣት ላይ ያሉ ውጤቶችን የማረጋገጥ፣ የኦዲት ግኝት ያለባቸውን ውጤቶች የመመርመር እንዲሁም የተረጋገጡ ውጤቶችን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ሥራ ላይ እንደሚገኝም አመልክቷል።

በተጨማሪም በፖለቲካ ፓርቲዎችና በግል ዕጩዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን በሕግ ባለሙያ ጉባዔ አማካኝነት የማደራጀትና ምሥክር የመሥማት ሥራ እያከናወነ ነው።

በቀጣይም በተጠቀሰው ሂደት ያለፉ ውጤቶች ለቦርድ ውሣኔ በማቅረብ እና በማፀደቅ በሕጉ መሠረት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ቦርዱ አስታውቋል።

ቦርዱ “በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 17” በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን በማቋቋም የካምፑ ነዋሪዎችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዲሣተፉ በመራጭነት መመዝገቡ ይታወቃል።

በመሆኑም በካምፖቹ በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፅ የመስጠት ሂደት ነገ እንደሚከናወን ቦርዱ በመረጃው አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🤪7👍3😁1
ኢሰመኮ በአርሲ ለተፈጸመው ጥቃት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ተጠያቂ አደረገ፤ ታጣቂ ቡድኑ ክሱን አስተባብሏል!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ የተፈጸሙት ጥቃቶች መንግሥት «ሸኔ» ብሎ በሚጠራው በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የተከወኑ ናቸው ሲል ከሰሰ። ታጣቂ ቡድኑ በበኩሉ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት እንደማይወስድ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ምርመራ ማድረጉን ተከትሎ ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “በቦታው በአካል በመገኘት፣ ከዐይን እማኞች፣ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት መረጃዎችና ማስረጃዎች መሰብሰቡን ገልጿል። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪1513👍7
በሸረሪና የተፈፀመው የድሮን ጥቃት‼️
በዛሬው ዕለት በሱዳን ድንበር የድሮን ጥቃት ከመፈፀሙ በፊት በትናንትናው  እለት የትግራይ አርሚ 13 ኮር 2 ታጣቂዎች በኤርትራ አድርገው በእግር ተጉዘው ወደ ሱዳን ለመሄድ ሸረሪና ደርሰው ነበር።
ከዚህ በተጨማሪ ዛሬ ሁለት ኦራል እና አምስት FSR የጦር መሳሪያ እና ሎጅስቲክስ የጫኑ መኪኖች ወደ ሸረሪና አቅንተው ነበር። በሱዳን የሚገኘው የአርሚ 70 ጦር አዛዥ ታጣቂዎቹን ለመቀበል ለዛሬ ሰኔ 1/2018 ዓ.ም ቀጠሮ ይዘው ነበር።
ዛሬ 5:45 ላይ የኢትዮጵያ አየር ሀይል በድሮን ጥቃት የፈፀመው በዚህ ምክንያት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍139👏3🕊2👌1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
2👍2
ተኩስ‼️
በጋምቤላ ከተማ የክልሉ ፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት አጠገብ ከ 12:20 አንስቶ እስካሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ በከተማዋ የሚኖሩ የአዩዘሀበሻ ቤተሰቦች ገልፀዋል። የተኩሱ መነሻ በግልጽ አልታወቀም ብለዋል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3👍2😢2😱1🙏1
Updateጋምቤላ‼️
የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ተኩስ መክፈቱን ገለፀ‼️
👉
ለሰዓታት በቆየው የተኩስ ልውውጥ የደረሰ ጉዳት ይኑር/አይኑር የገለፀው ነገር የለም።

ከጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በተሰጠ ወቅታዊ መረጃ መሠረት፣ ዛሬ ማምሻውን በጋምቤላ ከተማ ውስጥ በአንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል የተነሳ ያልተጠበቀ የተኩስ ክስተት መፈጠሩን ገልጿል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ የክልሉና የፌዴራል ፀጥታ አካላት በቅንጅት በመንቀሳቀስ ሁኔታው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር ፈጣንና ተገቢ እንቅስቃሴ አድርጓል ብሏል።

በዚህም ሂደት የፀጥታ አካላት ሁኔታውን ለማረጋጋት ባደረጉት ጥረት የተኩስ ልውውጥ መኖሩ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ግን በተደረገው የተቀናጀ የፀጥታ ሥራ ውጥረቱ ሙሉ በሙሉ እንዲረግብ ማድረግ ተችሏል።

በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታም በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለስ ተችሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ በማንኛውም አይነት ወሬ፣ ያልተረጋገጠ መረጃ ወይም አሉባልታ ሳይደናገጥ የዕለት ተዕለት ሥራውንና ማህበራዊ እንቅስቃሴውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6🥰1👏1🤔1😢1👌1🕊1
መረጃ‼️

ከተያዘው ሰኔ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በአፍሪካ ቀንድ ከመደበኛው ያነሰ ዝናብ ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ፣ በተለይ በማዕከላዊ፣ በሰሜን ምስራቅና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ደቡባዊ ሱዳን፣ ሰሜናዊ ኡጋንዳ፣ ከመደበኛው ያነሰ ዝናብ ይጥላል የሚል ከፍ ያለ ትንበያ መኖሩን ጠቅሷል።

በተጠቀሱት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰኔ እና ሐምሌ የአዝመራ መዝሪያ ወቅቶች ናቸው።

ባንጻሩ፣ ደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ አንዳንድ የቀጠናው አካባቢዎች ከፍ ያለ ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ ማዕከሉ ተንብዩዋል።

በመደበኛው ጊዜ ወይም ቀድመው ዝናብ ያገኛሉ ከተባሉት የቀጠናው አካባቢዎች መካከል ደሞ፣ የሰሜናዊ መካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች ይገኙበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🙏7👍2
“ወ/ሮ በረከት ወርቁን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ለችሎት እንዲቀርቡ የጋዜጣ ጥሪ እንዲወጣ ታዘዘ።”

ፖሊስ የሙስና ወንጀል ተከሰው በፖሊስ የፍለጋ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱትን ወ/ሮ በረከት ወርቁን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን ፖሊስ ለፍርድ ቤት ማቅረብ አልቻለም።

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ በ13 ተከሳሾች ላይ የተመሰረተውን ክስ መርምሯል።

በዚህ መዝገብ ውስጥ የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎችም ተካተዋል።

አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ ስልጣናቸውን ከህግ ውጭ በመጠቀምና የመንግስት ሥራን ተገቢ ባልሆነ መንገድ በመምራት ጉዳት አድርሰዋል በሚል ክስ አቅርቧል።

ለዛሬ ተይዞ በነበረው ችሎት ከ6ኛ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር የተመዘገቡ ተከሳሾች ባለመገኘታቸው ሂደቱ ተራዝሟል። ፍርድ ቤቱም እነዚህ ግለሰቦች በጋዜጣ ጥሪ እንዲጠሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በተለይ ወ/ሮ በረከት ወርቁ ከሀገር ውጭ መገኘታቸው በማህበራዊ ሚዲያ በሚታዩ መረጃዎች መጠቆሙን ተከትሎ፣ ጥሪው በአዲስ ዘመን እና በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጦች እንዲታተም ተወስኗል።

ችሎቱ አቃቤ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በማዘዝ፣ የጉዳዩን ቀጣይ ሂደት ለመከታተል ለሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via ሸገር ኤፍኤም

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤪14😁5👍4👏1🤯1🤣1
በፓስተሩ ያልተገባ ድርጊት ህይወቱ ያለፈዉ ወጣት‼️
ዋቅጅራ ገነት ይባላል፡ በምዕራብ ወለጋ የቂልሹ ካራ ተወላጅ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ይኖር የነበረ ለሰርግ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ሰአት በህክምና የልብ ድካም እንዳለበት እና ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለበት ተወሰነ።

የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆነችዉ ፍቅረኛው ህክምናውን ትቶ ፓስተር መሰረት ታዬ የሚባል ግለሰብ ጋር  እንዲሄድ ምክር ትሰጠዋለችሽ። ግለሰቡም ወደ ፓስተሩ ሔዶ   መጀመሪያ የተገጠመለትን የኦክስጅን ገመድ ፓስትሩ አስወገደለት።

"አዲስ ልብ ሰጥቼሃለሁ ተፈውሰሃል" ብሎም ላከው። ዋቅጂራ የሕክምና ባለሙያዎችን ንግግር ችላ ብሎ የነቢዩን ምክር ተቀበለ። በሚያሳዝን ሁኔታም ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የመጣዉ ተስፈኛዉ ወጣት ወደ ቤቱ ለማረፍ እንደገባ እስከወዲያኛዉ አሸለበ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁48🙈28💔14👀138😢8🤔5🤯3🙊3👍2🆒1
በአለም ዋንጫ ታሪክ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ ዳኛ ለመሆን የታጨው ዑመር አርታን ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ተከለከለ

በአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እውቅና ያገኘውና በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ላይ እንዲዳኝ ተመርጦ የነበረው ዑመር አርታን፣ ወደ አሜሪካ ለመግባት ያደረገው የቪዛ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበታል።

ይህ ውሳኔ በሶማሊያ ስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።

​የቪዛው መከልከል ግልፅ ምክንያት ባይቀመጥም፣ ውሳኔው ዳኛው በታሪካዊው መድረክ ላይ የመሳተፍ ህልሙን አደጋ ላይ ጥሎታል።

ፊፋ እና የሶማሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ለማስቀየር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ ጥብቅ የሆነው የአሜሪካ የቪዛ ፖሊሲ ትልቅ ማነቆ ሆኗል።

በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው አርታን፣ ይህ እገዳ ካልተነሳለት ታላቁን የስፖርት መድረክ ያጣዋል።

ቢቢሲ ስፖርት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤣12💔9👍2🤔2
በቤት ጣራ ላይ ሶላር ፓኔል እንዲገጠም የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ

ለጊዜው የሚተገበረው አዲስ በሚገነቡ ቤቶች ላይ ነው ተብሏል።

አዲስ የመኖሪያ ቤቶችና ሕንፃዎችን በሚገነቡበት ወቅት በጣሪያቸው ላይ የሶላር ፓኔል ቴክኖሎጂን እንዲገጥሙ የሚያደርግ አዲስ ብሔራዊ መመሪያ መዘጋጀቱን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከመጪው ሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይህ መመሪያ፣ በሀገሪቱ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት በታዳሽ ኃይል ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ሕጉ ለጊዜው አስገዳጅ ባይሆንም የመጀመሪያ ምዕራፍ ትግበራው በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚጀመር ተገልጿል።

የሶላር ቴክኖሎጂዎች ዋጋ ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም፣ የመግዛት አቅም ለሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች እንደሚዘጋጁ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3021👍5👏1😡1