አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
414 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
መረጃ‼️

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዲራህማን ዳሂግ ባካል፣ ሶማሊላንድ በባሕር በር ዙሪያ አሁንም ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር ዝግጁ መኾኗን ለሪፖርተር በሠጡት ቃለ ምልልስ ገለጡ።

ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መብት አላት ብላ ሶማሊላንድ እንደምታምን የተናገሩት ባካል፣ ኢትዮጵያ በርበራ ወደብን እንደፈለገች መጠቀም ትችላለች ማለታቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል።

ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ አግኝቻለሁ ያለችው የ19 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ባካል ኢትዮጵያ ወደቡን በሙሉ አቅሙ እስካሁን አልተጠቀመችበትም የሚል አጭር ምላሽ መስጠታቸውን ተገልጧል።

ኢትዮጵያ የሶማሊላንድን ቁልፍ አጋርነት ከግምት አስገብታ አንድ ቀን ለሶማሊላንድ እውቅና ትሠጣለች የሚል እምነት እንዳላቸው ባካል የገለጡት ሲኾን፣ ኾኖም ኢትዮጵያ እውቅና እንድትሠጣት ሶማሊላንድ ግፊት ማድረግ እንደማትፈልግ ተናግረዋል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22🥰6👍2👏1
የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና በማውጣት መምህራንን የሚያግዝ Application ወደ ሥራ አስገባ 🔥

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የሥራ ጫና ለመቀነስ እና የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” (Agentic AI Teacher Assistant) የተሰኘ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አውሏል።

ይህ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ ያለኢንተርኔት የሚሰራ ሲሆን፣ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ ቴክኖሎጂ ላይ ሳይመሰረት በአካባቢያዊ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተጭኖ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

በተጨማሪም መተግበሪያው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን መጽሐፍት በሙሉ ዳታሴት በመውሰድና በማስተካከል የተዘጋጀ ነው።

በመተግበሪያው ምን ምን ነገሮች ማከናወን ይቻላል ?

- የትምህርት እቅድ (Lesson Plan) ማዘጋጀት፣

- ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን ማመንጨት፣

- የማስተማሪያ ስልቶችን በራሱ ማቀናጀት ይችላል።

በማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ የሚሰራ ቀላል ሞዴልበማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ የሚሰራ ነውም ተብሎለታል።

በኢንተርኔት ኔትወርክ በሌላቸው የገጠርና ራቅ ያሉ አካባቢዎች ያለምንም ወጪ እና መቆራረጥ በመስራትም በከተማና በገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ያጠባል ተብሎ ታምኖበታል።

በሙከራ ደረጃ የሚገኘው ይኸው መተግበሪያ ቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎቹ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ የትምህርት ለውጥ ኦፕሬሽን (ETOL) ፕሮጀክት ድጋፍ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2615👍5👏1🤪1
ሰኔና ሰኞ‼️
“ሰኔ እና ሰኞ” ሲገጥሙ ጥፋት ይከተላል የሚለው ልማዳዊ ፍርሃት መሰረተ ቢስ መሆኑን ባለሙያዎች ገለጹ‼️

በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ዘንድ "ሰኔ እና ሰኞ" መግጠማቸው እንደ መጥፎ ዕድል ወይም የጥፋት ምልክት ተደርጎ የመወሰድ ልማድ ለዘመናት ሲነገር ቆይቷል። ሐሳባቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት የታሪክ ባለሙያው አቶ በላይ ስጦታው፣ ቀናቱ መግጠማቸው በራሱ የሚፈጥረው ምንም ዓይነት ለየት ያለ ጥፋት እንደሌለና ማህበረሰቡ እነዚህን መሰረተ ቢስ ልማዳዊ አመለካከቶች ሊቀይር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በታሪክ ሂደት ውስጥ ሰኔ እና ሰኞ የገጠሙባቸው በርካታ ዓመታት ተመዝግበዋል። በእነዚህ ዓመታትም ሆኑ በሌሎች ወቅቶች በርካታ ጉዳዮችን መነሻ ያደረጉ አውዳሚ ጦርነቶችና ከዚያም የከፋ አሰቃቂ ክስተቶች መከሰታቸውን ታሪክን በማጣቀስ አብራርተዋል። ነገር ግን ክስተቶቹ በቀጥታ ሰኔ ወር ከሰኞ ከመግጠሙ ጋር ሳይሆን ልክ እንደ ሌሎች ቀናት የገጠሙ ተራ ክስተቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። የሰኔ እና ሰኞ ክስተቶች መፈጠር የሰዎች ውሳኔና የተፈጥሮ መስተጋብር ውጤቶች እንጂ ቀናትን ተከትለው የሚመጡ ባለመሆናቸው፣ ማህበረሰቡ ከሰኔ እና ሰኞ ጋር ተያይዘው የሚነገሩ ልማዳዊ ፍርሃቶችን አስቀርቶ፣ ወቅቱን ለተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ሊጠቀምበት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ሌላኛው ያነጋገራቸው የፎክሎር ባለሙያ አቶ ንጉሡ ወዳጅነህ እንደሚሉት፣ ይህ አባባል ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ድጋፍም ሆነ ሳይንሳዊ ማስረጃ የሌለው መሆኑን አንስተዋል። አባባሉ በማኅበረሰቡ ዘንድ እስከ አሁን ድረስ በስፋት ጥቅም ላይ ሊውል የቻለበት በርካታ ምክንያቶች መኖራቸውን በመጠቆም፤ ለማሳያነትም ከሰኔ እና ሰኞ መገጣጠም ጋር ተያይዘው የተመዘገቡ አጋጣሚዎች ማህበረሰቡ ነገሮቹን እንዲያያይዛቸው ማድረጉን ጠቁመዋል።

እንደ መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘገባ በኢትዮጵያ በረጅም ዓመታት ታሪክ ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም መጥፎ ድርጊቶች ተከትለው እንደሚመጡ በማህበረሰቡ ዘንድ ቢታመንም፤ ይህ ግን ምንም ዓይነት መሠረት የሌለው መሆኑን ባለሙያዎቹ አመላክተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1412😁5🤪3🤯2😡2👏1👌1🤡1
ኤርትራ ስለ ፅምዶ ደብዳቤ ፃፈች‼️
ኤርትራ 'ፅምዶ በህዝቡ የመጣ እንጂ በመሪዎች አይደለም' የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላከች።

ኤርትራ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ (ዩኤንኤስጂ) የላከችው ደብዳቤ ምስጋና በማቅረብ የጀመረ ሲሆን ከፌዴራል መንግሥቱ እውቅና ውጪ በኤርትራ እና ትግራይ "በማህበረሰብ ላይ የተመሰረተ ከአንድ አመት በላይ ተከታታይ የህዝብ ለህዝብ ውይይት፣ የማህበረሰብ ውይይቶች፣ የባህል ልውውጦች እና በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ተግባራት “ጽምዶ ንሰላም"(መተሳሰብ ለሰላም) በሚል ሀገር በቀል መሪ ቃል  መጀመሩን ገልጿል።

ይህ ህዝባዊ ዘመቻ እምነትን መልሶ ለመገንባት፣ ማህበራዊ ትስስርን ወደነበረበት ለመመለስ እና በአመታት ግጭት እና መለያየት ህይወታቸው በእጅጉ የተጎዳ ማህበረሰቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው ብሏል።

የፅምዶ ጠቀሜታ በእንቅስቃሴው ላይ ብቻ ሳይሆን በኦርጋኒክ እና በአካባቢው ባለቤትነት ላይ ነው፣በእራሳቸው የማህበረሰቡ አባላት የሚመራ፣ በዋናነት በጋራ ድንበሮች የሚኖሩ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ቤተሰቦች፣ በውይይት እና ቀጥተኛ ሰብዓዊ ተሳትፎ መግባባትን፣ ፈውስ እና አብሮ መኖርን ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነትን ያሳያል።

በባህላዊ እሴቶች፣ በመከባበር እና በጋራ ኃላፊነት በተመሰረቱ ተግባራዊ ተግባራት እርቅን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል ያሳያል።

ውጥኑ የተባበሩት መንግስታት ሰላምን ለማስቀጠል እና ህዝብን ያማከለ የሰላም ግንባታን የሚደግፉ መርሆዎች ትርጉም ያለው ምሳሌ ይሰጣል።

ለዚህ ማሳያ ይሆናል የተባለ ተጓዳኝ ቪዲዮ ከደብዳቤው ጋር አብሮ መላኩን በደብዳቤው ላይ ተጠቅሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14🤪14👍8🥰3😎1
በቲቤት ሰማይ ላይ የታየው አስደናቂውና አስፈሪው የደመቀ ቀይ ብርሃን‼️

ከሰማይ ወደ መሬት ሳይሆን ከመሬት ወደ ጠፈር የሚተኮሰው ያልተለመደው መብረቅ።

ቲቤት በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኝ፣ ከኔፓል፣ ህንድ እና ቡታን ጋር የምትካለልና እጅግ ሰፊ በሆነው የኪንግሃይ-ቲቤት እምብርት ላይ ያለች ከፍተኛ ተራራማ ቀጠና ናት።

በአማካይ ከባህር ጠለል በላይ ከ4,000 እስከ 5,000 ሜትር ከፍታ ላይ በመገኘቷ "የዓለም ጣሪያ" (Roof of the World) በሚል ስያሜ ትታወቃለች።

በዚሁ ልዩ ስፍራ በቅርቡ በቲቤት ሻናን ክልል በሚገኘውና ከባህር ጠለል በላይ ከ5,000 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው ፑማ ዩምኮ ሐይቅ (Lake Puma Yumco) አቅራቢያ በተከሰተ ኃይለኛ የነጎድጓድ ማዕበል ላይ እጅግ አስደናቂ እና አስፈሪ የሆነ የበራ ቀይ የብርሃን ምሰሶ ብልጭታ በቪዲዮ ተቀርጾ ወጥቷል።

የሳይንስ ልብ-ወለድ ፊልም የሚመስለውና "ሬድ ስፕራይትስ" (Red Sprites) በመባል የሚታወቀው ይህ ክስተት፣ ልክ እንደ ግዙፍ የባህር እንስሳ ቅርፅ ያላቸው የብርሃን ዘንጎች ወደ ጠፈር ሲዘረጉ ታይቷል።

ክስተቱን በከፍተኛ ጥራት የቀረጸው ዶንግ ሹቻንግ የተባለ የቻይና የሥነ-ፈለክ ተመራማሪና ፎቶግራፍ አንሺ ሲሆን፤ ክስተቱ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ይህ ክስተት በተለምዶ እኛ ከምናየው መብረቅ እጅግ በጣም የተለየ ሲሆን የሚከሰተውም ከምድር ገጽ ከ50 እስከ 90 ኪሎ ሜትር ከፍታ ባለው የከባቢ አየር ክፍል ላይ ነው።

ከታች ባለው ደመና ውስጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ብልጭታ ሲከሰትና ከደመናው በላይ ባለው የላይኛው ከባቢ አየር ላይ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስክ ሲፈጥር የሚመጣ ነው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🙉5👍3🤔1
አሻራ መስጠት ሊቀር ነው‼️
ለፓስፖርት በአካል አሻራ መስጠት ሊቀር ነው

📌ዜጎች ፓስፖርታቸውን ቤት ሆነው መጨረስ ይችላሉ ተብሏል።

​የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተገልጋዮች ለአሻራ በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቸው የፓስፖርት አገልግሎትን በኦንላይን ብቻ ማግኘት የሚችሉበት አዲስ አሰራር እየዘረጋ መሆኑን አስታወቀ።

​የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት እንደገለጹት፣ አዲሱን አሰራር ለመተግበር የፓስፖርት ሲስተሙ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር እየተቀናጀ ይገኛል።

ይህም ዜጎች በፋይዳ ላይ ያለውን መረጃ በቀጥታ በመጠቀም ከቤታቸው ሳይወጡ ፓስፖርታቸውን በእጃቸው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

​በተጨማሪም በኦንላይን ምዝገባ ስም የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን ለመከላከል፣ አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ሆኖ ከ10 በላይ ሰዎችን መመዝገብ እንዳይችል ጥብቅ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱን ተቋሙ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2818👏10👌2🤣2🥰1🎉1😍1
በዓፋር ሰደድ እሳት መነሳቱን ተዘገበ

በአፋር ክልል በራህሌ ወረዳ ዳትጋራብ ጫካ ውስጥ ሰደድ እሳት መነሳቱን ወረዳው አስታውቋል።

የአደጋው መንስኤ እስካሁን አልታወቀም ብለዋል።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስፍራው ባለመኖራቸው አደጋውን መቆጣጠር አልተቻለም ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢83👍3😱1👀1
ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ ተቋም የሚሰጠውን የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ለናይጄሪያው የፋይናንስ ግዙፍ ተቋም ‘ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ’ መስጠቱን በይፋ አስታወቀ።

​ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የተሰጠው ይህ ፈቃድ፤ ባለሥልጣኑ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ለወራት ያደረጉትን ጥብቅ የሕግና የሰነድ ምርመራ ተከትሎ የተሰጠ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክር ሀና ተኸልኩ በተለይ ለካፒታል ጋዜጣ ተናግረዋል።

ዩናይትድ ካፒታል ‘ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር’ የተሰኘ ሙሉ በሙሉ የራሱ የሆነ የአካባቢው ቅርንጫፍ በመክፈት ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ ያካበተውን የአፍሪካ አቀፍ ልምድ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል።

​ባለስልጣኑ እንደገለፀው ፤ ይህ ሙሉ በሙሉ በውጭ ተቋም ባለቤትነት የተያዘ ፈቃድ መሰጠቱ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽን ማሻሻያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ማረጋገጫ ነው። ተቋሙ በሕግ ከተቀመጠው የ25 ሚሊዮን ብር አነስተኛ ካፒታል በላይ፣ ከ1.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3😡2🎉1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የትግራይ ተወላጆች በሱዳን ጦርነት‼️
ከላይ የሚታየው ቪዲዮ የህወሃት አርሚ 70 ተብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች የአርቡርሃን ጦርን በመደገፍ በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙ ናቸው።
በትናንትናው ዕለት በሽራሮ አካባቢ ገመሃሎ በህወሓት ታጣቂዎች ላይ የኢትዮጵያ አየር ሃይል የፈፀመው ድንገተኛ የድሮን ጥቃት ታጣቂዎቹ ወደ ሱዳን ለመሄድ እየተንቀሳቀሱ ስለነበር ነው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪13👍95💔3🤡2👏1😱1🕊1
የውጭ ባለሀብቶች እና ተቋማት ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና ለማቃለል በማለም፤ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና በዉጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ነዳጅ እንዲያስገቡ የሚፈቅድ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አድርጓል።

ባለፈዉ ሳምንት ይፋ የሆነዉ ይህ መመሪያ፤ እውቅና የተሰጣቸው ተቋማት የተጣራ  የነዳጅ ምርቶችን በፍራንኮ ቫሉታ ስርዓት እንዲያስገቡ የሚፈቅድ ሲሆን፣ ይህም ከሀገር ውስጥ የባንክ ስርዓት ምንም ዓይነት የውጭ ምንዛሬ ሳይጠይቁ የራሳቸውን ፍላጎት እንዲሸፍኑ የሚያስችል ነው።

ይሁን እንጂ አዲሱ አሰራር አጠቃላይ የነዳጅ ገበያውን ለግል ነጋዴዎች ክፍት የሚያደርግ ባለመሆኑ፣ በዚህ መንገድ የገባ ነዳጅ ለሕዝብ ሊሸጥ፣ ለሶስተኛ ወገን ሊተላለፍ ወይም በተለመደው የሀገር ውስጥ የንግድ ነዳጅ አቅርቦት ላይ ሊቀላቀል እንደማይችል በጥብቅ መከልከሉን የዘገበው ካፒታል ጋዜጣ ነዉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍6🤪5👏2👌1
ኢሰመኮ ሶስት ሰዎች ናቸው የሞቱት አለ
" ሁለት የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንዲሁም አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ በአጠቃላይ የሦስት ሲቪል ሰዎች ሕይወት አልፏል " - ኢሰመኮ

• የአርሲ ሀገረ ስብከት 13 ምዕመናን መገደላቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል !

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ግንቦት 23 እና 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ያከናወነውን የክትትል እና የምርመራ መረጃ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ "በምሥራቅ አርሲ 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምእመናን መፈናቀላቸውንና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን " ማሳወቃቸው ይታወሳል። የሟቾችን ዝርዝርም ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

ኢሰመኮ ከአይን እማኞች፣ ከተጎጂዎች እና ከመንግሥት አካላት አሰባሰብኩት ባለው መረጃ ፣ በጥቃቱ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላትና ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፣ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን፣ የንብረት ውድመት እና ቃጠሎ መድረሱን ማረጋገጡን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በምርመራ ሂደቱ አረጋገጥኩኝ እንዳለው፣ በአሰኮ ወረዳ ደለተ ጫፋ ቀበሌ ከግንቦት 22 ቀን ጀምሮ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በመስተዋሉ፣ በአካባቢው ሚሊሻዎችና የኦሮሚያ ጸረ ሽምቅ ፖሊስ እንዲሁም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን መካከል ግጭት ተፈጥሯል።

ይህንን ግጭት ተከትሎ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት ከአካባቢው መሸሽ ያልቻሉ ኃይሉ ንጉሴ እና ሰሙ አባይነህ በተባሉ ሁለት የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንዲሁም ከብቶች በመጠበቅ ላይ በነበረ ባቶ ሰፈኖ በተባለ አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ በአጠቃላይ የሦስት ሲቪል ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ ችሏል።

በተጨማሪም በጥቃቱ የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መቃጠሉን ኮሚሽኑ ያረጋገጠ ሲሆን የቢዮ ቡጡሌ የሼክ ሙስተፋ መስጅድ አጥር ላይ ጉዳት መድረሱን ቁጥራቸው በውል ባልታወቁ ቤቶች ላይ ቃጠሎ መከሰቱን እና በጤና ጣቢያ፣ በመኖሪያ ቤቶችና የንግድ መደብሮች ላይ ዘረፋ መፈጸሙን አስታውቋል።

በጥቃቱ ምክንያት ከ2,650 በላይ የሚገመቱ የአካባቢው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውንም ኢሰመኮ አረጋግጧል።

ኢሰመኮ በአርሲ ዞን በሽርካ፣ በአሰኮ፣ በአንቆሎ ዋቤ፣ ጉና እና መርቲ ወረዳዎች ላይ በታጣቂዎቹ ሲፈጸሙ የነበሩ ጥቃቶች ዳግም እንዳይከሰቱ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ እና ጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በተለያዩ ጊዜያት ማሳሰቡን አስታውሷል።

በመሆኑም መንግሥት በአካባቢው ላይ በተደጋጋሚ መሰል ጥቃቶች መከሰት መቀጠላቸው አሳሳቢ መሆኑን ከግምት በማስገባት፣ በአስቸኳይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችን በማሰማራት ሰላምና ደኅንነትን የማረጋገጥ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስቧል።

በመንግሥትና በአጋር አካላት ለተፈናቃዮች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብና ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲመቻች የጠየቀው ኮሚሽኑ፤ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በደረሰው ሞትና ጉዳት ማዘናቸውን ገልጸው፣ መንግሥት በቂ የጸጥታ ኃይል በመመደብ የዜጎችን በሕይወት የመኖርና የንብረት መብቶች ለአደጋ እንዳይጋለጡ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ኢሰመኮ ጉዳዩን አስመልክቶ ዝርዝር የምርመራ ሪፖርት ወደፊት ይፋ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን፤ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ የሚሰነዘሩ ፍረጃዎችና ቅስቀሳዎች ተጨማሪ ግጭት ሊቀሰቅሱ ስለሚችሉ፣ ማናቸውም ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2824💔6👍3😢2🤷2😡2🙉1🙊1
ሰበር ዜና‼️
ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳይል ተኮሰች።
እስራኤል ኢራን ለምትፈፅመው የሚሳኤል ጥቃት ዝግጁ ነኝ ማለቷን RT ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍168🥰2🕊1👀1
በትግራይ ክልል ዛሬም የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ።

ዛሬ እሁድ ግንቦት 30 ቀን አመሻሹ ላይ ከሽራሮ አቅራቢያ ሽምበኒላ በተባለ ስፍራ አዲስ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል። ይህ በሶስት ቀናት ውስጥ በትግራይ የተፈጸመ ሁለተኛው ጥቃት ሲሆን ከቀናት በፊት የተካሄደውን ተመሳሳይ ጥቃት ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግስቱን ማውገዙ ይታወሳል።

የዛሬው የድሮን ጥቃት የጦር መሳሪያ በጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ተነግሯል። ከሁለት ቀናት በፊት የተካሄደው ጥቃትም በተመሳሳይ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እና ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ዘግይተው የወጡ መረጃዎች ማመላከታቸው አይዘነጋም።
እነዚህ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ያሉት፣ ህወሓት ክልሉን ወደ ማስተዳደር መመለሱን ማሳወቁን፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህወሓት እና በኤርትራ መንግስት መካከል እየተደረገ ነው ያሉትን ግንኙነት ማውገዛቸውን ተከትሎ ነው። የድሮን ጥቃቱ በተፈጸመበት በዚህ ሰዓትም የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብጽ መግባታቸው ታውቋል።

የፕሬዝዳንቱ የግብጽ ጉብኝት ትኩረት በውል ባይታወቅም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የህወሓትን እና የኤርትራ መንግስትን ጥምረት ከማውገዛቸው ባለፈ፣ በሁለቱ ቀናት የተፈጸሙት ጥቃቶች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ እና የኤርትራ ሰራዊት አባላት በስፋት በሚታዩባቸው አካባቢዎች መሆናቸው፣ ጥቃቱ በኤርትራ እና በህወሓት መካከል ተፈጥሯል በተባለው አዲስ ግንኙነት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ያሳያል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍7👀3👏1😁1🕊1🤪1
የመካከለኛው ምስራቅ ሰማይ እሳት ለብሷል!

ኢራን በደርዘን የሚቆጠሩ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷ ቀጣናው ወደ ከባድ ጦርነት እያመራ ነው።

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ወደለየለት ቀውስ ተቀይሯል።

የኢስራኤል መከላከያ ሰራዊት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በሰጠው እጅግ አስቸኳይ መግለጫ ኢራን በርካታ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን በቀጥታ ወደ እስራኤል መተኮሷን ይፋ አድርጓል።

በአሁኑ ሰአት በሰሜናዊ የእስራኤል ከተሞች የአየር አደጋ ማስጠንቀቂያ ደወሎች በከፍተኛ ሁኔታ እያስተጋቡ ሲሆን ህዝቡ በአስቸኳይ ወደ መከላከያ መጠለያዎች እንዲገባ ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል።

ይህ መጠነ-ሰፊ ጥቃት የተሰነዘረው እስራኤል ዛሬ ማለዳ ላይ በሊባኖስ ቤይሩት ዳሂዬህ አካባቢ ላይ ለፈጸመችው ከባድ የአየር ድብደባ ማዕበል ኢራን የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ በይፋ ከዛተች በኋላ ነው።

ሁኔታውን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ትኩረት የሳበ ሲሆን እንደ ኳታር ያሉ የጎረቤት ሀገራት የንግድ አውሮፕላኖቻቸው የኢራንን የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲቀይሩና እንዲርቁ በአስቸኳይ እያዘዙ ነው።

ይህ የኢራን እርምጃ የቀጣናውን ጦርነት ወዴት ሊመራው ይችላል? እስራኤልስ ምን ዓይነት ከባድ የአጸፋ እርምጃ ትወስድ ይሆን የሚለው መላውን ዓለም በስጋት ውስጥ ጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
36👍5🕊3👏1😢1💔1🤪1